Friday, December 19, 2014

ሰበር ዜና!


ባህርዳር በተቃዉሞ እየተቀወጠች ነዉ፡፡አዲስ አበባም እንዲሁ!
በባህርዳሩ ተቃውሞ ሰባት ሰዎች ሲቆስሉ ሶስት ሞተዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ጥረት እያደረ ቢሆንም ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች አምስት ያህል ወጣቶች እንደቆሰሉ ተገልጾአል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡
ይህ በንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ቤኒ መስጅድ በዛሬዉ ዕለት ሙስሊሙ ማህበረሰብ በረቀቀ መልኩ የተቃዉሞ ጽሁፎችን በፊኛ በማዘጋጀት ጸረ ወያኔ ተቃዉሞ አሰምተወል። መንግስት በሴኩላሪዝም ሽፋን እየፈጸመ ያለውን የሂጃብ ገፈፋ የሚያወግዝና በተጨማሪም በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ እጸፈጸመ ያለውን የፍጥ መዛባት፣ በማረሚያ ቤቱ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማውገዝ ነው። መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቃውሞውን በሃይል አስቁሚያለሁ ሲል የነበረ ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ግን ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገልጽዋል። ከላይ ነዉና ትዛዙ ዘንድሮ ይህ ለክርስቲያኑም ሆነ ለህዝበ ሙስሊሙ የማይበጅ ባንዳ ስርዓት ሞት-ሞት እየሸተተዉ ነዉ።ድል ለጭቁኑ የኢትዮዽያ ህዝብ !!!

Thursday, December 18, 2014

ሀገር ማለት ሰው ነው፣ ሰው ነው ሃገር ማለት“


December 18, 2014
አበበ ሃይሉ
የቴሌቭዥኔን ጣቢያ EBC (የውጭ ጣቢያ እንዳይመስላቹህ የኛው ጉድ የሆነው የኢትዮጲያ ? ቴሌቭዥን ነው ) ላይ ሳረገው
“ሃገር ማለት ሰው ነው ፣ ሰው ነው ሃገር ማለት”
የሚል ዜማ እየሰማሁ የባቡሩ መስመር ፣የአባይ ግደብ ፣ብሄር ብሄረሰቦች ሲደንሱ፣ አረንጓዴ የተላበሰ ምድር ብቻ ባጠቃለይ የሚስብ ነገር እስክሪኑ ላይ ከሙዚቃው ጋር ይሄዳል።Update: Ethiopian opposition coalition
በተመሳሳይ ጊዜ ፓልቶኬን ከፍቼ ስሰማ እጅግ አስደናጋጭና አሳዛኝ የሴት ልጅ የስቃይ ድምጽ ከብዙ ሰዎች ግርግር ጋር ይሰማኛል። ጆሮዬን ይበልጥ ወደ ፓልቶኩ ሳደላ፡ ና ወደዚ!ዝም በል/ይ!በለው!ዞር በል ከዚ! የሚሉና እያስፈራሩ ሰዎችን የሚደበድቡ የፌደራል ፖሊሶች ድምጽ በጉልህ ይሰማኛል ። ድንገት ግን ድምጹ ጠፋ ። የስልኩ ባለቤት ፖሌሶቹ ሳይቀሙት/ሟት አይቀርም ። ከዛም ሌላ ወንድ!በሌላ ስልክ ፓልቶኩ ላይ ማውራት ጀመረ 《ምናለ እኔም እዚ ባልሆንኩና ይሄንን ጽዋ አብሬ ልጠጣ ይገባኝ ነበር》 የሚል እጅግ ልብ የሚነካ ነገር ሲናገር አደመጥኩ። ቅዳሜ ህዳር 24 የዘጠኙ ፓርቲዎች የትብብር ሰልፍ ከጥዋቱ 3 ሰአት ላይ እንደሚጀመር ስለማውቅ እኔም ካለሁበት በጥዋት ተነሳሁ፥ ግን ምን ያረጋል በአንድ ሃገር ላይ ሁለት ፍጽም ተቃራኒ የሆኑ ኩነቶችን አንዱን በቴሌቭዥን ሳይ ሌላውን በፓልቶክ ላይ ለማድመጥ ቻልኩ።
የዘፈኑና ሰዎቹ ላይ የደረሰው ነገር ሊገናኙልኝ አልቻሉም። ” ሃገር ማለት ሰው ነው ፣“ ይህ ማለት እንደገባኝ ከሆነ ሃገር ያለ ሰው ሃገር ሊባል አይችልም ነው ። ቀጥሎም “ሰው ነው ሃገር ማለት፣” የሚለው ደግሞ ሀገርን የሚመራ ፣የተሻለ የሚያረጋት፣የራሷን ዳን ድንበር የሚጠብቅላት ፣የማንነቱ መገለጫ የሚያረጋት··· ሰው ነው ማለት ነው። ታዲያ ይህ ከሆነ ዘንዳ ሃገሬን የተሻለች ሃገር ላድርጋት አንተ ከ23 አመት በላይ አስተዳድረሃት እንደ ሃገር ልታቆማት አልቻልክም ተራዬን እኔ ልሞክር አልያም የተሻለ ይረከብ ማለትለዚህ ሁሉ ግፍ የሚያበቃ ነው እንዴ?ጥያቄው እኮ አነተን ከምድረ ገጽ ላጥፋህ አልያም እንጦሮጦስ ልክተትህ አይደለም ።
ወረቀት ላይ ለሀገሩ የሚገባትንና የሚመጥናት ነገር አንተ የያዝከው መንገድ አይደልም የሚል መፈክር በያዙ ሰዎች ላይ አንድ ቀውጢ የጦር ቀጠና አስመስሎ ግፍ መፈጸም ምን ያህል አረመኔነትና ስልጣን ባህሪያቸውን አውሬ እንዳደረገው ይበልጥ አሳይቶናል። እጅግ አሳፋሪው ነገር ደግሞ ሃና (በአስገድዶ መደፈር ህይወቷ ያለፈ)ላይ የተፈጸመው ድርጊት አንገታችንን አስደፍቶ ደሞን ፍርድ ይክሳት ዘንድ ስንጠብቅ በራሱ የህግ አካል በሆነው የፌደራል ፖሊስ ሴቶች እህቶቻችን ላይ እንደዛ አይነት አስነዋሪ የግፍ ድብደባ መፈጸም በውነት ህሊና ያለው ሰው ልብ የሚያቆስል ድርጊት ነው ። የሴቶችን መብት አስከብሪያለሁ ብሎ ወሬ ከሚነዛ መንግስት ይህ አሳፋሪ ስራ ነው። እንደውም ሴቶች እህቶቻችን ላይ ለሚደርሰው ዘግናኝ ድርጊቶች የማበረታቻ ስራ ነው። በዘፈኑ ላይ የተጠቀሰው “ሰው ” ተብሎ የተጠቀሰው አካል ማን ይሆን?ምን አልባት ገጣሚው ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት በአስፈላጊው ሰው እጅ አልገባለት መሰል?
“ሃገር ማለት ሰው ነው፣ሰው ነው ሃገር ማለት”
ይህን ሁሉ እያሰብኩ እያለ ደግሞ ወደ ማምሻውን አንድ መነጽር ያረገ ወጣት በቴሌቭዝን መስኮት ብቅ ብሎ 《 እነዚህ ቦታዎች ላይ እጅግ ሰፋፊ የልማት ስራዎች የሚካሄድባቸው ናቸው እንዴት ብለው እነዚህ ቦታዎች ላይ ሰልፍ ይወጣሉ እነዚህ ሰዎች በጥባጭ ናቸው ሰላማዊ አይደሉም》 ብሎ ሲናገር ሰማሁትና እውነትም ገጣሚው ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት አልተረዱለትም አልያም አውቆ የተኛ አይነት ጨዋታ ይዘዋል ብዬ እንድደመድም አደረገኝ። እስኪ ይታያቹሁ ተይዞ የተወጣው መፈክር ባጭሩ ብናስቀምጠው እኮ ለሃሪቱ የተሻለ አስተዳደር ይገባታል እንጂ የባቡሩ ፣መንገዱ ፣ግድቡ ይቁሙ ያለም ሰልፈኛ የለም።ሲጀምር እኮ እነዚህ የልማት ስራዎች የሚሰሩት ለሃገሬው ሰው መገልገያነት ነው ። ዜጋውን አፈናቅለህ ፣እንዲሰደድ አርገህ ፣እየገደልክና እያሰቃየህ ፣ ሃሳብህ እኔ ከማስበው ውጭ መሆን የለበትም ብለህ ልማት ነው የሚካሄደው ማለት እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ እኔ እንዲህ ከተናገርኩ በስልጣን ላይ ስልጣን ፣ በሃብት ላይ ሃብት ··· አገኛለሁና ሌሎች ለምን ስቃይ ሲቀበሉ አይኖሩም አይነት የአህያዋን አይነት አስተሳሰብ ነው።
እዚሁ ዜማ ላይ እጅግ ደስ የሚልና ትልቅ መልእክት የሚያስተላልፍ ስንኝም አለ
“እኛ ነን ልጆቿ ምሰሶና ማገር”
ምሰሶ ቤቱን እንዳይፈርስ ፣ ተስተካክሎ እንዲቆም ፣ዘላቂነት እንዲኖረው እንደሚያረገው ሁሉ ምሰሶውን ስንነቀንቀውና ስናፈርሰው ቤቱ እንደሚወድቀው ሁሉ ምሶሳችንን ነቅንቆ ለመጣል በመፍጨርጨር ላይ ያለን መንግስት ይሄማ እንዴት ሆኖ ብሎ/ላ እራሳቸውን እስኪስቱ የተደበደቡ ፣ እጃቸውን የተሰበሩ፣ሰውነታቸው በግርፋት የበለዘ ፣ ከስራ የተፈናቀሉ ምሰሶውን መልሶ ለማቆም የታገሉ የቁርጥ ቀን የሃገሪቱ ልጆች ናቸው፡ ይህንን ነው በህዳር 24ቱ ሰልፍ ላይ ያየንው ። “ይሄንን ስቃይ አብሬ መካፈል ነበረብኝ“ የሚል ጀግንነት፣ አንተ ምትገልበት ማሳሪያና ጉልበት እንዲሁም ስልጣን ቢኖርህ እኔም ለሀገሬ ብሎ ለመሞት የተዘጋጁትን ጴጥሮሳዊያንን ነው ።
ኢትዮጲያ ለዘላለም በክብር ትኑር!

Tuesday, December 16, 2014

ስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ!! ∙ዜጎችን በአደባባየይ የሚደበድብ ‹‹መንግስት››


