Thursday, February 28, 2013

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።
የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

Wednesday, February 27, 2013

የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት
በዲሴምበር 2011 ‹‹ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር፡፡ በዚያን ወቅትEthiopia The Politics of Fear in the police states ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው፡፡በዘገባው ላይ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ያሰፈረው ነጥብ (10 ከሙስና የፀዳ ማለት ሲሆን 0 ደግም በሙስና ንቅዘት ያጨማለቀው ማለት ነው) ኢትዮጵያ 2.7 ነበር ያገኘቸው፡፡ በሙሰና ከታወቁት የኣለም ሃገሮች ዋነኛዋ ኢትዮጵያ ናት ይል ነበር:: የግሎባል ፊናንሻል አንተግሪት ድርጅት ደግሞ ባለፉት ፲ ኣመታት ከኢትዮጵያ 11.7 ብልዖን ያሜርካን ብር በሀገወጥ መንገድ ከኣገሪቷ ወጥቶአል ብሎ ዘገቦ ነበር::
ባልፈው ኣመት: አሁንም በስላጣን ላይ ያለው ገዢ ኣስተዳደር ኢትዮጵያን በሽብርተኞች ማነቆ ውስጥ ተወጥራ እንዳለች ሃገር አድርጎ ለማቅረብ ባወጣው የልመናና የገንዘብ መቧገቻ እቅዱ ባለሶስት ክፍል የፕሮፓጋንዳ የቅጥፈት ታሪክ ‹‹አኬልዳማ›› በማለት (ወይም የደም መሬት በማለት ከአክትስ 1፡19 በመዋስ፤ የአስቆሮቱ ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ በመሸጥ ባገኘው ገንዘብ የተገዛ መሬት) ከልብ ወለድ የማይሪቅ ትርኢት ለሕዝብ ኣቅርቦ ነበር፡፡ ይህም ትርኢት በአትዮጵያና በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰዎች በሚታገዝና በሃገርም ውስጥ ባሉት የሚደገፍ የሽብር ተግባር አምባ አድርጎ ለማሳመን የተሰራ ነው፡፡ አኬልዳማ ሲጀምር በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰት የሚችል በማለት የደም ጎርፍ መምጣት እንደሚችልና፤ ሸብር ዓለምን በማጥፋት ላይ ነው፡፡ ‹‹አኬልዳማ›› ሲተረት: “ሽብርተኝነት የቆምንበትን መሬት እያነቃነቀ፤ ዕለታዊ እንቅስቃሴያችንንም እየገታ መሆኑን በቅጥፈታዊ ፈጠራ ለማሳየት የቀረበ ትርኢት፡፡ አሁን እየተናገርኩ ያለሁት ስለዓለም አቀፉ ሥብርተኝነት አይደለም፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በገዢው መንግስት ለኢትዮጵያ የተቀመጠውን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳና በዚያም ውስጥ ስለተካተተው አኬልዳማ ተብሎ ስለተቀፈቀፈው፤ ሸብርተኝነት ለኢትዮጵያ አስጊና አሳሳቢ ችግር ነው…… ስለተባለው ነው፡፡”
በአኬልዳማ ውስጥ ተቀነጫጭቦና ተቆርጦ የተቀጣጣለ የቪዲዮ ቅንጥብጣቢ፤የአልቃይዳና የአል ሸባቢ ተከታዮች የመለስ ዜናዊን መንግስት ለማፍረስና ሃገሪቱንም ለማመሰቃቀል ተነስተዋል በማለት የሕጻናት የአዛውንቶች፤ እሬሳ በመንገድ ላይ ወድቀውና በደም ተጨማልቀው በዝንቦች የተወረሩ እሬሳዎች፤ የተቆራረጡ እግሮች፤ የነደዱ ተሸከርካሪዎች፤ በቦምብ የፈራሱ ሕንጻዎች፤ የህክምና ባለሙያዎችም የተጎዱትን ሲያክሙና በኒው ዮርክ በሽብርተኞች የፈረሱት የትዊን ታወር ምስሎች በማገጣጠም የገዢውን መንግስት ስጋት አሳማኝ ለማድረግ ምስሉን አቀነባብሮ አቀረበ፡፡ በዚህም የሕብረተሰቡ ሕሊና ውስጥ የፈጠረው ስጋት ቢኖር የገዚዎች ውሸትና ተራ ፕሮፓጋንደ እንጂ ከዚያ ያለፈ ለማሳመን የቻለው የለም፡፡ ማስረጃውን እንመልከት ብሎም ያቀረበው ዘጋቢ ቁጭት በውስጡ እየነደደ የሃሰት ስሜቱን ታግሎ በማውጣት በጥፈሩ እየቆመና ቃላትን እየረገጠ በሚያስፈራና ቀፋፊ በሆነው ድምጹ ህጻናትን እያሰበረ አርጉዝ ሊያጨነግፍ በሚችል ስሜት አቀረበው፡፡ እስቲ እውነተኛውን ማስረጃ እንመልከት፤ ይላል ‹‹አኬልዳማ››: “ባለፉት ጥቂት ዓመታት፤ 131 የሽብርተኞች ጥቃት ተካሂዶ 339 ተገድለዋል 363 ቆስለዋል፤ 25 ደግሞ በሽብርተኞች ታፈነው ተገድለዋል፡፡” ቅጥፈት የተሞላበት፤ ማጭበርበሪያ የሆነ፤የተዛባ ትረካ የተካተተበት አኬልዳማ በተቃዋሚዎች ላይ ሕዝባዊ ጥላጫና ጥርጣሬ ለመንዛት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነበር፡፡ውጤቱ ግን እንደታሰበውና እንደታሰበው ሳይሆን መክኖ ቀረ፡፡
2013 የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት
ወደ ፌብሪዋሪ 2013 ፈጠን ብለን እንሂድ:: በቅርቡ ተጣርቶ በወጣው ባለ 448 ገጾች የዓለም ባንክ ዘገባ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ ከአናት እስከ ታች ድረስ በባለስልጣናቱና በአጃቢ አገልጋዮቻቸው ንቅዘትና ሙስና የተዘፈቀች ሃገር ናት ይላል፡፡ በዘገባው መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የንቅዘቱ መፈልፈያ ማህጸን ነው፡፡ ገዢው ኣስተዳደር በጣሙን የገዘፈ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ በቴሌ ላይ ኢንቬስት ቢያደርግም፤በአፍሪካ ሁለተኛው የቴሌፎን ስርጭት ዝቅተኛ የሆነበት ሃገር ከመሆን አላዳነውም፡፡ በጣም አናሳ አግልግሎት ሰጪ ድርጅት ከመሆንም አልፎ፤ከተጠያቂነት ነጻ የሆነ የዘረፋ ማእከል ነው፡፡በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ታዛቢዎች ድርጅቱ በሙስናና በንቅዘት የተገነባ ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ በየትኛውም የአገልግሎት አሰጣጥ መመዘኛ ተጎታችና እርካታ ይሉት አገልግሎት የሌለው በየጊዜው በሚነደፈው የሙስና እቅድ ውስጥ ተውተፍትፎ አገልግሎቱ እርባና ቢስ ነው፡፡ የፍትህ ስርአቱም ቢሆን ሕብረተሰቡን በነጻ እንዳያገለግልና የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ተደርጎ በገዢው ኣስተዳደር ንጹሃንን በመወንጀል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በመግታት አገዛዙ ከመንበሩ ሳይለቅ የሚቀጥልበትን ሁኔታ የሚተገብር የፍትህን ስርአት የጣሰ ነው፡፡ ይህም በህጋዊ ኢፍትሃዊነት ብቻ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር ለጉቦና ለንቅዘት ተጋልጦ ያለ አንድ የገዢው መንግስት የጦር መሳርያ ነው፡፡ ገዢው መንግስት በስልጣን መቆየቱን እንጂ ለሃገርና ለህዝብ እድገትና ልማት ጨርሶ ደንታ የሌለው በመሆኑ ከጉቦ ውጪ አንዳችም ጉዳይ በስርአት አይከናወንም:: የዚህም ሂደት ዋናው አስፈጻሚ ሞተር ገዢው ፓርቲና ጀሌዎቹ ናቸው፡፡
በፌብሪዋሪ 5/2013 ላይ በአዲስ አበባ ያለው ገዢው ኣስተዳደር ‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› (የቅዱስ ጦርነት እንቅስቃሴ) በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ (ዶኩሜንታሪ) ፊልም በእኩይ አስተሳሰብና ዲያብሎሳዊ ግንዛቤው የኢትዮጵያ ሰላማዊ ሙስሊሞች ያነሱትን ሃይማኖታችንን ለኛ ተዉልን፤ ሰብአዊ መብት ይከበር፤ በማለቱና በሰላማዊ መንገድ እንሰማ በማለታቸው፤ በየቦታው ካሉና የኢትዮጵያ ሙስሊም ሕብረተሰብ ከማያውቃቸው፤ ተግባራቸውን ከማይቀበለውና ግንኙነትም ከሌለው ጋር ገዢው ኣስተዳደር በተካነበት የቅጥፈት ዘመቻው ጥያቄ እንዳሰኘው በሚያዝበት ቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ አሰራጭቶ ነበር፡፡
‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› በሁለንተናዊ መልኩ የ‹‹አኬልዳማ›› ግልባጭ ነው፡፡ መሰረታዊ ልዩነቱ የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ለይቶ ለማስፈራሪያነትና ለስም ማጥፊያ ተብሎ በአንድ የሃይሞነት ተከታዮች ተነጣጥሮ መተግበሩ ነው፡፡ በአጠቃላይ ዘጋቢው ፊልም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት እንዲከበር፤ ኣስተዳደሩ በእምነታቸው ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም በመጠየቃቸው፤ ያላለሙትንና ጨርሶ ያላሰቡትን ሕዝቡ ናቸው ብሎ እንዲቀበል፤ እነዚህ ደም የጠማቸው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም፤የማሊው አንሳር ዲን፤ አልቃይዳ አልሻባብ ሃማስ ቅርንጫፍ ተከታዮች በማለት ያልሆኑትን ናቸው በማለት በተለመደው የፍርሃትና የመደናገጥ ዜማው ታርጋ በመለጠፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ዶኩሜንታሪው ተቆቋሪ በመምሰልና አዛኝ ቅቤ አንጓችነቱን በማጠናከር በሙስሊሙ መሃል የተሸሸጉ ጥቂት ሽብርተኞች በማለት ይኮንናል፡፡ ዘጋቢው ፊልም በየትም የአፍሪካ ያልታየ የቂመኝነትና የትእግስት ማጣት እኔ ካልኩት ውጪና ከምፈቅደው ባለፈ ንክች ያባ ቢላ ልጅ ይሉት ዓይነት ድንፋታ ብቻ ነው፡፡
ውሸት ሞልቷል፤ እርቃኑን የቆመ ውሸት አለ፤የጎደፈ ውሸት አለ፤የሆዳሞች ውሸት አለ፤የመልቲዎች ቅጥፈት አለ:: ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደሞ እነዚህ ሁሉ ውሸቶች የተጠናወቱት ነው፡፡ ይህን የሚያቀለሸልሽ ዶኩሜንታሪ ከተመለከትኩት በኋላ፤ በቅርቡ ያለፈው መለስ ዜናዊ የሜይ 2010ን ምርጫ 99.6 በሌብነት የተገኘ ድል አስመልከተው የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢዎች ስለተከናወነው የድምጽ ሌብነቱ ፊት ለፊት ሲጋፈጡት የሰጠው ምላሽ ታወሰኝ፡፡ መለስ እጅ ከፍንጅ በመያዙ የአውሮፓ ዩኒየነን የምርጫ ዘገባ በመኮነን ከአንድ መሪ በማይጠበቅ መልኩ ማፈሪያ የሆነውን ‹‹ዘገባው ቆሻሻ ስለሆነ ንብረቱ ወደሆነው ወደ ቆሻሻ መጣያ ሊወረወር ይገባዋል›› ነበር መልሱ፡፡ ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደካማ፤ አስቂኝ፤ማሰብ ከተሳነው ህሊና የወጣ፤ማስመሰያ፤ መርዘኛ፤ በጉራ ያበጠ፤ ድንፋታ ነው፡፡ ይህን መሰሉ የመለስ አባባልም የቅራ ቅንቦ ክምር ነውና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ወደ ቆሻሻ ቱቦ ተደፍቶ ከእጥብጣቢውና ከቆሻሻው ፍሳሽ ጋር ሊቀላቀል ይገባዋል፡፡
ፈጽሙ የተባሉትን ያለ ጥያቄና ስስብእናቸውን ለጥቃቅን ጥቅም በመሸጥ ታዛዥነታቸውን የሚያረጋግጡትን አሰባስቦ ተመረጡ ብሏል፡፡ ቀድሞ ለዘመናት ከመንግስት ተጽእኖና ቁጥጥር ነጻ የነበረው አስልምና ካዉንስል አሁን በገዚዎቹ የሚታዘዝና የገዚዎቹን ትእዛዝ በመቀበል የሚያስፈጸም የካድሬዎች መጠራቀሚያ ሰፈር ሆኗል፡፡ መያዙ፤በሽብርተኝነት ወንጅላ ካውንስሉን የመቆጣጠር ህልሙን ተግባራዊ ማድረጉ በኢትዮጵያ ውስጥ ገዚዎቹ ሃይማኖቶቹን መጠቀሚያ የማድረጉ ሂደት እየባሰ መሄዱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ጊዜ በርካታ ሙስሊሞች በመላ ሃገሪቱ ለእስራት እየተዳረጉ ነው፡፡ በኦክቶበር 29 ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት 29 ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ሰዎችን በሽብርተኝነትና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል በሚል ለእስር ዳርጓል፡፡
ጂሃዲስቶች ተመልሰው እየመጡ ነው?!
‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› የኢትዮጵያ መንግስት ጂሃዲስቶችን ከጓዳው እያወጣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስፈረራ የመጀመሪያው አይደለም፡፡በ2006 ዓም የመለስ ዜናዊ ታንኮች መንገዳቸውን ወደ ሞቃሾ ከማምረታቸውና በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን የሱማሌ ህዝቦችን ከመጨፍጨፋቸው በፊት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ከቤት ንብረታቸው ከመፈናቀላቸውና ከመልቀቃቸው አስቀድሞ መለስ ዜናዊ የሶማልያን ጂሃዲስቶች፤ ሽብርን ፈጥሮ፤ በሚገዛው ሃገር ውስጥ የሚፈጽመውን ሽብር፤ ጭቆና፤ ግፍ፤ መጠን ያጣ በደል፤ የሰብአዊ መብት ገፈፋ፤ የፍትህን መዛባት ከዓለም ገጽታ ለመሰወርና አዲስ ባወጣው የሶማሌ ጂሃዲስቶችና ……… በመተካት በተለይም የአሜሪካንን መንግስት ትኩረት ከኢትዮጵያ የግፍ አመጽ በማሸሽና ወደ ሶማሊያ ላይ በማስተኮር የአሜሪካንን መንግስት የዲፕሎማቲክ ድጋፍ ሙሉ ፈቃድ ተጎናጸፈ፡፡
‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› ወይም እስልምናን ማስፈራሪያ ማድረግ ጥበብ
‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› የሚያስጠላ የሙያ አልባዎች ቅጥ የሌለው ፕሮፐጋንዳ ሲሆን ማንም ቢሆን ከተመለከተው በኋላ የዘገምተኛ መሃይም አስተሳሰብ ከማለት ቀልድ ሌላ ትርጉም አያገኝለትም፡፡ ለአዘጋጂዎቹ ግን ቁም ነገር የሌለው ተብሎ ብቻ የማይተው ሳይሆን ጠቅላላውን የሙስሊም ማሕበረሰብ ዝቅ አድርጎ የመመልከትና እንደ መሪም ሃላፊነት የጎደለው ጋጠ ወጣዊ ተግባር ሊባል ብቻ ነው የሚቻለው፡፡ ለማስተላለፍ የተፈለገውም በጥላቻ የተሞላና በሰላም የኖሩትን የአንድ ሃገር ሰዎች በማከፋፈልና ጠብ እንዲጫርና ጣልቃ ገብቶ የተለመደ የመግደል የማቁሰል ሱሱን ለመወጣት ተብሎ ‹‹ጥሩ ክርስቲያኖች›› ላይ ‹‹መጥፎ ሙስሊሞች›› ሊፈጽሙ ያሰቡት ደባ›› በማለት፤ ሁለቱ እንዲጋጩ፤ አለመግባባት ጨርሶ ሳይኖራቸው አንዱ የሌላው ችግር ደራሽ፤ አሳቢ፤ በሃዘንም ሆነ በደስታ አብረው በመቆም ዘመናት ባሳለፉት ወንድማማቾች መሃል አለመግባባት በመፍጠር በድንገት የሙስሊም ሽብርተኞች መጡብህ በሚል ስር የሰደደና የተካኑትን የማናቆር ተግባር በመተግበር የእስልምና መንግስት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱብህ ነው በማለት ክርስቲያኑ እንዲነሳሳ በመጨረሻም ግጭቱ እንዲሰምርላቸው ነበር ቅዠታዊ ስልት ነበር፡፡ ቀደም ሲል‹‹አኬልዳማ›› ብለው የፈጠሩት የቆርጦ ቀጥል የማፍያ ተግባራቸው፤ ሙስሊሙን ክርስቲያኖች ሊያጠፉህ መጡብህ ለማለት ተብሎ ቢተላለፍም፤ አቅራቢውም ትንፋሽ እስኪያጥረው ቃላቱን እየረገጠና በዘጋቢው ፊልም ውስጥ የነበሩትን ንጹሃን ዜጎች፤ ከአለቆቹ በበለጠ ጥላቻው ከሮበት እስኪታይ ድረስ ቢንደፋደፍም ውጤቱና ሕዝባዊ መልሱ ግን ከ ‹‹ዶሮን ሲያታልሏት………›› አላለፈም፡፡ እንዲጠሉ የታቀደላቸው ጭርሱን የፍቅር አድባራት ሆኑ፡፡ በእዝ ማስጠላትና ማራቅ ባለመቻሉ ግለሰቦችን ከእገሌ ጋር ቢቀርብህ ይሻላል በሚል ከንቱ ተራ ማስፈራርያ መጠቀሙም ቢሆን ብዙም አልሰመረም፡፡
ገዢው መንግስት በዚህ ዱክትርናው በርከት ያሉ የፕሮፓጋንዳ ግቦችን ለመፈጸም ሞክሯል 1) የማን አለብኙ መንግስት ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር፤በሃይሞኖቶች መሃል ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆምና የማይመጥናቸውን የራሱን ፍላጎት ለሟሟላት ሲል ብቻ ሽብርተኞች፤አክራሪ ጂሃዲስቶች፤ የመግደል አባዜ የተጠናወታቸው በማለት የራሱን መታወቂያ በሙስሊማኑ ላይ ለመለጠፍ መሞከር: 2)የክርሰትና እምነት ተከታዮችን በማነሳሳትና ነገር በመቆስቆስ ጥላቻና በመዝራት በሙስሊም ወንድሞቹ ላይ ጥርጣሬና እምነት እንዲያጣ ለማድረግ መሞከር፤ 3)ሙስሊሞችን ለይቶ በማወቅና ስማቸውን በእኩይነት በማቅለም ፍርሃት እንዲያድርባቸው ማድረግ፤ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ማጋጨት፤ ሁሉንም የሕብረተሰብ አባል እንደሚጠሉና ለራሳቸው የሚሆን ዓለም ለመፍጠር የሚጥሩ በማስመሰል ሌላውን የሕብረተሰብ አካል በጥላቻ እንዲነሳሳባቸው ማድረግ፤እንዲሁም ለመወንጀል ለመያዝ በግፍ ለማሰርና ለማሰቃየት በመጨረሻም የሚመኘውን የሰውን ልጅ ክብር በማዋረድ ለመከራ መዳረግ፡፡ 4)መላው ሕብረተሰብ ላይ ያጠላበትን የመከራ የርሃብ የችግር የድህነት የኤኮኖሚና የፖለቲካ እጦቱን፤ሙስሊሙን ጂሃዲስቶች ናቸው በሚል ከንቱ የጉሮ ወሸባዬ ያልተቃኘ ዜማው በማደናቆር ሃሳብንና ቁጭትን ለማስለወጥ የተዘረጋ የኢህአዴግ ዲያብሎሳዊ አካሄድ ነው፡፡ 5) ጨርሶ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ አስቦትና አንስቶት የማያውቀውን አስተሳሰብ የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም፤ ቦምብና ሌሎች መሳርያዎች ለማንሳት እንዳቀዱ በማስመሰል ፕሮፓጋንዳውን እንደ የእድር የቀብር ጥሪ ቢያናፋም ቀብሩ የማን እንደሆነ ሕብረተሰቡ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ አልተቀበለው፡፡ እርግጥ ገዢው መንግስት የሕዝብን ቁጣና የበቃህ ስሜት በሚገባ ስለተረዳው በማድረግ ላይ ያለው አስተሳሰብንና አመለካከትን በማስቀየር ጊዜ መግዛትን ነው፡፡ የዓለም ባንክ ጥርት ያለው የ448 ገጽ ዘገባ፡፡
ይህንን የበሬ ክምር እበት በመመልከት ጊዜያቸውን ማጥፋት ለማይፈልጉ (ማየት ካለባቸህ ደግሞ አፍንጫችሁን ጠቅጥቁት) እንደዘጋቢ ፊልም ለማለፍ ቅንጫቢው እነሆ፡፡ የዶኪመንተሪ ቅልመዳ ትርኢት ሲከፈት መክፈቻውንና ማስረጃውን በጸሁፍ በማስቀደም ይጀምራል ‹‹ጥቂት ግለሰቦች የእስልምና ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ፤የሥብር ተግባራቸውን ለመፈጸም ሲሉ ባደረጉት እንቅስቃሴ ላይ የቀረበ ማስረጃ፡፡ ከብሔራዊ ደህንነት አግልግሎት፤ ከፌዴራል ፖሊስ፤እና ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተቀነባበረ፡፡ ፊልሙ ማስረጃዎችን በመቅረብ እያንዳንዱ ተጠርጣሪ የእስልምና ሃይማኖትን መጋረጃ በማድረግ የአልቃይዳንና የአልሸባብን እቅድ በኢትዮጵያ ለመተግበር ያደረገውን እንቅስቃሴ ያስረዳል›› ይላል፡፡
ለ13 ሴኮንዶች ቀስ እያለ በጽሁፉ ምስል ይተካና ያለአንዳች ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የአንድ ‹‹ሽብርተኛ›› ተብሎ የተፈረጀ ዜጋ ገጽታ በጥቁር ግድግዳ ፊት ለፊት ቀስ እያለ ተመለካቹን በሚያስደነግጥና በሚያስፈራራ መልኩ ለ8 ሴኮንዶች ብቅ ይልና እያዘገመ ወደ ቀኝ ይሄዳል፡፡ይህ በፎቶሾፕ ምስሉ የተቀነባበረውና ቆርጦ የተቀጠለው ሰው አውሬ፤በረኸኛን እንዲመስል ቃሉን በለሰለሰና በረጋ መንፈስ ሙስሊም በሆኑና ባልሆኑ መሃል ‹‹ጂሃዲ›› ያለ ልዩነትና በሕብረተሰቡ ውስጥ የሌለ አመለካከት ለማስያዝ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ድራማ ነው፡፡ ይህን ዘጋቢ ያሉትን ማስረጃ ያዘጋጁት እርባና የለሾች እራሳቸውና የናጣቸውን የፍርሃት ድባብ በማቅረብ ለምን ሕብረተሰቡን የማይፈራውን ፍርሃት እንዲፈራ ያደርጉታል፡፡
‹‹ማስረጃ›› ተብሎ የሚደመጠው የያዘው ‹‹ኑዛዜ›› (በአብዛኛውከሁለት አለያም ከ3 አረፍ ተነገር ያልዘለለ፤ወንጀለኞች እንዲመስሉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረባቸው ሆኖ ተከሳሦቹ የጥፋተኝነት እምነታቸውን ያረጋገጡበት ቢባልም በመርማሪው በኩል ምን እንዳለም ሆነ እንደጠየቀ አንዳችም ቃል አይሰማም) በአሜሪካን መንግስት የዓለም አቀፍ ሃይማኖቶች ነጻነት ኮሚሽን የተጠቀሱት 29 ተከሳሾች ዘገባ ግን ከተባለው አንዱንም አላካተተም፡፡ (እነዚህ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ሰዎች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይኼው ፊልም ለሕዝብ እንዳይቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ሰሚአጥቶ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ አይነት እየተላለፈ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ አሳፋሪ መንግስታዊ የፍትህ ጥሰት የት ይታያል? ከቃል አሰጣጡ የሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ጂሃዲስቶች የኢ ቲ ቪ ትርኢት ተከትሎ፤የቪዲዮ ቁራጭ ትእይንት ይከተላል፤ ወጣቶች (ሙስሊም አሸባሪዎች እንዲመስሉ ከሌላ ቪዲዮ ላይ የተቀነጨበ) ከአንድ ነገር ለማምለጥ ሲሸሽ ይታያል፡፡ ከኢንተርኔት የተለቃቀሙ ሌሎች ምስሎችም ተቆርጠው በመቀጠል፤በጭንቅላታቸው ላይ ስካርፍ ያሰሩና መሰወሪያ ፊታቸው ላይ ያከናነቡ በዓለም ላይ በተለያየ ወቅት ሽብርተኞች የተነሱትን ቪዲዮ መጠቀሚያ በማድረግ ቦታውና ጊዜው የማይታወቅ ፊልም ቀርቧል፡፡
የጽሁፍ መግለጫው ተከትሎ ይመጣና በድምጽም ‹‹ቦኮ ሃራም በኢትዮጵያ›› በሚለው ይታጀባል፡፡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ተሰልፈው ይታያሉ፡፡ አንድ ወጣት ሙስሊምም በአንድ ቦታ ቆሞ ለተሰበሰቡት ‹‹ሙስሊሞች አሸባሪ፤ ወንጀለኞች፤ እና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ይፈልጋሉ ተብለን ተወንጅለናል›› ይላል:: በርካታ ሰዎች ጥምጣም ያደረጉና መሳርያ ያነገቡ ሰዎች መልክና ሁለንተናቸው ጨርሶ ኢትዮጵያዊያን የማይመስሉ፤ አንድ ጢሙን ያጎፈረ ሰው ሲናገር ሌሎች ጉድጓድ ሲቆፍሩና መሳርያ ከተቀበረበት ሲያወጡ፤ ዓላማችን የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ነው በማለት ሲነጋገሩ ይደመጣል፡፡ ከዚሁ ጋር በመንግስት ‹‹ሽብርተኞች የሚል የማደናገሪያ ስም የተለጠፈባቸው የ29ኙ ተከሳሾች ምስል በቴሌቪዥኑ መስኮት ላይ ይመላለሳል፡፡ ይህም የሚነገረው ጉዳይ አባሎች ናቸው ብለን እኛ ተመልካቾች እንድናምን ሆን ተብሎ የተደረገ ቢሆንም ተመልካቹ ግን ከማመን ይልቅ በስህተት ልጆች ለጨዋታ ያቀነባበሩትን ፊልም መሰል ዝብርቅርቅ መጨረሻና መጀመርያ የሌለው በማለት በሚገዘው መንግስት ተራ ወንበዴነት አዝኖ ታዝቧል፡፡ በቃላትና ግድ የምታምኑትን እመኑ በሚል የማስገደጃ አካሄድ ቀረበ እንጂ ማስረጃ ተብሎ በምንም መልኩ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ የግፍ ተከሳሾቹ ምስል ከየቦታው ተለቃቅሞ ሽብርተኞች፤ የሽብርተኞች ጥፋት በሚለው ቃል ብቻ በመታጀቡ ንጹሃኑ ያልሆኑትን ያደርጋቸዋል ብሎ የሚያምን ገዢ ዲክታተራዊ የቃዠ መንግስት ብቻ ነው፡፡
የሕግ የበላይነት ወይስ የመሃይሞችና የሕግ የበላይነት
የገዢው ፓርቲ ሰዎች በተደጋጋሚና አፋቸው በተከፈተ ቁጥር ምን ያህል ሕገመንግስቱን እንደሚያከብሩትና ለሕግጋቱም የቱን ያህል ታማኞችና ተገዢዎች እንደሆኑ ይቦተልካሉ፡፡ ባለፈው ሴፕቴምበር የፕሮፐጋንዳው ሂትለራዊው ሚኒስቴር በረክት ስምኦን ስለ መለስ መታመምና መሞት በየቀኑ ታላቁን የወቅቱን ውሸት ሲዋሽ ሲዋሽ ደሞ ሲቀላምድ ደሞ ሲቀላምድ፤ ችግር የሌላ መሆኑንና በሕገመንግስቱ መሰረት መተካካቱ እንዳለ ነው የሚለውን ያልተቃኘ ቱልቱላውን ሲነዛ ከረመ፡፡ እንደ መገናኛ ሚኒስትርነቱ ስምኦን የ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት››ን መተላለፍ ያዘዘው እሱ ነው፡፡ ማንንም ሰው የሚያስገርመው ግን እነዚህ ለሕገ መንግስቱ መከበርና ልዕልና ቆመናል በማለት በየጊዜው ከበሮ የሚደልቁት ማን አለብን ባይ ዲክታተሮች እነዚህን የፈጠራ ክሳቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉትን ንጹሃን ዜጎች ከችሎቱ አስቀድሞ እንዲህ አይነቱን ፓርቲያዊ የስልጣን ማክረሚያ ፍርዳቸውን ማስተላለፋቸው መብት መጣሳቸው መሆኑን አንገታቸው ላይ የተሰካው ቅል አያስታውሳቸው ይሆን? ድርጊታቸው የሼክስፒርን አባባል አስታወሰኝ፡፡ ‹‹ዲያቢሎስም ለራሱ መጠቀሚያ መጽሃፍ ቅዱስን ይጠቅሳል›› ያለውን፡፡ እነዚህ ሰዎች ያላዋቂ ሳሚ ናቸው ወይስ የሰይጣን ቁራጮች? ላለፉት በርካታ ዓመታት በተደጋጋሚ እንዳልኩት በኢትዮጵያ ላለው አረመኔ መንግስት ስለ ሕግ የበላይነት ማውራት ለዲያቢሎስ መጽሃፍ ቅዱስን እንደማንሳት ነው፡፡ አይግባቡምና፡፡ ሕገመንግስቱ እግር አውጥቶ እየዳመጣቸው እንዲገባቸው ሊያደርግ ቢሞክር እንኳን ጨርሶ ድንጋያማ ሕሊናቸው ተፈረካክሶ ያልቃል እንጂ አይገባቸውም፡፡
