Friday, June 28, 2013

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው


June 28, 2013
ከኢየሩሳሌም አርአያ
ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ “አላማና ግብ” አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ “በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ።” ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..« አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።sebehat nega one of the founders of TPLF
ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ። አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።

ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት


June 28, 2013
ይነጋል በላቸው
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የ…
የሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡
…በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንበርና በነሲብ ነበር እስትንፋሷ ውሎ እሚያድረው፡፡ ሰውዬው የሚፈልገው ሁሉ እዛው ባለበት እየቀረበለትና እንደአንበሣ በብረት አጥር ውስጥ እየኖረ በስልክና በደብዳቤ ሲገዛንና ሲሸጠን ኖረ፤ ፈጣሪ በወደደው ሰዓት ያን የእፉኝት ልጅ ወሰደ፡፡ ጦስ ጥንቡሱ ግን አሁንም እንደገነነ አለ፤ መቃብር ውስጥ ሆኖ በመግዛት መለስ አንደኛ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ይቺ ራዕይ የሚሏት ሀገርን የማጥፋት ተልእኮ በየወያኔው ጭንቅላት ውስጥ ሠርፃ ገብታ እነሱንም እኛንም ዕረፍት ነስታለች፡፡ አዳሜ እየተነሣ “ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት!” ይላል፡፡ “ራዕያቸው ምን ነበር?”ተብሎ ሲጠየቅ በቅጡ የሚመልስ የለም፡፡ የፈረደበት የአባይ የሚሌኒየም ይሁን የሕዳሴ ግድብ አለ፡፡ እሱው መሰለኝ ትልቁ ራዕይ፡፡ በሌሎች ሀገሮች እዚህና እዚያ የተትረፈረፈ የወንዝና የኩሬ ግድብ እኛ ሀገር ሲደርስ ብርቅ ሆኖ ሰውን በመዋጮና በተስፋ ቁንጣን እየገደለ ነው፡፡ ራዕዩ ይሄው ነው፡፡ በተረፈ በሚሊዮኖች ላብና ደም ጥቂት ቅንጡ ሀብታሞችን የመፍጠር ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለብዙ አሠርት ዓመታት ተከፍሎ በማያልቅ ብድር መንገድና ሕንጻ መሥራት ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ይበልጡን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚመስል መልኩ የሀገርን ሀብት ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በማዋል በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና በኮብል ስቶን ሥራ አደራጅቶ ዜጎችን በጥቅም መከፋፈል ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዕይታ ሳይቀር የሚዘገንን የኔቢጤ (ለማኝ)፣ ወፈፌና ሰካራም፣ ብስጩና ግልፍተኛ፣ በረንዳ አዳሪና የዐዋቂና ሕጻናት ሴተኛ አዳሪዎችን በየዋና ዋና ከተሞች በብዛትና በስፋት ማምረት በልዩ ራዕይነት ካልተመዘገበ በስተቀር የመለስ ራዕይ ብሎ ነገር የሚጨበጥ ነገር አላየሁም – በዋና ራዕይነት እንዲመዘገብለት ከተፈለገ ዋናው የመለስ ራዕይ የተከፋፈለችና የደከመች፣ ለኤርትራ በምንም መንገድ የማታሰጋ ጥንጥዬ ኢትዮጵያን በሂደት መፍጠር ነው – ይሄ የሚታየው ብልጭልጭ ነገርና የዕድገት እመርታ የሚመስል የፎቅና የአስፋልት ወይም ሌላ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሁሉ መለስ ሳይወድ በግዱ በሥሩ ባሉ ጥቂት ሀገር ወዳድ ወያኔዎች አማካይነት የተከሠተ – ‹ከሬዲቱ› ለርሱ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን ለማለት ነው- በመለስ የጥፋት ራዕይና በአፈጻጸሙ መካከል እንደሳይድ ኢፌክ ሊቆጠር የሚችል አጋጣሚ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው – መለስ ኢትዮጵያን በማጥፋት ሂደት ተጠምዶ ሳለ ያን ሂደት ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ መስሎ መታየት ወይም ማታለል ስላለበት ለዚያም ሲባል አንዳንድ የሚታዩና የሚጨበጡ ነገሮችን ማድረግ ስለነበረበት በኢትዮጵያዊ ስብዕና ዓለም አቀፍ አመኔታን ለማግኘት ሲል ባልጠበቀው ሁኔታ ከእጁ ሾልከው ክፉ ገጽታውን በጥሩ ቅባት ያዋዙለት አጋጣሚዎች ነበሩ ወይም ናቸው(ለዚህም ይመስላል ብዙ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰው ‹ምትሃት› ተወናብደው የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮ እንዳያውቁ የተደረገውና ዐይናቸው በወያኔ ጥፋት ላይ እንዳያማትር እንዲያውም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የርሱ ነገረ ፈጅ እስከመሆን እንዲደርሱ የተሞከረውና አሁን አሁን ደግሞ እየቆጫቸው መምጣቱን እየተገነዘብን ያለነው…) ፡- በሕክምና አነጋገር ለጉበት የወሰድከው መድሓኒት ኩላሊትህን ሊጎዳ ይችላል – ኔጌቲቭ ሳይድ ኢፌክት፡፡ ለራስ ምታት የወሰድከው መድሓኒት ከጨጓራ ህመምህ ሊፈውስህ ይችላል – ፖዚቲቭ ሳይድኢፌክት፡፡ የመለስም የአባይ ግድብና ሌላው ግርግር ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ እውነት ያለፈ አይደለም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ፍቅርና የሀገር መውደድ ስሜት ቢኖረው ኖሮ… ታውቁት የለ – ምን ወደዚያ ውስጥ ከተተኝ … ፡፡ ይቅርታ – በዋናው የሃሳብ መስመሬ ላይ እንደአረብ ጣቢያ ጣልቃ እየገባ ኳርት የሚለዋውጥብኝና እንድዘባርቅ የሚያደርገኝ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግር በመሆኑ ታገሱኝ፡፡
ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው? የት ተቀምጦ? በስምና በአካል ይታወቃል ወይ? ብለን እንጠይቅ፡፡
እኔ በ
ግል እንደምታዘበው ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደራት የሚገኘው ሰው አይመስለኝም፤ መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ ግማሹ ቅዱስ ነው፤ ግማሹ ደግሞ እርኩስ ነው – አሁንም በኔ ዕይታ፤ ዕይታየ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የኔ ጉዳይና የናንተ የኅሊና ፍርድ ነው፡፡
ቅዱስ ያልኩት በተከመሩብን ሁለንተናዊ የፖለቲካና ማኅረሰብአዊ ችግሮች የተነሣ እርስ በርስ ተበላልተን እንዳናልቅ እየረዳን ያለ አንዳች ኃይል መኖሩን ከመገመት ባለፈ ስለማምን ነው፡፡ ይህ ኃይል ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ እንደሚታየው ጭቆናና የኑሮ ውድነት አንድም ሰው በአንጻራዊ ሰላም ከቤት ወጥቶ ወደቤት በሰላም ባልገባ ነበር – እውነቴን ነው የምለው ይህን ዓይነት ደግ መንፈስ ባይጠብቀን ኖሮ ተበላልተን ለማለቅ የሚፈጅብን ጊዜ ሰዓታትን ብቻ በወሰደ ነበር(ሦርያንና ሊቢያን… ያዬ ይፍረድ – ሊያውም ከኛ በእጅጉ ያነሰ ጭቆናና እንግልት ደርሶባቸው!) ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው በረንዳ አዳሪ፣ ሥራ አጥና ቤት አልባውም በ”ሰላም” ካደረበት ከየቱቦውና ከየላስቲክ ቤቱ ወጥቶ በቀጣዩ ቀን በየአደባባዩ ባላየነው ነበር፡፡ ካለአንዳች አለሁህ ባይ የመንግሥት መዋቅር በራሱ ኃይልና እንዲሁ በኪነ ጥበቡ ርሀብና ችግሩን ችሎ የሚኖር ሕዝብ ማየት የሚገርምም የሚሰቀጥጥም በድንቃ ድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውም የሚሌኒየሙ ተዓምር ነው፡፡ አንድም ሥራና አንድም ደመወዝ የሌለው በሚሊየን የሚገመት ዜጋ ቀኑን አለበቂ ምክንያት እዚህና እዚያ ሲንከራተትና ሲንገላወድ ውሎ አሁንም ልድገመውና በየሥርቻውና በየሥርጓጉጡ በ”ሰላም” አድሮ የቀጣይዋን ዕለት ጀምበር ለማየት እባቡር መንገዱ ላይ ተሰጥቶ መታየቱ የትንግርትን እንጂ የመንግሥትን ኅልውና አያመላክትም፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገራችንን በትረ ሥልጣን ከያዙ ሥውር ኃይሎች ውስጥ የተወሰነውን ‹የፓርላማ ወንበር› የተቆናጠጠው አንዳች የተቀደሰ ነገር መሆን አለበት ብዬ አምለሁ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ማን እየተዘባነነ ማንስ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በርሀብና በጥም እየተሰቃዬ ይኖር ነበር? ሀሰት ነው?
