በዛሬው እለት ሰሚ ያጣው የስደተኞች ጭሆት ከቴል-አቪቭ ወደ እየሩሳሌም ፓርላማ ተዛውሯል ። ለሦስት ቀናት የተዘጋጀው ሰሚ ያጣው የስደተኞች ጭሆት በ እስራእል አሁንም እንደቀጠለ ነው። ከ 100 በሚበልጡ አውቶብሶች ተሰብስበው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰሚ ያጡ ስደተኞች በአሁኑ ስዓት በ እስራኤል ክኔሴት(ፓርላማ) ፌት ለፊት ድማፃቸውን ማሰማት ጀምረዋል። እስካሁን ድረስ መንግስትን በመወከል ማንም እንዳላናገራቸው የገለፀልን የስብሰባው ተካፋይ የሆነውና ለክሊክ-ሐበሽ ፎቶዎችን የላከልን ደሴ ውዱ ሰላማዊ ሰልፉ በ እስራኤል መንግስት መልስ ማጣቱ ነገሩ እንዳሳሰበው ገልፆልናል።
No comments:
Post a Comment