በላይ ማናዬ
ካዛንቺስ በተለምዶ እንደራሴ በተባለው ቦታ ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ረፋድ ላይ የሆነው እንዲህ ነው….
በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ እና በሌሎች 8 ፓርቲዎች ስምምነት የተመሰረተው የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የትግል መርሃ-ግብር ማሳረጊያ ሊደረግ በነበረው የ24 ሰዓት የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ ያሉ ሁኔታዎችን ለመዘገብ የሰልፉ መነሻ በሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሰልፉ ይጀምርበታል ከተባለው ጊዜ መዘግየቱን አስመልክቶ ከቢሮ ወጣ ብዬ ሁኔታውን ለመቃኘት እየሞከርኩ ነበር፡፡ ድባቡ ፍጹም ዝብርቅርቁ የወጣ ነበር፡፡ ሰልፍ ለመውጣት የወሰኑት ሰዎች በቢሮው ውስጥ መሰናዷቸውን እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ከቢሮ ውጭ ያሉ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ኃይሎች ደግሞ ቁጥራቸው በየደቂቃው እየጨመረ አካባቢውን መክበብ ተያይዘውት ነበር፡፡
ሁኔታውን በአንክሮ ለተመለከተው በደቂቃዎች ውስጥ ‹ፍጥጫ› ሊጀመር እንደሚችል አመላካች ነበር፡፡ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የእውቅና ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብቻለሁ፣ ስለሆነም ሰልፉን ለማድረግ ወስኛለሁ ሲል መንግስት በበኩሉ ሰልፉን ‹ፈቃድ አልሰጠሁትም› ሲል አስታውቆ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ትብብሩ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ‹ማሳወቅ› እንጂ ‹ማስፈቀድ› አይጠበቅብኝም ሲል አዋጅ ጠቅሶ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡
በዚህ አለመግባባት ውስጥ ተሁኖ ነበር የአዳር ሰልፉ ሊካሄድ ሽርጉድ ይባል የነበረው፡፡ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ሰልፉ ከሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ውስጥ ተጀመረ፡፡ የሰልፉ አጀማመር በራሱ የሚገርሙ ነገሮች ነበሩት፡፡ ባላሰብኩት ፍጥነት ቢሮ ውስጥ የነበሩት ሰዎች በአንዴ ሰብሰብ ብለው ቀጥታ ከበር እንደወጡ መፈክሮችን እያሰሙ በፈጣን እርምጃ ወደፊት ተስፈነጠሩ፡፡ እርምጃየን በእነሱው ፍጥነት ልክ አስተካክየ መቅረጸ-ድምጼን አበራኋት፡፡ ‹‹ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት!....›› እያሉ መፈክሩን አስተጋቡት፡፡
ፖሊሶች በሰልፈኞች ፍጥነት ግር የተሰኙ መሰሉ፡፡ ሰልፈኞቹ በጣም ብዙ ፖሊሶች በተሰደሩበት መንገድ ፊት ለፊት ቀጥታ ገሰገሱ፡፡ ይህኔ ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ተቁነጠነጡ፡፡ ሰልፈኞች መፈክራቸውን ለወጡ፤ ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው! ፖሊስ የህዝብ ነው! ፖሊስ የህዝብ ነው!›› እያሉ ለፖሊሶች መልዕክት ለማስተላለፍ ሞከሩ፡፡ ይህኔ ሁኔታዎች ከመቅጽበት ተለዋወጡ፡፡ እዛ የነበረው የ‹ፀጥታ ሰራተኛ› በሙሉ እንደንብ ሰልፈኞች ላይ ሰፈረ፡፡ እንደደነበረ ፈረስ ያገኙትን መርገጥ ጀመሩ፡፡ በሰልፈኞች ላይ የሆነው ሁሉ በእኔም ላይ ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ዱላ ካረፈብኝ በኋላ ያለውን የዱላ ብዛት አሁን አላስታውስም፡፡ ብቻ ዘግናኝ ነበር!
በእርግጠኝነት በሂደቱ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ቀድሜ ብገምትም፣ የሆነው ግን ከግምቴም በላይ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነበር፡፡ ሴቶች እና እድሜያቸው ከ70 በላይ የሆኑ አዛውንቶች ርህራሄ አልተደረገላቸውም፡፡ እንዲያውም በእነሱ ላይ ሳይበረታ አልቀረም፡፡ ያ ሁሉ ፖሊስና ‹ሌሎች የፀጥታ ሰራተኞች› እንደአሸን የፈሉ ነበሩ፡፡ አንድም ዱላ ሳይሰነዝሩ ሰልፉን ማገት በተቻላቸውም ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ትዕዛዝ ይመስላል፤ ዜጎችን ደብድብ የሚል ትዕዛዝ! ያሳፍራል፣ ያሸማቅቃል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አቧራ ላይ ተጥለው ተደበደቡ፡፡ ሴቶች ሆዳቸውን ተረገጡ፡፡ አዛውንቶች ዘለፋ ከተሞላበት ኃይለ-ቃል ጋር ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ ጋዜጠኛ ሰልፍ ላይ ተገኝተህ መዘገብ አትችልም ተብሎ ተቀጠቀጠ፡፡ አቶ ኤርጫፎ ኤርደሎ እና አቶ ቀኖ አባጆቭር (አባዬ) ተይዘው ከእኛው ጋር ሲንገላቱ ሳይ በእኔ ላይ የደረሰውን ሁሉ ረሳሁት፡፡ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሚሆኑ ‹የጸጥታ ሰራተኞች› የአሳፋሪው እርምጃ ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በእርግጥ እነ አባዬ ስለእኛ እንጂ ስለራሳቸው አልተሰማቸውም፡፡ እኛ ደግሞ በእነሱ ላይ ስለሆነም የበለጠ እናዝን ነበር፡፡
ይህ ሁሉ ድርጊት በካዛንቺስ እንደራሴ አካባቢ ከመሆኑ ከደቂቃዎች በፊት ብዙ ዜጎች በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ስፍራዎች እየተያዙ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ መንግስት የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ዜጎችን ለማፈን ቆርጦ እንደተነሳ ተገነዘብኩ፡፡ በዕለቱ የሆነው ተራ እስር አልነበረም፤ አፈሳ ነበር የተደረገው፡፡ ጅምላ እስር ነበር የተፈጸመው፡፡ ካዛንቺስ እንደራሴ አካባቢ የሆነው ግን በኃይልና በድብደባ የታጀበ ነበር፡፡ በድብደባ እራሱን ስቶ የቆየው ወጣት አቤል ኤፍሬምን ጨምሮ ብዙዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን በመኪና እንደእቃ እንድንጫን ተደርገን ካዛንቺስ አካበቢ ወደሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተጋዝን፡፡ ጣቢያ እንደደረስን በአንድ ቦታ እንድንሰበሰብ ተደርገን በፎቶ እና ቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ ተደረገብን፡፡ የሚገርመው ራሱን ስቶ ወድቆ የነበረው አቤል ሳይቀር በዚያ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ህክምና ሳያገኝ ቀረጻው ይደረግበት ነበር፡፡ ግራ ቀኜን ዞር ዞር ብዬ የተያዙ ሰዎችን አስተዋልኩ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ የተለያዩ የፓርቲ አመራሮች ተይዘዋል፡፡ አንዳንድ በዚያ ሲያልፉ የተገኙ፣ ስለጉዳዩ ምንም የማያውቁ ሰዎችም አብረው ተጀምለው ተይዘዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል በሁኔታው ተደናግጠው የሚያለቅሱ ሰዎች ይገኙበት ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሰልፍ ይሁን ሌላ የሚያውቁት ጉዳይ አልነበረም፡፡ እንዲሁ በቦታው ስለተገኙ ብቻ የተያዙ ነበሩ፡፡
ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እያለን ከመስቀል አደባባይ የተያዙ ሰዎችም በጣቢያው እንደሚገኙ ተገነዘብኩ፡፡ በጣም ብዙ ፖሊሶች ግቢውን ሞልተውታል፡፡ ብዙዎች ሰልፈኞችን ይሳደባሉ፤ አንዳንዶች አሁንም ለመደባደብ ሲቋምጡ አስተዋልኩ፡፡ ገረመኝ! ከመደብደብ የሚገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ቀደም ብሎ በተያዝንበት ቦታ ላይ ብዙ ከተደበደብን በኋላም ቢሆን ድብደባው እንዲቆም ትዕዛዝ የሰጡት የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዘውዴን በዓይኔ ፈለኳቸው፡፡ ግን ላገኛቸው አልቻልኩም፤ የእውነት ከድብደባው የሚገኘውን ትርፍ ማወቅ እፈልግ ነበር፡፡ ፍርሃቴ ልበለው አልያ ድንጋጤዬ ብን ብሎ ጠፍቶ ስለነበር ማናቸውንም አይነት ጥያቄ ልጠይቃቸው እፈልግ ነበር፡፡ የእውነት በወገኖቼ መካከል መገኘቴን እንኳ እጠራጠር ነበር፡፡ እንዴት ሰው አንዲት ጠጠር እንኳ በእጁ ሳይዝ፣ በሰላም ድምጹን ስላሰማ ብቻ ይህን ያህል ድብደባ በራሱ ወገኖች፣ በመንግስት ኃይሎች ይደርስበታል?
ስድስተኛ ብዙም አልቆየንም፤ የቪዲዮ እና የፎቶ ቀረጻው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ወደሌላ ፖሊስ ጣቢያ እንድንዛወር ተደረግን፡፡ የደረስንበት ፖሊስ ጣቢያ ፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ ነበር፡፡ በዚህ ፖሊስ ጣቢያ ደርሰን ትንሽ ጊዜ እንደቆየን ቃላችንን እንድንሰጥ ተደረግን፤ ድጋሜ ፎቶ እንድንነሳ ሆነ፣ አሻራም ተነሳን፡፡ ይህን አድርገው ወደተለያዩ ክፍሎች ካጨቁን በኋላ ምሽት ላይ እንድንወጣ ታዘዝን፡፡ በዚህ ጊዜ በታሳሪዎች መካከል የተለያዩ አስተያየቶች ይሰጡ ጀመር፡፡ አንዳንዱ ልንፈታ ነው ሲል ሌላው ደግሞ ወደ ካምፕ ሊወስዱን ነው ይል ነበር፡፡ ቀሪዎች ደግሞ ወደሦስተኛ ፖሊስ ልንወሰድ እንደሆነ ግምታቸውን ሰነዘሩ፡፡ እነዚህኛዎቹ ልክ ነበሩ፡፡ ጉዙው ወደ ሦስተኛ ነበር፡፡ በፖለስ መኪና እና ሞተር ሳይክል ታጅበን፣ የሳይረን ድምጽ በሚያሰማ ሞተረኛ መሪነት ሦስተኛ ፖሊስ (የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት) ተወሰድን፡፡
ወደሦስተኛ ፖሊስ እንድንዛወር የተደረግነው ታሳሪዎች ከመስቀል አደባባይ የተያዙትን አይጨምርም፤ ቁጥራችንም 44 ነበርን፡፡ ሌሎቹ እስከተፈቱበት ዕለት ድረስ እዚያው ፖፖላሬ ጣቢያ ቆይተዋል፡፡ ሦስተኛ ፖሊስ እንደደረስን በሁለት እንድንከፈል ግድ ሆነ፡፡ በአመራር ደረጃ ላይ ያሉት ወደቀዝቃዛ ክፍል (በረዶ ቤት) እንዲገቡ ሲደረጉ፣ ሌሎቹ ደግሞ በተለያዩ ክፍሎች (ጨለማ ክፍልን ጨምሮ) እንድንገባ ተደረግን፡፡ በዚያው በህዳር 27/2007 ዓ.ም ዕለት የሦስተኛ ፖሊስ ቆይታችን አሃዱ ተባለ፡፡ (በነገራችን ላይ አብዛኞቻችን ታሳሪዎች ለ24 ሰዓታት ያህል ምግብና ውሃ በአፋችን አልዞረም ነበር፡፡)
የስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ
ሦስተኛ ፖሊስ አሁን ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት ስፍራ ነው፡፡ ቦታው ድሮ በሚታወቅበት ገጽታው ሳይሆን በቅርቡ በተገነባው ዘመናዊ ህንጻው ተጀቡኖ በግርማ ሞገስ የሚታይ ነው፡፡ ይህ ቦታ በፌደራል ፖሊስ የማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያን ተጎራብቶ የሚገኝ ነው፤ (አንዳንዶች ከማዕከላዊ ጋር በምድር ዋሻ ይገናኛል ይላሉ፤ ይህን በተመለከተ እንደ ቀልድ ከእስር በወጣንበት ቀጣይ ቀን ሞባይል ስልኬን ልወስድ ወደጣቢያው ባመራሁበት ወቅት ለመርማሪዬ ፖሊስ በቀልድ መልኩ ጥያቄ አንስቼለት ነበር፡፡ መርማሪው ‹‹ማዕከላዊ እና እኛ አንገናኝም!›› ነበር ያለኝ በጥያቄየ ግር በመሰኘት አተያይ እያየኝ)፡፡ ሦስተኛ ፖሊስ በህንጻው ዘመናዊ ይሁን እንጂ በአሰራር ግን ብዙ ገራሚና አሰቃቂ ድርጊቶችን የሚያስተናግድ ቦታ መሆኑን በቆይታየ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡
ወደ ጉዳዬ ስመለስ፣ ሦስተኛ የገባን ዕለት (ህዳር 27) በሌሊት ምርመራ ሲደረግብን ነበር ያደርነው፡፡ በፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ የሰጠነውን ቃል በመድገም ሙሉ ማንነታችን ከመዘገቡ በኋላ ሌሎች ምርመራዎችም ተደረጉምብን፡፡ በምርመራው ወቅት ከሞላ ጎደል ድብደባ አልደረሰብንም፡፡ ምናልባትም በተያዙበት ወቅት የተደበደቡት ይበቃቸዋል ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጣዩ ቀን ሁላችንም ፍርድ ቤት እንድንቀርብ የተደረግን ሲሆን ፖሊስ ፍርድ ቤቱን 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠየቀ፤ የትብብሩ አመራሮች በበኩላቸው በሰልፈኞቹ በኩል የተፈጸመ አንዳችም ህገ-ወጥ ተግባር አለመኖሩን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ በነጻ እንዲያሰናብተን ጠየቁ፡፡ በተለይ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ኢህአዴግ በዘንድሮው ምርጫ ሙሉ ለሙሉ እንደምናሸንፈው ስላወቀ ነው ያሰረን፤ ይህም ህገ-መንግስቱን የጣሰ ነው›› ሲሉ አስረድተው ነበር፡፡
በዚሁ ፍርድ ቤት በቀረብን ጊዜ ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ታዝቤያለሁ፡፡ በተለይ በታሳሪዎች በኩል የደረሰባቸውን ድብደባ ተከትሎ ህክምና አለማግኘታቸውን፣ እንዲሁም አመራሮቹ በበረዶ ቤት ስለሚገኙ ለጤናቸው አስጊ ስለሆነ የተሻለ አያያዝና ህክምና እንዲደረግላቸው ለፍርድ ቤቱ ባስረዱ ጊዜ የዕለቷ ዳኛ ያሉትን አልረሳም፤ ወደ ፖሊሶች ዞር ብላ ‹‹የጠየቁትን ህክምና እንዲያገኙ አድርጉ፣ ለእናንተም ለመቅጣት እንድትችሉ በህይወት ይቆዩላችሁ›› ነበር ያለችው፡፡ ጆሮዎቼን ማመን ነበር ያቃተኝ! ሁኔታው ሰው ቅጣት እንዲቀበል ብቻ ነው በህይወት መቆየት ያለበት ማለት ነው ብዬ ራሴን እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡
ፍርድ ቤት የነበረን ቆይታ አብቅቶ ወደ ሦስተኛ ተመለስን፡፡ ምርመራውም ቀጠለ፡፡ በምርመራ ወቅት ተመሳሳይና አሰልቺ ጥያቄዎች ነበር በተደጋጋሚ የሚቀርቡልን፡፡ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ መርማሪዎቹ የኢሜልና ፌስ ቡክ አካውንት እስከ ይለፍ ቃል (password) ድረስ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ነበር፡፡
ኢሜልና ፌስቡክ ይኖረኝ እንደሆን ጠየቀኝ፡፡ እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ አስከትሎ አካውንቱንና ፓስወርዱን እንድነግረው ጠየቀኝ፡፡ ‹እንዴት ይሆናል፣ ይሄኮ የግል ጉዳይ ነው፤ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት ስጠኝ ትላለህ?› ስል መልሼ ጠየቅኩት፡፡ ፈቃደኛ ባለመሆኔ አንዴ በንዴት ሌላ ጊዜ በማባበል አይነት የጠየቀውን እንድነግረው ሞከረ፡፡ በአቋሜ መጽናቴን ሲያይ፣ ‹‹ይሄኮ የመንግስት አሰራር ስለሆነ ነው፤ ባትናገርም እኮ መንግስት ያውቀዋል›› አለኝ፡፡ አልመለስኩለትም፡፡ እሱም ‹‹ኢሜልና ፌስቡክ አካውንት አለው፣ ግን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም›› ብሎ የምርመራ መዝገቡ ላይ ሲያሰፍር አነበብኩ፡፡
ከምርመራ ክፍል ወጥቼ ሌሎች ታሳሪዎች ጋር ስንገናኝ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳስተናገዱ ነገሩኝ፡፡ ለመሆኑ ይሄ ምን አይነት የመንግስት አሰራር ይሆን?
የሦስተኛ የስድስት ቀናት ቆይታዬ ለእኔ ብዙ ነገሮችን እንድቃኝ ያስቻለኝ ስለነበር መታሰሬን በግድም ቢሆን ሳልወደው አልቀረሁም፡፡ ምናልባት ባልታሰር ኖሮ እኒያን ሁሉ ባለብዙ ታሪክ እስረኞች አላውቃቸውም ይሆናል፡፡ በታዳጊ ሃና ላላንጎ አስገድዶ መደፈር ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት አምስት ተጠርጣሪዎች እስከ በነፍስ ግድያና ሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው እስከገቡት ወንድሞች ጋር ብዙ ታሪኮችን አደመጥኩ፡፡ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን እና እየደረሰባቸው ያለውን ሰቆቃም ለመገንዘብ ቻልኩ፡፡
ሦስተኛ ፖሊስ በዘመናዊ ህንጻ ውስጥ ኋላቀር የምርመራ ዘዴ የሚተገበርበት ስፍራ መሆኑንም ከብዙ ሰዎች ላይ በደረሰው በደል አየሁ፡፡ በምርመራ ወቅት በተፈጸመባቸው ድብደባና ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎች ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እዛ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በረዶ ቤት (የትብብሩ አመራሮች ታስረውበት የነበረው ቤት) አንዱ የምርመራ ወቅት ማቆያ አሰቃቂ ስፍራ ነው፡፡ ሌላው ‹ቆመህ እደር› የሚባል ሲሆን ተጠርጣሪዎች ለቀናት በዚህ ስፍራ ቆመው ውለው ቆመው እንዲያድሩ የሚደረግበት እንደሆነ በዚህ ሁኔታ ላይ ያለፉ ታሳሪዎች አጫውተውኛል፡፡ ብዙዎች በ‹ቆመህ እደር› ያለፉ ሰዎች የተለያዩ የአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ሰለባ ይሆናሉ፡፡
እውነትም በሦስተኛ ፖሊስ ያለው የምርመራ ስልት እጅግ ኋላቀር ብቻ ሳይሆን ኢ-ህገ-መንግስታዊም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ተጠርጣሪዎች ሰውነታቸው በስፒል ይጠቀጠቃል፣ ትልቅ ሃይላንድ ውሃ ተሞልቶ ብልታቸው ላይ ይንጠለጠላል፣ እግራቸውን ከፍተው ቆመው እንዲያድሩ ይደረጋል፣ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸማል፣ ከብዙዎቹ እስረኞች አፍ እንደሰማሁትና በአካላቸው ላይ የደረሰውን ጉዳት በዓይኔ እንዳየሁት፡፡ በዚህ አይነት ምርመራ የሚያልፉ ሰዎች ምርመራቸው እስኪያልቅ (ለሳምንታት) ከቤተሰብ ጋር መገናኘት አይፈቀድላቸውም፡፡ በነገራችን ላይ በሰልፉ ወቅት የተያዝን እና በሦስተኛ የነበርን ወንድ እስረኞች በሙሉ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንድንገናኝ አይፈቀድልንም ነበር፡፡
በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ባለው ከባድ የማሰቃየት የምርመራ ዘዴ የተሰቃዩ ተጠርጣሪዎች አንዳንዶቹ ራሳቸውንም ለማጥፋት ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸውን አግኝቼ አናግሬያቸው ነበር፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ራሱን ለማጥፋት የገፋፋውን ምክንያት እንዲህ ሲል አስረዳኝ፣
‹‹ምርመራው እጅግ ኢሰብዓዊ ነው፡፡ ራስህን ትጠላለህ፡፡ በቃ በግድ እመን ነው የሚሉት፡፡ ወንጀሉን ሳትፈጽም እዚህ ተጠርጥረህ ብትገባ በግድ ወንጀለኛ ነኝ በል ትባላለህ፡፡ ድብደባው ፋታ የለውም፡፡ በየዕለቱ ማታ ማታ እየወሰዱ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ይቀጠቅጡሃል፡፡ ሰው አትመስላቸውም፡፡ በሀሰት የጠየቁህን አንድ ወንጀል ብታምንላቸው ሌላ ወንጀል ፈጥረው እመን ይሉሃል፡፡ በቃ መዝገቡ ክፍት ነው፤ አንተን ይጠብቃል እመን ይሉሃል፡፡ ከነገ ዛሬ ማሰቃየቱ ያበቃል ስትል ማብቂያ የለውም፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሁሉ ስቃይ ለምን አልገላገልም ብለህ ታስባለህ፡፡ በዚህ ጊዜ ትዝ የሚልህ ደግሞ ራስን ማጥፋት ነው፡፡››
ይህ የብዙ ሰዎች አንደበት የተናገረው እውነታ ነው፡፡ ድርጊቱ በህግ ያልተፈቀደ ቢሆንም ምርመራው ግን በዚህ መልኩ እንደሚከናወን ብዙዎች አስረዱኝ፡፡ የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 19 (5) ስለተያዙ ሰዎች እንዲህ ይላል፣ ‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡››
ሌላ ተጠርጣሪ በምርመራ ወቅት ያጋጠመውን ገጠመኝ የግዱን እየሳቀ አወጋኝ፡፡ ‹‹ለምርመራ በገባሁበት ክፍል ውስጥ መርማሪዎቼ በዱላ ተቀበሉኝ፡፡ ከጥያቄ በፊት ዱላ ይቀድማቸዋል፡፡ ደብድበው ደብድበው ሲደክማቸው እኔን እግሬን ከፍቼ እንድቆም በማዘዝ እነሱ ኮምፒተር ላይ ፊልም እያዩ መዝናናት ጀመሩ፡፡ ከሰዓታት በኋላ ሽንት ቤት እንዲወስዱኝ ለመንኳቸው፡፡ ተሳለቁብኝ፡፡ እየቆየሁ እየቆየሁ ስሄድ ሽንቴን መቆጣጠር እንዳልቻልኩ በመግለጽ ‹ስለወንድ ልጅ አምላክ› ስል በድጋሜ ተማጸንኳቸው፡፡ ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡ ከዚያ ‹በቃ እዚሁ እሸናለሁ› ብዬ ሽንቴን ለቀቅኩት፡፡ በጣም ታፍኜ ስለነበር ሽንቴ እጅግ መጥፎ ጠረን ፈጠረ፡፡ ይገርምሃል ለእኔ ሳይሆን ለቢሯቸው አዝነው እንደውሻ አባርረው ከቢሮ አስወጡኝ፡፡››
ለመሆኑ እነዚህን የስቃይ ድምጾች ሰሚያቸው ማን ይሆን?

Tuesday, December 9, 2014

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን !!!


በአብዛኛው በወጣት ወንዶችና ሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነበት የዘጠኝ ፓርቲዎች ኅበረት፣ “ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የተሰኘ የአንድ ወር መርሀ ግብር አውጥቶ፤ ችግሮችን ተጋፍጦ አብዛኛውን ተግባራዊ አድርጓል። የመርሀ ግብሩ አቢይ አካል የነበረውና በህዳር 27 እና 28 ሊከናወን ታድቆ የነበረው የ24 ሰዓት የአደባባይ ተቃውሞ ግን በአገዛዙ የኃይል እርምጃ ምክንያት በታቀደው መንገድ ሊከናውን አልቻለም። የህወሓት ቅልብ የሆኑት ሲቪል የለበሱ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊስ በተቃውሞው ተሳታፊዎች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ፈጽመዋል።
ከጅምሩ፣ የፓርቲዎቹ ኅበረት የተቃውሞ ማሳወቂያ ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስገባት የገጠመው ችግር የህወሓት አገዛዝ የመንግሥትን መዋቅር ለፓርቲ ሥራ፤ የመንግሥት ተቀጣሪዎችን ደግሞ እንደ ህወሓት አገልጋዮች የሚጠቀምባቸው መሆኑ አንዱ ማሳያ ሆኗል። ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቅ የፈለጉት ፓርቲዎች ህወሓት የዘረጋውን አፋኝ ሥርዓት የሚታገሉ በመሆናቸው ብቻ ደብዳቤዓቸውን የሚቀበል እንኳን አጥተው ተጉላልተዋል። ለሰልፉ ቅስቀሳ ማድረግም በራሱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ወጣቶች ተንገላተዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። ያም ሆኖ ውጣ ውረዶች ታልፈው ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ. ም. ደረሰ።
የኅበረቱ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ጥሪውን የሰማ ሕዝብ ወደ መስቀል አደባባይ ማምራት ሲጀምር ሲቪል የለበሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች እና ፌደራል ፓሊሶች ከሰንደቅ ዓላማዎችና መፈክሮች ባለፈ አንዳች ነገር ያልያዙትን እድሜያቸው ከሃያዎች ያልዘለሉ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን ደብድበዋል፤ ብዙዎቹም አፍነው በአሰቃቂ ሁኔታ እያንገላቱ ወደ እስር ቤቶች ወስደዋል። ወጣቶች ተወልደው ባደጉበት አገር፤ ስሜታቸውን በነፃነት ለመግለጽ በመድፈራቸው ብቻ በጭካኔ ተረግጠዋል፤ ተፈንክተዋል፤ እጅና እግሮቻቸው ተሰብሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህ የህወሓትን ፋሺስታዊ እርምጃ አጥብቆ ይቃወማል። ግንቦት 7፣ ህወሓት ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ እንዲህ ዓይነቱን ፋሺስታዊ ተግባር መፈፀሙን የማይተው እኩይ ኃይል እንደሆነ ያውቃል፤ በዚህም ምክንያት የትግላችን ግብ ህወሓትን ማስወገድና በምትኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረት መሆን ይኖርበታል ብሎ ያምናል፤ ለዚህም ይታገላል።
ግንቦት 7፣ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም. “መብቶቻችንን በህወሓት ዘረኛ አምባገነኖች አናስነጥቅም” በማለት አደባባይ የወጡ ወጣቶችን ጽናት ያደንቃል። ህወሓት የሚለውን ሳይሆን የይስሙላ ህጉ የፈቀደላቸውን ለማድረግ በመድፈራቸው በህወሓት የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የሚደረገውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት አራምደውታል።
እያንዳንዱ የፓለቲካ ድርጅት ከዚህ ኩነት የሚወስዳቸው ተጨማሪ ትምህርቶች ቢኖሩም የሚከተሉትን ነጥቦች ብዙዎችን ያስማማሉ ብለን እናምናለን።
1. ህወሓት በምንም ዓይነት ቢሆን የያዘውን ስልጣን ለሕዝብ ፈቃድ ማስገዛት አይፈልግም፤
2. ህወሓት አገራችን ወደ ትርምስ እየገፋት እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፤
3. ስልጣኑን የሚያሳጣው ከመሰለው እና አቅሙ እስካለው ድረስ ዘግናኝ እርምጃዎችን ከመውሰድ አይመለስም፤
ከህወሓት አገዛዝ መገላገል የሚቻለው ተገዶ ሲወገድ ብቻ ነው። ህወሓት እንዲወገድ ደግሞ የመጨቆኛ አቅሙ መዳከም ይኖርበታል። ህወሓትን የማስወገጃ አማራጭ መንገዶች ብዙ ሲሆኑ ተቀናጅተው ቢሠሩ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ ብለን እናምናለን፤ “ሁለገብ ትግል” የምንለው የትግል ስልት ጭብጥ ይህ ነው። “እምቢ ለነፃነቴ” ብሎ የተነሳ ሕዝብ ህወሓትን ምን ያህል እንደሚያስደነግጥ በተደጋጋሚ ታይቷል። ህዳር 27ን መንደርደሪያ አድርገን በመውሰድ ከዚህ በተሻለ ለተደራጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አመጽ ራሳችን እናዘጋጅ።
በዚህ አጋጣሚ ግንቦት 7፣ ለመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ማድረግ ይሻል። የመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በህወሓት ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ የተበደላችሁ መሆኑን እናውቃለን። የህወሓት ሹማምንት ከሆኑ አዛዦቻችሁ መላቀቅና ራሳችሁን ነፃ የማውጣት ኃላፊነት የወደቀው በእናንተው በራሳችሁ ላይ ነው። ሠራዊቱ ራሱን በራሱ ነፃ ማውጣት ይኖርበታል። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ህወሓት መወገዱ የማይቀር በመሆኑ ሠራዊቱ ራሱን ነፃ አውጥቶ ከሕዝብ ጋር ካልወገደ እጣ ፈንታው የተሸነፈ ሠራዊት መሆን ነው። ከዚህ በላይ የሠራዊቱ አባል እየደበደበ ያለው የራሱን ልጅ፣ ወንድሙን ወይም እህቱን እንደሆነ ይወቅ። ይህ ወሳኝ ጊዜ ነው እያንዳንዱ የሠራዊቱ አባል በግል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ሊሰማው ይገባል።
በሁሉም ዓይነት የትግል ዘርፎች የኢትዮጵያ ወጣቶች በስፋት እየተቀላቀሉ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው። ጊዜው የለውጥ ነው። የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ መደረግ ያለበት ወቅት ላይ ነን። በህዳር 27 ቀን በህወሓት ቅልብ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊሶች አማካይነት የደረሰው ጉዳትና የፈሰሰው ደም ለፍትህና ለነፃነት የተከፈለ ዋጋ ነው። ህመማችሁ ህመማችን፤ ትግላችሁ ትግላችን ነው። የተለያዩ መንገዶች ወደ ነፃነት አደባባይ እያመሩ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Monday, December 8, 2014

ብሄራዊ ብድር የዕድገታችን ምንጭ እንጂ የደኅንነታችን ስጋት ሊሆን አይገባም


እኛ ሰዎች ሁሌም ከምንፈራዉና ከምንጠላዉ አንዴ ከገባንበት ደግሞ የቱንም ያክል ብንጠላዉና ብንፈራዉ እየደጋገምን የምንዘፈቅበትና በቀላሉ የማንወጣዉ አዘቅት ቢኖር ብድር ወይም የብድር ልጅ የሆነዉ ዕዳ ነዉ። ብድር ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ የንግድ ድርጅቶች፤ ማዘጋጃ ቤቶች፤ ትላልቅ ኮርፓሬሺኖችና አገሮች በአጭርና በሪጂም ግዜ የሚያጋጥማቸዉን የገንዘብ እጥረት የሚሸፍኑበት መንገድ ነዉ። ወይም ቀለል ባለ አማርኛ ብድር ወደፊት በምናገኘዉ ገቢ ዛሬን መኖር ማለት ነዉ። ብድር ግለሰቦች፤ ድርጅቶች ወይም አገሮች የመከፈል አቅማቸዉን እያዩ ቢበደሩና የተበደሩትን ገንዝብ ዉጤታማ በሆነ መንገድ ከተጠቀሙበት የእድገትና የብልጽግና መንገድ የሚከፍት አለዚያም የምንበደረዉ ብድር ከአቅም በላይ ከሆነና ዉጤታማ ባልሆነ መልኩ ከተጠቀምንበት ደግሞ በቀላሉ የማንወጣዉ መቀመቅ ዉስጥ ይዞን የሚገባና ጫናዉ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚተላለፍ ዕዳ ነዉ። ዕዳ ደግሞ በተለይ አገሮች የሚገቡበት ዕዳ ተከፍሎ ካላለቀ ወይም በምህረት ካልተሻረ በቀር ወለዱ ወለድ እየወለደ በተበዳሪ አገሮች የኤኮኖሚ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያደርግ የዕድገትና የብልፅግና ጠላት ነዉ። ዛሬ ሰፋ አድርገን የምንመለከተዉ ብድርና ዕዳን ቢሆንም ዋናዉ ትኩረታችን ግን አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በታዳጊ አገሮች የኤኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያደርገዉን ብሄራዊ ብድርና ዕዳ ነዉ። ሁላችንም እንደምናዉቀዉ አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ አመታት በብድር ላይ ብድር እየተበደረች አንዱንም ሳትከፍል በድጋሚ እየተበደረች ከድጡ ወደማጡ እየገባች ነዉ።
የኢትዮጵያ መንግስት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የዉጭ አገር ምንጮች ብድር መበደር ከጀመረ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል።ከቀዳማዊ ሚኒልክ በኋላ ኢትዮጵያን ለረጂም አመታት የመሩት ሦስቱ መንግስታት የብድር ጥማት ከፍተኛ ቢሆንም በብድር መጠኑም ሆነ በተከማቸ የዕዳ መጠኑ ዛሬ በስልጣን ላይ አንዳለዉ እንደ ወያኔ አገዛዝ የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነት ለአደጋ ባጋለጠ መልኩ ብድር የተበደረና ዕዳ ዉስጥ የተዘፈቀ አገዛዝ ኢትዮጵያ አይታ አታዉቅም። የወያኔ አገዛዝ አገር ዉስጥ ቦንድ እየሸጠና ብሔራዊ ባንክን እያስገደ በተለያየ መልኩ የሚወስደዉ ብድር ከአለም ባንክ፤ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት፤ ከዉጭ አገር ባንኮችና አበዳሪ አገሮች በየአመቱ ከሚበደረዉ ብድር ጋር ተደምሮ የዛሬዉን ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን የዛሬዉን ኢትዮጵያዊ የልጅ ልጆች ጭምር ባለዕዳ አድርጓቸዋል።
የወያኔ አገዛዝ ለህዳሴዉ ግድብና ለእድገትና ትራንስፎርሜሺን ዕቅድ ማስፈጸሚያ በሚል የአገሪቱን አመታዊ ገቢና የመክፈል አቅም በላገናዘበ መልኩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ገንዝብ ከተለያዩ የአገር ዉስጥና የዉጭ አገር ምንጮች እየተበደረ ነዉ። ይህ መጠነ ሰፊ ብድር በረጂም አመት የሚከፈልና ከፍተኛ ወለድ የተሸከመ ሲሆን ወያኔ ይህ ብዙ ኢትዮጵያዉያንን ያሰጨነቀ ብሄራዊ ዕዳ አልበቃ ብሎት ከአቅም ዉጭ የጀመራቸዉን ፕሮጀክቶች ለማስጨረስ ነዉ በሚል ሰበብ አሁንም አገራችን ኢትዮጵያን ከዕዳ ወደ ዕዳ እየከተታት ይገኛል። በተለይ ወያኔ አበዳሪ አገሮች፤ የአለም ባንክና ወዳጆቹ የሆኑ መንግስታት ጭምር ተዉ ይቅርብህ ብለዉ እየመከሩት አልሰማ ብሎ በዚህ አመት ለመሸጥ ያሰበዉ ሉዓላዊ ቦንድ ወይም ፈረንጆቹ ሶቨርን ቦንድ ብለዉ የሚጠሩት ቦንድ ሽያጭ የጉዳዩ አሳሳቢነት የገባቸዉን ኢትዮጵያዉያንንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከወዲሁ እያሰጨነቀ ነዉ። በእርግጥም ሉዓላዊ ቦንድ ሽያጭ የሚያስጨንቅ ብቻ ሳይሆን አንደ ኢትዮጵያ አይነቶቹን ቀድሞዉኑም ዕዳ ዉስጥ የተዘፈቁ ደሃ አገሮች ህልዉና አደጋ ዉስጥ የሚከት የኤኮኖሚ ዕድገትን ብቻ ሳይሆን የአገር ደህንነትን ጭምር የሚፈታተን አደገኛ ጅምር ነዉ። ለመሆኑ ሉዓላዊ ቦንድ ምንድነዉ? አደገኛነቱስ ምኑ ላይ ነዉ?
ሉዓላዊ ቦንድ አገራቸዉ ዉስጥ ዝቅተኛ ቁጠባ የሚታይባቸዉ ብሔራዊ መንግስታት አገራቸዉ ዉስጥ ከአቅማቸዉ በላይ የሆነ የገንዘብ እጥረት ሲያጋጥማቸዉ የሽያጭ ዋጋዉ በአገራቸዉ ገንዘብ ሳይሆን ያወጣናል ብለዉ በሚያምኑት በሌላ አገር ገንዘብ ለምሳሌ በዶላር ወይም በዩሮ የተተመነ ቦንድ እየሸጡ ገንዝብ የሚበደሩበት መንገድ ነዉ። የየአገሩ መንግስታት ቦንድ አየሸጡ ገንዘብ መበደራቸዉ አዲስ ክስተት አይደለም፤ ሆኖም መንግስታት በተለይ የታዳጊ አገሮች መንግስታት ቦንድ የሚሸጡት አገራቸዉ ዉስጥ በአገራቸዉ ገንዘብ ነዉ። ሉዓላዊ ቦንድን ልዩ የሚያደርገዉ ቦንዱ የሚሸጠዉ በአለም አቀፍ ደረጃ ሆኖ ሽያጩ የሚከናወነዉ ደግሞ በዉጭ ምንዛሪ መሆኑ ነዉ። ሉዓላዊ ቦንድ ሽያጭን ከመደበኛ ቦንድ ሽያጭ የሚለዩት ብዙ ነገሮች አሉ።
ሉዓላዊ ቦንድ ከሌሎች መደበኛ ቦንዶች ጋር ሲነፃፀር ብዙ ዉስብስብ ችግሮች አሉበት። ለምሳሌ ሉዓላዊ ቦንድ የሚገዙ አገሮች ወይም ድርጅቶች ቦንዱን የሚገዙት በዉጭ ምንዛሪ ነዉ፤ ሁለተኛ ሻጩ አገር ለቦንዱ የሚከፍለዉ ወለድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ። በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ብዙዉን ግዜ ሉዓላዊ ቦንድ የሚሸጥ አገር ከቦንዱ ሽያጭ የሚያገኘዉ ገንዘብ ወለዱ የተቀነሰለት ገንዝብ ነዉ። ለምሳሌ በ10 በመቶ ወለድ የአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ሉዓላዊ ቦንድ የሚሸጥ አገር እጁ ላይ የሚገባዉ ዘጠና ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ብድሩን መልሶ ሲከፍል የሚከፍለዉ ደግሞ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ቦንድ ሻጩ አገር ወለዱን የሚከፍለዉ በተበደረዉ ገንዝብ ተጠቅሞበት ሳይሆን የተበደረዉ ገንዘብ ገና እጁ ላይ ሳይገባ ነዉ ወለዱን የሚከፍለዉ። ለሉዓላዊ ቦንድ የሚከፈለዉ ወለድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ስለሆን ብዙ አገሮች በተለይ ታዳጊ አገሮች ሉዓላዊ ቦንድ መሸጥ የማይፈልጉት ይህንኑ ለብድሩ የሚከፈለዉን ከፍተኛ ወለድ ሰለሚፈሩ ነዉ።
የወያኔ አገዛዝ እንደተራ ወረቀት እየፈበረከ ገበያ ዉስጥ የሚበትነዉ ገንዘብና ከአገር ዉስጥ ባንኮች ከአቅሙ በላይ የሚበደረዉ ገንዝብ ኢትዮጵያ ዉስጥ የዋጋ ንረቱን ምን ያህል ሰማይ ላይ እንደሰቀለዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ምን ያክል እንዳደኸየ ሁላችንም በግልጽ የምናዉቀዉ ሀቅ ነዉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የአገራችን ገበሬና ሠራተኛ የወያኔ ብልሹ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ለአመታት ከፈጠረዉ የዋጋ ንረት በሽታ ሳይድን ነዉ ሌላ ሉዓላዊ ቦንድ የሚባል በቀላሉ የማይድን አደገኛ በሽታ ፊቱ ላይ የተደቀነበት።
ሉዓላዊ ቦንድ ደሃ አገሮች የሚሸጡትና ኃብታም አገሮች የሚሸጡት እየተባለ በሁለት ይከፈላል። ኃብታም አገሮች የሚሸጡትን ቦንድ ከነወለዱ ከፍለዉ ይጨርሳሉ ተብሎ በቦንድ ገዢ አገሮችና ድርጅቶችና ስለሚታመን እነዚህ አገሮች ለሚሸጡት ሉዓላዊ ቦንድ የሚከፍሉት ወለድ ዝቅተኛ ነዉ። ኢትዮጵያን መሰል ደሃ አገሮች ግን ብድር የመክፈል ችሎታቸዉ አስተማማኝ ስላልሆነ ሉዓላዊ ቦንድ ሲሸጡ ለቦንድ ገዢዉ የሚከፍሉት ወለድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ። ስለሆነም ደሃ አገሮች በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አይነቶቹ ለመጀመሪያ ግዜ ሉዓላዊ ቦንድ ለሚሸጡ አገሮች ቦንድ ለመሸጥ ከመወሰናቸዉ በፊት ማስተካከል ያለባቸዉ ብዙ ነገሮች አሉ። በነገራችን ላይ ሉዓላዊ ቦንድ መሸጥ በራሱ ምንም ጥፋት የለበትም። እንዲያዉም ህዝባዊና አገራዊ ሃላፊነት የሚሰማቸዉ መንግስታት ሉዓላዊ ቦንድ በመሸጥ የፋይናንስ ጉድለታቸዉን በመሸፈን የአገራቸዉን እድገት አቅጣጫ ቀይሰዉ ጠንካራ ኤኮኖሚ የመገንባት አቅም ማግኘት ይችላሉ። በኛም አገር ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎቸ አንደኛ አገራዊ ሃላፊነት ቢሰማቸዉ፤ ሁለተኛ በአቅማቸዉ ቢኖሩ፤ ሦስተኛ በአገር ስም የተበደሩትን ገንዘብ መዝረፍ አቁመዉ ሁሉንም ለአገር ጥቅም ቢያዉሉትና ተበድረዉ በሚሰሯቸዉ ፕሮጀክቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ተጠቃሚ ቢሆን አገራችን መደበኛ ቦንድም ሆነ ሉዓላዊ ቦንድ በመሸጥ የምትበደረዉ ገንዘብ ብሄራዊ አቅም ስለሚገነባ ዕዳዉ ብዙም አያስፈራንም። ችግሩ ያለዉ ሉዓላዊ ቦንድ መሸጡ ላይ ሳይሆን እዚህ ዉሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት መወሰድ ያለባቸዉን እርምጃዎች በጥንቃቄ መዉሰዱ ላይ ነዉ። የወያኔም ትልቁ ችግር ያለዉ እዚህ ላይ ነዉ። የቦንዱ ሽያጭ ይዞት የሚመጣዉን ጣጣና ፈንጣጣ ግምት ዉስጥ ሳያስገባ ነዉ ሉዓላዊ ቦንድ እሸጣለሁ ብሎ ያወጀዉ።
የወያኔ አገዛዝ የበጀት ዲሲፕሊን የሌለዉ፤ በአቅሙ የማይኖር፤ እመራዋለሁ የሚለዉን አገር ኃብት የሚዘርፍና በሚያደርጋቸዉ ነገሮች ሁሉ ኢትዮጵያን የማያስቀድም የአገርና የህዘብ ጠንቅ የሆነ ክፉ አገዛዝ ነዉ።ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የወያኔ ፓርላማ የሉዓላዊ ቦንድ ሽያጭ ረቂቅ ህግ አፀደቀ ሲባል ቀልባቸዉ የረገፈዉ ከላይ የተጠቀሱትን የወያኔ ጠባዮች በሚገባ ሰለሚያዉቁ ነዉ። ወያኔ ከአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ የብድር ምንጮች በሚበደረዉ ገንዘብ መንገድ፤ ህንፃና ግድብ ሊሰራ ይችላል። እነዚህ ነገሮች በመሰራታቸዉ የሚከፋ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለንም። ብዙ ኢትዮጵያዉያንን የሚከፋቸዉ ወያኔ በነሱ ስም በተበደረዉ ብድር በጀመራቸዉ ፕሮጀክቶች ሁሉ መጠቀም አለመቻላቸዉና በገዛ አገራቸዉ የበይ ተመልካች መሆናቸዉ ነዉ። እዚህ ላይ የህዳሴዉን ግድብ አንደ ምሳሌ ወስደን መመልከት እንችላለን። የህዳሴዉን ግድብ የእንጂኔሪንግ ኮንትራት ያለምንም ጨረታ አሸንፎ ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሰዉ መስፍን ኢንጂኔሪንግ የተባለ የወያኔ ድርጅት ነዉ። ለህዳሴዉ ግድብ ማሰሪያ ሲሚንቶ የሚያቀርበዉ የወያኔዉ መሶብ ሲሚንቶ ፋብሪካ ነዉ። ለግድቡ ፕሮጀክት የትራንስፖርትና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጡት የአዜብ መስፍን ዘመዶች ናቸዉ;፡ ለህዳሴዉ ግድብ ሰራተኞች የምግብ አገልግሎት የሚሰጡት የወያኔ ኩባንያዎች ናቸዉ። የህዳሴዉን ግድብ እንደምሳሌ ወሰድነዉ እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ በብድርም ሆነ በእርዳታ ገንዘብ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ሁሉ ተጠቃሚዉ ወያኔና ባለ ሟሎቹ ናቸዉ። ወያኔ እንደ ተራራ የቆለለዉን ብድር እስከነወለዱ የሚከፍለዉ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ነዉ።
የአለም ባንክንና አለም አቀፉን የገንዝብ ድርጅት ጨምሮ ብዙ የኤኮኖሚ ሳይንስ ጠበብቶች አገሮች በተለይ የዉጭ ዕርዳታ ጥገኛ የሆኑ ደሃ አገሮች ሉዓላዊ ቦንድን አገር ዉስጥ ለሚያጋጥማቸዉ የገንዘብ ጉድለት ማሟያ አድረገዉ እንዳይጠቀሙ በተከታታይ ያስጠነቅቃሉ። የወያኔ አገዛዝም ይህ ማስጠንቀቂያ በተከታታይ ከደረሳቸዉ መንግስታት አንዱ ነዉ። ሆኖም የማንንም ምክር የማይሰማዉ ወያኔ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ሉዓላዊ ቦንድ በመሸጥ መዘዙ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚተላለፍ ክፉ በሽታ እየዘራ ይገኛል። ወያኔ እስከዛሬ የተበደረዉ ብድር ምኑም ሳይከፈል ሉዓላዊ ቦንድ ከጀመረ በእናት አገራችን ላይ እንደ ትልቅ ተራራ የሚቆለለዉን ብሄራዊ ዕዳ የምንከፍለዉ እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳንሆን ገና ያልተወለዱ የልጅ ልጆቻችን ጭምር ናቸዉ።
ኢትዮጵያ ኤኮኖሚዋ ያልዳበረ ደሃ አገር በመሆኗ አበዳሪ አገሮችን ብድር ሰርዙልኝ ብላ ሳትወተዉት፤ የብድር ክፊያ ግዜዋን ሳታራዝም፤ ወይም የብድር ዉል ማሻሻያ ጥያቄ ሳታቀርብ እስከዛሬ የተበደረችዉንና ለወደፊትም የምትበደረዉን የዉጭና የአገር ዉስጥ ብድር የመክፈል ሃላፊነቷን ጤናማ በሆነ መልኩ መወጣት የምትል አገር አይደለችም። እንደዚህ የምንለዉ ደግሞ ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን ስለምንጠላ ሳይሆን በሚከተሉት ማስረጃዎች ላይ ተንተርስሰን ነዉ። 1ኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዕዳና አጠቃላይ አገራዊ ምርት (GDP) መጧኔ ቁጥሩ ከፍተኛ ነዉ።
ይህ ማለት ኢትዮጵያ የተቆለለባት ዕዳና ቤሄራዊ ገቢዋ ይቀራረባሉ፤ እኩል ናቸዉ ወይም ዕዳዋ ከገቢዋ ይበልጣል ማለት ነዉ። 2ኛ የአገራችን የዉጭ ብድርና የዉጭ ንግድ ገቢ መጣኔ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ምርታችንን ለአለም ገበያ አቅርበን የምናገኘዉ የዉጭ ምንዛሪ ከዉጭ አገር ዕቃ ሊገዛልን ቀርቶ የተበደርነዉን ብድር ወለዱንም መክፈል አይችልም ማለት ነዉ። 3ኛ የወያኔ አገዛዝ የብድር ዕዳና አገዛዙ አገር ዉስጥ በግብር መልክ የሚሰበስበዉ ገቢ መጣኔ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ። ቀለል ባለ አማርኛ የወያኔ አገዛዝ ሁሉንም ነገር ትቶ በሚሰበስበዉ ገንዘብ ዕዳዉን ብቻ ቢከፍል ከእዳዉ ለመላቀቅ ብዙ አመታት ይፈጅበታል።


