Saturday, January 24, 2015

ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”


January 24, 2015
በኢትዮጵያ የመገናኛ-ብዙሃን ነጻነት ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰት
እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2015 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫን ካሸነፈ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና መረጃ የማግኘት መብትን በመገደብ በግል መገናኛ-ብዙሃን ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አባብሶታል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 60 ጋዜጠኞች ሃገር ለቀው የተሰደዱ ሲሆን ሌሎች 19 ጋዜጠኞች ደግሞ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ መንግስት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ህትመቶችን ዘግቷል፤ እንዲሁም አብዛኛዎቹን የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ስርጭቶች በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ኢትዮጵየዊያን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ጉዳዮችን በተመለከተ ነጻ መረጃ እና ትንታኔ የሚያገኙበትን እድል አጣቧል። በግንቦት 2007 በሚካሄደው ምርጫ መገናኛ-ብዙሃኑ ህዝቡን በወሳኝ ጉዳዮች ላይ በማስተማርም ሆነ መረጃ በመስጠት ረገድ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችሉ ነበር፤ እንዲሁም የመከራከሪያ መድረክ በመሆን ሊያገለግሉ ይችሉ ነበር፤ ይሁን እንጂ መንግስት በሃገሪቱ ላለው ብቸኛ የበላይነት የግሉን መገናኛ-ብዙሃን እንደ ስጋት አድርጎ በመውሰድ የግሉን መገናኛ-ብዙሃን፣ ነጻ ጋዜተኝነትን እና ተቺ ትንታኔን ለማጥፋት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም የከፋ ውጤት አስከትሏል።Ethiopian free press
የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ የሆነው የኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (Committee to protect Journalists) መረጃ እና የሂዩማን ራይትስ ዎች ጥናት እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ከኢራን በመቀጠል በዓለም ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞችን ለስደት የምትዳርግ ሀገር ሆናለች። የመንግስት አካላት አፋኝ ህጎችን መሰረት አድርገው ጋዜጠኞች በየወቅቱ ያሉ ክስተቶችን እና ጉዳዮችን አስመልከተው በሚሰሩት ዘገባ እና ትንታኔ ምክንያት በተደጋጋሚ ክስ ይመሰርቱባቸዋል፤ ፍርድ ቤቶችም ክሱን ተከትለው የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት እስክንድር ነጋን እና ርዕዮት ዓለሙን የመሰሉ ግለሰቦች በአዲስ አበባ እና በክልሎች የሚገኙ ተለይተው የሚታወቁም ሆነ የማይታወቁ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ጋዜጠኞች እየደረሰባቸው የሚገኘውን ፈተና የሚያሳዩ ምልክቶች ሆነዋል። ጋዜጠኞቹ በርካታ ስጋት ውስጥ የሚገኙ፣ ማስፈራሪያ የሚደርሳቸው፣ አልፎ አልፎም አካላዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው እና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የወንጀል ወይንም የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው፡፡ የፍርድ ቤት ክርክራቸው ፍትሃዊ የፍርድ ሂደትን የሚጥሱ አሰራሮች የሚታዩበት ሲሆን ፍርድ ቤቶቹም በያዟቸው ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው ውሳኔዎች ገለልተኛ እንዳልሆኑ የሚያሳይ ነው።
በኢትዮጵያ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የህትመት መገናኛ-ብዙሃን ከመግስት ጋር የቀረበ ትስስር አላቸው፤ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ከመንግሰት የተለየ አቋም እምብዛም አያንጸባርቁም።የግል የህትመት መገናኛ-ብዙሃን በርካታ ከቁጥጥር ጋር የተያያዙ ችግሮች ያጋጥማቸዋል እንዲሁም በደህንነት ሰራተኞች ተከታታይ ወከባ ይደርስባቸዋል፡፡ መንግስትን የሚተቹ የህትመት ውጤቶች በየጊዜው ይዘጋሉ፣ የበሰለ ትችት የሚያቀርቡ የህትመት ውጤቶችን የሚያትሙ እና የሚያከፋፍሉ አሳታሚዎች እና አከፋፋዮችም ተዘግተዋል፡፡ የመንግስት ፖሊሲዎች ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ጋዜጠኞች እና የቤተሰብ አባሎቻቸው ጭምር የጥቃት፣ የመታሰር እና የገቢ ምንጫቸውን የማጣት ዘላቂ ስጋት ላይ ይወድቃሉ፡፡ መንግስት አብዛኛውን የመገናኛ-ብዙሃን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ሲሆን የቀሩት ጥቂት የግል መገናኛ-ብዙሃንም በተለይ ለአሳሳቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሚሰጡት ሽፋን ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ የሚያደርጉ ያደርጋሉ ይህም እንዘጋለን ከሚል ፍርሃት የመነጨ ነው፡፡
ይህ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት ነጻ ጋዜጠኝነትን እና ትንታኔን ለመቆጣጠር እንዲሁም መረጃ የማግኛ መንገድን ለመገደብ የተጠቀማቸውን ዘዴዎች የሚዘግብ ነው፡፡ ሪፖርቱ ከ70 የሚበልጡ የአሁን እና የቀድሞ ጋዜጠኞችን እና የመገናኛ-ብዙሃን ባለሙያዎችን ቃለ-መጠይቅ በማድረግ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የሚገኝበትን አስከፊ ሁኔታ እና በዚህም ምክንያት ሃሳብን በመግለጽ ነጻነት እና መገናኛ-ብዙሃን ላይ የደረሰውን አሉታዊ ተጽዕኖ ይዘረዝራል፡፡
በስፋት በተዘገቡ ጉዳዮች ላይ ከዓለምዓቀፍ ማህበረሰብ የተሰነዘሩ ውግዘቶች ቢኖሩም የኢትዮጵያ መንግስት ለገለልተኛ የመገናኛ-ብዙሃን ድምጽ ምንም አይነት የመለሳለስ ምልክት አላሳየም፤ እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም የግል መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ በእጅጉ ተባብሷል፡፡ አስር ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ክስ የተመሰረተባቸው ጋዜጠኞችን ዝርዝር ተቀላቅለዋል እንዲሁም አምስት መጽሄቶች እና አንድ ጋዜጣ በመንግስት የዛቻ እና የማስፈራሪያ ዘመቻ ከተካሄደባቸው በኋላ እንዲዘጉ ተደርጓል፡፡ ዘመቻው በመንግስት በሚተዳደረው የቴሌቪዥን ጣቢያ የህትመት ውጤቶቹ ሽብርን እንደሚደግፉ አስመስሎ ማቅረብ፣ የህትመት ውጤቶቹን የሚያትሙ ማተሚያ ቤቶችን ማዋከብ፣ በህትመት ውጤቶቹ የማከፋፈል ስራ ላይ የመንግስት ጣልቃ ገብነት፤ እንዲሁም ከደህንነት ባለስልጣናት በርካታ ዛቻዎችን መሰንዘርን ያካትታል፡፡ ይህም በመጨረሻ በደርዘን የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች እና በርካታ የህትመት ውጤቶች ባለቤቶች ሃገር ለቀው እንዲሰደዱ እና ባለቤቶቹ የወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው በማድረግ ተከናወኗል። ፍርድ ቤቶች ሌላ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ ሳይቀርብ መንግስትን የሚተቹ ጽሁፎችን ብቻ መሰረት በማድረግ በሶስት የህትመት ባለቤቶች ላይ በሌሉበት እያንዳንዳቸው ከሶስት አመት የሚበልጥ እስር እንዲቀጡ ወስነውባቸዋል፡፡ የሌሎች የህትመት ባለቤቶች ክስም በሂደት ላይ ነው፡፡
መንግስት ከሚፈፅማቸው ትኩረትን የሚስቡ እስሮች በተጨማሪ መገናኛ-ብዙሃንን ለማዳከም እና ለመዝጋት ሌሎች በርካታ በግልጽ የማይታዩ የእጅ አዙር መንገዶችን ይጠቀማል፡፡ የደህንነት ሰራተኞች በአሳሳቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ የሚጽፉ ጋዜጠኞች ላይ ተከታታይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ያደርሱባቸዋል፡፡ እነዚህ ዛቻዎች ብዙውን ጊዜ ከጋዜጠኞቹም አልፎ ወደ ቤተሰባቸው እና ጓደኞቻቸው ድረስ ይዘልቃሉ፡፡ የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያ ተቀብለው በሚሰሩት ዘገባ ላይ ቅድመ-ምርመራ የማያካሂዱት በአብዛኛው ክስም ሳይመሰረትባቸው በዘፈቀደ ይታሰራሉ እንዲሁም ተጨማሪ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርሳቸዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ አካባቢዎች በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ያልተገባ አያያዝ እና ድብደባ የተለመደ ሆኗል፤ በአብዛኛው ጊዜም የወነጀል ክስ ተከትሎ ይመጣል። ብዙዎቹ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ የግል ጋዜጠኞች በርካታ ጊዜያት እስር ተፈጽሞባቸዋል፤ እንዲሁም ከደህንነት ባለስልጣናት፣ ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች፣ እና ከቀድሞው የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አሁን ደግሞ የመንግስት ኮምዩኒኬይሽን ጉዳዮች ቢሮ ከተባለው መስሪያቤት ባለስልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዛቻዎችን ተቀብለዋል፡፡
ይህም በመጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በራሳቸው ላይ ቅድመ-ምርመራ በማድረግ የገዥውን ፓርቲ አጀንዳ ከማራገብ ወይንም ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ዘገባ እና እና ትንታኔ ማቅረብ ከመቀጠል አንዱን የመምረጥ ከባድ ፈተና ውስጥ እንዲወድቁ ያደርጋል።
በግለሰብ ጋዜጠኞች ላይ ከሚደርሰው ጥቃት በተጨማሪ የግል መገናኛ-ብዙሃን ባለቤቶች የህትመት ውጤቶቻቸውን የሚያሳትሙባቸውን ማተሚያ ቤቶች ለማዳከም ባለስልጣናቱ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ፡፡ በመግስት ስር የሚተዳደረው እና በመደበኛነት ጋዜጦችን የማተም አቅም ያለው ብቸኛ ማተሚያ ቤት የግል ህትመት ውጤቶችን ስራ ያዘገያል ወይንም አይቀበልም፣ በአንድ አጋጣሚ መንግስት በጣም አሳሳቢ ነው ባለው ጉዳይ ላይ ዘገባ ያሳተመን ጋዜጣ 40,000 ኮፒ ህትመት አቃጥሏል፡፡ የደህንነት ሰዎች የግል ህትመት ውጤቶች አከፋፋዮች ላይም የሚያደርጉትን ክትትል እና የሚያደርሱትን ጥቃት ጨምረዋል፡፡ የጋዜጠኞች የመረጃ ምንጮች በተደጋጋሚ ለጥቃት እየተጋለጡ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ለመነጋገር ፍርሃት የሚያድርባቸው ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ ነው።
መንግስት የግል ጋዜጠኞች ማህበር ለማደራጀት የሚደረግን ሙከራ ያግዳል እንዲሁም የግል የህትመት ውጤቶች ያላቸውን ፖለቲካዊ ትስስር በተመለከተ የደህንነት ባለስልጣናት ሰፊ የኋላ ታሪክ ጥናት ያካሂዳሉ፡፡ የመንግስት ወይም የገዥው ፓርቲ ሙሉ ደጋፊ ያልሆኑ የግል ህትመቶች ለሚያቀርቡት የህትመት ፈቃድ አሊያም እድሳት ጥያቄ ባለስልጣናት ምላሽ ለመስጠት ይዘገያሉ፡፡