በሌላ በኩል የሚታየውን መቋጫ የሌለው የግፍ አገዛዝና የዘረኝነት ቱማታ ስንቃኝ ከነዚህም ጋር የሚቆራኘውን አጠቃላይ የድቀት ሕይወት ስንታዘብ በተለይ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ አመራር ረገድ የእርኩሱ መንፈስ ምን ያህል የበረታ እንደሆነ መረዳት አይቸግርም፡፡ ስለዚያም ምክንያት ይመስለኛል ይህ በመለስ የሙት መንፈስ የሚነዳ የአጋንንት መንጋ አንዳች ሥፍራ ተደብቆ ደህና ሰው ወደ አመራር ዝር እንዳይል እነአዜብንና በረከትን እየተመሰለ በላያችን ላይ የሚያንዣብብብን፡፡ እንደሚወራው አዜብ ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሆና አይደለም ጽዳትና ዘበኛም ሆና ብትመጣ እንኳን ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት፡፡ በሌላ ቦታ እያለች የማዘጋጃ ቤት ሹሞችን በስልክ እያስፈራራችና በአካል እያስጠራች ስንትና ስንት ግፍና በደል መፈጸሟ እየታወቀ አንድያውን በዚያ ቢሮ ስትገኝማ ከተማዋን ብቻ ሣይሆን እኛን ነዋሪዎቹን በጅምላና በችርቻሮ ባወጣንበት ዋጋ ቸብችባ በጥቂት ወራት ውስጥ ትጨርሰናለች፡፡ አዜብ – ዮዲት ጉዲት – እንኳንስ ማዘጋጃ ቤት ገብታ በሩቅ እያለችም – ለብልግናየ ይቅርታና – ለውሽማዋም ይሁን ለምትፈልገው ማንኛውም ሰው ቦታ ለማሰጠት፣ መብራት ለማሰጠት፣ የንግድ ፈቃድ ለማሰጠት፣ (እንዳስፈላጊነቱ ተመላሽ ሊደረግ ወይ ላይደረግ የሚችል) የባንክ ብድር ለማሰጠት፣ በመንግሥት ወጪ ረጃጅም የስልክና የውኃ መስመር ለማዘርጋት፣ የፈለገችውን ለማሾም ወይም ለማሻር፣ ንጹሕን ሰው ካለበደልና ጥፋቱ ዘብጥያ ለማስወረድ፣ በጥፋቱ የታሠረን በቅጽበታዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት በሕግ ሽፋን ለማዘረፍና ለራሷ ካምፓኒዎች ወይም ለመሰላት ለማሰጠት፣ በነባርና አዳዲስ የአክሲዮን ካምፓኒዎች ራሷን በአባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ለማስገባት፣ ወዘተ. ታደርገው የነበረውና አሁንም ከማድረግ የማትመለሰው አቅል ያጣ ሩጫ በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ሴትዮዋ ለገንዘብና ለእንትን ሲሏት ገደል እንደምትገባ የሚያውቋት ይመሰክራሉ – አጉል ተፈጥሮ፤ ከምን ዓይነት ሥጋና ደም ተፈጥራ ይሆን ወገኖቼ? በዚህ ዓይነቱ ለከት የሌለው የገንዘብና የሀብት ፍቅሯ ነው እንግዲህ ሰውዬውን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንደውሻ አሥራ በርሱ ስምና በርሷ ድፍረት ባጠራቀመችው ንዋይ ከዓለም መሪዎች መለስን በሀብት የሚበልጠው እንዳይገኝ ከፍተኛ ጥረት ላይ የነበረችው – በየባንኩ ብዙ ገንዘብ ታቁር የነበረችው፣ በየዓለም ማዕዘናት ብዙ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ትመሠርት የነበረችው፣ በፍቅረ ንዋይ መታወሯ እንዳንዳች እያደረጋት እንዲያ ዐይን ባወጣ መንገድ ትዝብት ላይ ወድቃ የነበረችው፡፡ ይህች በገንዘብና በእንትን ፍቅር ያበደች የድብቁ ቢግ ብራዘር ተወዳዳሪ ሴት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብትገባ ምን ተዓምር ልትሠራ እንደምትችል ገምቱ – የምን መገመት ነው – ፍንትው ብሎ እየታዬ! የስንቱን ቤት እንደምታፈናቅልና ባወጣ እንደምትሸጥ፣ ስንቱን የኪስ ቦታ እንደምትቸበችብ፣ እንደ አንደኛው ባሏ ‹የዐይናችሁ ቀለም አስጠላኝ› እያለች ስንቱን ምሥኪን ሰው ከሥራና ከደመወዝ እንደምታግድ፣ እንደምታሳስርና ደብዛ እንደምታስጠፋ፣ ስንትና ስንት የሀገር ማፈሪያ ወንጀልና የቁጭ በሉ አሣፋሪ ድርጊቶችን እንደምትሠራ፣ ስንቱን ኮበሌ ካልተኛኸኝ እያለች ከትዳሩና ከጤናማ ኑሮው እንደምታፈናቅል (“አሮጊት ለምኔ! ገንዘብና ሥልጣን ባፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ አሻፈረኝ የሚልን መቀመቅ እንደምታወርድ)፣ … በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል – እባካችሁን ‹ህልም እልም› ብለን ሁላችን እናማትብበት፡፡ አዜብ ብሎ ከንቲባ? ወያኔ ይህን ካደረገ በርግጥም ራሱን ለማጥፋት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህችን የአጋንንት ውላጅ የባንዳ ልጅ ማሳረፍ ይገባል – በሰላም፡፡ በቃ – በመለስ ቀብር እንዳለችው ልጆቿን በማሳደግ ፈተና ላይ ብቻ ታተኩርና በዚያው ትታይ፡፡
አዜብ በሌብነቷ አይደለም ሹም አትሁን እያልኩ የምከራከረው፤ በሌብነቷ ከሆነ መብቷ ነው፡፡ ዓለማችን በሌቦችና አጭበርባሪዎች የተሞላች በመሆኗ የርሷ ሌባ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም – በአመራርም ሆነ በተራ ዜጋነት ሌባና አጭበርባሪ ሀገር ምድሩን ሞልቶታል፡፡ አዜብ በተፈጥሯዊ ደመ ሞቃትነቷና ያንንም ተከትሎ በጉልህ ስለሚንጸባረቅባት የሴሰኝነት ጠባይዋ አይደለም ሹም እንዳትሆን የምመኘው፡፡ ያም መብቷ ነው – ካልሰለቻት እንኳንስ ነባር ታጋዮችን አዳዲሶቹንና እምቦቀቅላ ታጋዮችንም ታነባብራቸው፡፡ አዜብም ሆነች ቤቲ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መብት እስከፑንት (ላንድ) ቢጠቀሙበት የነሱ ጉዳይ እንጂ የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡ እኔን ክፉኛ የሚያሳስበኝ ድንበር የማያውቀው ውሸቷ ነው፡፡ በተራ ቃል ‹ውሸታም› መባል በፍጹም አይመጥናትም፡፡
በባህር ዳሩ የወያኔ ስብሰባ የተናገረችው ውሸት ስለሷ ባሰብኩ ቁጥር ስለእውነት በጣም ያመኛል፡፡ በዚያ ስብሰባ ‹መለስ ከዓለም መሪዎች በደመወዙ ብቻ ቤተሰቡን እያሰቃየ የኖረ ብቸኛው መሪ ነው፤ ከስድስት ሺ ብር ደመወዝ ለኢሕአዲግ ተቆርጣ በምትደርሰው አራት ሺህ ምናምን ብር ወርን ከወር እየጣጣፍን በመከራ ሲያኖረን የነበረና አእምሮውን ብቻ ይዞ የተወለደ… ይህ ሊሠመርበት ይገባል ፤ ሰው የሚለው አይደለም – እርሱ በዚያች ትንሽ ደመወዝ ብቻ ኖሮ ያለፈ የተለዬ መሪ ነው…› እያለች የቀላመደች ዕለት ስለርሷ ጨረስኩ፡፡ ስለርሷ ብቻም አይደለም፡- ስለወያኔ/ኢሕአዴግም ያኔውን ጨረስኩ፡፡ አንድ አንጋፋ ድርጅት ያን የመሰለ በሬ ወለደ ዓይነት ነጭ ውሸት ሰምቶ እርምጃ አለመውሰዱ ገርሞኛል – የዚያን ድርጅት የለዬለት ባዶነትም አረጋግጫለሁ፤ የሴትዮዋ ንግግር እውነትነት ቢኖረውም እንኳን የሀገርንና የድርጅትን ምስል በማጠየም ረገድ ቀልማዲት ያደረገችው ነገር እጅግ ሰቅጣጭ በመሆኑ በሕይወት የመኖርን መብት ሳይጨምር ከብዙ ነገር ልትታገድ በተገባት ነበር፡፡ ሕዝብ በሆነ ምክንያት በይሁንታ አፉን ቢለጉም እውነት እንዳይመስላቸው፡፡ ሕዝቡ በዕውቀት ከነሱ ስለሚበልጥ በዚያን ሰሞን ይህን የአዜብን የድህነት ወሬ የቡና ማጣጣሚያ ነው ያደረገው – ሳይጠማን እየጠጣን ብዙ ቡና ፈጅተንበታል – ጊዜው ሲደርስ ይህንን ኪሣራችንንም ታወራርዳለች፡፡ የዚህች ቀልማዳ ሴት ንግግር በአሣፋሪነቱና አጸያፊነቱ በሺዎች ዓመታት አንዴ እንደሚያጋጥም እጅግ ነውረኛ አነጋገር ሊወሰድ ይችላል፡፡ የርሷ ስህተት እንደግለሰባዊ ስህተት ተቆጥሮ በዝምታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ የወያኔው ድርጅት በፍርሀት ይሁን በሌለው ይሉኝታ እርሷን በዝምታ ማለፉ ግን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ህፀፅ ነው፡፡ ለነገሩ አሁንም ብዙም አልረፈደምና የሴትዮዋን ተፈጥሮ የምታውቁ ወያኔዎች እባካችሁን አንድ ነገር አድርጉ – ለናንተው ስትሉ፡፡ እኛ ሁሉንም ለምደነዋልና ስለኛ ብላችሁ እንደማትጨነቁ እናውቃለን፡፡ ሀፍረቱ ይበልጡን ለእናንተው ስለሆነ አዜብን ግዴላችሁም ተዋት፡፡
