ሳውዲ አረቢያ በዘመቻው የሚፈናቀሉት ዜጎች አሳሳቢነትና የእኛ ምልጃ.
ይህንን ጽሁፍ የወሰድኩት ነብዩ ሲራክ ከጻፈው የማለዳ ወግ ከሚለው ጽሁፍ ላይ ነው እና አዎ ይህ የሁላችንም ምልጃ ”ልመና ” ነው እባካችሁ ስሙን ለቦንድ እና ለተለያዩ ነገሮች ስትሰበስቡን እንደምንሰማችሁ እናንተም ዛሬ ስሙን በሳኡድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ድምጽ…………..
በዘመቻው የሚፈናቀሉት ዜጎች አሳሳቢነትና የእኛ ምልጃ. . .
ሰማችን ማንቴስ ብልንና እድሜያችን ቆልለን ከደላንና ከቀናን በጠያራ ፣ አልሆን አልመች ሲል የባህር የበርሃውን ሰቆቃ ተፋጠን እዚህ ለደረስነው ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ባለውለታችን ናት ! በአሰሪዎችና በአንዳንድ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች የሚደርስብንን የመብት ጥሰት ቸችለን ላለፍን ሰላማዊ ነዋሪዎች አረባዊቷ ሀገር ከሀገራችን ተሻላለች እስከማለት መደረሳችን ራሳችን ጠቅመን ቤተሰቦቻችን መጥቀም ችለናልና ነው ! ይህች የምናመሰግናት ሃገር ዛሬ ዛሬ የምታወጣህ ህግ ዛሬ ዛሬ እየጎዳን ለመሆኑ ጥር ጥር የለኝም! በሰሞኑ አሰሳና ፍተሻ አባወራውም ሆንን የቤት እመቤቷ ህገ ወጥ ተብን እንደጣን ልንቀር የምንችልበት አደጋ ተደቅኖብናል። ዜጎች በከባድ ውጣ ወረድ ለአመታት ያፈራነው ሀብት ቀርቶ የአብራክ ከፋይ ልጆች ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ ከሀገር ለሚባረሩበት አካሄድ አሰፈሪና አስደንጋጭ ነው!
ከ የመንግሰት ተወካዮቻችን አደጋውና ስጋቱ ባየለ ቁጥር “የዝሆን ጀሮ ይሰጠኝ “ብለው ዝምታን መምረጣቸው ለምን ይሆን? አደጋውን መጋፈጥ ስንጀምር ሊያማክሩ ሊዘክሩ ይገባል የሚል ጥሪ አቤቱታ ጉትጉታችን ለምን አይሰሙንም? ውጋታችን ካለወጋችሁ ፣ ህመማችን አሟችሁ፣ እስካልሰበሰባችሁን እስካላመካከራችሁን ድረስ የዜጎች ተወካይንታችሁ ምኑ ላይ ነው? በጭንቃችን ካለደረሳችሁ የመኖራችሁ ጥቀሙን ንገሩና ? ህዝብ ጠርታችሁ እሰክትመክሩ ዝም አንለም! አጮልቃችሁ በምታዩት በዚህ ገጽና በተለያየዩ መድረኮች ድምጻችን ከፍ አድርገን እንናገራለን ! አዎ የሚፈናቀሉት ቤተሰቦቻቸውን ሃብት ንብረታቸውን ይዘው የሚገቡበትን መንገድ ከሳውዲ መንግሰት ጋር ከመደራደር ጀምሮ ግፉ አኑ ሃገር ቤት ንብረታቸውን ይዘው እንዲገቡ ልዩ የነጻ ቀረጥ ፍቃድ እንዲሰጥ ታመቻቹ ዘንድ እንማለዳችኋለን!!! ምንጭ ፍሪደም ብሎግ
Category: AMHARIC NEWS
No comments:
Post a Comment