የድረ-ገጽ መገናኛ ብዙሃንም በተሻለ መልኩ የተያዙ አይደሉም፡፡ በውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚመሩ በርካታ ጦማሮች እና ድረ-ገጾች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታዩ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም ዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁት በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ የሚያቀርቡ የጦማሪያን ስብስብ 80 ቀናት ክስ ሳይመሰረትባቸው በእስር ከቆዩ በኋላ በጸረ-ሽብር አዋጁ እና የወንጀል ህጉ መሰረት ተከሰዋል፡፡ በቀረበው ክስ መሰረት በክስ ዝርዝር ሰነዱ ከተጠቀሰባቸው ማስረጃ መካከል አንዱ ቴክኒካል ቴክኖሎጂ ኮሌክቲቭ በተባለው በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የግላዊ መረጃዎችን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ የሚረዱ ተግባራትን እና መሳሪያዎችን በሚያቀርበው ዓለም ዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የዲጂታል ደህንነት ጥበቃ ስልጠና ወስደዋል የሚል ነው፡፡ የዞን ዘጠኝ አባላት መታሰር እና መከሰስ በሃገሪቱ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ላይ የፍርሃት ድባብ ፈጥሮአል። ይህም ጦማሪዎች እና የኢንተርኔት ላይ ተሟጋቾች በፌስቡክና በመሳሰሉ እና ሌሎች ማህበራዊ ድረ-ገጾች በሚለጥፏቸው ትችቶች ምክንያት ችግር ውስጥ ልንገባ እንችላለን የሚለውን ስጋታቸውን በእጅጉ ከፍ አድርጎታል፡፡
በሬድዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭት ላይ ያለውም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የሃገሪቱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመንግስት ስር የሚገኙ ሲሆን ገለልተኛ የዜና ዘገባ እና ትንታኔ አይቀርብባቸውም፡፡ ከ80 በመቶ የሚበልጠው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖረው በገጠራማ አካባቢዎች በመሆኑ እና ሬድዮ እስከአሁን ዋናው የዜና እና መረጃ ማግኛ ምንጭ ከመሆኑ አንጻር ይህ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚያቀርቡ ጥቂት የግል ሬድዮ ጣቢያዎች ዝግጅቶቻቸውን አየር ላይ ከማስተላለፋቸው ከቀናት በፊት የመንግስት ባለስልጣናት እንደሚገመግሙት እና እንደሚያጸድቁት ለሂውማን ራይትስ ወች ተናግረዋል፡፡ ተቀባይነት ካገኘው ይዘት የሚያፈነግጡ አሰራጮች በመንግስት ባለስልጣናተ የሚፈጸም እስር እና ወከባ ጋር መጋፈጥ ሊኖርባቸው ይችላል።
በርካታ ጋዜጠኞች ከማያቋርጥ የማዋከብ እና የፍርሃት ሕይወት ለመገላገል ሲሉ ከመንግስት ጋር ትስስር ባለው መገናኛ-ብዙሃን ተቀጥረው መስራት ይመርጣሉ፡፡ አንዳንዶች የመንግስት ባለስልጣናትን እስከማያስቆጣ ድረስ ባለው መለያ መስመር ላይ ሆነው ትችቶችን የሚያቀርቡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ የመንግስትን የልማት ውጤቶች በማስተዋወቅ እና በማጋነን የመንግስት ፕሮፖጋንዳ አራጋቢዎች ሆነው ይሰራሉ፡፡ በእነዚህ መገናኛ ብዙሃን የኢህአዴግ አባልነት እድገት ለማግኘት የሚጠየቅ መስፈርት ነው፡፡
በኢጥዮጵያ የሚገኙት የውጭ መገናኛ ብዙሃን ውሱን ናቸው። የአሜሪካ ድምጽ ቮይስ ኦፍ አሜሪካ (ቪኦኤ) እና የጀርመን ድምጽ ዶቼቬሌ የቴሊቪዥን እና የሬድዮ ሽፋን በመስጠት በርካታ የዲያስፖራ ጣቢያዎችን ተቀላቅለዋል፡፡ ሆኖም የአየር ሞገዳቸውን በማገድ፣ በሰራተኞቻቸው እና የመረጃ ምንጮቻቸው ላይ ዛቻ እና ጥቃት በማድረስ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ የዲያስፖራ መሰረት ያላቸውን ስርጭቶች የሚመለከቱ እና የሚያዳምጡ ግለሶቦችን በማጥቃት እና በማሰር ጭምር መንግስት የሃገር ውስጥ ተከታታዮቻቸውን ለመገደብ የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማል፡፡
እ.ኤ.አ. ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማሕበራት ላይ በደረሰው ጫና ምክንያት በርካታ የሲቪል ማሕበራት ስራ ለማቆም የተገደዱ ሲሆን ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ጥብቅ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ንቁ እና ነጻ የመገናኛ-ብዙሃን ዘርፍ በመንግስት አስተዳደር ላይ ተሳትፎን ለማበርከት እና የሰብዓዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ እንዲከበሩ ለማገዝ ያለውን አስፈላጊነት የበለጠ ያጎላዋል። አለመታደል ሆኖ በፖለቲካ ሁነቶች ላይ ገለልተኛ ሽፋን እና የዜና ትንታኔ ለመስጠት ያለውም ጥቂት ክፍተት እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም. የበለጠ ተጣቧል፡፡ ከግንቦት 2007 ምርጫ መቃረብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ የፖለቲዊ አተያዮች እና ትንታኔዎችን የሚያገኙበት እድል እየተመናመነ ነው።
በኢትዮጵያ የሚገኙ መገናኛ-ብዙሃን ሁኔታን ለማሻሻል በአጭር እና በረጅም ጊዜ አሁንም ብዙ ሊደረግ ይችላል፡፡ እንደ መጀመሪያ እርምጃ መንግስት ክሶችን በአስቸኳይ በማንሳት የታሰሩ እና የተፈረደባቸው ጋዜጠኞች እና ጦማሪያንን ክስር ሊለቅ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ንቁ እና ገለልተኛ የመገናኛ ብዙሃን መኖር ለሃገሪቱ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ እንዲሁም በመጪዎቹ ሳምንታት እና ወራት መንግስት የጸረ-ሽብር ህጉን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሃኑ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ አፋኝ ህጎችን ማረም አለበት፡፡ የሚወጡ ህጎች እና የሚፈጸሙ ተግባራት የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት እና ዓለምዓቀፍ መለኪያዎች ጋር በሚጣጠም መልኩ መሆኑን ባለስልጣናት ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
ምክረ ሃሳቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስት
  • ሁሉንም ክሶች በአስቸኳይ ማንሳት እንዲሁም በወንጀል መቅጫ ህጉ እና በጸረ-ሽብር አዋጁ መሰረት ተከሰው በዘፈቀደ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን በሙሉ መፍታት።
  • የጸረ-ሽብር አዋጁ እና የመገናኛ-ብዙሃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጁ መሰረዝ አሊያም በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት እንዲሁም በክልላዊ እና ዓለምዓቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ህጎች ላይ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት መብት ከተቀመጡ መስፈርቶች ጋር በሚጣጣም መልኩ ከፍተኛ መሻሻያ ማደረግ፡፡
  • የስም ማጥፋትን የወንጀል ቅጣት እንዲያስከትል ተደርጎ በወንጀል መቅጫ ህጉ አንቀጽ 613 ላይ የተደነገገውን ማሻሻል።
  • በህትመት እና ብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ላይ መንግስት ያለውን የባለቤትነት ድርሻ መገደብ ፤ እንዲሁም የግል መገናኛ-ብዙሃን ባለቤትነትን የሚገድቡ ጉዳዮችን ለማስቀረት እና ገለልተኛ እና ንቁ መገናኛ-ብዙሃንን ለማበረታታት የሚያስችሉ የህግ እና የፖሊሲ ማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ።
  • አዳዲስ የህትመት እና የሬድዮ ስርጭቶች ቁጥጥርና ፈቃድ አሰራር ቀልጣፋ ማድረግ እና ከፖለቲካዊ ይዘት ነጻ ማድረግ። ቁጥጥር አድራጊ ባለስልጣን አካላት ገለልተኛ መሆን አለባቸው፤ እንዲሁም አስተዳደራዊ እና ተግባራዊ እንቅስቃሴያቸው ከመንግስት የደህንነት አካላት አና ከመንግስት ኮምዩኒኬይሽን ጉዳች ቢሮ መለየት አለበት፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ገለልተኛነትን ለማረጋገጥ ማሻሻያዎች ማድረግ።
  • የሃገር ውስጥ እና የውጭ ጋዜጠኞች በመላው ሃገሪቱ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን የሚገድቡ አሰራሮችን ማስወገድ፣ ይህም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ በሚባሉ አካባቢዎች በነጸነት መንቀሳቀስን እንዲጨምር፣ ፖሊስ እና የደህንነት ሰዎች መገናኛ-ብዙሃን በነጻነት ይንቀሳቀሱ ዘንድ ፈቃድ እንዲሰጡ መመሪያ መስጠት፤ በዛቻ፣ በማስፈራራት እና በማሰር የጋዜጠኞችን እንቅስቃሴ የገደበ ማንኛውም ፖሊስ በያዘው የማዕረግ እርከን ልዩነት ሳይደረግ መቅጣት።
  • የፖለቲካ ፓርቲ ፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የጦማሪያን ድረ-ገጾችን ማፈን እና ቅድመ ምርመራ ማድረግን ማቆም እንዲሁም ለወደፊት እንደዚህ አይነት ድረ-ገፆችን ላለማፈን በይፋ ቃል መግባት።
  • የሬድዮ እና የቴሌቪዥን አየር ሞገዶችን ማፈን ማቆም ፤ ለወደፊቱም የሬድዮ እና ቴሌቪዥን አየር ሞገዶችን ላለማፈን በይፋ ቃል መግባት።
  • አስተያየት የመስጠት እና ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት መብቶችን ለማዳበር እና ለመጠበቅ የሚንቀሳቀሰው የተባበሩት መንግስታት ልዩ ራፖርተር ኢትዮጵያን እንዲጎበኝ እና የግል የህትመት እና የብሮድካስት መገናኛ-ብዙሃን ያሉበትን ሁኔታ እንዲገመግም እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ሁኔታ እንዲያጠና ግብዣ ማቅረብ።
የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት እና ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ለዓለምዓቀፍ የኢትዮጵያ ለጋሾች
  • በዘፈቀደ የታሰሩ እና በወንጀል ህጉ እና በጸረ-ሽብር አዋጁ መሰረት የተከሰሱ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን በሙሉ እንዲፈቱ በይፋ ጥሪ ማቅረብ አና በተናጥል ጫና ማሳደር።
  • የጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ዓለምዓቀፍ የፍርድ ሂደት መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ የፍርድ ሂደት ክትትሉን ማሻሻል እና መጨመር።
  • የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የሚገኙበትን ሁኔታ ለመገምገም እስር ቤቶችን እና ማቆያ ጣቢያዎችን ለመጎብኘት ጥያቄ ማቅረብ።
  • ሃሳብን የመግለጽ ነፃነትን የተመለከቱ አሳሳቢ ጉዳዮች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ልማትን እና ደህንነትን እንደሚጎዱ ያላቸውን ስጋት ለመንግስት ባለስልጣናት በይፋ እና በግል መግለፅ።
  • ገለልተኛ የጋዜጠኝነት ማህበር የሚፈጠርበትን መንገድ ጨምሮ የኢትዮጵያ መገናኛ-ብዙሃን የሙያ ብቃት እንዲዳብር ድጋፍ ማበርከት፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚገኙ ለግል መገናኛ-ብዙሃን ጋዜጠኞች የተለዩ እድሎች መኖራቸውን ማረጋገጥ እና የመገናኛ-ብዙሃን አቅምን ለማሳደግ ያለሙ እንቅስቃሴዎች እንዲካተቱ ልዩ ጥረት ማድረግ።
  • ነጻ ጋዜጦች እና ሌላ አይነት ህትመቶች መንግስታዊ ያልሆኑ ወይም በመንግስት ቁጥጥር ስር ያልገቡ ማተሚያ መሳሪያዎችን የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ድጋፍ ማድረግ።
በመንግስት ለተያዙ እና ከመንግስት ጋር ትስስር ላላቸው ማተሚያ ቤቶች
  • ከመንግስት ጋር የተለየ ትስስር ያላቸው ህትመቶች ከሚታተሙበት የጊዜ ሰሌዳ በሚጣጠም መልኩ ሁሉንም ፈቃድ ያላቸው የግል መገናኛ ብዙሃን ህትመቶችን በተገቢው የጊዜ ገደብ እና አግባብ ባለው ሁኔታ በገለልተኝነት ማተም።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን አስተላላፊዎች
  • የተለየ አደጋ ያለባቸውን የመረጃ ምንጮች ለመለየት የሚጠቀሙበትን አሰራር ማጠናከር እና አደጋውን ለመቀነስ የሚወስዱትን እርምጃ ማዳበር፤ ይህም የግለሰቡ ማንነት እንዳይታወቅ ማድረግ፣ ማንነታቸውን በተመለከተ ያላቸውን መረጃ ሚስጥራዊ አድርጎ ማስቀመጥ እና ከፍተኛ ታዋቂነት ላላቸው ግለሰቦች ያለውን አደጋ እንዲገነዘቡት ማድረግን ይጨምራል፡፡
ለኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳ መንግስታት
  • ጋዜጠኞች እና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ጨምሮ ጥገኝነት ጠያቂዎች ለጥገኝነት ማመልከቻቸው በአፋጣኝ ምላሽ መስጠት እና ሊደርስባቸው ከሚችለው ጥቃት ከለላ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ።

Friday, January 23, 2015

ለልጆቼ የማይሆን ተስፋ አልነግራቸውም” የነፃነቱ ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ


ከልጅ አያሌው ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ትግል እስከወዲያኛው ከዳር ለማድረስ ቆርጦ ልጆቼን ቤተሰቦቼን ሳይል ከራሱ በላይ በሀገሩ ፍቅር ተበልጦ የተሻለ ነው የሚለውን፣ አማራጭ የሌለውን፣ የኤርትራን ጫካ መርጦ የማይቻል የሚመስለውን ችሎ ብዙዎች ፈቀቅ ማድረግ ያቃታቸውን የመተባበር የመያያዝ በአንድ ገብቶ ለአንድ አላማ የመታገልና ኢትዮጵያን እንደቀደመው ታላቅ ሀገር የማድረግ ውጥን የተሻለና የሚያግባባ ሀሳብ በመሸከፍ ከሚመራው ንቅናቄ ከግንቦት 7 ጋር እጅግ እውነት የማይመስሉ ድንቅ ስራዋችን በመስራት ጠማማውን በማቅናት ኮረብታውን በመደልደል አንድ መሆን ሳይችሉ ለአመታት ሲኳትኑ የነበሩትን በኢትዮጵያዊነት እንዲተሳሰሩ በማድረግ ፍቅር የሰራ ትልቁን መሰረት የጣለ ምርጥ የኢትዮጵ የቁርጥ ልጅ አንዳርጋቸው ፅጌ። ዛሬ እሱ በማረፍያው ሰዓት አግባብ ባልሆነ መንገድ ከአውሬዋች እጅ ወድቆ ይህን መልዕክት አስተላልፏል። ለልጆቼ የማይሆን ተስፋ አልነግራቸውም። ይሄ መልዕክት ኢትዮጵያን ለሚወዱ ሁሉ እጅግ የሚያም ነው ምክንያቱም እየከፈለ ያለው መሰዋት ለኛ ለኢትዮጵያኖች ስለሆነ። አንዳርጋቸውን ከግንቦት 7፣ ግንቦት 7ን ከአንዳርጋቸው መነጠሉ የማይሞከር ነው ምክንያቱም ሀቁ የሚነግረን እሱና እሱን ከሚመስሉ ወንድሞች ጋር ታላቅ የሆነ ኢትዮጵያን የማዳን ራዕይ ሰንቀው በግድ ሳይሆን በፍቅር ተሳስረው አንዳይነት አላማ አንግበው ማድረግ ከሚችሉት በላይ ሌተቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከማንም በላይ የየግል ህይወታቸውን መኖር እየቻሉ ያለመታከት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ታላቅ ለማድረግ የተሰለፉለት አላማ መሆኑ በግልፅ የሚታይ ሀቅ ስለሆነ። ታድያ አንዳንዶች የኢትዮጵያዊነትን ካባ የለበሱ የሚመስሉ እየደረሰበት ያለውን ስቃይ በመኮነን ድንቅ ሰው ታላቅ ሰው መሆኑን አክለውበት ጀግናችን ነው ብለው ሲያበቁ አንዳርጋቸውና ንቅናቄው አምነውበት: በአሁን ሰአት ካለው የሀገራችን አንዲሁም የጎረቤት ሀገራት ሁኔታን በማጤን አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን በመረዳት በትግል የዘረጉትን ገመድ በጥሶ ለመጣል ያስችለናል የሚሉትን የሰነፍ ስንቅ በመሰነቅ እየተሄደበት ያለውን መልካም መንገድ ፈንጂ የተጠመደበት በማስመሰል አንዳንዴ በዛበኩል ትግል ለሚያደርጉት ከልብ ያዘኑ በመምሰል አልሆን ሲላቸው ደግሞ በዛ በኩል የሚደረግ ጉዞ ለሀገር አደጋ አለው በማለት ነጋ ጠባ ያለ ህፍረት መከራቸውን ሲያዩ ስምለከት ከሚቆረጥላቸው አበል ጥቂቱን እንኳን ደጉሜ ነፃ ሰው ባደርጋቸው እልና ፀረ ትግልና ፀረ ነፃነት መሆናቸው ሲታወሰኝ ከእንዲህ አይነቱ ሱስና አመል ማላቀቁ ከአቅሜ በላይ መሆኑን ሳውቀው አንድላይ ደባልቆ ማሸቱን እመርጥና እተወዋለው። በነገራችን ላይ ይሄ አባዜ በነዚህ እኩይ ተግባር ባላቸው ጥቂት ሰዋች ብቻም አይቀነቀንም ይልቁንም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ያለምንም ማወላወል አንገታቸውን ሊሰጡ በሚችሉ ሰዋችም ወቅት አየጠበቀ እንደሚያጓራ ዛር ሲያወራጫቸው ይስተውላል ታድያ የችግሩን መንስኤ ሳጠናው ፍቅር ሆኖ አግኝቸዋለው ፍቅር ደሞ እዚ ውስጥ ምን ከተተው ትሉኝ ይሆናል? ይሄኛው ወዲህ ነው አትጣበቅ እንጂ አንዴ ከተጣበክ አትታጠር እንጂ አንዴ አጥር ከሰራህ ማየትም መስማትም የምትፈልገው ያፈቀርከውን ብቻ ነው ወገኖቼ በድርጅት ፍቅር እንዳታብዱ የትም ስለማያደርስ :አንዴ ግን ከተለከፋቹ የተሰራው እናንተ ካልሰራችሁት የተጀመረው እናንተ ካልጀመራችሁት የታሰበው መልካም ሀሳብ ከናንተ ቀድሞ ካልፈለቀ ገደል አፋፍ ላይ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ተይዛቹ እንኳን የማዳን እጅ ቢዘረጋ አይናቹ ማየት የለመደውና የምታፈቅሩት እጅ አለመሆኑን ስታውቁ መዳንን ትፀየፉታላቹ ገደል መግባቱን ትመርጣላቹ ስለዚ እውነት ሀገራችንን ማዳን ከፈለግን ሜዳው ሰፊ ነውና እኔ ካልባረኩት የሚለውን ፍሬ ከርስኪ ትተን ሌላውን ከመጎተት የተሻለ የምንለውን ሜዳ በመምረጥ ለሀገራችን አለኝታ እንሁን። ሌላኛው ደግሞ እጅና እግሩ ተጠፍንጎ የታሰረበት ይመስል ከማሳየት ይልቅ ጥግ ይዞ የታላቹ፣ የት ገባቹ፣ ጦርነት የሆሊውድን ፊልም አይነት እየመሰው በከንቱ ምኞት መሬት ላይ ወርዶ ህይወቱን ለሀገሩ አሳልፎ ለመስጠት ነጋ ጠባ መከራውን የሚያየውን የነፃነቱን አርበኛ ከሶፋው ላይ ተደላድሎ ተቀምጦ እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ ቢራውን እየተጎነጨ ከኮንፒውተር ጀርባ ሆኖ ሲከተክተው ይውላል ደሞ እፍረትም የለውም ትግላችን፣ የኛ ትግል፣ እያለ እየደጋገመ ሲናገር ይደመጣል እኔ ግን እላለው: መጀመርያ እጃችንን ከኪሳችን ታግለን ነፃ እናውጣው። ሀገራችንን ለማዳን የሚደረገውን ትግል ለመደገፍ ሰበብ አንደርድር። በመጨረሻም አንድ ወዳጄ ለጨዋታ ባወረዳት ቅኔ ለጠቅ አድርጌም የኔንም የመልስ ምት አክዬ ልደምድም፣ እኔ እናገራለሁ ቆሜ ከፊታቹ ጠሀይ አልወጣ አለች ከሰሜን ወርዳቹ መልስ የጠሀይን መውጫ ልብህ እያወቀው ብላ ተኛ ሆነህ የቆረጠውን ሰው በየትኛው ወኔነው የምትጠይቀው ቅኔው የወዳጄ ሆና እሱ ባያቀነቅናትም ይህቺን ዘፈን ብዙዋች ይዘፍኗታል እስኪ ካስተማረች በተን ላድርጋት፣ ለመሆኑ የጠሀይ መውጫ በሰሜን ሆነ እንዴ? የኔ ጥያቄ ነው ጠሀይ በምስራቅ ወጥታ በምዕራብ ትጠልቃለች የወዳጄ ጠሀይ ግን :ከወትሮው ለየት አለችብኘ ለነገሩ ራቅ አድርገው ካሰቡት ጠሀይ በእድሜም የጠገበች እንደመሆኗ ተወዳጅነቷ ዋዛ እንደማይሆን አልጠራጠርም።
ወዳጄም የመናፈቅ ብዛት ሳያናግረው አልቀረም ስለዚህ ወንድሜ ጠሀይን እኛ አላገድናትም መውጫዋም በምስራቅ ነው እኛ ግን መንደርደርያ የለንምና በሰሜን ከተናል ባይሆን ባገኘናት እድል ተጠቅመን ከሰሜን ተነስተን የጠፋችብህን ጠሀይ ከዚህ ሰፈር ሳይሆን ሰፈሯ ድረስ በመምጣት ብቅ እንድትል ማረጋችን እንደማይቀር ላረጋግጥልህ እወዳለሁ የምትቸኩል ትዕግስት የሌለህ ከሆነ ግን ጠሀይ ብቅ እንድትል ስትፈልግ በደቡብ፣ ስትፈልግ በምዕራብ፣ የሚያስጠጋህ ከገኘህ በዛ በኩል ሞክር። ምስራቁ ቅርብ ነውና ባትደላደል እንኳን ጫፍ የሚያስይዝህ ካገኘህ ያው መደወል አትወድም ምልክት አድርግልኝ ያለህበት ድረስ መጥቼ እቀላቀልሀለው እውነቴነው የምልህ ጠሀይቱ እናቴ ጋር እስካደረሰኘ ድረስ የማልቆፍረው ገድጓድ የማልወጣበት ተራራ፣ የማልሞክረው አቋራጭ አይኖርም። በሰሜን የከተቱት ብዙ ጊዜ ተጠይቀው ሲመልሱት ካደመጥኩት ቅንጭብ የተወሰደ ነው በሚል ይያዝልኝ። ስለዚ መጠላለፉን ትተን የምንችለውን እናድርግ ያ ከሆነ ትግሉን መሬት ላይ አውርዶ እየሰራ ያለውም በአየር ላይ ያለውም በመጨረሻዋ ቀን የነፃነቷ ጠሀይ በሀገራችን ስትወጣ እኩል ይቋደሳሉና። ይህንን ለመፃፍ ያነሳሳኝ “ለልጆቼ የማይሆን ተስፋ አልነግራቸውም” የሚለው የጀግናው ታጋይ የአንዳርጋቸው ንግግር መሆኑነ አሰምርበታለሁ። በዘገየን መጠን የምናጣው ይበዛልና ባለመጠላለፍ ወደፊት እንሂድ፣ እኔ የሁሉም ነኝ የተሻለ አማራጭ ያለው ይገዛኛል። ኢትዮጵያ ለዘላላም በክብር ትኑር! እናቸንፋለን! ልጅ አያሌው source,-http://www.zehabesha.com/amharic/?p=38237

ገጣሚ ታገል ሰይፉ ወደ ደደቢት ያልሄደው አላማውን በመቃወም እንደነበር ገለጸ (ከአስገራሚ ትንታኔ ጋር)


(ኢ.ኤም.ኤፍ) በቅርቡ የህወሃት 40ኛ አመት ሲከበር፤ በርካታ የኪነ ጥበብ ሰዎች የተደረገላቸውን ግብዣ ተቀብለው ወደ ትግራይ ማምራታቸው ይታወሳል። ሁሉም አርቲስት ግን… ፖለቲካዊ ይዘት ያለውን ጉዞ አልተቀበለም። ሁሉም የየራሳቸው ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል። ህዝቡ ወደ ደደቢት የሄዱትን ያወገዘውን ያህል ጥሪውን ሳይቀበሉ የቀሩትንም ማመስገን ይገባው ነበር። ወደ ደደቢት ካልሄዱት መካከል፤ እነአብርሃም ወልዴ፣ እነጆሲ፣ ላፎንቴን፣ ደረጄ ኃይሌ፣ ሰይፉ ፋንታሁን እና ሌሎችም ሊመሰገኑ ይገባል። ሁሉም በየራሳቸው መንገድ የራሳቸው ምክንያት ቢኖራቸውም፤ ለመጀመሪያ ግዜ ምክንያቱን በአደባባይ ለመግለጽ የበቃው ገጣሚ ታገል ሰይፉ ግን፤ “ጥሪ ቢደረግልኝም ስላላመንኩበት ቀርቻለሁ።” ብሏል።

