ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛው ጠቅላላ ጉባኤዉን ለማድረግ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው
የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛዉን ጠቅላላ ጉባኤ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ ነው። አራተኛው የንቅናቄው ጠቅላላ ጉባኤ በበርካታ አገርን፣ ህዝብንና ንቅናቄውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተመካክሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። በተለይ በአሁኑ ግዜ አገራችንና ህዝቦቿ ላይ የወያኔ ስርዓት እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጥቃትና ውርደት ለማስቆም የሚያስችል እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያበቃውን የትግል ስልት በመከተል በአጭር ግዜ ውስጥ አቅምና ቀጣይነት ያለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችለውን በመዋቅርም ሆነ በአሰራር ዙሪያ ባሉ ጉዳዮች መክሮ አስፈላጊውን ውሳኔ ይሰጣል።
በመጭው ሳምንታት የንቅናቄውን አራተኛ የዓባላት ጉባኤ በሚመለከት ቀጣይ መግለጫዎችን እንደሚሰጥ የአዘጋጅ ኮሚቴው ማስታወቅ ይወዳል።
የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ፣
ሚያዚያ 2005 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment