Thursday, April 25, 2013

የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ገለፁ

April 25, 2013 12:45 pm
ወደ ቤንሻንጉል የተመለሱት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
Amhara People in Benshangul Kililከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በፍኖተሰላምና በተለያዩ አካባቢዎች ተበትነው ከቆዩ በኋላ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እስካሁን እርሻ አለመጀመራቸውንአስታውቀዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እንዳስታወቁት ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንደሚመለሱ ተነግሯቸው ቢመጡም፣ ስፍራው ሲደርሱ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለህብረተሰቡ አስቀድመው የተከራየነውን መሬት እንዳያስረክቡን በመቀስቀሳቸው ሊቀበሏቸው እንዳልፈለጉ አስረድተዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት አካላት “ተመልሰው የመጡት መሬታችሁን ሊቀሟችሁ ነው እንዳታቀርቧቸው” ተብለዋል የሚሉት ተፈናቃዮቹ “እርሻችንን እንዳትነኩ ወደ መሬታችንም እንዳትደርሱ” መባላቸውን ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡
በዚሁ ምክንያት እጅግ ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ መንግስት በአካባቢው በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፃመውን ግፍ እንዲያስቆም ተማፅነዋል፡፡ አክለውም “እኛ ያለ ባለመሬቱና ያለ መንግስት ፈቃድ የሰው መሬት አንነካም፤ ይህንን የአካባቢው የመንግስት አካላት ለህብረተሰቡ ሊያስረዱልን ይገባል፡፡ ሰርተን ለመኖር ተቸግረናል” ብለዋል፡፡

Wednesday, April 24, 2013


ፍየል ወዲህ…” – ይኸነው አንተሁነኝ

ሚያዚያ 23 2013
“ከእንግዲህ የገበሬው ችግር የርሃብ ችግር ሳይሆን የሚያመርተውን የተትረፈረፈ ምርት በርካሽ እንዳይጥለውና በገንዘብ መልክ የሚኖረው ገቢ እንዳያንስበት ነው፡፡” ባለራዕዩ መለስ ዜናዊ በዘመነ አካለ ስጋው የወሸከተው ደርዝ የሳተ ቃል
የተለያዩ መንግስታት ሕዝባቸውን ለማስተዳደርና ቁሳዊ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት፣ የሀገራቸውን ጸጥታና ደህንነት አስጠብቆ ለመምራት፣ እንዲሁም ከሌላው ዓለም ጋር ጥቅምን ያገናዘበ ግንኙነት ለመመስረት የሚያግዙ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ያጸድቃሉ ይተገብራሉም። አፈጻጸሙንም በተመለከተ የተለያዩ መመዘኛዎችን በማውጣት ይከታተላሉ፤ ተጠቃሚውን ምሕበረሰብ መሰረት ያደረገ የእርምት እርምጃዎችንም መውሰድ ከአንድ መንግስት ነኝ ከሚል አካል የሚጠበቅ ሃቅ ነው። ይህ ሲሆን እንግዲህ የተዘጋጁትን ፖሊሲዎች፣ አተገባበራቸውንና ሊያመጡ የሚችሉትን ውጤት በተመለከተ የሚወጡ መንግስታዊ ቅድሚያ መግለጫዎችም ሆኑ ማብራሪያዎች ከዚያም ሲያልፍ እቅዶችና የተስፋ ቃሎች በሙሉ በባለሙያ የተቃኙና በመሰረታዊ የትንበያ ሳይንስ የተዳሰሱ ሊሆኑ መቻላቸው አያጠያይቅም እጅግ በጣም ቢያንስ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ለሚሰማቸው መንግስታት። ፍየል ወዲህ…

Tuesday, April 23, 2013

የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች!


በሰሎሞን ተሰማ ጂ.
Email: solomontessemag@gmail.com

የነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) የተደራጁትም ያልተደራጁትም ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጡንቻቸውን አፈርጥመው፣ ክራንቻቸውን ስለው፣ ጥፍሮቻቸውን ወድረው ሊዘነጣጥሉ የሚችሉበት አቅምና ጉልበት አላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ያ ጉልበት ስለሌላቸው፣ ቀበኛ ባሕሪያቸውን በጩኸትና በስም ማጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ያከናውኑታል፡፡ በልዩ ልዩ መልክና ቅርጽ የተደራጁት “የመሠረታዊ ነፃነት ጠሮች (ቀበኞች)” ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ገሚሶቹ በገዢነት (በፓርቲነት)፣ አንዳንዶቹ በሃይማኖታዊ ማኅበራት ሽፋን፣ ሌሎቹ ደግሞ በአነስተኛና ጥቃቅን ቡድንነት የተደራጁ አዳሚዎችና አሳዳሚዎች ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በአንድ-ለአምስት ሕዋስ ሥር (as a gangster) የተደራጁ “የጎበዝ አለቆች” ናቸው፡፡ በነዚህ አካላት ጭፍን አካኼድ የተነሳ፣ የዜጎች መሠረታዊ ነፃነትና መብት ይደፈጠጣል፡፡ የሥልጣናቸውና የመጉዳት አቅማቸው መጠን የተለያየ ይሁን እንጂ፣ ሁሉም የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) ናቸው፡፡ ለምን እንደሆኑና እንዴትስ ከዚህ ደረጃ እንደደረሱ ለማሳየት ጥረት አደርጋለሁ፡፡Freedom: the quality or state of being free
የሥነ-መንግሥት ተመራማሪዎች፣ ልዩ ልዩ ዓይነት ነፃነት አለ-ይላሉ፡፡ ሁሉንም ለመዘርዘር አልቃጣም፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ የሐሳብ መስጠት ነፃነት፣ አንድ ሰው አምላኩን ሃይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ የማምለክ ነፃነት፣ ተሰብስቦ የመወያየት ነፃነት፣ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት፣ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትና ነፃነት፣ የመሳሰሉት እያሉ ይዘረዝራሉ፡፡ ሁሉም ታዲያ “ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ነው የሚከወኑት” ይላሉ፡፡ አልተተገበረም አንጂ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ 27 መሠረት፤ የሃይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነፃነት የዜጎች መብት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 መሠረት፣ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የመድረግ ነፃነትና አቤቱታንም የማቅረብ መብትን በተመለከተ ነጩ ወረቀት ላይ ሰፍሯል፡፡ ግን አልተተገበረም፡፡ የከፋ በደል ነው፡፡ የበደልም በደል! (“የሰው ልጅ በሠለጠኑትም ሆነ ባልሰለጠኑት አገሮች መሠረታዊ ነፃነት እንጂ ፍፁም ነፃነት ሊያገኝ እንደማይችል የሚታወቅ ነው፤” ሲሉ ተመራማሪዎቹ ያክላሉ፡፡)
ስለ“መሠረታዊ ነፃነት” ምንን ከመጻፌ በፊት፣ ስለዚህ የነጻነት ዓይነት ለመፃፍ ያሳሰቡኝን ምክንያቶች ላነሣ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው የሩዶልፎ ግራዚያኒ ደጋፊዎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 30 መሠረት፤ “የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የመድረግ ነፃነትና አቤቱታንም የማቅረብ መብትን” እንዴት በካልቾ እንደመቱት በመመልከቴ ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ፣ አንዳንድ ሰዎች (በግልም በቡድንም ሆነው) እንዴት የሌሎችን መሠረታዊ ነፃነት እንደሚጣረሩ ለማሳየት ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሜ ግን፣ “ነፃነት ማለት ምንድነው?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስም እሞክራለሁ፡፡ በአቦ ሰጡኝ የመጣልኝ መልስ፣ “ነፃነት የሰው ልጅ ከአላህ ወይም ከእግዚአብሔር (አዳላህ እንዳትሉኝና ከእግዚአብሔር ወይም ከአላህ) በተፈጥሮ የተሰጠውን ክብር መጠበቂያው ሚዛን ነው፡፡” የሚል ሆነ፡፡ መሠረታዊ ነፃነት የሌለው ሰው፣ በሰው ፊት ሰው የበለጠው፣ ከሰው በታች የሆነም ነው፡፡ ነፃነት የሌለው ሰው፤ በሰው ፊት የተዋረደ፣ የተናቀ፣ ሕቁር (Inferior) ፍጥረት ነው፡፡ ነፃነት የሌው ሰው በአፀደ ሕይወት ቢኖር እንኳን፣ መኖሩ እንደሰው ሳይሆን እንደዕቃ፤ እንደ“እንትና” ሳይሆን እንደ“እንትን” የሚታይና የሚቆጠር ፍጡር ነው፡፡ “እንትን” የሚል ቅጽል የሚሰጠው፣ መሠረታዊ ነፃነት ለሌለው ሰው ነው፡፡ እንትንነት ክብራቸውን በፍርፋሪ ለሸጡና መሠረታዊ ነፃነታቸውን ለተገፈፉ የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ ለሕቁር ፍጥረታት የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ እንደዔሳው የብኩርና ክብራቸውን በምስር ንፍሮ ለሸጡና ለለወጡ ፍጥረታት የሚሠጥ ስያሜ ነው፡፡ እነዚህ አምላክ/ፈጣሪ በተፈጥሮ የሰጣቸውን ክብር የቸበቸቡ ፍጥረታት ደግሞ፣ ሰላማዊ ሰልፎችን የሚከለክሉ፣ የመናገርንና የመጻፍን መብት ለመገደብ የሚንጠራወዙ፤ ፖሊስ ወይም የፀጥታና ደኅንነት ኃይል ተቀጣሪዎች ሲሆኑም ሌሎችን በዱላ የሚደበድቡ፣ የሚሳደቡና በተራ ስም አጥፊነት ተግባር የሚጠመዱ ናቸው፡፡ ኅቁር ፍጥረታት ክብር ስለሌላቸው፣ ማንንም አያከብሩም፡፡
ኅቁር ፍጥረታት ሰላማዊ ሰልፍ ሲሏቸው፣ እፊታቸው ድቅን የሚልባው የአመጽ ሰልፍ ነው፡፡ ለኅቁር የፀጥታና የዘመኑ ሹሞች የሚታያቸው፣ በሕግ ፊት ሰዎች እኩል መሆናቸው ሳይሆን፣ ተደብዳቢነታቸው ነው፡፡ ኅቁራን ሹሞችና አሽቃባጮቻቸው፣ ሰብዓዊ መብትን መጣስና መሠረታዊ ነፃነትን ማሳጣት የእንጀራ ገመዳቸው እንዳይበጠስ ማረጋገጫ ነው፡፡ ኅቁራን ባለሥልጣኖች፣ የጉልበት ሥልጣን እንጂ የመንፈስ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ለኅቁር ፍጥረታት፣ ካላግባብ በአሸባሪን ስለታሰሩ ወገኖቻችን ሲነገራቸው፣ እንደሰረሰር ሰርሳሪ የቄራ ለማጅ፣ ዋናውንና ሙዳውን ስጋ ትተው አገጭና ሌንጬጭ ይፈልጣሉ፡፡ ኅቁራን ፍጥረቶች፣ “ለአህያ ማር አይጥማትም” እንደሚባለው፣ ትልቁ ዓላማ አይጥማቸውም፡፡ ለኅቁር ፍጥረታት፣ መሳደብና ስም ማጥፋት ቋሚ ተግባራቸው ነው፡፡ ለኅቁራን፣ መቼም ቢሆን የቃላት ስንጠቃና “ከቁንጫ መላላጫ” ማውጣት የተለመደ ተግባር ነው፡፡
እንደአለመታደል ሆኖ ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ገዢዎች የዔሳው የመንፈስ ልጆች ናቸው፡፡ የእነሱ አጫፋሪዎችና ሎሌዎቻቸው ደግሞ የባሰባቸው “ኅቁሮች” ናቸው፡፡ ኅቁርነት፣ “ከመምህሩ ደቀ-መዝሙሩ” እንደሚባለው እየከፋና እየሰፋ የሚሄድ ነቀርሳ (Cancer) ነው፡፡ በቅርቡ ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት፣ ኅቁራን “በቆብ ላይ ሚዶ” የሚሽጡም ናቸው፡ በዚህ አላዋቂነትና ጠብደል መታወር ውስጥ እየኖሩ እንደምን የሌሎችን መሠረታዊ ነፃነት ሊያከብሩ ይችላሉ? ፈጽሞ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ስለሠጠው መሠረታዊ ነፃነት ስለማያውቁ፣ ወይም በያውቁም ሆን ብለው ስለሚክዱት፣ የሌሎችን ነፃነትና ክብር የገፋሉ፡፡ (ኋላ እመለስበታለሁ፡፡) አባቶቻችን አገራችን በተወረረች ጊዜ ነፃነትን አጥቶ ሆድን በፓስታና በሹታ ጎስሮ፣ ገላን በአቡጀዲና በጨርቅ ሸፍኖ ከመንቀዋለል ይልቅ፣ መሠረታዊ ነፃነትን ማጣት ምን እንደሚደርስባቸው ስላወቁ፤ “ነፃነት ወይም ሞት!” ብለው በጀግንነት ተጋድለው አለፉ፡፡ በፍርሃትና በጥቅመኝነት ታውረው፣ “ከመሞት መሰንበት” ያሉትም ቢሆኑ፣ ያለመሠረታዊ ነፃነት መኖር ምን ምን እንደሚል አሳምረው ቀምሰውታል፡፡ በዱር በገደል የተጋደሉትና በእስር አዚናራ የተጋዙት ምንኛ እድለኞች ነበሩ?
በነሐሴ 1960 ዓ.ም በወጣው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ስለመሠረታዊ ነፃነት ሲያወሱ፣ “የባሕል ነፃነት ነው” በማለት ሊገልፁት ሞክረዋል (ገጽ 5 ላይ ይመልከቱ)፡፡ “በሀገራችንና በሕዝባችን ዘንድ የባሕል ነፃነት ወይም የመሠረታዊ ነፃነት ከነትርጉሙም አይታወቅም፡፡ ነገሩ ግን የሀገርን ነፃነት የማጣትን ያህል ደም የሚያፋስስ ነው፤” (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ነሐሴ 9/1960)፡፡ ይሄው የመሠረታዊ ነፃነትን የማጣትና የማሳጣት ተንኮል፣ ከጥንት ጀምሮ በምዕራባውያን (በቄሳራውያን ሃይሎች) ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ መሠረታዊ ነፃነት ገፈፋው ዘዴ በጣም ረቂቅና ስልታዊም ነው፡፡ ከባሕልና ከመሠረታዊ ነፃነት ገፈፋ ስልቶች መካከል አንዳንዶቹን ለመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ዘዴ፣ የገዢዎችን መብት ለአንዳንድ ተገዢዎች መስጠት ነው፡፡ ሁለተኛ፣ ተገዢዎች ማንነታቸውን ክደው፣ የሀገርና የብሔራዊ ስሜታቸውን ማስካድ ነው፡፡ ሦስተኛውና ዋናው ችግር ደግሞ፣ ተገዢው ባሕሉንና ወጉን እንዲንቅና በራሱ እንዳይተማመን የማድረግ የሥነ-ልቦና ክሽፈት ነው፡፡
ከመጀመሪያው ነጥብ ጀምሮ መተንተን ያለበት ነው፡፡ ገዢዎቹ ለአንዳንድ ተገዢዎች፤ “በብሔር፣ በዘር ወይም በሃይማኖት ተዋጽዖ ስም” የይስሙላ የገዢነት መብት ይሠጧቸዋል፡፡ የአገሩን ሰርዶም በአገሩ በሬ ማለት እንደዚህ ነው እያሉ ይደልሏቸዋል፡፡ ጣሊያን አንዴ ልጅ አያሱን ልጅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የአፄ ዮሐንስን ወይም የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ልጆች ከተገዢነት አውጥታ ገዢ ልታደርጋቸው ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ ገዢዎች የሚከተሉት ስልትና ብልሃት ተመሳሳይ ነው፡፡ መሠረታዊ ነፃነቱን የተገፈፈው ሰው፣ የነፃነት ገፋፊውን ቋንቋና አነጋገር በቅጡ እንዲኮርጅ ከተደረገ በኋላ፣ የነፃነት ገፋፊውን አገር ዜጎች ያላቸውን ክብርና የይስሙላ ማዕረግ ይሰጡትና፣ የትውልድ አገሩንና የወገኖቹን መሠረታዊ ነፃነት የሚንድ “ምልምል አሽከር” ይሆናል፡፡ እንደዚያ ለመሆን የሚጠበቁበት ነገሮች ቀላል ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ቋንቋውን ማጥናት፣ ሁለተኛ፣ የወራሪውን ሀገር ዜጎች አክባሪ መሆኑን ለማሳየት መስገድ/እጅ መንሳት፣ ሦስተኛ፣ የወራሪውን አገር ከትውልድ አገሩ በላይ እንደሚያፈቅርና እንደሚወድ ማሳየት ነው፡፡ በተቻለ መጠን የሀገሩ ሕዝብና የሀገሩን ፍቅር ክዶ የብሔራዊ ስሜቱን አንጠፍጥፎ ደፍቶ ሞራለ-ቢስ መሆን በቂው ነው፡፡ ያን ጊዜ፣ ከተገዢነት ወጥቶ፣ የፈረስ ስም ተሰጥቶት፣ (ማጆር፣ ወይ ሰር፣ አልያም ደግሞ አፈ-ቄሳር፣ ማንትሴ እየተባለ) የይስሙላ ገዢ/ሹም ይሆናል፡፡ እንዴት ዓይነት አዘቅት ነው ጃል!