tagel
የዚህ ሁሉ መነሻ፤ የኢዮፒካ ሊንክ ሬድዮ ጋዜጠኞች ያቀረቡት ቀለል ያለ የሚመስል ጥያቄ ነበር። እንዲህ ብለው ጠየቁት። “ሰዎች ስላንተ እንዲያውቁ የምትፈልገው ነገር ምንድነው?” አሉት። ገጣሚ ታገልም ሲመልስ፤“ከተፈቀደልኝ ሰዎች እንዲያውቁት የምፈልገው…” ብሎ ጀመረ።
“ሰዎች የማይረዱት ነገር አለ። ለምሳሌ ባለፈው የመቀሌ ጉዞ ላይ እኔ አልሄድኩም። አርቲስቶች ሲሄዱ ጥሪ ተደርጎልኛል። ነገር ግን የደደቢቱን ጉዞ ስላላመንኩበት ቀርቻለሁ። ስለማልፈልገው ማለት ነው። …ለነሱም የምለው ነው። በተለይ ባለፉት 15 አመታት ብዙ ነገር አልተሰራም። ለስነ ጽሁፍ የሚመች ግዜ አይደለም። ስነጽሁፍን ትኩረት አልሰጡትም። እያየን ነው። ግድቡ ሲገነባ ደስ ይላል። ቤት ሲሰራ ደስ ይላል። ነገር ግን የሞራል ሃብታችን እየወደቀ ነው። በደርግ ግዜ ለስነ ጽሁፍ ትኩረት ተሰጥቶት አድጓል። ብዙ ትላልቅ ደራሲዎቻችን በሳንሱር ዘመን ነው የወጡት። እንደነጸጋዬ ገብረመኅን፣ እነ በአሉ ግርማ… አሁን ግን እንደነዚያ አይነት ትላልቅ ሰዎች አልወጡም። ምክንያቱም ለስነ ጽሁፍ ትኩረት አልተሰጠም። ይህ መንግስትን ዋጋ ያስከፍለዋል።
“እንዲያውም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሞቱ ግዜ ለሳቸው የተሰማኝን ሃዘን የሚገልጽ ግጥም አቅርቤ ነበር። እና ከዝግጅቴ በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ‘ጠቅላይ ሚንስትሩ ለኪነ ጥበቡ ማደግ ምን አድርገዋል?’ ሲለኝ ‘ምንም’ ነበር ያልኩት። እርግጥ ይህ ያልኩትን ቆርጠው አውጥተውታል። …እናም ወደ ትግራይ ለጉብኝት ሲሄዱ ስላላመንኩበት እኔ አልሄኩም።
“በሁለተኛ ደረጃ የግል አቋም አለኝ። ለምሳሌ ‘በደርግ እና ኢህአዴግ’ መካከል የተካሄደው ጦርነት
 የሁለት ወንድማማቾች ጸብ ነው። እዛ ጸብ ውስጥ አንዱን በሌላው ላይ ጀግና ማለት እምነቴ አይደለም። ለኔ የመንግስት ጀግንነት የሚጀምረው ጦርነቱን ጨርሶ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ባሳያቸው ለውጦች ነው የምለካው። እንጂ እዛ ጋር ገዳይም ወንድሜ ነው፤ ሟችም ወንድሜ ነው። አንዱን በአንዱ ላይ ጀግና ለማለት እዚያ አልሄድም። አስፈላጊም አልነበረም። አሁን እኔ እንደዚህ አይነት አቋም አለኝ። ሆኖም አንዳንድ ድረ ገጾች ላይ ስታይ፤ (ለአባይ ግድብ ያቀረበውን ግጥም አይተው፤ ሰዎች ‘‘ባንዳ ባንዳ’ ብለው የሰደቡትን በማስታወስ ይመስላል… የንዴት ትንፋሽ አስማ) የአባይ ጉዳይ ሲሆን በዚህ ሁሉ ልዩነት መሃል አገሪቱን ዲያብሎስም ቢመራት የአባይን መገደብ እደግፈዋለሁ። ብዙ ሰዎች ይህንን በደንብ አይረዱትም። ….ወደኋላ ሄደህ ብትመለከት ወንድሙን ገድሎ ስለመጣው ኢህአዴግ ጀግንነት ጽፌ አላውቅም።
“…ከመንግስት ጋር ብዙ ደስ የማይሉኝ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። አባይ ሲባል ግን… ይህ የአገር ጉዳይ ነው። …ማንም የፈለገውን ትርጉም ቢሰጠው ይህ ለዘመናት አያት ቅድማያቶቻችን እንዲሆን ሲመኙት የነበረው ነገር ነው። ስለዚህ አባይን በተመለከተ ሰዎች በዚህ በኩል ቢረዱኝ ደስ ይለኛል፤ ለማለት ነው።”
 ብሏል።
ገጣሚ ታገል ሰይፉ በዚህ ቃለ ምልልሱ ላይ አሁን ባለው የኢህአዴግ አስተዳደር ዘመን የትውልድ ዝቅጠት መድረሱን ሳይጠቅስ አላለፈም። ትልቁ የሞራል እሴት እየተሸረሸረ፤ ወጣቱ የራሱን ተራ ጥቅም የሚያስቀድም ጥቅመኛ እና ግለኛ መሆኑን በሰፊው ዘርዝሯል። በቃለ ምልልሱ መጨረሻ ላይ የኢትዮፒካ ሊንክ ጋዜጠኞች ጭምር ገጣሚ ታገልን፤ “ጀግና” የሚል ቅጽል ሰጥተውት ቃለ ምልልሳቸውን አብቅተዋል።

ኢትዮጵያ የማን ነች?


“ኢትዮጵያ የማን አገር ነች” የሚል ጥያቄ ከዚህም ከዚያም እየተሰማ ነው። ህወሃቶች ከፈጠሯቸው ቀውሶች መካከል አንዱ ይሄው ነው። ዜጎች የአገር አልባነት ስሜት ውስጥ ገብተው የገዛ አገራቸውን “የማን ነች” ብለው እንዲጠይቁ መገደዳቸው።
ለኢትዮጵያዊያኑ ኢትዮጵያ አገራቸው እየሆነችላቸው አይደለም። ኢትዮጵያዊ መሆን ወንጀል እስኪመስል ድረስ በዜጎች ላይ ግፍ እየተፈፀመ ነው። የሚፈፀመው የግፍ ዓይነት ወሰን የለውም። ግማሹ በጠራራ ፀሃይ ደሙ እንዲፈስ ይደረጋል። ሌላው ለቁም ስቃይ ወደ ወይኒ ይጋዛል። ቀሪውም እትብቱ የተቀበረበትን አገር ትቶ ለመሰደድ ይገደዳል። በአገሪቷ ውስጥ የሚፈፀመውን ወሰን አልባ በደል የተመለከቱ ኢትዮጵያን ከውዳቂ መንግስታት ተራ መድበዋታል። በኢትዮጵያችን የዜጎችን መብት አስከብሮ ለመምራት ብቃት ያለው መንግስት ባለመኖሩ እጣ ፈንታችን እንዲህ ከውዳቂ አገራት ተርታ መግባት ሁኗል።
ኢትዮጵያን ለመምራት ብቃት ያለው መንግስት ቢኖር ኑሮ ለረዥም ዘመን በሰላም ተጎራብተው ይኖሩ በነበሩ ህዝቦች መካከል ግጭት ተፈጠረ መባልን ባልሰማን ነበር።ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ሆን ተብሎ በሚፈጠር ግጭት ብዙ ደም ፈሷል። አማራው ከኦሮሞው፤ ትግሬው ከአማራው እና ከአፋሩ፤ ሶማሌው ከኦሮሞ፤ኦሮሞው ከጉጂው፤ ኑዌር ከአኙዋክ፤ ዲዚ ከሱርማ፤ ሌሎችም ብዙ ግጭቶች በየቀየው ተፈጥረው አይተናል። የብዙ ዜጎችም ህይወት ተቀጥፏል። ይሄ ሁሉ ደም መፋሰስ የሚከሰተው ህወሃት ከህዝብ ፈቃድ ያልሆነ እና ከህዝቡ የተለየ በመሆኑ ነው።
ህወሃቶች ከህዝብ የተለዩ ብቻ ሳይሆኑ የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጡ ብድኖች ስለመሆናቸው ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ህወሃቶች “አማራና ተፈጥሮ” የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ናቸው ብለው መፃፋቸው እና ማስተማራቸው የህዝብ ጠላት መሆንን ስለመምረጣቸው ቋሚ ምስክር ነው። ህወሃቶች በስልጣን የሚያቆየን በህዝቦች መካከል የሚፈጠረው አለመተማመንና የጠላትነት ስሜት ብቻ ነው ብለው ከልባቸው ያምናሉ። በህዝቦች መካከል የሚፈጠረው አብሮነት፤ አብሮነቱን ለማዘመን የሚረዳ መተማመን፤ ይሄም የሚወልደው አንድነትና ህብረት በህወሃት ዘንድ የሚወደድ ነገር አይደለም። በህወሃት ዘንድ የሚወደደው በህዝብ መካከል የሚፈጠረው የአለመተማመን ስሜት ይህም አለመተማመን የሚወልደው ግጭት ነው። ግጭት ተፈጥሮ የንፁህ ደም ሲፈስ በህወሃቶች መንደር ደስታ ይሆናል።በዜጎቹ ግጭት እና ደም መፋሰስ ተደስቶ የሚኖር ቡድን እንደ ህወሃት ዓይነት በየትም አገር ታይቶ አይታወቅም።
ከሰሞኑ በአማራ ክልል ነዋሪዎችና በትግራይ ክልል ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተከሰተ መባልን ሰምተናል። ይሄ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ ነገር ነው። ህወሃት ከመፈጠሩ በፊት በሠላም ተጎራብቶ የሚኖር ህዝብ ዛሬ ደም መፋሰስ ደረጃ ወደ ሚያደርሰው ግጭት ተሻግሮ መስማታችን አሳፋሪ ነው። ህወሃቶች ከመቸውም ግዜ በላይ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠናክሯል እያሉ ሳይታክቱ በሚያወሩበት በዚህ ግዜ አብሮ ለብዙ ዘመን የኖር ህዝብ ወደ ግጭት የመግባቱ ነገር የህወሃቶች ትሩፋት ሁኖ እናገኘዋለን። ህወሃቶች በዘመናቸው ካተረፉልን ቀውሶች መካከል ሳይጠቀስ የማይታለፈው በህዝቦች መካከል የሚፈጥሩት ግጭት ነው። በህዝቦች መካከል በሚፈጠረው ግጭት ብቻ እድሜያችን ይረዝማል ብለው ማመናቸው ህወሃቶች የገበቡት የክፋት አዘቀት ምን ያክል ጥልቅ እንደሆነ ያሰየናል።
ጥላቻ ለህወሃቶች የመኖሪያቸው ድንኳን ሁኖ አቆይቷቸዋል። ከእነርሱ ያልሆኑት በሙሉ ከጠላትነት በታች ስፍራ የላቸውም። ሁሉንም ጠላት አድርጎ ማየት ደግሞ ከፍርሃት እና በራስ ላይ ዕምነት ከማጣት የሚመነጭ መሆኑ ይታወቃል። አሁን አሁን እነዚህ ቡድኖች ፍራቻቸው ፈሩን ለቆ የራሳቸውን ጥላ የመፍራት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። የራሱን ጥላ መፍራት የጀመረ ቡድን ራዕይ ኖሮት በሰከነ መንፈስ አገርን የመሰለ ትልቅ ነገር ለመምራት ብቃት አይኖረውም። ህወሃቶች አስቀድሞ በነበርው የአቅም ማነስ ተግዳሮታቸው ላይ ፍርሃት ታክሎበት አገሪቷን ወደ ከፋ ሁኔታ ሊወስዷት እየሞከሩ ነው።
ለህወሃቶች አገር ማጥፋት ጀግንነት ሁኖ እንደሚቆጠር ድርሳናቶቻቸው ይመሰክራሉ። ለምስሌ “እኛ ከሌለን አገሪቷን እንበትናታለን” የሚለው ሟርት በእያንዳንዱ የጥፋት ቡድኑ አባል ልብ ውስጥ የተፃፈ ሃሳብ ነው። ከዚህ በላይ አገር የሚያጠፋ ሃሳብ የለም።” እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” የሚሉ ቡድኖች በአገሪቷ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው ስለ ሰላምና እድገት ማውራት ፈፅሞ አይቻልም። ሠላም ማለት የጦርነት አለመኖር ማለት አይደለም፤ ልማትም ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ማቆም ማለት አይደለም። ሠላምም ሆነ ልማት ህወሃቶች ከሚያወሩት የተለየ የአስተሳሰብ ደርዝ ያለው ትልቅ ፅንሰ ሃሳብ ነው። ህወሃቶች ይህን ትልቅ ትርጉም ያለውን ቁም ነገር ለመረዳት አዕምሮአቸው የተከፈተ አይደለም። በክፉ አስተሳሰባቸው ተተብትበተው፤ ከቂምና በቀል ራሳቸውን መለየት አቅቷቸው ራሳቸው ለራሳቸው የገነቧቸውን ህንፃዎች እየቆጠሩ ኢትዮጵያ በልማት እየገሰገሰች ነች ይሉናል። ዕለት ዕለት የንፁህ ሰው ደም እያፈሰሱ ከመቸውም ግዜ በላይ ሠላማችን ተጠብቋል ሲሉም ፈፅሞ አያፍሩም። ይህን ወሬያቸውን እውነት ነው ብለን እንድንቀበል የሚያደርገን አንዳችም እውነት የለም። ህወሃቶች የሃሰት ልጆች በመሆናቸው መዋሸት በእነርሱ ዘንድ የፖለቲካ ጥበብ ነውና በትልቁም በትንሹም ይዋሻሉ።
ለእነዚህ የጥፋት ቡድኖች የልማትንና የሠላምን ምንነት ለማስተማር መሞከር በጭንጫ መሬት ላይ መልካም ዘርን እንደመዝራት ይሆንብናል።የህወሃቶች አዕምሮ በጎ ነገር የማይዘልቅበት ፍፁም ጭንጫ ሁኗል። እነዚህ ቡድኖች ከህዝቡ ሁሉ በላይ ጠቢብ የሆኑ ይመስላቸዋል። እንደ ፈጣሪ ቃል እነርሱ ያሉት ካልሆነ ህዝቡ ሁሉ ቢጠፋ ግድ እስከማይኖራቸው ድረስ በትዕቢት ታውረዋል። ትዕቢተኛ ቡድን አገርንና ህዝብን ያጠፋል እንጂ አያለማም። ደም መፋሰስን ያበዛል እንጂ ሠላምን አያመጣም።የህወሃቶች የስንፍናቸው ብዛት የወለደው ግጭት አብሮ በኖረው ወደፊትም አብሮ መኖር በሚችለው ህዝብ መካከል ደም እያፋሰሰ ነው።በቅርቡ በአማራ እና በትግራይ ክልል ድንበር አካባቢ ተነስቶ የሰው ህይወት ያለፈበትን ግጭት ምሳሌ አድርጎ ማቅረብ ይቻላል።
በአጠቃላይ ህወሃቶች በአገሪቷ ጫንቃ ላይ እስካሉ ድረስ ሠላምም ሆነ ልማት ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነገር በኢትዮጵያችን አይኖርም። እነዚህን የጥፋት ልጆች ከቅዥታቸው ነቅተው ከሰው መሃል ሁነው እንደ ሰው ልጅ ያስባሉ ብሎ መጠበቅም ከንቱ ምኞት ነው። ለብዙ ዘመን ከዛሬ ነገ ከቅዥታቸው ነቅተው ሰው ይሆናሉ ብለን ስንመኝ ነበር። የቻሉትን ያክል ዘርፈው በቃኝ ይሉ ይሆናል የሚልም ተስፋ ነበረ። ምኞታችንና ተስፋችን ግን እንዲሁ በከንቱ ውሃ በልቶት ቀርቷል። በጎ ምኞታችንን የሚገዳደሩን ኃይሎች በወንበሩ ተቀምጠው ፈራጅ ሆነው ሳለ፤ ተስፋችንን በሚያመክኑ ቡድኖች እግር ተወርች ታስረን እያየን ዝም ብለን እንኖር ዘንድ ሰው መሆናችን ሊከለክለን ይገባል።አዎን ሰው መሆናችን ብቻ ህወሃቶች የሚፈፅሙትን እኩይ ተግባር ለማስቆም እንድንነሳ ያደርገናልና ሁላችንም አብረን ተነስተን በፍርድ ወንበር የተቀመጡ ክፉዎችን አደብ እናስገዛለን።
ህወሃቶች አገር አጥፊ ኃይሎች እንደሆኑ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚስማማበት እውነት ሁኗል። ከዚህ እውነት ለጥቆ የሚያሳስበን ብርቱ ነገር በዚያች አገር እጅግ በጣም ብዙ አደር ባዮች የመፈጠራቸው ነገር ነው።”እኛ ምን እናድርግ ታዘን ነው እንዲህና እንዲያ የምናደርገው “የሚሉ የሂሊና ሙግት የሌለባቸው ዜጎች በዚያች አገር የመብዛታቸው ነገር አሳሳቢ ነው። ሰው ለቁሳቁስ፤ ለሚበላና ለሚጠጣ ኃላፊ ነገር ብሎ የወንድሙን ደም ማፍሰስ ሲጀምር ያን ግዜ አገር መፍረስ ትጀምራለች። በተለይም እንዲህ ዓይነቱ ነውር ድርጊት በህግ አስከባሪው አካል መፈፀም ሲጀምር አንድ አገር እንደ አገር የመቀጠሏ ሁኔታ አደጋ ላይ ይወድቃል። ዛሬ በኢትዮያችን የፍርድ ቤት ወንበሮች በምናምንቴዎች ተይዘዋል፤ የፍትህ መዶሻዎችም በጨካኞችና በሃሰተኛ ልጆች እጅ ወድቀዋል። አገርንና ህዝብን ለመጠበቅ የተሰለፉ ኃይሎች የህዝባቸውን ደም በከንቱ የሚያፈሱ ሁነዋል። የፖሊስ ኃይሉም የዘራፊዎችንና የነፍሰ ገዳዩን ቡድን የሚጠብቅ እንጂ የዜጎችን ሠላም የሚጠብቅ ሊሆን አልቻለም። እነዚህ ኃይሎች ከሂሊናቸው በላይ ለሥጋቸው እንዲገዙ የሚያደርጋቸው ምን እንደሆነ ባናውቅም አደር ባይነታቸው አገርንና ህዝብን በብርቱ እየጎዳ እንደሆነ መካድ አይቻልም።
ታዝዤ የገዛ ወገኔን ገደልኩ የሚል የመከላከያ ኃይል አባል፤ ታዝዤ በሃሰት ማስረጃ ክስ መሰረትኩ የሚል ፖሊስ እና አቃቤ ህግ ፤ታዝዤ በሃሰት ማስረጃ ፈረድኩ የሚል ዳኛ ነገ የሚያስጠይቅ ዘመን ሲመጣ ማምለጫ ምክንያት እንደማይኖረው ሊገነዘበው ይገባል። ታዞ ወንጀል መፈፀም ከወንጀሉ ነፃ አያደርግም። በተለይም በህግ አስከባሪውና አስፈፃሚው አካል ይህን መሰሉ ነውር ሲፈፀም ማየት ለኢትዮጵያችን ትልቅ ውድቀት መሆኑን እነዚሁ አካላት እንዲያውቁት ያስፈልጋል።ታዞ ደግሞ ደጋግሞ ወንጀል መፈፀም ከአደር ባይነት በላይ የሆነ ራሱን የቻለ ወንጀል ነው። በንፁሃን ላይ ወንጀል ሲፈፀም አይቶ እንዳላዩ መሆን፤ ሰምቶም እንዳልሰሙ መምሰል አደር ባይነት ሊባል ይችላል ታዞ የገዛ ወገንን መግደል ግን ወንጀል መሆኑን ማወቅ ይገባል። ኢትዮጵያችን ከገጠሟት ቀውሶች መካከል አንዱ ነፍሰ ገዳዮችን እያዩ ዝም የሚሉ አደር ባዮች የመበራከት ነገር ነው። ከትላልቅ የኃይማኖት መሪዎች አንስቶ እስከ ተራው ምዕመን ድረስ ያለው ኃይል በዚህ እርግማን የተያዘ እስኪመስል ድረስ በዝምታ ተውጧል።ይህ ዝምታ የሚሰበርበት ግዜ እሩቅ አለመሆኑን ስንናገር በህወሃቶች ዘንድ ድንጋጤ እንደሚሆን እናውቃለን። እናም ዝምታው ይሰበራል።ዜጎችም ለፍትህ፤ለእኩልነት እና ለነፃነት የሚያደርጉትን ትግል አፋፍመው ይቀጥላሉ። እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል የተዘጋጁ ወጣቶች ሰይፋቸውን ከሰገባው መዘዋል።
ግንቦት ሰባት ንቅናቄም የጥፋት ኃይል መሆንን ምርጫቸው ያደረጉ ህወሃቶች የገነቡትን የጥፋት መረብ እንበጣጥሰዋለን። በወገኖች መካከል የሚፈጠረው ግጭት የመኖሪያቸው ድንኳን የሆናቸው የጥፋት ኃይሎችን አደብ ለማስገዛት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል እየሰራን ነው። ህወሃቶች ሆይ በዜጎች ደም እየቀለዳችሁ አትቀጥሉም። በተገኘው አጋጣሚ በተገኛችሁበት አምባ ሁሉ እንታገላችኋለን። በሚገባችሁ ቋንቋም እናናግራችኋለን። ደግሞም እውነት ከእኛ ዘንድ ስላለ አለ ምንም ጥርጥር እናሸንፋችኋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

50 ዓመት ሙሉ ባንድ ዱላ -- ዮናታን ተስፋዬ


(የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ)
ትናንትና የርዕዮትን ልደት ኢህአዴግ ሊያፈርሰው በሚቅበጠበጥበት የአንድነት ፓርቲ ቢሮ ለማክበር ተገኝተን ነበር ... (በእውነቱ ልደቷን በዛ መልኩ ለማክበር ለደከሙት አዘጋጆች ምስጋና ይገባል) ...
እናላችሁ የርዕዮትን ልደት ስናከብር ከተቀመጥኩበት ወንበር ላይ በሀሳብ ተነስቼ የኋሊት ወደ 50 ዓመታትን አዘገምኩ፡፡ ይህን ሁናቴ የፈጠረው በተለይ በርዕዮት ላይ በማእከላዊ ይፈፀም የነበረውን ግፍ ሳስብ ነበር፡፡ እርግጥ ማዕከላዊን ሳስብ ከርእዮት ሌላ ብዙዎች ባይነ ህሊናዬ ይዞራሉ - ዞን 9 ጦማርያን ደግሞ ልቤን ከነኩት ውስጥ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡
በተለይ የዚሁ የዞን 9 ጦማርያን አባላት ስለደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዘርዘር ባለ መልኩ ለ(ኢ)ሰመጉ በላኩት ሪፖርት ላይ የሰፈረውን የመርማሪዎች የጭካኔ ተግባርና ይፈልጉት የነበረው ነገር የኋሊት ግስጋሴዬን በንጉሱ ዘመን በተፈፀመ አንድ ክስተት ላይ አሳረፈኝ፡፡
ሰሞኑን ‹‹ግዝትና ግዞት›› የተሰኘ በኦላና ዞጋ የተፃፈ መፅሃፍ እያነበብኩ ያገኘኋት ታሪክ ነበረች ማረፊያዬ፡፡ በታሪኩ በ1959 ዓ.ም በብ/ጄነራል ታደሰ ብሩ የተመራው እና በዛው ዓመት ጥቅምት 23 የታቀደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተፈጠረ አንድ ክስተት ነበር፡፡ ይኸውም ህዳር 10 ቀን 1959 ዓ.ም ምሽቱን በሲኒማ አምፒር ሁለት የእጅ ቦምቦች የመፈንዳቱ ነገር ነው፡፡ በእለቱ በተከሰተው ፍንዳታም 14 ሰው ተጎድቶ እንደነበር አዲስ ዘመን በወቅቱ ዘግቦት ነበር፡፡
ይህን ክስተት ተከትሎም ‹ታአምራዊ› በሆነ ምርመራ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ይውላሉ፡፡ መ/አለቃ ማሞ መዘምር እና አቶ ተስፋዬ ደጋጋ፡፡ እዚህ ሁለት ሰዎች እርግጥ ለጄነራል ታደሰ የቅርብ ሰዎች መሆናቸው ስለአያያዛቸው ሁናቴ የሚያስረዳን ነገር ይኖረዋል፡፡ የሆነ ሆኖ እኔን በሀሳብ ያናወዘኝ ለእናንተም ላካፍላችሁ የወደድኩት ጉዳይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ስለተያዙበት እና ስለምርመራው ነገር ነው፡፡
እስቲ ከመፅሃፉ ይቺን ጀባ ልበላችሁ→
‹‹እንደተያዙም የምርመራው ትኩረት ምን እንደነበር ሲናገሩ፤ ‹‹ከተያዝን በኋላ የተካሄደው ምርመራ ጥቅምት 23 ቀን 1959 ዓ.ም በተደረግው ሙከራ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ቤታችን ከተፈተሸ በኋላ ግን በቤታችን ውስጥ ቦምብ መገኘቱ እና ‘የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ’ የተሰኘው በመ/አለቃ ማሞ መዘምር የተዘጋጀ በብዙ መቶ ገፆች ላይ የተፃፈ ረቂቅ መፅሃፍ ስላገኙ ጧት ማታ በድብደባ የሚደረገው ምርመራ በዚሁ ፅሁፍ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የቦምቡን ነገር የሚያነሱት በኛ እንደተወረወረ አድርገው የፃፉትን እድንፈርም ሲፈልጉ ብቻ ነው፡፡ በዚህ አይነት መ/አለቃ ማሞ መዘምር ብዙ ጊዜ ቦምቡን እንደወረወረ አድርገው በፃፉት ቃል ላይ እንዲፈርም ሞክረው እምቢ ባለ ቁጥር መደብደብና ማጎሳቆል ሆነ፡፡ በምርመራ ጊዜ ስለጥቅምት 23 ሙከራና ስለኦሮሞ ህዝብ ታሪክ መፅሃፍ፤ በፊርማ ጊዜ ግን ስለቦምቡ የመሆኑ ሚስጥር እየዋለ ሲያድር ግልፅ ስለሆነ እውነተኛውን ነገር ፍርድ ቤት በምንቀርብበት ጊዜ ለመግለፅ በማሰብ በፃፉት ነገር ላይ ሁሉ መፈረም ጀመርን፡፡››
ይህን ፅሁፍ ሳነብ አሁን ባለሁበት ዘመን የተፃፈ የጋዜጣ ፅሁፍ እንጂ የምር የታሪክ መፅሃፍ የማነብ ሁሉ መስሎ አልተሰማኝም ነበር፡፡ በዞን 9ጦማርያን፣ በነርዕዮት ፣ በነእስክንድር፣ አብረሃ፣ የሺዋስ . . . የሆነው ከዚህ የተለየ አልነበረም፡፡ አሁም በማዕከላዊ እየተገረፉ ያሉ የነፃነት ታጋዮች ይኸው በድብደባ እመኑልን በሚል ሰብብ መከራቸውን ያያሉ፡፡ ደብዳቢው ይቀየራል ዱላው ግን ያው ነው፡፡ 50 ዓመታት አለፉ - ዘመን ተቀየረ፤ ዛሬም ግን የተለየ አቋም ያለው ሰው ከዱላ እና ስቃይ የሚድንበት ስርዓት አልተፈጠረም፡፡ ‘አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ’ እንዲል ቴዲ - እውነት ነው አዲስ ገራፊ፣ አዲስ ተገራፊ - 50 ዓመት አንድ ዱላ! የዱላ ስርዓት!
እጅግ የሚያሳዝነው ግን ባለንበት መቆም እንኳን አቅቶን ወደ ኋላ የመውረዳችን ነገር ነው፡፡ የዛሬ 50 ዓመት ላይ የነበረው ስርዓት ቢያንስ ስዩመ እግዚአብሔር - ፍፁማዊ መሆኑን አውጆ ያለ መሆኑ ይወስዳቸው የነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ባወግዝም የምረዳበት አይን ግን ከዘመኑ አንፃር ነው(Order of the day)፡፡ ሌላው ጉዳይ ደግሞ በወቅቱ የዚህ አይነት ምርመራ ይደረግባቸው የነበሩት ወንድሞች ስርዓቱን ወቅቱ በሚፈቅደው(በሚያስገድደው) መልኩ በሀይል መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ መንቀሳቀሳቸው የዘውዱ ስርዓቱ ሊበቀላቸው ቢፈልግም ያሳዝን ይሆናል እንጂ አያስገርምም፡፡
በዚህ በኔው ጉደኛ ዘመን ግን እንኳን መፈንቅለ መንግስት ሊያስነሱ ‘የሚፈለገው’ ለውጥ በራሱ ጊዜ ተወስዶና በተጠና መልኩ ይሁን ብለው የሚከራከሩና ቅድሚያ ማህበረሰቡ መንቃት፣ ስለሀገሩ ተጨባጭ ሁናቴም aware መሆን አለበት ብለው ያስተማሩ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን በተመሳሳይ ወይም በከፋ መልኩ መሰቃየታቸው እጅግ የሚያስቆጭ እና ምን ያህል ኋላ ቀር ስርዓት ውስጥ እንዳለን የሚያመላክት ነው፡፡ ምርመራው በዱላ ብቻ ሳይሆን ፍፁም ከሰብዓዊነት ውጪ በሆነና የሰውን ክብር ሆን ተብሎ በማዋረድ የተሞላ መሆኑ፣ ለማሸማቀቅ በስነልቡና ጭምር የሚፈፀመው በደል በራሱ እጅግ እጅግ ያሳምማል፡፡ ያስቆጫል!
እናም ርዕዮት ዛሬ የዚህ ፈላጭ ቆራጭ፣ ዘመኑን ፈፅሞ ያልዋጀ እና ኋላ ቀር ስርዓት ሰለባ ሆና የዛሬ 50 ምናምን ዓመት አባቶቿ የሄዱበትን መንገድ እየሄደች ነው፡፡ በጨለማ ቤት እጥፍጥፍ ብለው የተኙባትን መደብ እሷም ጎኗን አሳርፋበት እያለፈች ነው፡፡ ብዙዎች የዚሁ ሰላባ ሆነዋል፤ እየሆኑም ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ጊዜው ይለወጣል እንጂ ያው አንድ አዙሪት ውስጥ ነን፡፡ ጥቂቶች ሰፊው ህዝብ ላይ የሚያዙበት አዙሪት፡፡ እፍኝ የማይሞሉት ይህን ትልቅ ሀገር ለብቻቸው ሲፈነጩበት ይኸው 50 ዓመት ያለፈው አዙሪት፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ወደ ትግል የሚገፋ ምን ነገር እንዲመጣ እንጠብቅ? እስከመቼስ ይሆን ጥቂቶች በዚህ መልኩ ዋጋ እየከፈሉ ብዙዎቻችን ዳር ቆመን ከንፈር መጣጭ ሆንን የምንዘልቀው?
አምናለሁ የግፍ ፅዋው ይሞላል! አምናለሁ በመጨረሻም ህዝብ ይነሳል፣ ከፊት ሆኖ የሚመራ መሪም ይኖረናል! ነፃ ሆነን ተፈጥረን ተገዢ የምንሆንበት አንዳች ምክንያት የለም የምንልበት ቀን፣ ሆ ብለን የምንነሳበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ይሰማኛል! ነገ አዲስ ቀን ነው!
‹‹ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ 
የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት እርስቴ 
ቀላል ይሆናል - ቀላል ይሆናል!››
እናቸንፋለን!

