Wednesday, May 28, 2014

ጠረኑ የሚከረፋው የግንቦት ሃያ 23ኛ ዓመት “ዓመድ”


(ቀጭኑ ዘ-ቄራ)
amanuel
ሚስት ከቤቷ ጥጋ ጥግ ትንንሽ ጊዜያዊ ጉልቻ ጎልታ ካንዱ ወዳንዱ እየተዛወረች ስራዋን ስትሰራ፣ ስትቀቅል፣ ስታነኩር፣ ስትጋግር፣ ስትወጠውጥ … ድንገት ባንዱ አቅጣጫ እሳቱ መልኩን ቀየረ። ቀስ ብሎ ለካስ ወደ ቤቱ ተዛምቶ ነበርና ቤቱ ነደደ። እሳቱን ያዩ ለማጥፋት እየተሯሯጡ ደረሱ። አልሆነም የቤተሰቡ መኖሪያ ነደደ። ቤቱ የቆመው ለመቀጣጠል በሚያመች ማዋቀሪያ ነበርና ወደ አመድ ተቀየረ። ልክ እንደ ጎሳ ፖለቲካ!! እንደ ግንቦት 20 ዓመዳማ ፍሬዎች!!
እሳቱን ለማጥፋት የሞክሩት ጎረቤቶች አዘኑ። “እሳት በቀላሉ የሚበላው ቤት ይዘሽ ዙሪያውን እሳት ማቀጣጠል አልነበረብሽም” ብለው ገሰጿት። ማጣፊያው ያጠራት ሴት “እባካችሁ ባለቤቴ ሲመጣ አትንገሩት” አለቻቸውና ተማጸነች። ጎረቤቶቿ በንግግሯ ተገርመው “ከሄደበት ሲመጣ የሚገባበት ካገኘ ማን ይነግረዋል” ብለዋት ተሰናበቷት። “ቤት ባገር ይመሰላል” እያለ የሚያስተምረኝ የመሰየሚያ ቤት ባልደረባዬ ታወሰኝ፡፡
የተለመደው ሰላምታዬን በቅድሚያ ኑሮ ለሚያላምጣችሁ … ለኑሮ ችጋር ሰለባዎች ይሁን!! ክረምት/ቡሄ መጣ። ክረምት ስጋት የሆነባችሁ ኗሪዎች “አንድዬ ይከልላችሁ” ከማለት የዘለለ ምርቃት የለኝም። ዶፉን፣ ውርጩን፣ ቁሩን …. በደጅ ሁናችሁ የምትገፉት የ”ኗሪዎች” “አኗኗሪዎች”፣ በወጉም አኗኗሪ መሆን እንኳን ያቃታችሁ፣ ለናንተም ምርጫ ደርሷል። አሁን እናንተን ምን ብለው ይሆን “ምረጡኝ” ብለው የሚጀነጅኗችሁ? ለነገሩ እኮ ዝናብ ሲመጣ የሚያነቡ ቤት ውስጥ ያሉ የውጪ/ደጅ አዳሪዎች ከናንተ ይበዛሉ። በፈረቃ የሚተኙትስ ከናንተ በምን ይሻላሉ? አረ ስንቱ … ቀኝኑ ዘ-ቄራ ነኝ!! ቋሚን አሳንሰው ለሙት መንፈስ በሚገብሩና በሚሰግዱ መመራትም ያው የደጅ ኑሮ ማለት ነው። ያለ ህግ መገዛትም ያው የዱር ኑሮ ነው !! ሲያስጠላ!!
ነብስ ይማር፣ ነብስ ያሽርልን!! ደጅ መውደቅ መከራ ሆነ። ደጅ በወደቁት ላይ ሌሎች ደጅ አዳሪዎች ማከል እንዲቆም የጠየቁ – “ታጨዱ” ። ለሰላማዊ ጥያቄ ያለ ጥይት መፍትሄ የለም ወይ? ያለ ጠብ መብ መንጃ አማራጭ የለም እንዴ? ሰዎች በተሰበሰቡ ቁጥር መደንበር ለምን? ያ ግብር የሚገባበት “የባቢሎን ሽራፊ” በደም ተነከረው የሲኦል ካባው አልቆበት ይሆን? ግራ የሚያጋባ ነው እኮ!! ቀጭኑ ተጨነቀ!!
የኢትዮጵያ ወቅታዊ አቋቋም እዛም እዛም እሳት የለኮሰችውን ሴት ይመስላል። ኦሮሚያ የእሳት ነበልባል አለ። አማራ ክልል እሳት ከረመጠ ውሎ አድሯል። ደቡብ ያለው እሳትም ልንደድ አልንደድ እያለ ነው። ሶማሌ ክልል ያለው እሳት ሃፎቱን እየሰበቀ ነው። አፋር ክልል በራሁ ጠፋሁ የሚል እሳት አለ። ጋምቤላ ከራሷ እሳት ሌላ ከአጎራባቿ የሚነደው እሳት እያጋላት ነው። ሁሉም ጋር እሳት አለ። እሳቱ ከያቅጣጫው ቤንዚን እየተርከፈከፈበት ነው። ኢህአዴግም በየቀኑ እሳቱን እየቆሰቆሰ 23 ዓመታትን “ደም ግብሩ” አድርጎ ልደቱን ለማክበር እየተክለፈለፈ ነው።
ላለፉት 23 ዓመታት የጎሳ ፖለቲካና ጥላቻ እየተጋቱ ያደጉ ትውልዶች ዙሪያውን እየፎከሩ ነው። የኢትዮጵያዊነት ልጓማቸውን ኢህአዴግ በጣጥሶ ስለጣለው ፉከራው ገደብ እንዳይለቅ ያስፈራል። ቀጭኑ ከየአቅጣጫው በሚሰማው በርግጓል። ለነገሩ ያልበረገገ ማን አለ? የገደሉ፣ ያስገደሉ፣ እየገደሉ ያሉ፣ ወደ ፊትም ለመግደል ቃታ ላይ የተጣዱ፣ ከሁሉም በላይ “እርሙና ግፉ በስማቸው የሚፈጸምባቸው” ተጨንቀዋል። ወደ ልቡና ወደ ቀልቡ የሚመለስ አልተገኘም። 23 ዓመታት ለትምህርት አልሆነም። አገሪቱ በጥላቻና በቂም እየነፈረች የሚያዝን መሪ ድምጽ አልተሰማም።
የሃይማኖት መሪዎችም በባቢሎን ቅሪት ተለውሰው፣ በካድሬነት ካባ ተሸፍነው “እረኝነታቸውን” ረስተውታል። “ደ-መና ሲሆን ዝናብ እንደሚመጣ” መለየት አልቻሉም። ታውረዋል። ልቡናቸው ደንድኖ የሎጥን ሚስት ሆነዋል። ደጉ መንፈስ ስለራቃቸው እይታቸው ከከርሳቸው ማለፍ አልቻለም። አማኑኤል ያለው “እብድ” ትዝ አለኝ። “የሚፈራ፣ የሚከበር ጠፋ፣ ማንን ፊት እናስቀድም? ማን ነው ቀልብ ያለው? መቅደስ ውስጥ ማን አለ? ክፋት፣ ክፋት፣ ክፋት….” እያለ ይጮህ ነበር። እንዲህ ስላለ ታስሯል። ተጠፍሯል። ቀናነት መጥፋቱ ያስጨነቀውን “ቀና” ሰው፣ ቀናነት የጎደላቸው አስረው ላርጋክቲን ይወጉታል። ግን ማን ነው በሽተኛ? ቀጭኑ ጠየቀ!!
አማኑኤል የጤነኞች መከማቻ ነው። አማኑኤል በቤት ጣጣ፣ በሃቴቴና በውቃቢ፣ በጋኔን “ግብር አነሰኝ” ቁጣ ከሚመጡት በስተቀር አብዛኞቹ የተነኩበት ጉዳይ ያሳዝናል። ካንዳበታቸው የሚወረወረው ሁሉ እውነት ነው። “አገሬ አይ እድልሽ” እያሉ የሚለፈልፉ፣ “አትግደል፣ አትግደል፣ አትግደል … “ እያሉ የሚወተውቱ፣ “ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ልብ ያለው ያስተውል፣ አዳምጡን፣ ስሙኝ፣ ጆሯችሁን አቁሙ” እያሉ የሚያስጠነቅቁ ውብ ሰዎች አማኑኤል “እብድ” ተብለው አሉ። የሚገርመው ጡረተኛዋ ቀዳማዊት እመቤት ናቸው “የበላይ ጠባቂያቸው” አይ አለም!!
አንድ ጊዜ አንድ የአማኑኤል ሰራተኛ የነገሩኝ ታወሰኝ። አማኑኤል ሆስፒታል ያሉ ታካሚ እህቶች “ውርጃ ይከናወንላቸዋል” አለኝ። የሰማሁትን ማመን አቃተኝ። እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ማብራሪያ አቀረብኩ። ሰራተኞች እንደሚተናኮሱዋቸው/እንደሚገለገሉባቸው ተረዳሁ። አፈርኩ። አመመኝ። አሁን ማን ነው ጤነኛ? የሚገርመው ውርጃ የሚፈጽምላቸው የግል ተቋም እንዳለ መሰማቱ ነው። ጉዳዩን ብዙም ማጣራት ባልችልም “እብዶች” ስለማርገዛቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ አለ። ወ/ሮ አዜብ እንደ አሁኑ ሳይተነፍሱ ይህንን እንኳን ለፍርድ ቢያቀርቡ ምንኛ ከኖረው ሃጢያታቸው ሁሉ በነጹ ነበር!! መስመር ሳትኩ መሰል ወደ መነሻዬ ልመለስ።
አዎ ቤት አገር ነች። ቤት ከተቃጠለ መጠለያ የለም። በተለይ በግራም በቀኝም መሸሻ የሌላቸው ምስኪኖች ያሳዝናሉ። “አለን አለን ሲሉ፣ ይናዳል ገደሉ” ተብሎ የለ!! ከተናደ ተናደ ነው። ደርግ ሲናድ ጥላ ሳይቀር ያስደነግጥ ነበር። ሲናድ ጥላም ያስፈራል። ሲናድ ስንቄን፣ ሃብቴን፣ ወርቄን፣ ፋብሪካዬን፣ ህንጻዬን፣ መኪናዬን፣ ቤተመንግስቴን…. የሚባል ዘባተሎ ሃሳብ የለም። ሁሉም እንደ ጉም ይተናል። እንደ ሴትየዋ ቤት “ዓመድ” ይሆናል። ዓመድ!! ታዲያ ያ-ክፉ ሃሳብ ሳይሰለጥን ሁላችንም ወደ ልባችን ብንመለስስ? ስለ ሰላም ብናለቅስ? ይቅር ባይነት “ዓመድ” ከመሆን ይሰውራልና !! ከግንቦት ሃያ ያተረፍነው የጎሳ ፖለቲካ ምሱ ዓመድ ነውና 23ኛውን “በዓል” የግንቦት 20 ዓመዳማ ፍሬዎች!! ብንለውስ? ክብር ይህንን ጊዜና የተሰውበትን ዓላማ ሳይመለከቱ ላለፉ ታጋዮች!! ግን ይህንን በደማቸውና ባጥንታቸው ላይ የተገነባውን “ዓመድ” የሚያደርግ የፖለቲካ ቀመር ከሚያዩት ሞታቸው አይሻልም? ፍሬዎቹን ኢህአዴግ በሰፊው ስለሚመጣባቸው አልፌያቸዋለሁና። ለማመጣጠን ኢቲቪን ይመልከቱ!!

Ethiopian Demonstration, protests against The Ethiopian regime on 8th Ma...