ቁጭ ብዬ በእርጋታ ሳስበው ሕዝብንና የታሪክ ፍርድን ንቆ ይህችን ሴት ባለሥልጣን ማድረግ የኋላ ኋላ ኢሕአዴግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስለኛል፡፡ እናም ኢሕአዴግ ለክብሩ ሲል – ክብር ካለው ነው ለዚያውም – አለበለዚያም ውርደቱን ቅጥየለሽ ላለማድረግ ሲል ይህችን ሴት ከማዘጋጃ ቤት ሹምነት የዕጩ መዝገብ ይፋቃት፡፡ እኔ ውርድ ከራስ ብያለሁ፡፡ ሰውን መናቅ ፈጣሪን መናቅ እንደሆነ ለሃይማኖት የለሹ ወያኔ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – በአምባገነኖች ዘንድ ማይምንና እንደጤናማ ሰው ማሰብ የማይችልን አጋሰስ መሾም የተለመደ ነው፡፡ ሲበዛ ግን ያንገሸግሻል፡፡ ሕዝብ ስቆ ቢያልፈው የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ፣ አይደለም ይህችን በሰው ቋንቋ ከመናገሯ ውጪ ከውሻ ብዙም የማትለየው ሴት ትቅርና ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አምባገነኖችን አይቀጡ ቅጣት አከናንቦ በጭቁኖች መሃል አዋርዷቸዋል፡፡
ይህች መናኛ ሴትም ከወያኔ ጋር የምትዋረድበት ዘመን እየመጣ ቢሆንም ማምሻም ዕድሜ ነውና ማሰብ ያልተሳናችሁ በጣት የምትቆጠሩ ወያኔዎች ካላችሁ የዛሬን ማሩን፤ ቀድሜ እንደገለጽኩት ውርደቱ የጋራችን ነው፡፡ ይበልጡን ግን – ልድገምላችሁ – የእናንተው ነው፡፡ ሴትዮዋን መሾማችሁ የግድ ከሆነ ብትፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓት፡፡ ያ ቦታ ከሕዝብ የራቀ በመሆኑ አንገናኝምና እንደፍጥርጥራችሁ፡፡ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ግን ሺዎችን በየቀኑ የሚያስተናግድ የሕዝብ መናኸሪያ በመሆኑ ባለሥልጣናቱ የሕዝብን ቀልብ እንደነገሩም ቢሆን የሚስቡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህች ሴት እኮ አርከበ ዕቁባይ ለሕዝብ ጥሩ ሠራ በመባሉና ሕዝብም በተወሰነ ደረጃና በግል አበርክቶው ስለወደደው በዚያ ቀንታበት ኤች አይ ቪ ሲመረመር የሚያሳየውን ቢልቦርድ በተሰቀለ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲወገድና ከዕይታ እንዲሠወር አድርጋለች፡፡ የባል ተብዬው የመለስና የሚስት ተብዬዋ የአዜብ የክፋት ደረጃ እንግዲህ እስከዚህ የወረደና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ ነው – ለቅጣት መምጣታቸውን በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ተራ ዜጋ ምቀኛና ቀናተኛ ቢሆን ምንም አይደለም፡፡ የአንድን ሀገር በትረ ሥልጣን የጨበጠ ቁንጮ ያገር መሪና ሚስቱ ግን እንዲህ ያለ በራሱ በመለስ ወራዳ የቋንቋ አጠቃቀም ለመግለጽ እንዲህ ያለ ወራዳና ልክስክስ ጠባይ ሲያሳዩ የሀገርን አጠቃላይ ውድቀት ነው በጉልህ የሚያስረዳን፡፡ ያልዘሩት መቼም አይበቅልም፡፡ የዘራነውን እያጨድን ነን፡፡
ለማንኛውም አዜብን በከንቲባነት መሾም – ምክትልም ሆነች ዋና ለውጥ የለውም – የሚያስከትለው አደጋና ውርደት ታስቦበት በጊዜ አንድ ነገር እንዲደረግ የዜግነት ጥሪየን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡
በሌላም በኩል ይሄ ለይምሰል ያህል በብሔረሰብ ተዋጽዖ አንጻር የሚደረገው ሹመት ይቁም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ማንም አያምንም – ይህን ያረጀ ያፈጀ ሥልት አንቀልባ ውስጥ ያለ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቀዋልና፡፡ እኔ ለምሳሌ በደመቀ መኮንን መሾም ምክንያት አልተደሰትኩም፡፡ አንደኛውና ትልቁ ነገር እንደውሻ አጥንትና ደም አላነፈንፍም፡፡
በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም የሚኒስትር ካቢኔ ከኮንሶና ከሙርሲ ቢሆን ሃሳቡ አይበላኝም፤ ወያኔንም የጠላሁት በመጥፎ ድርጊቱ እንጂ በተሹዋሚዎች የዘር ሐረግ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሁለተኛ የደመቀ መሾም ስሜትን በማይነካ የቃላት አጠቃቀም ለየዋሃን አማሮች ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ የፈጠጠውን ኢትዮጵያዊ እውነት ለሚረዳ ሰው ‹አማራ ተሾመልኝ!› በሚል የሚያስፈነጥዝ አይደለም፡፡ ራሱን ከጥቃት የማያድን አማራ፣ የራሱ ናቸው የተባሉ ወገኖችን ጥቃትና እንግልት ለማስቆም አንዳችም ተሰሚነት የሌለው በድንና ገልቱ ሰውዬ ተሾመልኝ ብዬ ጮቤ የምረግጥ ሞኝና ተላላ መስዬ ከታየኋቸው – አዝናለሁ – ሞኞቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ደመቀን መሣይ ከረፈፍ ሆዳሞች በሥርዓቱ ውስጥ ወይነው ገብተው ሀገሪቱን ምን ያህል እየጎዱ እንደሆነ ማስታወስም ተገቢ ነው፡፡ በጣም የምወደው ኦባንግ ሜቶ ቅድም ሲናገር እንደሰማሁት ሁልጊዜም እኔ ራሴ እንደምለው ወያኔ ማለት በዘርና በቋንቋ ተወስኖ ወይም ተቀንብቦ የተቀመጠ አለመሆኑንም መረዳት ይገባል፡፡ መነሻውና አስኳል አመራሩ ከትግራይ ይሁን እንጂ ለዚህ የወያኔ ሥርዓት ማበብና ማፍራት ዋና ተባባሪዎቹ ትግሬ ያልሆኑ የተጋቦት ወያኔዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ግን ግን “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ዞረ” እንዲሉ ሆኖብን አንዴ የፈረደበትን የትግራይ ሕዝብ ብዙዎቻችን እንወርድበታለን፡፡ በበኩሌ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ የእያንዳንዳችን ልብ ሳይሰበር ነገ ይቅርታ እንደምንባባልና አብሮነታችን ካለሣንካ እንደሚቀጥል በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ንዴትና ብስጭት የማይፈጥረው አእምሮኣዊ ምስል ባለመኖሩ ደመናው ሲጠራና እውነት ስታሸንፍ አሁን ችግር የሚመስሉን ብዙ ነገሮች ከላያችን ላይ ተገፍፈው ይጠፋሉ፤ ያለ ነገር ነው – በዚህን መሰሉ ጊዜ የሚያጋጥም ብዙ ነገር አለ፡፡ መምሰልና መሆን ስለሚለያዩ የደፈረሰው ሲጠራና የሰላም አየር በሀገራችን ሰማይ ሲያረብብ የግጭትና የሁከት እርኩሳን መናፍስት ተጠራርገው ይወገዳሉና ስለነገው ከመጠን በላይ አንጨነቅ፡፡ የወቅት ንፋስ የሚፈጥራቸው ብዙ አላፊ ክስተቶች አሉ – በኛ ብቻ ሳይሆን በየሀገሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳትና ለዚያ በርትቶ መታገል እንደሚገባ ተረድተን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ተባብረን ይህን የለያየንን ቆሻሻ ሥርዓት ለማስወገድ አብረን መታል ብቻ ነው የሚያዋታን፡፡ አለጥርጥር ሥርዓቱ ይወድቃል – ችግሩ በጣም ብዙ ምናልባትም ከእስካሁኑ የከፋ ቨስጠሊታ የታሪክ ጠባሳ ሳይተው የሚወድቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም ምክክር፣ ትብብርና ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ምን ጊዜም ከእውነት መንገድ ለማትወጣው ነገር በመለያየት አዲስ ግን በወያኔያዊ ትልምና ዐቅድ የተለወሰና በፀረ-ኢትዮጵያነት የተመረዘ ታሪክ ለማስመዝገብ የምንቻኮል ሰዎች ካለን ቆም ብለን እንድናስብ በእገረ መንገድ ጠቆም ባደርግ ደስ ይለኛል – ከወያኔ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ የሕዝቡ ችግረና ፍላጎት ይግባን፡፡ ‹ሕዝቡ ምን ይላል? ምንስ ይፈልጋል ?› ብለን እንራመድ እንጂ በየግል ፍላጎታችን የተጓዝን ተሳስተን አናሳስት፤ ታሪክም ይቅር አይለንም፡፡ መደማመጥ ለመልካም የጋራ ስኬት ጠቃሚ መሆኑን እየዘነጋን ለየህልማችን እውን መሆን በተናጠል ስንሮጥ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ፡፡
ማንዴላ እጅ ሆነዋል፡፡ ምናልባትም ይህች ጽሑፍ በአንዱ ድረ ገፅ ከመለጠፏ በፊት አንዳች ነገር ሊከሰት ይችላል፤ ወይም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ዜና ዕረፍታቸውን እንሰማ ይሆናል – ለነገሩ ‹እግረ ቀጭን እያለ እግረ ወፍራም ይሞታል› እንዲሉ ከማንዴላ በፊት ለምሳሌ እኔ ራሴ ልቀድም እችላለሁ፡፡ የወደፊቱን ያለማወቃችን ምሥጢር ነው ሕይወትን ትርጉም ያላት እንድትሆን ያደረጋት፡፡ ተስፋ ባትኖር ሁሉም በቁም እንደሞተ ያህል ነው – ጧት ከቤቱ በሰላም የወጣ ሰው ማታ ሬሣው ወደቤቱ ሊመለስ እንደሚችል ቢያውቅ ማንም የመኖር ጉጉት አያድርበትም – የእግዜሩም እንበለው የተፈጥሮ ጥበብ መገለጫም ይሄው ነው – ስለወደፊቱ አለማወቅ፡፡ በዚህም አለ በዚያ በማንዴላ ሁኔታ ዓለም በጭንቀት ላይ የምትገኝ ትመስላለች፡፡ ጭንቀቷ ግን ለማንዴላ ለራሱ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምሥጢሩ ወዲህ ነው፡፡(በነገራችን ላይ ‹ድኅረ ገፅ› የምንል ሰዎች ‹ድረ ገፅ› ማለትን ብንለምድ ደስ ይለኛል፡፡ ‹ድኅረ› ማለት ‹በኋላ›(post) ማለት እንደሆነና ‹ድረ› የሚለው ቃል ግን ‹ድር› ከሚለው የአማርኛ ቃል ተወስዶና ከ‹ገፅ› ጋር ተጋምዶ ‹website› የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እንዲተካ መደረጉን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ዕውቀት አይናቅምና በተለይ ድረ-ገፆች እባካችሁን ይቺን ነጥብ አትናቋት፡፡ መናደድ ሲያምረኝ ከምናደድባቸው ነገሮች አንደኛዋ ይህች ነች፡፡ )
