Wednesday, October 22, 2014 @ 02:10 PM Alma
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩ በጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብየበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀን ዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውንከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይል በህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘው የሽፍታ ቡድንየበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እና አረመኒያዊስብስብ እንደሆነበተደጋጋሚ ስገልጽ ቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደር ከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስትደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያ ቡድን ነው፡፡
በዚህች ትችቴ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እያራመደ ያለውን የሀገር ውስጥየዲፕሎማሲ ፖሊሲ ለመቃኘትአይደለም፡፡ ሆኖም ግን ትኩረት በማድረግ ለመዳሰስ የምሞክረውህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የተባለው የወሮበላ ስብስብቡድን በማራመድ ላይ ያለውን ዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ፖሊሲን ለመቃኘት ነው፡፡ በቅርቡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲቅጥር ግቢውስጥ አረመኒያዊ እና ግልብ መንፈስ የተጠናወተው አንድ የጦር መሳሪያ ታጥቆ ኢትዮጵያውያን/ት ሰላማዊተቃዋሚዎችን ተኩሶ ለመግደል በርካታ ጥይቶችን ሲተኩስ የነበረውን እና ለግድያሀራራው ሳይሳካለት የቀረውን የወያኔ ወኪልለመግለጽ የወሮበላ ዲፕሎማሲ እና የወሮበላዲፕሎማት የሚሉትን ቃላት እጠቀማለሁ፡፡
እንደ ሬውተርስ የዜና ወኪል አገላለጽ ‘ባለጠመንጃው ሰው’ እየተባለ ይጠራ የነበረው በአሜሪካየኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ እንደጅብራ ተገትሮ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎቻቸውንለማቅረብ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ በሄዱት በንጹሀንኢትዮጵያዊያን/ት ዜጎች ላይ ሲተኩስየነበረው በስም ሰሎሞን ታደሰ ገብረስላሴ የተባለው የወያኔ ባለሙሉ ስልጣን የደህንነትአታሼነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 29/2014 የተደረገው የሰሎሞን ገብረስላሴ አስደንጋጩ እናአሳፋሪው የእሩምታ ተኩስ ጉዳይበዓለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮበክብር እና ሞገስ ሳይሆን በቅሌት እና በውርደት፣ በጥበበኛነትእና በምሁርነት ሳይሆንበጅላጅልነት እና በደንቆሮነት፣ በታጋሽነት እና በአርቆ አስተዋይነት ሳይሆን በግልፍተኝነት እናበቅርብአሳቢነት ሲታወስ ይኖራል፡፡
እንደ ሬውተርስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ “የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ቃል አቀባይ ከቀኑበ12፡15 ሰዓት በሰሜናዊምዕራብ ዋሺንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ ተኩስ እንደተሰማ ፖሊስ በስፍራው በመገኘትተኳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ እስርቤት ልኮታል፡፡ የዓይን እማኞች እንደገለጹት ከሆነ የጥይት ተኩሱ የተከናወነውሰላማዊተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተጠጉ ጊዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነውብለዋል…“
“የወያኔን ኤምባሲ መውረር”
በሰላማዊ ተቃዋሚዎች የተወሰዱ በርካታ የቪዲዮ ክሊፖች እንደሚያስረዱት እና የኢትዮጵያሳቴላይት ቴሌቪዥን/ኢሳትአገልግሎት እንዳመለከተው በቅርቡ በኢትዮጵያ በኦጋዴን እናበጋምቤላ ክልሎች በወያኔ ገዥ አካል ታጣቂዎች በንጹሀን ዜጎችላይ የተወሰደውን አረመኒያዊጭፍጨፋ እና ግድያ በማስመልከት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘትተቃውሟቸውንለመግለጽ እና የወያኔው አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ግርማ ብሩ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ የፊት ለፊትውይይትለማድረግ በሄዱት የሰላማዊ ተቃዋሚ ቡድን ግለሰቦች ጥያቄ ማቅረብ ምክንያት ነበር፡፡
አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ ከወሰደው የቪዲዮ ክሊፕ እንደሚታየው ሰላማዊተቃዋሚዎች በመጀመሪያ ወደኤምባሲው ቅጥር ግቢ ለመግባት ሲያደርጉ የነበረውን ሁኔታ በግልጽያመለክታል፡፡ የተወሰደው የቪዲዮ ምስል የተሰባሰቡሰላማዊ ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ቅጥር ግቢበመግባት በግቢው ውስጥ ባለ መቀመጫ ቦታ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡የኤምባሲውሰራተኞች ለደህንነት ተብሎ ከታጠረው መስታወት በስተጀርባ ሆነው በመመልከት ላይ ነበሩ፡፡ሰላማዊተቃዋሚዎች አምባሳደሩን ማነጋጋር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ በርካታዎቹ ሰላማዊተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ከፍበማድረግ ጩኸት በማሰማት መፈክሮችን ያስተጋቡ ነበር፡፡ከመካከላቸው አንዱ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ይህ የወያኔ ኤምባሲእንጂ የኢትዮጵያ ኤምባሲአይደለም፡፡“ ሌላኛው ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረበ፣ “ከአቶ ግርማ ብሩ(ከወያኔው አምባሳደር) ጋር ለመነጋገር እንፈልጋለን፡፡ ከእርሳቸው ጋር ስለኦጋዴን፣ ጋምቤላ እናስለአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይመወያየት እንፈልጋለን፡፡“ ሌሎች ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ደግሞየአንዳርጋቸው ጽጌ (ከጥቂት ወራት በፊት በወያኔ ገዥ አካልከየመን ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያከተወሰዱት የግንቦት 7 የአመራር አባል) ምስል ያለበትን ቲሸርት በመልበስ እርሳቸውከእስርእንዲፈቱ ሲጠይቁ ነበር፡፡ ሌላ አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣“እስክንድር ነጋ (በዓለም አቀፍደረጃ እውቅና ያለው እና በወያኔ ገዥ አካል የ18ዓመታትእስራት ተበይኖበት በአሁኑ ጊዜ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤትበመማቀቅ ላይ የሚገኘው)ጋዜጠኛ ይፈታ“ ሌላው ማንነቱ በውል ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ጨኸትሲያሰማነበር፣ “በጎሳ ክፍፍል አገዛዝ ታመናል፣ እናም ሰልችቶናል“ በግልጽ እንዲህ የሚል ጥያቄአቅርቦ ነበር፣ “በእንደዚህ ያለ ወሮበላአገዛዝ እስከ መቸ ድረስ ነው ስንገዛ የምንኖረው? እኛታመናል፣ እናም በዘራፊዎች እና በወሮበሎች መገዛት ሰልችቶናል!“
