Thursday, March 14, 2013


ለሙ ዉስጥ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸው ታወቀ

ከአዲስ አበባ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብሎ በሚገኘዉና ልዩ ስሙ ለሙ እተባለ በሚጠራዉ ቦታ በኦሮሞና በደቡብ ክልል ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ለግዜዉ ቁጥሩ በዉል ተለይቶ ባልታወቀ ሰዎች ላይ የሞትና የአካል መቁስል አደጋ መድረሱን የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ምንጮች ይፋ አደረጉ። ከኢሳት ምንጮች በተገኘዉ መረጃ መሰረት ግጭቱ የተነሳዉ ለሚ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በኮብል ድንጋይ ማንጠፍ ስራ ላይ በተሰማሩ የኦሮሞና ደቡብ ክልል ተወላጆች መካከል ሲሆን ባለፈዉ ማክሰኞ ለተቀሰቀስዉ ግጭት መነሻ የሆነዉ ከዚህ ቀደም በአንዲት የኦሮሞ ተወላጅ ሴት ላይ ጉዳት ያደረሰዉን  የደቡብ ክልል ተወላጅ ለመበቀል የኦሮሞ ተወላጆች ተደራጅተው በመምጣት በደቡብ ክልል ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ  ከ10 እስከ 12 ሺ ሰራተኞች እንዳሉበት በሚነገረው  የኮብል ድንጋይ ማንጠፍ ፕሮጀክት ላይ እንደዚህ በዘር ጎራ እየለዩ መጣላትና መገዳደል የተለመደና ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሆን ብሎ የፈጠራቸዉ ችግሮች አካል ሲሆን የአካባቢዉ ፖሊስ ሀይሎች ለይስሙላ ወደ ቦታዉ እየሄዱ ደም መፋሰሱን ለማስቀረት ቢሞክሩም አንድም ቀን ተሳከቶላቸዉ እንደማያዉቅ ለማወቅ ተችሏል። የኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ግጭቱን አስመልክቶ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ፖሊስ ሀላፊዎችን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራዎች ቢያደርገም እንዳልተሳካለት ገልጿል።

    No comments:

    Post a Comment