Saturday, April 6, 2013


ዜና በጨዋታ፤ ልዕልናም ተሰዋች!

lelnaፍትህ ጋዜጣ ከተዘጋች ወዲህ የፍትህ ጋዜጣ ማኅበረሰብን በማቀፍ አዲስ ታይምስ መጽሄት እንደ ፍትህ ሆና በአዲሳባ የመረጃ ክፍተቱን ስትሞላ ቆይታ ነበር፡፡ ነገር ግን መንግስት ቀፈፈው፡፡ “እንዴት አይኔ እያየ ከእኔ ውጪ ሌላ ሰው ናገራል!”  ሲልም አለቅጥ ተቆጣ ተቆጣናም አዲስ ታይምስንም መስዋት አደረጋት፡፡
አዲስ ታይምስ ከተሰዋች በኋላም የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆች እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም፡፡ ልዕልና የተሰኘች አዲስ ጋዜጣ ደግሞ ጀመሩ፡፡ ጋዜጣዋ ከዚህ በፊት በገበያ ላይ የነበረች ስትሆን ከገበያው ከወጣች በኋላ የቀድሞ ባለቤቶቿ ከፍትህ አዘጋጆች ጋር ባደረጉት ውል መሰረት ድጋሚ መታተም እንደጀመረች የሚነግሩን ነግረውናል፡፡
ትላንት አርብ መጋቢት 27/2005 ትወጣ ይሆን ተብላ በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው ልዕልና እንደ ወንድሞቿ እነ ፍትህ ሁሉ መሰዋቷን ከአዲሳባ የደረሰኝ ወሬ ያስረዳል፡፡ ይሄኔ የመንግስታችን ዋና ጠበቆች “እንኳን እርሷ አቶ መለስስ ተሰውተው የለ እንዴ!” ሊሉን ይችላሉ፡፡ እርሳቸው ሰውዬ እንዴት ነው ነገሩ በጦር ሜዳ የተገደሉ እየመሰለኝ መጣ እኮ… ወይስ ለዚህ ያበቃቸው የአቤ ጩኸት መሆኑ በካቢኔው ታምኖበታል፡፡
ለማንኛውም ጩኸታችንን የምናሰማባቸው ጋዜጦች በሙሉ እየተሰዉ ነው፡፡ ምናልባትም በአካል የምንጮኸበትን ጊዜ እያቀረቡልን ሊሆን ይችላል…
በመጨረሻም
ለዚህ ሳምንት ልዕልና ጋዜጣ ልኬው የነበረውን ወግ በድረ ገጻችን ላይ አጣብቄዋለሁ፡፡ መልካም ቅዳሜ ይሁንላችሁ!

No comments:

Post a Comment