Monday, May 26, 2014

የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ስልጣናቸውን በህዝብ ፈቃድ ላይ እንዳልቆመ አሳምረው ያውቃሉ። ነጻ የህዝብ ምርጫ ቢኖር ምን እንደሚሆኑ የዛሬ ዘጠኝ አመት በአይናቸው አይተዋል፣ በጀሮቸው ሰምተዋል። ከዚያ ተመክሮ ተነስተው ዳግም የህዝብ ፈቃድ ላለመጠየቅ ምለዋል። ቅዱሱን የዴሞክራሲና የፍቅር መንገድ ሳይሆን ሳይጣናዊውን የከፋፍሎና አናክሶ የመግዛትን መንገድ ዋና ምርጫቸው አደርገው ከወሰዱ ሰንብተዋል። የፍትህና የዴሞክራሲ ሂደት በኢትዮጵያ እነሱ እስካሉ ድረስ እንዳይነሳ አድረገው ቀብረውታል። በራሳቸውና ጥቅማቸው ላይ ኮሽታ በመጣባቸው ቁጥር ችግሩ በምስኪኑና የነሱ ሰለባ በሆነው ህዝብ ውስጥ መካከል እንደተፈጠረ ግጭት ለማስመሰል እና ለማድረግ የማያደርጉት ነገር የለም።
ወያኔ ሰሞኑን በመላው የኦሮሞ ተወላጆች የመጣበትን ተቃውሞ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ጠብ ለማድረግ ያላደረገው ነገር የለም። መሰረታዊ የሆነውን የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ የባህርዳር እና በሌሎች የሀገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች ደግፈው ሂወታቸውን ያጡለትን የጋራ የወገንን ጥያቄ ለመቀልበስና፣ የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ጠብ ለማድረግ ያላደረገው ጥረት የለም።
መሰረታዊ የሆነውን የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ በጥይት ብቻ ሊመልሰው እንደማይችል የተረዳው ወያኔ፤ በግርግሩ ውስጥ አማሮችና ኦሮሞዎች ደም እንዲቃቡና እንዲጋጩ አድርጎ ገላጋይ ለመምሰል የሚያደርገው ሙከራ ባይሳካለትም ይህን ተንኮል በህዝቡ ውስጥ የመትከል አባዜ ስራውን በስፋት ተያይዞታል። ሰሞኑን በመላው ኦሮምያ ካድሬ በማሰማራትና ገላጋይ በመምሰል ዋናውን የወያኔ መሬት ዝርፊያ ይቁም የሚለውን ጥያቄ በማለባበስና በማፈን ዘዴ ላይ ይገኛል።
ወያኔ ይህን ስልት የመረጠው ወያኔን የምንቃወም የነጻነትና የዴሞክራሲ አንድነት ሃይሎች የትብብር ደረጃ ያለበትን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት ነው። በርግጥ ይህን ሳይጣናዊ በር የከፈትንለት እኛው የነፃነትና የዴሞክራሲ ሃይሎች ነን። በመካከላችን የተቀናጀና የተባበረ እንቅስቃሴ ማድረግ አለመቻላችን በብዙ መልኩም ህዝባችን የሚያስተባብር የጋራ አመራር በመጥፋቱ ነው።
የወቅቱም ሆነ የዘላቂው ችግር መፍቻ ይህ የዴሞክራሲና የነጻነት ሃይሎች የተግባር ህብረትና ቅንጅት መሆኑን ለመማሪያ ከሰሞኑ ተሞክሯችን የበለጠ መማሪያ ያለ አይመስለንም። የወያኔ ጉልበት የተቃዋሚዎች ክፍፍል ብቻ ነው። እኛ ተጠቂዎቹ የችግሩን ማስወገጃና የዘላቂ የሀገራችንን ህይዎት የሚመራ የጋራ ራእይ አለማበጀታችን ነው። ሌባው ህዝባችንን የሚከፋፍልብን በራችንን በርግደን ስለከፈትን እና ለመከፋፈል ስለተመቸናቸው ነው። ይህን በር ከፍተን እስካቆየነው ድረስ የህዝባችን ደም በግፍ መፍሰሱ፣ ህዝባችን መዘረፉና በውርደት መኖሩ ይቀጥላል።
ከወያኔ ፍትህም ሆነ የህዝባችን መሰረታዊ ችግር መፍትሄ አይጠበቅም። ከእባብ እንቁላል ርግብ መጠበቅ አይቻልምና።
ግንቦት 7 የየፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በኢትዮጵያ የአንዱ ብሄረሰብ ችግርየሚፈታው የሁላችንም ችግር ሲፈታ መሆኑን ያምናል። የተናጠል ትግላችን ከሚያስጠቃን በቀር ውጤት የለውም ብሎ ያምናል።
በእኛ የግንቦት 7 አስተያየት የሰሞኑ የወያኔ ጭካኔና ደባ ከቁጭት ዘሎ የዘላቂ መፍትሄ መፈለጊያ እድል አድረገን ልንጠቀምበት ይገባል። ይህንና ተመሳሳይ ጥቃቶችን ተባብረን መመከት ባቃተን ቁጥር የህዝባችን መከራ እያራዘምን ነው። በዚህ ወቅት ህዝባችን ከአገራችን አጽናፍ እስከ አጽናፍ አንድ ድምጽ መሰማት መቻል ይኖርበታል። የሁላችንም አይን ያን ጊዜ ወያኔና ጉጅሌዎች ላይ ብቻ ይሆናል። ወያኔ የሚደግስልን የጎን ለጎን ግጭት ድግስ የሚከሽፈው ይህን ጊዜ ብቻ ነው።
በሚደርሱን መረጃዎች መሰረት ወያኔ በተለይ በኦሮሞ ህዝብና በሌላው ብሄረሰቦች መካከል ስር የሰደደ ጠብ ለመፍጠር በመራወጥ ላይ ይገኛል።
ለዚህ ተግባር የሚሆን የሰው፣ የገንዘብና የሚዲያ ሃይል አደራጅቷል። የተደገሰው የብሄር ለብሄር ግጭት ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ ብሄረሰብ ውስጥ ክፍፍል በመፍጠር ህዝብ የማባላት ድግስ ነው። ወያኔ ለውጪ አሳዳሪዎች የህዝቡን ደም የማፈሰው የእርስ በእርስ ግጭት ለማስወገድ ነው የሚል መልስ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ራሱ የሚያደርሰውን ጥፋት ሁሉ በተቃዋሚዎቹ እና በራሱ ህዝብ ውስጥ ባሉ ሰለባዎቹ ላይ ለማመካኘትና በዚሁ እብሪቱ ለመቀጠል መወሰኑን አረጋግጠናል።
ግንቦት 7 ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ህዝቡ የወያኔ የተንኮል መሳሪያ እንዳይሆን የልዩነት በሩን እንዲዘጋ የቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ለሁሉም የነጻነትና ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች የእንተባበር ጩኸቱንም ደግሞ ያሰማል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Saturday, May 24, 2014

መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ!


በ10 ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባን አጥለቅልቋታል።
ስላማዊ ሰልፉን የጠራው በፕሮፌሰር መራራ ጉድና የሚመራው መድረክ ፓርቲ ነው።
ሃሳባችንን በነጻነት መግለጽ እንፈልጋለን ! ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ይከበር!!!
ተቃውሞ ባሰም የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን !!!
መድረክ ለኦሮሞ ተማሪዎች ያለውን አጋርነት ይገልጻል !! ቪቫ መድረክ !!!
መድረክ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከሚጠበቀው በላይ በድምቀት የተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሱን መርጃዎች ይጠቁማሉ።
ግምቱ በ10ሺዎች የሚገመት የአዲስ አበባ እና አካባቢ ከተሞች ህዝብ ዋና ከትማዋን በሰልፍ አጥለቅልቋታል፤ የዛሪው ሰላማዊ ሰልፍ ድንቅ ነው፤ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዘኛ መፈክሮች ያነገቡ ከአዛውንት እስከ ወጣት እና ሴቶች ሰልፈኞች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
“Stop the massacre!. Bring culprits to justice!
Free all political prisoners! Stop the land grab!”
Hiriira nagaa Madrek. “Stop killing peaceful protesters”
” Stop eviction of farmers in the name of development”.1939864_10152474121284743_977829773025148542_n
10300805_881910458504953_7373829237705832672_n
10338305_881910225171643_7532438988631167186_n
10349138_881910438504955_3488204613342913393_n

Monday, May 19, 2014

”Resistance……. Because if we fight we might lose but if we don’t fight we’ve already lost”!!


It is now our duty to carry on the work those heroes who died for justice, freedom, equality and peace throughout Ethiopia. These great people have done their share. It is we the living who must now do our own share to make sure they do not die in vain and to make sure that justice is done.
We owe the same thing to all our extraordinary freedom fighters, the prisoners of conscience from every ethnic group, the Zone9 Bloggers, the Oromo students, journalists,human rights activists and all freedom-loving people who are locked up in prison by ethnic apartheid regime of the TPLF.
It is time to cross the line and advocate for the sisters and brothers throughout Ethiopia. There are heroes from every ethnic group, models of how to live humanly in this fallen world. It is the responsibility of the living and the free to carry on the work they have started.
It is the responsibility of every free Ethiopian to carry on the torch, not only for themselves, but also for their children, their grandchildren and those yet to be born. These are all our family members. It is time for the greater family of Ethiopians to intervene to stop our own destruction and to replace it with justice, equality, morality and love!
10308363_662660357139353_4799078142732101947_n

Posted by: Kumilachew Gebremeskel Ambo

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ? (ተመስገን ደሳለኝ)



 ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ
በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን
አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ
ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ
አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን
በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡

 አርባ አራት ዓመት ወደኋላ…
 በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ እንቅስቃሴ
መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962 ዓ.ም በአራት ገፅ
ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ
የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር
መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ
በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-

“…ማንንም ሰው የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃ የቱ ነው ብላችሁ
ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ባሕል የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ ብሔራዊ ልብሳችሁ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የአማራ
ወይም የትግሬ ይላችኋል፡፡”

 ይህ ሀቲት በወቅቱ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ቁጣ ከመቀስቀሱም በላይ ዋለልኝን በ‹ፀረ-አማራና ትግሬነት› አስፈርጆ
ለውግዘት ዳርጎት ነበር፡፡ እራሱም ቢሆን በአንድ የዩንቨርስቲው መድረክ ላይ የተሰነዘረበት ከባድ ተቃውሞ በፈጠረበት
ብስጭት ‹‹እኔም አማራ ነኝ፤ ያውም ከአማራ ሳይንት-ቦረና›› ማለቱ ይታወሳል (ቦረና በተለምዶ አማራ መጥቶበታል
የሚባለው አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡ ግና፣ ዋናው ጥያቄ የእርሱ አማራ መሆን ያለመሆን አይደለም፤ እዚህ ድምዳሜ ላይ
የደረሰበት ምክንያት ከተጨባጩ እውነታ ጋ ምን ያህል ይዛመዳል? የሚል ነው፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ ከዚህ ጽሑፍ በፊት
ብሔር ተኮር ጎዳዮችን አንስቶ ካለማወቁም በዘለለ፣ ሌሎች ሲያነሱ ፅንፈኛ ተቃዋሚ ስለነበረ ነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ ኢብሳ
ጉተማ (ኋላ ላይ የኦነግ መስራችና አመራር የሆነው) ‹‹ኢትዮጵያዊ ማነው?›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ግጥም እጅግ ተናድዶ
‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ግጥም ታቀርባለህ? ዘረኛ ነህ፤ ኢትዮጵያውያንን የመከፋፍል ዓላማ ነው ያለህ?›› በማለት
እስከመቃወም መድረሱ የክርክሩ አንዱ ጭብጥ ነው፡፡

 ታዲያ ዋለልኝ መኮንን ድንገት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ከምን የተነሳ ይሆን? በርግጥ ለዚህ ድንገቴ የአቋም ለውጥ ሶስት
መላ-ምቶች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹በአፄው ሥርዓት ላይ አሴረዋል› ተብለው ከተከሰሱትና ‹ኦሮሞ እየተጨቆነ
ነው› የሚል እምነት ከነበራቸው ጄነራል ታደሰ ብሩ ጋር በታሰረበት ወቅት፣ በጄነራሉ ስብከት አመለካከቱ ተቀይሮ ሊሆን
ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹መገንጠልን መደገፍ በመጨረሻ የማትገነጠል ሀገር እንድትኖር ያደርጋል››
በማለት ከተከራከረበት ከራሱ አቋም ጋር የሚያያዝ ነው፤ ሶስተኛው ‹የሻዕቢያ (ኤርትራውያን ተማሪዎች) አሊያም የአሜሪካኑ
የስለላ ተቋም (ሲ.አይ.ኤ) መጠቀሚያ ሆኖ ነው› የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከዋለልኝ ጀርባ ‹ስውር እጅ›ን ለመፈለግ
ያስገደደው በጊዜው ብዙሁ ተማሪ ለሀገሪቱ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ‹የንጉሣዊው አስተዳደር ኋላቀርነት እና ስግብግበነት ነው› ብሎ
ከማመኑም ባለፈ፣ ከፌዴራላዊ ይልቅ የቻይና ኮሙኒስታዊ ሥርዓት አድናቂ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የተማሪውን
እንቅስቃሴ በመምራት በዘመኑ ከዋለልኝ የላቀ ተሰሚነት የነበረው ጥላሁን ግዛው ‹‹ጎሰኝነትን›› በአደባባይ አጥብቆ ይቃወም
እንደነበረ፣ በ1968 እ.ኤ.አ የታተመው ‹‹Struggle›› ቅፅ 3፣ ቁጥር 1 መጽሔት ጋር ያደረገውን ቃለ-መጠይቅ መጥቀስ
ይቻላል፡-
 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
2


‹‹በመጀመሪያ ደረጃ በጎሰኝነትና በሶሻሊዝም መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ጎሠኝነት በተወሰነ አካባቢ ብቻ
የሚቀርና አካባቢ ቀመስ ነው፡፡ ሶሻሊዝም ግን ዓለም ዓቀፋዊ ነው፡፡ …እንደ ዩንቨርስቲ ተማሪነታችንና እንደ እጩ
ምሁርነታችን የሕብረተሰባችንን አቋም ከመደብ አንፃር መተንተን እንጂ በጎሣ መከፋፈል አይገባም›› ማለቱ ይታወሳልና፡፡
 የህወሓት-ውልደት

 ዋለልኝ መኮንንን ‹‹የብሔር ጭቆና›› ትንተናን መሰረት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የፋኖ ድርጅቶች መመስረታቸው
አይካድም፡፡ ከእነዚህም መንግስታዊውን ሥልጣን ለመጨበጥ የበቃው ህወሓት አንዱ ነው፡፡

 የአማራና ትግሬ ጨቋኝነትን የሚያውጀው ጽሑፍ በተሰራጨ በአምስተኛው ዓመት የትግርኛ ተናጋሪውን ብሔራዊ ጭቆና
ለማስረገጥ ጽሑፉን እንደ ሰነድ ማስረጃ ቆጥረው ‹‹ትግራይን ነፃ እናወጣለን!›› ያሉ ፋኖዎች ነፍጥ አንግበው በረሃ
ቢወርዱም፣ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት አካባቢ ‹‹እንታገልለታለን›› በሚሉት ዘውግ ተወላጆች ሳይቀር መናፍቅ
ተደርገው መወገዛቸው ይታወሳል፡፡ ደራሲና ገጣሚ አስማማው ኃይሉም ‹‹ኢህአሠ›› በተባለው መጽሐፉ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹በ1969 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ በእምባ ሰገንይቲ ወረዳ ነበለት አካባቢ ሽምዕጭ ተብሎ በሚጠራው መንደር
የህወሓትና የኢሕአሠ አባላት ሕዝብን ለመቀስቀስ ተገኝተው ነበር፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የድርጅታቸውን ዓላማ
ካስረዱ በኋላ ያካባቢው አዛውንት ማሳረጊያውን ንግግር አደረጉ፡፡ አዛውንቱ መሔድ የሚሳናቸው ስለነበሩ ሰዎች
ደግፈው ወደ በቅሏቸው እንዲያወጧቸው ከጠየቁ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ፡፡ ወደ ህወሓት አባላት
እጃቸውን ዘርግተው ‹እናንተ ከሆዳችን የወጣችሁ ልጆቻችን ናችሁ›፤ ወደ ኢሕአሠ አባላትም ፊታቸውን አዙረው
‹እናንተ ደግሞ ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት መጥታችሁ ለእኛ ስትሉ ነው የምትታገሉት፡፡ የሆነው ሆኖ እኛ የትግራይ
ሰዎች ሆነን ስንቀር ኢትዮጵያ ከማን ጋር ልትቀር ነው? ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዊ ከሚል ጋር ነው የምንወግነው›
ሲሉ ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡›› (ገፅ 235)

 ህወሓት በትግራይም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን አገዛዛዊ ጭቆና፣ የብሔር አስመስሎ እስከ መገንጠል
ቢንደረደርም፣ የገጠመው ተቃውሞ ፕሮግራሙን ለመከለስ አስገድዶታል፡፡ ዘግይቶ ላገኘው ድጋፍም ቢሆን ከዘውግ ተኮሩ
ተረት-ተረት ይልቅ አምባ-ገነናዊው የደርግ አስተዳደር የወለደው ሽብርና ጭፍጨፋ የተሻለ ጠቅሞታል፡፡ ለዚህም በዛሬይቷ
ትግራይ ከሶስት ያላነሱ ፀረ-ህወሓት ድርጅቶች መኖራቸው ማሳያ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

 በሌላ በኩል ከህወሓት ምስረታ አንድና ሁለት ዓመት አስቀድሞ ወደ አደባባይ የመጡት ኢህአፓና መኢሶን የትግል
አጀንዳቸው የመደብ ቅራኔ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ይህ ግን በወቅቱ ከህወሓትም በከረረ መልኩ ‹‹የብሔር ጥያቄ በመገንጠል
ብቻ ነው የሚፈታው›› የሚል እምነት ተከታዩ ኦነግን ህልውና አያስክድም፡፡ እዚህ ጋ የምንመለከተው ሌላኛው ግራ አጋቢ
ጉዳይ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ሠልፍ (በ1957 ዓ.ም) አስተባብሮ
የሕግ-መወሰኛው ምክር ቤት ድረስ የመራው ባሮ ቱምሳም (በአብዮቱ ሰሞን የኢጭአት የአመራር አባል ነበር) ሆነ፤ የመኢሶኑ
ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ኃይሌ ፊዳን የመሳሰሉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቆች፣ ከኦነግ በተቃራኒው ከብሔር ይልቅ
የመደብ ጥያቄ አቀንቃኝ የነበሩ መሆኑን ነው፡፡ በነገራችን ላይ በግሌ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ብያኔ እነዋለልኝ የለጠጡትንና
ያጎኑትን ያህል እንኳ ባይሆንም እንደገና መከለስ እንደሚያስፈልገው አምናለሁ፡፡

 የሆነው ሆኖ ህወሓት መንግስታዊውን ሥልጣን በጨበጠ ማግስት ‹የሰነበተውን የብሔር ቅራኔ በማያዳግም ሁኔታ የሚፈታ›
ሲል ያንቆለጳጰሰውን ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ቢተገብርም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን የመግታት አቅም
እንደሌለው ለማረጋገጥ የአንድ እጅ ጣቶች ያህል ዓመታት እንኳን አልፈጀም፡፡ በደቡብ በጉጂ እና ጌዲዮ፣ በጉጂ እና ቡርጂ፤
በጋምቤላ በአኝዋክ እና ኑዌር፤ በቤንሻንጉል በጉምዝ እና በርታ መካከል የተከሰቱት የይገባኛል ግጭቶች በማሳያነት ይጠቀሳል፡፡

 የፌዴራሊዝሙ ቀዳዳዎች
 ዘውግ ተኮር ፌዴራሊዝሙ፣ ገና ከጠዋቱ ለከፋ ዕልቂት ሊዳርግ እንደሚችል በማስታወስ ይሰሙ የነበሩ የተራዘሙ
ጩኸቶችን ችላ ብሎ ዛሬ ላይ ቢደርስም፤ ለፕሮፓጋንዳ በሸነቆራቸው ቀዳዳዎች እየገባ ያለው ከባድ ንፋስ ከራሱ አልፎ
ሀገሪቷንም ከበታኝ አደጋ ፊት አቁሟታል፡፡ ለዚህም አገዛዙ የፈጠራ ትርክቱን ለማስረፅ የሄደበት የኑፋቄ መንገድ የአንበሳውን
3

ድርሻ ይወስዳል፡፡ በፓርቲው ካድሬዎች በኩል በየዕለቱ የሚዘራው የጥላቻ ፖለቲካ፣ ሐውልት ማነፅ፣ ከፋፍሎ ማቆም እና
መሰል ስልቱ በተጨማሪ ሜጋ በሚያሳትማቸው መጻሕፍት እልቂት ጠሪ ዘውግ ተኮር ቅስቀሳዎችን እስከማሰራጨት መድረሱን
ተመልክተናል፡፡ ለአብነትም የሚከተለውን ግጥም ልጥቀስ፡-

“ነፍጠኞች እቤታቸው በክብር ይጎለታሉ፣
 እኛን በኃይል አስገድደው ያሰራሉ፣
 ቁጥቋጦ እንደምትመነጥረው መንጥራቸው
 ወደመጡበት ወደ ሸዋ አባራቸው፡፡” (“ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ቅፅ 3፤ ገፅ 145)

 ግና ‹‹ሸዋ›› ሱዳን ወይም ግብፅ አይደለምና ዛሬ ከጉራፈርዳ እስከ ደንቢዶሎና ጊምቢ ለተተገበረው የማባረር ዘመቻ ዋነኛው
ተጠያቂ የሥርዓቱ ኤጲስ ቆጶሳት መሆናቸውን ግጥሙ ያስረግጣል፡፡ በግልባጩ እነዚህ ሰዎች በ97ቱ ምርጫ ዋዜማ፣ ሚያዚያ
30 ቀን መስቀል አደባባይ ቅንጅት በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ አቶ በድሩ አደም ‹‹ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን››
ማለታቸውን፣ ወደ ዘውግ ጥላቻ ከመቀየራቸውም በላይ፣ የቅንጅቱን አመራሮች ለቅመው ካሰሩ በኋላ የሰውየውን ንግግር
‹‹የዘር ማጥፋት ሙከራ!›› ሲሉ ለመሰረቱባቸው ክስ በማስረጃነት ማቅረባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ በዚያው ሰሞን አቦይ
ስብሃት ነጋም የብአዴን ጓዶቻቸውን ‹‹እኛ ወደመቀሌ ስንባረር፤ እናንተን መንዝ ላይ አራግፈን ነው የምንሄደው!!›› አሉ
መባሉም ጉዳዩ በራስ ላይ ሲደርስ ምን ያህል አሳማሚ እና ለበቀል እንደሚያነሳሳ ሁነኛ ጥቁምታ ቢሰጥም፣ ገዥዎቻችን
ትምህርት ሊወስዱበት አለመቻላቸው ያስቆጫል፡፡ እንዲያውም ከምርጫ 97 በኋላ በዩንቨርስቲዎች ግቢ የሚነሱ
ተቃውሞዎች ዘውግ-ተኮር ወደመሆን ነበር የተሸጋገሩት፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዩንቨርስቲዎች በተናጠል (በህወሓት፣
ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን) ስር ማደራጀት የጀመረው ከዚሁ ምርጫ በኋላ እንደነበረ አይዘነጋም፤ ለእንዲህ አይነቱ
የፓርቲው ተልዕኮ ደግሞ እንደ ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ አይነት የገዥው-ፓርቲ መንፈስ የሰረፀበት ‹‹ምሁር›› ጠቀሜታን
ለመረዳት አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ያለበትን ሁኔታ መቃኘቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ሁለት አስርታት የህወሓት
አባልና ደጋፊ ተማሪዎች የግቢውን መንፈስ አይመረምሩም (አይሰልሉም) ነበር እያልኩ አይደለም፤ በግላጭ የጓደኞቻቸውን
እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ሪፖርት ያደርጉ ነበርና፡፡ በአናቱም የዘውግ ተኮር ፖለቲካው መተግበር በጀመረበት ወቅት ወደ
ትምህርት ቤት የተላኩ ልጆች፣ ዛሬ ለዩንቨርስቲ መብቃታቸው፣ አጀንዳው በቅፅበት ሊፈፀም የመቻሉን እውነታ በኦሮሚያ
ሰሞኑን የተመለከትነው ቀውስ በቂ ማሳያ ይሆናል፡፡

