Saturday, February 22, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠለፍ እና ወያኔ


February 21, 2014
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ መጠለፉን ተከትሎ የአየር መንገዱ ተጠቃሚዎች ቁጥር ይቀንሳል ተብሎ ይገመታል። ይህን የተረዱት የወያኔ ሹማምንት መክረው ዘክረው የደረሱበት ስልት ቢኖር የረዳት አብራሪውን ቤተሰቦች በማስፈራራትና በማግባባት ረዳት አብራሪው አእምሮው የታወከ “እብድ” እንደሆነ እንዲናገሩ ማድረግ ነው።
የረዳት አብራሪው እህት “ወንድምሽ ጭቅላቱን ያመው ነበር ብለሽ ከተናገርሽ በንጻ ይለቀቃል” የሚል ምክር በተላኩ የደህንነት ሰዎች እንዲደርሳት የተደረግ ሲሆን ሌሎችም የቤተሰቡ አባላት እሷ የተናገረችውን እንዲደግፉ ወያኔ ጫና እያደረገባቸው ነው።
በዚሁ መሰረት ጫና ተደርጎባችው ይሁን የብአዴን አባል በምሆናቸው ምክንያት ዶ/ር እንዳላማው የተባሉ የረዳት አብራሪው ወንድም ቪኦኤ ላይ ቀርበው ምንም እንኳን ወንድማቸው የአእምሮ ሁከትም ሆነ ጭንቀት እንዳለበት እሳቸው ባያውቁም እህቱ ያለችውን ግን ሙሉ ለሙሉ እውነት ነው ብለው ደግፈዋል። (ወይንም እንዲደግፉ ተደርገዋል)።
እንደተለመደው በቪኦኤ በኩል “ረዳት ፓይለቱ አእምሮው የታወከ፣ እብድ ነው” የሚለውን ዜና የሰራው ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማእግዜር መሆኑ የዘገባው መልዕት በወያኔዎች እንደተጠነሰሰ ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን እንደ ወንጀለኛ እንዳይታይና ጥገኝነትም እንዲሰጠው በሚል የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
Ethiopian Airlines flight hijacked by it's pilot

Thursday, February 20, 2014

መከላከያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?


