የአውሮፓ ህብረት የልኡካን ቡድን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊ መብት አያያዝን እንደሚገመግም ተነገረ

ከልኡካኑ መሪዎች አካባቢ በተገኘዉ መረጃ መሠረት ጉብኝቱ የሚካሄደዉ በልማት ሽፋን ሲሆን የልኡካኑ ቡድን በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብች አያያዝ እና ችግሮች ዙሪያ ከተለያዩ የአገዛዙ ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገርም ለማወቅ ተችሏል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የዜጎች ሰብዓዊ መብት በቋሚነት ከሚረገጥባቸዉ ቦታዎች አንዱ የቃሊቲ እስር ቤት ሲሆን የአዉሮፓዉ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ልኡካን ቡድኑ የቃሊቲ እስር ቤትን ለመጎብኝት ከወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች ፈቃድ ያግኝ አያግኝ ምንም የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም የልኡካን ቡድኑ መሪ ደጋግመዉ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ዉስጥ በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ጉዳይ የልኡካን ቡድኑ ከሚያተኩርባቸው ነገሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ለማቅ ተችሏል። ከዚህ ቀደም 16 የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ ለሀይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ መጻፋቸው የሚታወስ ነዉ።
No comments:
Post a Comment