ሌላው ከተገዢነት ደረጃ ወጥቶ ወደ ይስሙላ ገዢነት መብት የሚደርስ ሰው፣ ከአፋፉ ጫፍ ላይ ለመድረስ ክህደትን የሙጥኝ ማለት አለበት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የይሁዳ ሰው ሆኖ ሳለ፣ የገዢዎቹን ሮማዊነት መብት ያገኘውና ከእስር ቤት የተለቀቀው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ እንደጳውሎስ ያለውን መብት ያገኘ ሰው፣ ከእስር ቤት ወጥቶ ስለፎለለ ነፃነትን ያለገደብ ያገኘ ይመስለዋል፡፡ ለሌሎች ተገዢዎችም ትልቅ ሰው መስሎ ስለሚታያቸውና በየአደባባዩም ስለሚወጣጠርና ስለሚበጣጠስም ጭምር፣ እርሱን መስሎ ለመገኘትና እርሱ የደረሰበት የክህደት አፋፍ ላይም ለመቆም ብዙ ወገኖቹ በማመጽ ፈንታ ጀርባቸውን ለሸክም፣ ኅሊናቸውንም ለሎሌነት ይሰጡታል፡፡ ተገዢዎች መሠረታዊ ነፃነታቸውን ለማግኘት ከመታገል ይልቅ፣ የገዢነትን መብት ለማግኘት ይንጠራወዛሉ፡፡ ብዙዎችም ነፃነት የሚባለውን አኃዝ ከነመኖሩም ይረሱታል፡፡ ትግሉ ሮማዊ፣ እንግሊዛዊ፣ አሜሪካዊ፣ ፈረንሳዊ፣ ጣሊያናዊ፣ ሳዑዲአረባዊ ወይም ሊባኖሳዊና ኳታራዊ ምንትስ ለመሆን መንጠራራት ይሆናል፡፡ ገዢዎች ከሚሠሩት ሃጢያት ሁሉ እንዲዚህኛው ዓይነት በክፋት የተሞላና የረጅም ጊዜ ቀውስ የሚያስከትል መርዝ የለም፡፡
ነፃነት ገፋፊዎች ይሄንን ሳያደርጉ ሁለት ዓላማዎችን ይዘው ነው፡፡ 1ኛ) የገዢዎቹን (የራሳቸውን) ትልቅነትና የሌላውን ትንሽነት አሳምኖ የበላይም ሆኖ ለመኖር የተዘየደ ደባ ነው፡፡ 2ኛ) አገሩና ሕዝቡም የኋላ ኋላ የይስሙላ ነፃነት ሲሰጠው፣ የባሕል ተገዢ ሆኖ እንዲቀርና የመሠረታዊ ነፃነት ጣዕም ሳይቀምስ እንዲቀር ለማድረግ የተሸረበ ታክቲክ ነው፡፡ በመሆኑም ነፃነት ገፋፊዎች በእቅድና በብልሃት ወደ ዓላማቸው ይደርሳሉ፡፡ አንዱ ዘዴ ከላይ የጠቀስነው የገዢነት መብት መስጠት ሲሆን፣ ሁለተኛው ዘዴ ደግሞ የነሱንና የባሕላቸውን ትልቅነት እንዲሁም ከፍተኝነት የተገዢዎቹንና የባህላቸውን ትንሽነትና ዝቅተኝነት ከልጅነታቸው ጀምሮ በማስተማር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ትምህርት በአንድ ሕዝብ አእምሮ ውስጥ ሲቀረጽ ባሕል ለዘላለሙ ይጠፋል፡፡ አብሮትም መሠረታዊ ነፃነት ድራሹ ይጠፋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየአውደ ምህረቱ፣ በየመስጂዱ፣ በየማኅበር ቤቱና በየመንዙማ ዝየራው፣ በየጽዋውና በየወዳጃ ቤቱ ሳይቀር የባሕል ወራሪዎቹ ትልቅነት ስለሚሰበክና ስለሚደሰኮ ዜጎች ከማይወጡት የመሠረታዊ ነፃነት እጦት ውስጥ ገብተው እንዲዘፈቁ ይዳርጋሉ፡፡ የፖሊስና የወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ስለገዢዎች የበላይነትና ስለሠልጣኞቹ የበታችነት በዘዴ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ ከዚያ ፀጥ-ለጥ ብለው ተገዢ ከመሆን ውጭ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡ ጃስ ሲሉት የሚናከስ፣ ጭላጭ ሲያቀርቡለት የሚልስ ውሻና ድመት ይሆናል፡፡
የተገዢዎቹን ሥነ-ልቦናም የበለጠ ለማኮስመንም ሲባል፣ ገዢው በተገዢው ዓይን ከታምራት የማያንሱ ነገሮችን ሲሰራ እንደነበረና እየሠራም እንዳለ ተደርጎ በየመድረኩና በየአደባባዩ ይደሰኮራል፡፡ ተገዢው ሕዝብ የፈለገውን ያህል ቢማርና ጥበበኛ ቢሆን እንኳን፣ ገዢዎቹ የሚሠሩትን ምትሃት ከቶም የማይደርስበት “ራዕይ” መሆኑን እንዲገነዘብ ተደርጎ ይሰበካል፡፡ የገዢዎቹ ራዕይና አርቆ-አሳቢነት ከሞቱም በኋላ በመገናኛ ብዙሃን እየተደሰኮረለት፣ ለሙት መንፈስ ሳይቀር ታማኝ ሆኖ እንዲገዛ ይደረጋል፡፡ ዱሮ-ዱሮ “ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ” ነበር የሚባለው፡፡ አሁን ደግሞ “ከጓድ አብዮታዊ መሪያችን ጋር ወደፊት!” ወይም “ከባለራዕዩ መሪ ጋር ወደፊት!” በሚል ሽፋን፣ ሕዝቡ መሠረታዊ ነፃነቱን እንዳይጠይቅ፣ አልፎ-ተርፎ ነፃነቱን ሲገፈፍም ዝም ብሎ እንዲያይ፣ “አሜን” ብሎ እንዲገዛም ያመቻቹታል፡፡ (ብቻቸውን አይደለም፣ ጭፍራና ጀሌ አስከትለው ነው፤ ካድሬዎቻቸውን አስደግድገው ነው፡፡)
ፕ/ር ጌታቸው እንደጠቀሱት፣ ገዢዎች የሚፈጽሙት ሦስተኛው መቅሰፍት ከሁሉ የባሰ ነው፡፡ ተገዢዎች ነፃ ቢወጡ እንኳን ራሳቸውን ችለው የሚያድሩም እንዳይመስላቸው አድርገው በባዶ ፕሮፓጋንዳ ያሸብሯቸዋል፡፡ ገዢዎቹ (ከሃሊዎቹ) የሌሉበት ነገር እንደሚዘባረቅ፤ “እነርሱ ያልገዙት አገር እንደሚበታተን፤ ዜጎች እንደ ሩዋንዳና ቡሩንዲ እንደሚተላለቁ፣” ሟርትና ጥላቻን ይደሰኮራሉ፡፡ ባዶ ሟርትና ፕሮፖጋንዳ መሆኑን ለመረዳት ተገዢዎች ለማመን እስኪቸገሩ ድረስ ፕሮፓጋንዳ ይሠራባቸዋል፡፡ ያንንም ለማወቅ፣ “በእርግጥ ባህላችንና እምነታችን የተመቸ ነውን?” ብሎ የሚጠየቅ ሰው ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜም፣ የገዢዎቹ ሟርትና ማስፈራሪያ በሥልጣን ከመቆየት የዘለለ ቁብ እንደሌለው ይረዳል፡፡ “ጠመንጃ ነካሾች፣ በሥልጣን ኮርቻው ለመፈናጠጥና ለመቆየት ብለው የሚነዙትን ሽብር ፋይዳ-ቢስነት ለመረዳት፣ በመጀመሪያ ባህልን ጠንቅቆ ማወቅ” እንደሚያስፈልግ ኤድዋርድ ሳይድ Orientalism በተባለው መጽሐፉ ይመክራል፡፡
ስለባህል ምንነት ለመረዳት የሚፈልግ ሰው ካለም፣ “ባሕል ማለት ቋንቋ፣ ዜማ፣ ዘፈን፣ የአለባበስ ዓይነትና ዘዴ፣ የጸሎት ወይም የአምልኮ ሥነ-ሥርዓት፣ ከቤተሰብና ከጎረቤት ጋር ያለው ተራክቦ፣ በአረጋውያንና በልጆች ብሎም በወራዙት መካከል ያለውን ግንኙነትና ሥርዓት እንዴት ነው?” ብሎ መጠየቅና መመርመር አለበት (ፕ/ር ጌታቸው፣ 1960)፡፡ እስከምናውቀውና እከተረዳነው ድረስ፣ የኢትዮጵያውያን ባሕል በፈሪሃ እግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ነው በመሆኑ፣ ዕልቂትን አያስከትልም፡፡ እልቂት ቢከሰት እንኳን የእልቂቱና የግድያዎቹ ፈፃሚዎች ራሳቸውንና ሀገራቸውን ክደው፣ የገዢዎቹ ደረጃ ላይ ደርሰናል በሚሉት የነፃነት ገፋፊዎች ጭካኔ የሚፈፀም ነው፡፡ የእውነተኛ ኢትዮጵያውያን መዋግደ ኅሊና የተገራና ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለው በመሆኑ፣ ለጭካኔ ብርታት የለውም፡፡ ትክክለኛ ኢትዮጵያውያን ኅቁር ፍጥረታት አይደሉም፡፡ ከነፃነታቸውና ከሰብዐዊነታቸው ያለፈ፣ የሚያስቀድሙት ሃብትም ሆነ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ኅቁር ፍጥረታት ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ያስቀድማሉ፡፡ “ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይቅደም!” ሲሏቸው፣ “መልካም አስተዳደር እናሰፍናለን!” ይላሉ፡፡
ምዕራባዊያኑም ሆኑ አንዳንድ የምስራቅ አገሮች በአገራችን ላይ የባሕልና የመሠረታዊ ነፃነት ገፈፋን ስፖንሰር ያደርጋሉ፡፡ በከተሞቻችን አካባቢ እንደምናየው፣ ኦርቶዶክስሰ ክርስቲያኖቹ እንደሶሪያና ሊባኖስ ካህናት፣ ሙስሊሞቹም እንደ ሳዑዲና የመን ሼኪዎች፣ ካቶሊኮቹም እንደቫቲካን ቀሳውስት፣ ፕሮቴስታንቶቹም እንደጀርመንና አሜሪካን ፓስተሮች ለመሆን ይቸጋገራሉ፡፡ የሃይማኖትና የፖለቲካ መሪዎቹ፣ ራሳቸውን ክደው በሌሎች ባሕል ኮራጅነት ተጠምደው እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ ከራሳችን አለባበስ የእነርሱ አለባበስ፤ ከራሳችን ዜማና ዘፈን የነርሱ ጋጠወጥ ስልት፣ ከራሳችን የቤተሰብ ኑሮ የነርሱ ቤተሰባዊ ኑሮ፣ ከራሳችን ወግና ሥርዓት የነርሱ ወግና ሥርዓት፣ ከራሳችን አገር የነርሱ አገር የሚሻል መሆኑን ሊያሳምኑን ጥረዋል፡፡ የዚህ የዚህ ታዲያ፣ በዓድዋና በማይጨው ለምን የብዙ ኢትዮጵያውያን ንፁህ ደም ፈሰሰ? በሽንብራ ኩሬና በመተማ፣ በዶጋሊና በኦጋዴን ለምን ጀግኖች ተሰው? አገራችን እንዳትገዛና በእነርሱ እንዳትተዳደር አልነበረምን?!” እንጂ፤ “አገሪቱማ ሳትገዛና ሳትተዳደር መቼ አድራ ታውቃለች! ዋናው ምክንያት እነሱ በምንም መልኩ እንዳይገዙን መሰረታዊ ነፃነታችንን እንዳናጣ አልነበረም እንዴ? የራሳችን ባህል እንድንጠብቅና የነሱን ባህል እንዳንይዝ አልነበረምን?” አሁን ታዲያ ምን ነካን? ምን ዓይነትስ ጥንጣን በላን? ምን አነቀዘን? (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ 1960፡፡)
ከላይ በጠቀስነው መጣጥፋቸው ላይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንደገለጹት ከሆነ፣ “በማናቸውም ረገድና በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ መሠረታዊ ነፃነት እንጂ ነፃ ነፃነት የለም፡፡” ነፃ ነፃነት (Absolute Freedom) የሌለው፣ በነፃ ነፃነት ውስጥ መኖርም ስለማይቻል ነው፡፡ ነፃ ነፃነት አለ ካልን፤ የሕዝቡ የርስ በርስ ግንኙነት ባዶ (ዜሮ) ነው ማለታችን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ኃላፊነትና ግዴታ እስካለ ድረስ “ነፃ ነፃነት” የለም፡፡ ያለው መሠረታዊ ነፃነት ነው፡፡ አንዱ ከሌላው የሚቀበለውና ለሌላውም የሚሠጠው እስካለው ድረስ ነፃ ባህልም የለም፡፡ አንዱ ከሌላው ይዋሳል፤ ያውሳልም፡፡ ነፃ ባህል የለም፤ ነፃ ነጻነትም የለም፡፡ ያለው መሠረታዊ ባህልና መሰረታዊ ነፃነት ነው፡፡ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ መሰለፍ አትችሉትም የሚሉትና የሚያስሩት ወገኖች፣ የመሠረታዊ ነፃነት አፈና እያካሄዱ ነው፡፡ አንድ ሃሳብ ወይም አጀንዳ ሲነደፍ የሚጮኹና የሚፎክሩትም ወገኖች፤ መሠረታዊ ነፃነትን ለመግፈፍ በአነስተኛና ጥቃቅን ገዢነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡ ሃሳቡን ሳይሆን አሳቢውን የሚዘልፉና የሚሳደቡም ኅቁራን ካሉም፤ አንድ ለአምስት የተደራጁ የገዢዎቹ አባሪዎችና ተባባሪዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ አይደሉም፡፡
መሠረታዊ ነፃነትን የሚገድበው መንግሥት የሚባለው አካል ብቻ አይደለም፡፡ የመንደር ጎረምሳ፣ የቀዬ ጠብደልና የአጥቢያም ጎበዝ አለቃ ጭምር ናቸው፡፡ በግሌ መሠረታዊ ነጻነትን የሚገፍን አገዛዝ፣ ሥርዓትና መንግሥታዊ መዋቅር ለማጋለጥና አላህ ወይም እግዚአብሔር የሰጠኝንም ነፃነት ለማስከበር እጥራለሁ እንጂ፤ በአንድ ለአምስት ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን ከተደራጁ የመሠረታዊ ነፃነት ገፋፊዎች ጋር ቅንጣት ሴኮንድም አላጠፋም፡፡ በአንድ ለአምስት ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን የጎበዝ-አድማ ላይ ለተሰማሩት ወገኖቼም ሆነ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን የምናገረው ሃይለ-ቃልም የሚከተለተው ነው፡፡ “እርስ በርስ መፎካከታችንን ትተን፤ መሠረታዊ ነፃነታችንን የሚገፉትንና እያወናበዱ እንግዛችሁ የሚሉንን፤ ካድሬ ሆናችሁ፣ ሎሌ ሆናችሁ ቋንቋችንን ተናገሩ፤ የእኛን ባሕል ተከተሉ፣ የእኛን ሃይማኖት እመኑ፣ እናንተ ምንም ስለማታውቁ፣ እኛ ሁሉንም እናውቅላችኋለን፤ በአጠቃላይ “እኛን ምሰሉ” ባዮችን የአገዛዝ ዘመን እናሳጥር፡፡ እርስ በርስ ስንቦቃቀስ፣ የገዢዎቻችን እድሜ አራዝመን የእኛንም ሆነ የሕዝባችን ስቃይ ከማራዘም፣ የመሠረታዊ ነፃነት ገፋፊዎችን ጎራ ከማጠናከር በስተቀር የምናተርፈው ቅንጣት ታክል ፍርፋሪም ሆነ ሰደቃ እንደሌለ ማወቅ አለብን፡፡ አይመስላችሁም ጎበዝ?!
(የሳምንት ሰዎች ይበለን!)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችና የብዕር ጀግኖቿ ጦርነት

የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችና የብዕር ጀግኖቿ ጦርነት
በፍቅር ለይኩን
fikirbefikir@gmail.com
“ብዕር …፣ ብዕር …፣ የብዕር ኃይል ምንጊዜም ያሸንፋል!”
(ናይጄሪያዊው የብዕር ጀግና ኬን ሳሮዊዋ)
የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት ተመሠረተበትን የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ለማክበር በተለይ የኅብረቱ ዋና መቀመጫና ለአፍሪካ አንድነትምMap of Africa ሆነ ለኅብረቱ እውን መሆን ከንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እስከ ደርግ እና አቶ መለስ ዜናዊ ድረስ ብርቱ ጥረት ግንባር ቀደም ሚና በተጫወተችው በኢትዮጵያ፣ በመዲናችን አዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር መጠነ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ለበዓሉ ዝግጅትም ልዩ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከተቋቋመና አብዛኞቹ አፍሪካ አገራትም ነፃነታቸውን ከተጎናጸፉ በኋላ አፍሪካውያን በልባቸው ትልቅ ተስፋንና ራእይን ሰንቀው ነበር፡፡ አፍሪካ በጥቁር አፈሯ የአብራኳ ክፋዮች፣ በልጆቿ መሪነት ወደተሻለ ፖለቲካዊ አስተዳደርና መረጋጋት፣ ማኅበራዊ ተሐድሶ፣ ኢኮኖሚያዊ እምርታና ዕድገት ትገሠግሣለች ተብሎ ነበር በብዙዎች ዘንድ የተገመተው፣ የታሰበው፣ የታቀደውም፡፡
ግና ለአፍሪካ ይመጣል ተብሎ የታሰበው፣ ያ ብሩህ ዘመን የተገመተውንና የተጓጓለትን ያህል ብዙም ተስፋ ሰጪና ብሩህ አልነበረም፡፡ እዚህም እዛም የፈነዱት የብዙ አፍሪካውያን ሕይወት የቀጠፉ የእርስ በርስ ግጭቶችና ጦርነቶች፣ ስደትና መፈናቀል፣ በወታደሮችና በጦር ኃይል የታገዘ ደም አፋሳሽ የሆኑ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች፣ ሙስናና ዝርፊያ አኅጉሪቱን ባልተጠበቀ ፍጥነት ወደ ምድራዊ ገሃነምነት ነበር የቀየሯት፡፡ አፍሪካ ዳግም እንባ በስፍር የሚቀዳባት፣ ልጆቿ እርስ በርሳቸው የሚጋደሉባት፣ የሚተራረዱባት፣ ጽልመት የዋጣት የሰቆቃ፣ የመከራና የዋይታ ምድር ሆነች፡፡
በዚህ አጭር መጣጥፌ በብዙ ተስፋ ስለተደረገው የትላንትናው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት በአፍሪካ አገራት ውስጥ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በሌሎችም ዘርፎች ስላስመዘገበው ስኬቶች፣ ስላጋጠሙት እንቅፋቶችና ውድቀቶች ለመተንተን አይደለም አነሣሴ፡፡
ይሁን እንጂ የዚህ ጽሑፌ ዋና ትኩረት የኅብረቱን 50ኛው የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ባሉት አፍሪካውያን አገራት ውስጥ፣ የምድሪቱ የብዕር ጀግኖች በየአገራቸው የተነሡትን አምባገነኖችን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን፣ የአስተዳር ብልሹነትን፣ መሪዎቻቸው የተዘፈቁበትን ሙስና፣ የሞራል ዝቅጠትንና ውድቀትን… ወዘተ በማጋለጣቸው የተነሣ በየጊዜው የተነሡ አፍሪካውያኑ አምባገነኖች የብዕር ጀግኖቻቸውን ያሳደዱበትን፣ ያጋዙበትንና እንዲያም ሲል ሞት ያወጁባቸውን የአፍሪካ የምንጊዜም ምርጥ የብዕር ጀግኖች ስለሆኑ ኃያላኖች ታሪክ ጥቂት ላካፍላችኹ ወድጄ ነው፡፡
ዛሬም ድረስ የየአገሮቻቸውን አምባገነኖች ለማረም የተነሡትን የከበሩ ምሁራኖችን፣ ጸሐፊዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የጥበብና ብዕር ሰዎችን ጉሮሮ ለመፍጥረቅ እንደወትሮው ኃይል የማያንሳቸው አፍሪካና አፍሪካውያን አምባገነኖች በየጓዳው በተጽእኖ በትርና በአድርባይነት መርዝ ዛሬም ድረስ ስንቱን የኪነ ጥበብ ሊቅ በግፍ ረግጠው እየገዙ እንዳለ ሊታሰበን ይገባል፡፡ ለአብነትም ያህል በአገራችን በቀደመው ትውልድ ዘመን እነ አቤ ጉበኛ፣ እነ በዓሉ ግርማ፣ እነ ጸጋዬ ገ/መድኅን የመሳሰሉ ኃያላኖች በትንታግ ብዕራቸው አማካይነት ስለ ነፃነት፣ ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ በመጮኻቸው ነበር የእብሪተኞችና የአምባገነኖች ሰይፍ ሰለባ ለመሆን የተዳረጉት፡፡
በእኛው ዘመንም በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙ ሽልማቶች ባለቤት የሆነው እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እንዲሁም ከሰሞኑ እንኳን የመንግሥታቱ ድርጅት ዩኔስኮ ለነፃ ፕሬስና ሐሳብን በነፃነት ለመግለጥ እውን መሆን አምርራ በብዕሯ የታገለች ምርጥ፣ ጀግና ሴት፣ የብዕር አርበኛ ተብላ የተሸለመችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙና ሌሎችም በገዛ አገራቸውና መንግሥታቸው ‹‹አሸባሪ›› በሚል ሰበብ በወኅኒ እንዲወረወሩ ያደረጋቸው እምቢ ለእውነት፣ እምቢ ለፍትሕ፣ እምቢ ለነፃነት ባለችው ኃያል ብዕራቸው የተነሣ መሆኑን ማንም ይስተዋል ብዬ አልገምትም፡፡
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ተቋማት ድምፃቸውን ከፍ አደርገው የእነዚህን ኢትዮጵያውያን የብዕር ዐርበኞች ገድል እያወጁ፣ ለሥራቸውም ከፍ ያለ ክብር እየሰጡ ነው፡፡ መቼም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና የፕሬስ ተቋማት በታሪክ ‹‹አሸባሪዎችንና ሽብርተኞችን›› ሲሸልሙ፣ ሲሾሙና ሲያከብሩ አይተንም፣ ሰምተንም አናውቅም፡፡ ለመሆኑ መንግሥት ይህን እውነት በአደባባይ እያየና እየሰማ ምን እያሰበ፣ ምንስ መከራከሪያ እያዘጋጀ ይኾን?! ለመሆኑ ‹‹አሸባሪነትስ›› በመንግሥታችን መዝገበ-ቃላት ውስጥ ያለው ፍቺስ ምን ማለት ይኾን?!
ባለፉት ዓመታትም ወጣቱ ከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ በጥበብ ሥራው የዛሬው የትላንቱን ለመቀጣትና ለመበቀል ከሆነ ራእዩና ፍላጎቱ ለኢትዮጵያ የታለመው ሰላም፣ ብልጽግና፣ ዕድገትና ዲሞክራሲ አድራሻው ወዴየት ነው?! ቂም በቀል ይቅር፣ ለአንድ እናት ምድራችን በማንዴላ የእርቅ መንፈስ እጅ ለእጅ እንያያዝ፣ እንደጋገፍ፡፡ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በዘር መለያየታችን ይቅር፣ ኢትዮጵያችን ሁላችንም የጋራ ቤት፣ የጋራ እናታችን ናት፡፡ ሰንደቀ ዓላማችን፣ ቋንቋችን ፍቅርና ፍቅር ብቻ ይሁን!!
አለበለዚያ ግን የዛሬው መንግሥት በተራው በትላንቱ ላይ በጥላቻ ጥርሱን የሚነክስና የበቀል ሰይፉን የሚያነሣ፣ በቋንቋና በዘር የሚለያየንን የባቢሎንን ግንብ የሚያቆም ከሆነ ‹‹አዲስ ንጉሥ እንጂ መቼ ለውጥ መጣ?!›› ብሎ በማዜሙ የተነሣ ከፍቅር፣ ከፍትሕና ከእርቅ መንፈስ ጋር የተፋቱ የዘመናችን አንዳንድ ብኩኖችና እብሪተኞች በወጣቱ ከያኒ ላይ ጥርሳቸውን ክፉኛ ነክሰውበት፣ እንዲያ ሲያጥላሉትና ሲያወግዙት ለመስማት የተገደድንበት አጋጣሚ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡
ሌላው ቀርቶ በግሌ የማስታውሰው በኦሎምፒያ አካባቢ ተሰቅሎ የነበረው የወጣቱ ከያኒ ‹‹ጃህ ያሰተሰርያል!›› የሚለው የጥበብ ሥራው አልበም ፖስተር ከላይ እስከ ታች ነጭ ቀለም ተረጭቶ ያየኹበትን ትእይንት አሁን ድረስ ሳስታውስ አምባገነኖችና እብሪተኞች በልባቸው ያረገዙትን ክፋታቸውንና በቀላቸውን ለመተግበር ምን ያህል ርቀት ሊጓዙ እንደሚችሉ ነው በሐዘንና በጸጸት ውስጥ ሆኜ እንዳስብ ያደረገኝ፡፡
አፍሪካውያኑ አምባገነኖች በዚህ አካሄዳቸው አገራቸውን የዕድገት፣ የዲሞክራሲ፣ የነፃነትና፣ የፍትሕ ምች እንዲያጠናግረው የፈቀዱ ማን አለብን ባዮች ዓይኖቻቸውን ሳያርገበግቡ ምን መጠበቅ እንዳለባቸው አሳምረው ያውቁታል፡፡ ለእውነት፣ ለሰብአዊ መብቶች፣ ለፍትሕና ለሕዝብ ብሶት የቆሙ የጥበብ ድምፆችን፣ ብሩሾችንና ሐቀኛ ብዕሮችን በዋሉበትና ባደሩበት እያደፈጡ ሲያሴሩና ጥበብን አልከስክሰው በእውነት ላይ ለመማገጥ የታቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እናም ሊደፋፈሩ የሚገባቸውን ጀግኖቻቸውን ያዋክባሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ያግዛሉ፣ ይገድላሉ፣ ያስገድላሉ፡፡
ድንግል አፍሪካ፣ በተፈጥሮ ሀብቷ አቻና አምሳያ የሌላት አፍሪካ… የማርና ወተት መፍለቂያ ምድር እማማ አፍሪካ፣ አውሮፓውያኑ የአፍሪካ በዕዳን ወራሪዎች ካደረሱባት ግፍና መከራ ያልተናነሰ ከማኅፀንዋ የወጡ፣ ጡትዋን ጠብተው ያደጉ ልጆቿ፣ ነፍጥ ማንገታቸው ልባቸውን በእብሪት የወጠረው ወታደራዊ መሪዎቿ ይህ ነው ማይባል የግፍና የመከራ ዘመንን አስቆጥረዋታል፡፡ ለዛሬ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት በነበሩት በጄኔራል ሳኒ አባቻ ዘመነ መንግሥት ለእስራትና ለሞት ስለተዳረገው ስለ ኃያሉና ጀግናው ብዕረኛ፣ ደራሲ ኬን ሳራዊዋ ታሪክ በጥቂቱ ላካፍላችኹ ወደድኹ፡፡
የናይጄሪያዊው ጁንታ መንግሥት የስቅላት ገመድ በአንገቱ ገብቶ በሕይወቱ ላይ ስለተፈረደበት የነፃነት ታጋይ፣ የጥበብ ፊታውራሪ፣ የሕዝብ ልጅ፣ የናይጄሪያውያኑ የኢጎኒ ጎሳ ተወላጅ፣ የሕዝቡ የቁርጥ ቀን ልጅ ስለሆነው ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ሐያሲ፣ ነጋዴ፣ የፖለቲካ ሰው፣ ሃይማኖት ሰባኪ ኬን ሳሮዊዋ፡፡
የፈላጭ ቆራጩ የሳኒ አባቻ መንግሥት የደህንነትና የፀጥታ ክፍል ኃላፊዎች ኬን ሳሮዊዋ እትብት ከተቀበረበት ቀዬ ነዳጅ ቀድተው እንዳሻቸው መሆን እንደማይችሉ የተረዱት ናይጄሪያውያኑ አምባገነኖች ይህን በሕዝቡ ፍቅር የተነደፈውን ሐቀኛ ሰው ከማጥፋት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ እናም ይህን የሕዝብ አለኝታ ከምድራቸው ሊያጠፉት መከሩበት፤ መክረውበትም አልቀረ ያን የሕዝባቸውን የንጋት ኮከብ ገና በአፍላ ዘመኑ ብርሃኑን ጨክነው አጨለሙት፣ አጠፉት፡፡
አምባገነኖቹ ሳሮዊዋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያቀናበሩለት የውንጀላ ሴራም እንዲህ የሚል ነበር፡፡ በዋና ከተማይቱ አቡጃ ትልቁ አደባባይ በጠራራ ፀሐይ በተጠመደ ፈንጅ የታፈሩና የተከበሩ የሚባሉ በሳኒ አባቻ ፊት ሞገስ ያገኙ ሦስት አዛውንቶች በድንገት ተገደሉ፡፡ የእነዚህ አዛውንቶች ግድያ ከኬን ሳሮዊዋ ጋር ሚያገናኘው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ በወቅቱ በተደረገው ማጣራትም ግድያው የተፈፀመውም ሆነ አደጋው የተጣለው ወታደራዊውን ጁንታ በሚቃወሙ ወጣቶች መሆኑ ተገልፆ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ወታደራዊው አምባገነን መንግሥት ድርጊቱን በቀጥታ ከሳሮዊዋ ጋር በማያያዝ ለሳኒ አባቻ መንግሥት የእግር እሳት የሆነው የነፃነት ታጋዩ ኬን ሳሮዊዋ በዚህም አለ በዚያ በሐሰትም ቢሆን ተወንጅሎ ከሚወዳት አገሩና ሕዝቡ መወገድ ነበረበት፡፡ እናም ናይጄሪያዎቹ አምባገነኖች ይኽን ውሳኔ አስቀድመው አቅደውና ወስነው የዚህን ጀግና የብዕር ሰው ሞት/እረፍት ለማፋጠን ተቻኮሉ፡፡
ናይጄሪያዊው ደራሲና ብዕርተኛ ኬን ሳሮዊዋ በወቅቱ ሰለ አምባገነኖቹ ወታደራዊ መሪዎች እርምጃ እንዲህ ነበር ያለው፡- ‹‹እነዚህ ሰዎች ነፍሰ ገዳዮች ሆነው ሳሉ እኔን በከንቱ ለመወንጀል ይጥራሉ፤ በበኩሌ የመሠረቱብኝን ክስ እንኳን ለመስማት አልፈልግም፡፡ ችሎቱ በሚካሄድበት ወቅት ማለፊያ የሆነውን መጽሐፌን አንስቼ አነባለኹ፡፡ እነዚህ ሰው በላ ጭራቆች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ፍትሕንና እውነትን የተጠየፉ አምባገነኖች፣ በሚያዩት ሁኔታ እርካታ አግኝተው እንዲፈነጥዙ ዕድል አልሰጣቸውም፡፡››
ጀሽዋ ሐመር የተባለ ጋዜጠኛ ኬን ሳሮዊዋ ያለአግባብ ተወንጅሎ ወኅኒ ከተጣለ በኋላ አግኝቶ ለማነጋገር ብዙ ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ የናይጄሪያ ፖሊሶች ጋዜጠኛውን አታክተውና አሰላችተው ለመሸኘት ያደረጉት ጥረት ግን በሰውዬው አይበገሬነትና ብሎም በሳሮዊዋ ጠባቂ ትብብር ከሸፈና በስተመጨረሻ ሊያገኘው ቻለ፡፡ ጋዜጠኛው ጀሽዋ ሳሮዊዋን ባገኘው ጊዜ ብረት ባነገቱ ወታደሮች ተከቦ ነበር፡፡
ሳሮዊዋ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ ፒፓውን እያጨሰ ነበር፡፡ እንዳየኝ ይላል ጋዜጠኛ ጀሽዋ እንዳየኝ ተነሣና ጨበጠኝና ለመሆኑ ከቀናት በፊት የላኩልህ ደብዳቤዬ ደረሰኽ ሲልም ጠየቀኝ፡፡ እኔም ደብዳቤው እንደደረሰኝ አንገቴን በማወዛወዝ ገለጽኩለት፡፡ አብረን በቆየንበት ጊዜ ሳሮዊዋ የአገሩ አምባገነን መንግሥት መሪዎች ፍርደ ገምድሎች፣ ጨካኞችና የሰው ደም የጠማቸው ሆነው ሳለ በከንቱ ሲወነጅሉት የቱን ያህል ልቡ እንደተጸየፋቸው አጫወተኝ፡፡ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ኬን በሠራው ሥራ ሁሉ ፍፁም ጸጸት እንደሌለበትና የአሸናፊነት ስሜት እንደሚሰማውም ነገረኝ፡፡
በዚህ ጨዋታችን መካከልም የእስረኞቹ መኪና መጣ፡፡ ሳሮዊዋ መኪናው ላይ ከሚጫኑት ዋንኛውና አንዱ ተረሻኝ ነበር፡፡ መኪናው ላይ ከወጣ በኋላ የተለየኝ በአውራ ጣቱ አሸናፊነት/የድል ምልክት እያሳኝ በፈገግታ እንደታጀበ ነበር ይላል ጋዜጠኛው ጆሽዋ፡፡ ኬን ሳሮዊዋ በሕይወቱ ጀምበር ማዘቅዘቂያ የመጨረሻ ሰዓት ላይ ጋዜጠኛው ወዳጁን በዚህ መልኩ ከተለየው በኋላ ሳሮዊዋና ሁለት ሌሎች እስረኞች ጥብቅ በሆነ የጥበቃ አጀብ ወደሚሰቀሉበት ፖርት ሐርኮት እስር ቤት ተወሰዱ፡፡
ከመገደያቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ንስሐ ይቀበሉ ዘንድ አንድ እንግሊዛዊ ካህን ወደ ወኅኒ ቤቱ መጡ፡፡ በስፍራው የነበረ አንድ የዓይን ምስክር እንደገለጸው ሁለቱ እስረኞች ያለ ቅጥ እየተንሰቀሰቁ ሲያለቅሱ ሳሮዊዋ ተመልክቶ ጠጋ በማለት ለእናት ምድራቸው ናይጄሪያና ናይጄሪያውያን መሥዋዕት በመሆናቸው ሊኮሩ እንደሚገባቸው በመንገር በድፍረት የሞትን ጽዋ ይጠጡ ዘንድ ነበር ያበረታታቸው፡፡
የሞት ፍርዳቸው በሚጸናበት ረፋድ ጠዋት ላይ ኬን ሳሮዊዋ አዘውትሮ ከከንፈሩ የማይነጥላትን ፒፓውን ለአባቱ እንዲሰጡለት ገዳዮቹን ተማጸነ፡፡ ጥያቄውን የተቀበለው ሰው ግን አልነበረም፡፡ ወዲያው የአምባገነኖቹ ቅጥረኛ የሆኑት ወታደሮች የእስረኞችን ዓይን በጥቁር ጨረቅ ሸፍነው ወደ መስቀያው ስፈራ እያጣደፉ ወሰዷቸው፡፡ ኬን ሳሮዊዋ የመጀመሪያው ተሰቃይ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በሚገርም ሁኔታ በኬን ሳሮዊዋ አንገት ውስጥ የተጠለቀው ገመድ ለአራት ጊዜያት ያህልም ቢበጠስም በአምስተኛው ግን እነዛ ጨካኞችና እብሪተኞች ሕይወቱን በስቅላት ከነፍሱ ነጠሏት፡፡
ግዑዙ ገመድ እንኳን እምቢ ለፍትሕ፣ እምቢ ለእውነት ብሎ በኬን ጎን በቆመበት፣ በመሰከረበትና ባመጸበት በዛች ቅጽበት አምባገነኖቹ ልባቸውም ሆነ ዓይናቸው ታውሮ ይኼን እውነት ለመገንዘብ ሕሊናቸውም አእምሮቸውም ጨለመባቸዋልና ሊምሩት አልወደዱም፡፡ ወታደሮቹ ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው፣ በክፉው፣ ሸካራና ጠማማ ጎዳና ላይ ከመገሥገሥ የሚያግዳቸው ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ነበር ለናይጄሪያ ሕዝብና ለመላው ዓለም ለማሳየት የሞከሩት፡፡
ታጋይ፣ ደራሲ፣ ጸሐፊ … የሆነው ኬን ሳሮዊዋ በናይጄሪያ ደቡብ ምስራቅ ጠረፍ በኒጀር ወንዝ ዳርቻ የሚኖር የኢጎኒ ብሔር ተወላጅ ነበር፡፡ በ54 ዓመት ዕድሜው በግፍ በገመድ ተንጠልጥሎ ለሕልፈት የበቃው ሳሮዊዋ በተለያዩት ጊዜያት በጋዜጦች ላይ ባቀረባቸው መጣጥፎች፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ የሰላ ትችቶቹ፣ በቴሌቪዥን ዝግጅቶቹና ዘገባዎቹ በድፍን ናይጄሪያ ከፍተኛ ተወዳጅነትንና ዝናን ለማትረፍ የቻለ ስመ ገናና ጸሐፊና ገጣሚ ነበር፡፡
‹‹ሶልጀር ቦይ›› የተሰኘ ወጥ የፈጠራ ሥራው ከአገሩ አልፎ ከበሬታን ያተረፈለትና ተነባቢ ሥራው ለመሆን በቅቶለታልም፡፡ ሳሮዊዋ በኑሮው የተደላደለ ቱጃር ለመሰኘት የሚችል፣ የግሉ የሆነ ፕሬስ መሥርቶ በመንቀሳቀስ ላይ የነበረና ይህ ጎደለው የማይባል ሰው የሚባል ዓይነት ቢሆንም እንኳን ናይጄሪያና ናይጄሪያውያን ዕጣ ፈንታ በአምባገነኖቹና በጨካኙ ወታደራዊ ኃይሎች እጅ መውደቁ እረፍት ስለነሣው አምባገነኖችን በብዕሩ አምርሮ ለመዋጋት ተነሣ ጀግና የብዕር ሰው ነበር፡፡
ታጋዩና ደራሲው ኬን ከትውልድ ቀዬው በገፍ የሚቀዳው ጥቁር ወርቅ (የነዳጅ ዘይት) የናይጄሪያ 90 በመቶ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም በላይ ለሙስናና ለምዝበራ ለተዘፈቁት ወታደራዊ ገዢዎች መንደላቀቂያነት ሲውል ታዝቧል፡፡ ሕዝቡ ይህ ነው በማይባል ድህነትና ጉስቁልና ውስጥ ተዘፍቀው አምባገነኖቹ እንዲህ መቀማጠላቸው የሕሊና እረፍት የነሣው ሳሮዊዋ ይህን ግፍ ለመበቀል ነበር ብዕሩን በድፍረት ያነሣው፡፡ በዚህም አምባገነኖቹንና ሙሰኞቹን ናይጄሪያውያንን ክፉኛ ነበር ያሰጨነቃቸው፡፡
ደራሲና ታጋይ ኬን ሳሮዊዋ ሙያውን አክባሪና በሙያው ተደሳች እንደነበር ለእንግሊዛዊው ደራሲ ዊሊያም ማድዬ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ነበር ማንነቱንና ሥራውን የገለጸው፡-
በእጅጉ የማከብረውንና የምወደውን የኢጎኒ ሕዝብ እነዚያ አበሳውንና ፍዳውን በሚያስቆጥሩት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችን እንዲጋፈጣቸው ለማድረግ የሥነ ጽሑፍ ስጦታዬን እንደ ታላቅ መሳሪያ ለመጠቀም በመቻሌ በሕይወቴ ውስጥ ትልቁ ነገር ሆኖ ይመዘገባል፡፡ ብዕሬን ለወገኖቼ አርነት ማዋሌን ያህል ሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ ለወገኔ የእኔ ድምፅ፣ የእኔ ጩኸት በጣሙን ወሳኝና አስፈላጊ ነበር፡፡
በእጅጉ የሚደንቅ ነው!! ፖለቲከኛ ሆኜ እንዲህ ያለ ነገር ማድረግ አልቻልኩም፣ በንግዱ ዓለም ተሰማርቼ በነበር ወቅትም አልሳካልኝ ያለ ነገር ነበር፡፡ ብዕር አንስቼ ከወረቀት ጋር ማዋኻድ ስጀምር ግን ከባዱ ነገር ቀላል ሆነ፡፡ አልሳካ፣ ድምፁም አልሰማ ያለው ነፃነትና የፍትሕ ድምፅም ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በምድሬ በናይጄሪያ ተሰምቶ አምባገነኖቹንና እብሪተኞችን መግቢያና መውጫ አሳጣቸው፣ እረፍትም ነሣቸው፡፡
ብዕር …፣ ብዕር …፣ የብዕር ኃይል ምንጊዜም ያሸንፋል፡፡ ለእኔ ከዚህ በላይ ደስታ የለም፡፡ በዚህ ወቅት የፈለገው ነገር ቢመጣም በቆራጥነት ለመጋፈጥ ተዘጋጅቼያለኹ፡፡ እንደሚመስለኝ በዚህ ሰዓት ታላቅ የሆነ የሞራል ድል የተጎናጸፍኩት እኔ ነኝ፡፡ በጠላትነት የተነሡብኝ አምባገነኖች፣ ጠላቶቼ ከዘላለማዊ እፍረትና ጸጸት ከማያመልጡበት የሲኦል ቅርቃር ውስጥ እንደገቡ ሆነው ነው የሚሰማኝ፡፡ ነበር ያለው ያ ጀግና የብዕር ሰው!!
በእያንዳንዱ ናይጄሪያዊ ሕዝብ፣ የአርነት ታጋዮችና በዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ ብሎም የኪነ ጥበብ ወዳጆችና አፍቃሪዎች ልብ ውስጥ ኬን ሳሮዊዋ ዛሬም ነገም ሕያው ሆኖ ይኖራል፡፡ አባቻና መሰል አምባገነኖች ግን በአረመኔያዊ ግብራቸው ታሪክ በትዝብት ሲያስታውሳቸው ይኖራሉ፡፡
በመጨረሻም በአገራችን ታላቅ የሆነ ብዕራዊ ተጋድሎ ያደረጉትን እነ ጸጋዬ ገ/መድኅንን፣ እነ አቤ ጉበኛን፣ እነ በዓሉ ግርማን አርአያ አድርገው ዛሬም ስለ እውነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ነፃነት … በጨዋ፣ በታረመና ባላመነዘረ ብዕራቸው ተጋድሎ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵውያን ሁሉ ያለኝን አድናቆትና ክብር ለመግለጽ እወዳለኹ፡፡
በአቤ ጉበኛና በበዓሉ ግርማ መንፈስ፣ ሌሎችም በዚህ ዘመን የእነርሱን ብዕር ቁርጠኝነትና ወኔ የተቀላቀሉ ኃያላንና ጀግኖች ብዕረኞች ለተገፉ ወገኖቻቸው፣ ለሰው ልጆች መብት፣ ለፍትሕና ለእውነት በመቆም በተባ ብዕራቸው ላደረጉትና እያደረጉት ላለው ታላቅ ተጋድሎ ሊዘከሩ የሚገባቸው የምን ጊዜም የኢትዮጵያ የብዕር ጀግኖቻችን ናቸውና ልናከብራቸው፣ ልንዘክራቸው ይገባናል ለማለት እወዳለኹ፡፡
ሰላም! ሻሎም!

One Response to የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችና የብዕር ጀግኖቿ ጦርነት

  1. April 23, 2013 at 2:34 pm

Sunday, April 21, 2013

Ethiopia’s genocidal minority junta verging on madness?
The Horn Times News 21 April 2013
by Getahune Bekele, South Africa

Human rights institutions urged to assist in stopping the illegal transfer of political prisoners to Zeway death camp

Located 170 kms south-east of Addis Ababa on the outskirt of Zeway town, the Zeway death camp has been in the news recently after the ruling minority junta began sending political prisoners to the camp since early March 2013.
Chillingly dubbed “the Auschwitz of Africa” the prison was established by former TPLF strong man Tamrat Layne
Warlord turned Pastor Tamrat Laine
Warlord turned Pastor Tamrat Layne
(pictured) in 1993 as forced labor camp to provide cheap slave labor force for his massive sunflower and vegetable farms in the area which he co-owned with the uncontestable black billionaire Sheik Alamoudi Mohammed.
However, after the 2005 nationwide anti-TPLF insurrection, the walled in ghetto with high death rate than any other prison in Ethiopia was transformed into death camp by the late evil tyrant Meles Zenawi.
The high death rate is attributed to malaria infestation, cholera outbreak, tuberculosis, severe malnutrition and unbearable overcrowding; and to widespread torture and extrajudicial killings committed by carefully selected corrupt Tigre camp guards.
In the camp synonymous with poor sanitation, prisoners drink untreated water drawn from the nearby Lake Zeway. The stench of human waste and raw sewerage hangs in the air and gets worse during rainy season.
According to investigation done by the Horn Times and vital information obtained from former inmates, suicide is rampant at the country’s most brutal facility where the minority Tigre junta enslaves Ethiopians forcing them to live with rats and lice inside concrete cells in unspeakable squalor.
“Zeway concentration camp is the most frightening place to be at specially if you are a political

የሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥት ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደ ነው

 
ከኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የጋራ እንቅስቃሴ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ሚያዝያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም. (April 20, 2013)Ethiopian flag, Green, yellow and red
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔረሰቦችና ሀይማኖት ተከታዮች ሀገር ናት። እነዚህ ብሔረሰቦች ለብዙ ዘመናት በአንድነትና በሕብረት ተደጋግፈው፤ ተጋብተውና ተስማምተው ኖረዋል። ከውጭ የመጣባቸውን ጠላትም በተባበረ ክንዳቸው መክተው በመመለስ በዓለም ታዋቂ ታረክ አስመዝግበዋል። በአሁኑ ወቅት ከመሀከላቸው የበቀሉ ተንኮለኞች ለፓለቲካ ሥልጣንና ለግል ጥቅም ማራመጃ ሲሉ የሚያካሂዱትን የመከፋፈል እርምጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተከታታይ እያከሸፈው ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት በጦር ኃይል እያስገደዱ በአንድ ብሔረስብ ላይ ያተኮረ አስከፊና አደገኛ የዘር ማጥፋት ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።
ይህንን ሰላም ወዳድና በሰላም የኖረ ሕዝብ እርስ በራሱ በማጋጨትና አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳሳ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር/ሕወሓት መሪዎች ከፅንሳቸው ጀምረው በፖሊሲ ደረጃ ነድፈው እስካሁን በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ። ወደፊትም በሥልጣናቸው ለመቆየትና ከሕዝብ የሚዘርፉትን ንብረት ካለምንም ተቃውሞ ለማካሄድ ወገኖቻችንን በዘርና በቋንቋ በመለያየት ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ሆን ተብሎ በተቀየስ የዘር ማጥራት ፖሊሲ አማካኝነት ለጊዜው ከተወሰኑ ክልሎች በማፈናቀል ላይ ናቸው።
የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ከአመስራረቱ ጀምሮ በተለይም በአማራው ኅብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ የዘር ጥላቻ ፓሊሲ በተለያየ መልኩ ሲያስፈጽምና ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል። ይህም ድርጊቱ በአጭሩ ካልተቀጨ በቀር በደቡብ አፍሪካና በሩዋንዳ ሀገሮች ከተካሄዱት የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች የማይተናነስ ዕልቂት በአገራችን ሊደርስ እንደሚችል መገመተ አያዳግትም። በቅርቡ ከቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ወደ 8000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የአማራ ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ ከሚኖሩበት አካባቢ ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸው የዚህ አንዱ ማስረጃ ነው። ከእነዚህ ውስጥም በርካታ ሕፃናት፣ እርጉዞችና አዛውንቶች እንደሚገኙበት ታውቆአል። ተፈናቃይ ወገኖቻችን ያፈሩትን ንብረት እንኳን ሳይሸጡና ሳያሰባስቡ በመሣሪያ ኃይል ተገደው እንዲባረሩ በመደረጉ ብዙዎች ለከፋ አደጋና እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት ተዳርገዋል።
ባለፈው ዓመትም እንደዚሁ በተመሳሳይ ሁኔታ ብዛታቸው 20,000 በላይ የሆኑ የአማራ ተወላጆች ከደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ወረዳ ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀው በያሉበት ከተበታተኑ በኋላ፤ በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በትክክል አይታወቅም።የተፈናቃዮቹን ስቆቃ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለዓለም ኅብረተሰብ ለማሳወቅ ጋዜጠኞችም ሆኑ የተቃዋሚ ድርጅት ተወካዮች ተከታትለው እንዳይዘግቡ በአካባቢው በሚገኙ ካድሬዎቹና ታጣቂዎች አማካኝነት ከተፈናቀሉት ተጎጅዎች ጋር ግኑኝነት እንዳይኖር ዘረኛው መንግሥት ከልክሏል። በአንድ ሕብረተሰብ ላይ ይህንን የመሰለ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ መመልከት በታሪክ ተወቃሽ ከማድረጉም በላይ፤ በተለይ ግን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የድርጊቱ ተባባሪ የሆነ ሁሉ ወደፊት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን ሊታወቅ ይገባል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬውም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት በአንድ ሕዝብ ላይ በዘር ቆጠራና በቋንቋ ምክንያት ነጥሎ ጥቃት ማድረስ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የሚደነግግ ጠንካራ ሕግና የማስፈጸሚያ ደንቦች አሉት። በተለይም ኢትዮጵያ ይህንን የተባበሩት መንግሥታት ሕግ ተቀብላ በፊርማዋ ያጸደቀች በመሆኑ፤ የሕወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች በቀጥታ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው። ለጊዜው በጉራ ፈርዳና በቤንሻንጉል-ጉሙዝ አካባቢዎች የተፈጸሙት አረመኔያዊ ተግባራት በአጋጣሚ ይፋ ሆነው ወጡ እንጂ፤ በሌሎች አካባቢዎች በስውር የተፈናቀሉ ከነቤታቸው በእሳት የተቃጠሉ፤ ገደል የተጣሉ፤ በየጫካው ለዱር አራዊት ቀለብ የተደረጉ እንዳሉ የታወቀ ነው። በአንድ ወቅት የሕወሓት መንግሥት የሕዝብ ስታቲስቲክስ መ/ቤት ዲሬክተር በ2000 ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ከ2 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ አማራዎች መረጃው ከሚያሳየን ውጭ የት እንደገቡ አናውቅም በማለት ለፓርላማ ተብዬው ቀርበው አስረድተዋል። በዚህ መረጃ ላይ መንግሥት እስካሁን ይህን ያህል ብዛት ያለው ወገኖቻችን የት እንደገቡ የሰጠው መግለጫም ሆነ ማብራሪያ የለም።
ሕወሓት/ኢሕአዴግ ይህንን በአማራው ላይ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋት ተግባሩን በዚህ ብቻ ያቆማል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ እነኝህን የሕዝብ ጠላቶች በቃኝ ብሎ ከሥልጣን እስካላስወገደ ድረስ፤ ዘመቻው በተጠናከረና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም እንደሚቀጥል የተረጋገጠ ነው። ከአማራው ቀጥሎ የኦሮሞው፤ ከኦሮሞው ቀጥሎ የወላይታው እያለ ይቀጥላል። ምክንያቱም የዘረኛው መንግሥት ዕድሜ የሚራዘመው ወይንም የመኖሩ ምሰሶ የተመሠረተው ወገንን ከወገን በማናቆርና በማጋጨት ላይ በመሆኑ ነው። ይህን አስከፊና አረመኔያዊ ተግባሩን ለማስቆምም ሆነ ለመግታት የሚቻለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተነሱበትን የጥፋት ሴራ በሚገባ ተገንዝቦ ይህንን አደገኛና ጠባብ የዘረኛ ቡድን ከሥልጣን አስወግዶ በምትኩ በሕዝባችን ፈቃድና ሙሉ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ እውነተኛ መንግሥት ሲያቆም ብቻ ነው።
ይህ ጉዳይ የሚመለከተውም ሁሉንም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ክፍል በመሆኑ ሁላችንም በቋንቋ፣በጎሳና በሃይማኖት ሳንለያይ በአንድነት ተነስተን በመቆም በተባበረ ኃይል የሕወሓት/ኢሕአዴግን አምባገነናዊ ሥርዓት በማስወገድ በፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት በጋራ መሥራትና መታገል አለብን።
ለዚህም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የጋራ እንቅስቃሴ አስተባባሪ ኮሚቴ በሚቻለው ኃይሉ ሁሉ የዘረኛውን ቡድን እኩይ ተግባራት ለማጋለጥና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሠረታዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶቹን ተጎናጽፎ በአሸናፊነት እንዲወጣ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማድረጉን ይቀጥላል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የጋራ እንቅስቃሴ አባላት፥
ጥምረት ለነፃነት ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ

ESAT Daily News Amsterdam April 20 2013 Ethiopia

Thursday, April 18, 2013


ሰበር ዜና – ‹‹ለፓትርያሪኩ መመሪያ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል›› የተባሉት ኣባይ ፀሃየ ከደጅ ተመለሱ

  • በሦስት ቡድኖ የተደራጀው የጨለማው ቡድን ‹‹የኣባይ ፀሃዬን አመራር›› ያቀናጃል
  • መመሪያው÷ የልዩ ጽ/ቤት፣ ፕሮቶኮል፣ ጥበቃ ሓላፊዎችን ምደባ ይመለከታል ተብሏል
  • ‹‹ኣባይ ፀሃዬ ከስኳር ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን በበላይነት እንዲመሩ ከመንግሥት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በትግራዎት እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ ለሚኒስትሮች የሚፈለገውን ጥቅም እያቀረብን እናስፈጽመዋለን፡፡››
/ኣባይ ፀሃዬ ለፓትርያሪኩ የሚሰጡትን ‹‹አመራር›› ከእነ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ ያስተባብራሉ የተባሉት በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት አባ ገብረ መድኅን ኀይለ ጊዮርጊስ ዛሬ ጠዋት የተናገሩት/
  • ፓትርያሪኩ ‹‹አባ›› ነኝ ባዩን ከግቢው እንዲያርቁላቸው መመሪያ ሰጥተዋል፤ ተፈጻሚነት ይኖረው ይኾን?
  • መንግሥት፣ የቤተ ክርስቲያን አመራርና ምእመኑ ጉዳዩን ከምር አጢነው አቋም እንዲወስዱ ተጠይቋል፡፡
abai-tsehaye-tigraionline
አቶ ኣባይ ፀሃዬ
ከአምስተኛው ፓትርያሪክ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ፣ የመንበረ ፓትርያሪኩን ላዕላይ መዋቅሮች በመቆጣጠርና ለተቋማዊ ለውጥ የታቀዱትን ተግባራት በማምከን÷ 1)ቡድናዊና ግለሰባዊ ጥቅሙን አስጠብቆ ለመቆየት፣2)ኦርቶዶክሳዊ ማንነትን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ደብዛውን ለማጥፋትበልዩ ኹኔታ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የጨለማው ቡድን÷ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በጎጠኝነት፣ በፖሊቲካዊ ታማኝነትና በጥቅም ስቦ እና አቅርቦ ማሰለፍ መጀመሩ ተዘገበ፡፡
በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎችና ድርጅቶች ውስጥ በሓላፊነት ደረጃ የተቀመጡ ጥቅመኞችን ጨምሮ የታወቀ ሹመት የሌላቸውን ነገር ግን የሁሉ ፈጣሪና ገባሪ ለመኾን ‹‹ሥልጣን›› ያገኙ ግለሰቦችን የሚያካትተው የጨለማ ቡድኑ÷ በፓትርያሪኩ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ላይ ማሰለፍ የጀመረው‹‹የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ነው›› ተብሏል፡፡ ቡድኑ በዚህ ስትራተጂው የህወሓት/ኢሕአዴግን ባለሥልጣናት ተጽዕኖ በመጠቀም በማንኛውም ቦታ በተለይም በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ላይ ተጽዕኖውን ለማጠናከርና ያሻውን ለመፈጸም ማቀዱ ነው የተነገረው፡፡
ይኸው ስትራተጂ ባለፉት ኻያ ዓመታት መንበረ ፓትርያሪኩ ለክፍፍልና ትርምስ የተዳረገበት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለጥቃትና ድብደባ የተጋለጡበት እንደነበር ያስታወሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ስልቱ በመልኩ አዲስ ባይሆንም በይዘቱ ግን ቡድኑ የተለየ ቁመና ይዞ የተደራጀበት መኾኑን ያስረዳሉ፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ፅልመታዊ ቡድኑ ለሦስት ኀይል ተከፍሎ በተለያዩ ግለሰቦች የሚመራ ሲሆን የተመረጡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን እየተፈራረቀ በመወትወት/በማግባባት ተመሳሳይ ጉዳይን ከተለያየ አቅጣጫ እያስተነተነ ስለጉዳዩ አንድ ዐይነት ቀለም/ሥዕል ለመፍጠር ግፊት ያሳድራል፤ ለኾነ ርምጃ የሚያበቃ ውሳኔ እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡ በዚህም ቡድኑና አባላቱ ለመንግሥት ቀራቢና ተቆርቋሪ፣ ለቤተ ክርስቲያን አሳቢ መስለው ጋርዮሻዊና ግለሰባዊ ጥቅማቸውንና ሥልጣናቸውን ያስጠብቃሉ፡፡
ለሦስት ኀይል የተከፈለውን ‹‹የጨለማ ቡድን›› የሚመሩት ግለሰቦች፡-
  • አባ ገብረ መድኅን ኀይለ ጊዮርጊስ – በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳምአበምኔ
  • አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል – በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ዋና ሓላፊ                              
  • ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ – በመዋቅር የማይታወቀው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅContinue reading 

በረኀብ የተዳከሙት ደቀ መዛሙርት ልመና በፖሊስ ታገደ፤ ፖሊስ ደቀ መዛሙርቱን ለመርዳት ከሚሞክሩ ምእመናን ጋራ ተወዛግቧል

  • ሓላፊዎቹ ከመምህራን የቀረቡላቸውን ሦስት ማግባቢያዎች በሙሉ ውድቅ አድርገዋል
  • ደቀ መዛሙርቱ በኮሌጁ አስተዳደር ላይ ክሥ መመሥረታቸው ተጠቁሟል
  • በአዲስ አበባ ዘመድ/መጠጊያ የሌላቸው ደቀ መዛሙርት በእጅጉ ተቸግረዋል
  • ፓትርያሪኩ ‹‹ጣልቃ አልገባም›› ማለታቸው የመምህራኑን ጥረት ጎድቷል
  • ‹‹ሃይማኖት የሌለው መምህር አያስተምረንም ባልን በረኀብ እየተቀጣን ነው›› /በደቀ መዛሙርቱ ከተለጠፉት ጥቅሶች አንዱ/
ሚያዝያ 7 ቀን 2005 ዓ.ም፤ ንጋት ላይ ነው፡፡ በአራት ኪሎ ወ.ወ.ክ.ማ በኩል ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴCollege bld 01 ካቴድራልበሚያስገባው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሦስተኛ በር በርካታ ምእመናን ተሰባስበዋል፡፡ ዕለቱ የቅድስት ሥላሴ ወርኀዊ በዓል መታሰቢያ እንደመኾኑ የምእመናኑ ቁጥር ከፍተኛ ነበር፡፡ በኮሌጁ ቅጽር ውስጥ ቆመው ጥቁር ቀሚሳቸውን እንደለበሱ መሥመር ይዘውና ፊታቸውን በካቴድራሉ መውጫና መግቢያ ላይ አድርገው በዝምታ የቆሙትን ደቀ መዛሙርት ይመለከታሉ፡፡ የብዙዎቹ ደቀ መዛሙርት ገጽታ ድካምና ጉስቁልና ይነበብበታል፡፡ ከፊት ለፊታቸው ነጭ ጨርቅ ተዘርግቷል፡፡
በኮሌጁ በር ላይ የተለጠፉት ጥቅሶች ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አኳኋን የተገኙበትን ምክንያት የሚያስረዱ ነበሩ – ‹‹ሃይማኖት የሌለው መምህርአያስተምረንም ባልን በረኀብ እየተቀጣን ነው››፤ ‹‹ወንጌል ይዘውበረኀብ እያሠቃዩን ነው››፤ ‹‹የረኀብ እሳት እየገረፈን ነውናረኀባችንን አሥታግሱልን››፤ ‹‹እየሞትንም ቢኾን ሙስናንና ዘረኝነትን እንዋጋለን››፡፡ ከምእመናኑ የቻሉት በአጥሩ አሻግረው/አሾልከው በጨርቁ ላይ ምጽዋት ይጥሉላቸዋል፤ ያልቻሉት አዝነው ይሄዳል፡፡ አንዳንዶቹም ወደ ቅጽሩ ቀረብ ብለው ማብራሪያ ይጠይቃሉ፤ ምን እንርዳችኹ ባዩም ጥቂት አልነበረም፡፡ ኮሌጁ መዘጋቱንና ከሳምንት በላይ ምግብ መከልከላቸውን ለምእመናኑ ያስረዱት ደቀ መዛሙርቱ ችግራቸውን ገልጠው ይናገሩ ነበር፡፡
ትዕይንቱ የተቀየረው ከቆይታ በኋላ በስፍራው የደረሰው የፖሊስ ኀይል በወሰደው ርምጃ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ርዳታ መጠየቃቸውን የተከላከለው ፖሊስ በኮሌጁ መግቢያ በር ላይ የተለጠፉ ወረቀቶችን ቀዳዷል፤ ምእመናኑም እንዲበተኑ አድርጓል፡፡ የታሸገ ውኃ እንኳ በአጥር ለማቀበል የተደረገውን ሙከራ ፖሊስ እንዳይገባ ሲከላከል ታይቷል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በግቢያቸው ውስጥ ተወስነው ርዳታ እየጠየቁ ባለበት ኹኔታ የፖሊስ ኀይሉ ከጸጥታ ማስከበር ባሻገር የወሰደውን ርምጃ ፊት ለፊት የተቃወሙ ምእመናን ከፖሊስ አባላቱ ጋራ ሙግት ገጥመው ታይተዋል፡፡ የሙግቱን ፋይዳቢስነት የተረዱ ጥቂት ምእመናን፣ ‹‹ምንም ቢኾን ልጆቻችን ናቸው፤›› በሚል ሰብሰብ ብለው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩን ለማነጋገር ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ያመራሉ፡፡
ምእመናኑ በበጎ ሐሳብ ተነሣስተው ያደረጉት ሙከራ ግን እንዳሰቡት አልተሳካላቸውም፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩን በቅዳሴ መግቢያ ሰዓት ለማግኘት ሲጠባበቁ የነበሩት ምእመናኑ የገጠማቸው ኀይለ ቃልና ማመናጨቅ ነበር፤ ከቅዱስነታቸውም የሰሙት ቃል ቢኖር ‹‹ወደ ቅዳሴ እየገባኹ ነው›› የሚል እንደነበርና በዚህም ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ ቅንነትና ለኮሌጁ ማሰብ ብቻ ለውዝግቡ እልባት ለመስጠት በቂ ነው የሚሉት ምእመናኑ፣ ደቀ መዛሙርቱ በምርጫው ወቅት ይዘውት የነበረውን አቋም በማስታወስ ‹‹ምናልባትም መፍትሔውን አዘግይቶ ለመበቀል ይኾን?›› የሚል ጥርጣሬ እንዳደረባቸው አልሸሸጉም፡፡ Continue reading 

የቅ/ሥላሴ መን/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ቀሚሳቸውን አንጥፈው ሲለምኑ ዋሉ

  • የኮሌጁ ካፊቴሪያ ለደቀ መዛሙርቱ ምግብ እንዳያዘጋጅ በሊቀ ጳጳሱ ታዝዟል
  • ሊቀ ጳጳሱ ሁሉም መምህራን በመደበኛው የቀን መርሐ ግብር እንዳያስተምሩ ከልክለዋል
  • ሊቀ ጳጳሱ በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሥራውን እንዳይጀምር አድርገዋል
  • በሊቀ ጳጳሱ ዙሪያ የተሰለፈው የቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን ፓትርያሪኩንም እያሳሳተ ነው
  • ደቀ መዛሙርቱን ለማስወጣት የተጠራው የፖሊስ ኀይል ርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልኾነም
  • በኮሌጁ የሚዘዋወሩ ስመ ደኅንነቶች ደቀ መዛሙርቱን፣ መምህራኑንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን እያስፈራሩ ነው
ይህ ፻ውን የሐራ ዘተዋሕዶ ዘገባ ለንባብ ያበቃንበት ጦማር ነው፡፡ ከጦማሮቹ የሚበዙት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተቋማዊ መገለጫ ለመኾን ስለ ደረሰው ጥቅመኝነትን የመከባከብ፣ ሙስናንና የአሠራር ብልሹነትን የማንገሥ፣ ከሙሰኞችና ጥቅመኞች ጋራ የመደራደር አስተሳሰብና ተግባር የሚመለከቱ ናቸው፡፡ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር እና የደቀ መዛሙርቱ ውዝግብ አያያዝና እየተወሳሰበ የመጣበት ኹኔታ ከዚህ የተለየ መነሻ የለውም፡፡
የኮሌጁ መምህራን እንደሚናገሩት፣ የትምህርት አስተዳደሩ እንዲሻሻልና የደቀ መዛሙርቱ አካዳሚያዊ መብቶች እንዲከበሩ የቀረቡ ጥያቄዎችንሓላፊነት በተሞላበት መንገድ ደቀ መዛሙርቱን ከመምህራኑ ጋራ በግልጽ በማወያየት ምላሽ መስጠት ይቻላል፡፡ ይህም ካልኾነ የመማር ማስተማሩን ጤናማነት/ሰላማዊነት ለመጠበቅ ተቃውሞ የቀረበባቸውና ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ መስማማት ያልቻሉ መምህራን ከሓላፊነታቸው ገለል እንዲሉ ማድረግ ነው፡፡
His Grace Abune Timothy
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ
(የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ)
እየኾነ ያለው ግን ላለፉት 14 ዓመታት በኮሌጁ የበላይ ሓላፊነት ከቆዩ ሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በቅ/ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ የማጣራት ሥራውን ጨርሶ ጥያቄያቸው ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የተቃውሟቸው ሁለቱ ሓላፊዎችና መምህራን ወደ ክፍል ገብተው እንዳያስተምሩ በመከላከላቸው እልክ የተጋቡት ሊቀ ጳጳሱ ‹‹ያቋረጣችኹትን ትምህርት በአግባቡ አልጀመራችኹም››በሚል የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር ከመጋቢት 30 ቀን ጀምሮ የተዘጋ መኾኑን የኮሌጁን ክብ ማኅተም ይዞ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት በወጣ ማስታወቂያ አሳስበዋል፤ በቁጥር 181 ያህል የሚኾኑት የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርትም ንብረት አስረክበው በአስቸኳይ ከኮሌጁ እንዲወጡ አዝዘዋል፡፡
ሊቀ ጳጳሱ በተለይ ከቀኑ መርሐ ግብር አስተባባሪና በክፉ ምክር እያሳተ የግል ጥቅሙን ከሚያካብተው ዘላለም ረድኤት ጋራ በመኾን ያወጡትን ይህን ማስታወቂያ የተቃወሙት ደቀ መዛሙርት ግን ከኮሌጁ አልወጡም፤ መምህራኑም ከማስተማር አልታቀቡም ነበር፡፡ ይህ በእጅጉ ያስቆጣቸው ሊቀ ጳጳሱ ትላንት ጠዋት መምህራኑን አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ‹‹ማስተማር እንደሌለባችኹ ለማሳወቅ›› በሚል አጀንዳ ሲወዛገቡ ውለዋል፡፡ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ከቀትር በኋላ ቀጥሎ የዋለው ስብሰባው በንዴት በጦፉና አንዳንዶቹም ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ ‹‹አንተ አንቺ ቀረሽ›› እላፊ ቃላት በሚነጋገሩ መምህራን ቁጣ የተሞላ ነበር ተብሏል፡፡
‹‹የሁለት ሰዎች ችግር ኮሌጁን ሊያዘጋ አይችልም›› ያሉት መምህራኑ ችግሩን በመመካከር መፍታት እንደሚቻልና በዚህ የማይፈታ ከኾነ ግን መምህራኑን መለወጥ የተለመደ አሠራር መኾኑን ተናግረዋል፡፡ መምህራኑ በቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር እንዳያስተምሩ መከልከላቸውንና መርሐ ግብሩን ላልተወሰነ ጊዜ የመዝጋት ርምጃ የገለጹት ‹‹ከእግዝአብሔር ማዕድ ለምን ትለዩናላችኹ!››በሚል እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የቀኑ መርሐ ግብሩ ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን የሚገልጸው የአስተዳደሩ ውሳኔ በደብዳቤ እንዲሰጣቸው የጠየቁት መምህራኑ‹‹የምንጠይቀውን አካል እንጠይቃለን፤›› በማለት መዛታቸውም ተነግሯል፡፡
የመርሐ ግብሩን መዘጋት ተከትሎ ሊቀ ጳጳሱ ለካፊቴሪያው ሓላፊ በቃል ባስተላለፉት ትእዛዝ ካፊቴሪያው ከትላንት በስቲያ ምሽት አንሥቶ ምግብ እንዳያዘጋጅ፣ ሠራተኞችም በምግብ ቤቱ ውስጥ እንዳይታዩ ተደርገዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከትላንት በስቲያ ምሽት ጀምሮ ራትና ምሳ በመከልከል በረኀብ እንዲቀጡ መደረጋቸውን በትላንቱ ስብሰባ መምህራኑ በጥብቅ ተቃውመዋል፡፡
ማስታወቂያው በወጣበት ዕለት ምሽት በግቢያቸው የተሰበሰቡት ደቀ መዛሙርት በበኩላቸው÷ ሁለቱ መምህራን እንዳያስተምሩ ከመከልከላቸው በቀር 90 ከመቶው የመማር ማስተማሩ ሂደት በቀጠለበት ኹኔታ በሊቀ ጳጳሱ የተወሰደው ርምጃ ተቀባይነት እንደሌለው ተወያይተዋል፡፡ በጎጠኝነትና በጥቅም ሊከፋፍሏቸው በሚሞክሩት ጥቂት የኮሌጁ ሓላፊዎች ተንኮል ሳይለያዩ ፣ በረኀብ ሳይፈቱ ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪሰጠው ድረስ በተቃውሟቸው ለመቀጠልም ተስማምተዋል፡፡ Continue reading 