የዓለም ሕዝብ አንድ አባሉ ከ94 ዓመታት በላይ በመሬት ላይ እየኖረ እንዲሰቃይ የሚፈልግ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰዎች እስከዘላለሙ እንዲኖሩ የሚፈለግበት ምኞት – ከልብ ስለመሆኑ ማወቅ ቢያስቸግርም – በብዛት የሚታየው በኛይቷ ሀገር በኢትዮጵያ ነው፡፡ የመቶ ሃያ ዓመት ሽማግሌ ሲሞት ፊት የሚነጨው በሌላ ሀገር አይደለም – በኢትዮጵያ ነው – ሊያውም ይበልጡን በአማራው አካባቢ፡፡ ባህላችን ከኛ ወቅታዊ ግንዛቤ በልጦ የሚገኝበትን ሁኔታዎች አንዳንዴ እንታዘባለን፤ ከአንዳንዴም በላይ እንዲያውም፡፡ ለዚህም ነው በዛሬዋ ውሎየ እንኳ ሁለት ተቃራኒ ጸሎቶችን የታዘብኩት – አንድ ከኢትዮጵያውያን፣ አንድ ከደቡብ አፍሪካውያን፡፡ መቼም እኛ ከነሱ በልጠን እግዜሩ ለማንዴላ የማቱሳላን ዕድሜ እንዲሰጥልን ልንጸልይ እንደማንችል ቢያንስ ኅሊናችን ያውቃል – እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፡፡ ይህ ምን ያሳያል? ፊት ለፊት የሚታየው ባህላችን ለሰው መጥፎ የማይመኝ መሆኑንና በብዙ ነገር ከሌሎች የምንለይ ሕዝብ መሆናችንን ነው ለዓለም እያስመሰከርን የምንገኘው – ምነው እውነተኛና በምንም ዓይነት ማዕበል የማይናወጥ አቋም ባደረገልን!
ማንዴላ እንዳይሞት የምንፈልግበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ዓለማችን በሰው እጦት ምች ስለተመታች ጥሩ ሰው ስናገኝ እንደብርቅ እናየዋለን፤ ሞት እንዳይነጥቀንም እንሳሳለታለን፤ እስከወዲያውም አብሮን እንዲኖር እንመኛለን – ትውልድ ቢያልፍም ከቀጣዩ ትውልድ ጋር፡፡ ብዙ ደጋግ ሰዎች ቢኖሩን ኖሮ የዓለም ሕዝቦች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት ያለቪዛና የትራንስፖርት ወጪ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ፕሪቶሪያ ሆስፒታል ዙሪያ ባልከተመ ነበር፡፡ ጥሩ ሰው ብርቅ በሆነበት ዘመን መፈጠር እንዴት መታደል ነው! መለስም እንዲያ የተንጫጫንለት እኮ የርሱን አእምሮ ይዞ የሚወለድ – እንደአዜብ አነጋገር በዓለም የአንጎል ገበያ ተመራጭ ጭንቅላት ይዞ በሺዎች ዓመታት አንዴ የሚወለድ ዐዋቂና ታዋቂ በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ለመለስ የነጨሁት ፊት እስካሁን አላገገመም፤ የምለብሰውም ማቅ ከላየ ላይ አልወረደም፡፡ እርግጥ ነው – ይበልጡን ለክፋት ቢጠቀምበትም መለስን በዕውቀቱ መቀጣጠብ አይቻልም፤ ሰይጣን ለዘዴው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባል መለስም የነበረው ሁለገብ ዕውቀትና ብልጣብልጥ ተፈጥሮ ከብዙዎች መሪዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የኔነህ ሳይለኝ ቢሞትም የኔነው ማለት ወጪ የለውምና ሳልወድ በግዴ የኔነው ብዬ ብቀበለው ከሚኮሰኩሰው ኢትዮጵያዊነቱ አንጻር ብቻም ሳይሆን ከአጠቃላይ ስብዕናው የሚፈልቁ ብዙ የሚደነቁ ሰብኣዊ ተሰጥዖዎች እንደነበሩት አልክድም – አጭበርባሪው፣ አስመሳዩና መልቲው መለስ ዜናዊ፡፡ ግን ተሰጥዖዎቹን ለተንኮልና እንደሥራየ ቤት ነገርን በመጠምዘዝ ሕይወቱን ጨርሶ ዕውቀቱን ሳይጠቀምበት ሞተና ዐርፎ ዐሣረፈን፡፡ በሚስቱ ሲንገበገብ የነበረ አንድ ፈላስፋ መቃብሯ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሯል አሉ፡- My wife lies here; let her rest in peace, so do I.
አትታዘቡኝ፡፡ በበኩሌ ማንዴላ እንዲያርፍ እጸልያለሁ – በሰላም ማረፍ ለኔ አይገባኝም – ሰው እየሞተ ምን ሰላም አለና፤ ማንዴላ በ‹ሰላም› እንዲያርፍም በ‹ሰላም› እንዲድንም ከጸሎት ጀምሮ ሁሉም ነገር ቢደረግም እስከዚች ሰዓት ድረስ አልዳነም ወይም አላረፈም፤ የዚህን ደብዳቤ የመጀመሪያ ረቂቅ ስጽፍ – አሁን ሰዓቱ ከሌሊቱ ስምንት ገደማ መሆኑን ልብ ይሏል – የማንዴላ የጤና ሁኔታ እንደሰሞኑ ሁሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ፤ ከአሳሳቢነቱም የተነሣ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ሊያደርጉት የነበረውን የሀገር ውጪ ጉዞ እስከመሠረዝ ደርሰዋል፡፡ ዕንቁ ልጃችን – ብርቅዬ የአፍሪካ ብቻ ሣይሆን የዓለማችን ልጅ ማዲባ ሲያርፍ ደግሞ ነፍሱ በማኅተመ ጋንዲና በእማሆይ ተሬዛ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ እንድትቀመጥ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆን ዘንድ የሁላችንንም ጸሎት እኔም በበኩሌ እጸልያለሁ፡፡ ይቅርታችሁን – ቀደም ብዬ ማዲባን በአንቱታ የጠራሁት ብዙ ሰው ያለው እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ከሰው ለመመሳሰል ነው፤ ስጨርስ በአንተ የጠራሁት የሕዝብ ሰው አንቱ እንደማይባል ስለምረዳ የአንጀቴን ነው – የሕዝብ ሰው ማለት ደግሞ የሚፈቀርና የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አብንና ወልድን ማን አንቱ ይላል? ቅድስት ማርያምንስ? ኧረ መለስ ዜናዊንስ ማን በአንቱታ ጠርቶት ያውቃል? የሕዝብ ሰው ማለት እንዲህ ነው – ቺንዋ አቼቤ A man of the people የሚል ርዕስ ለአንድኛው መጽሐፉ የሰጠው እኮ ለነማንዴላ ዓይነቱ መላ ሕይወታቸውን ለራሳቸው ጥቅም መስዋዕት ላደረጉ ሣይሆን ለነመለስ ዜናዊ ዓይነቱ ለቤት ቀጋዎች ለውጭ አልጋዎች ነው፡፡ ዓለም ግን ምን ዓይነት የዕንቆቅልሽ ምድር ናት ጎበዝ?!
ውድ ማንዴላ ሆይ! ሁልጊዜ ከኅሊናችን አትጠፋም – በአካል ብትለየን በመንፈስ ምንጊዜም አብረኸን አለህ – ከአሁኑም ከወደፊቱም ትውልዶች ጋር፤ ፈጣሪ አንተን እንደወሰደ በምትክህ ለዓለም ሰላም የሚተጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን አሳቢ ዜጎችን እንዲልክልን ስትሄድ አሳስብልን፡፡ አፈሩን ገለባ ያድርግልህ፡፡ የሁለት ወር ሀገርህን ኢትዮጵያንም በፈጣሪ ፊት አስባት፡፡ ስቃይና ጣር ሳይበዛብህ በቶሎ ሂድልን፡፡ በዚህች አንተን ሳይቀር ለ27 ዓመታት በእሥር ባንላታች የእርጉማን ምድር ከአሁን በኋላ ለሴከንድም መቆየቱ መከራና ስቃይ መጨመር እንጂ ጤናውም ጤና አይሆንህም፡፡ ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፤ ‹ቆይልን› የምንልህ በአንተ ስቃይ የኛን ‹ኢጎ› ለማስደሰት እንጂ አንተ አልጋ ላይ ውለህ የመከራ ቀናትንና ሌሊቶችን በእዬዬ ማሳለፍህ፣ በድጋፍ ሰጪ የሕክምና ቴክኖሎጂ እየታገዝክ ካለ እንቅልፍ መቆየትህ አንዳችም ነገር አይፈይድልንም – ለአንተም ለእኛም፡፡ በሀገሬ ሰው ይሙት ተብሎ እንደማይጸለይ አውቃለሁ ማዲባየ – ግን ‹ይህን አለ› ተብዬ ኩነኔ መግባቱን እመርጣለሁ እንጂ ስትሰቃይ ለማየት ከእንግዲህ ቆይልን አልልህም፡፡ በቃ፡፡ በሰላም ሂድልን፡፡ ስትመጣ እንደምትሄድ ይታወቅ ነበር፡፡ እኛም በሕይወት አለን የምንል ወገኖችህም ወረፋችንን ጠብቀን እንከተልሃለን፡፡ ዱሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ይብላኝ ለኛ ግና፡፡ በጅቦችና በእሪያዎች መካከል እንደተጣልን ተለይተኸን ለምትሄደው ለኛ ይብላኝ እንጂ አንተማ ከፋም ለማም 95 የሚጠጉ ክረምቶችን ለሕዝብህ ስትል ከአፓርታይድና ከመጥፎ ግላዊ ገጠመኞችህ ጋር ስትፋለም ኖረህ አሁን በመጨረሻው ሥጋዊ ሽንፈትህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል፡፡ በዚያች በደቡብ አፍሪካዊቷ አዜብ እንኳን ያየኸውን አበሳ ማን ይረሳዋል? ብቻ ሆድ ይፍጀው ማዲባየ፡፡ እዚያው እስክንገናኝ ደህና ሰንብትልኝ፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ፤ በዚህ ዓለም አቀፍ ሀዘን መጽናናት ለሚያስፈልገው ሁሉ ፈጣሪ እንዲያጽናናው እመኝለታለሁ፡፡