በኢሳት የተወሰደ የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው ሁሉም ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙት ነገሮች ሁሉከኤምባሲው ቅጥር ግቢየተከናወኑ መሆናቸውን ነው፡፡ ከአራት ሰላማዊ አመጸኞች መካከልአንደኛው የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ የያዘ ሲሆን ጥቁር ልብስወደ ለበሰው እና መሳሪያወደታጠቀው ገብረስላሴ የሚባል የኤምባሲው አታሼ ሲቀርብ ያሳያል፡፡ ወዲያውኑምገብረስላሴበማነጣጠር ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አቅጣጫ መተኮስ ጀመረ፡፡ ሆኖም ግን ዒላማውን ስቷል፡፡ሰላማዊ አመጸኞችያለምንም ፍርሀት ወደ ገብረስላሴ መቅረብ ጀመሩ፡፡ ማንነቱ በውል ያልታወቀአንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ድምጹንከፍ በማድረግ በድጋሜ ጩኸቱን ማሰማትጀመረ፣ “እኛ ወንጀለኞች አይደለንም፣ ግርማ ብሩን ጥሩልን፣ ከእርሳቸው ጋርለመነጋገርእንፈልጋለን፡፡“ ሌላው ሰላማዊ ተቃዋሚ ገብረስላሴን በድፍረት እንዲህ ይለው ነበር፣ “ወደ ፊትቀጥል፡፡ ተኩስ!“በዚህን ጊዜ ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በማነጣጠር እነርሱንስሜታዊ እንዲሆኑ በመገፋፋት ወደ ኤምባሲውዋና ህንጻ በመግባት የሽሽት ሙከራ ማድረግጀመረ፡፡ በዚህ ሂደት ላይም ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመደገንበተደጋጋሚለማስፈራራት ሞከረ፡፡ በመጨረሻም ጥይቶቹን በሙሉ ተኩሶ ስለጨረሰ ሽጉጡ ጥይት አልባበመሆን የባዶ ሽጉጥድምጽ ሲያቃጭል ይሰማ ጀመር፡፡ ባለመሳሪያው እብሪተኛ ደንቆሮ ወደኤምባሲው ህንጻ ዘልቆ በመግባት አስተማማኝ ጥበቃባለበት ለእንግዶች ጊዚያዊ ማረፊያወደተዘጋጀው ወደ ሰራተኞች አካባቢ በመሸሽ ሄደ፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚወደባንዲራ መስቀያ ቦታው በመሄድ በመሀከሉ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን የወያኔን ባንዲራከተሰቀለበት በማውረድበኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ በመተካት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅልታየ፡፡ በመጨረሻም ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ወደኤምባሲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ወደጊዚያዊ ማረፊያ ቦታው በመሄድ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ መጮህጀመሩ፣”ነጻነት ነጻነት…“በማለት፡፡
ለተለያዩ ድርጅቶች የሚሰራው የምርመራ ጋዜጠኛ እና ዕውቁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተሟጋችየሆነው አበበ ገላው ከሌላ ምንጭያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣“በዩኤስ አቃቤ ሕግ በዋሺንግቶን ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊየሆነው ቢል ሚለር በገብረስላሴላይ በመግደል ሙከራ እና ታጥቆም በመገኘቱ ምክንያት ለህግ ቢቀርብ እስከ 30ዓመታትበእስራት ሊያስቀጣ የሚችል የክስ መጥሪያ ወጥቶበታል“ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ መንግስት መምሪያቃል አቀፈባይየሆኑት ጀን ፔንሳኪ የወያኔ ገዥ አካል የተኳሹን የገብረስላሴን ያለመከሰስ መብትለማንሳት እና ለህግ እንዲቀርብ ለማድረግፈቃደኛ ያለመሆኑን መግለጹን በማስመለከት እንዲህብለው ነበር፣ “ለኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኗል፣ እናም በአሁኑጊዜ የወንጀልተጠርጣሪው ግለሰብ አገር ለቅቆ ወጥቷል፡፡“
አስቀያሚውን የጫካ ትዝታ በዋሺንግተን ዲ.ሲ መተግበር?
እስከ አሁን ድረስ በዋሺንግተን ዲ.ሲ የዲፕሎማሲ ታሪክ የወያኔ “ዲፕሎማሲ” በሰላማዊ መንገድጥያቂያቸውን ባቀረቡ ዜጎችላይ መሳሪያ አውጥቶ በመተኮስ ማስተናገድ የዴሞክራሲ አባትበሆነችው አሜሪካ ውስጥ ካሉ በየትኛውም ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ በታሪክ ያልተሞከረየመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሰሎሞን ገብረስላሴ አነጣጥሮ ተኳሽ ነውን? ጫካውስጥበነበረበት ወቅት ከደርግ ጋር ሲያካሂደው የነበረው የዚያ ጦርነት አስቀያሚ ትዝታ ድንገት ብልጭብሎበት ይሆን እንዴ?ሰሎሞን ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሟቸውን በሰላማዊመንገድ ለማሰማት በተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችላይ በየትኛውም የዲፕሎማሲያዊ ተቋም ላይተሞክሮ ያልታወቀውን ስልጣኔ የጎደለውን የደንቆሮዎች ድርጊት በመናፈቅ ተኩስከፍቶወገኖቻችንን ለመጨረስ መሞከሩ በእውነት በጫካ በነበረበት ጊዜ ወያኔን ሲቃወሙ የነበሩትንወገኖቻችንን ሁሉ ሲጨርስእንደነበረው ሁሉ አሁንም ያንን እኩይ ምግባር የዓለም የዴሞክራሲተምሳሌት በሆነችው አሜሪካ እምብርት ዋሺንገተን ዲ.ሲ.ላይ ልምዱን ለማስታወስ ያህልሲነሽጠው የክለሳ ስራ መስራቱ ይሆን እንዴ? ‘ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ’ እንዲሉ!
ገብረስላሴ የፈጸመው እኩይ ድርጊት በስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ተመራማሪዎች ‘አስቀያሚ ትዝታ’በመባል የሚታወቀውንከአዕምሮ ጋር ተቆራኝቶ የሚኖረውን እና ሳይታሰብ እና በድንገት ቅጽበታዊበሆነ መልኩ በአንድ ምክንያታዊም ሆነኢምክንያታዊ ክስተት በሚፈጸምበት ጊዜ ላይ ግንፍል ብሎበመውጣት ወደ ድርጊት ከሚሸጋገር ስነልቦናዊ ድርጊት ጋርይመሳሰላል፡፡ ከዚህ አንጻር ገብረስላሴያልታጠቁ ሰላማዊ አመጸኞችን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ አካባቢ በተመለከተ ጊዜበአዕምሮስነልቦናው ውስጥ ተቀርጾ የተነበበው በከፍተኛ ወኔ እና ከባድ መሳሪዎችን ታጥቆ በመምጣትየእርሱን የአማጺ ቡድንወያኔን ለመውጋት የመጣ ሰራዊት መስሎ ነው የታየው፡፡ በግልብአዕምሮው ውስጥ ተጽፎ የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ሌላ በጎነገር በቡድንም ሆን በግልያልለመዱትን እና ያላዩትን ነገር ለሰሎሞን ገብረስላሴ ከየትኛው ተሞክሮው ተቀምሮ በአዕምሮውጓዳውስጥ አድሮ ሊከሰት ይችላል ተብሎ ይታሰባል? ጀግናው ገብረስላሴ ያንን የመሰለ ድርጊትበሚጽምበት በዚያን ጊዜ የሀገሮችመስተጋብር ማስፈጸሚያ የሆነውን ኤምባሲን የሚጠብቅ መስሎአልታየውም፡፡ ይልቁንም በአዕምሮው ላይ ተቀርጾ የኖረው እናአሁንም ያለው የወያኔን የመሬትውስጥ ምሽግ ጫካ በነበረበት ጊዜ ከጠላት ለመከላከል የሚያደርገውን ቅጽበታዊእርምጃመውሰድን ነው የሚያስታውሰው፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በድል አድራጊነት በሚመስል መልኩ ሽጉጡንእያወዛወዘበዲፕሎማት ወግ ጥቁር ሱፉን ገድግዶ ለብሶ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስበታላቋ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በከፍተኛ ደረጃ የውጭ አገርየዲፕሎማት ሰው መቀመጫ ወንበር ላይ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩእረስቶታል፡፡ አይ ጫካመኖር! የጫካ አስተሳሰብ እኮ በጫካው ውስጥ ያሸነፈ ይኑር የሚለውን የአራዊት አስተሳሰብንየተላበሰሆኖ ይገኛል፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በጫካ ህይወቱ ጊዜ ጠላትን ለመከላከል እና አለቆቹንጠላት ከሚያደርሰው ጥቃት ለመጠበቅከአዛዦቹ ይሰጥ የነበረውን ትዕዛዝ ተቀብሎ ይተገብርወደነበረበት የወያኔ አማጺ ቡድን እግረኛ ተዋጊነት ስራው ተመለሰ እንጅዘመናዊ አስተሳሰብ እናየትምህርት ክህሎት ከሚጠይቀው ዲፕሎማትነት ጋር ትውውቅም ሆነ ዝምድና የሌለው መሆኑንበሚገባተግብሮ እና አስመስክሮ ወደ አገሩ ሳይሆን ወደ መፈንጫው ተመልሷል፡፡
