እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡
ተመሰገን ደሳለኝ
ዳግም ተመልሰናል!!
ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ ‹‹አጋር ፓርቲ››ነት እየቀየረ ያለው ኢህአዴግ ፍትህ ጋዜጣን እና አዲስ ታይምስ መፅሄትን በጉልበት ከነጠቀን በኋላ፣ ለሶስተኛ ጊዜ በሌላ ጋዜጣ ተመልሰናል፡፡ ጋዜጣዋ ‹‹ልዕልና›› ትባላለች፡፡ ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ለአንዴ ብቻ ታትማ ተቋርጣ ነበር፡፡ አሁን ግን የነበረባት የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ በሀገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ መሰረት ወደ እኛ መዞሩን አበስራለሁ፡፡ እናም ዛሬ በዕለተ ቅዳሜ ለአንባቢያን ትደርሳለች፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ግን ‹‹አርብ አርብ ይሸበራል፤ …›› እንዲል ንጉስ ቴውድሮስ፣ ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና ትቀጥላለች፡፡

እንደመውጫም ይሆነኝ ዘንድ በአዲሷ ጋዜጣችን ላይ ‹‹ከተዘጋው በር ጀርባ›› በሚል ርዕስ ላቀረብኩት ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን እዚህም ልድገመው፡-
እነሆ በሶስተኛው በር ተገናኝተናልና አብዝቼ አላማርርም፡፡ ባማርርስ የት እደርሳለሁ? ማነው አገዛዙንስ ከስሶ የረታ? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው በሀገሬ መሬት ላይ ህግ የበላይ ሆኖ የሚያውቀው? ለማንኛውም የጠፋው ብርሃን በዚህ መልኩ ዳግም ይፈነጥቅ ዘንድ ስለተከፈለው ዋጋ ወይም ውጣ ውረድ ገድል የመፃፍ ፍላጎት የለኝም፡፡ ፍላጎቴ ከባልደረቦቼ ጋ በፀና መንፈስ በጀመርነው ጎዳና እንተም ዘንድ የመንግስትን አፈና አውግዛችሁ የሞራል ድጋፍ ለሰጣችሁን ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ላሳያችሁት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፣ በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ ነውና-ቺርስ ለነፃነታችን!
እነሆ በሶስተኛው በር ተገናኝተናልና አብዝቼ አላማርርም፡፡ ባማርርስ የት እደርሳለሁ? ማነው አገዛዙንስ ከስሶ የረታ? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው በሀገሬ መሬት ላይ ህግ የበላይ ሆኖ የሚያውቀው? ለማንኛውም የጠፋው ብርሃን በዚህ መልኩ ዳግም ይፈነጥቅ ዘንድ ስለተከፈለው ዋጋ ወይም ውጣ ውረድ ገድል የመፃፍ ፍላጎት የለኝም፡፡ ፍላጎቴ ከባልደረቦቼ ጋ በፀና መንፈስ በጀመርነው ጎዳና እንተም ዘንድ የመንግስትን አፈና አውግዛችሁ የሞራል ድጋፍ ለሰጣችሁን ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ላሳያችሁት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፣ በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ ነውና-ቺርስ ለነፃነታችን!
One Response to እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡
Search ECADF
Recent Posts
- የህወሓት ስረወመንግስት በኢሕኣዴግ ጡዘት
- በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለተከናወነ አሳዛኝ ተግባር የሚገልጸው ተንቀሳቃሽምስል መግለጫ።
- አለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በኦስሎ ኖርዌይ ንግስት ሶኒያ በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከብሮ ዋለ
- እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡
- ሲገርሙ አውስትራልያዎች …. ከግራጫ ፀጉር ጋር – ውድድር?
- እኛም እንድገመዋ… ርዕዮትን እያሰሩ … ቐሽ ገብሩን ቢዘክሩ… “ሼም” የለም በአገሩ…!?