በ‹‹ሽብርተኘነት የተጠረጠሩት›› ሙስሊሞች ጉዳይ እና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ላይ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ጉዳይ ሊተኮርበት የሚገባው 3 ነጥብ አለ፡፡ 1) እነዚህ ተከሳሾ ቅድም ችሎት ታሳሪዎች ስለሆኑ በሕገመንግስቱ ላይ በተደነገገውና በሌሎችም ሃገሪቱ ከገባችባቸው ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች አኳያ መብታቸው ሊከበርላቸው ግድ ነው፡፡ 2) እነዚህ ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን በፈቃደኝነትና በነጻ አለመስጠታቸውን የሚያረጋግጠው በካቴና ቀርቦ የነበረው ተጠርጣሪ ሲሆን ሌሎችም ቢሆኑ አያያዛቸውና ያሉበት ሁኔታ ሕጋዊ ስርአትን የተከተለ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ 3) ሁሉም 29 ታሳሪዎች የፖለቲካ እስረኞች ናቸው፡፡ ሕገመንህስቱን ለማክበር በሱም ለመመራት ጨርሶ ፈቃድ የሌላቸው መሪዎች፤የጣሳሪዎቹን ሰብአዊ መብት ያከብራሉ ማለት የማይሞከር ነው፡፡የሃገሪቱ መሪዎች ባላቸውና በሚያሳዩት ተግባራቸው ምን ያህል ከእውቀትና ከሰለጠነው ፖለተካ ጋር እንደማይተዋወቁ ነው በማሳየት ላይ ያሉት፡፡ እነዚህ ገዢዎች ከመሰረቱ ጀምሮ ከተንኮልና ከግፍ በደል በስተቀር አንዳችም ተግባር አለመፈጸማቸውንና ማንኛቸውንም ጉዳይ ይተገብር የነበረው የሞተው አለቃቸው እንደሆነ ሳያፍሩ በመናገር የራሳቸውን ብቃት የለሽ መሆን አውጀዋል፡፡ ማንም ተከሳሽ በፍርድ ሂደት ወንጀለኛ እስካለተባለና እስካልተፈረደበት ጊዜ ድረስ ነጻና ንጹህ ነው፡፡ በምንም መልኩ በግዳጅ የተገኘ ቃል ለማስረጃነት ሊቀርብ አይችልም፤ ድርጊቱም ዓለማቀፋዊ ድንጋጌዎችን ያልተከተለ ነው፡፡ ሰብአዊ መብትን ይገረስሳል፤ የፍትህን የበላይነት ይቃረናል:: 4) በጣም የሚያሳዝነው ቀልድ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በኢቲቪ እና በሬዲዮ ድርጅቶች ላይ ያን የተቀነባበረና ቆርጦ የተቀጠለ የማፍያ አካሄድ ጨርሶ እንዳይተላለፍ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ፤ እነማን አለብን ‹‹እኛው የፈጠርነው ዳኛም ሆነ ችሎት ሊከለክለን አይችልም›› በማለት ትእዛዙን ጥሰው ሲያስተላልፉት፤ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ባለመፈጸሙና አግባብም ስላልሆነ የቀረቡትን ማስረጃ የተባሉትን ሁሉ አመኔታ ስለማንሰጣቸው ተቀባይነት አይኖራቸውም›› በማለት እንኳን ዋጋ ቢስ በማድረግ ፈንታ ችሎቱና በችሎቱ ወንበሮች ላይ የተጎለቱት እራሳቸው እርባና ቢስ ሆነዋል፡፡
ተስፋ የቆረጠ አምባገነንነት እና የዕጣቢ መውረጃ ቱቦ ፖለቲካ በዚህ ዶኩመንታሪ በኢትዮጵያ ያሉት ጨቋኝና ርህራሄ ቢስ ገዢዎች ከምንም በታች አዘቅዝቀው ወርደው ውረደታሞች መሆናቸውን ገሃድ ከማውጣታቸውም አልፎ የዝቃጭ መፈሰሻ ቱቦ ፖለቲከኛነታቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡ አንድ ብቸኛ ሆኖ ሊታይና ሊረጋገጥ የሚችለው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሽብርተኛ እነሱ ገዢዎቹ ብቻ መሆናቸው ነው፡፡በ‹‹አኬልዳማ ገዢው መንግስት ሆነ››ባለው መሰረት በአሸባሪዎች 131 ጥቃት ተፈጽሟል፤339 ዜጎች ተገድለዋል፤363 ቆስለዋል፤25 ደግሚ ተጠልፈው ለሞት ተዳርገዋል:፡ ይሁንና በራሱ በመለስ ዜናዊ ይሁንታ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን እንዳጣራው ምርጫ 2005ን ተከትሎ በጥቂት ቀናት ውስጥ በመለስ ዜናዊ አመራርና ትዕዛዝ መሰረት፤ 193 ሰላማዊ ዜጎች አንዳችም መሳርያ ያልነበራቸው 193 ሲገደሉ፤763ቱ ደግሞ ለከፍተኛ ቁስለት ተዳርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ ባረጋገጠው መሰረት የስለላ ሰራተኞችና የመንግስት ጦር አባላት አተኳኮሳቸው ሰልፉን ለመበተን ሳይሆን ለመግደል በመሆኑ ሁሉም አናታቸውንና ደረታቸውን እየተመቱ ነው የሞቱት፡፡ በሴፕቴምበር 2011 ዓለም በሙሉ የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎች፤ በሴፕቴምበር 16 2006 በአዲስ አበባ ከተማ 3 ቦምቦች አጥምደው ካፈነዱ በኋላ ፍንዳታውን የፈጸሙት ኤርትራዊያንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት አባላት ናቸው በማለት ሰበብ አድረጓቸዋል:: በዚህም ፍንዳታው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ለስብሰባ በመጡበት ወቅት መከናወኑ የጉዳዩን ተአማኒነት አጣጥሎታል፡፡ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ጉዳዩን በራሱ ባለሙያዎች ካስመረመረውና ካጣራ በኋላ ጣቱ የጠቆመው ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ሆኗል፡፡ ገዢዎቹ ስልጣን ወንበር ላይ ከተፈናጠጡ ጀምሮ የተካሄዱት ግድያዎች ቢቆጠሩ ከብዙ ሺሆች በላይ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ መንግስት ነኝ ባዩ በራሱ አፈንድቶ፤ አጥምዶ፤ ደብቆ፤ አግኝቶ ያፈነዳውን አድራጊዎቹ ሌሎች ናቸው ብሎ አመልካች ጣቱን ወደ ሌሎች ሰዎች ሲዘረጋ ሌሎቹ ሶስቱ ያቶች ወደ ራሱ ማመልታቸውን መገንዘብ አልቻለም፡፡
ጂሃዳዊ ሃረካት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ስም ለማጥፋት፤ለመኮነን፤ለማዋረድ፤ለመከፋፈል፤ ሆን ተብሎ የተፈበረከ ነው፡፡ ለዘመናት ጸንቶ በፍቅርና በመተሳሰብ የኖረውን የሁለቱን ሃይሞኖቶች ሂደት ለመበጥበጥ የተቀመመ መርዝ ነው፡፡ እዚህ ግባ የማይባል ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በዚህም ሊፈጠር የተሞከረው በሙስሊሙና በእስልምና ሃይሞኖት ተከታዮች መሀላ መለያያት ለማስረጽ ነው፡፡ ከዚህም ሙስሊሙን ዳግም ወደ ፖለቲካና መብት ጥየቃ እንዳይነሳ፤ በፍርሃት ለማሰር፤ለመወንጀልና ለማሰር መንገድ ለመክፈት ከኤኮኖሚ፤ ህብረተሰባዊ ግንኙነት፤ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለመለየት የታቀደ ማስደንበሪያ ነው፡፡‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት እስልምናን የመፍራትና ደንብሮ የማስደንበር፤ ፈርቶ የመስፈራራት፤ ያለቀንና የበቃውን የገዢነት ስልጣን የማቆያ ዘይቤ ነው፡፡ አይሆንም አልሆነም ይልቅስ ሁሉንም ያስተባበረ የገዢዎች ግፍ ሆኗል!
በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!
*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):
(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!
በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)
ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡
ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ በፍቅር አብረን ኑረናል፤ የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