ሰሎሞን ገብረስላሴ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ተልዕኮ እና የውጭ ዲፕሎማት የኗሪነት ፖሊሲእና ህግ ጥበቃ ምን እንደሆነእና ምን እንደሚመስል የማያውቀው መሆኑ በግልጽ ይነበባል፡፡አሜሪካ በውጭ የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ከማንኛውም የጠላትጥቃት ለመከላከል ፈጣን የሆኑ የባህርኃይል ሰራዊቷን በማሰማራት ጥበቃ እንደምታደርገው ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስአሜሪካየሚገኙትን የዲፕሎማሲ ፋሲሊቲዎችን ጥበቃ በሚመለከት ግን ኃላፊነቱ የወደቀው በአሜሪካየመንግስት መምሪያ፣በደህንነት አገልግሎቱ እና በአካባቢ የፖሊስ ወኪሎች የጋራ ጥረት ላይ ነው፡፡ከዚህ አንጻር የዋሺንግቶን ከተማ ፖሊስለዲፕሎማሲያዊ ፋሲሊቲዎች ደህንነት ሲባል የተለያዩመንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ስለሆነም ለጥበቃው በተለይምዘብ ለተወሰኑ ፋሲሊቲዎች ወይም ደግሞ ለደህንነት ጉዳይ ሲባል እየተዘዋወሩ የሚጠብቁዘቦችንበመመደብ እና የፖሊስ ምልክት ያለባቸውን ተሽከርካሪዎች በማሰማራት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡እንደዚሁም ደግሞ መረጃየማይሰጠው የደህንነት አገልግሎቱ መስሪያ ቤት በዋሺንግትን ዲ.ሲአካባቢ ላሉ የዲፕሎማሲያዊ ተቋማት ተገቢ የሆነ ጥበቃይሰጣል፡፡ ይህ የደህንነት አገልግሎትመስሪያ ቤት በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ እና በዲፕሎማቶች ፋሲሊቲዎች ላይ ሊፈጸምየታሰበአስተማማኝ አደጋ መኖሩን ሲያረጋግጥ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
ያለመከሰስ መብት የተጎናጸፉት ዲፕሎማቶች በማንኛውም መልኩ የጦር መሳሪያን በመጠቀምሌሎችን ሰላማዊ በሆነ መልክተቃውሟቸውን በሚገልጹ ያልታጠቁ ወገኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር፣ዲፕሎማቶች በእራሳቸው ሀገር በሌሎች ወገኖች ላይ ጥቃትለማድረስ ሲባል የጦር መሳሪያ ደብቆመገኘት፣ ወይም ደግሞ በድብቅ መሳሪዎችን በማከማቸት በዩናይትድ ስቴትስ ወይምበዩናይትድስቴትስ በሚኖሩ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን በሚያካሂዱ ዲፕሎማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘርንየሚፈቅድ ህግ፣ፖሊሲ ወይም ደግሞ ልምድ በፍጹም የለም፡፡ ዲፕሎማቶች አለመግባባቶችን እናውዝግቦችን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድለመፍታት የቃላት “ጥይቶችን” ይጠቀማሉ እንጅእንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ እየተገበረው እንደነበረው ቁጥር 38 የካሊበርሽጉጦችንአይጠቀሙም፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ አካባቢ መሳሪያ በመተኮስ ያልታጠቁሰላማዊ ተቃዋሚዎችንለመግደል በተደጋጋሚ ባደረገው የግድያ ሙከራ በዋሺንግተን ዲ.ሲየዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ህሊና ቢስ እና የሞራል ስብዕናንየጣሰ የወንጀል ድርጊት ሆኖ ሲታወስይኖራል፡፡ ይህ አስነዋሪ የወንጀል ድርጊት ወደፊት ለሚመጡት አስርት ዓመታትየወሮበላየዲፕሎማሲ እኩይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የሚያግዙ ለዓለም አቀፍ የህግ እና የዲፕሎማሲተማሪዎች አገልግሎትየሚውሉ የማስተማሪያ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ታላቅ እገዛን ያደርጋል፡፡
ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀውአትችልም፣
የዲፕሎማት ሰዎች ተቀራርቦ በመነጋገር፣ ስምምነት በማድረግ እና በመቻቻል (አብዛኛውን ጊዜበማታለል) ባለመግባባትየሚከሰቱ ውዝግቦችን ለመፍታት ይፈልጋሉ፡፡ የወሮበላ ዲፕሎማቶችሁሉንም ችግሮች እና ከዚእነዚህ ክሶች ጋር ተያይዘውየሚከሰቱ ውዝግቦችን በመግደል፣በመደብደብ ወደ ዘብጥያ በመወርወር እና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን እናጠላቶቻቸውንበማሰቃየት ይፈታሉ፡፡ ዲፕሎማሲ “በመንግስታት ተወካዮች መካከል የሚደረጉ ስምምቶችንለማምጣትየሚያገለግል ትምህርት እና የተግባር ተሞክሮ ነው፡፡“ ወሮበላ ዲፕሎማት ሰሎሞንገብረስላሴ የዲፕሎማት ትምህርቱን ያገኘውእና የቀሰመው ዙ ኢንላይ ከሚባለው ተረታዊየዲፕለማት ትምህርት ቤት ነው፡፡ “ሁሉም ዲፕሎማሲ በማንኛውም መንገድቢሆን የጦርነትቀጣይነት ነው፡፡“ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብትን መደበቂያ ምሽግበማድረግለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘለቀውን አከፊውን የወያኔን የጫካ ጦርነትወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማምጣት ፈለገ፡፡
የሰለጠኑ ወሮበላ ዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ የሚመረጡት እና የሚላኩት እጅግአናሳ በሆነ አጋጣሚ ነው፡፡አብዛኞቹ አገሮች ወደ ሌላ አገር የሚያሰማሯቸውን ዲፕሎማቶችየሚመርጧቸው በመንግስት መስሪ ቤቶች ከሚመድቧቸውበከፍተኛ ደረጃ ካሉ ሰዎች መካከልነው፡፡ አብዛኞቹ የሚመረጡት ዲፕሎማቶችም በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት የቀሰሙ፣ ሰፊልምድያካበቱ እና ጠለቅ ያለ የፖለቲካ እውቀት ያላቸውን ዜጎች ነው፡፡ ብዙ አገሮችም የዲፕሎማትሰዎቻቸውን ሾመውወደመደቧቸው አገሮች ከመላካቸው በፊት ሙያዊ የሆነ እና ከሙያው ጋርአግባብነት ያለው ስልጠና በማዘጋጀት እንዲሰለጥኑያደርጋሉ፡፡
እጅግ በጣም ውሱን ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሀገር ቢሆን እንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴያለውን ተራ ማይም ደንቆሮ መርጦእንደ ዩናይትድ ስቴትስ ባለች አገር ላይ ዲፕሎማት ብሎአይልክም፡፡ በዲፕሎማቲክ መስኩ በጣም ቀልጣፎች ያልሆኑ አገሮችእንኳ ለዲፕሎማሲ ተልዕኮየመለመሏቸውን ሰዎች ወደየሀገሮች ከመላካቸው በፊት ስለዲፕሎማሲ ስራ ሰልጠና ይሰጧቸዋል፡፡በዚህም መሰረት በየጊዜው ከሚለዋወጠው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር አብረው ለመሄድ እንዲችሉእገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ ያየሚሰጠው ስልጠናም በትክክለኛው መንገድ በዲፕሎማሲ ስራ እና ተግባርላይ ትኩረት ያደረገ እንጅ ስለጦርነት ስልት እውቀትወይም ዜጎችን በአገራቸው እንዴት መግደልእንደሚችሉ ለማሰልጠን አይደለም፡፡ ለምሳሌም ያህል አዘረባጃን የእራሷ የሆነ“የዲፕሎማሲአካዳሚ” አላት፡፡ ቡልጋሪያም የግሏ የሆነ የዲፕሎማሲ ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡ እንደዚሁምደግሞ ጋና ኮፊ አናንየሰላም ጥበቃ ስልጠና ማዕከል/Kofi Annan Peace Keeping Training Center የሚባል የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛተቋም አላት፡፡ በሌላ በኩልም የግልየዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ዩኒቨርስቲዎች ማለትም እንደ Tuft University’s Fletcher School of Law and Diplomacy እና ሌሎች ተቋማትም ከዓለም አቀፋዊድርጅቶች ጋር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶች አሉ፡፡