Leave a Reply

Thursday, June 27, 2013

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”


“ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”
tesfaye1
“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤ መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኳ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝቷል፤ ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላርሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ … ባካችሁ ተውኝ … ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣ በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር፤ ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጥቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላርሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል፤ እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣ አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ… (ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡ ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም፡፡ስትደበደብ፣ ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ፤ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነው የነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ (ምንጭ ፍኖተ ነጻነት)

ወያኔ ሕወሃት የደደቢቱን አስታውስ!


June 25, 2013

ይኸነው ዓለሙ
ሰኔ 25 2013
በሚያስደንቀው የሀገራችን ምርጫና ከዚሁ የምርጫ ሳጥን በሚገኝ የሕዝብ ድምጽ፤ በሰላማዊ መንገድ ወያኔ ሕወሃትን እናሸንፋለን ብለው ቀን ከሌት ከሚደክሙትም ሆነ ሰላማዊው አማራጭ አዋጭ አይደለም በማለት በነፍጥ ወያኔን ለማንበርከክ እየታገሉ ያሉ ኢተዮጵያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ሆነ ድርጅቶችን በሀገር ፍቅር ማጣትም ሆነ ተቆርቋሪነት፣ በሕዝብ ክብር መጉደልም ሆነ ሀላፊነትን መዘንጋት ለመውቀስ የሚያበቃ የሞራል ልዕልና ወያኔ ሕወሃት የለውም። ሌላው ቀርቶ በጫካ ዘመን አስተሳሰቡና ምግባሩ ይቅርና መንግስት ነኝ ካለ በሗላ ባሳያቸውና እያሳያቸው ባሉት ምግባሮቹ እንኳ ቢገመገም በሀገራችን ካሉት ሀገራዊም ሆኑ ክልላዊ ፓርቲዎች እንዲሁም በነፍጥ እየታገሉ ካሉት ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ጋር ለመወዳደር የሚያበቃ ተክለ ሰውነት እንዲሁም የሀገርና የሕዝብ ፍቅር አልታየበትም።
እነዚህን ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶች አንድ ጊዜ የሀገራችንን ጥቅም አሳልፈው የሸጡና ከአሸባሪ ጋር የወገኑ ሌላ ጊዜ ከሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ያበሩና ሀገር ለማፈራረስ የተዘጋጁ እያለ ለመክሰስ እራሱ ወያኔ ሕወሃት ማነው? እንዴትስ አሁን ላለበት የገዥነት ወንበር በቃ? በነማን እርዳትነት? አሁንስ ስለ ሀገራችንና ሕዝባችን ያለው አመለካከት ምንድን ነው? እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መመልከት ተገቢ ይሆናል።
በመጀመሪያ ደረጃ ለሕዝባችን በሰላማዊም ሆነ በሌላ አማራጭ እየታገሉ ካሉት ድርጅቶች ፍጹም የተለየ በነበረው እንቅስቃሴው በዓለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ ተብሎ ተፈርጆ የሀገራችን ማፈሪያ የነበረው ድርጅት ራሱ ወያኔ ሕወሃት እንጅ ሌሎች የሀገራችን ፓርቲዎች ድርጅቶች ወይም ንቅናቄዎች አልነበሩም። የህ የወገንና የሀገር ማፈሪያ የሆነው ቡድን ወያኔ ሕወሃት በተለይ ከ1968 እስ 1982 ዓ/ም በነበሩት ዓመታት በሕዝባችንና በሀገራችን ላይ በፈጸማቸው አስር የከፉ የአሸባሪነት ስራዎች ምክንያት ስሙ በዓለም አቀፉ የአሸባሪዎች ዳታ ቤዝ ተመዝግቦ ይገኛል። “የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንደሚባለው ሆነና ዛሬ ግን ራሱ ተመልሶ እንደፈለገ በሚያዘው ፓርላማው በመጠቀም ስለ ሕዝባቸው አርነት ስለ ሀገራቸው ነጻነት እየታገሉ ያሉ ድርጅቶችን አሸባሪ የማያስቡና ለሕዝባቸው ደንታ የሌላቸው ለማለት በቃ።
ዛሬ በሂወት የሌሉትም ሆኑ በአካለ ስጋ የሚንጠራወዙት አብዛኞቹ የወያኔ ቁንጮዎች ያኔ በጫካ ዘመናቸው በዓለም ዙሪያ ለልመና ይንቀሳቀሱ የነበሩት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ከነበረችው ሶማሊያ ጋር በማበርና ከሶማሊያ በተገኘ ፓስ ፖርት በመጠቀም እንደነበር ሲታወስ ወያኔ ሕወሃት በተቃዋሚዎች ላይ አፉን ለማላቀቅ ምን የሞራል ብቃት አለው? ያስብላል። ከዚህ በተጨማሪም ከጎረቤት ሱዳንና ግብጽን ጨምሮ ከአብዛኞቹ አረብ ሀገሮች ከፍተኛ እርዳት ይፈስለት የነበረው ወያኔ ሕወሃት ከታሪካዊ ጠላታችን ሱዳን ግዛት እየተንደረደረም የሽብር ጥቃቱን በሕዝባችን ላይ ይፈጽም እንደነበር መቼም የማንረሳው የሃዘን ትዝታችን ነው። ይህንን የሱዳን እርዳታም ከውሌታ በመቁጠር ይመስላል ርዝመቱ 1600 ኪሎ ሜትር ስፋቱ ደግሞ እስከ 60 ኪሎ ሜትር የሚደርሰውን ሰፊና ለም የሀገራችንን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ማስረከቡስ ምናልባት ከሀገር ፍቅርና ወዳድነት ለወገን ክብርና ሞገስ ከማሰብ ይሆን ይሆን?
ከወያኔ ሕወሃት በፊት የነበረው አንባገነን ገዥ ደርግ በድንበር ይገባኛል ምክንያት በ1969 ዓ/ም ሀገራችንን በግፍ ወርራ ከነበረችው ሶማሊያ ጋር ጦርነት ገጥመን በነበረበት ወቅት ከጠላት ጋር በማበር ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከሌላ አቅጣጫ ይወጉትና ያሰቃዩት የነበሩት እነዚሁ ያዛሬዎቹ ጉዶች ወያኔ ሕወሃቶች ለመሆናቸው የታሪክ መዛግብቶች ያስረዳሉ። ሌሎች የሀገራችን ሰላማዊም ሆኑ በሌላ አማራጭ ወያኔን ለመታገል የወሰኑት የዛሬዎቹ ድርጅቶች ግን በእንዲህ አይነት ቅሌት በማስረጃ በተደገፈ መልኩ አንዳቸውም ሲታሙ አልሰማንም። ሕዝባችንን ያለማቋረጥ እየወጋ ካለው ወያኔ ሕወሃት ጋር ከሚያደርጉት ትግል በስተቀር።
ጥቁር ሕዝብ ነጭን ሊያሸንፍ አይችልም የሚለውን የተሸናፊነት መንፈስ ጣሊያንን በተደጋጋሚ በመንበርከክ ለዓለም አዲስ ምእራፍ የከፈተችና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችን ሀገራችንን ልጆቿ ነን የሚሉት ወያኔዎች ግን አፋቸውን ሞልተው “ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድም ጦርነት አሸንፋ አታውቅም” በማለት ዓለም የሚያውቀውን ድንቅ ታሪካችንን ሲያራክሱና የሀገራቸንን ማንነትና የሕዝባችንን ጥንካሬ ብዙ ጊዜ ለማንኳሰስ ሲሞክሩ ታይተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በዓመተ ዓለም በሽህ የሚቆጠሩ ዘመናትን በሀገርነት ያሳለፈችውንና በዓመተ ምህረትም ላለፉት ሁለት ሽህ ዓመታት በሀገርነት የምትታወቀዋን ክቡር እድሜ ጠገብ ሀገራችንን ጎማምደው የመቶ ዓመት ያገር ጎረምሳ በማድረግም ወያኔ ሕወሃትን የመሰለ እኩይ ጎጠኛ ቡድን የትም አልታየም። ዛሬ የምናውቃቸው የሀገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ግን በእንዲህ ያለው ጉዳይ ሲታሙ ተሰምቶ አይታወቅም።
ባንዲራችን የሀገራችን መለያ ነው። ባንዲራችን ሕዝባችንን አንድ አድርጎ ባንድ ላይ ለማሰለፍ የሚጠቅመን የራሱ ትርጉም ያለው የሁላችን ማስተሳሰሪያ ምናባዊ ገመድ ነው። በተለይ በሀገራችን ደግሞ ለባንዲራ ያለን ክብርና ፍርሃት ከፍተኛ በመሆኑ ጥጋበኛን ለማረቅና ለማስተካከል “በባንዲራችን ይዠሃለሁ” እና “በባንዲራችን አምላክ” እየተባለ እስከመለመንና እስከመገዘት የደረሰ ክብር አለው- ባንዲራ። ወያኔ ሕወሃት ግን ይህን ያህል ክብር የምንሰጠውን የሀገራችንን መለያ የሕዝባችንን የአንድነት መታወቂያ እጅግ በጣም አዋርዶና ክብሩን ዝቅ አድርጎ እነደጨው መቋጠሪያ የጨርቅ ቁራጭ  ነው ሲል እራሱን በጣም ያዋርዳል ዝቅ ያደርጋል እንጅ ሌላ የፖለቲካ ጥቅም አያገኝበትም አላገኘበትምም። ባንዲራ  የጨርቅ ቁራጭ ነው በተባለበት ወቅት ስለባንዲራ ክብር ይከራከሩ የነበሩትን የአንድነት ሃይሎች አፍ ለማዘጋት ተብሎ የተነገረው ንግግር ውሎ አድሮ ወያኔ ሕወሃትን ዋጋ እያስከፈለው መሆኑን አሁን እያየን ነው። በሰላም የሚታገሉትም ሆኑ ነፍጥ ያነገቡት የሀገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ግን ለሀገራችን ባንዲራ ክብር በመስጠት የወያኔን አፍራሽ አባባል ታገሉት እንጅ ይህን በተመለከተም ጉዳይ ቢሆን በአፍራሽነትና በጠላትነት ሲሰለፉ አልታዩም።
ወያኔ ሕወሃት በውይይት ሞቅታ ወይም ሆን ብሎ በማንአለብኝነት አለዚያም ለሕዝባችን ያለውን ንቀት ለማሳት በሚመስል መልኩ አንዱን ካንዱ ለማበላለጥና ለማጋጨት ባለው ፍላጎትና ጥረት ሀገር እየመራሁ ነው በሚልበት ጊዜ እንኳ እጅግ ከመጠን በላይ ጠቦ ተፈጠርኩበት የሚለውን አካባቢ ብቻ በማወደስ “እንኳን ከናንተ ተፈጠርን” እስከማለት የደረሰ ጎጠኛና የማያስብ ጠባብ ቡድን ሀገር ከመምራት ደረጃ ያልደረሱትን ተቃዋሚዎች በሃላፊነትና ተጠያቂነት እጥረት ለመክሰስ የሚያስችል  የሞራል ብቃት የለውም።
ከዚህም እጅግ በከፋ መልኩ የሀገርን አንድነትና ሉአላዊነት ለማስከበር ለዘመናት በፍቅርና በመከባበር ላይ ታች ሲል የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት ለመናድና “የኔ አይደለም” ወይም “የኛ አይደለም” የሚለውን መጥፎ ስሜት በሕዝባችን ውስጥ ላማስገባት ሲል “ ትግሬዎች አክሱም አላቸው ይህ ለጉራጌው ምኑ ነው? አገዎች ላሊበላ አላቸው ይህ ለኦሮሞው ምኑ ነው? ጎንደሮች ቤተ መንግስት አላቸው ይህ ለወላይታ ምኑ ነው” በማለት ልዩነትን የሰበከው፣ አለመቻቻልን ያወጀው፣ የበላይና የበታችነትን ያስተማረው ወያኔ ሕወሃት በምን ሞራል ልዕልናው ነው ሌሎችን ተቃዋሚዎች የሀገርን ሉአላዊነት በመጋፋትና ለሕዝብ ፍቅር በማጣት ሊከስ የሚችለው?
አንድ አካል ወይም ቡድን በተለይም እንደ ወያኔ ሕወሃት አይነት በእኩይነቱ በዓለም ደረጃ የሚታወቅ ቡድን፤ የመጣባቸው መንገዶች፣ ያልደበዘዙት ዱካዎቹ እንዲሁም ያሁን ማንነቱ አፍ አውጥተው እሱነቱን እያሳበቁበት ይቅርና ራሱን የደበቀ ድርጅት ቢሆን እንኳ “እኔ ጥሩ ነኝ ስላለ ጥሩ የሚሆን፣ ሌሎች መጥፎ ናቸው ስላለም ሌላው ተከጥሎ መጥፎ የሚልለት አይደለም”። ሁሉም በሚሰራው ይመዘናል። በሰራውም ተቀባይነትን ሊያገኝ ወይም ሊያጣ ይችላል እንጅ ሕዝብ ዝም ብሎ በስማ በለው አይጥልም አያከብርምም። “ለቀባሪው አረዱት” እንዳይሆንብኝ እንጅ በተለይም እንደ ወያኔ ሕወሃት አይነት ጎጠኛ ቡድን በኢትኦጵያ ሕዝብ ክብር ካጣ የቆየ በመሆኑ ተቀባይነቱም በዚያው መጠን የወረደ ነው።
ስለሆነም “ሌባ እናት ልጇን አታምንም” ሆኖበት ራሱ ሲያደርገው የነበረውን የሽብር ስራ ሁሉ ሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ሊያደርጉት ይችላሉ ብሎ በመጠርጠር የራሱን ግልባጭ እነ እንቶኔ አደረጉ ወይም ሊያደርጉ ነው። ከጠላትችን ከእንቶኔ ጋር ሊተባበሩ ነው፣ የሀገራችን ጠላት እንቶኔ አስተባብሮና አደራጅቶ ሊልክብኝ ነው እና የመሳሰሉትን በማውራት እትት ሲል ከርሟል። ወያኔ ሕወሃት እያወራው ያለው እውነትም ይሁን ውሸት ይህን ነጥብ በተለይ አንስቶ በሀገር ፍቅርና ተቆርቋሪነት ጉዳይ የሀገራችንን ተቃዋሚዎች የታጠቁም ይሁኑ ሰላማዊ ፓርቲዎችን ለመውቀስም ሆነ ለመክሰስ ወያኔ ሕወሃት የሞራል ልዕልና ይጎድለዋል። ብቃትም የለውም።

በዋልድባ ገዳም በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ

June 26, 2013

በታሪካዊው በዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ሰበብ እየደረሰ ያለውን ችግርና በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ፣ ከዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እናድን ኮሚቴ) የተሰጠ መግለጫ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
waldiba-ethiopia

Leave a Reply

Wednesday, June 26, 2013

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው


June 26, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅትBereket Simon is the Ethiopian Communications Minister የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።

Monday, June 24, 2013

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”


June 22, 2013
አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ።
አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።Obang Metho’s Testimony before the Subcommittee on Africa
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” የዛሬ 22ዓመት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከተናገሩት፡፡
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡
“የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ የማይቀር ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። … ሕዝብ በጭቆና አገዛዝ እየተገዛ ዝም ብሎ የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል … ዝም ብሎ ግን አይቀመጥም … ይፈነዳል … ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፡፡
አቶ መለስ “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው … እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” ክሪስ ስሚዝ፡፡
“እድሜ ልካችሁን አትገዙም ብለን መክረናቸዋል” ዶናልድ ያማሞቶ፡፡
የምክክሩ መድረክ
“ኢትዮጵያ ድኅረ መለስ፤ የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች የወደፊት ዕጣ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ፤ ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ጸሐፊ ዶናልድ ያማሞቶ፣ የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስት፤ የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም እንዲሁም በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግሥት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አዶቴ አክዌ የተጋበዙበት የምክክር ሸንጎ ላይ የቀረቡት ሃሳቦች በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ነበሩ።
ሰብሳቢው በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤናና ሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሰብሳቢ ክሪስቶፈር ስሚዝ ደግሞ ኢህአዴግ ከፍተኛ ገንዘብ አፍስሶ ያኮላሽው ኤችአር2003 የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረቂቅ ህግ ከሟቹ ዶናልድ ፔይን ጋር በማዘጋጀት በምክርቤት ለማስወሰን ያስቻሉ ነበሩ።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት የግንቦት 7 ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደ እምነታቸው ንግግር አድርገዋል።
ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። በምክክር ሸንጎው ላይ ከተጋበዙት መካካል ኢህአዴግ በቀጥታ ባለመወከሉ “ያለመመጣጠን (ያለመወከል)” ችግር አልነበረም፡፡ ኢህአዴግም ተገኝቶ ቢሆን ኖር ሊናገረው ከሚችለው በላይ ተናጋሪና ተከራካሪ ስለነበረው የኢህአዴግ መኖር አስፈላጊ አልነበረም የሚል አስተያየት ስብሰባውን በአካል ተገኝተው ከታዘቡና በቀጥታ ስርጭት ከተከታተሉ ወገኖች ተደምጧል።
ያም ሆኖ ግን ምክክሩ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የበላይ ሰው ክሪስ ስሚዝ ቢሮ በመገኘት አሉ የሚሏቸውን መከራከሪያዎች አቅርበው ነበር። የጎልጉል ምንጮች ለማረጋገጥ እንደቻሉት ኢህአዴግ ምክክሩን ተከትሎ ኤች አር 2003 ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ የተጠቀመበትን መንገድ ገና ካሁኑ በድጋሚ ጀምሯል።
ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደር የእግር እሳት ሆኖ ያለፈውን የ1997 ምርጫ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከኢህአዴግ መሪ አቶ መለስ ጋር በርካታ ዲፕሎማቶች ተነጋግረዋል። አንዱ ከኒውጀርሲ ጠቅላይግዛት የአሜሪካ ም/ቤት ተወካይ ክሪስ ስሚዝ ነበሩ።
“ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል የተዘጋጀውን የምክክር ሸንጎ በመሪነታቸው ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው …” በማለት ነበር የገለጹዋቸው። የርሳቸው ገለጻ ታዲያ ከሁለት ዓስርተ ዓመታት በፊት ኢህአዴግ እንዲነግስ ሲወሰን ከቃል በላይ እሳት እየተፉ ንግግር ያደረጉትን ኢትዮጵያዊ አስታወሰ – የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው።
የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው የኢትዮጵያን ተላልፎ መሰጠት በዚሁ በሰኔ ወር ከ22ዓመት በፊት አስረግጠው በማስረጃና በማስጠንቀቂያ በመቃወመ፣ በማሳሰብ፣ እንደማይሆን በመምከር፣ አድሮ እንደሚያቃጥል በማስጠንቀቅ፣ ላቀረቡት ንግግር የክሪስ ስሚዝ ገለጻ በማረጋገጫነት የሚቆም እውነት ይሆናል።
አሜሪካ ራስዋ ቀብታና ባርካ በትረ ሹመት የሰጠቻቸውን ሰዎች ከ22ዓመት በኋላ መልሳ “ገምግሙልኝ” ማለቷ አስገራሚ የሚሆንባቸው ጥቂት አይደሉም። ሰብሳቢው በመግቢያቸው የተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅታዊ መገለጫ፣ ቀደም ሲል ሚ/ር ያማሞቶን በመጥቀስ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸውን መረጃዎች ለተከታተሉ “አሜሪካኖቹ ምን የማያውቁት ነገር አለና ነው የሚጠይቁት ያሰኛል” በሚል የሚገረሙ በርካታዎች ናቸው።
ለዚህ ይመስላል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ታሪካዊውን የኮሎኔል ጎሹ “ትንቢትና የኢትዮጵያ ህዝብን የሚወክል የምልጃ መቃተት” በማስታወስ ቀዳሚ የሆኑት። አስከትለውም “አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት። (ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ)” የሚል መልክት አስተላለፉ።
የጋራ ንቅናቄው መሪ በድርጅታቸው መርህ ላይ ተመሥርተው በሰጡት የምስክርነት ቃል “ህወሓት እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየመራ እንደሆነ፤ መለስ ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) ዓይነት መሪ እንደነበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 22ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለና የዛሬ 8ዓመት በዚሁ ቦታ ላይ ያማሞቶ ኢትዮጵያ በአቋራጭ መንገድ (ክሮስሮድ) ላይ እንደምትገኝ” መናገሩ አቶ ኦባንግ ካስታወሱ በኋላ “መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከስምንት ዓመት በኋላ አሁም አንሻገርም ወይ፤ አናቋርጠውም ወይ” በማለት ተሰብሳቢውን ያስደመመ ለሰብሳቢዎቹ ግልጽ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “ኢትዮጵያውያን የምንጠይቀው በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤ አሜሪካኖች የሚመኩበትን ሰብዓዊ መብት እኛ ተነፍገናል፤ የራሳችን ክሪስ ስሚዝ ይኑሩን ብቻ ነው የምንለው” ካሉ በኋላ በኃይለሥላሴም ሆነ በመንግሥቱ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ዕድላቸውን እንደተነፈጉ አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱም በዚሁ ም/ቤት የዛሬ 22ዓመት በወርሃ ሰኔ ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ የዛሬዋን ኢትዮጵያን መተንበያቸውን አቶ ኦባንግ በንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡ አሁንም የኢትዮጵያውያንን ቁርጠኛ አቋም ምን እንደሆነ ለአሜሪካውያኑ ግልጽ አድርገዋል “አሜሪካ እንድታድነን አይደለም የምንጠይቀው፤ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፤ በነጻነት መንገዳችን ላይ ግን ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ኦባማ ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚያገኙት ጥቂት ደመወዝ ለምርጫው ዘመቻ ረድተው ነበር፤ ከኦባማ ግን የሰማነው ነገር እስካሁን ምንም የለም፤ ነጻነታችንን እየለመንን አይደለም፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን” በማለት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን የነጻነት መንፈስ የቀሰቀሰ ንግግር አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ ለውጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ሰጥቻለሁ እንደሚል ከጠቀሱ በኋላ “ይህ ሁሉ ገንዘብ የት ነው የገባው፤ የት ነው የሄደው” በማለት ኢህአዴግ ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይ ሥልጣኑን እንደተቆጣጠረ፤ ሙስሊሙ መሪውን እንምረጥ ሲል አሸባሪ ተብሎ እንደሚፈረጅ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር አገርና መሬት ብቻ ሳይሆን የምንጋራው በደም የተሳሰርን መሆናችን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
አንድ ጊዜም እንኳን ጦርነት ሰብከውም ሆነ መሳሪያ አንስተው የማያውቁ መሆናቸውን የተናገሩት ኦባንግ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት “አሸባሪ” መባላቸውን በመናገር የኢህአዴግን አሸባሪነት አጋልጠዋል፡፡ እስካሁን በአገራችን ላይ የፈሰሰው ደም በቂ እንደሆነ የጠቆሙት የጋራ ንቅናቄው መሪ፤ በኤድስና ምግብ በማጣት የረደሰብን ዕልቂት በቂ እንደሆነና ከእንግዲህ ወዲህ መጋደል እንደሌለብን ሆኖም ከኢህዴግም ሆነ ከተቃዋሚ በኩል አመኔታ የሚጣልባቸው ሰዎች ስላሉ እስካሁን ያልተሞከረውን የዕርቅ መንገድ (ሥራ) በኢትዮጵያ መከናወን እንዳለበት አቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመሩት ድርጅት መርህና በሚታገሉለት የማዕዘን ሃሳብ ላይ ተተርሰው ሃሳባቸውን አጠቃልለዋል፡፡
በምክክር ሸንጎው ላይ የተገኙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው የንግግራቸውና የማሳሰቢያቸው ማሳረጊያ ሊባል የሚችል መልዕክት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ብርሃኑ “አስተውሉ፣ ልብ ብላችሁ ተገንዘቡ” በማለት ያሳሰቡት ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ የሚጠበቡበት፣ እንዲከሰት የማይፈልጉትን የመጨረሻው ስጋት ነው።