 የተጭበረበረው አጀንዳ
 ‹የብሔር ጥያቄ ዋነኛው የቅራኔ ቅርፅ ነው› የሚለው ህወሓት ይህን ጥያቄ መፍታት ሥርዓታዊ ግብ እንደሆነ እስኪሰለቸን
ቢደሰኩርም፤ አጀንዳውን ከማጭበርበሪያነት የዘለለ ዋጋ አልሰጠውም፡፡ እናም ታሪክ ቢያንስ በዚህ በኩል በበጎ
እንደማያስታውሰው ለመናገርም ብዙ ማስረገጫዎችን መጥቀስ አይገድም፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን እየናጣት ያለው፤ ጥያቄያችን
አልተመለሰም› የሚሉ ብሔርተኛ ቡድኖች መበርከት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በስያሜ ደረጃ እንኳን (መሬት ላይ ያላቸውን
ጉልበት ትተን) ከአስራ አንድ የማያንሱ ተገንጣይ ንቅናቄዎች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ የእነዚህን ከኦጋዴን እስከ ጋምቤላ፤
ከቤንሻንጉል እስከ አፋር ድረስ ያሉ አማፅያን እንቅስቃሴን የጥቂት ልሂቃን ቅብጠት አድርጎ መውሰድ ርትዕ አይሆንም (ስለምን
ቢሉ ደርግም ህወሓትን የሚያስበው እንዲያ ነበርና)፡፡ እናም ከትልቁ ኦሮሞ ጥያቄ መጠለፍ ጀምሮ፤ እነዚህ ጉዳዮች አስቀድሞ
ግንባሩ የብሔር ጥያቄን ለሥልጣን መወጣጫ ብቻ ለመጠቀም ማስላቱን ይጠቁሙናል፡፡

 ሌላኛው ጭብጥ አሁንም ድረስ ማንነት ተኮር ጥያቄዎች አለመቆማቸው ነው፡፡ ከቅማንት እስከ ወለኔ እና ቁጫ ድረስ ያሉት
‹‹ማንነታችን ታውቆ ዞን ይሰጠን›› ጩኸቶች ማቆሚያቸው የቱ ጋ እንደሆነ ራሱ ኢህአዴግም የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡
በግልባጩ ለእነዚህ ሶስት የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄ በቅርቡ የሠጠው ምላሽ ጭፍለቃ መሆኑን ስናስተውል፤ ‹ተነሳሁለት›
ከሚለው የብሔር ጭቆናን ማጥፋት አኳያ የሚነግረን ሀቅ ሥርዓቱ የሄደበትን ቁልቁለት ብቻ ነው፡፡

በሶስተኛነት ከዚሁ ጋር አያይዘን ልናነሳው የምንችለው ርዕሰ ጉዳይ የመገንጠል መብት ነው፡፡ ከዋለልኝ እስከ ጥላሁን ታከለ እና
ቱሞቱ ሌንጮ (ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ) ድረስ የነበሩ የዘመኑ ትውልድ መንፈስ ተርጓሚዎች መገንጠልን ሕብረ-ሱታፌ
(ሶሻሊስታዊ) ሥርዓት ለመገንባት መዳረሻ መንገድ አድርገው ቢያቀርቡትም፤ ጥራዝ ነጠቆቹ ህወሓቶች ሕገ-መንግስቱ ውስጥ
ቀርቅረውታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ‹‹መገንጠልን ለመከላከል ነው›› ቢሉም፤ ከፌደራሊዝሙ አወቃቀር አኳያ
‹የማይተገበር መብት› ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በዋናነት ሁለት ነጥቦች ይነሳሉ፤ ‹እንደ ስታሊኒስቷ ሩሲያ
4

ሁሉ መብቱ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቢካተትም፣ የማዕከላዊ መንግስቱ ሥልጣን ፍፁማዊ መሆን እንዳይተገበር ያደርገዋል›
የሚለው የመጀመሪያው ነጥብ ነው፡፡ ሁለተኛው የመብት አፈፃፀሙ ራሱ በተለያዩ አስገዳጅ ተዋረዳዊ ትግበራዎች መጠላለፉ
ነው፡፡ በተለይም ሁለትና ከዚያ በላይ ዘውጎችን ያቀፉ ክልሎች የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሱ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው
ለመረዳት የክልሎቹን አወቃቀር መመልከቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ነጥቦች ስንነሳ የመገንጠል ግብ ያላቸው
እንቅስቃሴዎች በትጥቅ ትግል አገዛዙን ካላስወገዱት በቀር በሕገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ሊተገበሩ
አለመቻላቸውን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ሁነትም ሥርዓቱ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያነበረው ከፋፍሎ ለመግዛት እንጂ፤
እስክንደነቁር በጩኸት ስለሚነግረን ‹‹ጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች›› መብት ደንታ ኖሮት እንዳልሆነ ያስረግጥልናል ብዬ
አስባለሁ፡፡

 ግን እስከመቼ?
 በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ኃይለስላሴ ቀጥሎ ረዘም ላለ ዓመታት ሀገሪቱን የመምራት ዕድል ያገኘው ኢህአዴግ
የተሻለች ሀገር የመገንባት በርካታ ዕድሎችን አምክኗል፡፡ ወደሥልጣን በመጣ ማግስት ዘውገኝነትን የመንግስታዊ መዋቅሩ
ብቸኛ ገፅ ሲያደርገው፣ ከብዙ ጫፎች ከተነሳበት ከባባድ ተቃውሞዎች መሀል፡- ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝሙ ማሕበረ-ባሕላዊ
መሰረቱ በጣም የተሳሳተ መሆኑን እና የዘውግ ማንነትን ብቸኛው የክልሎች ድንበር አሰማመር መነሻ ማድረግ ለእርስ በእርስ
የዜጎች ትንቅንቅ ያጋልጣል የሚሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ ሥርዓቱ ይህን ጆሮ ሰጥቶ ከማዳመጥ ይልቅ ቢያፈገፍግም፣ ያሳለፍናቸው
ሃያ ሶስት ዓመታት በሞቶችና በመከራዎች የተፃፉ ኩነቶችን አሳይተውናል፡፡ ‹‹ባለሥልጣን›› እና ‹‹ሥልጣን የለሽ›› (ባለቤትና
መጤ) በሚል ጨዋታ፣ በየክልሎቹ የሚገኙ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከክልሉ የሥራ ቋንቋ ውጪ በመናገራቸው ብቻ፣ አንዳችም
ተቋማዊ ውክልና እንዳያገኙ ማድረጉ፣ ከየአካባቢዎቹ በግፍ ለተፈናቀሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው መነሻ ሆኗል፡፡
አዲሱን የአዲስ አበባ የማስፋፊያ ዕቅድ ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞም ሌላ ቅርፅ ወደመያዝ መሻገሩ አንዱ
ሰሞነኛ ማሳያ ነው፡፡ በምዕራብ ወለጋ ለረዥም ጊዜ ኑሯቸውን መስርተው የነበሩት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አካባቢውን
ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸው የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየክልሎቹ ዘውጎች ‹‹መጤ›› ያሏቸውን
ማባረር ላለመጀመራቸው እርግጠኛ መሆን የምንችልበት ምንም አይነት ዋስትና የለንም፡፡ እናሳ! ይህ አይነቱ ክልልን
ከ‹‹መጤ›› ዘውግ የማንፃት ሂደት ማቆሚያው የቱ ጋ እንደሆነ ማን ሊገምት ይቻለዋል? ዘግናኝ ደም መፋሰስስ ሳያስከትል
ይህንን ክፉ ድርጊት መሻገር የምንችለው እንዴት ነው?

 እንግዲህ ይህ ሁሉ የፍርሰት መርዶ እየተሰማ ያለው፣ የሥርዓቱ ሰዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ለዚህ ከፍታ የበቁበትን ሃያ
ሶስተኛ የድል ዓመት በፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በሚሉበት ዋዜማ ላይ ቆመን ቢሆንም ‹‹ጊዜው ከቶም ቢዘገይ አልረፈደም››
እንዲሉ፤ ተገፍቶ ገደል ጠርዝ የተንጠለጠለውን የኢትዮጵያን ህልውና በደለደለ መሰረት አፅንተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር
አንዳች እርምጃ መውሰዱ ብቸኛ አማራጭ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህ ዘመን ለጣለው ትውልዳዊ የማንነት ዕዳ ክንውን
ቀዳሚው ተግባር ኢህአዴግን ‹‹በቃህ!›› ብሎ ማስቆም እንደሆነም መቀበል የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ግና፣ ይህ ሳይሆን
በወታደራዊ ጡንቻ ካሳለፍናቸው ዓመታት ጥቂቱን እንኳ እንዲሰነብት ከፈቀድንለት፣ የደም ባሕር ሲያጥለቀልቀን ቆመን
ለመመልከት ተስማምተናል ማለት ነው፡፡



ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
May 18, 2014

የወያኔን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማፋጠን ኅብረታችን ይጠንክር!!!


ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በግፍ ሕይወታቸው ባጡ ዜጎች መርዶ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እና ቁጭት ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይመኛል። ህወሓት እና አጋፋሪው ኦህዴድ በነዙት ሽብር ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ፣ የተደበደባችሁ እና ለእስር የተዳረጋችሁ ወገኖቻችንም ህመማችሁም እስራችሁም የሁላችንም ነው። መላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ከእናንተ ጋር ተገድሏል፣ ቆስሏል፣ ተደብድቧል፣ ተግዟል፣ ታስሯል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ግንቦት 7 ደጋግሞ ያስገነዝባል።
በህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ ያልተበደለ የኢትዮጵያ ክፍል የለም። የወያኔ አጋፋሪ የሆነው አህዴድ የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ሕፃናትንና አዛውንትን ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ፣ ሌላው አጋፋሪ ብአዴን ደግሞ በጎንደርና አካባቢው ተመሳሳይ ጭፍጨፋዎችን አካሂዷል። ወያኔ ከፋሺስት ኢጣልያ ወርሶ ለሃያ ዓመታት በትጋት ያራመደው “የከፋፍለህ ግዛ” ፓሊሲ ምርት እነሆ ዛሬ በዓይኖቻችን እያየን ነው። ፋሽስት ጣልያን ጀምሮት የነበረውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ስትራቴጄ ለማጠናቀቅ ህወሓት በጥድፊያ ላይ ነው። ይህን እኩይ ዓላማ ማስቆም የሁላችን ኃላፊነት ነው።
የመከላከያ ሠራዊት እና የፊደራል ፓሊስና አባላት ሆይ፣ ለዘረኛው ወያኔ መሣሪያ ሆናችሁ ወገናችሁን አትፍጁ! እናንተ የምታገለግሉት ሥርዓት፣ ከእናንተ መካከል ኦሮሞ ያልሆኑት እየመረጠ ኦሮሞዎች ወገኖቻችንን እንዲገሉ፣ አማራ ያልሆኑት ተመርጠው አማሮችን እንዲገሉ የሚልክ መሠሪ መሆኑን የምታውቁት ነው። ወኔን አንዳችንን በሌላችችን ላይ እያዘመተ እርስ በርስ ሊያፋጀን ቆርጦ መነሳቱን አስተውሉ። ይህን እኩይ ዓላማ የማክሸፍ ሥራ የናንተም ኃላፊነት እንደሆነ ግንቦት 7 ያስገነዝባል።
በወያኔ የስለላ መዋቅር ውስጥ ያላችሁ ህሊና ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን የምትሠሩት ሥራ አገራችን ወደየት ሊወስዳት እንደሚችል ቆም ብላችሁ አስተውሉ። እናንተ ዛሬ የምትወስዱት ቆራጥ እርምጃ የበርካታ ሕዝብ ሕይወት ሊታደርግ ይችላል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተከፋፍላችሁው ወያኔን መቃወም የትም አያደርስም። በኦሮሞው መገደል አማራው፣ ትግሬው፣ ወላይታው፣ ጉራጌው ካላመመው፤ አማራው ሲበደል ኦሮሞውና ሌላው እንዲያመው እንዴት መጠበቅ ይቻላል። እናንት ወጣቶች ከዘውግ ቆጠራ በላይ ሁኑ። ዛሬ የሚደረጉ ትናንሽ ነገሮች እንኳን የረዥም የወደፊት ውጤት እንዳላቸው ተገንዘቡ። የወደፊቱ ኢትዮጵያ የእናንተ ናት፤ የምትመኟችን ከራሷ ጋር የታረቀች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቅድሚያ እናንተ መታረቅ ይኖርባችኋል። የሁላችንም ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ነው ትኩረታችሁን እሱ ላይ አድርጉ።
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!!!! አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በወያኔ ዘረኛ ፕሮፖጋንዳ ተጠልፈው ንግግራቸው ሰው ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያቃቅሩ ሰዎችን አትስማ። የመረረ፣ የሚያስቆጣ ንግግር እንኳን ቢናገሩ ንቀህ ተዋቸው። በወያኔ ውስጥም ሆነ ከወያኔ ውጭ ሆነው ብሔርና ዘርን እያነሱ ተማረው ማስመረር የሚሹ ሁሉ ግባቸው አንድ ነው። በየትናቸው ወገን ቢሆኑ እነሱ የጥፋት ኃይሎች ናቸው፤ እነሱ የኢትዮጵያና የሕዝቧ ጠላት የሆነው የህወሓት መጠቀሚያ ናቸው።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ህወሓት እና ህወሓት የዘረጋው ሥርዓት ነው። የጋራ ትኩረታችን በጋራ ጠላታችን ላይ ብቻ ይሁን። ወያኔ ትኩረታችን ለመበተን ብዙ ነገሮችን ይጀምር ይሆናል፤ ርስ በራሳችን ከማባላትም አልፎ ጎረቤቶቻችንን መጎነታተል ይጀምር ይሆናል። በእንዲህ ዓይነት ድርጊት ትኩረታችን መበተን ፈጽሞ የለበት።
እኛ ኅብረታችንን ስናጠናክር የተዳከመው ወያኔ ይበልጥ ይዳከማል። ሊበታትኑን የዳከሩትን አሳፍረን ኅብረታችን እናጠነክራለን። ይህ ደግሞ የወያኔ ውድቀት እና የኢትዮጵያ ትንሣኤን ያፋጥናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Saturday, May 17, 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ


የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።
በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።
በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Thursday, May 8, 2014

የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ” በውቀቱ ስዩም


May 8, 2014
በውቀቱ ስዩም (በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)
Bewketu Seyoum is an Ethiopian writer
Bewketu Seyoum
ነጻነትና ፍትህ በሌሉበት አገር ውስጥ የልማት አውታሮችን መገንባት የት ለመድረስ ነው?የባቡር ሀዲድ ግንባታ ሳይ፣ የሚመጣብኝ እንደ አይሁድ በባቡር ታጭቀው ወደ መግደያ ጣቢያ የሚጓጓዙ ዜጎችን ነው። የኤሌክትሪክ ግንባታ ሳይ የሚመጣብኝ የኤሌክትሪክ መግደያ ወንበር ነው። የሚቆፈር ነገር ሳይ ድቅን የሚልብኝ የጅምላ መቃብር ነው።
የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ። ባንድ በኩል የዘመናችሁ ተካፋይ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። በሌላ በኩል፣ የመከራችሁ ተካፋይ ባለመሆኔ ሐፍረቱን አልችለውም። ያም ሆኖ ‹‹በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዛው ነው። ወትሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው›› የሚለው የዓለሙ አጋ የበገና እንጉርጉሮ ባጸደ-ነፍስ ላሉት ብቻ ሳይሆን ባጸደ-ወህኒ ላሉትም ይሆናል። ስሜቴን እንዴት መግለጽ እንዳለብኝ አላቅም። የገላውድዮስ ዜና- መዋእል ጸሐፊ በዚህ ሰዓት የሚሰማኝ ስሜት ከምእተ አመታት በፊት ተሰምቶት ነበር።
መዓልትኒ ኮነ ሌሊተ፣ዘኢነአምሮ ወጽልመት ዘኢልማድ መጽአ
ወደፈነ እንስሳ ወሰብአ
(ቀኑ ሌሊት ሆነና፣ ወጋገኑ ተሰደደ
እንግዳ ጨለማ መጣ፣ጠባዩ ያልተለመደ
ሰውን፣ እንስሳን ጋረደ)

Wednesday, May 7, 2014

የዞን 9 አባላት የፍርድ ቤት ውሎ


ሦስቱ የዞን 9 አባላትና ሶስቱ ሌሎች ጋዜጠኞች ዛሬ ሚያዝያ 29 2004 አም ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ በዝግ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፓሊስ ለምርመራ 10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ በዚህም የተሰጠው ምክንያት
1. ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እንዳንችል ሊሸሹ ይችላሉ
2. ከውጪ ገንዘብ በማስገባት የተገዙ ቁሳቁሶችን ለመያዝ ጊዜ ያስፈልገናል
3. የሰነድ ትርጉምና የባለሞያ ድጋፍ ለምርመራው አንፈልጋለን
4. ምስክሮችን ለማዘጋት ጊዜ ያስፈልገናል
ሲሆን ጠበቃቸው ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ዋስትና ለማስከልከል በቂ አይደሉም ሲል ተከራክሮአል፡፡ ፍርድ ቤቱ አስር ተጨማሪ ቀን የጊዜ ቀጠሮ የፈቀደ ሲሆን ግንቦት 9 ቀን ተመልሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
በተጨማሪም ተከሳሾች በቤተሰብና በህግ አማካሪ መጎብኘት አለመፈቀዱ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ጠቅሶ ከነገ ጀምሮ ቤተሰብ እና የህግ ባለሞያ እነዲያያቸው እንዲፈቀድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
ይህ በእነደህ እንዳለ የመጀመሪያ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ቀን የተጠረጠሩበት የተባለው ወንጀል ላይ ቀላል የማይባል ለውጥ የተደረገ ሲሆን የመጀመሪያው ክስ ላይ የነበረው |” ራሱን የሰብአዊ መብት ድርጅት እያለ ከሚጠራ ድርጅት ጋር በሃሳብና በፋይናንስ መተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ብጥብጥ ለማነሳሳት ” የሚለው ወደ “በህቡህ በመደራጀት በሽብርተኛነት ተግባር ከተፈረጀ ድርጅት ጋር በመገናኘት ገንዘብ በመቀበልና አገር እና ህዝብን ለማሸበር ሲንቀሳቀሱ” በሚል ለውጥ እነደተደረገበት የጠበቃው ንግግር ያመላክታል
በመጀመሪያውም ሆነ ሁለተኛው ክስ ላይ የተጠቀሱትን ወንጀሎች የዞን ዘጠኝ አባላት እንዳልፈጸሙት ማንኛውም የሽብር ተግባር ከተጠረጠረ ድርጅት ጋርም ፈጽሞ ግንኘነት እነደሌላቸው ና ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለው እነደማያውቁ እየገለጽን የተጠረጠሩበትን ወንጀል በየቀጠሮው መቀያየሩ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ እንደዞን 9 በሚያደርጉት እነቅስቃሴ ብቻ መታሰራቸውንና ጉዳዩ የፓለቲካ ክስ መሆኑን እንደሚያሳይ እንደምናምን ደግመን ለመናገር እንወዳለን፡፡
የዞን 9 ነዋሪያን ዛሬ ፍርድ ቤት በመገኘት ላሳዩትን አጋርነት ምስጋናውን እያቀረበ ነገ በተመሳሳይ ሰአት በፍቃዱ ማህሌትና አቤል ስለሚቀርቡ አጋርነታችሁን ማሳየት እንድትቀጥሉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ስለሚያገባን እንጦምራለን
Like ·  · 