ሊታምን በማይችል መልኩ የሚያስደንቀው እና የሚገርመው ነገር በአጠቃላይ የወያኔ የውጭ ጉዳይሚኒስቴር አመራርበዲፕሎማሲ የሙያ ዘርፎች ላይ የሰለጠነ ወይም ደግሞ በዚህ ሙያ ላይ በቂልምድ ያለው ዲፕሎማት የለውም፡፡ ለምሳሌ ያህልየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ቁንጮ የሆነውሰው የዲፕሎማሲ ሙያ ስልጠናም ሆነ ልምድ የላቸውም፡፡ ምንም፣ ባዶ! የውጭጉዳይ ሚኒስትርቴዎድሮስ አድኃኖም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከአስመራ ዩኒቨርስቲ በስነሕይወት/Biologyየትምህርት መስክ ነው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በማስተር ኦፍሳይንስ በImmunology of Infectious Diሰዓሰስበሚል ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ ያገኙሲሆን የፒኤች ዲ ዲግሪያቸውን ደግሞ በህብረተሰብ ጤና/Community Healthየትምህርትመስክ በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል፡፡ ለጤናሚኒስትርነት ተሾመው ነበር፡፡ በአንድ ጀንበርምሽት ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ እራሳቸውንየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገኙት፡፡ (እርግጠኛ ነኝ በአንድ ጀንበር ምሽትደግሞ እራሳቸውንጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገኙታል)፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ለጠቅላይሚኒስትርነትመወጣጫነት የመጀመሪያ ደረጃ እና ለሚጠብቃቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነትሹመታቸው ለይስሙላም ቢሆን ለማሟሻነትቢጠቅም በሚል እኩይ ስሌት የተቀነባበረ ነው፡፡እርግጥ ነው አምባገነንነት እና ወሮበላነት በተንሰራፋባት የመጨረሻ ደኃ ሀገርለዲፕሎማትነትመስፈርቱ ዘር እና ታማኝነት እንጅ ትምህርት እና ልምድ ምን ፋይዳ ይኖረዋል! (ሟቹ መለስዜናዊ በአንድ ወቅትስለሚኒስትሮቹ አሿሿም የትምህርት ብቃት ማነስ ጉዳይ በቴሌቪዥን ጥያቄበቀረበላቸው ጊዜ “ታማኝነት እንጅ ማይም ይሁኑ”በማለት የሰጡትን አስገራሚ እና ፈጣጣየስላቅ መልስ ልብ ይሏል፡፡)
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ እንዴት አንድ ምንም ዓይነት የዲፕሎማትነት ልምድ እና በመስኩም አስፈላጊየሆነው ትምህርት ሳይኖረውወይም ደግሞ ምንም መነሻ መሰረት ሳይኖረው እንዲሁምበአምበሳደርነት (ስለዓለም አቀፍ ህግ እና ዲፕሎማሲ ፍጹም ባይተዋርየሆነ [ከኢትዮጵያ እሳትወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ] በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ትችት ይመልከቱ) እንኳ ሳይሰራበድንገት እናቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ያህል ከባድ ኃላፊነት የሚጠይቅየሚኒስትርነት ቦታን ይይዛል?
ለዚህ መልሱ ግልጽ እና አጭር ነው፡፡ አድኃኖም በዘር ሀረጋቸው ብቻ እና ብቻ ነው የወያኔየከፍተኛ ዲፕሎማት ስልጣንየተሰጣቸው፡፡ በእርግጥ ይኸ ጉዳይ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ በአሁኑጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ምን ዓይነትየትምህርት ማስረጃ እና ብቃት አቅርቦ ነውጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው? መለስ በርቀት የትምህርት ፕሮግራም በተልዕኮከእንግሊዝ ሀገርበቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኘ፡፡ ለሁለተኛ ዲግሪውም ከኢራስመስዩኒቨርስቲ የዓለምብቸኛው ታላቅ አዋቂ ነኝ አያለ ሲፎከርበት የነበረውን የልማት ምጣኔሀብት/Development Economics የመመረቂያጽሁፉን ማጠናቀቅ ያልቻለ ሰው ነበር፡፡
ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለወሮበላ ዲፕሎማት ልዩ ስልጠና እየተሰጠ በብቃት ላይሳይሆን በዘር እና በታማኝነት ላይትኩረት በማድረግ የሚኸድበት ስልት እውነተኛውንየዲፕሎማሲ ስራ አካሄድ እንዲበላሽ አድርጎታል፡፡ ለአፍሪካውያን/ትየወሮበላ ዲፕሎማቶችማሰልኛ ተቋም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከአፍሪከ ህብረት የለማኞች አዳራሽ፣ ለአፍሪካ አምባገነኖችእናወሮበሎች መሰብሰቢያ ከተሰራው አዳራሽ ፊት ለፊት በቅርብ ርቀት ላይ ይገነባል የሚል ግምትአለኝ፡፡ የሚያስገርም ጉዳይይሆናል፡፡
ከእውነታዎች ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን፡፡ አሳማን የከንፈር ቀለም መቀባት ይቻላል ቆንጆለማስመሰል፣ ሆኖም ግን ከዕለቱመጨረሻ ያው ዓሳማ ዓሳማ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እንደሰለሞን ገብረስላሴ፣ ግርማ ብሩ ወይም ቴዎድሮሰ አድኃኖም እናሌሎች በርካታዎቹ ብሪፍ ኬዝ/ቦርሳ እና የይሰሙላ ክብር መስጠት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጨረሻም እራሳቸው እራሳቸውንሆነውያገኙታል፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች!
መንግስታዊ አገዛዝ ከወሮበላ (የጫካ አገዛዝ ጋር) ሲነጻጸር፣
የወያኔን አገዛዝ የወሮበላ አገዛዝ ነው በማለት በምገልጽበት ጊዜ ከምንም በመነሳት በጥላቻ ወይምደግሞ ለቡድኑ ክብርካለመስጠት አይደለም፡፡ አንዲሁም መለስ ዜናዊን “የአፍሪካ የለማኞችአለቃ” ነው በማለት ስገልጽ እራሱ በሚጠቀምባቸውቃላት ላይ መሰረት አድርጌ ነው፡፡ የእራሴንቃላት እና ሀረጎች እርሱ ከሚሰራቸው እውነታዎች በመነሳት ነው የምርጣቸው፡፡
የወያኔ አለቆች በምንም ዓይነት መልኩ ከወሮበላነት (የጫካ) አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደርበፍጹም ሽግግር አያደርጉም፡፡በጫካው ዘመናቸው ወጣት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸው ልምድየምሁርነት አስተሳሰባቸውን፣ የሞራል ስብዕናቸውን እናየማህበራዊ ልማት እይታቸውን በጫካውየቅኝት አስተሳሰብ ብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፣ ሸፍኖት ቀርቷል፡፡ ከዚያ አልፎአንዳንዶቹ ዘመናዊእና ላቅ ያለ የአካዳሚ ትምህርት የማግኘት ዕድል ያገኙ አባላቱ እንኳ ስልጣን ከያዙ በኋላበተመሳሳይ መልኩድሮ ወደነበሩበት የአስተሳሰብ አድማስ በመመለስ የአስተሳሰብ ግልብነት እናየሞራል ዝቅጠትን እና ባዶነትን አንጸባርቀዋል፡፡
የወጣትነት የመጀመሪያዎቹን ዓመታት በጫካ ውስጥ አማጺ ሆኖ ከማሳለፍ አንጻር ለመቀየርየማያስችል እና ቋሚ የሆነ የተቸከለአስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ በአካዳሚክ ዓለሙ ያሉም ሰዎችይህን ሲመለከቱቱ የአማጺያንን የጫካ ህይወት መኖር ያልረሱት እናበአዕምሯቸው ላይ የማይለቅችካል ስለሆነ ሆብስ “የመሆን ሁኔታ” እንዳለው በአእምሯቸው ላይ በጫካ አስተሳሰብየተቃኘአንዳች የሆነ ነገር አንደሚፈጠር ነው። የእንግሊዝ ፈላስፋ የነበሩት ቶማስ ሆብስ የሰለጠነመንግስት በሌለበት ጊዜ“እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው ጋር በጦርነት ይኖራል” በማለት የሙግትጭብጣቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ ህይወትበመሆን የተፈጥሮ ህግ ላይ “ብቸኛ፣ ደኃ፣በጭካኔ የተሞላ፣ አውሬአዊ እና ኋላቀርነት አስተሳሰብን የተላበሰ ይሆናል“፡፡ ሆኖምግን ሊነሳየሚችለው ጥያቄ ሆብስ የመሆን ሁኔታ እዳሉት ለአስርት እና ግማሽ ዓመታት በአማጺነት በጫካሲኖሩ የነበሩት የወያኔአማጺ አመራሮች ከጫካ ህይወታቸው ወጥተው ስልጣንን በኃይል ነጥቀውበስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡ እና የሰለጠነመንግስታዊ መዋቅር መሪዎች ከሆኑ በኋላበእርግጠኝነት ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜሲመሩበት የነበረውንየመሆን ሁኔታ እርግፍ አድርገው ትተው የወሮበላነትን መንግስታዊ አገዛዝ በሰለጠነ መንግስታዊአስተዳደርእንዲቀየር በማድረግ የህግ የበላይነትን በማስፈን እውነተኛ ሽግግርን ሊያመጡ እናህዝቡን በሚፈልገው መልክ ማስተዳደርይችላሉን?