በምክሩ ላይ በቀዳሚነት ምልከታቸውን ያብራሩት ዶ/ር ብርሀኑ ኢህአዴግ የዘረጋው የአፈና ስርዓት ያስመረረው ህዝብ፣ ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚያንኮታኩታቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሆን ብሎ የሚተናኮለው ህዝብ፣ ያለው ብቸኛ አማራጭ ብረት ማንሳት ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል። በቅርቡ የኢህአዴግ የአፈና ስርዓት ፈተና እንደሚገጥመው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አለመረጋጋት ቀጣናውን በሙሉ እንደሚረብሽና የአሜሪካንን ጥቅም በእጅጉ እንደሚጎዳ ዶ/ር ብርሃኑ በግልጽ በማስረዳት አሜሪካ ገንዘቧን በተገቢው ቦታ ላይ ማዋል እንዳለባት ምክር ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተቃዋሚ ኃይሎች አማራጭ ከማጣት የተነሳ ብረት ማንሳታቸውን የጠቆሙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር፤ ሕዝብ ዝም ብሎ በአስከፊ አገዛዝ ሥር እየኖረ እንደማይቀጥል አስጠንቅቀዋል፡፡
በመሆኑም አማራጭ ሲጠፋ ባገኘው መንገድ ሁሉ መብቱን ወደማስጠበቅ እንደሚገፋና በአሁኑ ወቅትም የተቃዋሚ ኃይሎች በመተባበር በኢህአዴግ ላይ ጥቃት መሰንዘር የሚስችላቸውን ብቃትና ኅብረት እንደፈጠሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለውም ኢህአዴግ በምንም መልኩ የማይሰማና በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ለማስረከብ የማይችል መሆኑን በተለይ በ1997 ምርጫ ካስታወቀ ወዲህ በግልጽ የሚከተለው መርህ በራሱ ማስረጃ እንደሆነ ዶ/ር ብርሃኑ በጥያቄ መልክ ለቀረበላቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢህአዴግ የደምሥር የውጭ ዕርዳታ እንሆነ የተናገሩት የግንቦት 7 መሪ አሜሪካ ከአውሮጳውያን ጋር በመተባበርና ለእያንዳንዱ የተሃድሶ ዕርምጃ ቀነ ገደብ በመሥጠት በተሰጠው ገደብ ውስጥ እስረኞች ካልተፈቱ፤ የምርጫ ኮሚሽን ካልተቀየረ፤ ወዘተ በማለት ዕርዳታው እንደሚቆም በማስጠንቀቅ አሜሪካውያኑ ለኢህአዴግ መመሪያ ቢሰጡ ለገንዘብ ሲል ኢህአዴግ ሊታዘዝ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም በድጋሚ የሰብሳቢውን ስም በመጥራት ትኩረት የጠየቁት ዶ/ር ብርሃኑ “የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
ከክሪስ አንደበት
ሰብሳቢው ክሪስ ስሚዝ በምክርቤት ስብሰባ ላይ ድምጽ መስጠት በሚገባቸው ረቂቅ ህጎች ላይ ሲሳተፉ ስለነበር ምክከሩ የጀመረው ከታቀደው ሰዓት 1፡30 ያህል ዘግይቶ በመሆኑ ይቅርታ በመጠየቅ ነበር መንበራቸው ላይ ተሰይመው ንግግር ጀመሩት። የምክክሩ ሊቀመንበር አቶ መለስ የዘረጉት አገዛዝ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ልዩ ባህሪው እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ምክከሩን ከፈቱ። ምክክሩ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲ ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩርና የአሜሪካ መንግሥት ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያመላከት ምክር የሚካሄድበት እንደሆነ አስገነዘቡ።
ኢትዮጵያ እስላማዊ አሸባሪነትን በቀጣናው በመዋጋት የአሜሪካ ደጋፊ አገር ሆና መቆየቷን፣ ሆኖም ግን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚፈጽመው ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት ተጠያቂ ማድረግ እስካሁን አለመቻሉን ሳይሸሽጉ ተናገሩ።
የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን፣ መንግስታዊ ባልሆኑ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ፣ ጋዘጠኞች እንደሚታሰሩ፣ በርካታ ዜጎች ከመሬታቸው እንደሚፈናቀሉ ወዘተ በመዘርዘር አስረዱ።
የአሜሪካ የዕርዳታ ድርጅት – ዩኤስኤይድ እንደሚለው ከሆነ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግልጽ ግንኙነት ማድረግ ወደፊት የዴሞክራሲና የለውጥ ሂደቶችን ለማሳካት ይረዳል ተብሎ ቢታሰብም፣ በክሪስ ስሚዝ አመለካከት ግን እምነቱ ሊተገበር የሚችል ቢመስልም እስካሁን ምንም ፍሬ እንዳላመጣ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።
እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ስልታዊ አፈናና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ለሌሎች አገራት መጥፎ ምሳሌ እየሆነ መሄዱን ሊቀመንበር ስሚዝ ጠቅሰዋል፡፡ ንጹሃን ዜጎች ስቃይ፣ ድብደባ እንደሚደርስባቸው፣ በኤሌክትሪክ እንደሚጠበሱና የግዳጅ ወሲብ እንደሚፈጸምባቸው፣ የአምነስቲ ሪፖርት መዘገቡን ክሪስ ስሚዝ በእማኝነት ተናግረዋል፡፡
ራሳቸው ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ረቂቅ ህግ አዘጋጅተው እንደነበርና በወቅቱ የነበረው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ግን ኢትዮጵያን በአሸባሪነት ላይ ወዳጅ በማድረጉ ምክንያት በነበረው ቸልተኝነት የተነሳ ተፈጻሚ ሳይሆን መቅረቱን አስታውቀዋል። ሚ/ር ስሚዝ እነዚህን ጉልህ ህጸጾች በመጠቆም ምክክሩ ላይ ተናጋሪ እንዲሆኑ የተጋበዙትን ክፍሎች በየተራ በማስተዋወቅ ጋብዘዋል። ከንግግሩ በኋላም ጥያቄዎችን ጠይቀዋል። ሌሎች ተሳታፊዎችም ጥያቄ በመሰንዘር ማብራሪያ እንዲወስዱ ተደርጓል።
ያማማቶ ምን አሉ?
ያማሞቶ በመግቢያ ንግግራቸው መለስን አወድሰዋል። አፍሪካን በዓለም መድረክ ከፍ እንድትል ያደረጉ መሪ በማለት አመስግነው ኢትዮጵያ ተሰሚነቷ እንዲጨምር ያደረጉ፣ ተሟጋችና ጎበዝ ተናጋሪ እንደነበሩ መስክረዋል።
ኢኮኖሚውን አሳድገዋል፣ ኢትዮጵያን በቀጣናውና በዓለም ታዋቂ አድርገዋል፣ በሶማሊያ ተሟጋች፣ በሱዳን አስታራቂ፣ በአፍሪካ የአየርንብረት ጉዳይ ደግሞ አንደበተ ርዕቱ አፈቀላጤ ነበሩ በማለት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ከሚደረድረው በላይ ቃል አከማችተው ምስጋና ቸረዋቸዋል።
ያማማቶ በማያያዝ እንደ አምባሳደርነታቸው በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ አስመልክቶ አቶ መለስን ማነጋገራቸውን ጠቁመዋል። በሰብዓዊ መብቱን መጓደል ዙሪያም በተመሳሳይ መነጋገራቸውን አክለዋል።
ካሊፎርኒያ ሎሳንጅለስ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ወረዳ ተወካይ የምክርቤት አባል ሚስዝ ባስ፤ ያማሞቶን መስቀለኛ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጠያቂዋ “የኢህአዴግ መንግሥት ዋናው ችግር ምንድነው? ለምንድነው ይህንን ሁሉ መከራና አፈና የሚያካሂደው” በማለት የመገረም የሚመስል ጥያቄ ጠይቀዋል።
ያማሞቶ እንደ መንተባተብ ሲሉ “ችግሩ ምንድ ነው?” በማለት ባስ በድጋሚ ጥያቄያቸውን ወረወሩ። “ችግሩ እንዳለ ነው” ሲሉ ደግመው መልስ የሰጡት ያማሞቶ “ጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም አፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንዳሉት ነው፣ የዴሞክራሲ እሴቶች አስፈላጊ ናቸው፣ መጥፎ ህጎች መወገድ አለባቸው፣ እንስራ፣ እንሞክር ብለዋል” አሉና መለሱ።
ኮንግሬስማን ሜዶውስ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ ሁሉን ተቆጣጥሮዋል፤ እኛ አሜሪካኖች ምን ልናደርግ እንችላለን? እንዴት ነው ልናስተካክለው የምንችለው? የሚል ጥያቄ ለያማሞቶ ወረወሩ። ያማሞቶም “ከምርጫው በኋላ ደስተኞች አለመሆናችንን ተናግረናል፡፡ ከበስተጀርባና በፊትለፊት እየሰራን ያለነው ነገር አለ፡፡ ጊዜ የሚወስድ ነው፡፡ ለምሳሌ በሴቶች ላይ የሚደረግ የመብት ጉዳይ አለ እናም ይህንን ከዩስኤድ ጋር እየሰራን ነው” አሉ፡፡
ሜዶውስ የረኩ አይመስልም “እና ያለው ፍርሃት ምንድርነው?” ሲሉ በድጋሚ መልስ መፈለጋቸውን አመለከቱ። “ነግረናቸዋል ፣ ለዘላለም ልትገዙ አትችሉም። ስለዚህ የተቃዋሚውን ተሳትፎ ማበረታታት አለባችሁ ። እነዚህ ተቃዋሚዎች አንድ ቀን መንግሥት ይሆናሉ። ስለዚህ ዝግጅት መደረግ አለበት ብለናቸዋል” የሚል የደፈና መልስ ከያማሞቶ ተሰጠ።
ጋንት፤ የዩኤስ ኤይድ ረዳት ዳይሬክተር
የሴፍቲኔት ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑንና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እየተረጋጋች እንደሆነ፣ ከዚህም ጋር በማከል ኢኮኖሚው እያደገ እንደሆነ ልክ የኢህአዴግ ወኪል መስለው ተናገሩ። ሰብሳቢው ስሚዝ “ቶርቸር በየቦታው አለ እና ይህንን እንዴት ነው ለማስታረቅ ወይም ለማቆም የሚቻለው?” ሲሉ ማብራሪያ ጠየቁ። ሚ/ር ጋንት “አስቸጋሪ ነገር ነው። ቶርቸር እንዳለ እናውቃለን ግን ዋናው ሥራችን መልካም ነገሮችን ለማበረታታት ነው የምንሞክረው” የሚል ምላሽ ሰጡ።
በሚ/ር ጋንት ንግግር ላይ ተንተርሰው ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ክሪስ ስሚዝ፣ ኢትዮጵያ ትምህርትን አስመልክቶ የሚሊኒየም ጎል ተሳክቷል ማለታቸውን ጠቅሰው “ጋንት ግን እኮ ጥራቱ በጣም የዘቀጠ እንደሆነ ነው ሪፖርቱ የሚያሳየው” ሲሉ ሞገቱዋቸው። የዩኤስ አይዲው ዳይሬክተር ጋንት “አዎ ችግር አለ ግን በርካታ መምህራን ተሰማርተዋል በትምህርቱ በኩል ዕድገት አለ” የሚል መልስ መመለሳቸው ለግንዛቤ ያህል የሚጠቀስ ሆኖ አግኝተነዋል።
ያማሞቶና ጋንት ያቀረቡትን ንግግርና ምስጋና ያደመጡ፣ በአካል ተገኝተው የተከታቱተሉ እንዳሉት በምክክሩ ላይ ኢህአዴግ ቢገኝም የሚጨምረው ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል አመልክተዋል።
ዳግም HR2003
የዛሬ አስር ዓመት፤ ኤች አር 2003 በምክር ቤት ደረጃ ከፍተኛ የሸንጎ (ኮንግሬስ) አባላትን ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ ፖሊሲ ሆኖ እንዲጸድቅ ባለመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ።
የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የጎትጓች (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ጎትጓቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘዙና ህጉ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው አዲስ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ህግ እንዳይሆን ተደረገ። ይህንኑ ህግ በማዘጋጀት ከሟቹ የምክርቤት አባል ዶናልድ ፔይን ጋር በወቅቱ ብዙ ደከሙት ክሪስ ስሚዝ የወቅቱን የቡሽ አስተዳደርን በንዝላልነት መድበው አሁን ይሀንኑ ህግ ተግባራዊ የሚደረግበትን አግባብ እንደሚገፉበት አመልክተዋል።
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድረጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ (ህወሓት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱ አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል።
ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረዋል።
ይህ የምክክር ሸንጎ እንዴት ሊዘጋጅ ቻለ ለሚለው ጥያቄ በርካታ ጥረቶች መካሄዳቸውን በመግለጽ ዝርዝር ያላቀረቡት አቶ ኦባንግ ሐሙስ በተካሄደው ምክክር በመካከል ላይ ሚ/ር ስሚዝና ሌሎቹ ተወካዮች በምክርቤት ድምጽ መስጠት ስለነበረባቸው ምክክሩ ተቋርጦ እንደገና ሲጀመር ያልታዩበትን ምክንያት ተናግረዋል። ምክክሩ በተባለው ሰዓት ተጀምሮ ያልቃል የሚል እምነት ስለነበራቸው ሌላ ተደራራቢ የጉዞ መርሃግብር አመቻችተው እንደነበር አመልክተዋል።
“አሁን ስራ ላይ ነኝ” ያሉት አቶ ኦባንግ “እስራኤል አገር ለሁለት ከፍተኛ ጉዳዮች መጓዝ ነበረብኝ። አንዱ የወገኖቻችን ጉዳይ ነው። ሌላኛው ደግሞ የአገራችን ጉዳይ ነው። ከጉዞዬ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት እችላለሁ” በማለት ሁለተኛው ስብሰባ ሲካሄድ እርሳቸው ወደ እስራኤል ለሥራ እየተጓዙ እንደነበር አስታውቀዋል።

Leave a Reply

ግንቦት ሰባት የትግል ቃልኪዳን የሚታደስበት ቀን ነዉ!!


ጋዜጣዊ መግለጫ
 የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪክና በባህል ትስስሩ፤ በረጂም ግዜ አብሮ መኖር ልምዱና እንዲሁም በነፃነትና ዲሞክራሲ ትግል ምዕራፉ ዉስጥ በጋራ ያፈራቸዉና በባለቤትነት የሚጋራቸዉ የተለያዩ እሴቶች አሉት። ቆየት ያሉትንና በኩራት የሚያስፈነድቀንን የአድዋን ድል ወይም በኃዘን ስሜታችንን ሁሌም የሚቆጠቁጡዉን የሰማዕታት ቀን ትተን የአጭር ግዜ ትዉስታችንን ስንፈትሽ ፊታችን ላይ እንደ መስታወት ድቅን እያሉ እራሳችንን ከሚያሳያዩን ቀኖች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ግንቦት 7 1997 ዓም የዋለዉ ታሪካዊ ቀን ነዉ። ይህ ቀን በኢትዮጵያ ህዝብ የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ሂደት ዉስጥ የፀሐይንና የጨረቃን ያክል ገዝፎና ደምቆ የሚታይ ልዩ ቀን ነዉ። ግንቦት ሰባት 1997 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ ብሩህና የወደፊቱን አመላካች የሆነ ፍሬያማ ጉዞ ጀምሮ ፍሬዉን ከማየቱ በፊት የጀመረዉን ጉዞ እንዲያቋርጥ የተገደደበትና ለዘመናት አንገቱ ላይ አንደ ቀንበር ተጭኖበት የቆየዉን የአምባገነኖች ክፉ ጫና አዉልቆ ለመጣል ሲዘገጅ ዝግጅቱ በአጭር የተቀጨበት ጨለማና ተስፋ፤ ቁጭትና ጽናት አንድ ላይ የታዩበት ትንግርታዊ ቀን ነዉ።
ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. በዛሬዉና ለወደፊት በተከታታይ በሚመጣዉ ኢትዮጰያዊ ትዉልድ ልብ ውስጥ ተስፋን፤ ልበሙሉነትን፤ ጅግንነትንና መስዋዕትነትን እየጠቆመ ለዘለአለም የሚዘከር ቀን ነዉ። ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያ ህዝብ በጠመንጃ ኃይል እላዩ ላይ የተጫነበትን ዘረኛ አምባገነን ስርዐት በምርጫ ካርድ ጥሎ ለእድገት፤ ለሰላምና ለአንድነቴ ይበጁኛል ያላቸዉን መሪዎቹን መርጦ ስልጣን ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ታሪካዊ እርምጃ የወሰደበትና አርቆ አሰተዋይነቱን ለአለም ህዝብ ያሳየበት ቀን ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት ሰባት አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ለህዝብ ምርጫና ፍላጎት የማይገዛና የስልጣን ዘመኔን ያሳጥርብኛል ብሎ ያሰበዉን ሁሉ ያለ ርህራሄ የሚገድል ጸረ ህዝብ ኃይል መሆኑን ያረጋገጠበት ቀን ነዉ።
ግንቦት ሰባት ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ቋንቋ፤ ክልልና ኃይማኖት ሳይከፋፍሉት ከዳር ዳር አንደ አንድ ሰዉ በመቆም ያሳየዉ የኢትዮጵያዊነት፤የአንድነትና፣ የወንድማማችነት ስሜት በጻነትና በዲሞክራሲ ትግላችን ታሪክ ዉስጥ ለዘለአለም ሲታወሱ የሚኖሩ የህዝብ ትዉስታዎች ናቸዉ። ሆኖም ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱንና ለዲሞክራሲ ዝግጁ መሆኑን ያረጋገጠዉን ያክል ጠላቶቹም እነሱ ስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሊኖር የሚችለዉ ዲሞክራሲ ከእነሱ ዉጭ ሌላ ማንንም ወደ ስልጣን የማያመጣ መሆኑን በጠመንጃ ኃይል ያረጋገጡበት ቀን ነዉ።
ግንቦት ሰባት 1997 ዓም የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ልብና አዕምሮ ዉስጥ መንግስትን በምርጫ ካርድ መቀየር እንችላለን የሚል ስሜት እንዳይለመልም በህግ ሽፋን ተከታታይ እርምጃዎችን መዉሰድ የጀመረበት ቀን ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብም በበኩሉ ነጻ የመገናኛ ተቋሞች፤ ነጻ ፍርድ ቤት፤ገለልተኛ የምርጫ ተቋምና ለህገ መንግስት የሚገዛ ጦር ኃይል በሌለበት ሁኔታ ዉስጥ የሚካሄዱ ምርጫዎች እንደማይጠቅሙት አዉቆ ወያኔን ማስገደድ የሚችል የትግል እስትራቴጂ የቀየሰበት ቀን ነዉ።
ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ በጠመንጃ ኃይል የነጠቀውን መብት በተቀነባበረ ሁለገብ ህዝባዊ ትግል ለማስመለስና ኢትዮጵያ ዉስጥ የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ብቻ መሆኑን ለማረጋገጥ አዲስ የትግል ስልትና ግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን አምጦ የወለደበት ቀን ነዉ። የግንቦት 7 ብቸኛ አላማ ኢትዮጵያ ዉስጥ መንበረ ስልጣን ትክክለኛ ባለቤቱ ወደ ሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እጅ ዉስጥ እንዲገባ ማድረግና የወያኔን አገዛዝ አገራችን ዉስጥ የመጨረሻዉ አምባገነን ስርአት ማድረግ ነዉ። ግንቦት 7 ይህ አላማዉ ግቡን እስኪመታ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን እንደሚገፋበት ለኢትዮጵያ ህዝብ የገባዉ ቃል ኪዳን ዛሬም ህያዉ መሆኑን ያረጋግጣል።


    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!