    ለእናት አገራቸዉ ለኢትዮጵያ የሚጨነቁ ኢትዮጵጵያዉያን የወያኔ ፓርላማ በቅርቡ ያፀደቀዉን የሉዐላዊ ቦንድ ሽያጭ ህግ አጥብቀዉ የሚቃወሙት እነዚህን ሁሉ ገሃድ የወጡ የአገራችንን ችግሮች በሚገባ ስለሚያዉቁ ነዉ። ለኢትዮጵያና ለህዝቧ እንጨነቃለን ስንል ደግሞ እንደ ወያኔ “እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል” በሚል የንፉጎች አባባል ተዉጠን አይደለም። ለትናንትናዋ ኢትዮጵያ እንደተጨነቅን ሁሉ ለዛሬዋ፤ ለነገዋና እኛ ካለፍን በኋላ ለሚመጣዉ ኢትዮጵያዊ ትዉልድም እኩል እንጨነቃለን። ለዚህም ነዉ የሉዓላዊ ቦንድ ሽያጩን ብቻ ሳይሆን ወያኔ ያመጣብንን መዐት ሁሉ ለማስቆምና አገራችንን በትክከለኛ የእድገትና የዲሞክራሲ መሠረቶች ላይ ለማስቀመጥ ወያኔ መወገድ አለበት ብለን የሞት የሽረት ትግል የጀመርነዉ።

    Wednesday, December 3, 2014

    ዞን ዘጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ


    December 3, 2014 -

    በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ዛሬ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ህዳር 24/2007 ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲሰጥ ለአቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም ሙሉ የክስ ወረቀቱ አርብ ለጠበቆቹ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
    zone 9በጠቦቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ ግልባጭ ሳይደርሰን ተሻሻለ የተባለው ክስ መሰማት የለበትም ብለው የነበር ቢሆንም፣ ክሱን አይታችሁ መቃወሚያ ካላችሁ አስተያየት እንድትሰጡበት እድል እንሰጣለን ያለው ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሰማ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ ያላቸውን አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡
    Source: ነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

    ምን አይነት ሰላማዊ ሰልፍ?


    በተክሉ አባተ (teklu.abate@gmail.com)
    ለመጀመሪያ ጊዜ በሰላማዊ ሰልፍ የተሳተፍኩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ግቢ ተማሪ እያለሁ ነበር:: በአራት ዓመት
    የትምህርት ቆይታዬ በርከት ያሉ ሰልፎች ተካሂደዋል:: አንዳንዴ የምግብ ጥራት ማሽቆልቆሉን በመቃወም ሌላ ጊዜ ነጻነትን
    ፍትህንና ዴሞክራሲን እንዲሁም የመሬት ክፍፍልን በመቃወም:: ምግብን በተመለከተ የተቀናጁ ሰልፎች አጀማመራቸው
    ምግብ-ነክ ይሁን እንጅ መደምደሚያቸው ፖለቲካ ነበር:: ድንገት ከሰልፉ መካከል አንዱ ተነስቶ "ፍትህና መብት ይከበር"
    ካለ ተሜ ወዲያው ተቀብሎ ያስተጋባዋል:: አንዳንዶች ደግሞ በራሳቸው ተነሳሽነት ቀድሞ የተዘጋጀ የጽሁፍ መፈክር ብቅ
    ያደርጋሉ:: በአቅራቢያቸው ያለ ተሜ እያነበበ ያስተጋባዋል:: ሌላው ይቀበለዋል:: የአንገት ስር እስኪወደር ድረስ ይፎከራል::
    ስሜት እየጋለ ይሄዳል:: የተሰላፊው ቁጥር የሚጨምረው ሰልፉ ከተጀመረ ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ ነው:: መጀመሪያ
    ላይ ፈራ ተባ እያሉ ከዳር ሆነው የሚመለከቱ ይበዛሉ.: በኋላ ድንገት ሰልፉን የሚቀላቀሉ ይበዙና ተሰላፊው ዋናውን በር
    የሚወጣው በሦስትና አራት ረድፍ ባለው ረጅም መስመር ነው::
    የሚገርመው ሰልፉ ሰላማዊ ተብሎ ቢጀመርም ሰይፋዊ ሆኖ ይጠቃለላል:: ካድሬ ሰላይ ፖሊስና ወታደር ሙያቸውን
    የሚያስመሰክሩበት ልዩ አጋጣሚ እስኪመስል ድረስ አካባቢውን ያጥለቀልቁታል:: ከጥቂት ማስፈራራት በኋላ ወደ ርምጃ
    ይሸጋገራሉ:: ተሜም እድሉን የሚለካበት ጊዜ ይገጥመዋል:: ግርግርና ዱላ በጥበቃ አካላት ይጀመራል:: ጥጋቸውን ይዘው
    በሚጠባበቁ አይፋ በሚባሉ ወታደራዊ መኪናዎች ተሜ ወደ ማሰቃያ ጣቢያዎች ይወሰዳል:: በደንብ የሚደበደቡ: የሚታሰሩ:
    ከትምህርታቸው የሚባረሩ: ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው ብዙ ናቸው:: ጀርባቸው እስኪላጥ እግራቸው እስኪጠቁር በፖሊስ
    የሚሰቃዩ ሞልተዋል:: በተለይ ሸጎሌ ተብሎ ከሚጠራው መጠርነፊያ ጣቢያ የተወሰዱት ያጋጠማቸው ስቃይ 'ታሪካዊ' ነበር::
    በባዶ እግራቸው እንደጦር በቆመ አሸዋ ላይ ያሴዷቸው ነበር:: በካድሬዎች ወከባ የተነሳ ትምህርት ያቋረጥንባቸው ጊዜያትም
    ነበሩ::
    የበለጠ የሚገርመው ደግሞ ለቀናት ከሚዘልቀው አካላዊ ስቃይ ይልቅ ተማሪዎች የሚደርስባቸው ሥነ-ልቦናዊ ጥቃት
    ነበር::ተማሪዎች ከእስርና ከስቃይ ለመውጣት ከፈለጉ መንግስትን ይቅርታ እንዲጠይቁ ይገደዳሉ:: ከዚያም በማናቸውም
    ተመሳሳይ ሰልፎች ወይም ዝግጆቶች ላይ ወደፊት እንደማይሳተፉ በሚገልጠው ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ ይደረጋሉ:: በመሆኑም
    ከእስራታቸው በኋላ ትንፍሽ እንኳን የማይሉ እየተበራከቱ መጥተው ነበር:: እስካሁንም ድረስ ያንን የገቡትን 'ቃል
    ኪዳን' ታሳቢ በማድረግ በመሳቀቅ የሚኖሩ አሉ::
    ውጤታቸው ምንም ይሁን ምን የተደረጉ ሰልፎች መደረግ የነበረባቸው ናቸው ብዬ አምናለሁ:: ውጤት ያመጡ ሰልፎች
    ነበሩ:: እነወይዘሮ ገነት ዘውዴ እና እነ ዶክተር ዱሪ ላባቸው እስኪመጣ ድረስ በተሜ ተፋጠዋል:: ቀላል የማይባሉ
    ለውጦችም ወዲያውኑ ተደርገዋል:: እነዚያ ሰልፎች የተማሪን ህይወት ያማከሉ ቢመስሉም (አንዳንድ የአዲስ አበባ ኗሪዎችተሜ ለዳቦ ጥራት እንጅ ለሃገሩ እድገት አይሰለፍም እያሉ ቢሳለቁም) ከብሄራዊ የዜግነት ግዴታዎችና መብቶች ጋር የተያያዙ
    ናቸው:: ነጻነት ፍትህ እኩልነት የተጠየቀባቸው ሰልፎች ነበሩና::
    የሰልፍ ሁሉ መጀመሪያ
    ከላይ ያለውን ታሪክ ያነሳሁት እንደመግቢያ እንዲያገለግለኝ ነው:: ዋናው ነጥቤ በአሁኑ ጊዜም ኢትዮጵያ ውስጥ የሰላማዊ
    ሰልፍን አስፈላጊነት ለማመላከት ነው:: የዜግነት መብት እስካልተከበረ ድረስ ሰልፍ ይካሄዳል:: ለመብትና ለአገር ክብር
    የሚደረግ ሰልፍ ሰው የመሆን አንዱ መገለጫ ነው:: ሰልፉ ግን መጀመር ያለበት ከግል ህይወት ነው:: በማይጠቅሙ ሃሳቦች
    የተሞላ አእምሮ ያለው ሰው በራሱ ላይ ሰልፍ መውጣት አለበት:: መብቱ በጓደኛው ወይም በሥራ ባልደረባው የሚጣስበት
    ካለ በዚያ ላይ ሰልፍ መውጣት አለበት:: አባል የሆነበት ድርጅት መብቱን የሚጥስበት ከሆነ ሰልፍ መውጣት አለበት:: ሰልፍ
    መውጣትም በአካል ወደአደባባይ መንጎድን ብቻ አይመለከትም:: ፍርሃትንና ይሉኝታን አስወግዶ ሃሰተኞች ወይም መብት
    እረጋጮች የሚሰሩትን ግፍ ፊትለፊት መናገርንም ያጠቃልላል:: በአደባባይ ሰልፍ ተገኝቶ በጓዳ መብቱንና ጥቅሙን የሚያስነካ
    ሰው ራሱን ያታልላል:: በውስጥም በውጭም በአካልም በሥነ-ልቦናም በግልም በቡድንም በደልን መቃወም ማጋለጥም
    ያስፈልጋል:: "መብቴ ተጣሰ" ብሎ ሰልፍ የሚወጣ የሌላውን ሰው መብት መጠበቅም ሊኖርበት ነው:: እያንዳንዳችን
    ለራሳችን መብት ሳናቋርጥ ሰልፍ መውጣት አለብን:: ይህ ከሆነ ነው የቡድን ሰልፎች የሚያምርባቸውና ውጤታማ
    የሚሆኑት:: ብዙ ሰዎች አብዝተው የሚጨነቁት ግን በቡድን ስለሚደረግ ሰልፍ ነውና ለጊዜው እሱን እንመልከት::
    ውጤታማ ሰልፍ
    በአጠቃላይ ሲታይ የትም ቦታ በማናቸውም ጊዜ የሚደረጉ ህግን መሠረት ያደረጉ የቡድን ሰላማዊ ሰልፎች ሁሉ ልዩ ባህርይ
    አላቸው:: ዳሩ ግን አንድ ሰልፍ ግልጽ ዓላማዎችና የአፈጻጸም ስልቶች ሊኖሩት ይገባል:: ይህ ደግሞ በጊዜና በቦታ ሊወሰን
    ይችላል.: ያም ሆኖ አንድን ሰልፍ ውጤታማ ነው ብሎ ለመፈረጅ በርካታ መለኪያዎችን ማሟላት ይኖርበታል:: ለእኔ የተሳካ
    ሰልፍ ማለት ቀጥለው የተዘረዘሩትን የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜያት አብዛኞችን መስፈርቶ ች ያሟላል::
     ሰልፉን ተከትሎ ተሰላፊዎች በራስ የመተማመንና የእርካታ ስሜት ማግኘት አለባቸው
     ተሰላፊዎች በቋሚነት የራሳቸውንና የወገናቸውን መብቶች ለማስጠበቅ ጽኑ አቋም ይይዛሉ
     ሰልፍ ህግን በማያከብረው በመንግስት ላይ ስጋትና ፍርሃትን ማስፈን አለበት
     መንግስት ለጊዜው በይፋ ለውጦችን ለማድረግ ቃል ባይገባም ወደዚያው የሚያደርሱ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርግ
    ማስገደድ አለበት
     መንግስት ተረጋግቶ ጭቆናውን እንዳይቀጥል ያደርገዋል
     የመንግስትን ጨቋኝነት የሌሎች ሃገራት መሪዎችና ተቋማት በደንብ እንዲያውቁት ያደርጋል
     አንዱ ሰልፍ ሌላ ሰልፍ ይወልዳል
     በሰልፉ ምክንያት የሚታሰር የሚደበደብ የሚሰደድ ወዘተ ካለ ስለእሱም ፍትህ ይጠይቃል ሌላ ሰልፍ በተሻለ ሁኔታ
    ይደረጋል መንግስት በሚያደርጋቸው ጥቂት የማስታገሻ ማሻሻያዎች አይታለልም
     በመጨረሻም የሚፈለገው ለውጥ በመጠንና በዓይነት ይገኛል
    የውጤታማ ሰልፍ መገለጫ ባህርያት
    ከላይ የተዘረዘሩትን እንዲሁም ሌሎችን ውጤቶች ለማሳካት አንድ ሰላማዊ ሰልፍ ማሟላት ያለበት ባህርያት ይኖራሉ::
    ጥቂቶችን እንዲህ ዘርዝያለሁ::
     በደንብ የተደራጀና የተመራ ሰልፍ የተሰላፊውን ቀልብ ከመሳብ በተጨማሪ ያልተሰለፉ ሰዎችም ወደፊት እንዲሰለፉ
    ይጋብዛል
     ለረጅም ጊዜ ወይም በተከታታይ የሚደረግ ሰልፍ እጅግ አመርቂ ውጤት ያመጣል
     ሰልፍ በሚደረጉ መጥፎ ሥራዎች ላይ ያለን ተቃውሞ ለማሰማት ብቻ ሳይሆን ለውጥ እንዲደረግ
    የሚያስገድድ መሆን አለበት
     ሰልፍ መንግስት መመለስ ያለበት ግልጽ ጥያቄዎችን ማቅረብ አለበት
     እንደ ጉዳዮች ትልቅነትና አሳሳቢነት እየታየ መንግስት መልስ የሚሰጥበት ጊዜም መገለጽ አለበት
     በተሰጠው ጊዜ መንግስት አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በአይነቱና በመጠኑ ልዩ የሆነ የተቀነባበረ ሰልፍና ህዝባዊ
    ተቃውሞ እንደሚደረግ ማሳወቅ አለበት
     ሰልፍ አስተባባሪዎች ሊታሰሩ ወይም ሊሰው ስለሚችሉ በርካታ መሪዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል
     ህዝቡ መብቱን በሚገባ እንዲያውቅና ትግሉን በቀጣይነት እንዲመራ ማድረግ ወሳኝነት አለው
     ህዝቡ ኃይልንና ስሜትን ተቆጣጥሮ ከሰልፉ ዓላማ ላይ ትኩረትን ማድረግ እንዳለበት መነገር አለበት
     ህዝቡ በአቋሙ ከጸና ጨቋኝ መሪዎች እንደሚሸነፉ ማስተማርና ሥልጣን የህዝብ እንደሆነ ማሳሰብ ያስፈልጋል
     ፖሊስና ወታደር በሚመጣበት ጊዜ ከመሮጥ ይልቅ ሁሉም ተረጋግቶ ባለበት እንዲጸና ማድረግ ያስፈልጋል
    ማጠቃለያ
    የኢትዮጵያ ህዝብ የግልም ሆነ የቡድን መብቱ ተረግጧል:: ኑሮ ከአቅሙ በላይ ሆኗል:: ይህ አላንስ ብሎ ያሰበውን
    እንዳይናገር አንደበቱ ተዘግቷል:: በተጨማሪም መንግስት አንዱ ህዝብ በሌላው ላይ እንዲነሳ የቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው::
    በመሆኑም እውነተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አማራጭ የሌለው የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሆኗል.: አገር ቤት ሆነው
    የሚታገሉት ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት መድረክ በመፍጠር ሰላማዊ ሰልፍ ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር
    28/2007 ዓ/ም ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ:: ይህ በዓይነቱ የተለዬ ሰልፍ በሁሉም ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ
    ሊደገፍና ሊበረታታ ይገባል:: በአካል በሞራል በሃሳብና በገንዘብ መደገፍ ይኖርብናል:: የሰልፉ አስተባባሪዎችም እጅግ ጥበብ የተሞላበት እቅድ ነድፈው ህዝቡን ደረጃ በደረጃ መምራት አለባቸው:: መንግስት
    ሊያሟላቸው የሚገቡ ጉዳዮች በቁጥር ተለይተው እስከነ ጊዜ ገደባቸው መቅረብ አለባቸው:: ጥያቄዎች የማይመለሱ ከሆነ
    ቀጣይነት ወዳለው ህዝባዊ ተቃውሞ ማሸጋገር ያስፈልጋል:: መስቀል አደባባይን እንደ ዋና ቢሮ አድርጎ በመላ ኢትዮጵያ
    ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዲካሄድ ማድረግ ወሳኝነት አለው:: ሰልፉ በመጠንና በቦታ ባደገ ቁጥር የመንግስት ጫና እየላላ
    ይሄዳል:: በመጨረሻም የህዝብ መብት ተከብሮ ሥልጣን ለህዝብ ይሆናል:: ከዚያም ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸውን
    እያጣጣሙ ሃገራቸውን እንደገና በኅብረት ይገነቧታል:: አላስፈላጊው ስደትና ስቃይ ታሪክ ሆኖ ይቀራል::