አጋጣሚ ሆኖ ከእነርሱ አባባል ታምራዊ ሀረጎች በመዋስ “እድገት እና ትራንስፎርሜሽን”ለማምጣት የምሁራዊ እና የሞራልብቃቱ ሳይኖራቸው ቀርቷል፡፡ ለወያኔ አለቆች በሰለጠነማህበረሰብ ውስጥ ገብቶ አብሮ መኖር አሁን ብዙ ገንዘብ እና ሀብትከመዝረፍ በስተቀር ለእነርሱህይወት በጫካ ውስጥ ይኖሩበት እንደነበረው ዓይነት ቀጣይነት ያለው ነው፣ ምንም ዓይነትልዩነትየለውም፡፡ በእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስ ምንም ዓይነት የተቀየረ ነገር የለም፡፡ ለ23 ዓመታትበስልጣን እርካብ ላይተፈናጥጠው ከቆዩ በኋላ ምንም ዓይነት የተማሩት ቁም ነገር የለም፡፡አሁንም ቢሆን በጫካ በነበሩበት ጊዜ ሲያራምዱትየነበረውን ሚስጥራዊ የፖለቲካ ፍልስፍናበህዝቡ ላይ በመጫን ለመቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜየተጠያቂነት እናየግልጽነት ባህሪን አያራምዱም ነበር፣ አሁንም ቢሆን አንድን ታላቅ አገር በቁጥጥራቸው ስርአድርገው ስርዓትባለው መልኩ ተጠያቂነት እና ግልጽነትን በተላበሰ ሁኔታ መምራት ሲችሉ ይህንንመተግበር ተስኗቸዋል፡፡ በጫካ ውስጥ ሆነውከደርግ ወታደራዊ አምባገነን ጋር ትግል ሲያደርጉበነበሩበት ወቅት ውሳኔ ሰጭነት በጥቂት የወያኔው መሪዎች ብቻ እና ብቻነበር፡፡ በዚያን ወቅትእነዚህ ጥቂት አመራሮች ይመሩት በነበረው ሰራዊት እና በአጠቃላይ በቁጥጥራቸው ስርአድርገውትበነበረው ህዝብ ላይ ጥሬ የሆነ አስተሳሰብን፣ ጭካኔ የተሞላበት ኃይልን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ሰላማዊአማጺያንን እናየሰላ ትችት ያቀርቡባቸው በነበሩት ወገኖች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃመውሰድ ጀመሩ፡፡ ከእነርሱ ሀሳብ ጋር ስምምነትየማያደርጉ ዜጎችን ማግለል፣ እንደ ሰላይነትበመቁጠር መግደል እና ማጥፋት ጀመሩ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መንግስታዊ ስልጣንንከተቆናጠጡበኋላም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ሌሎችንም ለስልጣናቸው አስጊናቸው ብለውየሚጠረጥሯቸውን ወገኖች ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል እና ከሀገር እንዲወጡማድረግን ስራየ ብለው መተግበር ጀመሩ፡፡ከእራሳቸው መካከል በሀሳብ በመለያየታቸውየተገነጠሉትን ተስፈንጣሪ ቡድኖች ርህራሄ በሌለው መልኩ አስወገዷቸው፣አዋረዷቸው!
በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ስልጣንን፣ ገንዘብን በመዝረፍ እራስን እንደማበልጸጊያ፣ የፖለቲካየበላይነት እና ማስፈራራትንእንደ መሳሪያ በመቁጠር ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔአገዛዝ በሙስና የበከተ እና የሙስናው በሽታ በኢትዮጵያ አካልላይ እንደ ነቀርሳ እየተሰራጨመሆኑን ሙስናን በኢትዮጵያ መመርመር/Diagnosing Corruption in Ethiopia በሚል ርዕስየዓለም ባንክ አዘጋጅቶ ባወጣው በባለ550 ገጽ ዘገባው ላይ በግልጽአስፍሮታል፡፡ ወያኔ በጫካ በነበረበት ጊዜ አመራር ላይመሆን ማለት የእራስን ስብዕና መትከልየነበረ ሲሆን አሁንም ቢሆን በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በእርሱደቀመዝሙሮችእንደ ትንሹ አምላክ ያህል ይመለክ ነበር፡፡ የእነርሱ ከጫካ አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደርያደረጉት ሽግግርየአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነት የነበረውን የደርግ አገዛዝ በማስወገድበአንድ ሰው፣ በአንድ ፓርቲ የወያኔ አገዛዝ ተኩት፡፡የወያኔ አመራሮች በደርግ አገዛዝ ላይ ያደረጉትለውጥ አለ ከተባለ “ለወያኔ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያ ህዝብም ጥሩነው” የማለታቸውአምባገናናዊ አመለካከታቸው ብቻ ነው!
