Wednesday, March 6, 2013


በአምስት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ብቻ 196 ፕሬሶች ከሕትመት ውጪ መሆናቸው ተዘገበ

በኢትዮጽያ ባለፉት አምስት ዓመታት በፖለቲካ፣ በማኀበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በስፖርት፣ በሃይማኖት፣ በፍቅር፣ በኪነጥበብ
እና በመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች አተኩረው ይታተሙ ከነበሩ 235 የፕሬስ ውጤቶች መካከል 196 ያህሉ በተለያየ ምክንያት ከህትመት ውጪ መሆናቸውን የአገዛዙ ብሮድካስት ባለስልጣን ሰሞኑን በድረገጹ በለቀቀው መረጃ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ከየካቲት 2001 እስከ ጥር 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ለ91 ጋዜጦችና ለ144 ያህል መጽሔቶች በድምሩ ለ235 ያህል የፕሬስ ውጤቶች የምዝገባ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አስታውሶ ከነዚህ መካከል እስከ ጥር ወር 2005 ዓ.ም ድረስ መዝለቅ የቻሉት 18 ጋዜጦች እና 21 ያህል መጽሔቶች በድምሩ 39 ያህል የፕሬስ ውጤቶች ብቻ መሆናቸውን አመልክቷል።
ባለስልጣን ተብየው በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአስደንጋጭ መልኩ ፕሬሶቹ ከሕትመት ውጪ የሆኑበትን ዝርዝር ምክንያት ማስረዳት ካለመቻሉም በላይ በያዝነው የካቲት ወር 2005 ዓ.ም “መሰናዘሪያ” እና “አዲስታይምስ” የተባሉ ጋዜጣና መጽሔት ከሕትመት ውጪ በመሆናቸው በሕትመት ላይ ያሉት ፕሬሶች ጠቅላላ ቁጥር ወደ 37 ዝቅ እንዲል ሆኗል።
ዘረኛውና አፋኙ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያን ሃሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ ሌት ከቀን እንደሚሰራ የሚታወቅ ሲሆን በርካታ የህትመት አዘጋጆችና ባለቤቶች ከፍተኛ የሆነ እንግልት እስርና ድብደባ ሲፈጸምባቸው እንደቆየ በስፋት መዘገቡ ይታወሳል።

    No comments:

    Post a Comment