Monday, May 5, 2014

የኃይለማርያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች


(ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ ) May 5, 2014
በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ራሱ መለስ ዜናዊ በድህረ ምርጫ 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ዘብጥያ ወርደው የነበሩትን የቅንጅት አመራሮች “ከእስር እንዲፈቱ ብፈልግም አክራሪው ኃይል ተቃወመኝ” ማለቱን ዊክሊክስ የተሰኘው የመረጃ መረብ የአሜሪካ አምባሳደርን ጠቅሶ ይፋ ማድረጉ ይህንኑ ያስረግጣል፡፡ የአምባሳደሩ መረጃ የተጋነነ፤ አሊያም “ተጋግሮ የቀረበለት ነው” ሊባል ቢችል እንኳ “ጭስ በሌለበት…” እንዲሉ፤ በግንባሩ ውስጥ አክራሪ ኃይል ለመኖሩ በጠቋሚነት ሊወሰድ ይችላል፡፡Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ መለስን ከተካበት ዕለት አንስቶ፣ ያደረጋቸው ዲስኩሮችም ሆኑ ለቀረቡለት ጥያቄ የሰጣቸው ምላሾች በአክራሪው ኃይል ተጽእኖ ሥር ማደሩን ያሳያል፡፡ የድርጅቱ የታሪክ ንባብም ቢሆን፣ በአቅመ ደካማ የመጠቀም የፖለቲካ ጨዋታው የሰነበተ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ኃይለማርያም ከሹመቱ በኋላ ከባሕሪው አፈንግጦ፣ ዝነኛዋን የመለስ ዜናዊን ሕዝባዊ ሽብር መፍጠሪያ ‹‹ቀይ መስመር››ን፤ ‹‹እሳት መጨበጥ›› በሚል ተክቶ የተቃውሞ እንቅስቃሴን በሙሉ እስከማስፈራራት መገፋቱም የዚሁ ውጤት ይመስለኛል። በተቀረ እርሱ ወደ ሥልጣን በመጣበት መጀመሪያ አካባቢ፣ ‹‹ኃይማኖተኛ››ነቱን ብቻ በመጥቀስ ‹‹ቤቴን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› በሚል ሥርዓታዊ ማፍያነትን ባደራጁ ጓደኞቹ ላይ ጅራፍ እስከማወናጨፍ ይደርሳል ተብሎ መገመቱ፣ በግንባሩ ውስጥ የተንሰራፋውን አክራሪ ኃይል በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ እዚህ ጋ ሳይጠቅስ የማይታለፈው ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም የወጣው ‹‹ሪፖርተር ጋዜጣ›› በልዩ እትሙ፣ ኃይለማርያም ‹‹ቄስ›› ተብሎ ሊቀባ አንድ ወር ሲቀረው በትምህርት ምክንያት ከሀገር እንደወጣ ካስነበበበት ጋር የሚያያዘው ነው፡፡ ወደ ፖለቲካው ከመቀላቀሉ በፊት የሚያመልክበትን ‹‹የኢትዮጵያ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን›› ቄስ ህዝቅኤል ጎዴቦን ‹‹ፖለቲካ ውስጥ መግባት ሀጢአት አይሆንብኝምን?›› ሲል መጠየቁን ጋዜጣው አትቷል፡፡ ግና፣ ምን ዋጋ አለው? ባልተጠበቀ ፍጥነት ከተራ ፖለቲከኝነት አልፎ የሀገሪቱ መሪ ለመሆን በመብቃቱ፣ ‹‹ቅስና››ው በመንገድ ሊቀር ተገደደ እንጂ፡፡ እርሱም ቢሆን ዛሬ እንዲህ አይነት ጥያቄ አያነሳም፤ በፈሪሃ እግዚአብሔሩም ቦታ፣ ፈሪሃ ኢህአዴግ ተተክቷል፡፡ እናም ከእስልምና መንፈሳዊ መሪዎች እስከ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ያሉ ንፁሀን፣ በራሱ አነጋገር ‹‹እሳት በመጨበጣቸው›› ወደ ‹‹ቃሊቲ›› ተላልፈው ምድራዊውን ገሀነም ይቀበሉ ዘንድ ቡራኬ ሰጥቷል፡፡
ሰሞነኛው ጉዳይ
አቶ ኃይለማርያም በስድስት ወር (በጥር) ለተወካዮች ም/ቤት ማቅረብ የነበረበትን ሪፖርት በዘጠኝ ወሩ ባለፈው ሳምንት ባቀረበበት ወቅት፣ ከምርጫው በፊት የፖለቲካ ማሻሻያ መጠበቁ የዋህነት እንደሆነ የጠቆመን፣ የም/ቤቱ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የጠበበው ምህዳርን አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ‹‹ዲሞክራሲ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ አይጠጣም (ፓርቲው ሥልጣን ከያዘ በቀጣዩ ወር ሃያ ሁለተኛ አመቱን መድፈኑን ልብ ይሏል)፣ ዲሞክራሲ ህልውናችን ነው፣ ቀይ ምንጣፍ አናነጥፍም…›› ጅኒ ቁልቋል በሚሉ የእብሪት ገለፃዎች ማለፉ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ሪፖርቱ በሀሰተኛና በማደናገሪያ ዘገባዎች የታጀለ እንደነበረ መታዘብ ተችሏል፡፡ ለማሳያነትም ያህል ጥቂቶቹን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-
‹‹ዕድገት›› ሲባል…
የኢኮኖሚ ዕድገትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፖርቱ ላይ ‹‹የሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ሂደት ሲታይ ላለፉት አስር ዓመት (ከ1996-2005) በየዓመቱ በአማካይ 10.9 በመቶ በማደግ ከፍ ባለ የእድገት ጉዞ (Trajectory) ውስጥ መሆኑን አመላክቷል›› ሲል ነግሮናል፡፡ ይሁንና አስሩን ዓመት ትተን የዘንድሮውን በመሬት ላይ ያለውን እውነት እንኳ ብንመለከት የሚያሳየው ተቃራኒውን ስለመሆኑ ለራሱም ቢሆን ይጠፋዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በአገሪቱ ሥራ-አጥነት (በከተሞች 40 በመቶ መድረሱን ጥናቶች ይጠቁማሉ) በአስከፊ መልኩ ተንሰራፍቶ፣ ስደት ዕጣ-ፈንታ ተደርጎ ኩብለላ የዕለት ተግባር በሆነበት፣ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ በኑሮ ውድነት እንደ ከባድ ማዕበል ወደላይ ጎኖ፣ ቁልቁል በአናት እየተተከለ በሚንገላታበት፣ ጎዳናዎች ቀን ቀን ልመና በወጡ ምንዱባን፣ ማታ ማታ ደግሞ ነፍሳቸውን ለማቆየት የሚውተረተሩ በዕድሜም በአካልም ትናንሽ የሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ተጥለቅልቆ… ባለበት በዚህ ዘመን ‹በየዓመቱ በአማካኝ 10 በመቶ እያደግን ነው› የሚልን አላጋጭ ሪፖርትን ሰምቶ በቸልታ ማለፉ ሰው የመሆን ጉዳይንም ፈተና ላይ መጣሉ አይቀርም፡፡
በዚህ ለሶስት ወራት በዘገየው ሪፖርት የዋጋ ንረትን ከአንድ አሃዝ እንዳያልፍ እየተሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ከየምርጫው አንድ ዓመት በፊት በመለስ ዜናዊ ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶች እንዲህ አይነት የዋጋ ንረት እንደሚቀንስ የ‹‹ሚያበስሩ›› እንደነበር ይታወሳል፡፡ የኃይለማርያምም ሪፖርት፣ ፓርቲው በምርጫ ዘመቻው ወቅት ሁሌ እንደ ስልት የሚጠቀምበትን ይህንን ጉዳይ አስጩኾ ከተለመደው የግብይት ሥርዓት አፈንግጦ መጠነኛ የዋጋ ማረጋጊያ በማድረግ የእሳት ማጥፊያ ሥራ ለመስራት ከመዘጋጀት ያለፈ ትርጉም ያለው ነገር የሚያመጣ ሆኖ አይደለም፡፡
አብዮታዊ ግንባሩም ቢሆን የምርጫው ማዕበል የሚጠራርገውን ጠርጎ፣ የሚወረውረውን ወርውሮ ማለፉ ላይ እርግጠኛ እንደሆነው ሁሉ፣ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የዋጋ ንረቱ ተመልሶ የቱንም ያህል ወደላይ ቢስፈነጠር የተቆጡ ድምፆች አደባባዩን እንደማይሞሉት ጠንቅቆ ያውቀዋል።
ሌላው የሪፖርቱ አስቂኝ ክፍል የግብርናውን ዘርፍ የተመለከተው ነው፡፡ ይኸውም ካለፈው ዓመት የዘንድሮው በእጅጉ ማደጉን ገልፆ እንደምክንያት ያቀረበው ‹‹ዋናው የዕድገት መሰረት በመሬት ማስፋት ሳይሆን በምርታማነት የመጣ መሆኑን የሚያሳይ ነው›› የሚል ነበር፡፡ ይሁንና እዚህ ጋ የሚነሳው ጥያቄ የዘርፉ ባለሙያ መሆንን የማይጠይቅ ቀላልና ግልፅ ነው፡- የግብርና ቴክኖሎጂ መሻሻል በሌለበት፣ የሰው ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣበት (አማካይ የመሬት መጠን ከአንድ ሄክታር ያነሰ ሆኖ)፣ ማዳበሪያ ለፓርቲ አባላት ብቻ በሚታደልበት፣ የዝናብ ወቅትን ብቻ ጠብቆ በሚዘራበት እና መሰል ችግሮች ባጨለሟት ኢትዮጵያችን ምርታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አደገ መባሉ እንዴት ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል? …መቼም በመለኮታዊ ኃይል ከሰማይ በወረደ መና ነው ሊሉን አይችሉም፡፡ ካሉ ግን ምን ማድረግ ይቻላል! ሰውየው ኃይለማርያም፣ ፓርቲውም ኢህአዴግ ነውና፡፡
እጅግ የሚያሳዝነው የእነርሱ ዕድገት፣ ምርታማነት… ቅብርጥሶ የሚለው ፕሮፓጋንዳ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በምግብ እጦት መጠቃታቸውን ዓለም አቀፍ ተቋማት እየዘገቡ ባለበት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንደ መስከረም አደይ አበባ በየሜዳው መፍካቱን አብስረውናል፡፡ ይሁንና ሀገሪቱ እንኳን ለግዙፍ ፋብሪካዎች የሚሆን የኃይል አቅርቦት ቀርቶ፣ አነስተኛ ፍጆታ ያለውን የከተማ ነዋሪ የመብራት ፍላጎትም ማሟላት ያለመቻሏ ጉዳይ ፀሀይ የሞቀው፣ ዝናብ ያጨቀየው የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ የግልገል ግቤ 3 ፕሮጀክትም ቢሆን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደደሰኮረው በሚቀጥለው ዓመት ሥራ የሚጀመር አለመሆኑን ግንባታውን የሚያካሄደው ካምፓኒ አስቀድሞ ማሳወቁን ሰምተን አረጋግጠናል፡፡
ሌላው በሪፖርቱ ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ ግርምት የሚያጭረው ከወራት በፊት በሳውዲ አረቢያ አሰቃቂ ጭካኔ የተፈፀመባቸውን ወንድም-እህቶችን በተመለከተ በአምስት መስመር ብቻ ተቀንብቦ የቀረበው ዘገባ ነው፡፡ የዚህን ሥርዓት ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከመራቅም በላይ፣ መበስበሱን የሚያስረግጠው እንዲያ በ21ኛ ክ/ዘመን ሊፈፀም ቀርቶ ይታሰባል ተብሎ በማይታመን ጭካኔ ደማቸው ደመ-ከልብ ሆኖ ስለቀረውና አስክሬናቸው በጎዳና ላይ ስለተጎተተው ወገኖቻችን፡- ‹‹የሳዑዲ መንግስት በተለያየ ምክንያት ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃዳቸውን ማስተካከል ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን አገር ለቀው እንዲወጡ በወሰነው መሰረት…›› በማለት በሪፖርት ተብየው አቃሎ ማቅረቡ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሁለት ነገር ያመላክታል፡፡ የመጀመሪያው ሥርዓቱ ለዜጎቹ ደህንነት ደንታቢስ በመሆኑ ቢያንስ በወረቀት ላይ እንኳን ነውረኛውን የሳውዲ መንግስት ለማውገዝ እና ወደፊትም ከእንዲህ አይነቱ ዲያብሎሳዊ ተግባሩ እንዲታቀብ ለማስጠንቀቅ አለመድፈሩን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በዚህን መልኩ ከተባረሩ ስደተኞች መካከል አሁንም ወደዛው የሞት ቀጠና ተመልሰው መሄዳቸው፣ ጠ/ሚንስትሩ እንዲያ የተዘባነነበትን ‹‹ዕድገት›› ልብ-ወለድ ማድረጉን ነው፡፡
መልካም አስተዳደር ሲባል…
የኃይለማርያም ደሳለኝ ሪፖርት በደምሳሳው እውነት ለመናገር የሞከረው መልካም አስተዳደር ያለመኖሩን በተመለከተ ብቻ ነው፡፡ ለማሳያነትም የሚከተለውን ልጥቀስ፡-
‹‹በአገራችን ከፌዴራል ተቋማት ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ደረጃው የተለያየ ቢሆንም፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደሚታዩ ሕዝቡ በተለያዩ መድረኮችና አገልግሎት በሚያገኝባቸው ሥፍራዎች ቅሬታዎች እያነሳ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡››
ከዚህ በተጨማሪም መንግስታዊ ጉድለቱ ከኪራይ ሰብሳቢነት አንስቶ፤ በመሬት አስተዳደር፣ በታክስ አሰባሰብ እና የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በማስፈፀም ሂደት፣ በአገልግሎት ተቋማት ውስጥ የሚታይ የአመለካከት ችግር፣ የሥራ ተነሳሽነት አለመኖር፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት መጥፋትንም እንደሚጨምር ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ይሁንና ሰዎቹ እንዲህ በድፍረት ያነበሩት ሥርዓትን ክሽፈት ቢያውጁም፣ ቅንጣት ታህል ‹የሕዝብ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል› የሚል ስጋት የለባቸውም፡፡ ስለምን? ቢሉ፣ በአንድ በኩል ስለዲሞክራሲ ማበብና የሕግ የበላይነት እየዘመሩ፤ በሌላ በኩል በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ተተብትበው ሥልጣንን በገዛ ፍቃድ ካለመልቀቅም አልፎ ቀጣዩን ምርጫ አጭበርብሮ እና ተቀናቃኞችን ጨፍልቆ ለማሸነፍ ዝግጁ መሆን የሚቻለው በእኛይቱ መከረኛ ኢትዮጵያ ብቻ እንደሆነ ገና ድሮ ገብቷቸዋልና፡፡
ሌላው የአገሪቱን ሀብት በጠራራ ፀሀይ የመዝረፍ እውነታውን ለመረዳት ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪፖርቱን ካቀረበበት ሁለት ቀን ቀደም ብሎ (በ14/8/06 ዓ.ም) የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2005ቱን የበጀት ዓመት በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ መስሪያ ቤቱ በተለያየ ምክንያት ከመንግስት ተቋማት በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ እንደባከነ የገለፀው የገንዘብ መጠን በድምሩ 3,207,752,247.05 (ሶስት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ብር ከዜሮ አምስት ሳንቲም) መሆኑን በግላጭ አስቀምጧል፡፡ ይህ እንግዲህ በቀጥታ ከጥሬ ገንዘብ ጋር የተያያዘ ውድመት ነው፡፡ ከዚህ ሌላ በርካታ ችግሮችና ዘረፋዎች መኖራቸውን ሪፖርቱ በስፋት ዘርዝሯል፡፡ ለምሳሌ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያን የተመለከተውን ማየት ይቻላል፡፡
ይህ መሳሪያ ሥራ ላይ መዋል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ለግብር ከፋዩ ከተሸጠው ውስጥ 89 በመቶው አገልግሎት ላይ ቢውልም፣ የሽያጭ መረጃን ወደ መረጃ ቋት የሚያስተላልፈው 12 በመቶ ብቻ ሲሆን፤ የተቀረው 88 በመቶ ምንም ነገር እንደማያስተላልፍ ተገልጿል፡፡ እናሳ! ይህ ስለምን ሆነ? ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱ መረጃ የማያስተላልፉት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችስ በእነማን ድርጅቶች እጅ ውስጥ የሚገኙት ይሆኑ? …እውን! ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚህ መልስ ይኖረዋልን?
የስኳር ኮርፕሬሽኖችን በተመለከተ
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሪፖርቱ ላይ ‹‹(አዳዲሶቹ) አብዛኛው የስኳር ፋብሪካዎቻችን በቀጣይ ዓመት ወደ ማምረት ተግባር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል›› በማለት ቢገልፅም፤ የኦዲት ሪፖርቱ ግን ተቃራኒውን ነው የሚያረዳን፡፡ ይገነባሉ የተባሉት ፋብሪካዎች በኮርፕሬሽኑ የአምስት ዓመት ዕቅድ መሰረት ሁለመናቸው ተጠናቅቆ ወደ ማምረት እንደሚገቡ መገለፁ አይካድም፡፡ ነገር ግን የጣና በለስ ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ግንባታ እስከ ጥቅምት 2005 ዓ.ም ያልቃል ቢባልም፤ በዛው ዓመት መጨረሻም ቁጥር አንድ 45 በመቶ፣ ቁጥር ሁለት 39 በመቶ ብቻ ሲጠናቀቅ፤ በኦሞ-ኩራዝ ደግሞ የፋብሪካው ግንባታ መጠናቀቅ በነበረበት ዓመት 42 በመቶ ብቻ የተሰራ መሆኑን ሪፖርቱ አጋልጧል፡፡ እንዲሁም እስከ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ይጠናቀቃል የተባለው የወልቃይቱ ፋብሪካ የኦዲት ሪፖርቱ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ምንም አይነት የግንባታ ሥራው እንዳልተጀመረ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የተንዳሆ ስኳር ልማት ፋብሪካ በታቀደለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ምክንያት 5146.09 ሄክታር መሬት ላይ የነበረው የሸንኮራ አገዳ ምርት ዕድሜው በመራዘሙ ተበላሽቶ እንዲወገድ በመደረጉ፣ ፋብሪካው ማግኘት የሚገባውን 102,440,145.00 (አንድ መቶ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ሺህ አንድ መቶ አርባ አምስት) ብር ተገቢ ባልሆነ መንገድ ያሳጣው እንደሆነ የኦዲት ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ታዲያ ጠቅላይ ሚንስትራችን ‹በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ› የሚለን የትኞቹን የስኳር ፋብሪካዎች ይሆን? እግዜር ያሳያችሁ! እንዲህ አይነት ያፈጠጠ ነጭ ውሸት የሚነግረን፣ ፕሮጀክቶቹን እስከዚህ ዓመት መስከረም ወር መጀመሪያ ድረስ በበላይነት ይመራ የነበረው አባይ ፀሀዬን አማካሪው አድርጎ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህ ሁኔታ የሚያመላክተው ሌላ ጉዳይ ቢኖር አቶ ኃይለማርያም ዛሬም ‹‹እመራዋለሁ›› ለሚለው አብዮታዊ ድርጅቱ ሩቅ የመሆኑን ምስጢር ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በተሾመ ማግስት፣ አቶ መለስ ማሌሊትን ቀብሮ ስለልማታዊ መንግስት ከማንችስተር እስከ ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲዎችና ዓለም አቀፍ የአደባባይ መድረኮች መከራከሩን ያልሰማ የሚመስለው ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በመጀመሪያው ከውጭ ጋዜጠኛ (ከቪኦኤው ፒተር ላይን) ጋር ባደረገው ቃለ-መጠየቅ ላይ ‹‹እኛ ተራማጅ ግራ-ዘመም ነን›› ሲል የተደመጠበትም መግፍኤ ይኸው ይመስለኛል፡፡
ኤርትራ ሆይ! ብረሳሽ…
ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት፣ አቶ ግርማ ሰይፉ መንግስት የኤርትራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማቀራረብ የሚያደርገውን ጥረት አስመልክቶ ያለውን አቋም በተመለከተ ላነሳው ጥያቄ፣ የሰውየው ምላሽ ከእውነታው ፍፁም ያፈነገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የኃይለማርያም ማብራሪያ ሁለቱ ሕዝቦች የቀድሞ ግንኙነታቸውን መልሰው እንዲያጠናክሩ ‹‹ኢትዮጵያውያን የኃይማኖት አባቶች እና ምሁራኖች ለሚያደርጉት ጥረት መንግስት ድጋፍ እያደረገ ነው›› የሚል ሲሆን፤ ኤርትራን በተመለከተ ደግሞ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በአሸባሪነት ፈርጆ ማዕቀብ ጥሎ እያሰቃያት ከመሆኑም በላይ በአካባቢው ከኢትዮጵያ በስተቀር ተሰሚነት ያለው ሀገር ያለመኖሩን የሚያመላክት አንድምታ አለው፡፡ ይህ ግን ምን ያህል እውነት ነው? ብለን ስንጠይቅ፤ በኤርትራ መገንጠልም ሆነ በለንደኑ ኮንፈረንስ የህወሓትን የበላይነት ያስረገጡትና በአሜሪካን አስተዳደር ተሰሚነት ያላቸው አምባሳደር ኸርማን ኮኽን ኤርትራን ከ‹‹ብርዱ›› ለማውጣት አሜሪካም ሆነች የተባበሩት መንግስታት የጣሉትን ማዕቀብ እንዲያነሱ እና ድንበሩ እንዲሰመር በአደባባይ መጮኽ ከጀመሩ መሰንበታቸውን እንረዳለን፡፡ እንዲሁም ሌላኛው አምባሳደር ዴቪድ ሺንም ኢትዮጵያ ባድመን እስከመስጠት ከሄደች በሁለቱ ሀገራት ሰላም ማምጣት እንደሚቻል ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እናም እነዚህን ሰዎች ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ አሜሪካውያን ፖለቲከኞች ኤርትራ እ.ኤ.አ. ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ሽብርተኝነትን ከመደገፍ መቆጠቧን ጠቅሰው በመከራከር ላይ መገኘታቸው እውነታውን ፍንትው አድርጎ ሳያል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ኢትዮጵያውያን የኃይማኖት አባቶችና ምሁራኖች…›› ንግግርም በሬ ወለደ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ የሀገሬ መንግስት ለተከታታይ አስራ ስድስት አመታት ‹ኤርትራ ሆይ! ብረሳሽ ቀኜ ይርሳኝ›ን የሚዘምረው ሀገር-በቀል ተቀናቃኞቹን በስመ-ሻዕቢያ መጨፍለቅ ሲፈልግ ብቻ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
እኛ ቀጥለናል!
ግንባሩ ‹‹ባለራዕይ›› በማለት ካቆለጳጰሰው የቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ህልፈት በኋላ፣ በጠባብ ብሔርተኞችና ጥቅመኞች በመሞላቱ መተካካቱን ተከትሎ ይፈረካከሳል የሚል ከውስጥም ከውጪም የሚሰማ ሹክሹክታ ነበር፡፡ በርግጥም የኃይለማርያም ወደ መንበሩ መምጣት ‹‹በአማራና ኦርቶዶክስ የምትመሰለው ሀገር፣ የአናሳውም ሆናለች›› ከሚለው የአቦይ ስብሐት እንቶ ፈንቶ ውጪ፣ ከተጠበቁት ሁነቶች ብዙዎቹን (በተለይ ሥርዓታዊ ልልነት ይፈጠራል የሚለው) በገቢር ከመስተዋል አልታደጋቸውም፡፡ ለዚህም ሁለት ማሳያዎችን እጠቅሳለሁ፡፡ የመጀመሪያው ባሳለፍነው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀረበው ሪፖርትና ማብራሪያ ላይ ተደጋግሞ የተነሳው ‹‹የአፈፃፀም ችግር›› የሚለው ነው፡፡ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተብሎ ከበሮ ከተደሰቀለት የተቀመጠ ግብ አኳያ፣ ነባራዊው ሁኔታ ስምም አለመሆኑን ራሱ ኃይለማርያምም ‹‹የአፈፃፀም ጉድለት›› በሚል የዳቦ ስም ሊያሳብብ ከመሞከር በቀር አልካደውም፡፡ አንድ ማዕከላዊ መንግስትን የሚመራ ግንባር፣ ሊያውም እስከ ቤተሰብ የወረደ የኃይል ማዕከል ለመገንባት የሚጥር ስብስብ፤ ከተሞችን እያሰቃየ ላለው የመሰረታዊ ግልጋሎቶች ዕጦትና የተቀመጡ ዕቅዶች አለመሳካት ይህን በመከራከሪያነት ማቅረቡ፤ የስርዓቱ ተቋማት መፈረካከስን ከማስረገጥ ያለፈ የሚነግረን ምስጢር የለውም፡፡
ሌላኛው የአማካሪዎቹ ስብስብ ጉዳይ ነው፡፡ ሰውዬው ከጎኑ የሰበሰባቸውን ጉምቱ ፖለቲከኞች ትተን፤ ለእያንዳንዱ ጉዳይ ካውንስል የማቋቋም ፍጥነቱን ብናስተውል ስርዓቱ በመለስ ዘመን የነበረውን ጥብቅነት አጥቶ መዋለሉን እንረዳለን፡፡ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እንዲመራ ካስቀመጠው ዶ/ር ደብረፅዮን ውጪ፣ ‹‹የኢኮኖሚ ካውንስል›› በሚል አይረቤ ስም ለማቋቋም መሞከሩ ሳይበቃ፤ በባጀት ዕጥረት እየተሰቃየ ያለውን አስተዳደሩን ለመታደግ የፋይናንሻል ምንጮችን ከውጪ የሚያፈላልግ ሌላ ካውንስል መሰል ስብስብ ማደራጀቱን ስንታዘብ፤ ስርዓቱ ቢያንስ እንደ መለስ ዘመን መቀጠል በማያስችል ወላዋይነት /Brittle state/ ለመፈተኑ ጥቁምት ይሰጠናል ብዬ አስባለሁ፡፡ በተለይም ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፖርቱ ላይ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማሟላት መንግስት የሐዋላ አግልግሎትን ማጠናከር እንዳለበት ከመግለፅ ባለፈ፣ ከ2000 ዓ.ም መጀመሪያ አንስቶ የህንዱን ካራቱሪ እና ሳውዲ ስታርን ጨምሮ ለበርካታ ባለሀብቶች ስለተሰጠው ሰፋፊ የእርሻ መሬት አንዳችም ነገር ትንፍሽ አለማለቱ የክስረቱ ዋነኛ ማሳያ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ ከመሬት ቅርምት ጋር አያይዘው የተቃውሞ ድምፃቸውን ላሰሙ ምሁራንም ሆነ ‹‹አንድ ሄክታር መሬት በሃያ ብር›› መሰጠቱን በመኮነን የድርጊቱን ኢ-ፍትሓዊነት በዘገባው ለገለፀው ታዋቂው ‹‹ኒዎርክ ታይምስ›› ጋዜጣ፣ መለስና ጓዶቹ መከራከሪያ አድርገው ያቀረቡት ‹‹በአጭር ጊዜ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ችግራችንን ይቀርፋል፣ የቴክኖሎጂና የሙያ ሽግግር እንዲደረግ ያስችላል›› የሚል እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ግና፣ ዛሬ ይህ ጉዳይ ሕልም ሆኖ ለውጭ ምንዛሪ ሐዋላን የሙጥኝ መባሉን እየሰማን ነው፡፡ እንዲሁም በራሱ በመለስ ዜናዊ በ2005 ዓ.ም በርግጠኝነት መውጣት እንደሚጀመር የተነገረለት የነዳጅ ክምችትም ቢሆን፣ ‹‹ውሾን ያነሳ…›› እንዲሉ የተዘጋ ፋይል ሆኗል (በነገራችን ላይ በፓርላማው. የፓርቲው ካድሬዎች ባለስልጣናቱ ላይ የሚያዘንቡት የጥያቄ እሩምታ የሚያመለክተው፣ ፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ ዘግይቶ ወደ ኢህአዴግ ሰፈር መምጣቱን ሳይሆን፣ የፓርቲውን የውስጥ የዕዝ ተዋረድ መሰነጣጠቁን እና ቡድንተኛነት ግንባሩን እያመሰው መሆኑን ነው፡፡ በተቀረ ከዚህ ውጪ ያለው መከራከሪያ ሁሉ ጥሩ የአደባባይ ቧልት ከመሆን የሚያልፍ አይመስለኝም) የሆነው ሆኖ ከላይ ኃይለማርያምን ያብራሩልናል ብዬ ለመጥቀስ ከሞከርኳቸው ጭብጦች በእጅጉ ባለፈ፣ ሪፖርቱን ያቀረበበት ተአብዮ እና የማንአለብኝነት መንፈስ በቅድመ-ምርጫው አንድ ዓመት ውስጥ አንዳችም የፖለቲካ ማሻሻያ እንዳትጠብቁ የሚለው ዋነኛው ሲሆን፤ አቦ ሌንጮ ለታ ‹‹ሰዎች አሳስተውታል›› እንዳለው፤ ዙሪያው ያሉት አለቆች እንዳዘዙት፤ ‹እኛ እየረገጥናችሁ እንቀጥላለን፣ እናንተም በተጨቋኝነታችሁ አዝግሙ› የሚለው ደግሞ ሌላኛው ውስጠ-ወይራ ጥብቅ መልእክቱ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማርያም ጥር 2003 ዓ.ም. ‹‹ምዕራፍ›› ከተሰኘ ኃይማኖታዊ መጽሔት ጋር ቃለ-መጠይቅ ባደረገበት ወቅት ‹‹ከመጽሐፍ ቅዱስ ደስ የሚልዎት ቃል የቱ ነው?›› በሚል ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠውን ምላሽ፣ አንድም ዛሬ የሚከተለውን መንገድ ቆም ብሎ እንዲፈትሽ ለማስታወስ፤ ሁለትም ለዚህ ተጠይቅ መደምደሚያ ይሆን ዘንድ ወደጃለሁና እንደሚከተለው አሰፍረዋለሁ፡-
‹‹መጽሐፍ ቅዱስን እወደዋለሁ፡፡ የዮሴፍ፣ የዳዊት፣ የሙሴ ሕይወት በጣም ይለውጡኛል፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን ሕይወት በጣም ያንጹኛል፡፡ ዳንኤልም በጣም ጠቢብ ነው፡፡ ስለዚህም እንደርሱም መሆን መልካም እንደሆነ አስባለሁ፡፡››
ወንድም ኃይለማርያም ደሳለኝ፡- የልብህን መሻት አምላክ ይሙላልህ!!
Like ·  · 

Sunday, May 4, 2014

ኢትዮጵያ በህግ አምላክ የሚባልባት ሀገር መሆኗ ቀርቷል


ግፈኛውና ዘራፊው የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ መሬት ከሚሰራቸው ትልልቅ ወንጀሎች አንዱና ምናልባትም ዋነኛው በህግና ሕገ-መንግስት ላይ የሚያካሄደው ቀልድና ጭዋታ ነው። ሕገ-መንግስት ህዝብን ከእብሪተኛ መንግስት መጠበቂያ መሳሪያ መሆኑ ቀርቷል። ህግና ሕገ-መንግስት ለወያኔ ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በጣት የሚበላ ነገር ነው። ወያኔና አፋኝ ስርአቱ ህግ የሚጠቅሱት ለራሳቸው ይጠቅመናል ባሉበት ሰዓት ነው። ህግ ለነሱ ካልተመቻቸው ተቀዶ የሚጣል ቆሻሻ ወረቀት ነው።
በኢትዮጵያ ምድር ዋናው ሕገወጥ ተቋም ራሱ ላወጣው ሕግ የማይገዛው ወያኔ/ህወሃት ነው። ለዚህ ነው “ለሚመለከተው አካል ከማሳወቅ ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ፈቃድ አይጠየቅም” የሚለውን ራሱ ያወጣውን ህግ ጥሶ ሰሞኑን ተቃዋሚዎችን ቁም ስቅላቸውን የሚያሳያቸው። ለዚህም ነው ሃሳብን በጽሁፍና በቃል ለመግለጽ ቅድመ ምርመራ እና እገዳ አይኖርም ብሎ ጽፎ፣ አለም አቀፍ የሰበአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዳሉ ተቀብያለሁ ብሎ የተናገሩና የጻፉ ሰዎችን የሚያሳድደውና በሽብርተኝነት የሚከሰው።
ኢትዮጵያ “በሕግ አምላክ” የሚባልባት ሀገር መሆኗ ቀርቷል። ወያኔ ይህን ለህግ ትልቅ ክብር ያለውን የህዝባችንን የዘመናት እምነት ድራሹን በማጥፋት ላይ ይገኛል። ፍትህ በወያኔ አፋኞች መዳፍ እጅ ወድቃለች።
በዚያ አስከፊ የደርግ መንግስት ስርአት እንኳን ዳኞችን “እንዲህ ብላችሁ ፍረዱ” የሚል ትእዛዝ አልነበረም።
ዛሬ በየፍርድ ቤቱ አለም እየታዘበ የሚከናወን አይን አውጣ አሰራር እና የህወሃት የንጹሃን ዜጎችን የፖለቲካ መቀጣጫ ቤት ሆኖ ተለምዶል። ፍትህ እና ፍርድ ቤት እንዲዋረድ ሆኗል። ፍትህና ዳኝነት ራሱ በህወሃት የታሰረበት ጊዜ ነው።
ባለፈው ሳምንት ወያኔ አፍሶ ማእከላዊ በማስገባት የሚያሰቃያቸው የዞን 9 የኢንተርኔት ፌስቡክ ተጠቃሚዎች በሀገሪቱ ህገ መንግስት ከተለመደው መሰረታዊ መብታቸው ውጪ ያደረጉት ቅንጣት ወንጀል የለም። ወያኔ በፈራ እና በደነገጠ ቁጥር ሺህ ህግ ይጥሳል፡፡ ወያኔ ደግሞ ጥላውን የሚፈራ ድንጉጥ ተቋም ነው።
የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ጠላት እንጂ እንደ አብሮ ኗሪ ዜጋ ማየቱን ከተዎ የሰነበተውም ለዚህ ነው።
ዛሬ ራሱ ወያኔም እኛም በሕግና በሕጋዊነት ላይ ያለን ተስፋ ተሟጧል። ስለዚህም ነው ምርጫችን ይህን ህገ ወጥ የወንበዴ መንግስት በትጥቅ አልባም ይሁን በታጠቀ ሁለገብ አመጽ ማስወገድ ብቻ ነው የምንለው።
ግንቦት 7 የወያኔን አያያዝ አይተን የሁሉአቀፍ የአመጹን መንገድ ተከትለናል። ፈልገን ሳይሆን ተገደን በወያኔ ምርጫ የተመረጠልንን።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወያኔ የህግና የሰላም በሩን ሁሉ ዘግቶ የተወልህን እና ሊከለክልህ የማይችለው ምርጫ የራስህን የነጻነት ትግል የአመጽ ሃይል ብቻ ነው። በየአለህበት በእምቢተኝነት ተነሳ!! መብትህንና ክብርህን ከወያኔ መጠበቅ የዋህነት ነውና ተነስ ተቀላቀል! ራስህን ነጻ አውጣ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!


Saturday, May 3, 2014

አንድነት ፓርቲ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ይቀላቀሉ! (ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር)


GizachewShiferaw3-150x150
  • digg
  • 116
     
    Share
ጤና ይስጥልኝ !
ግዛቸው ሽፈራው እባላለሁ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ነኝ።  አንድነት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ አግኘቶ፣ በአገሪቷ ባሉ ክልሎች ሁሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሰ ድርጅት ነው። አንድነት ከማንም ግለሰብና ድርጅት ጋር ፀብ የለዉም። የአንድነት ፖለቲካ የኢትዮጵያዊነት፣ የፍቅርና የመቻቻል ፖለቲካ ነው።  አላማችን ፣ የበለፀገች፣ ልጆቿ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ልዩነት ሳይደርገባቸው እኩል የሆኑባት፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መመስረት ነው።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት፣  ግልጽነት የጎድለው፣ ተጠያቂነት የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀና የመልካም አስተዳደር ችግር ያለበት እንደመሆኑ፣  በሕዝብ ላይ ትልቅ በደል እያደረሰ ይገኛል። የሚከተለው የተሳሳተና ጎጂ የመሬት ፖሊሲ፣  ዜጎች፣ በልማት ስም፣ በቂ ካሳ ሳይከፈላቸው፣ ከቤታቸው እና ከእርሻ ቦታቸው በኃይል እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው። የሰብአዊ መብት ረገጣው፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ….. በግፍ መታሰራቸው፣ የኑሮ ዉድነቱ ሕዝቡ ከሚሸከመው በላይ እየሆነበት ነው።
ሕዝባችን ከዚህ የተሻለ ይገባዋል።  ኢትዮጵያዉያን አሁን ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ አንቀበለም በማለት፣ ለዉጥ መጠየቅ፣  ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርብናል።
ሕዝቡ ድምጹን ማሰማት የሚችልበት መድረክ ያገኝ ዘንድ፣ አንድነት፣ በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እውቅና ያገኘበት፣ ሁለት ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ፣ እሑድ ሚያዚያ 26 ቀን፣ በአዲስ አበባ እና በደቡክ ክልል በምትገኝ የድራሼ/ጊዶሌ አዘጋጅቷል። የአዲስ አበባ እና የጊዶሌ ነዋሪዎች፣ በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በአክብሮት ጥሪ አቀርባለሁ።
ነጻነት ነጻ አይደለም። ነጻነትን ከሌሎች አናገኝም። ነጻነትን እኛዉ እራሳችን ነን ለራሳችን ማወጅ የምንችለው። እራሳችንን በግል ካያነው፣ ምንም ማድረግ የማንችል፣  አንድ ተራ ሰው አድርገን ልንቆጠር እንችላለን። ነገር ግን ተራ ሰዎች፣  በሚሊዮን ሲቆጠሩ፣ እነርሱን ማነቃነቅ የሚችል ምንም ኃይል አይኖርም። እንነሳ። ሰልፍ እንዉጣ። ድምጻችንን እናሰማ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! እራሳችንን ነጻ በማወጣት አገራችንን ነጻ እናውጣ !

እንግዚአብሄር አገራችን ኢትዮጵያን ይባርካት

ግዛቸው ሽፈራዉ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=454#sthash.shPPMChI.8J3GThxE.dpuf