    Tuesday, December 2, 2014

    To her Excellency Angela Merkel the Federal Chancellor of Germany


    December 2, 2014
    This is the voice of millions of Ethiopian all over the world, including the forgotten Ethiopian who starves democracy, freedom and Justice.This is the voice of prisoned journalists, bloggers and political prisoners who seeks fair and true justice. We believe your Excellency Angela Merkel stand for democracy and true non-discriminatory justice!
    You’re Excellency
    This is a briefing letter on Ethiopian issue; and the ever worsening human rights and infringement of constitutional rights that are pertaining as a result of gruesome human right violation in Ethiopia!
    1. Ethiopia deserves an independent press to advance democracy and the rule of law. We urge the EU and Germany to demand immediate release of journalists, bloggers, other media workers and political dissenters. There can’t be free and fair elections without an independent and free press and without the opening up of political space for all stakeholders.
    2.Forcible evictions, rapes, killings, dispossessions and persecutions of indigenous people and others from their lands—-Gambella, the Omo Valley, the Ogaden and Beni-Shangul Gumuz—and ethnic cleansing of Amharas throughout Ethiopia have reached a tipping point and entail existential risks for the country. These atrocities must be stopped by the global community before Ethiopia becomes the next Rwanda.
    We genuinely believe and trust that Germany as a democratic country the EU, and the UN system can and should take the lead in helping to stop the onslaught. We urge you to also reflect and give thoughts on the merit of a National Reconciliation and Peace process involving all stakeholders. We admit that Ethiopia is not at war on the scale of Rwanda or South Africa etc. But there is a silent war; and people are paying with their lives.
    We hope and pray you will agree with us that the German with the UN System and especially the German human right have a moral if not a fiduciary responsibility as a global human rights watchdog to consider this appeal.
    OHCHR is willing and ready to send special Rapporteurs to Ethiopia to investigate gross human rights violations including the uprooting and ethnic cleansing of Amharas. This won’t happen unless, under your leadership, the German participates in real terms and not in rhetoric.
    “We call upon the Government of Ethiopia to free all persons detained arbitrarily under the pretext of countering terrorism…Let journalists, human rights defenders, political opponents and religious leaders carryout their legitimate work without fear of intimidation and incarceration.” We should like to add. Let Ethiopians live wherever
    Her Excellency
    We know that today you will met with Ethiopian Prime Minister Mr Hailemariam Desalegn , it is known that you as a German Chancellor and as a good governor expected to urge the release of political Prisoners , journalists and bloggers and to discuss over the release of all political prisoners.
    With Best regards
    Ethiopians In Germany

    የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር

     
    ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ
    የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ ­ በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል።    
              ­­ ክንፉ አሰፋ ­­
    "እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን
    ግን ይኸውና ህገ­መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል... ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።"
      እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ
    ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ
    መስመር ገብቶለት፣  የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም... ይመስላል።
       የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ እና አለባበሱ የሚነግረን ግን  ሌላ ነው። በኢህአዴግ ዘመን መብቱ እንደተከበረና ኑሮው
    እንደተሻሻለ  የሚነግረን  ይህ  ሰው፣ መሰረታዊ  የሆነውን   የሰው  ልጆችን  የኑሮ  ፍላጎት  እንኳን  አላሟላም።  ለእግሩ ጫማ
    የለውም።  በባዶ እግሩ ነው የቆመው። ሃፍረተ ስጋውን ከሸፈነለት ብጣቂ ጨርቅ በስተቀር ሰውነቱም እርቃኑን ነበር።
      ለመገናኛ  ብዙሃን  ፍጆታ  አነጋገሩ  እንዲያሳምር  ተነግሮት  ሊሆን  ይችላል ­  ንግግሩ  ልክ  መካከለኛ  ገቢ  ካላቸው
    የምዕራብ አውሮፓ  ሃገሮች ተርታ የተሰለፈ ይመስላል። ይህ ደግሞ ገና የ'ትራንስፎርሜሽኑ' ተስፋ እንጂ፤ ለውጡ በብሄር
    ብሄረሰቦቹ  ላይ  እንደማይታይ  የቪድዮ  ምስሎቹ  ፍንትው  አድርገው  ነው  የሚያሳዩት።  ኢትዮጵያ  በአምስት  አመት  ጊዜ
    ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ላይ እንደምትደርስ ኢህአዴግ ቃል ገብቷል። በአሁኑ ግዜ ሰባት በመቶ ብቻ
    የሆነው የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ብሄር ብሄረሰብ እና ሕዝብ በአምስት አመቱ እቅድ 80 በመቶ ይደርሳል ብለውናል። በእስር
    ያለው  ጠንቋይ  ታምራት  ገለቴ  ነግሯቸው  ካልሆነ  በስተቀር  መቼም  ይህንን  ተረት  ተረት  በማህበራዊውም  ሆነ  በተፈጥሮ
    ሳይንስ ሊያረጋግጡልን እንደማይችሉ እርግጥ ነው። ከፈረሱ ጋሪው... እንዲሉ ከተግባሩ ወሬው፣ ከ’ህዳሴው ግድብ’ ስራም
    ሽልማቱ ቀድሞ መያዣ ­ መጨበጫው የጠፋ ነው የሚመስለው።
    ከገጠር  እየታፈሱ  ለሚመጡት  ለነዚህ  ምስኪን  ወገኖች  የ  ‘ብሄር  ብሄረሰቦች  እና  ህዝቦች’  መብት  ማለት  በአመት  አንዴ
    በጎዳና ላይ  እየወጡ መጨፈር እና ያለፈውን ስርዓት ማውገዝ ብቻ ነው የሚመስለው። ጭፈራውና ውግዘቱ እንደ ጥምቀት
    በዓል ስለተለመደ የግድ መደረግ እንዳለበት ያመኑበትም ይመስላል።
    የደርግ  ስርዓት  ሰዎች  በባህላቸውና  በቋንቋቸው  እንዳይዘፍኑ  ከልክሎ  እንደነበር  የሚጠቁም  መረጃ  የለም።   ደርግ  አስራ
    ሰባት  አመት  ገዛ፣   20  አመት ሙሉ  በብሄር ጭቆናው ሲወገዝ  ኖረ።  በባንዲራ  ቀን ውግዘት፣   በከተሞች  ቀን ውግዘት፣
    በብሄር  ብሄረሰቦችና  ህዝቦች  ቀን  ውግዘት፣  በግንቦት  ሃያ  ቀን  ውግዘት....  በየሽልማቱ  ስነ  ስርዓት  እና  በየበዓላቱ  ቀን
    ውግዘት....። የደርግ ሃጢያት መብዛት የነሱን ግፍ ይሸፍን ይመስል የኢህአዴግ በዓላት እና ውግዘቱ ከለት­ተለት ሲጨምር
    ብቻ ነው የምናየው ­ እንደ 11 በመቶው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያ እድገት።  የዚህ ሳምንት ወሬ ደግሞ በመቀሌ ስለተካሄደው ስድስተኛው የ ‘ብሄር ­ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን’ ነው። የመከር ወቅት
    ስራቸውን  እንዲያቆሙት  ተደርገው፣  ከየክልሉ  እየተጫኑ  ለጭፈራ  መቀሌ  የገቡ  አርሶአደሮች  ቁጥር  ቀላል  አይደለም።
    በዲያጎን እየተፈለጉ የተለቀሙ ልማታዊ አርቲስቶች እና የመድረክ አስተዋዋቂዎችም በስፍራው ተገኝተዋል።
      የእውቁ ኪነጥበብ ሰው ­ የኪሮስ አለማየሁ ልጅ ዛፉ ኪሮስ 'አንበሳ ገዳይ' በሚለው የትግርኛ ዘፈንዋ መድረኩን
    ይዛዋለች።  በርከት  ያለ  ሰው  መድረኩን  ከቦት  ይጨፍራል።  አዳራሹም  በ ‘ብሄር ­  ብሄረሰቦች  እና  ህዝቦች’  ተሞልቷል።
    መቀሌ፣ ኅዳር 27 ቀን 2004 ዓ.ም.።
      የእለቱ  የመድረክ  አስተዋዋቂ  'አንበሳ  ገዳይ'  የሚለው  የዛፉ  ኪሮስ  ዘፈን  የተስማማው  አይመስልም፤
    አልተዋጠለትም። አልያም ዘፈኑን እዚያው መድረክ ላይ እንዲያስተባብል ተነግሮታል። ተራውን ጠብቆ ማይክራፎኑን ያዘ።  
    "ህገ መንግስታችን  ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለዱር እንስሶችም..."
      ብሎ እየተናገረ እያለ እንደተለመደው መብራት ተቋረጠ።
       በዚህ 'ታላቅ' ቀን መብራት መቆራረጡ ቢያበሳጭም፣  በእንግድነት ወደ መቀሌ  የተጓዙት ‘ብሄር ብሄረሰቦች  እና
    ህዝቦች’ ኤሌክትሪክ ምን እንደሆነ ስለማያውቁ አልደነቃቸውም ­ የሚያውቁት ደግሞ የለመዱት ስለሆነ ­ ለእነሱ እንግዳ
    ነገር አይደለም።  ከቆይታ በኋላ ግን መብራት መጣ። ልማታዊው አርቲስትም ንግግሩን ቀጠለ።
    "...ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የዱር አራዊቶችንም መብት ስላስከበረ አንበሶች
    አሁን አይገደሉም።…"
      በማለት  የዘፈኑን  መልእክት  ለማስተባበል  እና  ጭብጡን  ለብሄር  ብሄረሰቦች  እና  ህዝቦች    ለማስረዳት  ሞከረ።
    እዚህ  ላይ  የመድረክ  አስተዋዋቂው  እና  ዘፋኝዋ  እንዳልተግባቡ  መገመት  ይቻላል።  ዛፉ  ኪሮስ  ዘፈንዋን  በዚህ  መድረክ
    ታቅርበው እንጂ መልእክቱ ላሁኑ ትውልድ ሳይሆን ምናልባት 'ተራራ ላንቀጠቀጠው' ለዚያኛው ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ
    የተሳነው  ይመስላል።  ያ  ቡድን  የትኛውን  ተራራ  እንዳንቀጠቀጠ  ባይገለጽልንም  አሁን  ያጠለለበት  የለውጥ  ደመና  ግን
    በተራው እያንቀጠቀጠው ለመሆኑ ከሚያደርጋቸው ግራ ገብ ድርጊቶቹ  መረዳት ይቻላል።
      የሆነው  ሆኖ  በአሉ  ለመቀሌ  ህዝብ  ልዩ  ስሜት  እንደሰጠው  ይታያል።   ይህ  ህዝብ  ከሌላው  ኢትዮጵያዊ  ወገኑ
    ተለይቶ፣  በእነ  መለስ  እና  በረከት  ካድሬዎች  ታጥሮና  ታፍኖ  የሚገኝ  ህዝብ  ስለመሆኑ  በርካታ  መረጃዎች  ይመሰክራሉ።
    ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚተቁሙት ከመንግስት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ውጭ ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን በዚያ
    ክልል  መጠቀም  ራሱ  እስከ  ስድስት  ወር  የሚያሳስር  ወንጀል  ነው።  ለ20  አመታት  የታፈነ    ህዝብ  ከሌላው  ወገኑ  ጋር
    ተቀላቅሎ ፣  አብሮ ሲጨፍር የሚፈጥርበትን ስሜት መገመት አያደግትም።  የደርግ ስርዓት የአሜሪካ እና የጀርመን ድምጽ
    ራዲዮን  የትግራይ  ህዝብ  እንዳይሰማ  አልከለከለም  ነበር። ወያኔ  ግን  የትግራይ  ህዝብን   የመናገር ብቻ ሳይሆን  የመስማት
    መብቱንም ጭምር ነው የነፈገው።   የሳተላይት ዲሽ ቴሌቪዥን ክልክል በሆነበት በዚያ ክልል የኢቲቪ አኬልዳማ ድራማ ይደገምልን ብሎ የትግራይ
    ህዝብ  ቢጠይቅ  ሊደንቀን  አይገባም።  ጆሮ  ካሰለቸው  የ'ህዳሴው  ግድብ'  ወሬ  እና  እጅ  እጅ  ካሉት  ከነ  ሰራዊት  ፍቅሬ
    አኬልዳማ  ትንሽም  ቢሆን  ዘና  ሳያደርጋቸው  አልቀረም።    የቴሌቪዥኑ  መግቢያ  ላይ  ታዲያ    'እንደምን  አመሻችሁ  ዲሽ
    የሌላችሁ" ብሎ ነው የሚጀምረው እየተባለም ይቀለዳል።  ይህ ህዝብ በስሙ ሲነገድበት እና ከሌላው ወገኑ ጋር እንዲቃቃር
    ሲደረግ የትግራይ ኢሊቶች ዝም ማለታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ነው።
      ስለ ዱር  አራዊት መብት  እና  ስለ  አንበሳ መግደል ሲነሳ ትዝ ያለኝ  የ1983ቱ  የአምባሳደር ተስፋዬ ሃቢሶ ንግግር
    ነበር። ቻርተሩ ሲጸድቅ በነበረበት ጊዜ የከምባታና ሃድያን ጎሳ እወክላለሁ ብለው ወንበር ይዘው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ
    በወቅቱ ሲናገሩ።
       "እኛ  አናሳ  ብሄር  ብሄረሰቦች  ዲሞክራሲ  ብቻ  ሳይሆን  የሚያስፈልገን፣    እንደብርቅዬ  እንስሣ  እንክብካቤም
    ይገባናል።" ብለው ነበር።
      ኢህዴግም በወቅቱ ለእነኚህ 'አናሳ ጎሳዎች' ልዩ እንክብካቤ እንደሚያደርግ ነበር ቃል የገባው።
      አቶ  ተስፋዬ  ይህንን  በተናገሩ  ከአመታት  በኋላ  ታዲያ  በሃዲያ  እና  ወላይታ  ወገኖቻችን  ላይ  ጥይት  እና  ቦምብ
    እንደዝናብ ወረደባቸው።  የ1993ቱ ብሄራዊ ምርጫ ተጭበርብሯል፣   ‘ድምጻችን ይከበር’ ብሎ የጮኸው የደቡብ ወገናችን
    በመለስ ወታደሮች ያለ ርህራሄ ነበር የተጨፈጨፈው።  ልዩ እንክብካቤው እና ዴሞክራሲው ቀርቶ ይልቁንም የቆሙለት፣
    በስሙም  ስልጣን  ያገኙበት፣    የራሳቸው  ጎሳ  በጥይት  ሲቆላ  አቶ  ተስፋዬ  ሃቢሶ  ሹመታቸውን  ላለማጣት  ሲሉ  ትንፍሽ
    አላሉም።  እንዲያውም  ዛሬም  ስለ  ‘ብሄር  ብሄረሰቦች  እና  ህዝቦች’  መብት  መከበር  ከሚነግሩን  እና  የሌሎችን  ጽሁፎች
    እየሰረቁ ከሚጽፉት ሰዎች አንዱ ናቸው።
       ማሌሊቶቹ የሃገሪቱ የዘመናት ችግር የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት መነፈግ ነው ሲሉ ሰበኩ። የዚህ ችግር
    መፍቻ ቁልፍም በእጃቸው  እንዳለ  ነገሩን። በለስ ቀንቷቸው ምኒሊክ ቤተ መንግስት ሲገቡም ጫካ ውስጥ  የጻፉትን ያንን
    የስታሊን ፍልስፍና ወደ ህገ­መንግስትነት ቀየሩት።  መፍትሄ ያሉት የጎሳ ፖለቲካም በጥላቻና በበቀል ተተካ።
       የማሌሊት ፍልስፍና ሲተገበር ታዲያ የመጀመርያ ሰለባ የሆነው አማራው ወገናችን ነበር። ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ እነ
    አቶ መለስ  ዜናዊ ይዘውት  የመጡት  የጥላቻና  የብቀላ ፖለቲካ  እንደስካር  ቶሎ  በረደ  እንጂ  አካሄዱ  እጅግ  ዘግናኝ  ነበር።
    በምስራቅ  እና  በምእራብ  ኢትዮጵያ  የአማራ  ዘር ጨርሶ  እንዲጠፋ  ተዘምቶበት  ነበር።  የአማራን  ዘር  ጭካኔ  በተሞላበት
    መንገድ  ከተበቀሉት  በኋላም  ጽዋው ወደ  አኙዋክ ­  ጋምቤላ  ሄደ  ፣  ከአኙዋክ ጭፍጨፋ  በኋላ  ደግሞ  ዘመቻው  በኦሮሞ
    ወገናችን ላይ ቀጠለ። በወላይታ ተከተለ፣  በኦጋዴን... ተዛመተ። የብሄር መብት እስከመገንጠልን ያስከበረው ህገ­መንግስት
    ጸድቆ በወረቀት ላይ ተቀምጧል። ይህንን መብት እየጠየቁ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ግን በዘራቸው ብቻ እየተመረጡ
    ማጥፋቱ ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።
      እነ መለስ እነ በረከት ለዘመናት ተዋልዶና አብሮ ሲኖር የነበረን ህዝብ እንደ እንግሊዝ ከፋፍለህ ግዛው ቅኝ ስርዓት
    ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ህዝቡን እርስበርስ እያጋጩት ላለፉት 20 አመታት ለመቆየት ችለዋል። የዘር ፖለቲካው ምስጢር
    ይኸው ነው። ይህንን ባያደርጉ ኖሮ እስካሁን እንደ ጉም ተበትነው በጠፉ ነበር።    ወደመቀሌው በዓል እንመለስ።  
      ብሄር ብሄረሰቦቹ በመቀሌ ከተማ በቡድን በቡድን እየዘፈኑና እየጨፈሩ ይጓዛሉ። በተለይ ከደቡብ የመጡት ብሄር
    ብሄረሰቦች  መብታቸው  ተከብሮላቸው  ወደ  እድገት  ጎዳና  ከተጓዙ  ከሃያ  አመት  በኋላም  ­  ጥንታዊው  የጋርዮሽ  ስርዓት
    ከሚመስለው አለባበሳቸው እንኳን አልተቀየሩም።
      መር  ከሃያ  አመት  በፊት  ቅጠል  ለብሶ  ይጨፍራል፣  ዛሬም  ቅጠሉን  አልቀየረም።  ዳውሮ  ድሮ  ለእግሩ  ጫማ
    አያደርግም ነበር አሁንም ጫማ የለውም። ከፊቾ ከ20 አመታት በፊት ከቀንድ የተሰራ የሙዚቃ መሳርያ ነበር የሚጠቀመው፣
    አሁንም እሱኑ ይዞ ነው መቀሌ የመጣው...። ሁሉም አንዳች ለውጥ አይታይባቸውም። ታድያ የዚህ ሕዝብ ነጻነቱ፣ ለውጡ
    እና እድገቱ የቱ ላይ እንደሆነ ማን ይሆን የሚያስረዳን?
      ህገ መንግስታዊ መብቴ ይከበርልኝ ባለ ብቻ ምላሹ የጥይት እና ቦንብ የሆነ ሕዝብ ቅጠል ለብሶ መጨፈሩ ምን
    ትርጉም ይሰጠናል? ይህ  ነጻነቱን ያሳየናል እንዴ? ወይንስ ዛሬም የእግር ጫማ እንኳን አለማድረጉ እንደ ባህል ተቆጠረለት?
       ጎንደሬው ሁመራ ላይ ለማረስ ፈቃድ ከመቀሌ መጠየቁ ነው የመብቱ መከበር? ወይንስ መቀሌ ላይ ሄዶ እስክስታ
    መምታት? አፋርና ኢሳ  ­ ጉርጉራ ላይ ካላረሰ ­   አማራው ኦሮሞ ምድር ላይ እንዳይሰራ ከታገደ መብቱ ምኑ ላይ ነው?
      ተረስቶ ይሆን ይሆናል እንጂ "የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?...” ብለው ነበር አቶ መለስ። ታዲያ ዛሬ
    ምን አዲስ ነገር ተገኘ?  በመቀሌ እየተደረገ ያለው የወላይታ ጭፈራስ ለአድዋው ምኑ ሊሆን ነው?  
    ‘የኢትዮጵያ  ጥንታዊ  ስልጣኔ  አንተን  አይመለከትህም’  ተብሎ  የነበረ  የወላይታ  ህዝብ  ዛሬ  የመለስን  ፎቶ  እና
    'ለልማት የተጋ ብቸኛው መሪ' የሚል መፈክር ይዞ በመቀሌ እንዲሰለፍ ተደርጓል።
      ደቡቡ የየራሱን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እርግፍ አድርጎ ትቶ ኢህአዴግ በፈጠረለት 'ወጋ ጎዳ' እንዲናገር አቶ መለስ፡
    ሲያስገድዱት  እነሱ  ግን  ልጆቻቸውን  በአለም  አቀፍ  ቋንቋ  ብቻ  እንዲማሩ  ነው  ያደረጉዋቸው።  ዛሬ  አቶ  መለስ  የነዚህን
    ጎሳዎች መብት መከበር ነው በመቀሌ እያበሰሩ ያሉት።
      ይህ ህዝብ እንዲሁ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች  እየተባለ ሲቀለድበት እንደዋዛ ሃያ አመታት አለፉ።
      በኢህአዴግ ዘመን ተወልዳ፣  ተምራ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀች ወጣት አንድ አፍሪካ ሃገር አግኝቼ አወራኋት።  ሜሮን
    ትባላለች።  ስለ  ብሄር  ብሄረሰቦች  እና  ህዝቦች  መብት  እና  ነጻነት  ልትነግረኝ  ሞከረች።  ዩኒቨርሲቲ  የሚያስገባ  ውጤት
    ሳይኖራት ይልቁንም ኢህአዴግ በሰጣት እድል ዩኒቨርሲቲ ገብታ እንደተማረች ስለተነገራት የመለስ ዜናዊ አድናቂ ናት።
      በወሬያችን መሃል  በድንገት ‘ብሄር ብሄረሰቦች  እና  ህዝቦች ማለት ምን ማለት  ነው?’ ብዬ ጠየቅኳት።  ጥያቄዬ
    ዱብዳ  ነገር  ሆነባት።  ለሚለኒየም  ግብ  ሲባል  ከተከፈቱት  ዩኒቨርሲቲዎች  ለስታስቲክስ  ማሟያ  የተመረቀች  ስለመሆንዋ
    አመለካከትዋ፣  አስተሳሰብዋ እና ንግግርዋ ይገልጸዋል።    ጥያቄዬን ለመመለስ እንደከበዳት ተረዳሁ። ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚለውን ቃል የሜሮን ትውልድ ለሃያ
    አመታት  ያለማቋረጥ  ሲሰማው  የነበረው  ጉዳይ  ነው።  ለዚህ  ትውልድ  የብሄር  መብት  ማለት  ግን  በየአመቱ  በጎዳና  ላይ
    ከሚደረግ ጭፈራ ውጭ የሚሰጠው ሌላ ትርጉም ያለ አይመስለኝም።
      ማን  ነው ብሄር?  ብሄረሰሰቦችስ  የትኞቹ ናቸው?  ህዝቦች  የሚባሉትስ?  ለዚህ ጥያቄ  እንኳንና ሜሮን ­ ወያኔም
    መልሱ እንደሚቸግረው ይገባኛል።
      ሜሮን ግን ኮስተር ብላ "ህገ መንግስቱ ነዋ!" አለችኝ።
      ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ወጣት ቀርቶ ከአንደኛ ደረጃ ተማሪ እንኳን የማልጠብቀውን መልስ በማግኘቴ ባዝንም ­
    በመልስዋ ግን ትንሽ ፈገግ ማለቴ አልቀረም።  
      ከአፍታ ቆይታ በኋላ ­ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ራሱ መለስ ዜናዊ ይመስለኛል ስትል ቀለደች ሜሮን።
      እዚህ ላይ ልብ  በሉ! ‘የህዳሴው  ግድብ’  ሽልማት  ስነ  ስርዓት  እየተደረገ  በነበረበት  ግዜ  የግድቡ "ወደር  የሌለው
    ተሸላሚ"ን ሰራዊት ፍቅሬ በቴሌቭዥን ሲያስተዋውቅ የሆነው ነገር ታወስውኝ።  ነገሩ ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰው እንግዳ
    ነበር።
      ሰራዊት  እና ሙሉአለም  እየተቀባበሉ ­  እየደጋገሙም 'የህዳሴው ግድብ ወደር  የሌለው ተሸላሚ' ይላሉ።  ከብዙ
    ደቀቃ በኋላም የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ ይፋ ሆነ።
    "ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች!" ሲል ሰራዊት ፍቅሬ በሚለኒየም አዳራሽ ለተሰበሰበው ህዝብ አበሰረ።
      ሸልማቱን  የሚሰጠው  አቶ መለስ ዜናዊ  ፣ ሽልማቱን  የሚቀበለው  የኢህዴግ ተወካይ ሲሆን  ፣ ይህም በተዘዋዋሪ
    አቶ መለስ ዜናዊ መሆኑ ነው።
      ሜሮን ይህንን ማለትዋ ከሆነ ­ ጥያቄዬን በትክክል እንደመለሰችልኝ ተረዳሁ።
      ሽልማቱ መጣም  አልመጣ  ለብሄር ብሄረሰቦቹ  የሚፈይደው  ነገር  አይኖርም።   በየአመቱ  የሚደረገው  የጎዳና ላይ
    ጭፈራ ግን የብሄረሰቦች መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታቸውም ሆኗል ብለን እንደምድም።
      የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር! ከዛ ካለፈ ግን የህይወት ዋጋም ያስከፍላል። ኦጋዴንን ያስተውሏል?

    ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ለተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ


    አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ትንታግ የሆኑትን ወጣት ፖለቲከኞች በሽብር ወንጀል ተካፍለዋል፣ ድርጊቱን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ ህዝብን ለአመጽ ቀስቅሰዋል በሚል የፈጠራ ክስ አጎሮ ስቃይ እየፈጸመባቸው ሲሆን የካንጋሮው ፍርድ ቤት አራቱ ወጣት ፓለቲከኞችን እና በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት ሌሎች 6 ተከሳሾች ለቀረበባቸው የፈጠራ ክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አገዛዙ በወጣት ፖለቲከኞች ላይ ያቀረበውን የፈጠራ ክስ እያወገዙ መቀጠላቸው ታውቋል። ወጣት ፖለቲከኞቹን ጨምሮ በአገዛዙ የፈጠራ ክስ ሰለባ ሆነው በእስር እየተሰቃዩ የሚገኙትን የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አገዛዙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የበይነ መረብ ዘመቻ መከፈቱም የታወቀ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ዘመቻውን በመደገፍ ፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉንም የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ አበክረው እየጠየቁ እንደሚገኙ ዘጋቢያች አመልክቷል።
    በሌላ ዜና የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ እያደረሰባቸው ያለው ወከባ፤ አፈናና እስር ትግሉ እንደማይቆም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አስታወቀ። “ነጻነታችን በእጃችን” ነው የሚለው ትብብሩ፣ ፋሺስታዊው አገዛዝ እየወሰዳቸው ባሉት እርምጃዎች ፈጽሞ ወደኋላ እንደማይል በማሳሰብ እቅዱን በህጋዊ መንገድ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።
    በመጨረሻም አገዛዙ ከአፈና ድርጊቱ እንዲገታና ለቀረበው ህጋዊ የዕውቅና ጥያቄ በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጥ የጠየቀው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግሉ አላማ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሆኑን በማመልከት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለቀጣዩ ትግል የሚቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲከታተሉና ከፓርቲዎች ጎን እንዲቆሙ፣ ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ፓርቲዎችም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

    ESAT Daily News Amsterdam December 01 2014 Ethiopia | ESATTUBE

    ESAT Daily News Amsterdam December 01 2014 Ethiopia | ESATTUBE

    Monday, December 1, 2014

    ለሀገር ነጻነት የወጣቱ ተሳትፎ ቀጣይነት ይኑረው!


    ከ1997 ምርጫ ማግስት ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጣቶችና በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎች ለሀገራቸው የዲሞክራሲ መብት መከበር እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ላቅ እያለ መምጣቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህን ተከትሎ ዛሬ ወጣቱ የወላጆቻችን ደምጽ ይከበር፣ ኢትዮጵያዊነት በዘረኝነት አይፈተንም! ነጻነት ዳቦ አይደለም! እስራትና ግድያ በኢትዮጵያ ይቁም! የወያኔ አገዛዝ በቃን! በሚሉ በበርካታ ወጣቶች ጩኸት የወያኔ ሹማምንትና አገልጋዮቹ ላይ የፈጠረው ድንጋጤ ወጣቱን ሽብርተኛ አስደርጎታል።
    ወጣቶች ህዝብን አስተባብረው ለተቃውሞ በማሳደም የወያኔን ዘረኝነት በመቃወም ረገድ የተለያዩ ዘዴዎችን ከሌሎች የነጻነት አቢዎት እንቅስቃሴ በመማር እምቢተኝነትን በማሳየት ጅማሮ ላይ ናቸው። ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ የተጀመረው የእምቢተኝነት ዘመቻ በሚቀጥለው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ይቀጣጠል ዘንድ ወጣቱ ሃላፊነት አለበት። ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው መራራ ትግል ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል። አባቶቻችን የውጪ ሀገራትን ወራሪዎች ወራራ ለመመከት ሁሉም ሰው የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ያደረጉት ጥሪ አሁንም ላይ ይሰራል።
    ለራሳችን ክብር፣ አንድነት፣ ለሀገር ነጻነትና ህልውና መከበር ኢትዮጵያዊ እምቢተኝነት የሚጀምረው ከትንሽ ነው። ህወሃት በጠላትነት የፈረጃችሁ የዛሬ ወጣቶች የሆናችሁ ዘመን በሚፈቅድላችሁ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በመላው ሀገሪቱ ወረቀት ከመበትን አንስቶ ሌሎች ይትግል ስልቶችን ተጠቀሙ። ኢትዮጵያ ሀገራችሁ በአንድ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መዳፍ ውስጥ ማልቀስ ከጀመረች ሰነባብታለች። ዜጎቿ የግለሰብም ሆነ የቡድን መብታቸው ተረግጦ በባርነት እየተገዙ ነው። ጉልበታቸውና ሀብታቸው እየተመዘበረ ሲሆን፤ ለነጻነት፣ ለዲምክራሲና ለፍትህ የጮኹ ሁሉ ሽብርተኛ ተብለው ወደ ማጎሪያ እየተወረወሩ ነው።
    ስለዚህ ስለ ሀገራችን፣ ስለራሳችን የግልም ሆነ የቡድን ጥቅም ስንል በሀገሪቱ የትኛውም ከፍል የተጀመረውን የእምቢ አልገዛም ባይነት እንቅስቃሴ እንደግፍ፣ እንሳተፍ! በባህርዳር የተጀመረውን የወጣቶች እንቅስቃሴን አድንቀን ይህ ተነሳሽነት በሌላውም የሀገሪቱ ክፍል መቀጠል ያለበት ነው።
    ይህን በማድረግ ወደ ትግሉ በመቀላቀል ካልተሳተፍን በስተቀር ትግላችን አንድ እርምጃ ወደፊት ፈቀቅ ማድረግ እንደማንችል ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም ሁሉም አካላት በያለበት በየሚኖርበት፣ በሚችለው አቅሙ ሁሉ ወደትግሉ በንቃት ተሳተፍ! አብረን ታግለን ነጻነታችንን እናረጋግጥ! ለኢትዮጵያ ትንሳኤ፣ የነጻነት አዋጆች ነጋሪ፣ አብሳሪ ትውልዶች እንሆን ዘንድ ሳንታክት እንታገል ዘንድ ወቅቱ የሚጠይቀው ጥሪ ነው።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

    የትግሬ ወያኔዎች በ ሶስት ወይ በ ምንናምን ይከፈላሉ ( ሄኖክ የሺጥላ )


    የትግሬ ወያኔዎች በ ሶስት ወይ በ ምንናምን ይከፈላሉ ( ሄኖክ የሺጥላ )

    የትግሬ ወያኔዎች በ ሶስት ወይ በ ምንናምን  ይከፈላሉ ( ሄኖክ የሺጥላ )

    Nov 30, 2014
    1.  የመጀመሪያዎቹ መጻኢው የ ወያኔ ህውሃት ዕጣ ፈንታ በደንብ የገባቸው እና ሰላም ምናምን በሚል የእርግብ ስዕል  የፈስ ቡክ ገጾቻቸው የተንቆጠቆጠ  ፣ ትንሽ ግዜ ስጡን እንጂ ስልጣን እንለቃለን የሚሉ ፣ በልባቸው ግን መሰሪዎች እና አደገኛ ሰላዮች ናቸው ። ይሄኛው ቡድን የተቃዋሚ  ቤተክርስቲያን ሄደው ይሳለማሉ ፣ የወያኔ ደጋፊ መሆናቸውን በፍጹም አታውቅባቸውም ፣ እንደውም አንዳንዴ ካንተ ጋ አብረው ስርዓቱን ይሰድቡታል ፣ ግን በጣም ተራ በሆኑ ነገሮች ላይ ነው ተቃውሞ-አቸውን የሚያቀርቡት ፣ ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ጥያቄ ስታነሳ ሰላም ይሻላል ፣ እኛ አንድ ሕዝብ ነን ይሉሃል ፣ በጣም ሙልጭልጭ ናቸው ፣ ከተቃዋሚ ጎራ ገብተው የፈለጉትን ነገር የማድረግ ብቃት አላቸው ። የማህበረ -ሰቡ የ’ለት ተለት ኑሮ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው ፣ ለቅሶ ላይ ከንፈር መጣጮች ናቸው ፣ በችግርህ ጊዜም ይደርሱልሃል ። ባጠቃላይ በደልህ ላይ የተዛባ አመለካከት እንድትይዝ የሚያረጉህ እነዚህ የወያኔ ክንፎች ናቸው ። ስለ ሰላም ሲያወሩ ” አፌ ቁርጥ ይበል !” የምትልላቸው ናቸው ፣ በጣም ዘመናዊ ናቸው ፣ አንተን ማለስለስ ሁነኛ ስራቸው ነው ። እነዚህ ሰዎች ስለ አባይ ቦንድ ጠቀሜታ ሲነግሩህ ላገር በመቆርቆር ስሜት ነው ስለዚህ በፍጹም ልታውቃቸው አትችልም ። ያም ሆኖ ማን ተቃዋሚ ነው ማን አይደለም የሚለውን ሪፖርትም የሚያቀርቡት እነዚህ ናቸው ። ምክንያቱም ካንተ ጋ ነው የሚውሉት ፣ ሃገራዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ በጣም የጠለቀ እውቀት አላቸው ( ለምሳሌ የእግር ኩዋስ እና የመሳሰሉት ነገሮች ላይ ማተኮር ይወዳሉ አንተም ወደዚያ እንድትመለከት ይገፋፉሃል )።  በጣም የተካኑ አስወጊዎች ናቸው ። በነሱ ላይ ቀወሜታ ( ተቃውሞ ) ያለው ሰው ሲነሳ በፊት ለፊት ሳይሆን በጀርባ ነው ስም የሚያጠፉት ። ” አንተ ሰሞኑን ይሄ ሄኖክ የጻፈው ጽሑፍ አይተከዋል ፣ ምን ማለቱ ነው ?  እኛ ኢትዮጵያውያኖች በዘር በጎሳ ሳንለያይ አንድ ሆነን የኖርን ነን ”  ምናምን የሚል አስተያየት በእጅ አዙር ጫር አድርገው ያልፋሉ ፣ ቁ ነገሩ  ያለው ሴረኝነታቸው ላይ ነው ። እነዚህ ሊገሉህ እያሰቡም ይወልዱልሃል ። ስለ ትግሬ ወያኔንት ስትጽፅፍ ፣ ወያኔ ዘረኛ ነው እኛ እንደነሱ መሆን የለብንም ይልሁሃል ። ማታ ስምህን የሚሰጡት ግን እነሱ ናቸው ።
    2) ሁለተኞቹ በስርዓቱ ዘመን የተፈጠሩ ወጣት አጉራ ዘለሎች ናቸው ። በምዕራቡ ስልጣኔ የጀዘቡ ፣ ብዮንሴንና ክሪስ ታከርን መሆን የሚፈልጉ ፣  ቤተሰቦቻቸው ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በሰበሰቡት ገንዘብ በድሎት ያደጉ ፣ ምንም እንዳያውቁ ተደርገው ያደጉ ድፍን ወጣቶች ናቸው ። እነዚህ ስድብ እንኩዋ ስርዓት እንዳለው አያውቁም ፣ ” አንተ ሸርሙጣ ” የሚል አባት ስለሆነ ያሳደጋቸው ከሱ የተሻላ ለመሆን የሚችሉትን ነገር ሁሉ ይሉሃል ፣ ከወጣቶች ጋ ተቀላቅሎ መኖር ይችላሉ ፣ ግን ውስጣቸው ባዶ ትልቅነት አለ ። ልቆች ናቸው ፣ የፈለጉትን ስም ይሰጡሃል ፣ የፈለጉት ሴት ላይ ይወጣሉ ፣ የፈለጉትን ይሳደባሉ ፣ ባጠቅላይ ፍቃድ የተሰጣቸው ቦዘኔዎች ናቸው ። ጡረታ ሲወጡ ማረፊያ አገራቸው  አማሪካ ወይም መሰል ሀገሮች ናቸው ። በፍጹም ልባቸው ጀግኖች ነን ብለው ያምናሉ ። የኢትዮጵያ ታሪክ ከትግሬ ወያኔ የሚጀምር እንደሆነ ነው የሚያውቁት ።  እነዚህን ስታሸንፋቸው ለመቀየር ብዙ አያስቸግሩም ባይ ነኝ ።
    3) ሶስተኞቹ አስኩዋል የምላቸው ናቸው ። ሁሉን ነገር ፊት ለፊት ነው የሚያደርጉት ፣ እብሪትን  ፣ ጥላቻን ፣  መሰሪነትን ባንድ ላይ የያዙ ናቸው ። አማራ መጥፋት አለበት ብለው ያምናሉ ፣ እሱም ብቻ ሳይሆን አማራ ሲጠፋ ከተቻለ ከኦሮሞ ጋ ቢጠፋ የሚል ሕልም አላቸው ። ጨካኞች ናቸው ። ለነዚህ የጠላት ትንሽ የለውም ። በደረግ ዘመን የሆነውን እንደ ጥርስ መንከሻ ይጠቀሙበታል ፣ ስለዚህ ከደርግ ጋ ምንም ዝምድና የሌለው ህጻን ሲገሉ የበደላቸው ማስታገሻ እንጂ ስህተት መስሎ አይታያቸውም ። የ 17 ዓመት ትግሉ በኢትዮጵያ ላይ የማዘዝ መብት እንደሰጣቸው አድርገው ይናገራሉ ፣ በምርጫ ስትላቸው ” እኛ በእሳት ሰንሰለት ጀርባችንን ገርፈን ነው እዚ የደረስነው አንተ በእስክርብቶ ልትወስድ አማረህ ወይ ይሉሃል ” ጥፋትን ፊት ለፊት ነው የሚፈጽሙት ፣ ለማንም አይራሩም ፣ ብዙ መቶ ሺ ህጻናቶችን ፈጅተዋል ፣ በ ወንጀሎቻቸው ሁሉ ደስተኞች ናቸው ፣ የበቀል ሰዎች ናቸው ፣ ምንም ያህል ብትወዳቸው አማራ ከሆንክ መጥፋት አለብህ የሚል አቁዋም አላቸው ። ይሄንን ስትናገር እናሱ አያስተባብሉም ፣ የሚያስተባብሉት ከላይ ቁጥር አንድ ላይ የተገለጹት ሲሆኑ የሚሳደቡት ደሙ ቁጥር ሁለት ላይ የተገለጹት ናቸው ። የነዚህ ሥራ ጠላት የመሰላቸውን ሁሉ እያደኑ ማጥፋት ነው ። የቁጥር 1 እና ሁለት ህልውናቸው  በነዚህ ሰዎች ላይ ነው ያለው ፣ ስለዚህ ያመልኩዋቸዋል ።
     ጥላቻቸውን  ባገኙት አጋጣሚ ያሳዩሃል ፣ ሰርግ ላይ ትግረኛ ዘፈን እስኪመጣ ( እስኪዘፈን ) ሌላውን ቁጭ ብለው ነው የሚመለከቱት ፣ ትግረኛ ሲሆን እንደ ሎጥ  ዘመን ሰዎች በ አይናቸው ነው ተነጋግረው  ነው መዝለል የሚጀምሩት ፣ በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ ጥላቻ ያስተምሩሃል ፣ ነገ መገንጠል ለሚፈልጉዋት ትግራይ የዛሬ የ ስነ ልቦናዊ የቤት ሥራ መሆኑ ነው ፣ ያሳዝኑኛል ፣ ስለዚህ ብዙ ከመጎዳታቸው በፊት መጥፋት አለባቸው ብዬ አምናለሁ ፣ ባጭሩ  ዶ/ር ጥላሁን ባንድ ወቅት እንዳለው “የኢትዮጵያዊነት ነቀርሳዎች ናቸው !”
    ትግሬ ስላልሆኑ ወያኔዎች ሰሞኑን እጽፋለሁ ( በጣም ብጠየፋቸውም ቅሉ !)

      ተመስገን ደሳለኝን ተቀበልኩት (ሕገ-መንግስት ሆይ የት ነው ያለኸው?)


      ከክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ (አበበ ቀስቶ)
      ከዝዋይ ወህኒ ቤት
      ቀኑ ቅዳሜ በመሆኑ ቤተሰቦቻችን እኛን ለመጠየቅ /ፈርዶባቸው የለ/ ወደ ዝዋይ ወህኒ
      ቤት የሚመጡበት ሰዓት ደርሶ፣ ተጠርተን እንደወጣን፣ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ የጠየቅናቸው
      ነገር ቢኖር፣ ምን አዲስ ነገር አለ የሚለውን የተለምዶ ጥያቄያችንን ነበር፡፡
      በዕለቱም የመጣልን የምስራች ልበለው ዜና አሊያም መርዶ ጋዜጠኛ ተመስገን ሦስት
      (3) ዓመት ተፈረደበት የሚል ነበር፡፡ በዜናው አልተደነቅንም፤ አልተገረምንም፤ ምክንያቱም
      በሥልጣን ላይ ያለው የህወሓት /ኢህአዴግ/ አምባገነን መንግስት፣ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ሌላ ሊሸልመው
      የሚችለው መልካም ሽልማት /ሜዳሊያ/ የለውምና፡፡ በነገራችን ላይ ዜናው ለኔ ፍጹም አልገረመኝም፤ እገረም የነበረው
      አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ተመስገንን በነጻ ቢለቀው ነበር፡፡
      የሆነው ሆኖ፣ ከቤተሰብ ጥየቃ ተመልሰን ገና ምሳ በልተን አረፍ እንዳልን ግን፣ የሰማነውን ዜና እውነታ በአካል
      የሚያረጋግጥልን አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ፍራሹን ተሸክሞ እኛ አለንበት ጭለማ ቤት /የቅጣት ቤት/ ድረስ
      መጣ፡፡ ዓይኔን ማመን እስቲያቅተኝ ድረስ ተጠራጠርኩ፤ ግን ሆነ፡፡ ተመስገን መጣ፡፡ እናም ውለን ሳናድር ተመስገን
      ደሳለኝን ተቀበልኩት! እነሆ ተመስገን ዝዋይ ከመጣ ዛሬ 15 ቀን ሆነው! ... ሕገ-መንግስት ሆይ የት ነው ያለሽው!?
      ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዳሉ፤ እግረ መንገዴን እስቲ አንድ ገጠመኜን ደሞ ላጫውታችሁ፡፡ ህወሓት
      /ኢህአዴግ/ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በሁኔታው ያልተደሰትን ጓደኛማቾች ተሰባሰበን፣ ከኛ ቀድመው ከብላቴ
      ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ወደ ኬንያ የተሰደዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችንና ሌሎች ወገኖቻችን ተቀላቅለን ለመታገል
      በመወሰናችን ተሰባስበን፡፡ ወደ ኬንያ የስደት ጉዞ ጀመርን፡፡ ይህ የሆነው ግንቦት 23 ቀን 1983 ዓ.ም ከሃያ ሦስት ዓመት
      በፊት ነው፡፡
      ታዲያ በዚህ ጉዟችን በአጋጣሚ አገረማርያም ከተማ የማረፍ ዕድል ገጥሞን ነበር፡፡ እዚያም አቶ አብርሃም ያየህና
      ጓድ ጌታቸው ሮበሌ (የአኢወማ ሊቀመንበር የነበሩ) ወደ ኬንያ ለመሸሽ በዚህ ሲያልፉ ተይዘው ያቤሎ ከተማ ፖሊስ
      ጣቢያ ታስረዋልና እባካችሁ ያቤሎ ከተማ ጐራ ብላችሁ አስፈትታችሁ ይዛችኋቸው ሂዱ የሚል የወገን ጥቆማ ደረሰን፡፡
      እኛም ይህን ጥቆማ ተቀብለን በሰማነው ዜናም ተደናግጠን ጉዟችንን ወደ ሞያሌ በማድረግ፣ ከምሽቱ 3፡30
      ሰዓት ላይ ያቤሎ ከተማ ደርስን፡፡ በወቅቱ ህዝቡ በነበረው /በተከሰተው/ ሁኔታ እጅግ ተቆጥቶ ከተማዋን ከዘራፊና
      ከዝርፊያ ለመጠበቅ በሚል ተደራጅቶ በየተራ ከተማውን ይጠብቅ ስለነበር መኪናችንን አስቁመው ከመሸ ከተማ መግባት
      እንደማንችል በትህትና አስረድተውን፣ ከከተማው ወጣ ብለን በማደር፣ ማለዳ መግባት እንደምንችል ነግረውን፣
      ተስማምተን ከከተማው ወጣ ብለን አደርንና ጠዋት ማለዳ ላይ ወደ ያቤሎ ከተማ ገባን፡፡
      ወዲያውም ወደ ያቤሎ ፖሊስ ጣቢያ ሄድን፤ የታሰሩትን አቶ አብርሃም ያየህና ጓድ ጌታቸው ሮበሌን እንዲፈቱና
      እኛ ጋር ወደ ኬንያ እንዲሄዱ እንፈልጋለን ስንል በወቅቱ ለነበሩ የፖሊስ አባላት ጥያቄ አቀረብን፡፡ ፖሊሶቹም ፍጹም
      ትህትና በተሞላበት ሁኔታ ተቀብለውን ካነጋገሩን በኋላ፣ ሁለቱ ሰዎችና ሌሎች አባሪዎቻቸው ትናንትና ተፈተው ወደ
      ሞያሌ ሔደዋል አሉን፡፡ እኛም ለፈጸሙት መልካም ተግባር አመሰግነን፣ ጉዟችንን ወደ ሞያሌ ቀጠልን፡፡
      ልብ አድርጉ! ... ያኔ በዚያ በ20ዎቹ የመጀመሪያ እድሜ ላይ የነበርን ወጣቶች የታሰሩ ወገኖቻችን ካልተፈቱ
      በሚል ነበረ ስንቆጣ የነበረውም፣ የጮህነውም፤ ዛሬ በጉልምስና እድሜያችን ግን በግፍ በወህኒ ቤት ተወርውረን ምንም
      ማድረግ ባንችል፣ ልክ እንደኛ የግፍ ሰለባ የሆነውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ተቀበልነው፡፡ ከነዚያ አገራቸውን
       ተመስገን ደሳለኝከውድቀት ለማዳን ሲሉ ብላቴ ከዘመቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ አሁን ከኔ ጋር ባንድ ቤት ሆነው በእስር
      እየማቀቁ ነው፡፡
      ልብ በሉ! ... ተመስገን ደሳለኝን የተቀበልነው ቤተመንግስት አይደለም፤ ሸራተን ወይም ሒልተን ባለአምስት
      ኮከብ ሆቴል አይደለም፡፡ ካምቦሎጆ አይደለም፡፡ ከ23 ዓመታት በኋላ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳናሳይ፣ ያችን እንኳ በዚያች
      ዕድሜያችን ያሳየናትን የፍቱልን ጥያቄ ማቅረብና እምቧ-ከረዩ ማለት አቅቶን፤ የነጻነት፣ የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የእኩልነት
      ጥያቄያችን ባለመመለሱም የተነሳ፣ እድለ ቢስ ሆነን ነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የተቀበልነው፤ በዝዋይ ወህኒ ቤት
      በሚገኝ 9ኛ ቤት በሚባል ጭለማ ቤት /የቅጣት ቤት/ ውስጥ ሆነን ነው፡፡ እረ ጐበዝ አንድ በሉ!... ይህ ነገር ማቆሚያው
      የትና መቼ ነው?...
      ተመስገን ደሳለኝ በአካል ወደኛ የመጣው ቅዳሜ በ22/02/2007 ዓ.ም ይሁን እንጂ፣ በተደጋጋሚ “ያልተገሩ
      ብዕሮችና!” ሌሎች የኢቲቪ ዶክመንመተሪ ፊልሞች፣ እንዲሁም በኢቲቪ የሚዲያ ዳሰሳ ፕሮግራሞች አማካኝነት
      ሳይወሰንበት በፊት በሀሳብ ከኛ ጋር ተቀላቅሎ ነበር፡፡
      እኛም ከነዚህ ዘገባዎች በመነሳት፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዕጣ-ፈንታ የተለመደው የግፍ እስራት ሊሆን
      እንደሚችል ከህወሓት /ኢህአዴግ/ ባህሪ የተነሳ፣ መገመት ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ አምነን ነበር፡፡ የሆነውም ደግሞ
      ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም በአፍሪካ ውስጥ፣ በተለይም በእኛይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት፣
      እንዲሁም ለሰው ልጆች የመናገርና የመጻፍ ነጻነት የሚታገል ታጋይ ሁሉ፣ ዕጣ- ፈንታው እስራት፣ ግርፋት፣ ስደት እና ሞት
      ብቻ ነው፡፡ ተሜም የመረጠው ለነጻነት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ እየታገለ የሚመጣውን መከራ መቀበልና
      የሚከፈለውንም ዋጋ መክፈል ብቻ ነው፡፡ “የፈራ ይመለስ!” አይደል ያለው፡፡ ቃሉንም በተግባር አደረገው፡፡ ብራቮ ተሜ!!!
      ተመስገን ፍራሹን ተሸክሞ እኛ ወዳለንበት ጭለማ ቤት /ቅጣት ቤት/ ሲመጣ፣ መጀመሪያ የያሁት እኔ ነበርኩ!...
      በቀጥታ ተንደርድሬ ተመስገንን ተቀበልኩት፡፡ ሌላ ምንም ምርጫ የለኝም፡፡ እሱም ቢሆን እኔንና ጓደኞቼን ሲያይ፣ ለቤቷ
      እንግድነት አልተሰማውም፡፡ ከዚያማ ምን ልበላችሁ፣ የተራብነውን መረጃ አንድ ባንድ አብራራልን፤ ዘረገፈልን ማለት
      ይቀላል፡፡
      ለኔ እንደ ምግብ ዝርዝር (ሜኑ) የተሰናዳ - ዝርዝር መረጃ ሳገኝ፣ በ3 ዓመቱ የእስራት ዘመኔ የመጀመሪያዬ
      በመሆኑ ተደስቻለሁ፡፡ እንደውም የተሰማኝ እርካታ ቃላት ሊገልጸው ከሚችለው በላይ ነው፡፡ በ21ኛው ክ/ዘመን መረጃ
      የተራብነውና የተቸገርነው የኢህአዴግ መንግስት ባለንበት እስር ቤት ከኢቲቪ ውጭ ማየትና ማድመጥ ስለከለከልንና
      ስላፈነን ነው፡፡
      ሰው መቼም ወደ እስር ቤት ይምጣ ባይባልም እንኳ፣ በተለይም ለወዳጅ ይህን ባይመኙለትም፣ እንደ ተመስገን
      ያለ አንጀት አርስ የመረጃ ሰው ለአንድ- አንድ ቀን ቢመጣልን የእስራት ጊዜያችንን ያጣፍጥልን ነበር፡፡ ግን! ... ለምን? ...
      ለምን?... ለምን ይምጣ!?
      ለትኩስ መረጃ ካለኝ ጉጉት አንጻር ይህንን ብልም እንኳ፣ የተመስገን ደሳለኝ መታሰር ለእኔ ፍጹም- ፍጹም
      ተገቢም አስፈላጊም አይደለም፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በውሳኔያቸው በፍጹም ተሳስተዋል፡፡ ኢህአዴጎች ሆይ!...
      ተመስገንን እንዲታሰር በመወሰናችሁ በዲሞክራሲ ላይ እጅግ ተሳልቃችኋል!... ድሮም የሌላችሁን የመንግስትነት ግርማ
      ሞገስ በድጋሚ አጥታችሁታል፡፡ የራሳችሁ ሕገ-መንግስት በአንቀጽ 29 ላይ የሚደነግገውን ድንጋጌ በመጣስ ለሕገ-
      መንግስታችሁ ክብር አሳጥታችሁታል … ኢህአዴግ ሆይ ሕገ-መንግስትህ ወዴት ነው ያለው፤ ፈልገህ ካገኘኸው ላክልኝ! ...
      እናም ወገኖቼ! በተመስገን ደሳለኝ ላይ የተጣለውን የግፍ ውሳኔ አጥብቄ እቃወማለሁ! … ደግሜ- ደጋግሜ አወግዛለሁ!››
      ከ5 ዓመት በፊት በወጣ አንድ “አዲስ ራዕይ!” በሚባል የኢህአዴግ መጽሔት ስለመተካካት በሚያወራው ጽሑፉ
      ላይ “በአሁኑ ሰዓት ያለው መተካካት፣ የሰው መተካካት እንጂ፣ የፓርቲ መተካካት አይደለም፤ በአሁኑ ሰዓት የፓርቲ
      መተካካት አይኖርም፡፡ እንደ ኢህአዴግ አስተሳሰብ የፓርቲ መተካካት ሊኖር የሚችለው ከ3 እና ከ4 ምርጫዎች በኋላ
      ነው፡፡ እስከዚያ ድረስ ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ ያለማቋረጥ መቀጠል አለበት›› ይላል፡፡ ካልተሳሳትኩ ይህንን ያነበብኩት
      ከ2002 ምርጫ በፊት ይመስለኛል፡፡ ታዲያ ይህንን የኢህአዴግ አቋምና ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል፣ ለሂደቱ እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው
      የተጠረጠሩና የተገመቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያን (ብሎገሮች) ሁሉ በሰበብ-በአስባቡ
      ተሰብስበው ወደ ወህኒ ቤት ይወረወራሉ፡፡ አገር ጥለው እንዲሰደዱ ይገፋሉ፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ ላቀደውና ላስበው
      ረዥም የሥልጣን ዘመን እድሜ እንቅፋት ናቸውና፡፡ እናም ተመስገን ደሳለኝ የዚህ የኢህአዴግ እቅድ ቀንደኛ ተቃዋሚ
      ተደርጎ ስለሚወስድና ቢገፉት… ቢገፉት ከሀገር አልሰደድ ስላለ፣ በግፍ ወህኒ ቤት እንዲገባና እንዲማቅቅ ተፈረደበት፡፡
      አለቀ በቃ! እውነታውና ሃቁ ይህ ነው፡፡
      ከላይ በገለጽኩት ጉደኛ የኢህአዴግ መጽሔት ላይ “አንድ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የጡረታ
      መውጫ እድሜ 65 ዓመት ነው” ይላል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች 65 ዓመት እስቲሞላቸው ድረስ መጓዝ የፈለጉትና ለመጓዝ
      የወሰኑት የዲሞክራሲን መርሆዎች በመጣስና በመጨፍለቅ ነው፡፡ ዕድሜያቸው 65 እስቲሞላ ድረስም፣ እንደ ጋዜጠኛ
      ተመስገን ደሳለኝ አይነት ቆራጥና የማይንበረከክ ጋዜጠኛ እጣ ፈንታው የግፍ እስራት ነው፡፡ ምክንያቱም
      አልተንበረከክምና፡፡ የቆመበትን የጋዜጠኝነት መርህ ለኢህአዴግ በሚመች መልኩ አልሸጥምና፡፡ እንደውም ከዚህ
      ከኢህአዴግ ፍላጎት በተቃራኒው “ጉዞዬን እስከቀራኒዮ ያደረገው!” በሚል ተፋልሟቸዋልና “እምቢ አልንበረከክም!” ብላ
      ዘማሪ አዜብ ኃይሉ እንደዘመረችውም ተመስገንም እምቢ አልንበረከክም እያለ የመከራን ጽዋ በመጎንጨት፣ መጓዝን
      መርጧል፡፡ ብራቮ ተሜ…በርታ!...በርታ!
      እኔ ግን በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን እጅግ አድርጌ ለአገሬና ላልታደለው ህዝቧ አዘንኩ! ... አፈርኩ! ... ምክንያቱም
      በዚህ ሥልጣኔ ባበበበት ዓለም፣ የቀደሙትን ትተን በዚህ በ2 ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ20 በላይ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች
      አገር ለቀው ተሰደዋል፡፡ ሦስት ጋዜጠኞች እና ስድስት ጦማርያን (ብሎገሮች) ተከሰው ፍ/ቤት እየተመላለሱ ነው፡፡
      ቀደም ሲል፣ የግፍ ፍርድ የተጣለባቸው እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙን
      የመሳሰሉት ጋዜጠኞችን በወህኒ ቤት መማቀቅ ከጀመሩ 3 ዓመት አልፏቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ አነሰ ብሎ አምባገነኑ የኢህአዴግ
      መንግስት የተዘጋና የተቋረጠ ክስ ከመንደርደሪያ ላይ አንስቶ ቆሻሻውን በማራገፍና እንደ አዲስ በመቀስቀስ ተመስገን
      ደሳለኝን 3 ዓመት ፈረደበት፡፡ … እኔ ግን! ... እኔ ግን ይህንን የግፍ ውሳኔ አጥብቄ እቃወማለሁ! አወግዛለሁም!
      ከተሰደዱት ጋዜጠኞች መካከል፣ ቀድሞ የኢትኦጵ ጋዜጣ ባልደረባ ሆኖ የማውቀው ሚሊዮን ሹርቤ፣ በነጻነት
      እየተናገረና እየጻፈ ባገሩ መኖር አቅቶት፣ በስደት አገር መሞቱም እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ይህም ልብ ይነካል፡፡ እናንተ የነጻው
      ፕሬስ አባላት ሆይ፣ የመከራ ዘመናችሁ መቼ ያበቃል! ... ስለእናንተ ልቤ በእጅጉ ያዝናል፤ … በሀዘንም ብዛት ይደማል፡፡
      ነገር ግን ሁሌም በእናንተ እኮራለሁ፡፡ … በመልካም ተግባራችሁ ለአገራችሁና ለህዝባችሁ ስትሉ ስለምትከፍሉትና
      ስለከፈላችሁት መራር መስዋዕትነት ልባዊ አድናቆትና ክብር አለኝ!
      ኢህአዴግ ተመስገንን ለምን ፈራው?... በተመስገን የሚመራው አሳታሚ ድርጅት በተለያዩ የህትመት ውጤቶቹ
      ከፍተኛ የህትመት ኮፒዎችን በማሳተም፣ በአገራችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲያብብ ከፍተኛ አስተዋጽ
      በማድረጉ የተለያዩ የፖለቲካና የእምነት ልዩነት ያላቸውን ጹሑፎች በነጻነት በማስተናገድ ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ
      በመንቀሳቀሱ፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከሚታተሙ የፕሬስ ውጤቶች የተሻለ ተነባቢና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ አመኔታ
      በማትረፉ ጭምር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
      ይህ ኢህአዴግን ያላመመው ምን ይመመው?... በዚህ ያልተቆጣ በምን ይቆጣ?... በነገራችን ላይ የኢህአዴግን
      ከፍተኛ አመራሮች ከመጽሐፉ ቅዱስ ቃል በእጅጉ የሚገባቸው “እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ” የሚለው ቃል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ
      ቀኑ- ቀኑና ቀናተኛ መንግስት ሆኑ፤ ቀናተኛ መንግስት ደግሞ በግፍ ከማሰር፣ ከመግረፍ፣ ከመግደልና ዜጎች አገራቸውን
      ጥለው እንዲሰደዱ ከማድረግ ውጭ ስራ የላቸውምና ኢህአዴጎችም ተመስገንን በማሰር ይህንን የአምባገነንነት
      መገለጫቸው በተግባር አሳዩን፡፡
      እኔ ባለኝ መረጃ፣ ኢህአዴግ ፍትህ ጋዜጣን በህትመት ሂደት ላይ ሳለች ሲያግታት፣ ተመስገንና ጓደኞቹ፣ አዲስ
      ታይምስ መጽሔትን ይዘው ብቅ አሉ፤ አዲስ ታይምስ መጽሔት ከሕትመት ፈቃድ ውጪ ስትደረግ ደግሞ ልዕልና ጋዜጣን
      ይዘው ብቅ አሉ፤ ኢህአዴግ ይህንንም በተለመደው ስራና ጥበቡ አቋረጣቸው፡፡ ይሄኔም አይታክቴዎቹ- ተመስገንና ጓደኞቹ
      ፋክት መጽሄትን እያሳተሙ በሰፊው ህዝብ ዘንድ ተነባቢነታቸው ቀጠለ፡፡ይህን ከድፍረት የቆጠረው የኢህአዴግ መንግስት በተመስገን ደሳለኝ ላይ እየከፈተ ካቋረጣቸው 126 ክሶች
      ውስጥ፣ የሶስቱን ክሶች ቆሻሻውን አራግፎ ክስ ሊመሰርት አነሳሳው፡፡ ከዚያም አደርገው፡፡ በለመደው የግፍ ፍርዱም
      ተመስገንን 3 ዓመት ፈርደበት፡፡ በእኔ ዕምነት ተመስገን የተቀጣውና የግፍ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ ቤት የተወረወረው
      ሮጦ ባለመድከሙ፣ ብዕሩ አልነጥፍ በማለቱ፣ በአልሸነፍ ባይነቱ እና በእልኽኝነቱ የተነሳ ነው፡፡ ሌላ ምንም ጥፋት
      የለበትም፤ ሊኖርበትም አይችልም፡፡ እኔ በዚህ መልኩ ገብቶኛል! ... ወገኖቼ!... እናንተስ?
      እናም ቀናተኛው የኢህአዴግ መንግስት በተመስገን ተስፋ አለመቁረጥና ቢገፋ … ቢገፋ ከአገር አልወጣ በማለቱ
      በእጁ ካቴና (ሰንሰለት) ከቶ አስረው በቃ! ... ተመስገን የታሰረበት እውነታ ይሄ ነው! ... የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር
      የሆንክ/ሽ/ ሁሉ፣ ሕገ-መንግስት የት ነው ያለው? ... ካገኛችሁት እባካችሁ ዝዋይ ወህኒ ቤት በሚገኘው 9ኛ ቤት /ጭለማ
      ቤት/ ቅጣት ቤት ድረስ ላኩልኝ፡፡
      በመጨረሻ ተመስገን እኛ በተከሰስንበት ክስ ላይ ያለኝን ተቃውሞ አስመልክቶ “ማቆሚያና ገደብ ያጣው
      የምስኪኗ የእናቴ እንባ!” በሚል ርዕስ የፃፍኳትን የመቃወሚያ ሀሳብ ሚያዝያ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በፍትሕ ጋዜጣ አትሞ
      አውጥቷል፡፡ በዚህም ለተገፉና ለተበደሉ ድምጽ ሆኖ ሲያገለግል እንደነበር እመሰክርለታለሁ፡፡
      ይህችን ጽሑፍ በማተሙ የተነሳ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 19
      ቀን 2004 ዓ.ም አብረን ቀርበን፣ ችሎቱ ሚያዚያ 22 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተመስገንን 4 ወር እስራት ወይም
      ሁለት ሺህ (2000) ብር በግፍ ሲቀጣው፣ እኔም ወግ ደርሶኝ እንደ አቅሚቲ 8 ወር እስራት ተፈርዶብኝ እንደነበር
      አስታውሳለሁ፡፡ በአሁኑ የግፍ ቅጣት ጥፋተኛ ነው ብዬ እንደማላምን ሁሉ፣ ያኔም በተፈረደበት የግፍ ቅጣት አላምንም፡፡
      አላመንኩበትም፡፡ ይህ የሚያሳየው ነገር ቢኖር፣ የሥርዓቱ መሪዎች አፋኝነትና ግፈኝነት አለመቆሙን ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ
      የግፍ ተግባር መፈጸሙን በሥልጣን ላይ እስካለ እንደማያቆም ጭምር ነው፡፡
      ለማንኛውም የተመስገንን ጥንካሬ ልታውቁ የምትችሉት እንደ እኔና እንደ ጓደኞቹ ለአስርም፣ ለአስራ አንድ ቀንም
      አብራችሁ ስትኖሩ ነውና፣ እኔም አሁን በእስር ቤት ውስጥ ባለው ጥንካሬ ተደንቄያለሁ፤ ተገርሜያለሁ፡፡ በርታ! ተሜ …
      በርታ! ተሜም የነጻነት ቀናችን መምጣቱን በተግባር እስኪረጋገጥ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም ዕምነቴ ጽኑ ነው፡፡ ትግሉ
      ይቀጥላል!!!
      አሉዋ ኮንትኑዋ!
      ከዝዋይ ወህኒ ቤት የተላከ
      ክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ
      (አበበ ቀስቶ)