Wednesday, April 30, 2014

*ከ95% የማያንሰው vs 5% የማይሞላ***

ጋዜጠኝነት ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ለጋዜጠኝነት የማትመች አገር መስላለች፡፡ 
1 ብእርን የጨበጡ፣ በሀሳባቸው ብልጫ ውድድሩን ለማሸነፍ የጣሩ፣ ሀሳባቸውን በጽሁፍ ሆነ በንግገር መግለጣቸው እንደነውር ተቆጥሮ ዶክመንተሪ የሚሰራባት፡፡ ሰብዓዊ መብት፣ፍትህ፣እኩልነት እነደማዕድን ተቆፍሮ እንኳን የማይገኝባት ሀገር ሆናለች ኢትዮጵያ፡፡ 
2 ዲሞክራሲ እንደ ሰማይ የራቃት፣ ችጋር ስጋዋን አልፎ አጥንቷን መብላት የጀመረባት፤ ለለውጥ የተነሱ አብረን ተባብረን ወደ ፊት እንራመድ ያሉ እንደ አረም እየተመነጠሩ የሚታሰሩባት ሀገረ መከራ ሆናለች ኢትዮጵያ፡፡
3 አንድነቷ ተጎንጉኖ የዘር እራቁትነት የለበሰች፣ ነገ እርስ በእርስ እንዳንበላላ የምታሰጋ፣ ጎጠኝነት እራቁቷን ያስቀራት፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ትምክህተኛ ሆኖ የሚፈረጅባት የመከራን ቁልቁል የምትጋልብ ሀገር ሆናለች ኢትዮጵያ፡፡
4 ብሄራዊ መግባባት የጠፋባት፣ ሌላውን ላለማስገባት ሁሉም በሩን የዘጋበት፣ የሀገር ትርጉም የጠፋባት፤ ስለ ሀገር ሲጠየቅ ‹‹ምን አገባኝ›› የሚልን ተረት ተናጋሪ የበዛባት ሀገር ሆናለች ኢትዮጵያ፡፡
5 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከራሳቸው ጋር መታረቅ አቅቶቸው አብሮቸው እየሮጠ ያለውን ጠልፈው የሚጥሉባት፣ ተገረፍን ታሰርን እያሉ በሰበብ አስባቡ አገር የሚለቁባት፡፡ ከዚህም የተነሳ ለውጥ ፈላጊው ህዝብ የተቃውሚ ፓርቲዎችን ጭመር በጥርጣሬ የሚያይባት፡፡ ለተቃዋሚም ለመሪም ያልታደለች፣ የመንግስት ለውጥ እንጂ እውነተኛ ለውጥ ያልሰመረላት አገር ኢትዮጵያ፡፡
…..ዛሬም ልጆቿ ይታሰራሉ፣ያለከልካይ ከቦታቸው ይፈናቀላሉ፣ ይደበደባሉ አካላቸው ይጎላል፡፡ሙስና የመጨባበጥ ያህል የቀለለባት፣ከደሀ 10 ካ.ሜ ተነጥቆ ለባለ ገንዘብ 10,000 ካ.ሜ የሚሰጥባት፡፡
ዜግነት በገንዘብ እና በአሸርጋጅነት (በተለጣፊነት) የሚከበርባት ሆናለች ሀገሬ ኢትዮጵያ፡፡

ታዲያ ይሄን ኧረ ማን ይናገርላት????????

ከ95% የማያንሰው የሀገራችን ህዝብ እንኳን ሶሻል ሚዲያ ሊጠቀም ይቅርና ሶሻል ሚዲያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንኳን ለማወቅ ያልታደለ ነው፡፡ ታዲያ 5% የማይሞላ የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚ ባለባት ሀገር ውስጥ እንዴት ነው ሀገር በሶሻል ሚዲያ የምትተራመሰው? የምር ያስቃል፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment