Thursday, May 30, 2013

የግንቦት 7 ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበ

የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ከግንቦት 11 – 19/2005 አ/ም በበርካታ ወቅታዊ፣ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና የድርጅቱን አዲስ ም/ቤት በመምረጥ ወያኔን በማስወገድ ረገድ ሊከተል የሚገባውን ጠቋሚ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን ከተሳታፊው በመውሰድ ወሳኝ የሆነ ውይይት አድርጓል።
ንቅናቄው ከተለያዩ አለማት በአባላት የተወከሉ ጉባኤተኞች እና በተለያዩ የስራ ክፍል የሚገኙትን የድርጅቱን አባላት ያሳተፈ፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉትም ጉባኤዎች እጅግ የላቀ አባላት የተገኙበት ነበር።
ጉባኤው የነበረውን የም/ቤት ሪፖርት፣ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ማናጅመንት ኮሚሽን፣ የግልግልና ዳኝነት ኮሚቴን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዳመጥ ጥልቅ የሆነ ወይይቶች አደርጓል።
የግንቦት 7 ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤ ደርጅቱ የጀመረውን ወያኔን የማስወገድ ትግል በየትኛውም አቅጣጫ አስፈላጊ ሆኖ የታመነበትን ማናቸውም መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘረኝነትን ስርአት ድባቅ መምታት፤ አልፎም ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አስቸኳይና ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ግዴታው አድርጎ መውሰድ ያለበት አጣዳፊ ስራ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አየርና የዲሞክራሲ ጮራ ሁሌም የሚፈነጥቅባት፣ ህዝብ ካለፍርሃትና ሰቀቀን ወጥቶ የሚገባባት፣ ህዝብ በነጻነት የፈለገውን ፓርቲ የሚመርጥበት፣ የሚያወርድበት፣ ስልጣን የህዝብ መሆኑን የሚረጋገጥበት፣ የመንግስት አካላት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ነጻ ሚዲያ ለመልካም አስተዳደር ግንባታ የሚያገለግልበት፣ ፍትህ ለሁሉም በእኩል የሚሰጥበት፣ ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ ቤተሰብ የመመስረት፤ ከቦታ ወደ ቦታ ያለምንም ገደብ የሚንቀሳቀሱበት መብት እንዲኖራቸው፣ እና የሃይማኖት ነጻነት ይኖረን ዘንድ የድርጅቱ ጉባኤተኞች ሙሉ መሰዋእት ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ሲሉ በድጋሚ ቃል በመግባት መራራ የሆነውን ትግል እጅ ለእጅ ተያይዞ ተራራውን ለመውጣት እና ለማቋረጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
ከ4ኛ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ጉባኤተኛው የግንቦት 7ን 5ኛ አመት ምስረታ ታሪካዊ ቀን አስቦ ውሏል። በዚህ በግንቦት 7, 1997 ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተሳትፎ ፍትህ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ በሀገሪቱ ይሰፍን ዘንድ ለዘመናት ተጭኖት የነበረውን ጫና ተቋቁሞ የወያኔን ስርአት በድምጹ የጣለበት ልዩ ቀን ነበር። ግንቦት 7, ሁሌም በታሪክ የሚዘከር ልዩ እለት ነው።
ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያዊ ትውልድ በግንቦት 7 ያሳየውን ልበሙሉነት፣ ጀግንነት፣ መሰዋእትነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት ለዘለአለም ሲታወስ ይኖራል። ይህንኑ በ97 የተጀመረው የትግል ፍሬ፤ ውጤት ያፈራ ዘንድ አስፈላጊ ያላቸውን ትግሎችን እያደረገ እንደሆነ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 5ኛ አመቱን ከአባላቱ ጋር ሆኖ ሲዘክር ተወያይቷል። ይህም ታሪካዊ የህዝብ ድል ቀን፤ በጠመንጃ ሃይል የነጠቀውን ወያኔን ለማስወገድ እና የህዝብን ድምጽ ለማስመለስ ድርጅታችን ማናቸውንም መንገድ በመጠቀም የሚያደርገውን የትግል ጅማሮ ግብ ለመምታት አሁን ከአለንበት በተሻለ በመጠናከር መሆኑንም ስምምነት ተደርሷል። ድርጅታችን ካለፈው ጉባኤ ጀምሮ ድርጅቱ ያደረገውን እንቅስቃሴ በስፋት ገምግሞ፤ በስራ ሂደት የታዩ ድክመቶችን አፍረጥርጦ ተወያይቶ፤ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ የሚጎለብቱበትን ሁኔታ ተመልክቶ፤ በድርጅቱ የእስትራቴጂ አካሄድ ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን አድርጎ፤ እነኝህን የእስትራቴጂ አቅጣጫዎች በተቀላጠፈ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ወሳኝ የመዋቅር ለውጦችን አጽድቆና ይህን አዲስ መዋቅር የሚያስፈጽሙ ያመራር አባላትን መርጦ፤ በከፍተኛ የጓዳዊ መንፈስና ልዩ በሆነ የትግል ወኔ ጉባኤውን በድል አጠናቋል::
በመሆኑም ግንቦት 7፣ በግንቦት 7 የገባውን ቃል ኪዳን ዛሬም ህያው መሆኑን ሲያረጋግጥና ትግሉ ከመቼውም በበለጠ ጽናትና ቁርጠኛነት እንደሚገፋበት ቃል ሲገባ፣ የሀገራችን ህዝብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ; አዛውንት፣ ወጣት፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ ዘር ቀለም ሳይለያችሁ በግንቦት 7/ 1997 የተሰረቀውን፣ የተነጠቅነውን የህዝብ መንበረ-ድምጽ ስልጣን ወደ ትክክለኛ ባለቤቱ እንዲመለስ የምናደረግውን የትግል ጉዞ ትቀላቀሉ ዘንድ ጥሪያችን ይድረሳችሁ!
የሀገራችን ወጣቶች ሆይ፡ ለነጻነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ቱርፋቶች መሰዋእት ሆናችሁ መሰዋእትነታችሁ በጥቁር ህዝብ የኢትዮጵያ ታሪክ ገድል ውስጥ ለዘላለም ተከትቦ ይቀመጥ ዘንድ ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታ አለባችሁ፡፡ ግንቦት 7 ትግሉን ጀምሯል። ኑ ተቀላቀሉ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Wednesday, May 29, 2013

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና ቀጥሏል አለ

24 בMay 2013 0 Comments
ኢሳት ዜና:-ለሰብአዊ መብቶች መከበር በመሟገት አለማቀፍ እውቅና ያለው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገው የዚህ አመት ሪፖርት መንግስት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን፣ የነጻውን amnestyintl_logo__2ሚዲያ ፣ የፖለቲካ ድርጅቶችንና የሲቪክ ማህበራት እንቅስቃሴዎችን መግታቱን ገልጿል።
“ሰላማዊ ተቃውሞ ማድረግ ተከልክሏል፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰዎችን ማሰር ፣ ማሰቃየት እና በእስር ቤቶች ውስጥ ሰቆቃዎችን መፈጸም ቀጥሏል” ያለው አምነስቲ “ዜጎችን በሀይል ከመኖሪያ ቀያቸው የማፈናቀሉ  እንቅስቃሴም” መጨመሩን አመልክቷል።
በርካታ ጋዜጠኞች መንግስትን በመተቸታቸው፣ የፖሊሲ ማሻሻል እና ለውጥ እንዲደረግ በመጠየቃቸው በሽብርተኝነት ተከሰው የብዙ አመታት እስር ተፈርዶባቸዋል ። በመንግስት በኩል ለፍርድ ቤት የሚቀርቡት ማስረጃዎች ሲታዩ ተካሳሾች ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመሰብሰብ መብታቸውን ተጠቅመው ያደረጉት እንጅ በሽብርተኝነት የሚያስከስሳቸው አለመሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
ድርጅቱ በፍትህ ጋዜጣ ፣ በሙስሊም የድምጻችን ይሰማ መሪዎች እና ደጋፊዎች ፣ እንዲሁም በተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ መንግስት እየወሰደ ያለውን ህገወጥ እርምጃም ተንትኖአል።
በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች በዱላ፣ በቦክስ፣ በጥፊ እንደሚመቱ፣ እጃቸው  ከግድግዳ ጋር ወይም ከጣራ ላይ
ታስሮ እንደሚደበደቡ፣ እንቅልፍ እንዳያገኙ፣ ለብቻቸው እንዲታሰሩ፣ በኤልክትሪክ እንዲጠበሱ፣ ውሀ ውስጥ እንዲዘፈቁ፣ በብልታቸው ላይ ከባድ እቃ እንደሚንጠለጠልባቸው፣ ተገደው የራሳቸው ያልሆነውን ቃል የራሳቸው እንደሆነ አድርገው እንዲፈርሙ እንዲሁም አንዱ እስረኛ ሌላውን እንዲደበድብ እንደሚደርግ አምነስቲ በሪፖርቱ ጠቅሷል።
የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰዎችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ እንደሚገድሉ፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሊ እና በሌሎችም ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን በዋቢነት አንስቷል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በደቡብ አካባቢዎችም ዜጎች በሰፋራ ስም እንደሚፈናቀሉ አምነስቲ በሪፖርቱ ማጠቃለያ ላይ ጠቅሷል።
በጉዳዩ ዙሪያ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ሉሲ ፍሪማን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ መብቶችን መጣስ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የዘንድሮውም ሪፖርት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ችግሮች እየተባባሱ መሄዳቸውን የሚያመለክት እንጅ መሻሻል እንዳልታየበት ሚስ ፍሪማን ገልጸዋል
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ሰብአዊ መብት በአፍሪካ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደረጃ እያቀረበ እንደሚገኝ ሚስ ፍሪማን ገልጸዋል

Tuesday, May 28, 2013

ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው

ዛሬ ግንቦት 20 ነው።ግንቦት 20 የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዘውር የተዘወረበት ለመሆኑ አሌ አይባልም። ዕለቱ እንደ አቶ ሃይለማርያም የመጀመርያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ እንዳደረጉት ንግግር ” ኢትዮጵያ ልትበታተን ስትል የዳነችበት ቀን” ነው ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው።ይህንን ሁለተኛውን ሃሳብ እኔም እጋራዋለሁ። ካለፈው ይልቅ መጪው ይቀርበናል።ያለፈውማ አለፈ።መጪው ግን ቢዘገይም ቢፈጥንም አይቀርም።እና ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ ለመጪዋ ኢትዮጵያ እንዴት አስጊ ያደርገዋል። ይህንን ለማብራራት ግንቦት 20 እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ ይዞት የመጣውን በጥቂቱም መጥቀስ ይፈልጋል።ስለተሰራው የመንገድ እርዝመት፣ህንፃ፣ወዘተ ማተት ይቻላል።እርግጥ ነው መንገድ ተስርቷል።ህንፃ ተገንብቷል።ከተሞች ሰፍተዋል።ይህ ሁሉ  ግን መጪውን አስፈሪ ጊዜ ለሀገር ከመተው አልገታውም።
መጪውን አስፈሪ የሚያደርገው የግንቦት 20 ውጤቶች ምን ምን ናቸው?
እንድሜ ለግንቦት 20 ብዬ ብጀምርስ-
• እድሜ ለግንቦት 20 ዛሬ ኢትዮጵያ በአለም ታይቶ በማይታወቅ መልክ በቁጥር ተከልላ ክልሎች ስለ ድንበሮቻቸው ሲደራደሩ አንዳንዴም ሲጋጩ ለማየት በቅተናል። ምሳሌ የአፋር እና ትግራይ፣ የሱማሌ እና ኦሮሞ፣ የአማራ እና አፋር ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።
• እድሜ ለግንቦት 20 አንድሰው ከአንዱ የሃገሪቱ ክልል ተነስቶ እንበል ደቡብ ወይንም ጅጅጋ  ገብቶ መሬት ገዝቶ ልረስ ወይንም ልነግድ  ቢል እርሱ ከመምጣቱ በፊት ከ 60 እና 70 አመት በፊት የሰፈሩቱ ከጉርዳፈርዳ፣ጋምቤላ፣ጅጅጋ እና አሶሳ ካለምንም ካሳ ሲባረሩ ያያል እና መጪው እያስፈራው አይሞክረውም።
• እድሜ ለግንቦት 20 ወላጆች ልጆቻቸውን በፈለጉት ቋንቋ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ በታሪካዊ አጋጣሚ የሚኖሩበት ክልል ቋንቋ ውጭ እንዳይስተምሩ ታግደዋል።ለምሳሌ ኦሮምኛ ተናጋሪ ልጁ በአማርኛ እንዲማር ቢፈልግ ግን በኦሮምያ ክልል ቢኖር አማርኛ ወደምነገርበት ክልል መሄድ ብቸኛ አማራጩ ነው።በምዕራቡ አለም የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ግን ልጁን በሀገሩ ቋንቋ እንዲያስተምር ባህሉን እንዲጠብቅ ድጋፍ ይደረግለታል።
• እድሜ ለግንቦት 20 ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሆና የባህር ኃይሏን በትና  30 እና 40 ኪሎሜትር እርቀት የባህሩ ማዕበል ሲማታ እየተሰማ ከ85ሚልዮን በላይ ሕዝብ ወደብ አጥቶ የጅቡቲን እና የሱዳንን ወደቦች በከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበታል፣
• እድሜ ለግንቦት 20  ጦርነት ቆመ በተባለበት ጊዜ በአዲስ አበባ ብቻ ከ 100ሺህ በላይ ”ጎዳና ቤቴ” ያሉ ሕፃናት መንገድ ላይ ፈሰው ኃላፊነት የሚወስድ መንግስት አጥተው ለማየት የበቃነው በግንቦት 20 ፍሬ ነው። (በቀድሞው መንግስት የተመሰረተው የሕፃናት አንባ እንዴት በአሁኑ መንግስት እንደፈረሰ ይህንን ሊንክ ከፍተው ቪድዮውን ይመልከቱ (http://gudayachn.blogspot.no/2013/05/main-play-list-on-home-page-playlist.html)፣
• እድሜ ለግንቦት 20 ከሃያ ሁለት አመት በፊት ”የጫት ቤት” ብሎ በር ላይ መለጠፍ የምያሳፍርባት አዲስ አበባ ዛሬ ጫት በየዘርፉ ”የበለጩ ፣የባህርዳር፣ የወልሶ ጫት ቤት” ብቻ ተብሎ ሳይሆን የሚለጠፈው ”ጫት እናስቅማለን፣ እንፈርሻለን” ተብሎ የተፃፈባቸው ባብዛኛው ትምህርት ቤቶች የሚገኙበትን ቦታ ፈልገው የሚከፈቱ የጫት ቤቶች በዝተው ለመታየት በቅተዋል። ምን ይህ ብቻ ዩንቨርስቲዎቻችን በየዶርሙ ጫት ሸጉጠው ሲገቡ- ሲ ቃምባቸው ደጉ መንግስታችን በዝምታ አልፎ ትውልዱን ጫት ቃሚ አድርጎታል።
• አድሜ ለ ግንቦት 20 ምሳ ሰዓት ላይ ከቢሮ ወጥተው ጫት ቅመው የሚመለሱ የባንክ ሰራተኞች፣መሀንዲሶች ወዘተ አፍርቷል ግንቦት 20።ከደንበል ህንፃ ጀርባ የሚገኙ የመቃምያ ቦታዎችን ብንመለከት በምሳ ሰዓት ደንበል ህንፃ የሚሰሩ ምሁራን ዩንቨርስቲ ሳሉ በተፈቀደላቸው የመቃም መሰረት ሥራ ከያዙ በኃላም ለመላቀቅ ትቸግረው ይታያል።እረ  እንዲያውም በሥራ ሰዓት ሾለክ ብለው የሚቅሙ ሰራተኞች መኖራቸውን የእዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ እማኝ ነው። እድሜ ለግንቦት 20።
• እድሜ ለግንቦት 20 ወላጅ አልባ ሕፃናት ጎዳና እንዳይወጡ በሕዝቡ የሚደገፍ እንደ ሕፃናት አምባ መስርቶ ከማሳደግ ይልቅ ለአንድ ሕፃን እስከ 25000 ዶላር መንግስት እየተቀበለ በጉዲፈቻ ስም ለአሜሪካ እና አውሮፓ የተቸበቸቡት እና ብዙዎች በህሊና ስቃይ እና የማንንነት ጥያቄ እንዲሰቃዩ የተደረጉት በግንቦት 20 ፍሬ ነው (ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)
• እድሜ ለግንቦት 20 ሴት እህቶቻችን ተስፋ ቆርጠው ለአረብ ሀገር ባርነት  በአስርሺዎች የተጋዙት በሄዱበት ሀገርም ስበልደሉ የሚሰማቸው አጥተው አሳር ፍዳቸውን የሚያዩት ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው።
• እድሜ ለግንቦት 20 ”የኤርትራ ጥያቄን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት የሚቻለው የ ሻብያን ሃሳብ በመቀበል ነው” ብለው ስያግባቡን የነበሩት  አቶ መለስ- ጦርነቱ አበቃ ከተባለ ከ ሰባት አመታት በኋላ ለዳግም እልቂት ”ድንበር” በሚል ሰበብ ዳግም የኢኮኖሚ ፀባቸውን ወደ ወታደራዊ ግጭት ቀይረው በአስር ሺዎች የረገፉት በ ግንቦት ሃያ ውጤት ነው፣
• እድሜ ለግንቦት 20 ስደት ቀድሞ የነበረ ቢሆንም በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ በባህር፣በእግር ወዘተ ወጣቱ ከሀገር የሚወጣው ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው (ወደየመን በጀልባ ተሳፍረው ከገቡት ስደተኞች ከ 70%በላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን በዘንድሮው ዘገባው መጥቀሱን ልብ በሉ) ፣
• እድሜ ለግንቦት 20 ወጣቶች ተምረው በእውቀታቸው ሀገርንም መጥቀም ሲገባቸው፣የስራ ዕድል የሚያገኙበት ወይንም  ስነልቦናቸውን የሚጠብቅ ግን ለፈጠራ የሚያዘጋጅ የስራ መስክ ከመፍጠር ይልቅ በምረቃቸው ጊዜ (የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  2004ዓም ምረቃ ላይ አቶ ጁነዲን ለተማሪዎቹ እንደተናገሩት)ከዩንቨርስቲ ሲወጡ  የኮብል ስቶን ሥራን መስራት እንደሚገባ የተነገራቸው በግንቦት 20 ውጤት ነው።
• እድሜ ለግንቦት 20 በሚድያውስ ቢሆን (ጎረቤት ኬንያን ለማነፃፀርያ እንጠቀም) ኬንያ የህዝብ ብዛቷ 30 ሚልዮን ሲሆን እኛ 85 ሚልዮን መሆኑን እናስታውስ እና ኬንያ በይዘታቸውም ሆነ በአቀራረባቸው የመንግስት እጅ ያልተጫናቸው 8 የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ 38 ራድዮ ጣብያዎች፣ ከእሩብ ሚልዮን በላይ አንባቢ ያላቸው በየቀኑ የሚታተሙ 4 ጋዜጦች (http://www.pressreference.com/Gu-Ku/Kenya.html#b) ሲኖሩ ሃሳብን የመግለፅ መብት እና በሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ የመወያየት ነፃነት ከእኛ ጋር ሊወዳደር የማይችል መሆኑን ስናስብ እና ጋዜጠኞች መንግስትን ወቀሱ ተብለው በአሸባሪነት ዘብጥያ መውረዳቸውን ስናስብ እድሜ ለግንቦት 20 እንላለን።
• እድሜ ለ ግንቦት 20 ጋና ነፃነቷን ስታገኝ የገነባነው ስታድዮም ዛሬ ጋና ከነፃነት አልፋ እስከ መቶ ሺሕዝብ የሚይዝ ስታድዮም ስትገነባ እኛ አሁንም አንድ ለእናቱ በሆነ ስታድዮም መገኘታችን የግንቦት 20 ውጤት ነው።እርግጥ ነው በዛሬው የግንቦት 20 በዓል የስፖርት አካዳሚ ምረቃ በአል እየተከበረ ነው። ስታድዮምስ ?
• እድሜ ለግንቦት 20 ቀድሞ ጉቦ የሚለው ቃል ሲነሳ ስለ 20 እና 30 ብር ጉቦ እናስብ ነበር። ዛሬ ጉቦ፣ሙስና እና ዝርፍያ ማለት አድገው ተመንድገው  ዝርፍያ ማለት የብሔራዊ ባንክን የወርቅ ክምችት በወርቅ መሰል ነገር መቀየር ሲሆን ጉቦ ማለት ደግሞ የሀገር መሬት እና ውሃን  ለሕንድ እና ለአረብ በርካሽ መቸብቸብ ፣ በባለስልጣናት ቤት እንደባንክ ቤት በኢይሮ ብሉ በዶላር ቢሉ በፈለጉት የገንዘብ አይነት ከቤት ማስቀመጥ ማለት ነው (በቅርቡ የግምሩክ ባለስልጣናት ቤት  ተገኘ የተባለውን ብር ያስታውሱ)።
ይህንን ሁሉ ስናስብ ነው እንግዲህ ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚያስፈራ የሚያደርግብኝ።ከሁሉ የከፋው ግን መንግስት ስለሰራሁት መንገድ እና ድልድይ ስታመሰግኑኝ መስማት ብቻ ነው የምፈልገው ከማለቱም በላይ መሰረታዊ ስህተቶችን ”የጨለምተኞች አመለካከት’፣ የአመለካከት ችግር” እያለ ማጣጣሉን መቀጠሉ ነው አሳዛኙ።
አበቃሁ
ጌታቸው, ኦስሎ

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!”

በአቤ ቶክቻው
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…
“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ
ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡Abe Tokichaw (Abebe Tolla) the Popular Ethiopian Political Satirist
አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡
መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡
ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴት ነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!
አስታውሳለሁ፤ “አባይ ይገደብ በቃ” ብለው ጠቅላዩ የወሰኑት ከሁለት አመት በፊት “በቃ” በሚል ሀይለ ቃል …ኢህአዴግ ይበቃዋል ግንቦት ሃያን ዘንድሮ ለመጨረሻ ጊዜ እናከብራለን ከዛም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተን በዛው እንቀራለን፡፡ ኢህአዴግ እስካልወረደ ድረስም እቤታችን አንገባም…. የሚል እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ በኩል ተጀምሮ የነበረ ጊዜ ነው፡፡
በዚህ በ”በቃ” ጦስ እነ ርዮት አለሙ እነ ውብሸት ታዬ እነ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር እነ ሂሩት ክፍሌ ወድያው ለእስር ሲዳረጉ ቀስ በቀስ ደግሞ ሌሎችም ለቃሊቲ እና ለቂሊጦ ተዳርገዋል፡፡ (በተለይ የነዚህ ወዳጆቼን ፍርድ ሂደት ስከታተል ነበር እና አጋነንክ ቢሉኝም ባይሉኝም የአቃቤ ህግ ማስረጃ “በቃ የሚለውን የፌስ ቡክ እና የአደባባይ እንቅስቃሴ ትኩር ብላችሁ አይታችኋል” የሚል ነበር)
እንቅስቃሴው በፌስ ቡክ ተጀምሮ በየአደባባዩም “በቃ” የሚል ሃይለቃል በመፃፍ ተሟሙቆ የቀጠለ ነበር፡፡ በርካቶችም ግንቦት ሃያ መስቀል አደባባይ የሚፈጠረውን ተዓምር እያሰቡ አንድም ደስታ አንድም ፍርሃት ሲፈራረቅባቸው አንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡
ይሄኔ አቶ መለስ ፈርሸው ዘየዱ፤ (ሁል ጊዜ ቁጭ ብለው አሰቡ… እያልንኮ ፍራሽ የሌላቸው አስመሰልናቸው… “ፈርቸው” ማለት ፍራሽ ዘርግተው እጅግ በተመስጦ ማሰብ ማለት ነው…) አስበው አስበውም፤ “ለምን አባይን አንገድበውም…” አሉ እርሳቸው ብለው እምቢ… እንዴት… ለምን… በምን… አይባልምና እሺ እሺ ተብሎ ተጀመረ፡፡ የዛን ጊዜውን ግንቦት ሃያም መንግስታችን ለአባይ ግድብ ድጋፍ ሰልፍ ውጡልኝ፡፡ አለ… በዛውም የህዝቡ የተቃውሞ ሃሳብ ተገደበ፡፡
የአቶ መለስን ብልጠት በመኮረጅ ፈተናዎች ይታለፋሉ ብለው የሚያምኑት አቶ በረከት ደግሞ ዛሬ እነሆ በግንቦት ሃያው አባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ እነደሚሰራ በቴሌቪዥናቸው ብቅ ብለው ነገሩን፡፡
ጥሩ ኮርጀዋል…! አኮራረጃቸው ስም ሁሉ ሳይቀር እንደሚቀዳ አይነት ኮራጅ ነው፡፡
ህዝቡ ይህንን ዜና ሲሰማ ምን አላቸው… የሚለውን ቤት ለቤት ሄደን መጠየቅ ብንችል ጥሩ ነበር፡፡ መጠየቅ ባንችል ግን መጠርጠር እንችላለን እና አንዲህ እንጠረጥራለን፤
“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” ሳይላቸው አይቀርም፡፡

One Response to “አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!”

Monday, May 27, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ፣ ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!

ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!
ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶች፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙና የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ለመንግስት አካላት በተለያዩ ጊዚያት ጥሪ ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ጥሪውን ከፍ ባለ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማሰማት በወሰነው መሰረት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ በመልበስ እንዲሁም ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞውን ለመግለጽ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡Addis Ababa, Ethiopia a call for demonstration
በዚሁም መሰረት ዜጎች በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስ መንግስት በሚፈፅማቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አባላቶቻችን ላይ ወከባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጋፋት የተፈፀሙ ድርጊቶችን እንቃወማለን፤ የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ግንቦት 17 ቀን ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊደረግ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ለሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ ሰልፉ የሚደረግ መሆኑን የማሳወቂያ ደብዳቤ ፓርቲው ቢያደርስም የቢሮው ኃላፊና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤአችንን አንቀበልም ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነቱን ሕገ ወጥ አሰራር በማውገዝ ሰልፉን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በመግለጫ ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡ በመጨረሻም የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ በአዋጁ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀንና ቦታ እንዲለወጥ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ሁለታችንም አካላት ባደረግነው ድርድር ሰልፉ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲሆንና የሰልፉ መነሻ ቦታ የፓርቲው ፅ/ቤት መድረሻ ቦታ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ወይም ጥቁር አንበሳ ዋናው ፖስታ ቤት ፊለፊት እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚሁም መሰረት፡-
1ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተጠቀሱት ጥያቄዎች እንደተጠበቁ መሆናቸውንና የግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም ዋና ዋና ጥያቄዎች መሆናቸውን፣
2ኛ. ለረጅም ጊዜ ያለ ህግ ተነፍገን የቆየነውን ሃሳባችንን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብት በትግላችን ያረጋገጥን በመሆኑ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍበትና በሰልፉ ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ማሳሰብ ይቻል ዘንድ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን እንድንወጣና ለሰልፉ መሳካት በምንችለው አቅም ሁሉ አስተዋፅኦ እንድናደርግ ጥሪ የምናቀርብ መሆኑ፣
3ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ሰላማዊ ታቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና ዜጎች ላደረጋችሁልን ድጋፍ ፓርቲው ምስጋናውን ማቅረብ የሚፈልግ መሆኑንና የፓርቲያችንን ጥሪ ለህዝቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲዳረስ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች ያደረጉት አስተዋፅዖ እጅግ የሚያስደንቅና የሚያስመሰግን መሆኑን ፣
እየገለፅን አሁንም ፓርቲው ያነሳቸው ጥያቄዎች መመለስ አላባቸው ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበርና ዜጎች በሰልፉ እንዲሳተፉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Photo: ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!
ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶች፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙና የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ለመንግስት አካላት በተለያዩ ጊዚያት ጥሪ ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ጥሪውን ከፍ ባለ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማሰማት በወሰነው መሰረት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ በመልበስ እንዲሁም ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞውን ለመግለጽ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚሁም መሰረት ዜጎች በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስ መንግስት በሚፈፅማቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አባላቶቻችን ላይ ወከባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጋፋት የተፈፀሙ ድርጊቶችን እንቃወማለን፤ የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ግንቦት 17 ቀን ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊደረግ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ለሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ ሰልፉ የሚደረግ መሆኑን የማሳወቂያ ደብዳቤ ፓርቲው ቢያደርስም የቢሮው ኃላፊና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤአችንን አንቀበልም ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነቱን ሕገ ወጥ አሰራር በማውገዝ ሰልፉን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በመግለጫ ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡ በመጨረሻም የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ በአዋጁ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀንና ቦታ እንዲለወጥ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ሁለታችንም አካላት ባደረግነው ድርድር ሰልፉ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲሆንና የሰልፉ መነሻ ቦታ የፓርቲው ፅ/ቤት መድረሻ ቦታ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ወይም ጥቁር አንበሳ ዋናው ፖስታ ቤት ፊለፊት እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በዚሁም መሰረት፡-
1ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተጠቀሱት ጥያቄዎች እንደተጠበቁ መሆናቸውንና የግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም ዋና ዋና ጥያቄዎች መሆናቸውን፣
2ኛ. ለረጅም ጊዜ ያለ ህግ ተነፍገን የቆየነውን ሃሳባችንን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብት በትግላችን ያረጋገጥን በመሆኑ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍበትና በሰልፉ ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ማሳሰብ ይቻል ዘንድ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን እንድንወጣና ለሰልፉ መሳካት በምንችለው አቅም ሁሉ አስተዋፅኦ እንድናደርግ ጥሪ የምናቀርብ መሆኑ፣
3ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ሰላማዊ ታቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና ዜጎች ላደረጋችሁልን ድጋፍ ፓርቲው ምስጋናውን ማቅረብ የሚፈልግ መሆኑንና የፓርቲያችንን ጥሪ ለህዝቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲዳረስ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች ያደረጉት አስተዋፅዖ እጅግ የሚያስደንቅና የሚያስመሰግን መሆኑን ፣
እየገለፅን አሁንም ፓርቲው ያነሳቸው ጥያቄዎች መመለስ አላባቸው ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበርና ዜጎች በሰልፉ እንዲሳተፉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ጥንቃቄ! እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ!

አርያ ጌታቸው
ሰማየዊ ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የሆነ ትኩረትን ሽፋንን በተለያዩ ሚዲያዎች አግኝቱዋል ፡፡ እነዚህን ሽፋኖች ያገኘበትን ምክንያትን ግን አንዳንድ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች “ድርጅቱ የአፍሪካ ህብረትን ስብሰባ ተጥቅሞ በጠራው ሰልፍና እንደማይፈቀድላቸው እያወቁ ለሚዲያ ፍጆታ በማዋላቸው ነው” የሚል እንድምታ በመያዝ የሰልፉን ቀን መራዘምና መተላለፍ እንደ ፖለቲካ ክስረት ቆጥረውታል፡፡ ይህንን ለማስረዳት ፓርቲው ባለፉት አራት ወራት ያደረጋቸውን ጉልህ እንቅስቃሴዎች እና የሚዲያውን ትኩረት ያገኘባቸው ኩነቶች በወፍ በረር ለማየት እንሞክር፡፡Addis Ababa, Ethiopia a call for demonstration
1. የካቲት 3 ቀን 2005 ዓም. በብሔራዊ ትያትር ቤት “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” በሚለው የ ፕ/ር መስፍን መጽሃፍ ዙሪያ ሀገሪቷ ውስጥ ያሉ እውቅ ምሁራንን ጋብዞ ያወያየው (አዳራሹ ሞልቶ ሰዎች መመለሳቸውን እንዳትዘነጉ) ከረጅም ጊዜ በሁዋላ እንዲህ አይነት ትልቅ ህዝባዊ ውይይት ሲደረግ የመጀመሪያው ነው፡፡
2. መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ፡፡ በጊዜው አባላቱና ደጋፊዎቹ ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት አመራሮቹ ቀድመው ቦታው ላይ በመገኘት የሰልፉን ሂደት ለማሰማመር ደፋ ቀና ሲሉ 6 የሰማያዊ ስራ አስፈጻሚ አባላት(ሊቀመንበሩን ጨምሮ) እና ታዋቂ ግለሰቦችን የፓርቲው አባላትን ጨምሮ 34 ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸው ከ 24 ሰዓት በኋላም ፈቷቸዋል፡፡ ይህ ሰላማዊ ሰልፍም አንድነት ፓርቲ ወ/ሪት ብርቱካን ታስራ በነበረበት ወቅት ከተደረገው ሰልፍ በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)
3. ፓርቲው በዋቢ ሸበሌ ሊያደርገው የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ እና የኢህአዴግን ውንብድናን ያጋለጠበት ቪዲዮና የሶሻል ሚዲያዎች ሽፋን፡፡
4. በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው የተመለሱ ዜጎችን ሁኔታ ለመመልከት የተጓዙት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ይዘውት የተመለሱት ማስረጃ እና በወቅቱ የፓርቲው አመራሮች ለሰኣታት በክልሉ የታጠቁ ኋይሎች መታሰራቸው፡፡
እንዲሁም ፓርቲው በየጊዜው በጽ/ቤቱ የሚያደርጋቸው ውይይቶችና እንቅስቃሴዎች ማለትም ከየካቲት – ግንቦት ባሉት አራት ወራቶች በብዙ ሰዎች እና ሚዲያዎች አይን እንዲገባ አድርጎታል፡፡በነዚህ ሂደቶች ውስጥ አነጋጋሪ ከነበሩት አንኳር ሀሳቦች ውስጥ፤ በአብዛኛው በወጣቶችና በሴቶች ዙርያ መመስረቱ፣ የበርካታ አንጋፋ ምሁራን ይሁንታ ድጋፍ ከጀርባ መኖሩ በተለይ (እንደ ፕ/ር መስፍን፣ ፕ/ር በፍቀዱ፣ ዶ/ር ያዕቆብ፣ ዶ/ር ዳኛቸው፣ ፕ/ር ገብሩ እና አርቲስት ደበበ …)፣ የአመራሮቹ ቁርጠኝነትና በሚኖሩት ማናቸውም ፕሮግራሞች ላይ ግምባር ላይ መገኘታቸውና ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኋላ አለማለታቸው… የመሳሰሉት አንኳር ነጥቦች ጋር የሰሞኑ በግንቦት 17 ቀን የጠሩት ታላቅ ሰልፍ የድርጅቱን ጅማሮ (ጅማሮ ያልኩት ፓርቲው ከተመሰረተ 1አመት ከ6 ወር ብቻ እንደሆነው ለማመልከት ነው) በማየት በሀገር ውስጥ ያለውን የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለወደፊቱም ተስፋ በማድረግ ጭምር ነው፡፡
ፓርቲው በግንቦት 17 ለጠራው ሰልፍ ያስቀመጠው ምክንያት ፓርቲው ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ ለመንግስት አቅርቦ መልስ የተነፈጋቸውን ጥያቄዎች
1. ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን እንዲቆም
2. የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ
3. የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ
4. መንግስት የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን መቆጣጠር አለመቻሉ
ከላይ ያሉትን ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ መፈለግ የሚል ነበር፡፡ ይህንንም ሰልፍ ለማድረግ ከመንግስት ምንም እንኳ ፈቃድ ባያስፈልገውም ማሳወቅ ይጠበቅበት ነበር፡፡ ህጉም በሚያዘው መሰረት ከ48 ሰዓት በፊት ቢያስገቡም የመስተዳድሩ ሃላፊዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በእማኞች ፊት ደብዳቤውን ጠረጴዛ ላይ ትተውት የሰልፉን ዝግጅት ቀጠሉ፡፡ እዚህ ላይ “ማሳወቅ” የሚለው ጉደይ የገባው ዜጎች ተቃውሟቸውን በሚገልጹበት ወቅት ከተቃራኒ ወገን ጥቃት እንዳይደርስባቸው እና ሰልፉ ወዳልታሰበ ረብሻ እንዳያመራ ጥበቃ ወይም ከለላ ለማግኘት እንዲሁም የትራፊክ ስርዓቱን ለማስተካከከል ለመሳሰሉት ጥንቃቄዎች ሲባል ብቻ እንጂ ሰልፍ ማድረግ በራሱ ፈቃድ አያስፈልገውም፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ መስተዳድሩ ያቀረበው ምክንያት እውነትም ይሁን ውሽት የህግ ክፍተቱን በጠቀም ወይም ህጉን ከለላ በማድረግ ሰልፉን ያራዘመበት መንገድ ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አንድ ፖቲካ ተቋም ሊያከብረው የሚገባ ሂደት ከመሆኑም በላይ ፓርቲው መንግስትን ትልቅ ጫና ውስጥ በመክተት ሌሎች ፓርቲዎች የአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ ተከለከልን በሚሉበት ወቅት እንዲሁም ፓርቲው ለመስተዳድሩ ያቀረበውን ደብዳቤ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑት አካላቶች፤ የሰላማዊ ሰልፉን ሂደት በመቀበል ደብዳቤ መጻፋቸው (አቤ ቶክቻው እንዳለው ሳይገግሙ) ፓርቲው በመንግስት አካላት ላየ ፈጥሮት የነበረውን ጫና በገሀድ ያሳያል፡፡
ይህ ማለት ግን በራሱ እንደስኬት ሊቆጠር የሚገባው ነው ብዬም አላምንም እንደውም ፓርቲው የበለጠ ትልቅ ውጥረት ውስጥ የሚገባበትና ሀላፊነትን የሚሸከምበት ጊዜ ነው የሚሆነው፡፡ ኢህአዴግ የ 1997 እና 1998 የነበሩትን የሰላማዊ ትግል እና የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪዎች እንዴት አድርጎ እንዳጨናገፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ኢህአዴግ በባህሪው ብዙ ተለዋዋጭ ስልት የሌለው የዛሬ 20 ዓመትም ዛሬም ባለበት የሚሄድ ድርጅት እንደመሆኑ የፊታችን ግንቦት 25 የሚካሄደው ሰልፍ ላይ ምን አይነት እክል ሊፈጥር ይችላል? የሰማያዊ ፓርቲ ዝግጅትስ ምን ይመስላል? የሚለውን በተግባር በሳምት ጊዜ ውስጥ የሚታይ ይሆናል፡፡
ጥንቃቄ! እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ!!
ፓርቲው ይህንን ሰልፍ ሲጠራ ከጎኑ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሺቪክ ማኅበራት አብረውት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም በውጭ ከሚገኙ እንደነ አኢጋን በአቶ ኦባንግ የሚመራው፣ የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ካውንስል፣ በኖርዌይ የሚገኘው አዲስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የመሳሰሉ ተቋማት ካልሆኑ በተለይ ሀገር ቤት ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ አለመፈለጋቸው መንገዱ ገና ረጅም መሆኑን ያሳያል፡፡ ሆኖም የየራሳቸው ምክንያት አላቸው ብንል እንኳ ከሰልፉ መራዘም በኋላ ዝምታቸውን በመስበር አንዳንድ ግለሰቦች ነገሩ “የከሸፈ” መሆኑን ለማብሰር ሲሯሯጡ ትንሽ እንኳ ትዝብት ውስጥ እንወድቃለን አለማለታቸው ያሳዝናል፡፡
እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ !! ይህ ሰልፍ ቁጥሩ ይብዛም ይነስም ከተሳካ አይነጥላችንን የምንገፍበት ነውና ጥቅሙ ለሰማያዊ ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ ትግል እንምናለን ለሚሉ ሀገር ውስጥ ላሉ ፓርቲዎች በሙሉ ስለሆነ ከተቻለ ባለው ጊዜ መተባበር ካልተቻለ እጅን መሰብሰብ እላለሁ!!

Sunday, May 26, 2013

የደህንነት ሹሙ ስዊድን ይመጣሉ አዲስ አደረጃጀትና አዲስ ሬዲዮ በስካንዲኔቪያ

eprdf1
በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) የብሔራዊ ደህንነትና የደኅንነት አገልግሎት ሁለተኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ስዊድን እንደሚመጡ ተሰማ። በስካንዲኔቪያ አገራትና በድፍን አውሮፓ በሚኖረው ዲያስፖራ ላይ የሚያተኩር “የግል” መሰል የሬዲዮ ስርጭት ለመጀመር መታሰቡም ተሰምቷል።
የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ኢሳያስ ስዊድን ይመጣሉ የተባለው በመጪው የሰኔ ወር ነው። የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውና አቶ መለስ በእጅጉ ይተማመኑባቸው እንደነበር የሚነገርላቸው አቶ ኢሳያስ ስዊድን ከደረሱ በኋላ ሊያከናውኑ ስላሰቡት ተግባር ዝርዝር ለመረዳት ጊዜው ገና እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል።
“ሆኖም ግን” ይላሉ ምንጮቹ፣ ” ሆኖም ግን አቶ ኢሳያስ ድርጅታቸው ኢህአዴግ በስካንዲኔቪያን አገሮች በተደጋጋሚ ያጋጠመውን ውግዘት አስመልክቶ አዲስ አደረጃጀት እንደሚገነቡ ታውቋል፡፡”
የኢህአዴግና የስርዓቱ ደጋፊዎችን ለማብዛት በልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅም አባላትን የመመልመሉ ስራ በተጠናከረ መልክ እንደሚሰራበትና የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ ለመጠርነፍ ይዋቀራል የተባለው አዲሱ ድር /ኔትወርክ/ ትኩረት የሚያደርገው “አብዛኛው አድፋጭ” ወይም “silent majority” ላይ እንደሆነ መረጃ ሰጪዎቹ ተናግረዋል። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲዎችን ማደራጀት አንዱና ዋናው የአደረጃጀቱ አግባብ እንደሆነም ተጠቁሟል።
ቀደም ሲል በስካንዲኔቪያን አገራት የዲያስፖራ ድር /ኔትወርክ/ በበላይነት ይመሩ የነበሩ የደህንነት ሰው ተጠርተው ይሁን በፈቃዳቸው ወደ አገር ቤት መሄዳቸውን ያመለከቱት የመረጃው ምንጮች፣ እኚሁ ሰው በአገር ቤት ቆይታቸው በስካንዲኔቪያ ስላለው የዳያስፖራ ሁኔታ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል።
ቀደም ሲል በእቅድ ደረጃ የተያዘው “ተቃዋሚ የሚመስል የሬዲዮ ስርጭት” የመክፈት አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቆሙት የጎልጉል የመረጃ ሰዎች “ለስካንዲኔቪያ አገራት የሬዲዮ ስርጭት ለመክፈት የታሰበው ኖርዌይ ቢሆንም አሁን ግን ስዊድን ተመርጣለች” ብለዋል።
በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስለሚገኙና ስቶክሆልም ባለው ኤምባሲ አማካይነት ዜጎች ወደ ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ በዚያው ስለሚያመሩ የሬዲዮ ስርጭቱን ስዊድን ለማድረግ እንደታሰበ ከምንጮቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።
ከዓመት በፊት ታዋቂ ጋዜጠኞችን በማሰባሰብ አሜሪካ አገር የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር ታስቦ እንደነበር በተለያዩ ጊዚያት መዘገቡ አይዘነጋም። ኢሳትን ለመመከት ታስቦ አሜሪካን ይቋቋማል የተባለው የኢህአዴግ የዜና ማሰራጫ ተግባራዊ ከመሆኑ አስቀድሞ መረጃው ይፋ በመሆኑ ይሁን በሌላ ምክንያት እውን ሊሆን አልቻለም።
የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ቪ.ኦ.ኢ (VOE) በሚል ምህጻረ ቃል በኢትዮጵያ አጎራባች አገር የሬዲዮ ስርጭት ለመክፈት ኢህአዴግ የጸና አቋም እንዳለው፣ የሚከፈተውም የዜና ተቋም በአህጉር ደረጃ ታዋቂ እንዲሆንና የዜና ኤጀንሲ ይዘት የሚኖረው ነው።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Speak Your Mind

Friday, May 24, 2013

ወያኔ እና እኛ ሙስና ስንል

በቅርቡ በሀገር ውስጥ ገቢና በጉሙሩክ አገልግሎት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ጥቂት ባለስልጣኖችና ተባባሪ የተባሉ ግለሰብ ነጋዴዎች፣ በሙስና ተወንጅለው ወህኒ መውረዳቸውን ተከትሎ ወያኔ ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ከተግባሩ የበለጠ የከበሮ ድምጽ እያሰማን ይገኛል። አንዳንድ የዋህም ይህን ከበሮ በመስማት ሙስናን ለማጥፋት ዘመቻ የተጀመረ መስሏቸው ተስፋ ሲያደርጉ ይታያል።
በመሰረቱ ሙስና በወያኔ ስርአት ውስጥ የስርአቱ መቆሚያ ምሰሶ ከሆነ ውሎ አድሯል። በሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት እየተመናመኑ በሄዱበት ፍጥነት ነው ሙስና እየደራ የሄደው። ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስና ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ መፈለግ ከዝንጀሮ ቆንጆ የመምረጥ ያህል ከባድ ሆኗል።
የወያኔ ትላልቅ ሙሰኞች ለምልክት ትንንሽ ሙሰኞችን አልፎ አልፎ በማሰር ፀረ ሙሰኛ መስለው ሊያሞኙን ቢሞክሩ ዛሬ የመጀመሪያቸው አይደለም። ወያኔ ሙስናን ክስ የሚጠቀምበት አንድም በውስጡ ካፈነገጡ ሃይሎች ጋር የፖለቲካ ልዩነትን ለማወራረጃ ወይም ለውጭ ለጋሾች ሙስናን የሚጠላ መስሎ ለመታየት ሲፈልግ ብቻ መሆኑን ከልምድ እና ከተግባሩ ህዝቡ ያውቀዋል።
የወያኔ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ድህነት ማቅ ቁልቁል እያስገባና ሀገሪቱ በእዳ እያስያዘ፣ በአንጻሩ ግን የስርአቱ ቁንጮ ባለስልጣናት በሙስና ተዘፍቀው፣ በልፅገውና ከብረው፤ ራሳቸውን ከሙስና ነጻ ሆኖ ለመታየት ሲያሻቸው ግልገሎቹን በማሰር እና በራሳቸው ሚዲያ አስረሽ ምችው ይጨፍራሉ።
በእኛ እይታ ወያኔ ራሱ ቆሞ የሚሄድ ሙስና ነው። ወያኔና ሙስናን፣ ሙስናንና ወያኔን መለያየት አስቸጋሪም ነው። የወያኔ አባልና ደጋፊ የሚሰበሰበው፣ የሚመለመለው በመንግስት ሀብትና ንበረት ሰዎችን በማባበል ነው። ይህም ሙስና ነው።
ወያኔ ለየእለቱ የፖለቲካ ድርጅታዊ ስራውና በምርጫ ጊዜ በገፍ ካለ አቤት ባይ የሚጠቀመው የመንግስት ገንዝብ፣ ተሽከርካሪ፣ ነዳጅ፣ ቢሮ፣ የሚከፈለው የመንግስት ውሎ አበል፣ የሚገለገልበት የህዝብ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ጋዜጣ ወዘተ የሙሰኝነት ስርአታዊነቱ መገለጫ ነው። የመንግስት ስራ እድልን ከተማሩ ዜጎች ሳይቀር እየነጠቀ በዘርና በወያኔ አባልነት መለኪያ ለተመለመሉ አባሎች የሚሰጠው ስጦታ ዘግናኝ ሙስና ነው።
ኤፈርት የተባለው የወያኔ ኩባንያ ከህዝብና ከመንግስት በተዘረፈ ሀብት መመስረቱን እንደማያውቅ ትተን ትላንት ከባንክ ካለተከራካሪ እየተበደረ የሚነግድብን ንግድ፣ ሲከስር ብድሩና ወለዱን መክፈል ሲያቅተው ወያኔ ሙስና ብለን ይህን እንድንጠራው አይፈልግም።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ ተገዶ ወይም ተወግዶ በሀገራችን በህግና ህግ ብቻ የሚሰራ መንግስት መመስረትን እንደ ግብ የምንቆጥረው ለዚህ ነው። ግንቦት 7 በሀገራችን ሙስና ላይ የአመረረ ትግል ማድረግና ሙሰኞችን ማጥፋት የሚቻለው ወያኔን ያስወገድን እለት ብቻ ነው። ስለዚህም የሀገራችን ህዝብ ሆይ ይህን ተረድተህ ትግሉን በአስቸኳይ ትቀላቀል ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

• facebook
• google_buzz
• twitter
• rss
• print
• bookmark
• email

የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የስራ መመሪያ ተቀበሉ!

ቅዳሜ ግንቦት 17/ 2005 በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያስተባብሩ የተለያየየ ስራ ዘርፍ አባላት ዛሬ ግንቦት 15 ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በፓርቲው ጽ/ቤት በኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀመንበርየስራ መመሪያና አጠቃላይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ለማስታወሻነትም በጋራ የፎቶግራፍ መነሳት ስነስርዓትተከናውኗል።
semayawi party members in Addis Ababa
blue party members picture, addis ababa

Monday, May 20, 2013

የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ከኢየሩሳሌም አርአያ
በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪ  «የኢትዮጲያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር» ተብሎ በሚጠራውና የገዢው ፓርቲ ተለጣፊ በሆነው “ማህበር” ጋዜጠኛ ፍሬው የቦርድ አባል ሲሆን፣ ይህ ማህበር በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚተጋ ነው ሲሉ ምንጮቹ በመግለፅ ተከታዩን ማስረጃ ያቀርባሉ። « ማህበር ተብዬው በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ በኩል « እነእስክንድር ነጋ አሸባሪ ናቸው» ብሎ ተከራክሯል፤ «አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ» ጋዜጦች ሲዘጉ «ከስረው ነው» በማለት የሽመልስ ከማልን መግለጫ የሚያጠናከር መግለጫ በማውጣት ከመንግስት ወግኖ ተሟግቷል፤ እንዲሁም በተመስገን ደሰላኝ ይዘጋጁ የነበሩት «ፍትህ፣አዲስ ታይምስና ልዕልና» ጋዜጦች በነበረከት ቀጭን ትእዛዝ እንዲዘጉ ሲደረግም የነፍሬው ማህበር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ መከራከሩን በዋቢነት የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ በአጠቃለይ ጋዜጠኛ ሲታሰር፣ ሲንገላታና ሲሰደድ ልክ መንግስት ተቀጥላ እየፈጠረ ለመወንጀል እንደሚሞክረው ሁሉ ይህም ማህበር ተመሳሳይ አካሄድ የሚከተል ፀረ-ፕሬስ ስብስብ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ተለጣፊ ማህበር ሊቀመንበር አንተነህ አብርሃም እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮቹ የአንተነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አብርሃ ሲባል የደኢህዴን/ኢህአዴግ ማ/ኮሚቴ አባል መሆኑን አጋልጠዋል።
በሌላም በኩል ምክትል የጋዜጣው አዘጋጅ ኤርትራዊው ፋኑኤል አንድ ሰሞን በኢቲቪ የህትመት ዳሰሳ ላይ ቀርቦ « የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ » ሲል በይፋ መናገሩን ያስታወሱት ምንጮቹ የስርአቱን ትክክለኛነት በመግለፅና በመከራከር የገዢው ፓርቲ «ቋሚ ጠበቃ» ሆኖ መታዩትን ጨምረው ገልፀዋል። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው አቤ ቶክቻው « የኢቲቪ አምደኛ» ሲል በወቅቱ ተሳልቆበታል)..
ምንጮቹ ከጋዜጣው ጋር በተያያዘ ሲቀጥሉ ይህን አሉ፤ የነፃ ፕሬስ ህልውና በአገሪቱ ጨርሶ እንዲጠፋ በተደረገበት ተጨባጭ እውነታ፣ የህትመት ዋጋ ጣራ በነካበት ሁኔታ ..«ሰንደቅ» የተባለው ጋዜጣ የሚያሳትመው ሁለት ሺህ ኮፒ ብቻ መሆኑ፣ ማስታወቂያ የሌለው መሆኑ፣ በተጨማሪ በሃገሪቱ ውድ በሚባለው ብርሃነ ሰላም ማ/ቤት መታተሙ እንዲሁም አዘጋጆቹ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመሆኑ ምስጢር ሼህ አላሙዲ መሆናቸውን ያስገነዝባሉ። በዚህን ያክል ኮፒ ትርፍ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮቹ፣ አላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉና ጋዜጣውም በየሳምንቱ ሼኹን ከፍ-ከፍ አድርገው የሚያሳዩና ድርጅቶቻቸውን የተመለከቱ ዜናዎች እያተሙ የማውጣታቸው ምስጢሩ ከገንዘብ ድጋፉ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
በዚሁ ጋዜጣ ላይ በረከት የሚፈልጉትና « ህዝብ ዘንድ መድረስ አለበት» የሚሏቸውን ምስጢራዊ ጉዳዮች  ለሁለቱ የጋዜጣው አዘጋጆች የስራ መመሪያ ጭምር ከመስጠት ባለፈ በረከትና ሽመልስ በተለያዩ የብእር ስሞች ፖለቲካዊ ነክ ፅሁፎች እንደሚያወጡ፣ የሚፈልጉትን መረጃ እንደሚያስተላልፉ፣ ምንጮቹ አጋልጠዋል። እንዲህ ሲሉም ያብራራሉ፥ « የእነአበበ በለውና እስክንድር ነጋ ንብረት እንዲወረስ የተለያዩ የብእር ስሞች (ሽመልስና በረከት) በመጠቀም በጋዜጣው ቅስቀሳ ሲካሄድ ከቀየ በኋላ በመጨረሻ በዋና ክስነት ከቀረበው ውጭ «የንብረት ክስ» በሚል ሌላ ክስ ተመስርቶ የንብረት ውርሱ ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ። መንግስት የሰጠውን ግዳጅ በመወጣት፣ ነፃ ፕሬስን ሽፋን አድርጎ የተሰማራው ሰንደቅ ጋዜጣ ከጀርባ ያነገበው «አላማ» እንዲሁም አካሄድ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬ በማስከተሉ የጋዜጣው የኮፒ መጠን ላለፉት አመታት ሊያድግ እንዳልቻ አስታውቀዋል። በተለይ የጋዜጣው ዋና <አላማ> ተቃዋሚዎችን በአለ በሌለ ጉልበቱ ጨፍልቆ በመምታት በይፋ እንደሚታወቅ አመላክተዋል።
ለዚህም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ሁኔታ በአስረጅነት ይጠቅሳሉ ምንጮቹ፤ አብዛኛው አገር ቤት ያሉ ምሁራን አድፍጠው ባሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ገዢውን ፓርቲ በአደባባይ ከሚቃወሙና የተለያዩ የመሟገቻ ሃሳቦችን ከሚያቀርቡ በጣት የሚቆጠሩ ምሁራን አንዱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነው በማለት ይገልፃሉ። ጋዜጣው « ዶ/ር ዳኛቸው የመኢአድ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከኢ/ር ሃይሉ ጋር መምከራቸውን» በማስቀደም አያያዞም « የብአዴን አባል ነበሩ» ሲል በተቃዋሚ ክፍሎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬን ለመጫር መሞከሩን የገለፁት ምንጮቹ በረከት ስሞኦን ያጠናቀሩት ዘገባ መሆኑን አጋልጠዋል። ይህ ዘገባ ጨርሶ ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚገልፅ ማስተባበያ ዶ/ር ዳኛቸው በጋዜጣው እንዲወጣ ከማድረጋቸው ባሻገር በፌስቡክ ባሰፈሩት መልእክት « እኔ የብአዴን አባል ብሆን ኖሮ ወረቀት በታኝ ሆኜ የምቀር ይመስላችኋል?. አባል ሆኜ ድምፄ ሳይሰማ የእነ ህላዌና በረከት ስምኦን ወረቀት በታኝ ሆኜ ልቀር አልችልም!» ብለዋል።
ምንጮቹ በማጠቃለያ ያነሱት፥ ፍሬው አበበ «ተከሰሰ» ተብሎ የተራገበውን ሲሆን፣ ከስምንት ወር በፊት የተዘገበን እና አዜብ በግልፅ ከቤተ መንግስት እንደማይለቁ በተነገረለት፣ሚሚ ስብሃቱ ሳይቀር ጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያምን የሚያኮስሥና በአንፃሩ ለአዜብ የወገነ ዲስኩር ማሰማቷና እርሷ ምንም ሳትባል «ጋዜጠኛው ተከሰሰ » የተባለው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ በነበረከት የተቀናበረ « ድራማ» ነው ሲሊ ያጣጥሉታል። ምክንያቱም ሁለት ነው፤ ቀዳሚው በኢትዮጲያ ነፃ ፕሬስ አለ የሚል ስእል በመስጠት እገረመንገዱን <ፍትህ አለ> በሚል እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚቀርበውን አለም አቀፍ ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ብሎም «በእነእስክንድር የተሰጠው ውሳኔ በነፃ የህፍትህ አካላት የተወሰነ ነው» ለማለት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ።

ወገኖቼ እባካችሁ ለጥያቄዬ መልስ ስጡኝ (ተሾመ ደባልቄ)

ተሾመ ደባልቄ
ዲሞክራሲና ትግል
ዲሞክራሲ አገሮች የሚኖሩ የወያኔ ጉጅሌዎች የሚወዱትን መሪ መርጠው ለኢትዮጵያ ህዘብ ግን ወያኔ ይበቃዋል ማለታቸው ማሞ ቂሎ መሆናቸውን ያቁታል?
ለህዝብ ነፃነት እታገላለሁ የሚል የግለሰብም ሆነ የቡድን ልዩነት የሚመጣው ከህዘብ ይልቅ እራሴን ላስቀድም የሚል ስግብግብነት ነው ቢባል ዕውን አይሆንም?
ነጻነትና ዲሞክራሲ ሲባል ሆዱን የሚቆርጠውና የሚያስለፈልፈው ዜጋ የሌባ እንጀራ የበላ ብቻ ይሆን?
ወያኔስ በድንቢጥ ምስክሮቹ 99.6 በመቶ ህዝብ መረጠኝ ብሎ መንግስት ነኝ ሲል ደጋፊዎቹን ቆረቆሮ ራስ ደንቆሮዎች እያለ የሚፌዝባቸው ምን ያህል ቢንቃቸው ነው?
ይህ አቢዩታዊ ዲሞክራሲ የሚሉት የወያኔ ሥርዓት ፓርላማ መግባት እንጂ መውጣት አያቅም ማለት ነው? አብዮት ነፍስ ለመብላት ዲሞክራሲ ደግሞ ለማጭበርበር ቢባልስ ያስወነጅላል?
ወያኔ የትግራይ ሪፐብሊክ የሚለውን ክልል ከኢትዮጵያ ነፃ አወጣሁ ካለ ከርሟል መቼ ነው ክልሉን ከወያኔ ሌቦች ነፃ የሚያወጣው? ሽብር አትፍጠሩ ክልሉ በኮንስትቱሹኑ የብሄር ሌቦች ምሽግ ነው የሚለን?
የምርጫ ቦርድ የሞሉት ሙህሮች ከቀኝ ወደግራ እንዲቆጥሩ ያስተማራቸው የሕዋዕት ካድሬ ነው ወይስ መምህር?
ልማትና ኢኮኖሚ
ኑሮ የተወደደው ኢኮኖሚው በፈጣን ስላደገ ነው የሚሉ ሙሁራን አጥንተው ነው ወይስ ወያኔ አስጠንቷቸው?
ሌብነትን ልማት ነው የሚሉን የወያኔ ጉጅሌዎች ባቋራጭ ሌቦችን ከንጹህ ዜጋ  እኩል ለማደረግ ይሆን?
የውጭ እንቭሰተሮች ወያኔ ላይ ነው ወይስ ሀገር ላይ እንቬሰት የሚያደርጉት?
አላሙዲ የሚባለው ኢንቨስተር ክልልም ገደብም የለውም ማለት ነው? ኮንስትትሹኑ ዶላር ያለውና ወያኔ ኢትዮጵያዊ ሌላው ደግሞ ብሄርና ብሄረሰቦች ናቸው የሚል ተጽፏል ማለት ነው? ታዲያ ወያኔ የትግሬ ነፃ አውጭ ነኝ ከሚል የሌቦች ነፃ አውጪ ነኝ ቢል አይቀልም?
አዲሱ የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር የአባይ ግድብን የሚቃወሙ ሀገራቸው እንዳያድግ የሚፈልጉ ናቸው እያለ የሚለፍፈው ወያኔ ወገንን ሽብርተኞች ማለት አልሰራ ስላለ ይሆን?
የትግራይ ልማት የሚባለው የልመና ድርጅት ትግራይን ሊያለማ ወይስ ኢትዮጵያን ሊያደማ የተቋቋመው? ካልሆነ ለምን በኢትዮጵያ ሥም ለምኖ በትግራይ ክልል ስም ይቸረችራል?
ልማት ተፋጥኗል የሚሉ ምሁሮች ኪሳቸውን እየዳበሱ ነው ወይስ ጥናት እያጠኑ?
በልመና እድገት አመጣለሁ የሚለው የወያኔ ሥርዓት ድህነትን ማስፋፋትን ለልመና ያመቻል ብሎ ይሆን? ድህነት ባይኖር በምን ሊኖር ነው፤ በማጅራት መች?
ሰባዊ መብት
የወያኔ የሰባዊ መብት ኮምሽን ሥራ የሚቀጠር ግለሰብ የራሱን መብት የማያውቅ ብቻ ይሆን?
የአለም መንግሥታትና ድርጅቶች ወያኔ ሰባዊ መብት ይጥሳል ሲሉ ጉጅሌዎቹ የስድብ ናዳ የሚያወርዱባቸው አንጥስም ወይስ ሰባዊ መብት አልገባንም ማለቱ ነው?
ፖሎቲካ
እኔ ፖሎቲካ አልወድም የሚሉ ግለሰቦች በአዙርኝ ወያኔ ተመችቶናል እንብላበት ተዉን ማለት አይሆንም?
የፖሎቲካ ፓርቲ ነኝ ማለት እራሴን ነፃ ላውጣና እንደወያኔን ልሁን ነው እንዴ?
ፖሎቲካ ምን ያደርጋል ልማት ነው ጥሩ የሚሉ፤ ሰርቄ ወድያለሁ ተወንጅዬ እስር ቤት መግባት አልፈልግም ማለታቸው ይሆን?
ወያኔ የዲያስፖራ ወገኖችን አክራሪ ፖለቲከኞች እያለ የሚዘፍነው ማሰርና መግደል ስላቃተኝ ሌላ ምርጫ የለኝም ማለቱ ይሆን?
ወያኔ ወገኖችን ተቀዋሚ ፖሎቲካ አትግቡ እያለ በካድሬዎቹ የሚያስፈራራው የውሸት መንግስት መሆኔን ይታወቅብኛል ማለቱ ነው?
ሙሥናና ሌብነት
የወያኔ ጉጅሌዎች ጆሮዋቸውን የደፈነው ከሌብነት እንጀራ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ዘረኛነት?
ሌባ…ሌባ ተብለው የተባረሩት የወያኔ ዲፕሎማቶች ወዴት፤ እስር ቤት ወይ ሹመት ?
የወያኔ መሪዎች እነደሙጫ ያጣበቃቸው ሌብነቱ ወይስ አቢዎታዊው ዲሞክራሲው?
ድሕነትን ሐጥያት ፣ ነፃነትን ወንጀል፣  ሌብነትን ልማት ያደረጉ የዘንድሮ ሙሁሮች  የዕውቀት ድክመት ወይስ የሌብነት ቁረኛ?
ብሔርና ብሔረሰብ
ወያኔ የብሄርና ብሄረሰቦች ፌደራሊዝም እያለ በራሱ ‘ብሄር’ ላይ ከማፌዝ በላይ ያተረፈው ዘረፋ ብቻ ነው ቢባል  አሸባሪዎች የሚላቸው ወገኖች አብረውት ዘረኛ፣ አሸባሪና ዘርፊ ያለሆኑቱን ማለቱ ይሆን?
በብሄሩ አንድን ሥርዓት የሚደግፍ ግለሰብ ወይ ቡድን ሌላ ባህሪ የሌለኝ ለሆጌ የምኖረ ዘረኛ ነኝ ማለቱ ይሆናል?
ብሄርና ብሄረሰቦች ብሎ ኢትዮጰያውያንን ለፖሎቲካ ጥቅም የሚቸረችር ሥርዓት ሆነ ቡድን ብሄሩንም ማንነቱንም የማያውቅ እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል ያለ ጠፍቼ አጠፋለሁ ያለ ሽብርተኛ ነው ቢባል በወያኔ ፍትህ በዘር ማጥፋት ያስወነጀል ይሆን?
የወያኔ የክልል ሥርዓት ቀስ በቀስ የቻይና የህንድና የአረብ ብሄረሰቦች ክልል ያስፍጋል ብሎ በአንቀፅ 39 መሠረት መገንጠል መብታቸው ነው ማለቱ ይቀራል?
አንድ ዜጋ ወያኔን የሚደግፈው በዘሩ ከሆነ ዘረኛ በስራው ከሆነ ቀማኛ ቢባል ትክክክ አይደለም?
አማራ እያጠቁ በአማራናቱ ኦሮሞን ባኦሮሞነቱ…ወዘተ ይደራጅ የሚሉ ጉጅሌዎች የወያኔን ኢትዮጰያኖችን ከፋፍል ሴራ ፍጻሜ ግብ አድርሱ የተባሉ አይመስሉም?
ትግሬ ነን የሚሉ የወያኔ ጉጅሌዎች ለምን በትግሬ ሥም ሀገርን ህዘብን መዝረፍና ማጥፋት መረጡ ብል ትግሬን  ወይስ ሌባንና አጥፊን ጠላሁ ማለት ነው ?
ፍትህና ሕግ
ንጹህ ዜጋን አሸባሪ ብሎ መወነጀል  የፈሪ በትር አይሆንም? ፍርሀት ደግሞ የሚመጣው በሰሩት ወንጀል ተሸብረው ንጹሃንን በማሸበር የሚሽሩ የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው ቢባል ሀሰት ይሆን?
በሀሰት ንጹሀን ላይ የሚመሰክሩ ግለሰቦች በቁም ሞተው በቁሙ ለሞተ ሥርዓት ያጎበደዱ ብቻ ናቸው ማለት አይቻላልም?
ሚሚ ስብሃቱ የተባለች የወያኔ ታናሻ የአፈ ጉባዬ ጉጅሊት (የበረከት ታናሽ) ‘ህግ ወጥ ሰፋሪ’ ያለቻቸው ዜጎች ከሬዲዎ ፈቃድ ሌላ የራሷን ህግ እንድታወጣ ፈቃድ የፍትህ ሚኒስተር ሰጥተዋት ይሆን? በወያኔ ሥርዓት ስንት ህግ አውጭ ነው ያለው?
ፍርድ ቤት የተጎለቱት ዳኞች እስር ቤት የላኳቸውን ዳኛ እነሱ ደግሞ እስር ቤት ቢወርዱ ፍትህና ነጻነት መጣ ማለት አይቻልም?
ወገንና ሀገር አጥፊዎች
የሀገሩን ህዝብ እነደጠላት የሚያይ ግለሰብ ሆነ ቡድን ሀገርም ዘርም ህሊናም ሀይማኖትም የሌለው ቅጥረኛ ነው ቢባል በወያኔ ሥርዓት ሽብርተኛ ወይ ትምከተኛ ያስብል ይሆን?
ወያኔ ጉጅሌዎች ለቅሶ የተቀመጡት ለሟቹ መሪያቸው ወይ እየተጋለጠ ላለው ወነጀላቸው?
ዘንድሮ ወያኔ ነኝ የሚል ግለሰብ ወንጀለኛ ነኝ ቢል በቶሎ ነጻ አይወጣም?
የኢትዮጵያን ኮንስትትሹን ያረቀቁት የወያኔ ጉጅሌ ሙህሮች እኒቨሰተርስ ወይ የውጭ ዜጎች ካልሆኑ በቀር እንዴት የሕዋዕት ማኒፈስቶ ሊመስል ቻለ?
የወያኔ ሙህሮች ከሥርሃቱ ጋር ሊሞቱ ካልቆረጡ በቀር እደመሀይም ለምን ደጅ ይጠናሉ?
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስተር ከወያኔ ባርነት ነጻ ልውጣ ብለው ከተቀዋሚውን ጎራ ቢቀላቀሉ ከአሻንጉሊነት ይድናሉ ማለት በስም ማጥፋት ያስወነጅል ይሆን?
በረከት ስሞን ምን ነካቸው ብሄራቸው ያልሆነውን ህዝብ እወክላለው ብለው ልባችንን በፕሮፖጋነዳ ከሚያደርቁን ያአማራ ፍቅር ነው ወይሰ ክልሉ ወያኔና ሻቢያ ክልልና ሀገር የነፈገው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ክልል ነው?
የቀድመው የወያኔ እመቤት የባለቤታቸው ለቅሶ አብቅቶ ላጠቁት የኢትዮጵያ ህዘብ ቢያለቅሱ እድገትና ትራነሰፎረሜሽን በፍጥነት ይመጣል ማለት ይቻላል?
ወያኔና ጉጅሌዎቹ ኢትዮጵያና አማራ ጠላት ነው ባንዲራም ጨርቅ ነው እያሉ ሲለፍፉ፣ ሲገሉ፡፣ ሲገፉ፣ ሲዘርፉና ሲዘፍኑ ከርመውና ሰንብተው ምነው ከአለማቸው ሽሽት መረጡ?
ዘር የማጥራት ወንጀል የሚፈጽሙ የወያኔ ባልስጣኖች ዘራቸውን ያውቃሉ ወይስ ወያኔ ነው የሚያድላቸው?
የመለሰ ፋውንዴሽንን የሚሉት አቋም ቻይና ወይ ህንድ አልያ ሳዓውዲ ሀገር ውስጥ ቢገነባ አይሻልም?
አስተዳደደር
ነፃ አውጭ ነኝ በሚል ስም የሚነግደው የገዠው ቡድን እንኳን ትግራይን ነፃ ሊያወጣ እራሱን ከሌብነት ነጻ ማውጣጥ ችሎታ የለውም ብል የግንቦት 7 ‘አሸባሪ’ ቡድን አባል ነህ ተብዬ በአሸባሪነት ልወነጀል እችል ይሆን?
ሠራዊቱ ተብዩ ለወያኔ ከህዘብ ዘበኛ ወይስ ህዘብን ከወያኔ ተከላካይ?
የመንግስት ሰራተኞች ሲባል ደሞዝ የሚከፍላቸው ህዘብ ወይስ ወያኔ?
በብሄር ሥልጣን የያዘ ሰው ማንን ነው የሚያስተዳድረው? እራሱን?
የኢትዮጵያን ኤምባሲ የሞሉት ዲፕሎማቶች ዜጋቸውን ወይስ ብሄረቸውን  የሚወክሉት? አልያ ለምን ወያኔ ኤንባሲ አይሉትም?
ሐይማኖት
ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በሀይማኖት ስም ዳግም ተወለድኩኝ የሚሉ ባጠፉትን ወንጀል እንዳይጠየቁ ምሸግ ያገኙ መሰላቸው ወይስ ተጸጽተው? አይዣቹህ የሚላቸውስ የሃይማኖት ሥርዓት ወንጀል የፈጸመ  ሁሉ ዳግም ከተወልዶ ነፃ መውጣት ትችላላቹህ ነው የሚሉት?
የዘመኑ ፓስተሮች የኢየሱስን ወይስ የወያኔን ቃል የሚሰብኩት?
ወያኔ የሾማቸው የሀይማኖት መሪዎች ሀይማኖትን ከሚያረክሱ ከመስቀል ይልቅ ጠመንጃ ታጥቀው ባለ ሀብት ነኝ ቢሉ አያምርባቸውም?
አቦይ ሰብሃት የሚባሉ የሽማግሌ ቅሌታም ንሳሃ እንዳይገቡ የነፍስ አባት የላቸው፣ እንዳይመኖክሱ ገዳሞች  አፍርሰዋል፣ እዳያስቀድሱ ቤተ ክርስትያና እንደሕዋዓት ቢሮ የካድሬ መዋያ ሆነዋል፤ አንደኛውን ዳግም ተወለድኩ ብለው የየሱስ በግ ነኝ እያሉ እንደ ቀድሞው ጠ/ሚንስተር ቢሰብኩ አይሻልም? ለመሆኑ የኢየሱስ በግ መሆን ሌባንም ያድናል እንዴ?
ኢትዮጵያዊያን የእስላም ሀይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ሀገራችን ሀይማኖታችን ወገናችን ወይ ሞት ሲሉ እሰየው ከማለት ምን አስደነገጠው ወያኔ?
የኦርቶዶክስ ሀይማኖት የአማራ መመሸጊያ ነው ስሉ ወያኔዎች ለትግሬ ወገኖች ምንድነች ነው የሚሉት?
በዲያስፖራ ያሉ ቤተ ክርስቲያናት ገለልተኛ ነን ሲሉ ከማን ነው የሚገለሉት? ከሀይማኖት ወይስ ከወያኔ?
ያልሀበሽ የሚሉት ወያኔ ያመጣብን አዲሱ ሞዴል ሀይማኖት ከኢኮኖሚ እደገትና ትራንስፎርሜሽን ጋር አብሮ የሚሄድና ባቋራጭ አላህ ጋር እንዲያገናኘን ነው ወይስ ወያኔ አላህ ነው እንድንል?
ጋዜጠኞችና ብዙሃነ መገናኛ (ሚዲያ)
ወያኔ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጋር እሳትና ጭድ የሆነው በውሸት ህዝብና አገር ሲያቃጥል ሰንብቶ የእውነት እሳተ ሰደዶ ስለመጣበት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
የበረሀ የጦረኛ ጀግናዎች ነን የሚሉ ወያኔዎች ኢሳት ቴሌቪዝን ፈርተው የተሸሸጉት የውሸት ጀግኖች ወይስ እውነቱ ፈሪዎች?
ሀገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ (ሚዲያ) አለን የሚሉ ግለሰቦች ወይ እውነቱን ተናግረው ወያኔ እሥር ቤት ቢገቡ አልያ እግራቸተውን ሰብስበው እቤታቸው ቢቀመጡ ከውሸት ጛደኝነት አይመረጥም?
ብሄር የሌላቸው በረከት ስምዖን የሚሏቸው የወያኔ የብሔር ብሔረሰብ ፌደራል ባልስልጣን የቡዙሀኑን መገናኛ ለ 22 አመት ሙጥኝ የሉት፤  ብሄር ስለሌላቸው ወያኔ ገለልተኛል ማስረጃ ያቀርባሉ ብሎ ወይስ የውሸት ባለሞያ ስለሆኑ?
ሚሚ ስህባቱ የሚባሉ በነጻ ሚዲያ ስም ወያኔ ብቸኛ ‘የግል’ ሬዲዎ ጣቢያ የለገሳቸው ግለሰብ ድሮ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋዜጠኛ፣ ብሄራቸው ትግሬና ዜግነታቸው አሜሪካ ሆኖ የአማርኛ ሬዲዎ የከፈቱት ብሄራቸውንም ዜግነታቸውንም ለውጠው ነው ማለት ነው? የወያኔ ሥርዓት ብሄር መለወጥ ይቸሃላል እነዴ? የሁሉም ብሄር ያካተቱ የሚል ኢትዮጰያዊ ብሄር መታወቂያ አለ እንዴ?
ኢትዮጵያን ጋዜጠኞች በእስር ቤትና በስደት አልቀዋል የቀሩት ምንድናቸው ማለት ነው?  የማስታወቂያ ሥራ ድርጅቶች?
ኢቲቪ የሚሉት የብዙሃን መገናኛ ከወያኔ ነፃ ቢወጣ ሥርዓቱ ሁለት ቀን ማደር ይችላል?
ያ ወፍራሙ ወያኔ ሬዲዎ ጣቢያ የከፈተለት ዘፋኙን ጋዜጠኛን የሚያዳምጡ ወገኖች በድምጹ ወይስ በዕውቀቱ ተማረከው? አብሮት የሚያጓራ ዶክተር ነኝ የሚል ግለሰብስ የውነት ዶክተር ነው ወይስ የእንድርያስ እሸቴ ጓደኛ?
በዲያስፖራ ያሉ አንዳንድ ድህረ ገጾች ስለ አሜሪካ ዲሞክራሲና ምርጫ ሲዘግቡ ደስ ይላሉ ግን የሀገር ድሞክራሲና ምርጫ ጉዳይ ሲሆን ቻይና እንዳሉ ጋዜጠኞች አይተነፍሱም፤ ፈሪ ከሆኑ ምን አስፈራቸው ወያኔስ ከሆኑስ ምን አስደበቃቸው ብሎ የሚጠይቃቸው እንዴት ጠፋ?
ታጋይ
ይሄ ታማኝ በየነ የሚባል ወገን ጦብያ ሀገራች ለዘላልም ትኑር እያለ የወያኔ ጉጅሌዎችን የሚያቃጥላቸው ለምን ደፈጣ ውጊያችሁን ተውና በህዝብ ፊት ኢሳት ላይ ግጠሙኝ አይላቸውም? ወገኖቼ እነዳይዋረዱ ብሎ አዝኖላቸው ይሆን?
ሕውዓቶች ጀግና ነን  ተራራውን አመስነው እያሉ ባዶ ሜዳ ላይ የሚፎክሩትና ዳንኪራ የሚረግጡት  እንዴት አንድ ኢትዮጵያዊ አርቲሲት ባዶ እጁን ፈረተው፣ ሸሸተውና እንቅልፍ አጥተው ሊደናበሩ ቻሉ?
ለምንድነው ወያኔ አገራቸውንና ህዝባቸውን በጣም የሚወዱ ኢትዮጵያኖችን ታጋዮች መርጦ መርጦ አሸባሪ የሚያላቸው?
ኦባንግ ሜቶ የሚሉት ኢትዮጵያዊው ቡልዶዘር ወያኔ የሚገነባውን የክልል ግንብ እያፈረሰ አንድ ህዝብ አንድ ሀገር ስላለ አሸባሪ ስም ያሸከሙት ወያኔን ወይስ ወገኑን ስላሸበረ ነው?
ዶ/ር ብርሃኑ የሚባሉት የግንቦት 7 መሪና ወገን በወያኔ አሸባሪ ተብለው የተፈረጀባቸው በግንቦት 7 ህዝብ ስለመረጣቸው ወይንስ ወያኔን ከግንቦት 7 ጀምረው ሽብር ስለጨመሩት?
ወገን በዲያስፖራ
በውጭ ያሉ የወያኔ ደጋፊ ኢትዮጵያውያን ከወያኔ በሓላ ሀገር አትኖርም ብለው ሀገር ሊከዱ አስበዋል እንዴ?
ዲያስፖራውን ፈሪ ያደረገው ወያኔ የሰጠውን መሬት ይወስድብኛል ብሎ ይሆን?
የሕዋት ካድሬዎች ስንት ብሄር ነው ያለቸው? አንደኛውን ኢትዮጽያ ነው ብሄሬ ቢሉ አይሻልም?
በውጭ ሀገር ለህዳሴ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚመጡ የወያኔ ጉጅሌዎች ኢትዮጵያንን ሁሉ ሲጋብዙ አባይ ክልል የለውም ማለት ነው? ለምን የትግራይ ክልል ግንባታ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አይጋበዙም?
ዲያስፖራ ያሉ የሕዋዓት አባሎች ዜግነታቸው ሕዋዓት ነው ወይስ ኢትዮጵያዊ?
ለምንድነው የወያኔ ጉጅሌዎች በዲያስፖራ ስማቸውንና ተግባራቸውን ደብቀው ድፍጢያ ውጊያ የያዙት፤ ስራቸው ወንጀል መሆኑን ያውቃሉ ማለት ነው?
ጥያቄው ይቀጥላል…

ታሪክን የኋሊት፤ የአቶ መለስ ድንጋጤ! (አቤ ቶኪቻው)

እንግዲህ ይህ ከሆነ አመቱ ሆነ አይደለ… ቅዳሜም ቅዳሜ፣ እሁድም እሁድ ነው እና ምናልባት ካልተገናኘን… እንዳንረሳው፤ ከወዲሁ ቀኑን እንደሚከተለው እንዘክረው… (በቅንፍም ኤድያ እነ እንትናዬ ደግሞ ሊበሳጩብኝ ነው… (በሌላ ቅንፍ እንግዲህ ይቻሉት እኛ ስንቱን ችለነው የለ…))Melese Zenawi
በመጀመሪያም፤
ብስጭቴ
እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው በሚል የተጠቀሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው)
ዋናው ወሬ፤
የሆነው ሆኖ ትላንት በዋሽንግተኑ ስብሰባ አቶ መለስ ዜናዊ ሲመጡ ከውጪ ያለውን የተቃውሞ ድምፅ በመከራ አልፈው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተሰብሳቢው ፊት፤ ከውጪ ያለው ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ እንዲሁም አዲሳባ ያለው ህዝብ ደግሞ በሰላማዊ ዝምታ በሆዱ ምን እያላቸው እንደሆነ ነጥብ ነጥቡን ነግሯቸዋል። እንደው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውብኝ እንጂ “እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ድረስ ነግሯቸዋል!” ብል የበለጠ ይገልፀዋል መሰል!
የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድርጊት ከዚህ በፊት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረው ጋዜጠኛ ጋር የሚቀራረብ ይመስላል። እንደውም በቪዲዮ እንዳየኋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የደረሰው የቅስም ስብራት “በጫማ መመታት በስንት ጣዕሙ!” ያሰኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስፍራው የተገኙት በባራክ ኦባማ ጋባዥነት ከቡድን ስምንት ሀገሮች ጋር ስብሰባ ሊቀመጡ እንደሆነ ባለፈው ግዜ አውርተናል፤ ከቡድን ስምንቱ ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ታድያ  “ግሎባል አግሪካልቸር ኤንድ ፉድ ሴኪዩሪቲ” በተባለው ስብሰባ ላይ ቁጭ ብለው እንደተለመደው ፐርሰንታቸውን እየጠቀሱ ሳለ ድንገት አበበ ገላው፤ “መለስ ዜናዊ…” ብሎ ሲጠራ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን “የደነገጡት መደንገጥ… ከአንድ ታጋይ የሚጠበቅ አይደለም” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ። እኔም እንዳየሁት ጆሯቸውን ማመን አቅቷቸው “የድርጅቴን ብቅል እየፈጨሁ ነው…” ብለው ሊያልፉት የከጀሉ ሁሉ መስሎኝ ነበር።
ብቻ በጣም ክው ማለታቸውን ፊታቸው አሳበቀባቸው። ከዛ እንደምንም ተረጋግተው…“ሰበንቲ….ፐርሰንት” ብለው ንግግራቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድምፅ ከመጀመሪያው ከፍ ብሎ “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር…” ማለቱን ቀጠለ አሁን ትንፋሽም ቃልም አጠራቸው። አስተያየታቸው “ምነው ዛሬ እግሬን በሰበረው!?” የሚሉ ይመስላሉ። ግን እንደምንም ብለው ለመቀጠል ሞከሩ። ድምፃቸውን ከአበበ ድምፅ ከፍ ለማድረግ እየጣሩ “ሰበንቲ…ፐርሰንት” አልቻሉም። “ምን ላይ ነበር ያቆምኩት…?” ለማለት የፈለጉ ይመስላሉ ባልንጀሮቻቸውን ቃኘት ቃኘት አደረጉ። እነርሱቴ “ራስህ ተወጣው!” ሳይሏቸው አይቀሩም… አበበ ቀጥሏል። “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር….” አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኛ በላይ ድምፅ ላሳር በሚመስል መልኩ ከአበበ በላይ ጮክ ብለው እና ድፍረታቸውን አሰባስበው፤ “ሰበንቲ ፐርሰንት ኦፍ ዘ ፖፕሌሽን ኢን አፍሪካ….” አሉ። ብሽሽቅ ነው የሚመስለው እንጂ የንግግራቸው አካል አይመስልም!
ድጋሚ አቋረጡ አበበ ግን የሚያቋርጥ አይመስልም በእንግሊዝ አፍ “እስክንድር ነጋ እና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ ምግብ ያለ ነፃነት ዋጋ የለውም! መለስ ዜናዊ አምባ ገነን ነው!” ብሎ እንቅጩን ነገራቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁና ቁና ሲተነፍሱ ኮምፒውተሬን አልፎ ሁሉ ይሰማ ነበር። በሆዴ “ይበልዎት አይሂዱ አላልኮትም ነበር!?” ብልም እውነቱን ለመናገር ግን አንጀቴን በልተውታል።
አቶ መለስ ከትላንትናው የበለጠ  ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸው ጭምጭምታ ሰምቻለሁ። ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው ካምፕ ዴቪድ ድረስ ህዝቡን ለማመላለስ የተሰናዱ አውቶቡሶች መኖራቸውን የደረሰኝ ጭምጭምታ ያስረዳል።
እኔማ የሚሰማኝ አጣሁ እንጂ ቀድሞውኑም ይሄ ስብሰባ ይቅርብዎ ብዬ ነበር። ይሄን ግዜ እርሳቸውም በሆዳቸው “ምነው ምነው ምነው በቀረብኝ” የሚለውን ሙዚቃ ሊያዜሙ እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ። ምንም ጠቅላይሚኒስትር ቢሆኑ ሰው አይደሉ እንዴ…!? ምክሬን ባለመስማታቸው መፀፀት ካልቻሉ እውነትም ሰውየው ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂ ሰው አይደሉም ማለት ነው!
ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቅስም ስብራት የሰማ አንድ ወዳጄ “ይሄኔ ጥሩ አዝማሪ ቢገኝ ይቺን ግጥም በል እስቲ ተቀበል ብሎ ማቀበል ነበር” ብሎኛል…
“አፄ መለስ ዜና እጅግ ተዋረዱ
ምግብ ብለው መጥተው አንጀት በልተው ሄዱ
አንተ አበበ ገላው እንደምን ቻልካቸው
መለስ ቀለስ ሲሉ ጎንበስ አረካቸው”
(አረ ጎበዝ ዜማ ፈልጉና ይችን ነገር ነጠላ ዜማ አደርገን እንልቀቃት በስንት ግዜ የተገኘ የግጥም አዚምን እንጠቀምበት እንጂ!)
በነገራችን ላይ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ አቶ መለስ አዲሳባ ሲገቡ ወይ በጭፈራ ሞቅ ደመቅ አድርገን ካልተቀበልናቸው ወይ ደግሞ ለጥ ብለን ተኝተን ካልጠበቅናቸው በብስጭት ሊጨርሱን ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም
ኦባማ ግን አራዳ መሆናቸው ነው ሰውየውን ጠርተው ልክ ልካቸውን የሚያስነግሯቸው!? የምር ሽምቅቅ አደረጓቸውኮ! (እኔ ልሸማቀቅ… ልላቸው ነበር አሁንማ አንዴ ጀምረውታል… ይወጡት እንግዲህ!)

Sunday, May 12, 2013

ሕወሓት ብኣዴንን እየዋጠው ነው! “ባንድ ወንጭፍ አማራውን በፍጥነት!”

ምንሊክ ሳልሳዊ
ከበረሃው ትግል ጀምረው አብረው እየነጎዱ የመጡት ሕወሓት እና ኢህዴን በኋላም ብኣዴን በአሁኑ ወቅት አጅግ ከባድ የሆነ የፖለቲካ ፊቲጫ ውስጥ መሆናቸውን በዙሪያቸው የሚደረጉት ድርጊቶች እያሳበቁ ነው::በሽግግር መንግስቱ ጊዜ ታምራት ላይኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ በነበረበት ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ዙሪያ የቀድሞ የኢህኣፓ ሴሎች መሰባሰብን ተከትሎ እንዲሁን ጣምራት የነበረው አቋም ተለክቶ በኤርትራ ጉዳይ ዙሪያ ያለው አመለካከት ተመዝኖ በወያኔ እና በሻእቢያ ጥርስ ውስጥ ገብቶ በሙስና ተፈርጆ በከባዱ አንገቱ እስኪሰብር ቀጥቅውት ከፖለቲካ ጨዋት ውጭ አድርገውታል::Ethiopian police have arrested a minister and 11 other people
እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረውን ሙሉአለምን በፈንጂ ባህር ዳር ላይ አጥፍተውታል:: የሕወሓት የፖለቲካ ቁማር በዚሁ አላበቃም መለስ ብለን ካየነው ብዙ ነው…..እያለ የቀጠለው የሕወሓት መጦ መትፋት እነ አዲስ ለገሰን እነ ተፈራ ዋልዋን እና ሌሎች የብኣዲን አባላትን ከህዝብ ጋር ከተቀላቀሉ በሁዋላ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሸተዋል በሚል መርዛዊ ጥላቻ በጡረታ በጤና ሰንክ በአምባሳደርነት ከአጠገቡ አባሯቸዋል::ለሃገራቸው ይሰራሉ ተብለው የተገመቱ የተጠበቁ የብኣዴን ታጋዮችን ወዴት እንደደረሱ እንኳን ሳይታወቅ አንጠባጥቧቸዋል:: በተጨማሪም በወታደሩ ክፍል የነበሩትን የብኣዴን ጀነራሎች እና የበታች መኮንኖች ለስልጣን ያሰጋሉ በሚል በተለያዩ እስር ቤቶች በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና በፖለቲካ ስም አስሮ ይገኛል::በቱረታም አባሯል::
ይህን ይህን ያን ያን …እያልን ያለንበት ላይ ስንደርስ ደሞ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በስልጣን ሽኩቻ ዙሪያ የተለያዩ መፋጠጦች እንደነበሩ እንዲሁም እንዳሉ ይታወቃል::ያ መፋጠጥ እና መሿኮት ቀጥሎ በኢህኣዴግ ስብሰባ ላይ በጡዘት ወቶ የነበረ ቢሆንም አልስፈላጊ አደርባይ ሙሰኛ በሚል አደገኛ እንደ ጌታቸው ሴኩትሬ አባባል “የገማ ቂቤ” እየተቀቡ አፋቸውን እንዲይዙ ተደርጓል ብኣዴኖች::
ሕወሓት ለያዘው አላማ እንቅፋት እንደሚሆንበት ከጅምሩ በብኣዴን ላይ የሾሉ ጥርሶቹን እየደጋገመ ሲሞርድ እንደነበር ይታወቃል:; ብኣዴኖች በተለያየ ጊዜያት በሙስና እንዲዘፈቁ እና ማስረጃ እንዲያዝባቸው በአጠገባቸው በሚመደቡ የህወሓት አባላት ከፍተኛ የሆነ ውስወሳ እና ክትትል በማድረግ መዝገባቸውን በሙስና ሰነዶች በመሙላት ለማስወገድ ሚናውን ተጫውቷል:: አሁንም እየተጫወተ ነው:: እንዲሁም ይህንን የፖለቲካ ቁማር በደቡብ ግንባር ላይም እየተጫወተ ይገኛል::
ሕወሓት ነባር የብኣዴን ታጋዮችን ሰብሰቦ ካስወገደ በኋላ በአማራው ክልል የተወለዱ አማርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያንን እና የትግራይ ተወላጆችን በመሰግሰግ ጉዞውን ሊቀጥል እየተራወጠ ይገኛል::
ህወሓት በዚህ ሰሞን ደሞ በብኣዴን ባለስልጣናት ላይ ዘመቻ ከፍቷል:: ዘመቻው ሁለት አላማዎችን የያእ ነው እንጂ በፍጹም ሙስና አይደለም::በእርግጥ ሙስና የለም ብለን አንናገርም ሆኖም ሊበሏት ያሰቧትን… እንደሚባለው በፖልርቲካው ላይ ችግር እየፈጠሩ ያሉትን ባለስልጣናት ማስወገድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሙስናን እንደቀዳሚ ተደርጎ ለህዝብ ማስነገር አስፈላጊ ነው …ለመሆኑ በሙስና ረገድ ከፍተኛውን የሙስና ባላባቶች የሆኑ የሕወሓት ባለስልጣናት እና የጦር ጄኔራሎች ለምን አይከሰሱም ? አይባረሩም? አይጠየቁም??…ባለፈው ጊዜያት ከጸረ ሙስና ኮሚሽን ዘሎ የወጣ መረጃ እንደጠቆመው የህወሓት አባላት በሙስና መዘፈቃቸውን የሚያሳይ እውነተኛ ምስክር ነው::
ሕወሓት ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሙስና ድርጊት እንደት ነው ሊወገድ የሚችለው?? ለምንስ የህወሃት ሙሰኞች ለፍርድ አይቀርቡም ስልጣናቸውንስ አይነጠቁም?? የጦር ጄኔራል የሆኑ የሕወሓት ቅምጥ መኮንኖችስ ለስልታን ጥበቃ በሚል ሰበብ ለምን ዝም ይባላሉ?? ይህን እና ተመሳሳይነት ያላቸው ጥያቄዎች ለመመለስ የሚከብድ ነው ለወያኔ::
በዚህ ሳምንት ደሞ እንደፋሽን የተያዘው ነገር ቢኖር ብኣዴኖችን መግቢያና መውጫ አሳጥቶ አፋቸውን በማስያዝ ምንም አይነት ጥያቄ እንዳይጠይቁ እና አንገታቸውን እንዲሰብሩ ማድረግ ነው::
ትላንት እና ጠዋት የደረሱን ማስረጃዎች እንዳመለከቱን ከሆነ መገናኛ አከባቢ በሚገኘው የጉምሩክ ዋና መስሪያቤት ውስጥ ሲቭል በለበሱ ደህንነቶች እና በፌዴራል ፖሊስ የታጀበ ኦፕሬሽን እየተደረገ እንደሆነ ቢያመለክትም በውስጥ የነበሩ ከ200 በላይ ሰራተኛች የሃገር ጉዳይ ነው ተብለው እንደወጡ እና አቶ መላኩ ብጫውን ታግቶ እንደነበር እና በኋላም በምን እንደሆነ ሳይታወቅ አቶ ገብረዋህድ እና ሌሎች የመምሪያ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተነግሮ ነበር :; ይህንን ለማጣራት በተደረገ ሙከራ መረጃ የሚሰጡን የብኣዴን እና አንዳንድ የሕወሓት አባላት ስልካቸውን እስከ ማታ ድረስ እንዲዘጉ ታዘው ነበር::
መረጃዎች እንደጠቆሙት በአቶ መላኩ ፈንታ እና በአቶ ገብረዋህድ መካከል ምንም አይነት መግባባት እንደሌለ እና በኣንድነት ሙስና ይፈጽማሉ ሊያስብል የሚችል አንድም ሁኔታ የለም ይላሉ እንደውስጥ አዋቂዎች እምነት:: ገብረዋህድ በጉምሩክ ባለስልጣን ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ሲሆን አቶ መላኩ እንደበላይነታቸው ሙሉ ስልጥኣን አልነበራቸውም:: አቶ መላኩ የፈረሙትን ገብረዋህድ ይሽር እንደነበር እና ይህም ጉዳይ ጥቆማ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርሶ ውሳኔ ደፍሮ የሰጠ አልነበረም::ገብረዋህድ ማለት እጅግ ቀንደኛ ዘረኛ የሆነ ሰው እንደሆነ ይታወቃል ስለዚህ ኢትዮጵያ ከሚለው መላኩ ጋር ተስማምቶ ሙስና ይሰራል ማለት ዘበት ነው::ታማኝነትም የለውም ::ገብረዋህድ ባንድ ወቅት በመስሪያ ቤቱ እነና ስርኣቱ ህልውናችን አንድ ነው ያለ ደፋር እና ዘረኛ ሰው ነው በሙስና ተብሎ ዘብጥያ መውረዱ አጠያያቂ ሲሆን እንደኔ ብኣዴኖችን ለመጥለፍ የተሸረበ ሴራ ነው::
ገብረዋህድ ከወይዘሮ አዘብ ጋር ቀረቤታ እንዳለው ይታማል:: ከላይ እስከ ታች በጉምሩክ ውስጥ የሞሉት የትግራይ ተወላጆች በሙስና ተጨማልቀዋል::እንዲሁም ስርኣቱ እጅግ ከሚንከባከባቸው ሰዎች አንዱ ነው:: በተለያየ ጊዜ የህወሃት ባለስልጣናት እና የጦር ጄኔራሎች በተለያየ ጊዜ ከውጪ የሚያስገቧቸውን ማንኛውም ነገሮች ጉምሩክ በነጻ እንደሚያሳልፍላቸው ሲታወቅ የህ ደሞ የገብረዋህድ ተትእዛዝ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ጸሃፊ ሆና የምትሰራ አንዲት የመሃል አገር ሰው የሆነች ትግሪኛ ተናጋሪ እንደነገረችኝ በተለያየ ጊዜያት ከጄኔራሎቹ አልፎ እሷ ራሷ ከተለያዩ አገሮች የምታስገባቸው እቃዎች በነጻነት ቤቷ ድረስ ተጭነው እንደሚመጡ አጫውታኛለች::
ይህን ተከቶ አቶ ብርሃነ ሃይሉ እና አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው በአማራነት ከህወሃት ተባረዋል :: ህወሓት ወዴት እያመራች ነው?? አማራውን እያደነዘዘች ማጥፋት :: ይህ ሊታገሉት የሚገባ ጉዳይ ነው:: ምክንያቱም ባለፉት ጊዜያት የተደረጉ ጉዞዎች ያልጣሟቸው ባለስስልታናት ጥያቄ እያቀረቡ ባሉበት በዚህ ወቅት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች መመልከት እና ማመዛዘን የራሳችን ድርሻ ነው::