One Response to ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

    Tuesday, February 26, 2013


    ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል

    #Ethiopia #StopCensorship
    From  Zone 9  blog
    ለምዕራባዊያኑ የመጨረሻ  ወር በሆነው ዲሴምበር ወር መጀመርያ በሀገረ አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን ጦማሪ እና እስክንድርነጋን ለማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነበር፡፡ በመድረኩ ላይ ስለ እስክንድር ነጋ የተናገሩት ተዋናይ ሊዬቭ ሽሬ የይበር እና ጸሐፊ ካርል በርንስቴይን ነበሩ፡፡ በርንስቴይን  ከ40 ዓመታት በፊት የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢ ሆኖ በሚሠራት ወቅት ከባልደረባው ቦብ ዉድወርድ ጋር በመሆ ን በአሜሪካ መንግስት ታሪክ ትልቅ የተባለውን እና የዋተርገቱ ቅሌት በመባል ሚታወቀውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ያሳተፈ የሙስና ቅሌት አጋልጠዋል፡፡ በነዚህ ሁለት ዘጋቢዎች ታሪካዊ ማጋለጥ ምክንያት በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ሆኗል፡፡
    የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሳሌ ተደርጋ የምተጠቀሰው አሜሪካ በወቅቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ አቅም የሚያንሳት ሀገር አልነበረችም፡፡ የፖለቲካ ባህሏም (በጥቅሉ) ተጠያቂነትን የሚያበረታታ እና ሙስናን የመሰሉ ተግባራትን አፀያፊ አድርጎ የሚቆጥር ነበር/ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም ሥርዓት መሐከል ግን እንክርዳድ አይጠፋውም፡፡ እናም መደበኛው የተጠያቂነት ሥርዓት ያልደረሰበትን ማማ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ  (fourth organ of government) በመባል የሚታወቀው ሚዲያ አጋለጠው፡፡
    ነጻ የሆኑ መገናኛ ብዙኃን መኖር እና ዜጎች ሐሳባቸውን መግለጽ እና መወያየት መቻላቸው የመንግሥትን እና የባለሥልጣናቱን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁልፍ መሣሪያዎች ናቸው፡፡
    እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት እያንዳንዱ የመንግሥት መዋለ ነዋይ ለሚፈለግለት ዓላማ መዋል አጥብቆ የሚፈለግ ነገር ነው፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ በደሃ ሀገራት FreddomofSpeech.phpስልጣን የሚይዙት ሰዎች/የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን አንድም የራሳቸውን ግለሰባዊ ችግር ከሀገሪቱ ችግር በማስቀደም ወይንም በስግብግብነት አልፎ አልፎም ደግሞ ከብቃት ማነስ ሀገራቸው እጅግ አድርጋ የምትፈልገውን መዋለ ነዋይ ያባክናሉ፡፡ ይባስ ብሎም አብዛኞቹ ደሃ ሀገራት የሚመሩት ሁሉንም ነገር መቆጣጠር በሚፈልጉ እና ለምንም አይነት ነጻነት እና መብት ደንታ በማይሰጣቸው መሪዎች  (totalitarian) ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገር ሃብት ሲመዘበር እና አለአግባብ ጥቅም ላይ ሲውል ለምን ብሎ የሚጠይቅ አካል አይኖርም፡፡ ካለምፍዳው እጅግ ብዙ ይሆናል፡፡
    የሕዝብ ውክልና የሌላቸው/የሚጎላቸው የድሃ ሀገራት መሪዎች ስልጣን ላይ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለመቆየት ሀገራቸው ላለባት ምጣኔ-ሃብታዊ እና ሌሎችም ችግሮች እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ አብዛኛዎቹ መሪዎች ሕዝብ በከፈለው ግብር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙኃንን የራሳቸውን ተረክ ለመፍጠር ይጠቀሙበታል፡፡ እነሱ ከሌሉ ሀገሪቷ የምትገባበትን ‹ሲኦል›  ይሰብኩበታል፡፡ ይህ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ምንም ዓይነት የተለየ ተረክ ለሕዝብ እንዲደርስ አይፈቅዱም፡፡ የሐሳብ አሀዳዊነትን በሕዝብ ላይ ለመጫን ይመቻቸው ዘንድ የበይነ-መረብ ማጥለል፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ጋዜጦች፣  መጽሔቶች ይዘጋሉ፤ ጋዜጠኞችን ያዋክባሉ፣  ያስራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ሀገርን የሚጠቅም ነው ብለው የሚያወጧቸው ምጣኔ-ሀብታዊ (ሌሎችም) ፖሊሲዎችን የተለየ ምልከታ ሰጥቶ ጥቅሞቹን እና ጉድለቶቹን ተንትኖ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ያላቸውን መጣጣም አመዛዝኖ ለሕዝብ የሚያቀርብ አማራጭ እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡ እናም ፖሊሲዎች መታረም ከሚችሉት ህፀፆቻቸው ጋር በሰሠሯቸው ሰዎች ተደጋግመው ከተወደሱ በኋላ ወደሥራ ይገባሉ፡፡
    እነዚህ መሪዎች አንድ መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮን ዘንግተዋል፡፡ ማንኛውም ጤነኛ ሰው የሚቀበለውን መረጃ እንደተሰጠው አይውጠውም፡፡ ሁልግዜም ባይሆን ባመዛኙ፣  የሰው ልጆች የሚሰጣቸውን መረጃ ማመዛዘን ይፈልጋሉ –  በተለይም ድጋፍ መስጠት/አቋም ሊይዙበት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሲሆን፡፡ አማራጭ ትንተና ያጡ ዜጎ ችአንድ አንዳንዶቹ (ጥቂቶቹ) የራሳቸውን ትንተና በመስጠት አቋም ሲወስዱ አብዛኞቹ ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞ የሚበቃ አቋም ለመውሰድ በቂ ትንተና ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡በመጨረሻም ፖሊሲውን ተፈፃሚ ለማድረግ የሕዝብ ተሳትፎ/ድጋፍ አጥሮናል ብለው የሚያማርሩ የመንግሥት ድምፆችን መስማት እንጀምራለን፡፡
    ምጣኔ ሃብት እና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት
    እ.አ.አ 1989 ድሬዝ እና ሴን የተባሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች ባያደረጉት ጥናት ነጻ መገናኛ ብዙኃን ባለበት ሀገር አንድም ግዜ ረሀብ ተከስቶ እንደማያውቅ ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም ሲደግፉ ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለባቸው ሀገራት መንግሥታትን (ዴሞክራሲያዊ ባይሆኑም እንኳን) ከሕዝብ የሚመጣ ጫና ውስጥ ስለሚከታቸው እና ይህንንም ለማስወገድ ሲሉ ቀድመው የሕዝብን ጥያቄ የሚመልስ እርምጃ ስለሚወስዱ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ኢሻም፣ ካፍ ማን እና ፕሪቼት የተባሉ ምሁራን እ.አ.አ  1997 ባደረጉት ጥናት መሠረት ደግሞ ግለሰባዊ ነጻነቶች  (ሐሳብን የመግለፅን ጨምሮ) ማክበር በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ምጣኔ-ሃብታዊ ውጤት  (Project’s Rate of return) እስከ 20 በመቶ ያክል ድረስ ይጨምረዋል፡፡ እንደነዚሁ አጥኚዎች ትንተና መሠረት ግለሰባዊ መብቶችን  (ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ/የመሰብሰብ ነፃነት፣ ሐሳብን በነፃነት የመያዝ እና የመግለጽ፣ ሕዝባዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት የመሳተፍ እና ነፃ ማኅበር ማቋቋም) አለማክበር በእኩል መጠን ከሚከሰት የዓመታዊ ምርት መቀነስ፣ የበጀት እጥረት ወይንም የወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ ከሚያጋጥም ንዝረት ባልተናነሰ ሁኔታ በመንግስት የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ውጤታነት ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡
    እንደ በመንግስት የሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ባይሆንም በግል ባለሀብቶች እና ተቋማት የሚካሄዱ ንግዶች ሐሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ለገበያ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች የኅብረተሰቡን ደኅንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል እንዳይሆኑ ከፍ አድርገው ይጠነቀቃሉ፡፡ በግድየለሽነት ወይንም በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚያደርጉት ሙከራ የህብረተሰቡን ደህንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ዕቃ ወይንም አገልግሎት ቢያቀርቡ ነፃ መገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡
    የሳንሱርዋጋ
    የሐሳብ ብዝኃነትን በመቆጣጠር ሕዝብ እነሱ የሚሉትን ብቻ እየሰማ እንዲነዳ የሚፈልጉ መንግሥታት ሐሳብን ለማፈን ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ሐሳብ ለማፈን ከከሚጠቀሙባቸው መንገዶች በይነ መረብን ማጥለል እና ጦማሮች እዳይከፈቱ ማገድ፣ በይነመረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ መሰለል እና በሳተላይት የሚተላለፉ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች ሞገዶችን መከልከል ይጠቀሳል፡፡
    የአውስትራሊያ መንግስት  በ2009 ዓ.ም ሊተገብረው ያሰበው የበይነ መረብ ማጥለልን በተመለከተ ዴቪድ በርድ የተባለ ጦማሪ እንደጻፈው በበይነ መረብ የሚተላለፉ መረጃዎችን ለማጥለል ጥቅም ላይ የሚውሉት ቴክኖሎጂዎች የበይነ መረብ አገልግሎት ፍጥነትን ከ2 በመቶ እስከ 70 በመቶ ይቀንሳሉ፡፡ የማጥለል ሥራውን  ‹በውጤታማነት የሚያከናውኑት› ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ፍጥነቱን በደንብ የሚቀንሱት ናቸው፡፡
    ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ደግሞ ኒውዮርክ ታይምስ አንድዜና ለኢትዮጵያዊያን ይዞልን ወጥቶ ነበር፡፡ ፊንፊሸር የተባለ በይነ መረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ ስለላ ለማድረግ የሚያስችል የረቀቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀሙ ከታወቁት  10 ሀገራት አንዷ ሀገራችን መሆኗን፡፡ እንደዘገባው ቴክኖሎጂውን ለመግዛት ከ350ሺህ  በላይ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ቁጥር አንድ ጠላቷ ድህነት ለሆነ ሀገር ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ ዜጎች ላይ ለመሰለል ይህን ያህል ወጪ ማውጣት እውነትም አሀዳዊ ተረክ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደሚኬድ ማሳያ ነው፡፡
    በሳተላይት የሚተላለፉትን ሬዲዮ እና የቴልቪዥን ስርጭትን ለመደገፍ ምን ያህል የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልግ እና እሱም ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ መገመትም ቀላል ነው፡፡
    ምንም እንኳን አከራካሪ ቢሆንም ዜጎች በነጻነት ሲያስቡ እና ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ሲችሉ አዳዲስ እና ውጤታማ የንግድ ሐሳቦች ማፍለቅ ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ ይህም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መንፈግ ከሚያስከፍሉት ቀጥተኛ ያልሆኑት ዋጋዎች ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡

    የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?

    From Borkena blog/ ቦርከና
    ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ  ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።
    እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ  የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን –ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት  ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት  የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
    የህገ-መንግስት ጉዳይ እና የዜጎች መብት ፋይዳ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው እንዳይባል፤ ትግል ጀመርንም ጨረስንም የሚሉባቸውን ቀናቶች በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ ናቸው። እንዲያውም ያለባቸውን የስነ-ልቦና ችግር ከሚያመላክቱ ነገሮች  እንደኛው ይሄው ነው። ህወሃት ስልሳ ሺህ  ሰው ሰዋበት የሚሉትን በዓላቸውን የሚያዳንቁትን እና ሰው እንዲያዳንቅላቸው የሚፈልጉትን ያህል ለኢትዮጵያ ነጻነት ከጎጠኝነት በጸዳ በንጹህ የሃገር ፍቅር ስሜት የወደቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ እንዲነሳም እንዲታወስም እይፈልጉም። ታሪኩ ሲነገር ያሳንሳቸዋላ!የሃሳብ ነጻነት ወደሚያፈኑበት ጉዳይ ስመለስ -የሚያፍኑበት እና ሃሳብ እንደጦር የሚፈሩበት ጉዳይ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ መሳሪያ እንቆ የተኮፈሰ የፓለቲካ ስብዕናቸውን የሚያኮስስ ስለሚመስላቸው። እደፊኛ የሚነፉትን ፕሮፓጋንዳ የሚያስተነፍስ ስለሚመስላቸው። የሃሳብ ልውውጥ ላይ ያለ ስለት ስለሚያስፈራቸው። አንግበው ለተነሱት የትምክህት እና የበላይነት ግንባታ ዓላማ እንቅፋት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይመስለኛል። የእምነት ነጻነትም እስከመንጠቅ የሄዱበት ምክንያት ከፍራቻ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የፍርሃት ገጹ ይለያያል።  የህወሃት መራሹ መንግስት ፍርሃት በአንድ በኩል በጥጋብ እና በማናለብኝነት የተከናነበ ይመስላል በሌላ በኩል ደሞ በልማት ዲስኩር ተከልሎ ከዲስኩሩ በስከጀርባ በምናቡ የሚስላቸውን “ጸረ-ልማት ሃይሎች” (ኢትዮጵያውያኖች እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ልማት ጠላቶች?) እንደምክንያት እየተጠቀመ የአፈና የሚጧጡፍበት የሞራል ፈቃድ አብረውት ክሚሰሩት “እህት ድርጂቶች”  ይወስዳል፡፡ በህወሃት “የማይበገር ጀግንነት” ውስጥ ያለው እውነታ (‘ሪያሊቲ’) ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብትን እስከመፍራት የሚያደርስ ፍርሃት ነው። የደህንነት ተቋማቱም እወቃቀር የሚሰማቸውን የፍርሃት ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ ይመስላል።ስለ ህወሃቶች እና ስለገነቡት የማፈኛ ተቋም የራሴም የሰዎችም ተሞክሮ አለኝ። ገና በልጂነት ባደኩባት የደሴ  ከተማ ፓሊስ(ህወሃት ለአፈና ተግባር ካሰለጠናቸው ውስጥ ነበር)   አንዱን ያለ እግባብ እያንገላታ ለማሰር ዱብ እንቅ ሲል (እንደዛ ይደረግ የነበረው ደሞ ለሃገሩ በብሄራዊ ውትድርና ዘምቶ የመጣ ዜጋ ነው-የገባው የሚመስለው የፖለቲካ ሁኔታ እንገቱን ባያስደፋው ኖሮ የዛን ለፍዳዳ ፖሊስ ጥርሱን የሚያራግፍ ጎበዝ ነበር። አውቀዋለሁ ) ነገሩ ከንክኖኝ ከፖሊሱ ጋር “የምን እደረገህ” ያደረገውም ነገር ካለ በስነ-ስርዐት ውሰደው የሚል ሙግት ውስጥ ገባሁ። ከዚያ በኋላ ፖሊሱ ልጁን ትቶ ወደኔ ዞረ። ዱላም ጀመረ። ታሳሪው እኔ ሆንኩ፡፡ እና ሂድ እልሄድም ውዝግብ ተጀመረ።  ጓደኛየ ታደሰ ባየ( ፌስ ቡክ ላይ አለ) በዛ በዝናብ ተንበርክኮ ሁሉ ለመነው ፓሊሱን፡፡ እኔ ደሞ እንኳን ልለምነው እንዴት ድንጋይ እንደሆነ በተጋጋሚ እነግረዋለሁ። የመምታት አቅሙን ተጠቅሞ ያ ሁሉ የፖሊስ ዱላ ወረደብኝ። በመጨረሻ ላለመታሰር ጨለማውን ምክንያት እድርገን ሁለታችንም አመለጥነው። የተመታሁት ብዙ እንደነበረ የገባኝ ግን በነገታው  መሄድ እቅቶኝ ቀኑን አልጋ ላይ ሳሳልፍ ነው።  ያኔ ተናድጄ ስለነበር ምንም አልተሰማኝም።   ሶስት ቀን ያህል ሳያስነክሰኝ አልቀረም።
    Eskinderኮተቤ እያለሁ ደሞ ሮብ  ሮብ መብራት ይጠፋ ነበር። በዚያ ምክንያት ረቡዕ ማታ አካባቢ ጥናት የለም ። ወክ ነው የምናደርገው። ወደ ገደራ እየሄድን ስናወራ የነበረውን ከኋላ ይሰማ የነበረ አስቁሞን መታወቂያችንን ከጠየቀ በኋላ እዚያው እካባቢ ወደ ነበረ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደን ተመዝግበን የሚጠይቁትን ጠይቀው ተመልሰናል።  ሌላ ጊዜ እንዲሁ አራት ኪሎ ላይ የከተማ አውቶብስ ይዞ የነበረ የትግሪኛ ተናጋሪ ሾፌር  በራሱ ስህተት እና ትክምህት ምክንያት ተሳፋሪውን ከአራት ኪሎ ይዞ ሚኒሊክ እካባቢ ወደነበረው ፓሊስ ጣቢያ ወሰደን። በትግሪኛ አወራ ከሰዎቹ ጋር። እኛ “ጥፋተኞች ሆንን።” የተማሪዎች ዲን ነው ጣልቃ ገብቶ ነገሩ ያለቀው።የሌሎችን ተሞክሮ በሚመለከት እዚያው ያደኩባት ደሴ ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ አፉን በደንብ ያልፈታ የህወሃት ታጣቂ እንድ ባዶ እጁን የነበረ ወጣት አሯሩጦ ከደረሰበት በኋላ ሰው እየተጯጯኽ የክላሹን አፈሙዝ ደረቱ  ላይ አድርጎ ተኩሶ ከገደለው በኋላ ክላሹን እንቆ እንደያዘ  ሲሄድ ያስቆመው ፓሊስ አልነበረም። ሌሎች ታጣቂዎችም ያሉት ነገር የለም። (በነገራችን ላይ ያኔ እስከማውቀው ድረስ የልጁ ገዳይ ለፍርድ እልቀረበም)እንደዛ እይነቱ የህወሃት ጭራቅነት በርሃ ባልነበሩት ዘመድ እዝማዶቻቸው ላይ ተጋብቶ “ምክንያታዊ” በሚመስል ሁኔታ  ስለፍትህ በሚጮሁ ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ቅጥ ያጣ ንቀት ማየት እሁን የተጀመረው እይነት ዘመቻ በበታችነት ስሜት በሚናጥ ስብናቸው እና እስተሳሰባችው ላይ የበላይነት እና የገዠነት ካባ ከሚደርብላቸው በስተቀር ትርጉም ያለው ጩኽት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። የማስጮህ ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም። ዛሬ ፌስ ብክ ላይ እንዲህ ያለ ዘመቻ ባለበት ሰዐት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ እስክንድር ነጋን በሚመለክት የነዚሁ የህወሃት ወገን የሚመስሉ ሰዎች ያደረጉትን ምልልስ ለአብነት እንዲሆን ያህል ከ’ሆም ፔጂ ላይ ስክሪን ሾት’ ወስጃለሁ፡፡
    ከዚያ ውጭ የህግ ስርኦት ያለበት ሃገር ቢሆን ኖሮ እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች ሃገር ውስጥ ያለው የሃሳብ ሙግት በጸጥታ ሃይል እና በ”ፍትህ አካላት” እየታፈነ ባዶ ሆኖ ሙግታቸውን እና የሃሳብ ክርክራቸውን ከውጭ ሃገራት ሰዎች ጋር ሲያደርጉ ማየት የህወሃት ደጋፊዎች እና ዘመዶች ባይሆኑ ኖሮ ሊያስገርም ይችል ነበር። ከታች በሊንክ ባስቀመጥኩት የዳንኤል ጽሁፍ የሂውማን ራይቱ ቤን ራውለንስ የእንግሊዝ መንግስት የዕርዳታ እሰጣጥ የሚተች የመጽሃፍ ሪቪው  አወጣ ብሎ  የእንግሊዝ መንግስት ትችት ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባው የሚል ጽህፍ አውጥቶ ብሎጉም ላይ ጭምር ለጥፎታል። የጽሁፉ ዓላማ ምን ነበር የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ እንደ ዳንኤል ያለው የህወሃት ፖለቲካ ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ሃገር ቤት በሚታተሙም ራሱ በፈጠረውም ብሎግ ላይ የመጻፍ ነጻነት ሲሰጠው ሌሎች ዜጎች (ለምሳሌ የዞን ዘጠኝ ብሎገር አባላት) የሚታፈኑበት ምክንያት ከላይ የገለጽኩት ነው። እፈናውን ተቃውሞ የሚደረገውን ተቃውሞ ያልተቀላቀልኩበት ምክንያት የሚጨምርላቸውን -ተዋጋን እያሉ ለሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ያኔ ልጆች ለነበሩት እና የደም ትስስር በሚመስል ምክንያት ብቻ እፈናን በምክንያታዊነት ለማስተባባል እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ለሚሞክሩትም ጭምር- ለትምክህታቸው  የሚጨምረላቸውን ሃሴት ላለመስጠት ነው። የዳኤል ፓስት
    ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነናዊነት ሌላ ዓለም ከሚስተዋለው በመሰረታዊነት የሚለይ እንደሆነ እምኖ ተቀብሎ የሚደረገው ተቃውሞ የህወህትን እምባገነናዊ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ እና ህወሃቶች በመንፈስም በፖለቲካም የማይጠቀሙበት እና ትምክህት የማይጨምርላቸው መሆነ አለበት ብየ ስለማምን ነው፡፡  በሌላ አንጻር ደሞ የሚደረገው ዘመቻ መሬት ላይ ያለ እና ለህዝቡ ስነ-ልቦና እና አስተሳሰብ ቅርበት ያለው ፣ በቀላሉ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ነው በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ያለው? ፌስ ቡክ ላይ ካለውስ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው ውጭ ስለ ህወሃት መራሹ መንግስት አፈና እና ቅጥ ያጣ እምባገነናዊነት የማያውቀም ምን ያህሉ ነው? ለ “ዓለማቀፉ” ማህበረሰብ ነው እንዳይባል ለዚሁ አፈና ለሚያደርሰው መንግስት ትብብር እና ርዳታ የሚሰጡት እነዚሁ ወገኖች ናቸው። ዳንኤል የእንግሊዝን የእርዳታ አሰጣጥ በመደገፍ የእንግሊዝን መንግስት የሚከላከል ጽሁፍ መጻፍ ደረጃ ላይ የደረሰበት ”የዲፕሎማሲ” ልምምድ ሳይሆን የፖለቲካ ትስስርንም ጭምር የሚያመላክት ይመስለኛል። ለሃወሃት የጥጸጥታ ሃይሎች ስልጠና እና ሎጂስቲክ የሚያቀርበው ማን ነው? ብዙዎቹ የህወሃት ፖሊሲዎች በርግጥ ከህወህት ብቻ የመነጩ ናቸው? “የመለስ” ራዕይን ጨምሮ?

    Monday, February 25, 2013


    በዋሽንግተንና አካባቢዋ ለምትገኙ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ የስብሰባ ጥሪ፤

    የኢትዮጵያ ጥንታዊት እናት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬም ከችግር ውስጥ ነች ያለችው። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ እጅግ የሚያሳዝንና ቤተ ክርስቲያናችንን ከመሰረቷ የሚያናጉEthiopian-Orthodox-Church-Holy-Synod ተግባራት እየተፈጸመባት መሆኑን በሀዘን እናስበዋለን። ይህ ከመንፈሳዊቷ ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትና ቀኖና በወጣና በማንለአብኝነት ስድስተኛ የፓትርያርክ ምርጫ በሚል የተያዘው ህገ ወጥ ሩጫም ለሕዝባችን የተሰወረ አይደለም።
    ይህንን በተመለከተ ህጋዊው ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔና የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ምዕመናን ሀላፊነትን የሚያስገነዘብ መንፈሳዊ መመሪያ ለመስጠት ለመጪው ማርች 3 ቀን 2013 ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል የዋሽንግተንና አካባቢዋ ሊቀ ጳጳስ መንፈሳዊ ስብሰባ ጠርተዋል። በዚሁ መንፈሳዊ ሰብሰባ ላይ በመገኘት የብጹዕነታቸውን መመሪያ እንዲቀበሉ
    በአክበሮት ተጠርተዋል።
    ቦታው – 1611 16ኛው መንገድ ኖርዝ ዌስት ዋሽንግተን ዲሲ – የቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤
    ሰዓት፦ የዕለቱ መንፈሳዊው ስነ ስርዓት ከተጠቃለለ ከ11 ኤኤም በሁዋላ ይሆናል።
    ቀኑ – ማርች 3 ቀን 2013 /እ.ኤ.አ/።
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።

    ትግሉ የሚጠይቀውን መሰዋእትነት ለመክፈል እኛም ዝግጁዎች ነን!