የኮሌጁ የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን እንዲለቁ ታዘዙ

  • መንሥኤው ‹‹ትምህርት በአግባቡ አልጀመራችኹም›› የሚል ነው
  • ‹‹ማስታወቂያው ለብቀላና እስር ሰበብ መፈለጊያ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ከዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ የኮሌጁን ንብረት እያስረከቡ ኮሌጁን እንዲለቁ አሳሰበ፡፡ ኮሌጁ ማሳሰቢያውን በዛሬው ዕለት በቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርቱ ላይ ያወጣው ‹‹ያቋረጣችኹትን ትምህርት አግባብነት ባለው መንገድ አልጀመራችኹም›› በሚል ነው፡፡ Continue reading 

የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር አባላት የተሐድሶ ኑፋቄን እንዲዋጉ ፓትርያሪኩ አሳሰቡ

  • ማኅበሩ በሦስት አህጉረ ስብከት ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ከፍቷል
  • የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሥራ አስፈጻሚን በዳግም ምርጫ አጠናክሯል
  • መናፍቁ አሰግድ ሣህሉን ለማስመረጥ የተደረገው ሙከራ ተቀባይነት አላገኘም
  • ሁለት የፀረ – ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት አባላት በሥራ አስፈጻሚነት ተካተዋል
  • ማኅበሩ ሕጋዊ ዕውቅናና ተቀባይነት ካላቸው የቤተ ክርስቲያናችን አካላት ጋራ ሁሉ ተባብሮ ለመሥራት ያለውን ዝግጁነት ዳግም አረጋግጧል
Theology Association Logoበቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ምሩቃንን በአባልነት በመያዝ የተመሠረተ ነው፤ ዋና ዓላማው÷ የወንጌል ትምህርት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጠት፣ የቤተ ክርስቲያናችን ዶግማ፣ ሥርዐት፣ ትውፊት እና ንዋያተ ቅድሳት በአግባቡ እንዲጠበቁ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ ነው – የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር፡፡
ማኅበሩ ዓላማውን የሚተገብርባቸውየስብከተ ወንጌል፣ የትምህርት፣ የኅትመትና ሥርጭት፣ የሕግ፣ የልማት፣ የመረጃና መዛግብት፣ የሒሳብና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም የቁጥጥር ክፍሎችን አዋቅሯል፤ እኒህን ተግባራት የሚያስፈጽሙ 12 የሥራ አስፈጻሚና አፈጻጸሙን በበላይነት የሚመሩ 12 የሥራ አመራር አባላት እንዳሉትም ማኅበሩ ያሰራጫቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ሁለቱ የነገረ መለኰት ኮሌጆች በዘረጓቸው የቀን መደበኛና ተከታታይ የማታ ትምህርት መርሐ ግብሮች ከሠለጠኑትና በቁጥር ከ1700 በላይ ከሚኾኑት ምሩቃን የሚበዙትን በአባልነት ያቀፈው ማኅበሩ÷ ከአባላቱ በሚሰበስበው ወርኀዊ አስተዋፅኦና ከበጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳውያን በሚያገኘው ድጋፍ አገልግሎቱን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ማኅበሩ በቀድሞው ፓትርያሪክ መልካም ፈቃድና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ፊልጶስ ጥረት በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደ ዋና ጽ/ቤት የሚገለገልበት ቢሮ የተሰጠው ሲኾን በአዲስ አበባ፣ መቐለ እና ጅማ አህጉረ ስብከት ሦስት ቅርንጫፍ ቢሮዎችን መክፈቱ ተዘግቧል፡፡ Continue reading 

የኮሌጁን ችግርና የደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቋመ

  • በቀን መርሐ ግብር አስተባባሪው የተለጠፈው ማስታወቂያ ሕገ ወጥ ነው
  • ሁለቱ ሓላፊዎች ከማስተማር እንደተከለከሉ ናቸው
  • የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ‹‹ሁለቱ ሓላፊዎች እንዳይነኩብኝ›› እያሉ ነው
ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ሦስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ቀዳሚ በኾነው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተባብሶ በሚታየው ሙስናና የአሠራር ብልሹነት ሳቢያ ደቀ መዛሙርቱ ያነሧቸውን አካዳሚያዊና አስተዳደራዊ ችግሮች የተመለከቱ ጥያቄዎች የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡
ከመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ፊልጶስ ፊርማ የወጣውና ለመንፈሳዊ ኮሌጁ አስተዳደር የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው÷ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ አራት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች በአመራርነትና በአባልነት፣ ሁለት የኮሌጁ መምህራንና ሁለት የደቀ መዛሙርቱ ተወካዮች በአስረጅነት የሚገኙበት ነው፡፡ Continue reading 

የኮሌጁ አስተዳደር የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን አስታወቀ

  • ማስታወቂያው የተለጠፈው በመርሐ ግብሩ አስተባባሪ ዘላለም ረድኤት ነው
  • ደቀ መዛሙርቱ በተቃውሟቸው ለመቀጠል በመስማማት ትምህርት ጀምረዋል
  • ‹‹ሲያስወጡን እንተናነቃለን፤ ኮሌጁን ቅ/ሲኖዶስ እንጂ ዘላለም አይዘጋውም›› /ደቀ መዛሙርቱ
  • የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ‹‹[ለደቀ መዛሙርቱ] እንኳን ምሳ ራት አልሰጥም›› እያሉ ነው
ሙስናንና የአሠራር ብልሹነትን በመቃወም ከሁለት ሳምንት በላይ በተቃውሞ የሰነበቱት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት በትላንትናው ዕለት ረፋድና ከሰዓት በኋላ በክፍል በመገኘት ትምህርት ጀምረዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ትምህርት በማቋረጥና በካፊቴሪያው ከመመገብ በመከልከል በኮሌጁ እየከፋ የመጣው ሙስናና የአሠራር ብልሹነት እንዲስተካከል፣ ለዚህም ተጠያቂ ናቸው ያሏቸው ሁለት ሓላፊዎች ከቦታቸው እንዲነሡ ያቀረቡትን ጥያቄ እየተማሩም ለመቀጠል በመወሰን ነው ትምህርታቸውን ለመጀመር የተስማሙት፡፡
በቀጣይ በሚቋቋመው ኮሚቴ መሠረት በሁለቱ ሓላፊዎች ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች በሚገባ ተጠንተው ውሳኔ እንዲሰጥባቸው በፓትርያሪኩ የተሰጠውን መመሪያ መቀበላቸውን የተናገሩት ደቀ መዛሙርቱ÷ ሁለቱ ሓላፊዎች ማለትም የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪ መ/ር ዘላለም ረድኤት እና አካዳሚክ ምክትል ዲኑ መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ በክፍል ተገኝተው ማስተማራቸውን እንደሚቃወሙና ይህም ተቃውሞ ሓላፊዎቹ ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ድረስ እንደሚቀጥል በመስማማት ነው ትምህርታቸውን የጀመሩት፡፡
ደቀ መዛሙርቱ የደረሱበት ውሳኔና ወደ ትምህርት የተመለሱበት ኹኔታ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ ይበልጥ እንደሚያጠናክረው የሰጉት የቀን መርሐ ግብር አስተባባሪው መ/ር ዘላለም ረድኤት ግን ከመማር ማስተማሩ ጤናማነት ይልቅ በቀጣይ የደቀ መዛሙርቱ የተቃውሞ ስልት ግላዊ ጥቅማቸው አደጋ ውስጥ መግባቱን በማሰብ ውዝግቡን የሚያባብስ ርምጃ መውሰድን መምረጣቸው ተመልክቷል፡፡ በተካኑበት አሳባቂነትና ነገር ሠሪነት የኮሌጁን መምህራንና አስተዳደር እርስ በርስ በማተራመስ፣ ከሰሞኑ እንኳ ተቃውሞ ያነሡባቸውን ደቀ መዛሙርት ሳይቀር በጥቅም ለመከፋፈል እስከመሞከር የሚታወቁት አስተባባሪው÷ የኮሌጁን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ በማሳሳት በትላንትናው ዕለት ባወጡት ማስታወቂያ፣ በተቃውሞ የሰነበቱት የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት በዕለቱ እስከ ቀኑ 8፡00 ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡Continue reading 

አንድ የኮሌጁ ደቀ መዝሙር ከዐርብ ጀምሮ በእስር ላይ ነው

  •  ልኡኩ ከኮሌጁ አስተዳደር ወግኗል በሚል እየተተቸ ነው
  • አምስት ደቀ መዛሙርት በረኀብ አድማው ተጎድተዋል
  • የደቀ መዛሙርቱ ዕለታዊ ምግብ ዳቦና ሙዝ ኾኗል
በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተጀመረው የደቀ መዛሙርት ተቃውሞ እንደቀጠለ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት÷ አምስት ደቀ መዛሙርት በረኀብ አድማው መጎዳታቸውንና አንድ ደቀ መዝሙር ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት ትምህርት በማቋረጥ የተጀመረውና ዘግይቶ በረኀብ አድማ በተጠናከረው የቀኑ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት ተቃውሞ÷ ሦስት የሁለተኛ ዓመት (ዲ/ን ገብረ እግዚአብሔር፣ ዲ/ን በኀይሉ እና ዲ/ን ጥላሁን)፣ አንድ የአራተኛ ዓመት (ዲ/ን ኤልያስ)፣ አንድ የአምስተኛ ዓመት (አባ ኢያሱ ሰብስቤ) ደቀ መዛሙርት ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጧል፡፡ ከአምስቱ ደቀ መዛሙርት አራቱ የሕክምና ርዳታ አግኝተው ወደ ኮሌጁ የተመለሱ ሲኾን አምስተኛው ደግሞ በጣም በመጎዳታቸው ከሕክምና ርዳታው በኋላ ወደ ቤተሰብ መመለሳቸው ተዘግቧል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በቀን አንዴ የሚቀምሱት ከውጭ የሚገዙትን ዳቦና ሙዝ ሲኾን ከምግብ ተከልክለው በመቆየታቸው ሳቢያ ብዙዎች ከፍተኛ ድካም እንደሚታይባቸው ተገልጧል፡፡
በኮሌጁ ተባብሰው ለሚታዩት አካዳሚያዊና አስተዳደራዊ ችግሮች የኮሌጁን ሁለት ሓላፊዎች ቀዳሚ ተጠያቂ በማድረግ ከሥልጣን እንዲነሡ የሚጠይቁት ደቀ መዛሙርቱ÷ ዲ/ን ኀይለ ጽዮን መንግሥት የተባለ የአምስተኛ ዓመት ደቀ መዝሙር ካለፈው ሳምንት ዓርብ ተሲዓት ጀምሮ በፖሊስ ከተወሰደ በኋላ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፤ ወደ  አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 04 ፖሊስ ጣቢያ የተወሰደውና በሰሞኑ የተቃውሞ መድረኮች ርቱዕና ብርቱ ተናጋሪ ነበር የተባለው ዲ/ን ኀይለ ጽዮን፣ ከሌሎች ተለይቶ ለእስር የተዳረገው ‹‹ተማሪዎቹን ለተቃውሞ አነሣሥተሃል›› በሚል መኾኑን ደቀ መዛሙርቱ ገልጸው፣ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ ፍ/ቤት ቀርቦ በዋስ ይፈታል ብለው እንደሚጠብቁም ገልጸዋል፡፡ Continue reading