- “ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቆች ሆነዋል” ስማቸው ያልተገለጸ እናት
- ለታማኝ ሚዲያ ታማኝ አምባሳደር
- ምነው “ክብርና ሞገስ ከኃይለማርያም ለገብረማርያም ተሠጥቶ” ደረት ተደልቆ፡ንፍሮ በድንኳን ተሰልቆ፡ቢልቦርድ ተወጥሮ፡እንባ በካሜራ ተቀድቶ፡ገና ብዙ ምሁራን የሚፈልቁበት ፋውንዴሽን ፈንድቶ።እባካችሁ ራዕዩን አታሳርሩት…
*‹‹ልዕልና››ለአንዴ ብቻ ታትማ ተቋርጣ ነበር አሁን ግን የነበረባት የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ በሀገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ መሰረት ወደ እኛ መዞሩን አበስራለሁ፡፡
- ይህ ነው ሕጋዊነት መቼም ኢህአዴግ አልሰማሁም አላየሁም ማለት የተለመደ ቅጥፈቷ ነው ፡፤ እነዲህ ለዓለም ሕዝብ ዜናው ይለቀቅና ይታመን እንጂ…ግን <> አጋር ጋዜጣ ናት? ለማናቸውም ከአንገራጋሪ ባለሥልጣን፡ከአንጎራጓሪ አቃቢ ህግ፡ ከጎርጓሪ ካድሬ፡ከጉርአንጉር ሸቃይ፡ይጠብቃትና ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና ትቀጥላለች፡፡አሜን በለው! ያው የፈረደበት አንባቢ አዕምሮው ሊናወጥ ነው ማለት ነው? ሌላው ግድ የለም ሰውዬውን የሚቀሰቅስ ፅሑፍ አውጥታችሁ ‘ራዕዩ’ ከመቃብር እንዳይሸበር አደራ።ያ ፈረደበት ባዶ ሳጥን በቤተሰብ አባላት ብቻ ተጎበኘና ተመረቀ አሉ ስንት ከንፈር መጣጭ አስመሳይ ሆድአደር ጥቁር ልብስ አሰፍተው መሃረብ ገዝተው ሆዳቸውን በጨው አጥበው ጮማ ሊበሉ እንደቋመጡ ጦማቸውን አድረው ዋሉ! ድሮስ ያልሞተ ታጋይ ሐውልት አለውን? – “አታስቢ ቢሏት የመገዘዝ አይጥ ምን ይበላ ይሆን አለች አሉ” ለመሆኑ ሀገር ውስጥ ወረቀትና ቀለም አለን?”"መብራት አለን? ባለፈው “ጀሃዳዊ ሀረካት” የሚባል ፊልም ለማየት አንዳንዶች ከምሽቱ ፭ ሰዓት በኋላ ጅቡቲ ሄደው እንደተመለከቱት እንደወደዱትና በሀገር ውስጥም ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ፊልሙ በነጻ እንደሚደገም ባለድርሻ አካላት ቃል ሲገቡ ተደምጠዋል። እኛ ከ፮ እስከ ፯ በመቶ ብቻ አድጋለች ስንላት ከርመን ለ፰ዓመት በተከታታይ ፲፩ ነጥብ ዕድገት ያስመዘገበች፡ የዓለም ኢኮኖሚ ቀውስ በጭራሽ ያልነካት ብቸኛዋ የዚህ ዘመን የኢህአዴግ ሀገር ሰሞኑን ወደ ፰ በመቶ ከፍ ብላ ፩ በመቶ ብቻ ማደጓን እራሷ መስክራለች ።ክበር ተመስገን በለው።!!
-አሁንም ይሰማናል! ያገባናል! ህዝብን አስፈራርቶ፡ እራስ አውርቶ፡ እራስ ሰምቶ፡እራስን አድንቆ፡እራስ ተመፃድቆ፡ኮሽ ባለ ቁጥር ተሸማቆ፡እንደእርጎ ዝንብ በሁሉ ቦታ ጠልቆ፡ለማየት ጓጓሁ ኢህአዴግ የፍርሃትና የማጭበርበሪያ ጭንብሉን አውልቆ!!በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬንና ሰላም፣ እኩልነት፣ አንድነት፣ የሰለጠነች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለማየት የዘወትር ምኞታችን ነው። የመናገር፡ የመፃፍ፡ የማንበብ፡ በሀገር ተዘዋውሮ የመኖርና፡ የሥራት መብት ለሁሉም ይከበርለት በለው።!! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን>>>>>>>>