February 20, 2014
ከበላይ ገሰሰ
Addera5021@yahoo.com
ህወሓት ደርግን ማሸነፍ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን ማሸነፍ ማለት ነው ብሎ ስለሚያስብ ተግባሩ ሁሉ የንቀት፣ የማንቋሸሽና የማዋራድ ስራ እየፈፀመ ይገኛል። ሌላውን ትተን ጥቂት የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑትን የህወሓት መሪዎች የግንጠላ አጀንዳቸውን ይዘው በረሃ የሸፈቱበት ቀን ልክ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ “ደደቢት ሂዳችሁ ታገሉሉኝ” ብሎ ወክሎ የላካቸው ይመስል “እኛ ታግለን ነፃ ስላወጣንህ እንደፈለግን እናደርጋሃለን” በማለት ዓይን አዉጣ በሆነ መንገድ ሰሞኑን “የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ ዳግም ልደት ነው” እየተባለ በመከላኪያ ሰራዊት ታጅቦ በመከበር ላይ ስለሚገኘው የህወሓት አስቂኝ፣ አስገራሚና አሳዛኝ ድራማ የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦችን በአጭሩ እንመልከት።Ethiopian troops belongs to the ruling party TPLF/EPRDF
የህወሓት ድራማ ቁጥር 1.
የህወሓት መሪዎች እናስተዳድራለን የሚሉት 90 ሚሊዮን የኢ/ያ ህዝብ ነው እየገዙ ያሉት። ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ጨምሮ ካድሬዎቻቸው፣ አባላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በቀጥታም ሆነ በስውር እየጋጡ ያሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ነው። የገጠሩን ትተን በሀሪትዋ ዋና ዋና ከተሞች ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ 90 ከመቶ የትግራይ ባለሀብቶች የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን የሚያካሂዱትና ባለቤት የሆኑት በሌሎች ክልሎች ነው። በአጠቃላይ የሀገሪትዋ ሀብት በተለያየ መልኩ የተቆጣጠሩት የህወሓት መሪዎች፣ ካድሬዎችና አጃቢዎቻቸው ናቸው። በመሆኑም በመሬት ላይ ያለው ህዝቡ የሚያውቀው ሐቅ ይህ ሆኖ ሳለ እነሱ የሚሉን ግን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነን” ነው። ልብ በሉ!! ስልጣን ላይ ያሉት እነሱ። ሀገሪቱን የተቆጣጠሩት እነሱ። ሀገሪትዋን እየዘረፉ ያሉት እነሱ። ነገር ግን ነፃ እናወጣለን የሚሉት ህዝብ አንድ ክልል ነው። ታዲያ!! ቆም ብሎ ላሰበውና ላስተዋለው ሰው ይህ መንግስት ከኛ አብራክ የወጣ ኢትዮጵያዊ መንግስት ነው ለማለት ያስችላልን?።
የህወሓት ድራማ ቁጥር 2.
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን ከነባንዴራዋ ከፈጠሩት የታሪክ አስኳል አንዱ መሆኑን ዋቢ የሚያስፈልገው አይደለም። ቢያንስ አንድ ሶስተኛው የትግራይ ህዝብ በመላ ሀገሪቱ ከሌላው ወገኑ ጋር ተሳስሮ፣ ሀብት አፍርቶ፣ ተጋብቶና ተሰባጥሮ በነፃነት ይኖራል። በኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጅ የሌለበት መንደር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሲኖርም እንደ መጤ ወይም እንደ ስደተኛ አይደለም ራሱም ሆነ ሌላው ሰው የሚያስበው “ሀገሬ!! መብቴ!! ነው” በማለት በልበ ሙሉነትና
በመተማመን ይኖራል። በሌላ አነጋገር ህዝቡ ለዘመናት በጋራ የኖሮው በመልካም ጉርብትና ብቻ ሳይሆን በራሱ ፈቃደኝነት በፍቅር፣ በወንድማማችነት፣ በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ባንድ እናት ሀገር ጥላ ስር ተቃቅፎ ባህሪያዊ ዝምድናን በመመስረት ነው። ዛሬ 90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ እሴት አለን የምንለውም ይኸው ነው። ታዲያ!! ይህ ከሆነ ሐቁ የትግራይ ህዝብ ነፃ የሚወጣው ከማን ነው? ነፃ የሚያወጣውስ ማን ነው? እውነት ለራሱ ነፃ
ያልወጣና የሻዕቢያ ሎሌ የሆነውን ዘራፊና ከሃዲ ድርጅት የትግራይ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱ ለታላቁ ህዝብ ውርደትና ሀፍረት አይሆንም ወይ? ለመሆኑ ባድመን ጨምሮ የትግራይን መሬትና ህዝብ የተደፈረው በሀይለ ስላሴ ግዜ ነውን? በሀይለ ስላሴ ስርዓት በትግራይ ምድር ሰው እንደ አራዊት በአደባባይ ተደብድቦስ ያውቃልን? ሀገርን እያፈረሱ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱስ የትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም መጠበቅ ማለት ነውን? በኢትዮጵያ ደረጃ ትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ፍትሕ ሳይረገጋጥ በትግራይ ብቻ ትክክለኛ ለውጥ ሊረጋገጥ ይችላል ወይ? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪና መድህን ቢሆን ኖሮ ህዝቡን ከሻዕቢያ ወረራ ያዳነው ማን ነው? እናንተ የትግራይ ነፃ አውጪ ነን ትላላችሁ ነገር ግን ሌሎች ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰቦችስ ማን ነፃ ያውጣቸው?
አዎ!! ይህ ዓይነቱ ድራማና ጥያቄ ላለፉት ሶስት ዓሰርተ ዓመታት እንቆቁልሽ ሆኖ የቆየና ገና በሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዘንድ በሆድ ውስጥ ታምቆ አንድ ቀን ሊፈነዳ የተቃረበ እሳተ ጎመራ መሆኑን አልጠራጠረም። ከላይ ለተጠቀሱት ጥያቄዎች ህወሓቶች መልስ ይሰጡኛል ብዬም አልጠብቅም። “ከኛ በላይ ወንድ የለም። ተልባ ቢንጫጫ በአንድ መውቀጫ። እኛ እንብላ እነሱ ይጩኹ። እኛ እንግዛ እነሱ ያልቅሱ። ያበጠው ይፈንዳ!! ብለው በንፁኃን ደም የሰከሩ፣ በፍቅረ ንዋይ ዓይናቸው የታወሩ፣ በቂም በቀል አእምሮዋቸው የደነዘዙና በጠባብነት ሻማ የተሸበቡ ካድሬዎችና መሪዎች ዛሬ ዊስኪ እየተራጩና ጮማ እየቆረጡ የልደት በዓላቸውን ቢያከብሩ ብዙም አዲስ ነገር አይደለም።
የህወሓት ድራማ ቁጥር 3.
የህወሓት መሪዎች ህዝቡን ለማታለል ከሚሰሩት ድራማ አንዱ በሀገሪትዋ ላይ ሕገ መንግስት፣ መድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ነፃ የመከላኪያ ኃይልና ፍትሕ መኖሩን ለማስረዳት ይሞክራሉ። እነዚህ መሰረታዊ መርሆዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ድርጅት ሞኖፓላዊ ስልጣን ለመጠበቅና ለማገልግል ሲባል ሌላ ቀርቶ ሰሞኑን የህወሓት መሪዎች ልደት ለማከበር እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከሚከተሉት ጭብጦች መረዳት ይቻላል።
  • ሕገ መንግስት አለ ይሉናል። ነገር ግን በሕገ መንግስቱ የሰፈሩ መብቶች ሌላ ዜጋ እንዳይጠቀምባቸው በተግባር ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ በነፃ መደራጀት ይፈቅዳል በነፃ መንቀሳቀስ ግን በሽብርተኝነት አዋጅ ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ይፈቅዳል ነገር ግን በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የብዙሓን መገናኛ አውታሮች በአንድ ድርጅት በሞኖፓል ተይዟል። የፃፈ ወይም የተናገረ ዜጋ ሁሉ ሰፈሩ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ሆኗል። ሕገ መንግስቱ ምርጫ ይፈቅዳል ነገር ግን የምርጫው መወዳደሪያ ሜዳ ተዘግቷል። በአጠቃላይ አንድ ድርጅት ራሱ ሕግ አውጪ፣ ራሱ ሕግ ፈፃሚ፣ ራሱ ገዳይ፣ ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ ዳኛ የሆነበት ስርዓት ነው ያለው።
  • በሀሪቱ መድብለ ፓርቲ ስርዓት አለ ይሉናል። ነገር ግን አውራ ፓርቲ ወይም ልማታዊ መንግስት በሚል ፓሊሲ ትርጉም ያለው ተቀናቃኝ የፓለቲካ ድርጅት እንዳይበቅል በሩ ተዘግቷል። በሕገ መንግስቱ ላይ አንድ ፓርቲ ከሌሎቹ ፓርቲዎች የበለጠ መብት እንዲኖረው ወይም በአውራ ፓርቲነት የሚፈርጅ አንቀፅ የለም። ነገር ግን ህወሓት ከሌሎቹ የተለየ መብት ያለው የበኩር ልጅ በመሆን የሀገሪትዋን ገንዘባዊ፣ ተቋማዊ፣ ማተሪያላዊና ሰብኣዊ ሀብት በቀጥታም ሆነ በተለያየ መልክ በመጠቀም በዓሉን ሲያከብር እናያለን። ሌላው ሀገር በቀል ኢትዮጵያዊ ድርጅት ያልተሰጠው መብት ለህወሓት ግን ከደደቢት በረሃ በመምጣቱና የመከላኪያ ሰራዊት ከጎኑ ስላሰለፈ ብቻ ሀገርንና ህዝብን እንደፈለገ እንዲንድ፣ እንዲዘርፍ፣ እንዲገድልና እንዲያፍን መብት ተሰጥቶታል።
  • መከላኪያ ሰራዊት ከፓለቲካ ነፃ ነው፣ የሕገ መንግስት ዘብ ነው፣ የህዝብ ሰራዊት ነው፣ የልማት ሰራዊት ነው፣ ወዘተ ይሉናል። ነገር ግን በተግባር ሲታይ የአንድ ድርጅት ህወሓት ጠበቃና አጃቢ እንጂ የህዝብ ወገንና መድህን ሲሆን አላየንም። ለምሳሌ ሰሞኑን እንዳየነው ሁሉ የመከላኪያ ሰራዊት ሳምንት በሚል ሽፋኝ እየተካሄደ ያለው ሰልፍና ኤግዚቪሽን ሆን ተብሎ ከህወሓት ልደት ጋር የተያያዘ እንዲሆን ተደርጓል።
“አትረፍ ያለው በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል እንዲሉ” የትግራይ ህዝብ ላለፉት አርባ ዓመታት ያሳለፈውን መከራና ስቃይ እንዳይበቃው ዛሬም ከጀርባው አልወረዱም። እንደ ህዝብ መከበር ሲገባው በአንፃሩ ህወሓት ከሕግ በላይ በመሆን አማራጭ መንገዶችን በመዝጋት የአንድ ድርጅት አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በተለይም የትግራይ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ!! ድርጅትና ግለ መሪዎች አላፊ ናቸው። ህዝብና ሀገር ግን ነባሪ መሆናቸውን አምነን ህዝባችንን ከጅብ ምንጋጋ እንዲላቀቅ እጅ ለእጅ ተያይዘን መነሳት አለብን እላለሁ። ዋስትናችን፣ መድህናችንና ጋሻችን አንድ ድርጅት ሳይሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን አማራጭ የሌለው የህልውና ጥያቄ ነው። ስለዚህ አንድ ድርጅት ወይም ግለ ሰቦች መምረጥ እንችላለን ነገር ግን አንዲት እናት ሀገር ነው ያለችን ሌላ አማራጭ የለንም።

Tuesday, February 18, 2014

ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው - ከዚያስ? “ኢህአዴግ የተጭበረበረ ሪፖርት አቅርቦ” ነበር

http://www.goolgule.com/world-bank-investigated-eprdf-whats-next/

ኢህአዴግ "አልመረመርም፣ አልበረበርም" በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡

ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች "የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ ሰለባዎችና ክሱን የመሰረቱት ክፍሎች በሚኖሩበት ቦታ በመገኘት ነዋሪዎችን በተናጠል ለማነጋገር እንፈልጋለን" በማለት ኢህአዴግን እንደሞገቱት አስታውቀዋል።

ኢህአዴግ በልማትና በህዝብ ስም የሚያገኘውን ከፍተኛ የዕርዳታ ገንዘብ የጦር ሃይሉን ለማደራጀት፣ የደህንነትና የፖሊስ ሃይሉን ለማስታጠቅና ርዳታ በሚለመንባቸው ዜጎች ላይ የተለያየ ወንጀል ፈጽሟል፣ አሁንም እየፈጸመ ነው በሚል መወንጀሉ ይታወሳል።
http://www.goolgule.com/world-bank-and-eprdf/

የምርመራው መነሻ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በቀድሞው ጠ/ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ፣ የህወሃትና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝና በየደረጃው ያሉ አስፈጻሚዎች በጋምቤላ ክልል የተከናወነው የጅምላ ጭፋጨፋ ነው። በወቅቱ የተካሄደው ጭፋጨፋ ከ400 በላይ የተማሩ የአኙዋክ ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ዓለም አቀፋዊ ሪፖርቶችና የጉዳዩ ሰላባዎች ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ነው። አቶ መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን የክስ ማስረጃ ተቀብሎ ክስ እንዲመሰረትባቸው ከድምዳሜ መድረሱም ይፋ ሆኖ ነበር። ኢህአዴግ በዚሁ ፍርድ ቤት ላይ የአፍሪካ መሪዎችን የማስተባባርና የፍርድ ቤቱን አካሄድ ማውገዝ የጀመረው አቶ ኦባንግ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አቶ መለስ ላይ የመሰረተው ክስ እንዲከፈት መወሰኑን ተከትሎ እንደሆነ በወቅቱ ከየአቅጣጫው አስተያየት የተሰጠበት ጉዳይ ነው።

ከዚህ "ዘግናኝ" እንደሆነ ከሚነገርለት ጭፍጨፋ በኋላም በጋምቤላ ሰፋፊ ለም መሬትን በኢንቨስትመንት ስም ነዋሪዎችን በሃይል እያፈናቀለ በመሸጡ ኢህአዴግ ይከሳሳል። በተለይም የኦክላንድ ተቋምና (Oakland Institute) ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ኢህአዴግ በስድብና "የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መንገድ ተጻራሪዎች፣ ርዕዮተ ዓለሙ ላይ የተነሱ፣ አይኗ እየበራ ያለችውን ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ወደኋላ ለመጎተት ልዩ ተልዕኮ ያላቸው፣ የነፍጠኛውን ስርዓት መልሶ ለመትከል የሚሰሩ፣ ጸረ ልማቶች፣ ወዘተ" በማለት ቢያጣጥላቸውም ቀን ጠብቀው ስራቸውን እየሰሩ ስለመሆናቸው እየተነገረ ነው።
http://www.goolgule.com/smne-published-amharic-report/

ጎልጉል ጥቅምት2፤ 2005 ዓም /October 12, 2012/ ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ላይ መውደቁን፣ ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ፣ ዓለምአቀፉ ሁሉን ያካተተ የልማት ተቋም /Inclusive Development International (IDI)/ የተባለውን ተቋም ጠቅሰን “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ" በሚል ርዕስ መዘገባችን ይታወሳል።
http://www.goolgule.com/eprdf-to-lose-600-million-dollars/

ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ማስረጃ በመያዝ፤ በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ በመሰብሰብ ተጠያቂ የሚያደርገው IDI ከሰለባዎቹ ውክልና የተሰጠው ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆም ነበር፡፡

የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ ተመልክቷል። ዝርዝሩ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
http://www.goolgule.com/eprdf-to-lose-600-million-dollars/

አቤቱታው ከቀረበ በኋላ ሁኔታውን ለማጣራትና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያመች ዘንድ ኢንስፔክሽን ፓናል በኢትዮጵያ በመገኘት ምርመራውን አካሂዶ ነበር፡፡ በክሱ መሠረት ፓናሉ በእርግጥ “የዓለም ባንክ ለልማት ሥራዎች የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ ክልል የሚኖሩትን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በመጣስ ላይ” እና ለደኅንነትና ወታደራዊ ጥቅሞች ላይ አውሎታል በማለት የምርመራውን ውጤት የዓለም ባንክ ቦርድ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቀረበ፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የውሳኔውና ሃሳብ አስመልክቶ “ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ” በሚል ሐምሌ 11፤ 2005ዓም /July 18, 2013/ በዘገብንበት ወቅት ከውጪ በሚመጣ ዕርዳታ ላይ ህልውናው የተመሰረተው ኢህአዴግ ገመዱ እየከረረበት መምጣቱን ጠቁመን ነበር፡፡
http://www.goolgule.com/world-bank-approved-a-full-investigation/

ኢህአዴግ የዓለም ባንክ ቦርድ ውሳኔውን እንዳያስተላልፍ የተለያዩ የውስወሳ (ሎቢ) ሥራዎችን ሲሰራ እንዲሁም የዓለም ባንክ የራሱን ማጣራት እንዳያደርግ ለማደናቀፍ ሲሞክርና ሲከላከል አምስት ወራት አስቆጠረ፡፡ በመጨረሻም ሐምሌ 11፤ 2005ዓም (July 18) ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከአዲስ አበባ፤ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በመሆን የዓለም ባንክን አመራሮች ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው እያለ ባንኩ ከአንድ ቀን በፊት ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ። ውሳኔው ባንኩ በራሱ ገንዘብ ማንም ሊያዝበት እንደማይችል ያሳየበትና ለኢህአዴግም እጅግ አሳፋሪ ውሳኔ መሆኑ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው ዓለምአቀፉ ሁሉን ያካተተ የልማት ተቋም Inclusive Development International (IDI) እና ሌሎች ክፍሎች አስተያየት ሰንዝረው ነበር። የዜናው ዝርዝር እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
http://www.goolgule.com/world-bank-approved-a-full-investigation/

ከዚህ ውሳኔ በኋላ የኅልውናው ጉዳይ ያሰጋው ኢህአዴግ የባንኩ መርማሪ ቡድን ሙሉ ምርመራ እንዳያካሂድ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቶ ነበር፡፡ ምርመራው ተካሂዶ ኢህአዴግ በእርግጥ ከዓለም ባንክ የሚሠጠውን ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ ማዋሉን ቡድኑ ካረጋገጠ፤ ኢህአዴግ በትንሹ 600 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያጣ፣ ጉዳቱ ከከፋም እስከ ቢሊዮኖች እንደሚደርስ ጎልጉል በዚሁ ዜናው ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።
http://www.goolgule.com/world-bank-approved-a-full-investigation/

ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሁለት ሳምንት በፊት ላይ ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ የነበረው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ሥራውን በትክክል እንዳያካሂድ ኢህአዴግ የራሱን “የተጭበረበረ ሪፖርት አዘጋጅቶ” እንደጠበቃቸው ለጎልጉል መረጃ ደርሶታል። በዚሁ ሪፖርት መሰረት "ችግሩ ካለበት ጋምቤላ ክልል መሔድ አያስፈልግም" በማለት ኢህአዴግ የባንኩን መርማሪ ቡድን ተከራክሮ ነበር። የምርመራው ቡድን አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት አገር ጥለው የኮበለሉትን የቀድሞ የጋምቤላ ክልል መሪ አቶ ኦሞት ኦባንግን የተኩት አዲሱ ፕሬዚዳንትም ረዳቶቻቸውን በመያዝ አዲስ አበባ ተገኝተው ኢህአዴግ የያዘውን አቋም "እኛን እመኑ፤ ነዋሪውን ማነጋገር አያስፈልግም" በማለት ለዓለም ባንክ ቡድን አባላት አቅርበው ነበር።

ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ከአዲስ አበባ ለጎልጉል እንዳሉት ሶስት ቀን የፈጀ ክርክር ከተደረገ በኋላ የዓለም ባንክ መርማሪ ቡድን በቅድመ ሁኔታ ጋምቤላ የተፈቀደለት ቦታ ብቻ እንዲሄድ ከስምምነት ላይ ተደረሰ። ኢህአዴግ ባዘጋጀው “የተጭበረበረ ሪፖርት” ላይ እንደገለጸው አስቀድሞ ሰፈራን የሚያካሂደው የጤና አገልግሎት፣ ትምህርት ቤት፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ መንገድ፣ የመኖሪያ ቤትና አስፈላጊ መስረተ ልማቶችን እንዳሟላ በስፋት ዘርዝሮ ነበር። በተመረጡት ቦታዎች ምስክርነት እንዲሰጡ የራሱን ሰዎች አዘጋጅቶ እንደነበርና በእድሜ የገፉ አባቶችና እናቶች አስተያየት እንዳይሰጡ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ነበር። በእድሜ የገፉት ሰላባዎች "የመጣው ይምጣ በማለት እውነቱን ለመናገር አይፈሩም፣ በቀላሉም አይደለሉም" የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የሚናገሩት እኚሁ ሰው "የመርማሪው ቡድን በቀላሉ የሚታለል አልነበረም" በማለት የዓለም ባንክ ቡድን በቅርቡ ከሚያወጣው የውሳኔ ሪፖርት በፊት ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል።

ከምርመራው ቡድን አባላት መካከል ሁለቱ በኬኒያና በደቡብ ሱዳን ስደት ላይ የሚገኙ የአኙዋክ ተወላጆችን በግንባር ተገኝተው ማነጋገራቸውን ጎልጉል አረጋግጧል፡፡ በተለይ አንደኛዋ እንስት መርማሪ ጭፍጨፋውን አምልጠው የተሰደዱትን ሰዎች ባነጋገሩበት ወቅት እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲያለቅሱ እንደነበር የሚያስታውሱት የጎልጉል የመረጃ ምንጮች፣ "ኢህአዴግ ለማጭበርበር ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት፣ የመርማሪዎቹ ቡድን አስፈላጊው መረጃ እንደነበረው፣ ጉዳዩን አስቀድመው ለዚህ ሂደት እንዲበቃ ያደረጉት ክፍሎች የያዙት እውነትና ውክልናውን ወስዶ የክስ ማመልከቻውን ያዘጋጀው ተቋም በቂ ልምድና ሚዛን የደፋ ተግባር ያከናወነ በመሆኑ ኢህአዴግ በተለያዩ ጊዜያት የተዘገቡት ኪሳራዎች ይደርስበታል፣ አሊያም በቀድሞው መንገድ የመቀጠሉ ጉዳይ አሳሳቢ ይሆናል" ሲሉ ግምታቸውን ሰጥተዋል።

ከተለያየ አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ያለው ኢህአዴግ፤ አሜሪካ እንደ ቀድሞው ባዶ ቼክ እንደማትሰጥና ካሁን በኋላ ሁኔታዎችን እየመረመረች ገንዘብ እንደምትለቅ መወሰኗ ይህንንም በህግ ማጽናቷ በቅርቡ ሊያካሂድ ካሰበው “ምርጫ” አኳያ የሰሞኑ ራስ ምታት ሆኗል፡፡ ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በአውሮጳውያኑም ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ባለበት ባሁኑ ወቅት ኢህአዴግ ፊቱን ወደ ቻይና የማዞር አዝማሚያ ሊያሳይ የፈለገ ቢመስልም የማያዋጣው እንደሆነ በስፋት ይታመናል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አቅጣጫው የጠፋበት አካሄድና ውጥረት በአገዛዙ ውስጥ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ፈጥሮ ችግሩን ሊያባብስ ይችላል እየተባለ ባለበት ወቅት የዓለም ባንክ ከዕርዳታና ድጎማ ጋር በተያያዘ የሚሰጠው ውሳኔ ሊፈጥር የሚችለውን ውጥረት ለመገመት ኢህአዴግ ምርመራው እንዳይካሄድ የተጠቀመውን ማደናቀፊያ መመልከቱ ብቻ በቂ እንደሆነ ይታመናል፡፡

የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ለምርመራ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ኢህአዴግ የቀድሞውን የክልሉን መሪ አቶ ኦሞት ኦባንግን በቁጥጥር ስር በማዋል ለሚከሰስበት ጉዳይ መስዋዕት አድርጎ ሊያቀርባቸው ዝግጅቱን አጠናቆ እንደነበር፣ አቶ ኦሞት ከደህንነትና ከቀድሞ ታጋይና የአሁኑ "ልማታዊ ኢንቨስተሮች" ጋር ባላቸው ትስስር የተነሳ መረጃ ደርሷቸው እንደኮበለሉ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
http://www.goolgule.com/the-hunt-for-omot-obang-olum-continues/

በአሁኑ ወቅት አውሮጳ እንደሚገኙ የሚነገረው አቶ ኦሞት ኦባንግ ከዓለም ባንክ ጋር በመገናኘት ከአኙዋኮች ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ አሁኑ ጊዜ ድረስ ለዘመናት የሚያውቁትን ምስጢር ሁሉ ለዓለም ባንክ በማጋለጥ ለራሳቸው ርካሽ የስደተኛ ጉዳይ መጠቀሚያነት ያውሉታል እየተባለ ከቅርብ ወገኖቻቸው ዘንድ ይሰማል፡፡

ኢህአዴግ በየመንደሩና በየክልሉ በተመሳሳይ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና ህገወጥ ተግባራት በተደራጀ መልኩ በማሰባሰብ ዱካውን እየተከተሉ መታገል፣ ዓለም አቀፍ መስመሮችን በመከተል ትግልን ማሳለጥ፣ ኢህአዴግ በሚፈልገው መልኩ ደረጃን ዝቅ በማድረግ አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ አለመግባትና አልሞና አስተውሎ መራመድ የወቅቱ ጥያቄ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ የዓለም ባንክ እዚህ ደረጃ የመድረሱ ዜና የአንድ ቀን ሥራ ውጤት እንዳልሆነ ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ሐምሌ 11፤2005ዓም /July 18, 2013/ “ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ” በሚል በዘገብንበት ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “እኛ በመሠረቱ ልማትን አንቃወምም፤ ሆኖም ግን በልማት ስም የሚሠጠው ዕርዳታ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለመርገጥ የሚውል ከሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ተጠያቂ መሆን ይገባዋል፤ የግልጽነትና ተጠያቂነት ዕጥረት እንዲሁም የሙስና በሽታ እንዳጠቃው በራሱ መሪዎች የሚነገርለት ኢህአዴግ፤ የፈለገውን ነገር እንደፈለገው የማድረግ አምባገነናዊ አሠራሩ ራሱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከተው” በመጥቀስ ድርጅታቸው በጥናትና በዕቅድ ከሚያካሂደው ሁሉን ዓቀፍ ትግል መካከል ይህ አንዱ እንደሆነና “በተጠናከረ መልኩ በመንቀሳቀስ ጉዳዩን ዳር በማድረስ የተጎዱ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን መከራ” እንደሚታደጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ይህንን የዓለም ባንክ ጉዳይ አስመልክቶ ከአንድ ዓመት በላይ ሲዘግብበት የቆየ ሲሆን በየጊዜው የወጡት የዜና መዘርዝሮች ለአንባቢው ግንዛቤ መስጠት ይችሉ ዘንድ በቅደምተከተል አቅርበናቸዋል፡፡

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!
ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!
ጥቅምት 2፤2005ዓም/October 12, 2012
(http://www.goolgule.com/eprdf-to-lose-600-million-dollars/)

“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”
ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል – የካቲት 9፤2005ዓም/February 16, 2013
(http://www.goolgule.com/world-bank-and-eprdf/)

ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ
የማነቂያው ገመድ ከርሯል፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ኦባንግ ሜቶ – ሐምሌ 11፤2005ዓም/July 18, 2013
(http://www.goolgule.com/world-bank-approved-a-full-investigation/)

***********
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Like ·  · 

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል


ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።

ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።

የህወሃት መሪዎች አማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ ወደሥልጣን ከመጡ ቦኋላ የተፈጠረ ሳይሆን ገና በጫካ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በጻፉት የድርጅታቸው የፖለቲካ መረሃግብር በግልጽ እንደተቀመጠው ለትግል ያነሳሳቸውም አማራ ብለው የሚጠሩት ብሄረሰብ እንወክለዋለን በሚሉት ብሄረሰብ ላይ አድርሰዋል በሚሉት የፈጠራ በደልና ቂም እንደሆነ አረጋግጠዋል። ላለፉት 23 አመታት አማራው ከሚኖርበት የራሱ ክልሉ ሳይቀር እንዲፈናቀል ተደርጎ እየደረሰበት ያለው በደል የዚህ የቆየ የወያኔ ቂም በቀል ውጤት መሆኑ ግልጽ ነው።

ሰሞኑን አለምነው መኮነን የተባለ ሆድ አደር የባንዳነት ተግባሩን በመፈጸም በአለቆቹ ፊት ግርማ ሞገስ ለማግኘት እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ እጅግ በወረደና ጸያፍ በሆነ ቃላት ያን ያህል ሲዘባበትበት መደመጡ አማራውን ብቻ ሳይሆን መላውን የአገራችንን ህዝብ አስቆጥቶአል።

በእርግጥ አለምነው መኮንን አማራን በማዋረድ የመጀማሪያው የወያኔ ተላላኪ አይደለም። የህወሃቶቹን ቁንጮዎች ስድብና ዘለፋ ወደ ጎን ትተን በወያኔ የዘር ፖለቲካ አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን ከፍተኛ አመራር እነ እነታምራት ላይኔ ተፈራ ዋልዋና በረከት ስሞን በተለያየ ወቅት ንቀትና ስድባቸውን አሰምተውናል። አለምነህ መኮንን እንደዚያ በወረደ ቃላት አማራውን ሲያዋርድ በስብሰባው አዳራሽ የነበሩ ህወሃት የፈጠራቸው የብአዴን ልጆች በሳቅ ካካታ ሲያጅቡት እንደነበረ እድሜ ለኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ከአዳራሹ ሾልኮ ለህዝብ ጀሮ የደረሰው የኦዲዮ ድምጽ አጋልጦአል።

ሁላችንም፤ እንደምንገነዘበው ወያኔ የገዛ ብሄረሰባቸውን ረግጠው በመግዛት የጥፋት አላማውን እንዲያስፈጽሙለት በራሱ አምሳል ከፈጠራቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን በታሪኩ አንድም ለህዝቡ የቆመ መሪ አፍርቶ አያውቅም። ለራሳቸውና ከአብራኩ ለተገኙት ህዝብ ምንም አይነት ክብር የሌላቸው የብአዴን መሪዎች ጣሊያን አገራችንን በወረረችበት ወቅት ለሆዳቸው ሲሉ ከባዕድ ጋር ተሻርከው ህዝባቸውን ካስጨፈጨፉት ባንዳዎች የከፋ ተግባር በህዝባቸው ላይ እየፈጸሙ ነው።

ወያኔ ለም የሆነውን የአማራ ግዛት እንዳለ የኔ ነው ወደሚለው የትግራይ ከልል ሲወስድ፤ በአማር ክልል ወስጥ በቀሩት ለም ቦታዎች የህወሃት ታማኝ ካድሬዎችን ከያሉበት እያጓጉዘ ሲያሰፍር፤ የአገሬውን አርሶ አደር እያፈናቀለ ለራሱ ታማኞች ለም መሬት እየሸነሸነ ለሰፋፊ እርሻ አገልግሎት ሲያድል አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን አንድም የተቃውሞ ድምጽ አሰምቶ አያውቅም። የብአዴን መሪዎች የወያኔን ተልዕኮ ከማስፈጸም አልፈው በሟቹ አለቃቸው በመለስ ዜናዊ ሥም እየማሉ በአገራችን ኢትዮጵያና በሚያስተዳድሩት የአማራ ህዝብና ክልል የሚፈጽሙት በደል ብዙ ነው። ልክ እንደ ብአዴን የዘረኛውን ወያኔ የጥፋት ፖሊሲ ለማስፈጸም ከሚተጉት አንዳንዶቹ አማራውን ከክልላቸው ለማጽዳት በቤኒሻንጉል፤ በቤንች ማጅና ጉራፈርዳ ወረዳ እርምጃ ሲወስዱና ንብረታቸውን ቀምተው ባዶ እጃቸውን ሲያባርሩዋቸው ብአዴን ቁጭ ብሎ ተመልካች ነበር። ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰነው ዳር ድንበራችን ላይ በተነሳው የባለቤትነት ጥያቄም ላይ የወሰደው አቋም በህዝብና በታሪክ ፊት ውሎ አድሮ የሚያስጠይቀው ነው።

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው ፋሽስቱ ወያኔ በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸመው ያለው አንዱን ዘር ከሌላው ጋር የማጋጨትና በተናጠል ደግሞ እያንዳንዱን ለይቶ የማዋረድና የማጥፋት ተግባር አሁን የተጀመረ ክስተት አይደለም። የቆየና ወያኔ ህዝባችንን ከፋፍሎ ለመግዛት ከመነሻው ሲጠቀምበት የነበረ ስልት ነው። ስለዚህ ወያኔ በራሱና በተላላኪዎቹ አማካይነት ላለፉት 23 አመታት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውና የፈጸመው ግፍ፤ ውርደትና መከራ እንዲያበቃ ሁላችንም እጅ ለ እጅ ተያይዘን መነሳት ይኖርብናል። በወያኔ ከፋፋይ አጀንዳ እርስ በርስ እየተናቆርን የጥቃት ሰለባ የመሆናችንን እንቆቅልሽ ለማስቀረት ከኛ በላይ ሃይል ያለው አይኖርም።

በተለይ ግንባር ቀደም የወያኔ ሰለባ የሆነው የአማራ ህዝብ ወጣት በጫንቃው ላይ ተፈናጠጠው የወያኔን የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚያስፈጽሙትን ከአብራኩ የተገኙ ባንዳዎች ላይ የጥቃት ክንዱን መሰንዘርና ለክብሩ መቆሙን ማሳየት ያለበት ጊዜው አሁን ነው።

በብአዴን ሥር የተሰባሰቡ የአማራ ተወላጆች፤ በመከላኪያ ሠራዊቱ፤ በፖሊስና በደህንነት፤ በወጣት ማህበር፤ በሠራተኛ ማህበርና በተለያየ ሙያ ማህበር ብአዴን ራሱ ያደራጃቸው ሁሉ ለክብራቸውና ለኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ሲሉ ከትግሉ ጎን በመሰለፍ የወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚያካሂደውን ትግል እንዲቀላቀሉ ንቅናቄው ጥሪውን ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
12Like ·  · 

Wednesday, February 12, 2014

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ! (በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት)


February 11, 2014

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡Ethiopian journalist Woubshet Tayemes journalist
ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡
የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡
‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡
ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት›
በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡
ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡
በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡
ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!
የዝዋይን ልጅ ውሃ ጠማው
ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡
ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!
ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!
የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ምንጭ ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ

Ben's Point of View on the Health of EPRDF

Tuesday, February 11, 2014

የሃገራችን ወጣት በዘመነ ወያኔ “በጨረፍታ”


በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ) የካቲት 4 2006
ሁላችንም እንደምናውቀው ከግዜ ወደ ግዜ አሰቃቂነቱ እየጎላ የመጣው የሃገራችን ወጣት የስደት ጉዳይና ለዚህም ዋነኛ መነሾ ስለሆነው በሃገር ውስጥ የሚኖረው የኢትዮጲያ ወጣት ማህበረሰብ እጅግ የከበደ የኑሮ ሁኔታ በጨረፍታ አንዳንድ ነገር ለማለት አሰብኩ።
ለምንድነው ደሃ የሆንነው? ለምንስ ነው ደሃ ሆነን የምንቀጥለው? ለምንስ ነው ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ የመኖር ተስፋው መንምኖ ለህይወት አስጊ የሆነውን ስደት እየመረጠ ያለው? ተብለው ለሚነሱት ጥያቄዎች በርካታ መልሶች ሊነሱ ይችላሉ ነገር ግን ከሚነሱት መልሶች ሁላችንንም የሚያስማማውና ሚዛን የሚደፋው “የዜጎችን መብት አክብሮ የሚያስከብር እንዲሁም መሰረታዊነት ያለው የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ሚዛናዊና ወጥ የሆን የኢኮኖሚ ስርዓት የሚገነባ ሁነኛ መንግስት ማጣታችን ነው” የሚለው ነው። በርካታ የሃገራችን ምሁራንም ሆነ በሞያው የበቃ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች በሃገራቸው የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦችን የሚያመነጩበት መድረክ እንዳይኖር የሚያደርግ ሌት ተቀን የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም ሲል ብቻ የኔ የሚላቸውን ግለሰቦች ከስልጣን ስልጣን እያቀያየረ የሚሾም ጎጠኛ ስርዓት እንደ እርግማን ተጭኖብናል። በዛው ፓርላማ ተብዬ እንኳን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተቃራኒ ሃሳብ እንዳይስተናገድበት ከላይ እስከታች ለሆነው ላልሆነው እጅ ሲያወጡና ሲያጨበጭቡ በሚውሉ የህዝብ ተወካዮች ነን ባይ አስገራሚ ግለሰቦች ሞልተውታል።
የወያኔ መንግስት እንደምንም ተብሎ በተገኘችው ቀዳዳ አንፃራዊ የሆን አማራጭ ሃሳብ ሲቀርብለት የሃሳብ አመንጪውን አካል ዘርና ማንነት በክፉ እየመነዘረ ሰርቶ የሚያሰራና በመጠኑም ቢሆን ሊያስተማምን የሚችል የኢኮኖሚ ስርዓት ተፈጥሮ ወጣቱ ተረጋግቶ ሃገሩ ላይ የሚኖርበትን እድል እያጨለመ የመብት ጥያቄዎችን እያፈነ ወጣቱን ለአስከፊው ስደት እየዳረገው ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ እጅግ የሚያመው ደግሞ ለህይወት አስጊ መሆኑና ምንም አይነት የህይወት ዋስትና እንደሌለበት መዓት ግዜ የሚለፈፍለት የአረብ ሃገራት ስደት ያ ሁሉ ስቃይና ህይወትን የሚያሳጣ መከራ በተሰደዱ ዜጎች ላይ በተጨባጭ እየታየ አሁንም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲጎርፉ ይታያል። ወጣቱም ሃገሩ ላይ ከመኖር ይልቅ ከሞት የማይሻል የስደት አማራጭ ያስደፈረው ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህዝብን አስተዳድራለሁ ብሎ በስልጣን የተደላደለው የወያኔ መንግስት ነው።
ያደጉ ሃገሮች መንግስታት አብዛኛውን ግዜያቸውን የሚያጠፉት የሃገራቸውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ፣ ለሰራተኛው የሚከፈለው የደሞዝ ክፍያና ዝቅተኛ የክፍያ እርከን ላለው የኑሮ ሁኔታ የሚያስኖርና በቂ ስለመሆኑ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል አስተማማኝ የሆን የጤና ሽፋን መቅረቡን ለማረጋገጥ ነው። እንደው ዘለን እነሱን እንሁን ለማለት አይቃጣኝም ነገር ግን የመፍትሄ ሁሉ መጀመሪያ ችግሩን መለየት ስለሆነ ችግሩ አገዛዙ የፈጠረብን መላ ቅጡ የጠፋ የኢኮኖሚ ስርዓት መሆኑን ለመጠቆም ነው። ከዚሁ ጋር አያይዤ አንባቢያንን አንድ ነገር እንዲያስተውሉ የምጠይቀው የሃገራችን አነስተኛው የደሞዝ መጠን ስንት መሆኑን ፣ መጠኑን የሚያውቅ ካለም ከወቅቱ የኑሮ ሁኔታጋ እንዴት እንደሚጣጣም እንዲያሰላስሉ ነው።
የህወሃት መንግስት  ባለስልጣናት ግን ስር ስለሰደደው የስራ አጥነትና ተያይዞ ስለሚመጣው የህይወት መመሰቃቀል ሲጠየቁ “ወጣቱ ስራ ፈጣሪ መሆን አለበት” የሚል መሰረት አልባ ለንግግር የቀለለ ለመተግበር ግን እጅግ የከበድ ብሂል እየተቀባበሉ ያስተጋባሉ።
ከወራት በፊት አቶ ቴውድሮስ አድሃኖም በአንድ የህክምና ዶክተሮች ምረቃ በዓል ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎቹ ሃገራቸውን በፍፁም ጥለው እንዳይሄዱ ሲደሰኩሩ ነበር። እውነታው ሁሉም ግድ ሆኖበት እንጂ ማን ሃገሩን ጥሎ መሄድ ይፈልጋል ነው። በዘመነ ወያኔ እየተንሰራፋ ያለው በትዕቢት የተሞላ የመብት ረገጣ ፣ መረን የለቀቀ የኑሮ ልዩነት ፣ ልጓም ያጣው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት እንዲሁም የስርአቱን ተጠቃሚዎችን እንጂ የማህበረሰቡን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበው የኢኮኖሚ ስርዓት የሃገራችንን ወጣቶች የወደፊት የኑሮ ተስፋና እድል ምን ያህል ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባው ለዚህም የተቀመጠ መሬት የወረደ መፍትሄ እንደሌለ የምናውቀው ገሃድ የወጣ ሃቅ ነው።
የተገኘው ስራ ተሰርቶ እንኳን ኑሮን ለማሸነፍ እንደ አማራጭ የሚታየው የቁጠባ ባህልም ባልተረጋጋውና ጠንካራ መሰረት በሌለው የኢኮኖሚ ስርዓት ምክንያት በሚፈጠረው መላ በሌለው የምንዛሬና የዋጋ ከመጠን ያለፈ ግሽበት ሳቢያ ከጨዋታ ውጪ ሆኗል። ማህበረሰቡ ለአመታት ቆሎ ቆርጥሞ የቆጠበው ገንዘብ ዋጋ እያጣበት ኑሮውን ለእለት ብቻ ካረገው ሰነባብቷል። ወጣቱም ከዛችው ከአነስተኛ ደሞዙ ቆጥቦ የወደፊት ኑሮውን እንዲሁም ቤተሰብ እንዳይመሰርት ይኸው ችግር እንቅፋት ሆኖበታል።
የስርዓቱ አመራሮችና ባለስልጣናትም የደሃውን ህዝብ ገንዘብ በአግባቡ ስራ ላይ ከማዋል ይልቅ ለግል ጥቅማቸው ወደ ውጪ ሃገራት ማሸሸት ስራዬ ብለው ይዘውታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ነፍሰ ጡር ሚስቶቻቸውን ሳይቀር ምዕራባዊ ሃገራት ላይ እየወሰዱ ማስወለድ መጀመራቸው በግልፅ የሚታይ በሃገር ላይ ተስፋ የማጣት አሳፋሪ ስነ ምግባር የተለመደ ሆኗል። ሃገር እንመራለን እያሉ ነገር ግን ወጣቱ ሃገራዊ ስሜቱ እንዲዳብርና ሃገሩ ላይ ተስፋ እንዲኖረው ምሳሌ የመሆንን ሃላፊነት አሽቀንጥረው በመጣል በሃገር የመኩራትን ስሜት እንደሁዋላቀርነት ሲቆጥሩት ማየት እጅግ ያሳዝናል።
መልካም አስተዳደር ከሚፈጥራቸው መልካም እንድምታዎች አንዱ ይኸው በሃገር ላይ ተስፋ ማሳደርን ከሁሉም ሃገርን ማስቀደምን ነው። መልካም አስተዳደር ሰርቶ ያሰራል እንዲሁም የዜጋው ጉዳት ይቆረቁረዋል። ነገር ግን የሃገራችን ጉዳይ የተገላቢጦሽ ነው “መልካም አስተዳደር መስርተናል” የሚሉት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ጭምር አካላቸው እንጂ መንፈሳቸው ሃገራቸው ላይ የለም። የወያኔ ስርዓት ለአመታት እያምታታና የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እንዲሁም በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የሃገራችን ወጣቶች ስደትና ተያያዥ እንግልቶች የተድበሰበሰ ሰበብ ሲሰጥ ቆይቷል። አሁን ግን ወጣቱ የችግሩ ዋና መንስኤ የመንግስት ተብየው ብልሹ አስተዳደርና መሆኑን ተረድቶ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት መታገል አለበት።
አሁንም ቢሆን የወያኔ ስርዓት ካልተወገደ ህዝባችን መቸገሩን ወጣቱም ውድ ሃገሩን እየተወ መሰደዱን አያቋርጥም። የወያኔን ስርአት መወገድ ለችግራችን ሁሉ የመፍትሄ ጅማሮ ቁልፍ እርምጃ ነው

Monday, February 3, 2014

አንድነት – የአማራውን ሕዝብ ክብር የደፈሩና ያዋረዱ አምባገነን ገዥዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!! (መግለጫ)


February 4, 2014
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
«ጉድ ሳይሰማ…» እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስርዓቱ እየተፈፀመበት ካለው ጭቆናና በደል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ፤ አፈናና ስደት፤ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት በተጨማሪም በአምባገነን ገዥዎች እየተዋረደ፣ በአደባባይ እየተሰደበና ሰብዓዊ ክብሩ እየተጣሰ ይገኛል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም ሀገራችን ላይ ያለው ስርዓት ህዝቡን የሚያዋርድ፣ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ስልጣኑን የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ የሌለው ነው፡፡Andenat Party UDJ
ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮች ትከሻውን ያጎበጡት የኢትዮጵያ ህዝብም ስርዓቱን ከነችግሩ መሸከሙ አልበቃ ብሎ መሪ ነን በሚሉት እየተበሻቀጠና ለውርደት እየተዳረገ ይገኛል፡፡
ፓርቲያችን በትኩረት እየተከታተለው ያለውና ሰሞኑን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይና በኢሳት ይፋ የተደረገው የአማራ ክልል ም/ ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን፣ የአማራውን ህዝብ በአደባባይ መሳደባቸውንና ማዋረዳቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መለቀቃቸውና የክልሉ መንግስት ለማስተባበል እንኳ ዝግጁ አለመሆኑ የሚያሳየው ንቀትንና ጥላቻን ብቻ ሳይሆን እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ ትከሻ ላይ ተቀምጠው ፀረ ህዝብ አቋም እንደሚያራምዱ ነው፡፡ ፓርቲያችን የብአዴን/ኢህአዴግ ባለስልጣን በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙትን ክብር የሚነካ አሳፋሪ ድርጊት በቸልታ ሊመለከተው እንደማይችል አስረግጦ ለመናገር ይወዳል፡፡ ፀረ ህዝብ አቋም የሚያራምዱ አምባገነኖችንም ከህዝብ ትክሻ ለማውረድ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል፡፡ አንድነት በቅርቡ በጉራ ፈርዳና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በዜጎች ላይ የተወሰደው የማፈናቀል ተግባር ስርዓቱና የስርዓቱ መሪዎች የፈጠሩት ችግር እንጅ የአካባቢው ሕዝብ የፈጠረው እንዳልሆነ ያምናል፡፡
አቶ አለምነው መኮንን የተባሉት ባለስልጣን የአለቆቻቸውን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ህዝብ «ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፣ ትምክህተኝነቱን ያልተወ፣ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ» ካሉ በኋላ «የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት» በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ለዚች ሀገር ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ክልል ህዝብ ዋጋ በማሳጣትና የሌሎች ጠላት አድርጎ በማቅረብ የማጥላላት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡
ፓርቲያችንም ይህንን አሳፋሪና የዜጎችን ክብር የደፈረ የባለስልጣኑ አባባል በቸልታ የሚታይ ሆኖ አላገኘውም፡፡
ስለዚህ፡-
1. ግለሰቡ በዚህ የተዛባ አመለካከቱ ለአማራ ክልል ህዝብ መሪ ሊሆን ስለማይችል በአስቸኳይ ከፓርቲና ከመንግስት ኃላፊነቱ እንዲነሳና ለህዝቡ ይፋ እንዲደረግ፤
2. ህዝቡን ያዋረደው ባለስልጣን ላይ እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ግን የግለሰቡ አመለካከት የብአዴንና የክልሉ መንግስት አቋም አድርገን የምንወስድ መሆኑ እንዲታወቅ፤
3. አንድነት ፓርቲ ፀረ-ህዝብ አቋም ያለው ግለሰብ ባደረገው የህዝብ ጥላቻ ንግግር (Hate speech) ተነስቶ ለሕግ የሚያቀርብ መሆኑ እንዲታወቅ፤
4. ፓርቲያችን ህዝቡን በማስተባበር በባህርዳር ከተማ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራና ድርጊቱን የማውገዝና እንዲቆም የማድረግ ርምጃ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስለዚህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የክልሉን ህዝብ እየመራው ያለው ብአዴን/ኢህአዴግ ለህዝብ ክብር የሌለው ድርጅት መሆኑን አውቆ ከፓቲያችን ጎን በመቆም እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም

ለሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ በባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የክብር መግለጫ ተበረከተላቸው


February 3, 2014 10:15 am
  • digg
  • 56
     
    Share
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ትላንት ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት መከበር ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት በቅርቡ 93ኛ ዓመታቸውን ላከበሩት ሌተናል ጀነራል ጃገማ ኬሎ የክብር መግለጫ ምስክር ወረቀት እንዳበረከተላቸው የማህበሩ ምክትል ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡1797118_415026495298978_204746632_n


የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ም/ጸሀፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ለፍኖተ ነፃነት የሚከተለውን ብሏል “ሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ታላቅ ተጋድሎ የፈፀሙ ናቸው፤ ማህበራችንም በኢትዮጵያ አንድነት ዙሪያ ስለሚሰራ እንደነዚህ አይነት ጀግኖችን ክብር ይሰጣል፡፡ ለዚህም ነው ለሌተናል ጀረናል ጃገማ የክብር ምስክር ወረቀት የሰጠናቸው፡፡ ”  አያይዞም “የብሔር ግጭቶች እንዳይፈጠሩና  ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው ላይ እንዲያተኩሩ የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡” ሲል ለሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ  ስለተሰጠው የክብር መግለጫ አብራርቷል፡፡
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አመራሮችና አባላት ለሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ በመኖሪያ ቤት በመገኘት የክብር መግለጫ  ምስክር ወረቀት ሲያበረክቱላቸው የአካላቸውን መድከም ተቋቁመው በሙሉ ወኔ ወጣቱ ትውልድ በዘር መከፋፈሉን ትቶ ኢትዮጵያን እንደቀድሞው አንድ ለማድረግ እንዲታገል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ወጣት ጥላዬ ተናግሯል፡፡1624557_415026681965626_2146485222_n
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6173#sthash.jVnhrWOk.dpuf