    ቅኝ ገዥዎችን በማሳፈር በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ተጋድሎ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረችውና በባርነት ስር ለቆዩ ሀገራት ፋና ወጊ የሆነችው ውድ ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ዛሬ በሀገር ውስጥ ወራሪ በሆነው ህወሃት/ወያኔ መዳፍ እጅ ገብታ በሁሉም ረገድ ከኢኮኖሚ እስከ ሰበአዊ መብት አያያዝ በአለም የመጨረሻዋ የሰው ልጅ መብት ረገጣ የሚፈጸምባት ተስፋ አልባ ሀገር ተብላ ተመድባ ትገኛለች።
    ይህችው የቀድሞዋ ኢትዮጵያ በክብርና በኩራት የአፍሪካ የነጻነት ፋናወጊ ተብላ የሚነገርላት፤ በዚህ ዘመን በባርነት አረንቋ እየኖረች፣ ህዝቧ የነጻነት ያለህና የትውልድ የድረሱልኝ ጥሪ ኤሎሄ ለወጣት ልጆቿ  እያቀረበች፣ እየተማጸነች አለች።
    ይህን ተከትሎ በሁሉም ግንባር ሀገር በቀል ወራሪ ህወሃት/ወያኔን ታግሎ ለማስወገድ እየተደረገ ያለው ትብብር የሚበረታታ ቢሆንም የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ና የአንድ ዘር የበላይነት ርዕዮተ ዓለምን አስወግዶ ነፃነት ከናፈቀው ህዝብ ጎን በመሰለፍ በሀገራችን የሰላም አየር በሁሉም ከተሞች እንዲሰፍን ለሚደረገው እልህ አስጨራሽ ጉዞ የምናደርገው እገዛ በቂ ነው ብለን አናምንም።
    ትውልዱ ለውጥ አያመጣም በሚል እስከአሁን የተደላደለውን ወያኔ፤ ከመንበሩ ፈንቅለው ሊጥሉት ዛሬ ራሳቸውን መሰዋእት ለማድረግ ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ፣ በታሪክ ማህደር ኢትዮጵያዊ ገድላቸው እንዲቀለምላቸው ቆርጦው የተነሱት የህዝባዊ ሃይል ታጋዮች ፤ የእማማ ኢትዮጵያን እንባ በእንባቸው ሊጠርጉ መከራና ስቃይን መርጠው መሰደዳቸውን ሰሞኑን በድጋሜ አስታውቀዋል።
    ህዝባዊ ሃይሉ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “ኢትያጵያዊነት እንደ ሸቀጥ የተሸጠበት የክፉ ቀን ውረደት ላይ እንገኛለን እና ከገባንበት የውረደት አዘቅት የመውጫ ጊዜው አሁን ነው፤ ነገም ሳይሆን ዛሬ ነው። ዛሬ በሃገራችን በወያኔ አምባገነናዊ እብሪት ያልታፈነ፣ ያልተዋረደና ያልተዘረፈ የሃገሪቱ ዜጋ አይገኝም። የወያኔ ሹማምንት በሃብት ላይ ሃብት፤ በድሎት ላይ ድሎት ሲጨምሩ፣ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ ግን መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መንገላታት፣ መታሰር፣ መደብደብና መገደል ሆኗል” ብለዋል ። ታዲያ እኛ ምን እንጠብቃለን?
    ሀገራችን ሀገር ሆና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ግንቦት 7 ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ከማንኛውም ሃይል ጋር ሆኖ ለድረሱልኝ ሀገራዊ ወገናዊ ጥሪ ደራሽ በመሆን በዛች ሀገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን በማስወገድ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታን ለማምጣት አምርሮ በመስራት ፍትህና ነፃነትን ከተጠማው ሕዝብ ጋር አብሮ ሊታገል ቃል በመግባት ለጥሪው ምላሽ ይሰጣል፡፡
    የማንኛውም የፖለቲካ/የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ወጣቱ፤ በተለይም አደገኛ በረሃዎችንና ባህሮችን በማቋረጥ ለመሰደድ ልብህ እየከጀለ ያለው የሃገራችን  ወጣት ሆይ! የመተባበሪያው ጊዜ አሁን ነው።  በውርደት እስከ መቼ ? ማንስ መጥቶ ሊታገልልን ይችላል? ስለዚህ በከንቱ ክቡር ህይወትን ከማጣት ስደትን አቁሞ ዘላለማዊ ክብር ወደ ሚያሰገኝለት የትግል ጥሪ ይቀላቀል ዘንድ ግንቦት 7 ንቅናቄም ጥሪውን ያቀርባል።
    በርግጥም ነው ድሎት ሳይሆን የህዝብ ስቃይ ጣርን፣ የሀገር ውርደትን ማየት አላስችል ያላቸው የህዝባዊ ሃይሉ የቁርጥ ቀን ወጣቶች፤ የጥቁር ደም ጥቁር አፈር የሰራቸው የአበው ልጆች የውርደትን ወላፈን፤ በማይቆምና በሚያቃጥል የትግል ወላፍን ሊመክቱት፣ ሊያስወግዱት፤ ተራራ፣ ጋራ ሸንተረሩን መርጠው ወያኔንን በሚገባው ቋንቋ ሊያናግሩት ሊጋፈጡት ቀናትን እየቆጠሩ ነው።
    የህዝብ ልጆች የከፈሉትና ወደፊትም የሚከፍለው ውድ መስዋእትነት የሌላ አምባገነናዊና ግፈኛ ሥርዓት መቋቋሚያ እንዳይሆን ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ተግባር በተናጠል ይሁን በ ጋራ በመሆን መሰዋእት በመክፈል አብሮ መስራት የግድ ነው ሲል ግንቦት 7 ንቅናቄም ያምናል።
    አምባገነኖች መውደቂያቸው ሲደርስ ሁሉም ነገር በቁጥጥራቸው ሥር ያለ ለማስመሰል መቅበጥበጣቸው የተለመደ ነው። የወያኔም መቅበጥበጥ ምክንያቱ መሠረቱ እየተናደ  በመሆኑ ነው። ቢቻለው የተፈጥሮ ቀመርን ሳይቀር በሱ መልካም ፈቃድ የሚከናወን መሆኑን ብናምለት ደስታው ነው። ይህ የሁሉም አምባነኖች የመውደቂያ ወቅት መለያ ባህርይ ነው።
    ስለዚህ ወያኔ ከሥልጣን ሳይባረር አንዳችም በጎ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሰብ አይቻልም። ስርአቱ ከገባበት የምቾት ማጥ ውስጥ በስብሶ ስለተቀመጠ ከቶ ጀሮዎቹ ለሰላማዊ ጥሪ ጮኸት የተደፈኑ ስለሆኑ፤ እያንዳንዷን ደቂቃ ሳንዘናጋ በንቃት ሁሉንም የተቃዋሚ ሃይላትን በማስተባበር ትግሉን የማቀጣጠያ ሰአት ላይ ነን።
    እኛ ግንቦት 7 ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ከማንኛውም ሃይል ጋር ሆነን  ለድረሱልኝ ሀገራዊ፣ ወገናዊ ጥሪ ደራሽ በመሆን፤ በዛች ሀገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን በማስወገድ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታን ለማምጣት አምርሮ በመስራት ፍትህና ነፃነትን ከተጠማው ሕዝብ ጋር በመቆም ለመታገል ዝግጁ መሆኑን ዛሬም ያሳውቃል።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

      Sunday, February 24, 2013

      በዘንድሮዉ ምርጫ ወያኔ የረጂም ግዜ አጃቢዎቹም ሊከዱት አንደሚችሉ በመነገር ላይ ነዉ ተባለ

      በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚደረገዉ የከተማና የወረዳ ምርጫ የወያኔ አጋር እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ከዚህ ቀደም ወያኔን አጅበዉ ምርጫዉን የብዙዎች ምርጫ ያስመሰሉ እንደ ራዕይ፤ ኢፍዴሃግ፤ መኢብንና ቅንጅትን የመሳሰሉ ፓርዎች ዘንድሮ ጭራሽ በምርጫዉ ላይ ላይሳተፉ ይችላሉ የሚል ወሬ አዲስ አበባ ዉስጥ እየነፈሰ መሆኑን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ በላኩልን ዜና ገለጹ። እነዚህና ሌሎችም የጋራ መድረክ እየተባለ በሚጠራው የፖለቲካ ስብስብ ዉስጥ ተሳታፊ የሆኑ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ ዝግጅት ማድረግ እንዲችሉ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ቀድሞዉንም ቢሆን ከአጃቢነት ዉጭ ምንም ማድረግ ከማይችሉበት የይስሙላ ምርጫ ሊወጡ እንደሚችሉ የየፓርቲዎቹ መሪዎችና በመናገር ላይ ናቸዉ፡፡
      እነዚህ ህዝባዊ ድጋፍና ተቀባይነት የሌላቸዉ ፓርቲዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዕጩዎችን ማቅረብ የግድ በሆነበት በዚህ የአካባቢ ምርጫ የአገሪቱን ሀብት እንደራሱ ንብረት ከሚቆጣጠረዉ ወያኔ ጋር መወዳደር ቀርቶ ለምርጫዉ ከሚያስፈልጋቸዉ የዕጩዎች ቁጥር ዉስጥ ከመቶ አምስቱን እንኳን ማቅረብ አለመቻላቸዉ ታዉቋል። ፓርቲዎቹም ይህንን በሚገባ ስለሚረዱ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርግላቸዉ ለገዢዉ ፓርቲ ለኢህአዴግ አቤቱታ ቢያቀርቡም ኢህኣዴግ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ጥያቄያቸዉን ሳይሰማ ቀርቷል።
      በዚህ የተነሳ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች በምርጫዉ ተሳትፈናል ለማለት ብቻ አንዳንድ ቦታ ላይ በጣት የሚቆጠሩ ዕጩዎች ቢያቅርቡም በከፍተኛ የገንዘብ ችግር የተነሳ በምርጫዉ ለመሳተፍ የሚችሉ ባለመሆናቸው የዘንድሮዉን ምርጫ የሚያዘጋጀዉ፤ የሚወዳደረዉና ከራሱ ጋር ተወዳድሮ የሚያሸንፈዉም ወያኔ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት ከ65 በላይ ፓርቲዎች ውስጥ ሃያ ስምንቱ ከምርጫ በፊት ውይይት ይቅደም ብለዉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ እራሳቸዉን ከምርጫው ማግለላቸው የሚታወቅ ሲሆን ዉሸት የማይሰለቸዉና በኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የተሞላው ምርጫ ቦርድ ግን 15 ፓርቲዎች በተወዳዳሪነት ተመዘግብዋል እያለ ህዝብን በማጣለል ላይ መሆን ታዉቋል።