ከወሮበላነት/ከጫካ አገዛዝ ወደሰለጠነ መንግስታዊ አስተዳደር የሚደረግ እውነተኛ ሽግግርየፍልስፍና እና የፖሊሲ ሁለቱንምነገሮች ስርነቀል በሆነ መልኩ መቀየርን ይጠይቃል፡፡ ይኸ ግንባዶ ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ እንደምለው የወያኔአመራሮች ትክክለኛ መንግስታዊመዋቅርን ይመሰርታሉ ወይም ደግሞ ትክክለኛ መንግስታዊ ስርዓትን ያራምዳሉ ማለትሰይጣንከመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሰ ያስተምራል እንደማለት ነው፡፡
ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር መሰረታዊ የሆኑትን መርሆዎች ማለትም የህግ የበላይነት፣የስልጣን ክፍፍልን፣ የቁጥጥርእና የኃይል ሚዛንን እና ህገመንግስታዊ የአስተዳደር ሂደትንበመተግበር በእውነታ ላይ የተመሰረተ ትችትን በትክክል ለተከናወኑስራዎች ደግሞ አድናቆትመስጠት እና መግባባትን ይጠይቃል፡፡ የወያኔ ወሮበላ አመራሮች ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ጉዳዮችእጅግበጣም አነስተኛ የሆኑ ልምዶች ወይም ደግሞ የተግባር ተሞክሮ ጭራሹንም የላቸውም፡፡በዚህም መሰረት ማንም ቢሆን እነዚህየወሮበላ ስብስብ አመራሮች በፖለቲካ ህይወታቸው ውስጥያልነበራቸውን እና በተሞክሮም የማያውቁትን ተጠያቂነትን እናግልጸኝነትን ሊያሰፍን የሚያስችልየፖለቲካ ስርዓት ለህዝቡ ማስፈን እና መተግበር ይችላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡በጫካውስጥ በነበሩባቸው ጊዚያት ምንም ዓይነት ነጻ ምርጫ አካሂደው አያውቁም፣ በመሆኑም እ.ኤ.አበ2005 በተደረገው አገርአቀፍ ምርጫ በዝረራ በተሸነፉበት ወቅት ተአምር የሆነ ያህልተገርመው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ታላቅ ትምህርትን ቀስመዋል፡፡እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገውአገር አቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ የድምጽ ውጤት በማምጣት (በመዝረፍ አላልኩም)ድልተቀዳጅተናል፡፡ በጫካ በነበሩባቸው ጊዚያት የሚናገሯቸው ቃላት እራሳቸው ህግ ነበሩ፣ ስለ የህግየበላይነት ምንም ዓይነትሀሳብ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ጊዜ ስልጣንን ከጨበጡ በኋላ የእነርሱቃል እራሱ ህግ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በእራሳቸው ስልጣንያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይቀጣሉ፡፡ በጫካ ውስጥበነበሩበት ጊዜ እነርሱ እራሳቸው ዳኛ፣ ችሎት እና አስፈጸሚ ነበሩ፡፡ በስልጣን ላይባሉበት ጊዜበጫካ ላይ ከነበሩበት ጊዜ የተለየ ነገር የላቸውም፣ ልዩነት አለ ከተባለም በጫካው ጊዜ ይፈጽሙትያልነበረ አሁንዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅርን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለይስሙላ የዝንጀሮፍርድ ቤቶችን በማቋቋም እነርሱ በሚፈልጉትመልኩ ውሳኔው እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ በጫካውስጥ በፍርሃት እና በበቀል ነው የኖሩት፣ እናም የሲቪል ነጻነቶች እና የእነዚህነጻነቶች አተገባበርለእነርሱ ባዕድ ናቸው፣ ፈጽሞ አይተዋወቁምና፡፡ በአሁኑ ጊዜም ህዝቡ በድንገተኛ መሬትአንቀጥቅጥ አመጽያስወግደናል በሚል ፍርሀት ውሰጥ ተቀርቅረው ሌት ቀን ሲባንኑ ይውላሉ፡፡እናም የሲቪል ነጻነቶች እና መብቶች ቅንጦት የሆኑነገሮች ሲሆኑ እነዚህ ቅንጦት የሆኑ ነገሮችምለእኛ ሳለይሆን ለምዕራባውያን ሰዎች ብቻ የተተው እንደሆኑ አድርገውይቆጥራሉ፡፡ ሆኖም ግንእነርሱ፣ የእነርሱ ደቀመዝሙሮች እና ደጋፊዎቻቸው ለሚሰሯቸው ወንጀሎች እና የሲቪልወንጀሎችሳይቀር ያለመከሰስ መብትን በመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸሙ እራሳቸውን በማስደሰት ላይይገኛሉ፡፡በአጭሩ ከዚህ የእኩይ አስተሳሰብ ባለቤት ከሆነው የወሮበላ ቡድን ዴሞክራሲያዊአስተዳደርን የተላበሰ ስርዓት በኢትዮጵያ ላይለማስፈን የሚያስችለል መንግስታዊ መዋቅር መጠበቅከባዶ ተስፋ የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዴት?
በአንድ ታትሞ በወጣ ዘገባ እንደቀረበው የወያኔ አገዛዝ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 29/2014በዋሽንግተን ዲ.ሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ወገኖቻችን ላይክስ ለመመስረት እንደሚንቀሳቀስ አሳውቋል፡፡ ዲና ሙፍቲ የተባሉትየኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይሚኒስቴር ቃል አቀባይ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፣ “የዩናይትድ ስቴትስመንግስትበኤምባሲው ቅጥር ግቢ ገብተው ጸረ መንግስት የሆኑ መፈክሮችን እያሰሙ የኢትዮጵያንባንዲራ በማውረድ ሁከት በፈጠሩትሰዎች ላይ የኤምባሲውን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እናበአጥፊዎች ላይ ክስ መመስረት እንዳለበት ይጠበቃል፡፡“ በሌላ በኩልየወጣ ዘገባም እንደጠቆመውሰላማዊ ሰልፈኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትስ ስቴትስ ኤምባሲ በመሄድ “ሰላማዊሰልፈኞችለህግ መቅረብ አለባቸው” የሚል ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡ “ በቪዲዮክሊፑ ላይ እንደሚታየው ሰላማዊሰልፈኞች የኢትዮጵያን ብሄር ብሀረሶቦች የሚወክለውን ባንዲራበማውረድ የጥንቱን እና የነጻነታችን አርማ ሆኖ ሲያገለግልየቆየውን አረንጓዴ፣ ቀይ እና ብጫቀለም ያለበትን የህዝቦች ነባር ባንዲራ በክብር ወደነበረበት ቦታው መለሱት፣ አከበሩትእንጂአላዋረዱትም፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ በወያኔ አገዛዝ የተቀነባበረ የመድረክ ላይ ተውኔት ነው፡፡
ሙፍቲ፣ ቴዎድስ አድሀኖም እና ሌሎች የወያኔ ደናቁርት ምን መመኘት እንዳለባቸው ጥንቃቄማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
መጀመሪያ፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ጥፋተኛ ለማድረግ በሚደረገው የውንጀላ ብያኔ ላይ ግልጽ መሆንአለበት፡፡ በአሜሪካ አገርየፌዴራል ወይም የኮሎምቢያ ወረዳ ግዛት ወንጀል ስርዓት ኮድ ላይ“ሻጥር ለመስራት” የሚል የወንጀል ጥቅስ አይታወቅም፡፡ምናባዊ የሆነ የወንጀል ክስ በመፈብረክክስ እንዲመሰረት ቢያስቡ እና ህዝቡን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉ የእነርሱ የአስተሳሰብአድማስበምን ያህል ጥልቀት እንደወረደ እና ስለአሜሪካ ህግ ያላቸውን ድንቁርና የሚያመላክት ነው፡፡(በእንደዚህ ዓይነት ፍጹምድንቁርና የተጠናወታቸው ፍጡሮች “ኢትዮጵያ የምትመራ” መሆኗንስመለከት በጣም ተሸማቀቅሁ፣ አዘንሁም!)