የመኢአድ ምክትል ፕሬዝደንት አዘዞ ጦር ካምፕ መወሰዳቸው ተነገረ።


ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው የተዘገበው የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘመነምህረት አዘዞ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ መታየታቸውን ፓርቲያቸው ገለጸ።
መኢአድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት የድርጅታቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው እንደነበር አስታውሷል።
አቶ ዘመነ በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ያወሳው መኢአድ ፤በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ መረጋገጡን ገልጿል።
<<በአቶ ዘመነ ላይ የደረሰባቸው ስቃይና እንግልት በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ ፈጽሞ የማይገመት ነው >>ብሏል-መኢአድ። ከአቶ ዘመነ በተጨማሪ ጠቅላላ ጉባኤውን ተሳትፈው የተመለሱት የፓርቲው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያሱ ሁሴን 3 አመት ተፈርዶባቸው እስር ቤት እንደሚገኙ እንዲሁም የፓርቲው አመራር አካላት የሆኑት አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንንና አቶ ጥላሁን አድማሴ ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልጿል።
በሌላ በኩል ምርጫ ቦርድ- መኢአድ በምርጫ 2007 እንዳይሳተፍ የኢህአዴግ ቀኝ እጅ ሆኖ በመስራት ላይ እንዳለ ያወሳው መግለጫው፤ ፓርቲው በምርጫው እንዳይሳተፍ ከተደረገ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡
ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በፓርቲው ላይ የሚፈጽሙትን በደል ለማስቆም በሚደርገው ትግልም ህዝቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ መኢአድ አቅርቧል።

”የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ


Fitsum Ze Ethiopia's photo.
Fitsum Ze Ethiopia's photo.
Fitsum Ze Ethiopia added 2 new photos.
”የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም” የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ
“በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተናገረ፡፡
ዮሐን ፔርሶን ኦጋዴን በረሃ
አንድ ዓመት ከሁለት ወር (14 ወራት) ከሥራ ባልደረባው ዮሐን ፔርሶን ጋር ኢህአዴግ አስሮት የነበረው ጋዜጠኛ ሺብዬ ለጎልጉል የአውሮጳ ዘጋቢ ይህንን የተናገረው በዖጋዴን ክልል የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም መሰራጨቱን ተከትሎ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡
“በአካል ሰላም አለኝ፤ አእምሮዬ ግን አልዳነም፤ ሁሌም እረበሻለሁ፤ በዓይኔ ያየኋቸው፣ በጆሮዬ የሰማኋቸውና በበቂ ምስክሮች ያረጋገጥኳቸው ሁኔታዎች ዕረፍት ይነሱኛል” ሲል አስተያየቱን የጀመረው ሺብዬ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግፍ ከሙያው አስገዳጅነት በመነሣት ከተባባሪዎቹ ጋር በመሆን ለዓለም እንደሚያሳውቅ ግልጽ አድርጓል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ከፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ተገኘ” በሚል ዘወትር እሁድ በሚተላለፈው የፖሊስ ክፍለ ጊዜ የተላለፈውን ዘጋቢ ፊልም (ድርሰት) የኢህአዴግን ዓመታዊ ቋት የምትሞላውን አሜሪካ በእስረኞች አያያዝ የገሃነም ተምሳሌት አድርጎ ያቀረበ ነው፡፡ ኢህአዴግ በልማት ስም የሚያገኘውንና ለባለሥልጣኖቹ የግል ሃብት ማካበቻ እንዲሁም በየጎሬው ለተፈጠሩ እስር ቤቶች ግንባታ የሚደጉሙትን አገራት በሰብዓዊ መብት አያያዝ ከዜሮ በታች አድርጎ ያብጠለጠለ ነበር፡፡ ከተለያዩ ድረገጾችና የዩትዩብ ምስሎች በተለያዩ እስርቤት ያሉትን በማነጋገር ተገጣጥሞ የቀረበው “ድርሰት” (ዘጋቢ ፊልም) ተከትሎ ይሁን አይሁን በግልጽ ባይታወቅም የኢህአዴግ የልብ ወዳጅ ኖርዌይ እነ ሺብዬ ያዘጋጁትን ዘጋቢ ፊልም ይፋ አድርጋለች፡፡
Nrk2 በተሰኘው የኖርዌይ መንግሥታዊ ቴሌቪዥን ማስተባበል በማይቻልበት ደረጃ በዖጋዴን የተፈጸመውን ርኅራኄ የሌለውን ዘግናኝ ሰቆቃ ለመመልከት ተችሏል፡፡ (በተለይ በአውሮጳ የሚኖሩ ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይችላሉ)
አብዱላሂ ሁሴን
የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪና የሚዲያ ክፍል ኃላፊ የነበረው አቶ አብዱላሂ ሁሴን ከሱማሌ ክልል ይዞት ወደ አውሮጳ ባመጣው በራሱ በኢህአዴግ ባለሙያዎች የተቀዱ ማስረጃዎች፣ ሰለባዎችና የክልሉ (ምክትል) ፕሬዚዳንት በግልጽ ሰቆቃና ግፍን ሲያውጁ በሚሰማበት፤ ወታደሮች ሲገድሉ፤ በቢሮ ግምገማ ላይ ተቀምጠው ስለፈጸሙት የግፍ ጀብዱ ሲተርኩና የፈጸሙት ግፍ አልቃም ተብሎ ሲገመገሙ እንደወረደ በሚያሳየው በዚህ ዘጋቢ ፊልም የእነ ሺብዬ መከራ በውል ቀርቧል፡፡ (ቪዲዮውን እዚህ ላይ መመልከት ይቻላል) በተለይም ፎቶ አንሺው ዮሐን ፔርሶን የክንዱ አጥንት በጥይት ተሰብሮ፣ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ ቀብረው ስቃዩን ሲያዳምጡ የሚያሳየው ምስል እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ ኢህአዴግ በእስረኞች አያያዝ “ጻድቀ ጻድቃን” ነኝ ባለ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኖርዌይ ቴሌቪዥን ያሰራጨው ዘጋቢ ፊልም የኢህአዴግን አውሬነት ያሳየ ለመሆኑ አብዛኞች አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡
የኢህአዴግ የልብ ወዳጅና የልማት አጋር ኖርዌይ እንዲህ ዓይነት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን ሊነካካ በሚችል ጉዳይ ጣልቃ ስትገባ ይህ በመጀመሪነት የሚጠቀስ ነው፡፡ እንግዲህ ይህንን ተከትሎ ነበር ጋዜጠኛ ሺብዬ አስተያየት የሰጠው፡፡ እርሱ እንደሚለው ሙያዊ ኃላፊነቱ በዚህ በዖጋዴን የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ እንዲጋልጥ አነሳስቶታል፡፡ ለወትሮው ወደ ዖጋዴን አንድም ሚዲያ እና የሲቪክ ተቋማት ድርሽ እንዳይሉ በሩን ጠርቅሞ የዘጋው ኢህአዴግ ባላሰበውና ባልጠበቀው መንገድ እነ ጋዜጠኛ ሺብዬ ይህንኑ ለመዘገብ ክልሉን ዘልቀው ሊገቡ ችለው ነበር፡፡
ማርቲን ሺብዬ እና ዮሐን ፔርሶን በኦጋዴን በረሃ
“ያየነውን ለዓለም ማሳየት፣ የኢህአዴግን ፕሮፓጋንዳ ማጋለጥ ዓላማችን ነው” የሚለው ሺብዬ በፖሊስ ፕሮግራም ቀረበ ስለተባለው የኢህአዴግ “ድርሰት” የሰጠው ምላሽ (ኢህአዴግ ይህንን ያህል ከሚለፋ) ማዕከላዊን እና ቃሊቲን ለጋዜጠኞች፣ ለቀይ መስቀልና ለዓለምአቀፍ ተቋማት ክፍት በማድረግ ምስክር ማግኘት ብቻ ይበቃዋል ሲል ፕሮፓጋንዳውን አጣጥሎታል፡፡ በቃሊቲ እስረኞች እንደሚሞቱ፣ በቂ የሚባል መጸዳጃ እንኳን እንደሌለ የተናገረው ሺብዬ አሁን ያለሁበት ቦታ የፈለኩትን ማድረግ የምችልበት ቢሆንም እዚያ ያሉትን ንጹሃን መዘንጋት ግን አይቻለኝም፤ ዘወትር እረበሻለሁ” በማለት ተናግሯል፡፡ በማያያዝም ይህንኑ ኢህአዴግን የሚያጋልጥ በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሐፍ በሚቀጥለው ወር ለገበያ እንደሚበቃ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ለሚማቅቁ ወገኖች መልካም ቀን እንዲመጣ ምኞቱን ገልጾዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘጋቢ ፊልሙ ይፋ በሆነ ማግስት ዓለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ኮሚሽን በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ወሬራ እና በመመሪያ ሰጪዎቹ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት በጦር ወንጀለኝነት ለመክሰስ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩ ታውቋል፡፡
ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች በእስር በነበሩበት ወቅት አቶ መለስ “የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” በማለት ለፈጠሩት ፓርላማ ሲፈላሰፉና በህግ የበላይነት እንደሚያምኑ እያስጨበጨቡ ሲናገሩ ቢቆዩም የልመና ኮሮጃቸውን የሚሞሉት የምዕራባውያን ዜጎችን አስረው መቀጠል እንደማይችሉ ሲረዱ “በዕርቅ” መፍታታቸው መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
በሌላ በኩል ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዖጋዴን ዙሪያው ገባ ታጥሮ ሰሚና ተመልካች እንዳይኖር ተደርጎ የከፋ ወንጀል ሲካሄድ እንደነበር የስዊድን ጋዜጠኞች ዜና ሳይሰማ ያገባናል ለሚሉ ወገኖች ሁሉ የማሳሰቢያ ዜና መስራቱ ይታወሳል፡፡ በተለይም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቀጥታ ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም፡፡ ከመግለጫው የተወሰደው ቃል እንዲህ ይነበባል፡-
“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቀበሌ መኖር የማይችሉ ዘላኖች (አርብቶ አደሮች) ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ሰሞኑን የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ”
“… ኦጋዴን በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተድበስብሶ ቢከርምም ዛሬ በሶማሊያ የተከሰተውን አስፈሪ ርሃብ ተከትሎ ይፋ መሆን ጀምሯል። ድርጅታችን በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ ክልል፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈፀሙትን ጭፍጨፋዎች በመቃወም እንዳደረገው ሁሉ በኦጋዴን የተፈፀመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ነው። የኦጋዴን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመሆኑ ይህ መግለጫ የሚደርሳችሁ አካላት በሙሉ ድርጊቱን በመቃወም አግባብ ያለው ተፅዕኖ በማድረግ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ ትግላችሁን እንድትቀጥሉ አጥብቀን እናሳስባለን” ሲል ጥሪውን አስተላልፎ ነበር። (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
በዖጋዴን የደረሰውን በተመለከተ እንዲሁም የሁለቱን ጋዜጠኞች በተመለከተ እስካሁን የዘገብናቸውን ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
ኢትዮጵያ፡ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የማሰቃየት ድርጊት ይፈጸማል፤ ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።
በሚዲያ መረሳት ያስፈራል፤ “ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”
“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!! ኢህአዴግ ለመክሰስ ሲፈልግ ፊልም እንደሚደርስ ተረጋገጠ

Thursday, January 15, 2015

ሬዲዩ ፋና፣ ‹‹አንድነት ከአሸባሪ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል›› በማለት ወነጀለ


January15,2014

ፍኖተ ነፃነት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሬድዩ ፋና እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ/ኢቲቪ) በአንድነት ፓርቲ ላይ የጠነሰሱት ሴራ ተጋለጠ፡፡
አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አያይዘው ገልፀዋል፡፡
አንድነት እየቀረበበት የሚገኘው ውንጀላ መሰረተ-ቢስ መሆኑን የገለፁት አመራሮቹ፣ ፓርቲው አሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስብ እና ለዚህም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የአንድነት ደጋፊዎች፣ በፓርቲው እውቅና ተሰጥቷቸው የድጋፍ ሰጪ ቻፕተር ማቋቋማቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹‹አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት ብቻ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ሰዎች ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ›› የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በበኩላቸው የፓርቲው የፋይናንስ አሰራር ግልፅነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ገልፀው፣ በየዓመቱም ኦዲት እንደሚደረግና ምርጫ ቦርድም ለተከታታይ ዓመታት የፓርቲውን የፋይናንስ አሰራር ግልፅነት የሚታይበት እንደሆነ ጠቅሶ ለፓርቲው ሰርተፍኬት መስጠቱን› አቶ ግርማ አውስተዋል፡፡ የራዲዮ ፋና ውንጀላም ከዚህ አንፃር ተገቢነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡ ይህን መሰሉን ውንጀላ የአንድነት አባል ነን የሚሉ ሰዎች ባሳለፍነው ሳምንት በሬዲዮ ፋና ላይ ቀርበው ያሰሙ ሲሆን የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኛ ነኝ የሚል ብሩክ ከበደ፣ የተባለ ግለሰብም ይህን መሰሉን ውንጀላ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዘደንት አቶ ግርማ ሰይፉ እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ በሬዲዮ ፋና “ሞጋች” በተባለ ፕሮግራም ላይ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም በቀረቡበት ወቅት የገዢው ቡድን ተጠሪ የሆነው ብሩክ ከበደ ፣ “አንድነት ፓርቲ በሽብር ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይሰበስባል” የሚል ውንጀላ ሲያቀርብ እንደነበር የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት አስረድተዋል፡፡
ገዢው ፓርቲ አሰርጎ ባስገባቸው ሰዎች “የደንብ ጥሰት አለ” የሚል ውንጀላ ሲቀርብበት የነበረው አንድነት ዛሬ ላይ ደግሞ ውንጀላው በህዝብ ስም በተቋቋሙት ሚዲያዎች አማካኝነት “በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል” በሚል ሌላ ውንጀላ እየቀረበበት ይገኛል፡፡
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ገዢው ቡድን “አንድነት ፓርቲ ከግንቦት ሰባት 1 ሚሊዮን ብር ተቀብሏል፡፡” የሚል ክስ በተላላኪዎቹ በኩል ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የሚያጋልጥ መረጃ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡

እኽኽ....እስከመቼ ?


ኢትዮጵያን እየገዛት ያለው የሰለጠነ መንግሥት ነው ወይስ በህገ- አራዊት የሚመራ የጫካ መንግሥት ? አንድ ፋኖ ከጫካ ወጥቶ 24 ዓመት ከተማ ገብቶ ለዚያውም ትልቋን አገር ኢትዮጵያ እየገዙ ፥ ከሸበጥ ጫማ ወደ ጣልያን ምርጥ የቆዳ ጫማ በትራንስፎርሜሽን ዑደት ከተለወጡ በኋላ ፥ በትግል ላይ ሳሉ አንገታቸው ላይ ሸብ የሚያደርጉትን « ኩሽክ » የተባለውን ሻርፓቸውን በሲልክ ክራቫት ከለወጡ በኋላ ትንሽ .... ከተሜ... ከተሜ ይሸታሉ ሲባሉ ፣ ጭራሽ « እዚያው ደደቢቴ ከያዘኝ ልክፍቴ » ከሚለው የአማራ ህዝብ ጥላቻቸው ጋር እስከመቼ ድረስ ነው አገራችንን እያመሷት የሚቀጥሉት ?
በጨቋኙና ግፈኛው የስታሊን አገዛዝ ዘመን ወደነበረ አንድ ቀልድ አዘል፣ ነገር ግን እውነት ገላጭ ሰፈር ልውሰዳችሁ፡፡ጊዜው የቀልድ ባይሆንም ፣ ፍራሽ አውርደን ሙሾ ደርድረን የምናለቅስበት ወቅት ቢሆንም የመለስ ራዕይ እየተፈጸመ ካለባት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ከስታሊን ዘመን ጋር ስለተመሳሰለብኝ ነው ቀልዱን የሰነቀርኩባችሁ ፡፡ ይቅር በሉኝ ፡፡ አንድ በድሜ የገዘፉ አሮጌት ሴት በስታሊን ዘመን ሁለት ሰዓታት ያህል በአንዘፍዛፊ በረዶ መሃል ቆመው አውቶቡስ ሲጠብቁ ፣ አውቶብሱ ጥቅጥቅ ብሎ ሳያቆምላቸው ያልፋል ፡፡ ጥበቃቸው ሰአታት ጨመረ ፡፡ በስተመጨረሻ አንድ ትንሽ የተረፈ ቦታ ያለው አውቶቡስ ቆመላቸው ፡፡ አሮጊቷ እንደምንም ብለው በአጋዥ ጎታቾች ተረድተው አውቶቡሱ ላይ እንደወጡ « ተመስገን አምላኬ ለዚህ ያበቃኽኝ ብለው ለፈጣሪያቸው ምስጋና ያቀርባሉ » ወዲያው የአውቶቡሱ ሾፌር ፣ እማማ ! እንደርሱ አይባልም ፡፡ ዘላለማዊ ክብር ለጓድ እስታሊን ነው የሚባለው ብሎ ያር ’ቃቸዋል ፡፡
ይቅርታ ጓድ ! እኔ ኋላ ቀር አሮጊት ስለሆንኩ ነው የማይባለውን ያልኩት በማለት ለሾፌሩ ከመለሱ በሗላ ሁለተኛ አይለመደኝም ጓድ በማለት ጥቂት ደቂቃዎች ቆይተው ፣ ጉሮራቸውን እኽኽ በማለት እንዳጠሩ ፣ ለአውቶቡሱ ሾፌር ሌላ ጥያቄ ወረወሩ ፡፡ ይቅርታ ጓድ ! እኔ አሮጊትና ማስታወስም የተሳነኝ ሰው ነኝ ፣ የግዜር ስሙን እንዳልጠራ ተከልክዬ ስታሊንን ማመስገን እንዳለብኝ ተነግሮኛል ፡፡ ስታሊን ሲሞት ደግሞ ምን ልል ነው ? በማለት እንደጠየቁ ? ጓድ ሾፌር ፈጠን ብሎ አዩ እማማ ! ያንግዜ ክብር ምስጋና ለፈጣሪ ብለው ይመልሳሉ አላቸው ብሎ በስታሊን ጊዜ የተቀመጡ የቀልድ መዘክሮች ያስታውሳሉ ፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ እንዳለው ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆኑ ነው ፡፡ስንት ዓመት በአዳር ጸሎት ሲያነበው የነበረውን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቃል ለእምብርቱ ማስፊያና ለሆዱ ሲል እንደካደው ፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ይቅር በሉኝ ደሳለኝ የሚል ስም ያላችሁ ፡፡ ስሙን ያራከሱት ወያኔዎች ናቸው ፡፡ ወያኔዎች አማራን ለማዋረድ ሲሉ ፣ለአህያቸው ሸገር ሲገቡ በፊት አውራሪነት እየነዱ ላስገቡት የቡላ አህያ መጠርያ ያወጡለት ስም ደስ አለኝ ይባላል ፡፡ ዛሬ በዙርያቸው የሰበሰቧቸውን ትግራይ ያልሆኑ ብሄረሰቦች ሁሉ ሲጠሯቸው « ደስአለኞች» እያሏቸው ነው የሚጠሯቸው፡፡
ማን ነው ቀልድ ያለው ከሶቭየት መንደር ብቻ ነው ያለው ? ፡፡ ኢትዮጵያችን እኮ የቅኔ መዝረፊያ አገር ብቻ አይደለችም የቀልድም መፈብረኪያ ጭምር ናት ፡፡ ኃይላማርያም ሳይረሳ ! ወደ ሰማሁት ቀልድ ልውሰዳችሁ ፡፡ ኃይለማርያም ደስ አለኝን የውጭ አገር ጋዜጠኞች ፣ እርሶም ተጋዳላይ ነበሩ እንዴ በማለት ይጠይቁታል ? ኧረ እኔ እቴ ! አባቴ ነበር ተጋዳላይ ! ዝርዝር ውስጥ አልገባም ኢትዮጵያ እውነትም የቅኔ አገር ናት ፡፡
እኽኽ ! እስከመቼ ?
ፈረንጆቹ short memory የሚሉት የመጃጀት በሽታ ካለተጠናወተን በስተቀር ወደ ኋላ 24 ዓመታት የተካሄዱትን ኢትዮጵያን ከአማራ ዘር ጋር በማመሳሰል ጥንታዊ ታሪኳን የማጥፋት ዘመቻ ሳንቆጥር እስቲ የቅርቡን ክስተት እንውሰድ፣ በመንገድ ሥራ ስም ለፋሽስት ጣልያን አትገዙ ብለው የገዘቱትንና መስዋዕት የሆኑትን አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ከስፍራው ሲነሳ ምን አለን ? ነብሱን ይማረውና ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እዚያች ሃውልት ስር ነበር ፣ አንድ ሰካራም ጀብራሬ ሽንቱን ሲሸና አግኝቶት ከጀብራሬው ጋር ቦክስ ተጋጥሞ በእልህ እመብርሃን ኢትዮጵያን ረሳሻት በሚል ግጥም ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት የሚለውን ድንቅ ተውኔቱን የደረሰው ፡፡
ወመዘክር ውስጥ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቀመጡ የታሪክ ድርሳናት ለስኳር መጠቅለያ ሲቸበቸቡና ፣ የአማራ ታሪክ በመጽሃፍ መልክ አይቀመጥም ተብሎ ሲቃጠሉ ምን አልን ? ጉድ አንድ ሰሞን ነው የአንድ ሳምንት ጩኽት ፡፡ ለዚህ ደግሞ የወያኔ ትግሬዎችን የተባበሯቸው ብዙ ደስአለኞች ጭምር ናቸው ፡፡ ለአንዲት ዛኒጋባ ቤት ማቆሚያ ቦታ እስከተሰጣቸው ድረስ እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው የሚሉ ሆድ አደሮች እስካሉ ድረስ ገና ብዙ ጉድ ይታያል ፡፡በወገኖቻቸው እልቂት ላይ ደደቢት ሄደው ፣ ወገን በወገኑ ላይ ላደረሰው እልቂት ካገር ገዳዮች ጋር ብብት ለብብት ተቃቅፈው ዳንስ ከሚያጦፉት ሰዎች በላይ ምን ምስክርነት አለ ? ደሳለኝ መባላቸው ሲያንሳቸው ነው ፡፡ ታንክ ላይ ወጥቶ ሰላምታ ከሚሰጥ አርቲስት ያድናችሁ ፡፡ ከሳሞራ ጉያ ውስጥ ሰምጣ ክምትደንስ መበለት ሴት ያርቃችሁ ፡፡
የጀግናዋ መሪ ጣይቱ ብጡል አሻራ የሆነው ፥ በታሪካዊ ቅርስነት ተመዝግቦ መያዝ የሚገባው ፥ ጥንታዊ ሆቴል ፣ ለባለጊዜዎች በማትረባ ሶልዲ ተሸጦ እኽኽ ብለን አዝነን እንዳልኖርን ፣ በዚህ ሆቴል ውስጥ በቅርቡ ደረታቸውን ለጥይት ያሉ ቆራጥ የኪነጥበብ ሰዎች መንግስት አስነፋጭ የሆኑ ህዝባዊ ሥራዎቻቸውን ስላቀረቡና ፣ ህብረተሰቡን ስላነቁበት የጎረበጠው የትግራይ ወያኔ ቡድን ፣ እዛው ጃዝ አምባ ላውንጅ አዳራሽ ላይ ክብሪቱን እንደጫረ እየተረጋገጠ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ያሳያችሁ ! ከጣይቱ ሆቴል እስከ ጊዮርጊስ ድረስ ርቀቱ ምን ያህል ይሆን ? ወይስ እሳት አደጋ ጣቢያ ከዚያ ተነስቶ ይሆን ? አላውቅም ድሮ በማውቀው ከሆነ የማወራው ይቅር በሉኝ ፡፡
ሴራው እንዲህ ነው !! ፡፡ ከጠዋቱ አንድ ሰአት በፊት አንድ የጃዝ አምባ ሠራተኛ ያለወትሮው በጠዋት ገብቶ ወጥቷል ፡፡እርሱ ከወጣ በኋላ ከጃዝ አምባው አዳራሽ ላይ እሳቱ ተነስቷል ፡፡ ያ ሰው ማነው ? ገብራይ ? ለታይ ?ወይስ ካላዩ አይታወቅም ፡፡ እንዲታወቅም አያስፈልግም ፡፡ ምክንያቱም ሴራው በአማራ ቅርስነት ተብሎ በሚገመተው ላይ መዝመት ነዋ !! እጅግ የሚገርመው ! ይህ በወያኔ ትግሬዎች የተለኮሰ እሳት ጣራውን ይዞት እስኪወርድ ድረስ ጊዮርጊስ አጠገብ ያለው የእሳት አደጋ ፣ የአደጋ መጥሪያ ስልኩን አጥፍቶ እሳቱ ስራውን እስኪጨርስ ድረስ ቁጭ ብሎ ነበር ፡፡እግዜር ያሳያችሁ ! ሰው በመኪና ሄዶ ነው ኧረ ! አገር ነደደ ያላቸው ፡፡መጥተውስ ምን ሠሩ ? ይዘውት የመጡት የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና አይሰራም ፡፡ ይህ የኔ ፈጠራ አይደለም እዚህ ጋዜጣ ላይ የሴራውን ደባ ታነቡታላችሁ ፡፡http://www.ethiopianreporter.com/…/8520-%E1%8B%A8%E1%8A%A5%…
አገራችንን እየገዛ ያለው ማነው ? እንደድሮው የሰፈር ጋንጊስተሮች ቡድን የቻይና ግሩፕ ? ኧረ እነርሱ በስንት ጣማቸው መንግሥት ባይሆኑም በሰፈር አዛውንቶች ተግሳጽ ጸጥ እኮ ይሉ ነበር ፡፡ እነኚህ እኮ ከመንደር ዱርየ በታች የወረዱ የደደቢት ደደቦች ናቸው ፡፡ የአንድ ጋዜጠኛ ሚስት ነሽ ብለው ፣ ከነህጻናቶቿ በምግብና በመኝታ ቀጥተው ወደመጣችበት አገር ዲፖርት የሚያደርጉ መንግሥት ናቸው ወይስ ዱርየዎች ? ያሳፍራል ! የደደቢቶቹ እነ ካህሳይና ወይም ግርማይ ኤርፖርት ላይ ስልጣን በችሎታ ሳይሆን በዘር ተሰጥቷቸው እስከዛሬ ስንቱን አስምጠው ? ስንቱን አሳልጠው ይሆን ? እኽኽ እስከመቼ !!
Like ·  · 
ሰላማዊ ትግል ውጤት እያመጣ እንደሆነ የሚታወቀው
የአምባገነኖች እስር ቤት በሰላማዊ ተጋዮች ሲሞላ ነው::
ማህተመ ጋንዲ
Like ·  · 

Tuesday, January 13, 2015

ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸውን ታስረው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተገለጸ


እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ ውጭ ጠያቂ ተከልክሏል
okello a
የቀድሞው የጋንቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸው ታስሮ ጨለማ ክፍል መታሰራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
አቶ ኦኬሎ ቂሊንጦ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ በእስር በሚገኙበት እስር ቤት እጅና እግራቸውን ታስረው ብቻቸውን ጨለማ ክፍል እንዲገቡ እንደተደረጉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ቂሊጦ ማረሚያ ቤት እስረኞችን ሊጠይቁ ሄደው እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ እዚያው በእስር ላይ ካሉ ሰዎች አቶ ኦኬሎ ያሉበትን ሁኔታ መረዳታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የ18 አመት እስር ፍርደኛው ታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ ውጭ ሌላ ሰው መጠየቅ እንደተከለከለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት


ወይዘሪት ወይንሸት፣ ንፍስ ስልክ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች ከረፋዱ 5፡30 ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባት ለፍኖተ-ነፃነት የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወይዘሪት ወይንሸት፣ ነፍሰጡር መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን ደብዳቢዎቹም ሆዷን በመርገጥ ድብደባውን ሲፈፅሙባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደብዳቢዎቹ ድብደባውን ፈፅመው የተሰወሩ ሲሆን ወይዘሪት ወይንሸት፣ በአሁኑ ሰዓት ራሷን ስታ ሆስፒታል መግባቷን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወይንሸት፣ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ድምፅ የአስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆና በመመረጥ በምርጫው ላይ ጉልህ ሚና በመጫወት ድርሻዋን መወጣቷ ይታወሳል፡፡ በእለቱ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአንድነት ስም የሚነግዱትን ግለሰቦች በማውገዝ አስተያየቷን መሰንዘሯን ተከትሎ ድብደባው ሊፈፀምባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወይዘሪት ወይንሸት፣ በፓርቲው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያላት ወጣት ከመሆኗም በተጨማሪ የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ሀላፊ በመሆን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ በአንድነት አባላት ላይ ድብደባ ሲደርስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ባለፈው እሁድ በአቶ መሳይ ትኩ፣ ላይ ድብደባ መፈፀሙ ይታወሳል፡፡
Like ·  ·  · 21515

ዶር ዳኛቸው አሰፋ( ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)


ኢትዮጵያ አለች ወይ?
አንድ የተማረ ሰው ከ አዲስ አበባ ወጥቶ ወደ ሌላ ክልል ሄዶ ስራ ሲሰራ ደሞዙ ተቆርጦበት ወይም ዘግይቶበት ሰለ መብቱ ቢጠይቅ የሚሰጠው ምላሽ እኔዴውም ከ አላገራቹህ መጥታቹህ ስራ ስላገኛቹህ ልታመሰግኑ ይገባል ይባላሉ፥፥ አሁን ያለንበት ደረጃ አሥከፊና አስቸጋሪ ነው፥፥ እነዴውም አሁን እየጠየቅን ያለነው፥ አገራችን አለች ወይ ነው? ኢትዮጵያ አለች ወይ? ልክ ከ አዲስ አበባ ወጣ ስትል ከየት ነው የመታኽዉ ትባላለህ፥፥ ልክ ሌላ አገር የሄድክ እስኪመስልህ፥፥ ምንም አይነት ፕሮቴከሽን የሌለባት አገር ሁናለች፥፥ መጀመሪያ የጠነሰሱት ቢህል አሁን እያበበ ነው፥፥ የ አገሪቱ ሁኔታ ኢዝ አት ስቴክ (is at stake)፥፥ አንተ ትቀልዳለህ ሶማሊያ :ጋምቤላ ተወው፥ እዚህ አምቦ እንኮ የኔ ተማሪወች ስራ ተቀጥረው የ እኛ ተማሪወች እስኪመጡ ብቻ ነው ስራ ሊኖራቹህ የምትችሉ ነው የተባሉት፥፥ አንተ ትቀልዳለህ! አገር የለንም ነው እንኮ የምልህ፥፥ ይህ ከ ሗላ ኪሴ አውጥቼ የምንገርህ እንድይመስልህ ልጄ፥፥ 62(ስልሳ ሁለት) አመቴ ነው፥፥ ያለው እወነታ ይህ ነው፥፥ አገር የሚባል ነገር አብቅቷል፥፥ ኣዝናልሁ ግን ያለው ሁኔታ ይህ ነው፥፥ህገ መንግስቱ ዜጋ የሚባል ቮካቡላሪ የለውም፥፥ እኛ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ነው የሚለው፥፥ አንድ ሰው በግልሰብ በዜግነት ስለ መብት የሚያወራበት ሁኔታ የለም፥፥በጣም በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው፥፥ ወጣ ካልክማ፥ አንተ እንዴት መጣህ? ይልሃል፥ ቱሪስትን ነህ ወይስ ምንድን ነህ? ይልሃል፥፥ ከየት ነው የመጣህ ነው እንኮ የምትባለው፥፥ የሚገርም ጉድ እንኮ ነው የፈላብን፥፥
አካዳሚክ ፊርደም የሚለውን ኮምፒሊትሊ አውጣው፥፥ ሁሉም ፕሮፌሰር፥ ሁሉም አስተማሪ አንገቱን ደፍቶ ዛሬ ነገ ያዙኝ ብሎ የሚኖርበት አገር ነው ዩኒቨርሲት ማለት ኢትዮጵያ፥፥ እነግራሃለው፥ የፈልጉትን ይበሉ እነግረሃለው፥ ይሄ ነው ያለው፥፥ስለ ሰቆጣ የጻፈው የህግ አስተማሪ ደብዳቤ ነው የተጻፈለት እንዲባረር፥፥ ያውም እሱ የብአዴን አባል ነው ምናምን ነገር፥፥ አካዳሚክ ፍሪደም የሚባል ቮካቡለሪወም የለ፥፥ ድሮ ቀረ፥፥ አሁን ሳምንት ምን አለኝ ቸርማኑ እና እኛ እንመርጥና እነሱ ሪኮሜንድ ያደርጉልናል፥፥ቼርማን አንመርጥም፥ ዲን አንመርጥም፥ ካድሬወች ነው የሚመርጡልን፥ ምን አለፋህ፥፥አንድ ዩኒቨርሲቲ አድሚሽኑን (admission) ያስረከበ ዩኒቨርሲቲ አካደሚክ ፍሪደም አለኝ ይላል እንዴ? በትዛዝ እንከሌን ተቀበሉ እነከሌን አተቀበሉ የሚባል ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፊሪደሙን ተወው አልኩህ፥፥እርሳው እሱን ፥ ይገባሃል የምልህ? አድሚሽኑን ያስረከበ ዩኒቨርሲቲ አካደሚክ ፍሪደም አለ ብሎ ሊያወራ አይችልም፥፥
መከፋፈልን እንደ ጸጋ የወሰደ ስርዓት እኮ ነው፥፥ምን ትጠብቃለህ እስኪ ንገረኝ፥፥ "የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ደስ ያላቹህ ብሄር ብሀረሰቦች ሆናቹህ ነው እኮ የሚለው፥ ዘፈኑ ሁሉ"፥፥አንተ ነገሩን እንዴት ነው የምታየው፥፥ አገር የለም፥ ህግ የለም፥ እየጠፋን ነው ምን ትላልለህ፥ ስለመብት ታወራለህ እንዴ፥፥ የእኛስ የተማሪወች ማህበር አለ አይደል እንዴ ካድሬወች ነው እንኮ ራን የሚያደርጉት፥፥ ሲቪል ማህበራት የሚባል ነገር የለም፥፥ ወይ ጠፈተዋል ወይ ተካተዋል፥፥