ሁለተኛ፡ የወያኔ ደናቁርት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አገር ማንኛውንም ዓይነት ባንዲራ የኮከብእና ነጠብጣብ ምልክትያለባትን የአሜሪካን ባንዲራም ቢሆን ማውረድ ወይም ማዋረድ ወንጀልአለመሆኑን ሊያውቁ ይገባል፡፡ እ.ኤ.አ በ1989በቴክሳስ ግዛት ጆንሰን የዩኤስ አሜሪካንንባንዲራ እ.ኤ.አ በ1984 የሬፐብሊካን ብሄራዊ ጉበኤ በዳህላስ፣ በቴክሳስ) ባቃጠለበትወቅትጀስቲስ ዊሊያም ብሪናን በአጠቃላይ ሀሳብ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፣ “በሀሳብመለያየትን የማስተናገድመብት ማረጋገጥ የአሜሪካ የመጀመሪያው የህግ ነጻነት ማሻሻያችንየመሰረት ድንጋይ ነው፣ መንግስት በዜጎቹ መካከል አንድነትንየሚያጠፋ ነገር በመፈብረክ የዘፈቀደትዕዛዝ በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ አይችልም፡፡“ ይላል፡፡ ስለሆነም ያ አንድ ዓይነትባህሪ እናመርህ ያለው መንግስት የአንድነት መገለጫ የሆነውን ምልክት በመጣስ ከዚያ መርህ ጋር የሚጣረስትዕዛዝንሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ በቀላል አነጋገር እንኳንስ ይህንን በሸፍጥ የተዘጋጀ የብሄርብሄረሰቦች የሸፍጥ ባንዲራ ከተሰቀለበትማዕዘን ማውረድ ይቅርና ጥንታዊውን እና የተከበረውንያሜሪካ ባንዲራም በእሳት ማቃጠል ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡
ሦሰተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት በጋዜጦች እና በድረ ገጾች የሚለቀቅ የዲፕሎማሲስራን እንደማይሰራ የወያኔአገዛዝ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ እነዚህ ደናቁርት የዩናይትድስቴትስ መንግስት የሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርግላቸውከተፈለገ በመጀመሪያ ደረጃ የፕሮቶኮልስነስርዓትን ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ከውጭመንግስታትየዲፕሎማቶች የተቃውሞ ጥያቄ ሲቀርብለት የውጭ መንግስታቱ የሚፈልጉትን ለማግኘት ሲፈልጉእነዚህ ቅሬታለማቅረብ የሚፈልጉ መንግስታት መከተል ያለባቸውን ህጎች እና የአካሄድስነስርዓቶች በመከተል እንዴት ምላሽ መስጠትእንደሚችል በጣም ዝርዝር በሆነ መልኩአስቀምጧል፡፡ የወያኔ ደናቁርት በቀጣይነት የሚደርስባቸውን ውርደት እና መሸማቀቅለማስቀረትበማሰብ ለእነርሱ ወገናዊነት እገዛን ለማድረግ የዩኤስ አሜሪካንን የመንግስት መምሪያ የውጭ ጉዳይሰነድ ቮሊዩም 5የእጅ መጽሐፍ ቁጥር 1ን እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ፡፡ (በነገራችን ላይስለዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብት መነሳት ጉዳይንበማስመልከት ጥያቄ አቅርባችሁልኝ ለነበራችሁአንባቢዎቸ በግንባር በመገኘት ምላሽ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ሆኖም ግን ለዚህ ስራይጠቅማችኋል በሚል እሳቤ “Diplomatic and Consular Immunity: Guidance for Law Enforcement and Judicial Authorities“በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን በመረጃ የበለጸገ ሰነድ እንድታነቡት እጋብዛለሁ፡፡
አራተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች እንደ ወያኔው የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑተከላካዮች የተሟላህገመንግስታዊ መብት ያላቸው እና አስገድዶ ቃል ያለመቀበልን፣ ያለመደብደብእና በሰውነት ላይ የሚፈጸሙ የጥቃትማስረጃዎችን ጭምር በማካተት አዘጋጅቶ ያስቀመጠ መሆኑንየወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ የወያኔ ደናቁርት እነዚህንየነጻነት ታጋይ ወገኖቻችንን በህግፊት አስቀርበው ለማስቀጣት ከልብ ፈልገው ከሆነ በዚህ በአሜሪካ የህግ ሰነድ ላይየተዘረዘሩትንእና የታጨቁትን ህጎች በሙሉ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አምስተኛ፡ የህግ ስርዓት ቢኖር ኖሮ ግርማ ብሩ እና ሌሎች የኤምባሲው ሰራተኞች እንዳደረጉትሁሉ ገብረስላሴም በታላቁየፍርድ ቤት ችሎት ቀርቦ ቃሉን መስጠት እና የማስተባበያ ማስረጃመስጠት የነበረበት መሆኑን የወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡትይገባል፡፡ በችሎት ፊት ቴዎድሮሰአድሃኖም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦቻቸው ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ቃልመስጠትየጽሁፍ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ተከላካይ በግርማ ብሩ፣ በገብረስላሴ፣በአድሃኖም እናበሌሎች ቀሪ ሰዎች ላይ መስቀልኛ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመስቀለኛጥያቄዎች ሲጠበሱ ምነው ጫካ ገብተን ደርግንበተዋጋን በለው ሳይመኙ አይቀሩም።
ስድስት፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ሊያጋጥመው እንደሚችል መጠበቅይኖርበታል፡፡ ማስረጃ ለመስጠትወደአሜሪካ የሚመለስ ከሆነ የዲፕሎማት ያለመከሰስ መብትእንደሌለው ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በጣም ከባድ በሆነ ወንጀል ክስምክንያት ምንም አይነትአስተያየት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አቃቤ ህግ በኩል አያገኝም። ያለመከሰስ መብቱእንደማይሰራ እናክስ ተመስርቶበት ወደ ፍትህ አካል ከመቅረብ እንደማያመልጥ ሊታወቅ ይገባል፡፡ገብረስላሴ አንድ ጊዜ በዩኤስ አሜሪካ ከተገኘእና ያለመከሰስ መብቱ ተነስቶ ጉዳዩ ፍርድ ቤትየሚታይ ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት ችሎት ከመቅረቡ በፊት ወዲያውኑ በቁጥጥር ስርውሎ ካለምንምዋስትና በቀጥታ ወደ ዘብጥያ ሊወርድ እንደሚችል ሊገነዘብ ይገባል፡፡
ሶሎሞን ገብረስላሴ እና የወያኔ አለቆቹ ከፍተኛ የሆነ የሲቪል ህግ ያለበትን እና አስከ አሁን ድረስበህይወታቸው አይተውትበማያውቁት የፍትህ ችሎት ላይ ይገለገላሉ የሚል ከጥርጣሬ የዘለለእምነት አለኝ፡፡ በገብረስላሴ ድርጊት ምክንያት በሰውህይወት እና ንብረት ላይ ይደርስ የነበረውንጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት የወያኔ ኤምባሲ እና ገዥ አካል ተጠያቂ ሊያደርግየሚችልየረዥም ጊዜ የፍርድ ሂደት ሊኖር ይችላል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ በሲቪል ጉዳዮች ላይ የሚታየው እናየሚሰጠው ብይንየመረጃ መለኪያ መስፈርቱነ ባገናዘበ መልኩ በአብዛኛው በሚቀርቡትማስረጃዎች ላይ መሰረት ተደርጎ ሲሆን ይህንንምለማሳካት ከባድ አይደለም፡፡
አብዛኞቹ አገሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማድረግ ስምምነት አድርገው ዲፕሎማት ልከውበመተባበር ከሚሰሩባት ሀገር ላይየተላከው ዲፕሎማት ወንጀል ሰርቶ ከዚያች ሀገር በመሸሽአምልጦ ወደ ሀገሩ የመጣን ዲፕሎማት በሀገራቸው ህግ መሰረትየሚቀጡ መሆኑን ማስተዋልአስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ባሉት የወያኔ አለቆቹ ቅጣትሊጣልበትእንደማይችል ጥርጥር የለውም፡፡ ይልቁንም የወያኔን ኤምባሲ ከጠላት ለመከላከል ባደረገውጀግንነት በወሮበላጓደኞቹ የበለጠ እንደሚወደስ እና ጀግና እንደሚባል መገመት ይቻላል፡፡
አገሮች እነርሱን በውጭ አገር ሄዶ ሊወክላቸው የሚችለውን ዲፕሎማት ለመምረጥ በአገሪቱ ካሉትየመንግስት ሰራተኞችመካከል በደረጃው እና በትምህርት ዝግጅቱ እና ብቃቱ ላይ በመመስረትእንዴት እንደሚመርጡ እና ለምንም የማይሆን የወሮበላዲፕሎማት ለምን መርጠው እንደማይልኩየእራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው፡፡ እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች በዲፕሎማትነትተወክለውሲሄዱ ምን መስራት እንደሚጠበቅባቸው እና የሄዱበትን ሀገር ህጎች እና ደንቦች ማክበር ብቻምሳይሆን የእራሳቸውንአገር ክብር ሊያዋርዱ ከሚችሉ ነገሮች እራስን ንጹህ በማድረግ በጥንቃቄመራመድ እና በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ህዝቡ የእራሱንፍርድ መስጠት እንዲችል መሰረት እንዲያዝዕድሉን መስጠት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
ዲፕሎማቶች ወንጀለኛ ከሆኑ የወሮበላ አፋኝ ስርዓቱ ታማኝ ሎሌዎች የሚመረጡ ከሆነ ገብረስላሴየሰራውን የመሰለ እኩይምግባር የተንጸባረቀበት ዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስለሆነምወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግንወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀውአትችልም።
ገብረስላሴ በመግደል ሙከራ ምክንያት የተባረረ መሆኑ እውነት ነው፡፡ ሆኖም ግን ህጉ ብቻ ነውእርሱን ነጻ ሊያደርገውየሚችለው፡፡ በአገሮች መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነትበማስመልከት የ1961ዱ የቬና ስምምነት አንቀጽ 31የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ ”አንድየዲፕሎማት ወኪል የሆነ ሰው ከሚቀበለው አገር የወንጀለኛ ህግ ያለመከሰስ መብቱንተጎናጽፏል“ይላል፡፡ ወደድንም ጠላንም የህግ የበላይነት ማለት ሌላ ሳይሆን እንደዚህ ነው፡፡
አንደው በነገራችን ላይ….
“በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በሶማሌ ሚሊሻዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችልአስጠነቀቀ“
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 15/2014 ሬውተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት የዩናይትድ ስቴትስኤምባሲ የሚስጠንቂያ መግለጫ ሰጥቷልበሚል የሚከተለውን ዘገባ አስነብቧል፣ “በቦሌ በሚገኙየምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶች፣ የእምነት ቦታዎች፣ የገበያአዳራሾች እና ታላላቅ የመገበያያቦታዎች ሌላ ማስታወቂያ እስካልተሰጠ ድረስ የአሜሪካ ዜጎች እንዳይደርሱ መራቅአለባቸውምክንያቱም እነዚህ ቦታዎች ሊከሰቱ በሚችሉ በአሸባሪ ቡድኖች የጥቃት ኢላማ ውስጥ ናቸው“ይላል፡፡ ሬውተርስበተጨማሪም እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰንዝሯል፣ “የኢትዮጵያ ባለስልጣኖችባለፈው ዓመት መጫረሻ አካባቢ አልሻባብ በአዲስአበባ ከተማ ጥቃት ለመሰንዘር የአውጠነጠነውአስከፊ የሆነ የአጥፍቶ መጥፋት የሽብር አደጋ እንዳለ መረጃ ከደረሰው በኋላየደህንነት ኃይሉበተጠንቀቅ ላይ መሆኑን“ ጠቁሞ ነበር፡፡
ይቅርታ አርጉለኝና ፣ ይኸ አስደንጋጭ ዜና ከተሰማ በኋላ የወያኔ ገዥ አካል እንደገና ሶማሊያንለመውረር እያደረገ ያለው ዝግጅትአለ ማለት ነውነው? እብደት ወይስ ብልሀት!? የዩኤስ ኤምባሲማስታወቂያ ኢትዮጵያ እንደገና ሶማሊያን እንድትወር የቀረበሀሳብን የመሞከረያ/መገምገሚያየዳግም ወረራ ወሬ ማናፈሻ ዘዴ ነውን? ዓላማው ይህ ከሆነ ሁሉም ነገር ሁሉ ፍጹምውድቀትመሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፈው ሴፕቴምበር 23/2014 ከወያኔ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመጠንያለፈ ክብካቤ ሲያደርጉመታየታቸው እና በቪዲዮ ክሊፕ መለቀቁ ስለታሰበው ወረራ በትክክልእንድጠረጥር አድጎኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከዚህ ጉዳይጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ ሲሉተደምጠዋል፣ “…እኛ [ከወያኔ የልኡካን ቡድን አባላት ጋር] ሰላም ማስከበር እናበሰላማዊመንገድ የግጭት አፈታትን በሚመለከት አሰራሮቻችንን በማሻሻል እንዴት ውጤታማ በሆነ መልኩመፍታት እንዳለብንተወያይተናል፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከዓለም ከማንኛውም ሀገር የተሻለችትሆናለች – ሰላምን ከማስከበር አንጻር ከብዙዎቹአንዷ ናት፣ በጣም መጥፎ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜእና ግጭትን በማስወገድ ረገድ ከዓለም ውጤታማ የሆነ የውጊያ ኃይል ያላትናት…“ በቅርብ ጊዜየተደረገው ማስታወቂያ የማይቀር የአሸባሪዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል እና ሌላኛው ጫማየወደቀመሆኑን የሚያመላክት ነገር ነውን?
ወደ ኋላ መለስ በማለት እ.ኤ.አ በ2006 አጋማሽ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ህዝብ ላይ ሙሉአስደንጋጭ እና አስከፊ የጦርነት ጥሪከማስተላለፉ እና ታንኮቹ የሞቃዲሾን ከተማ ከመውረራቸውእና ከመርመርመርሳቸው ሁለት ወራት ቀደም ብሎ አልሻባብ እናጂሀዲስቶች በኢትዮያ ላይ ጥቃትለመሰንዘር እየተባለ ብዙ ዲስኩሮች ተደርገው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 “ጂሀዲስቶችእየመጡነው/Jihadists are coming“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ ጦርነቱ ከመካሄዱበፊት ይደረግ የነበረውየፕሮፓጋንዳ ስራ በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር14/2006 የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች የቀድሞ እረዳትዋና ጸሐፊ የነበሩት ጃንዳይፍሬዘር እንዲህ የሚል ውንጀላ ሰጥተው ነበር፣ “የዲፕሎማቲክ እና የደህንነትባለስልጣኖችየእስልምና ህብረት ተዋጊዎች ከሌላው ወገን እገዛ ለማግኘት እና ከእነርሱ ጎን መሰለፍ እንዲችሉበኢትዮጵያ ላይጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ“ የሚል ውንጀላ አሰምተው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር27/2006 በስተሰሜን በኩል በ90 ማይሎችርቀት ላይ የምትገኘውን ሰትራቴጂካዊየሆነችውን የጆሀርን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የመለስ ዜናዊ ተዋጊ ኃይሎች ወደሞቃዲሾየሚያቃርበውን በረሀ መውረር ጀምረው ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ የእስላማዊህብረት ኃይሎችበኢትዮጵያ ላይ “ተጨባጭነት ያለው የደህንነት አደጋ ደቅነዋል” በማለትየወረራውን አስፈላጊነት እና ፍትሀዊነት አጸደቀች፡፡ይህንን ጉዳይ በማስመልከት የዩናይትድ ስቴትስየመንግስት መምሪያ ቃልአቀባይ የነበሩት ጎንዛሎ ጋሌጎስ እንዲህ ብለው ነበር፣“ኢትዮጵያበሶማሊያ እየተደረገ ባለው የመሻሻል እድገት ላይ በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ የደህንነት ስጋትተደቅኖ እንዳለ እናህጋዊ እውቅና ያለው የሶማሊያ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት በጠየቀው እርዳታመሰረት ኢትዮጵያ ድጋፏን እየሰጠች ነው፡፡“
ሶማሊያን የመውረር ዕቅድ በተግባር ለማዋል እየተሰራ ስለመሆኑ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እውነትለመናገር ይህ አካሄድአሁንም ቢሆን የሚፈይደው ነገር ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እ.ኤ.አኦክቶበር 8/2008 “በሶማሊያ የመለስ ዜናዊየሰላም አስከባሪነት ሸፍጥ ፍጻሜ/The End of Pax Zenawi in Somalia” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ላይ እንዲህየሚልጽሑፍ አስነብቤ ነበር፣ “እውነተኛው ጉዳይ ሲታይ ሶማሌዎች በመለስ ዜናዊ ወይም በሌላ በማንምግለሰብ ወይም ቡድንበኃይል በሚደረግ ተጽዕኖ ሰላም ማምጣት አይችሉም ፍላጎትም የላቸውም፡፡ ሶማሊዎች እና ሶማሊዎች ብቻ ናቸውየእራሳቸውን ችግሮች መፍታት የሚችሉት፣እናም ይህንን በሚጻረር መልኩ የሚደረጉ ጣልቃገብነቶች ሁሉ አንድም የለየላቸውውሸቶችናቸው፣ አለያም ደግሞ ምንም ባለማወቅ የሚደረግ አሳዘኝ የሆነ የዋህነት ነው፡፡“
ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀውአትችልም።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment