Thursday, October 31, 2013

እረፍት የሚነሳው ህምም


የኮንትራት ሰራተኞች ስቃይ፣ የእኛ ፍርሃትና የፖለቲከኞች ጭካኔ
saudi 1
እረፍት አደርግ ብየ ከማህበራዊ መገናኛ መድረኩ ገለል ባልኩባቸው እንደ ብርሃን ፍጥነት በሚወረወሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበርካታ ወዳጆቸ በርካታ መልዕክቶች ይደርሱኛል። ብዙው መልዕክት ደግሞ የሚያጠነጥነው በጅዳ እና በአካባቢው በተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች አሰቃቂ ስቃይ ላይ ያተኮራል … ለነገሩ የአብዛኞቹ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆኑ ከመልዕክቶች ጋር የሚላኩልኝ መረጃዎች እረፍት የሚነሱ ናቸው! …
አዎ ተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በመረጃነት የታጨቀባቸውን የመልዕክት መረጃ ጭብጦች እውነታ ለማረጋገጥ ወደ ጅዳ ቆንስል አመራሁ … መኪናየን አቁሜ ትንሽ እንደ ተራመድኩ እያለ ከፊት ለፊቴ  አንዲት ልጅ እግር ኢትዮጵያዊ ብቻዋን እያወራች ስታልፍ ስመለከት በመደናገጥ ሰላምታ አቅረብኩላት፣ መልስ ሳትሰጠኝ አለፈች!  ደነገጥኩና ባለሁበት ቆሜ በአይኔ ተከተልኳት … በፈጣን እርምጃ የሚያቃጥል የሚለበልበውን መሬት የምትደቃበትን የጠቆረ ባዶ እግሯን፣ እንደነገሩ ከላይዋ ላይ ደረብ ያደረገችውን ጥቁር “አበያዋን” እና ከፍ ሲል የተንጨፈረረ ጸጉሯን እያየሁ ፈዝዠ ቀረሁ … ከድንጋጤና ከፍርሃት ለአፍታ ነፍሴ መለስ ሲልልኝ ጠደፍ ጠደፍ ብየ ወደ ሔደችበት አቅጣጫ ተከተልኳት … ርቃኛለች … ሮጨ ልደርስባት ባለመቻሌ መኪናየን ወዳቆምኩት በመሔድ አስነስቸ ተከተልኳት … በደቂቃዎች ልዩነት ተሰወረችኝ! ምናልባት በዙሪያው በቆሙት መኪኖች መካከል፣ በመንገዱ ዳርም ሆነ በቤቶች አጥር ጥላ ፈልጋ ደክሟት አረፍ ብላ እንደሆነ በማለት መኪናየን አቆሜ ፍለጋየን ቀጠልኩ … ብዙ ሞክሬ አልተሳካልኝም … ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሰላም እያልኳት ገላምጣኝ የሄደቸው እህት የለችም!
በትካዜ ተውጨ በአሳቻ መንገድ አገኛት እንደሁ በሚል ዙሪያ ገባው እያማተርኩ ሳቀና ከጅዳ ቆንስል ግቢ በግምት 600 መቶ ሜትር ርቀት በአንድ አረብ ቱጃር ቤት አጥር ስር በሚገኝ አንድ ዛፍ ስር፣ ከመንገዱ ዳር አንዲት እህት ወድቃ ተመለከትኩ! ክው ክው ብየ ደነገጥኩ … ተጠጋኋት! የሚያምረው አይኗ ወይቧል፣ ሰውነቷ ደግሞ ዝላለች፣ ላብ ፊቷን አውዝቶታል፣ አፏ ግን አመድ መስሎ ደርቋል!  ጠይም ባለ ሰልካካዋ አፍንጫ ለግላጋ መልከ መልካሟን እህት ከብዙ ጉትጎታ በኋላ ማውራት ቻልኩ … ለነገሩ ማውራት አይባልም! ለረጅም ደቂቃዎች ለማውራት ያደረግኩት ሙከራ በሰጠችኝ ጥቂት መልስ አፏ ተፈታ ማለቱ ይቀላል! ዝርዝር ማውራት ግን አትፈልግም … ምንም አይነት እርዳታ እንደማትፈልግ በአጭሩ ገለጸችልኝ! … በቃ ከዚህ ባለፈ ብዙ ማውራትና መቀጠል አልቻልኩም!  የማደርገው ባጣ ቢያንስ በቆንስሉ መጠለያ ግቢ ከታጨቁትና በከፋ አደጋ ላይ እንዳሉ ከሰማሁትና አይቸ ካረጋገጥኩት 150 ከሚሆኑት ተፈናቃዮች ጋር ቢደባልቋት በሚል ለጅዳው ቆንስል ሃላፊ ለአቶ ዘነበ ከበደና ለዲያስፖራው እና በመጠለያ ላሉት ተፈናቃዮች እህቶች ተጠሪ ዲፕሎማት ለወ/ሮ ሙንትሃ ደጋግሜ ስልክ ደወልኩላቸው አያነሱም …
የማደርገውን እያሰላሰልኩ ሳልራመድ በአጋጣሚ አይኔን ወደ ቀኝ አሻግሬ ስመለከት አንድ ሌላ እህት ከቅርብ ርቀት ወድቃ ተመለከትኩ … ይህችው እህት በቁራጭ ካርቶን ቢጤ ተቀምጣና ጀርባዋን ለመንገዱ ሰጥታ እጇን እያፍተለተለች ትዘፍናለች ትስቃለች! ይህችንም ደጋግሜ ጠየቅኳት እየገላመጠች እያየችኝ መልሳ ትስቅና ትዘፍናለች! ዘፈኑ ኦሮምኛ መሆኑን እንጅ ዘፋኝና ትርጉሙን አላውቀውም! …  ፈዝዠ ቀረሁ!
saudi 2ደጋግሜ ወደ ቆንስሉ ሃላፊዎች፣ ወደ ኮሚኒቲ ሹሞች ብደውልም ስልኬን አይመልሱትም! … እንዲህ ስባዝን አንድ ለቆንስል እና ከኮሚኒቲ ሃላፊዎች ቅርበት ያለው ወንድም ከበስተኋላየ መጥቶ ጀርባየን ቸብ አድርጎ አስደነገጠኝ!  ድንጋጤየ ገርሞት “አቶ ነብዩ ምነው? ደነገጥክኮ!” አለኝ በአግራሞት እንደ መሳቅ እያለ  … የደነገጥኩት ከበስተኋላ የተኛቸው እህት ተነስታ የነረተችኝን መሰሎኝ መሆኑን እውነቱን ገልጨለት እንደ ቀልድ አድርገን ተሳሳቅን፣ ብዙም ሳንቆይ ስለ ወደቁት ለእህቶች አንስተን ተጨዋዎትን … ወዳጀ በቅርብ ርቀት የወደቁ እህቶች እያሳየኝ እንዲህ አለኝ “አየህ ይህችኛዋ ለሶስት ቀናት አንዴ እዚህ ትወድቃለች አንዴ እዚያ ታገኛታለህ ፣ ያችኛዋንም እንደዚያው …” ብሎ ሊቀጥል ሲል በጥያቄ አስቆምኩት ታዲያ ምን አደረግክ?  “እኔ ምን አደርጋለሁ!  የእኛ ዜጋ ረክሷል እኮ … እስኪ ወደ መጠለያውና ግባ፣ ያበዱ የታመሙ ደህና መጥተው በመጠለያው የሚያብዱትን ሲያዩ እነሱም የሚያብዱት ቁጥር እኮ ቀላል አይደለም!” ሲል የመርከሳችን ነገር ሊያስረግጥልኝ ሞከረ!   ግን ይህንን ስታይ ለምን ወደ ምትቀርባቸው ሃላፊዎች ደውለህ አታስረዳቸውምና ሌላው ቢቀር ከግቢው ውስጥ ከተደባለቁ ይበዱም ይሙቱ ማንነታቸው ቢያንስ ይታወቃል?  አልኩት፣ ከግቢ ውጭ እንዲህ ሲወድቁ የሚከተልባቸው አደጋ እንደሚከፋ፣ ከወራት በፊት ከቆንስሉ እና ከመጠለያው ግቢ በር  ካለው ዛፍ ራሷን ሰቅላ ስለሞተቸው፣ ከቅርብ ርቀር ከሚገኘው ሌላ ዛፍ ወድቃ ስለሞተችው እህት የሚያውቀው የምናውቀውን አሳዛኝ ክስተት ለማስረዳትም ላማስረዳትም  እየሞከርኩ ብየ አከልኩለት … አይገባህም እንደ ማለት የለበጣ ሳቁን ከፊቱ ላይ እየነሰነሰ ምላሽ ንግግሩን  ቀጠለ …  “ያንተ ነገር እኔ መቸም እንዳንተ አላበድኩም፣ ፓስፖርት ማደስ፣ ቤተሰቦቸን ሃገር ቤት ሔጀ መጠየቅ እፈልጋለሁ፣ አንተ እንኳ ዱላውንና መገፋቱን ለምደህዋል፣ በል አሱን ተወው!” ሲል እያሳሳቀ ደገመና “እንዳንተ መች አበድኩ!” ብሎኝ አረፈው …
ፍርሃትን ፈርቶ ሰብዕናውን የደፈጠጠበት ይህ አጋጣሚ ቢያስቆጣኝም የተሰማኝን አፈንድቸ ወዳጀን ላስበረግገው አልፈለግኩም … እንዲያውም ላግባባው ሞከርኩ … ለሁሉም እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲያጋጥም አንድም ለሃላፊዎች አለያም ያገባኛል ለምንል ሰወች መረጃውን ብታቀብሉን መልካም ነበር በማለት ሃላፊዎች ለማግኘት እና ለማሳወቅ ፈልጌ አይመልሱም ብየ ወሬየን ሳልጨርስ ንግግሬን ከአፌ አቋረጠው እና መለሰልኝ “አትድከም ማናቸውም ላንተ አይመልሱልህም፣ እያጋለጥካቸውና ድክምታቸውን ለአለም እያሳየህ ባይመልሱልህ አይደንቀኝም፣ በነገራችን ላይ ሳልፈልገው ልንገርህ አስገደድከኝ፣ ባለቤቴ የፌስቡክ ጓደኛህ ነች፣ በጣም ትከታተልሃለች፣ ታከብርሃለች፣ ባንተ ነገር ሁሌ እንጣላለን። እኔ በሃላፊዎች አካባቢ የምትባለውን ስለምሰማ ለእለት ጉርሱ ሳያነሰው ለምን ይጽፋል፣ ለምን ከመንግስት ጋር ይፋጠጣል፣ ልጆቹን ለምን አርፎ አያሳድግም ባይ ነኝ። እርሷ ግን በእኔ ሃሳብ ፍጹም አትስማማም። መረጃውን የሚቀበል አጣ እንጅ ጠቃሚ ነው ትላለች። እኔም የምለው ያንን ነው ሰሚ ሳይገኝ መጮህ አንተን ይጎዳሃል ባይ ነኝ … እና ብዙ ጊዜ በዚህ ተጣልተን ሁሉ እናውቃለን። አንድ በቅርቡ የሰራችውን ልንገርህ … ከሁለት ቀን በፊት ስለ መጠለያው ቪዲዮ በፌስቡክ መልዕክት መቀበያ አልደረሰህም?” ሲል ጠየቀኝ፣ ማን እንደላከው ንገረኝና ልነገርህ አልኩት፣ ነገረኝ፣ መረጃው እንደደረሰኝ አረጋገጥኩለት፣ ተግባባን … ንግግሩን ቀጠለ …saudi 3
“አየህ ሚስቴ እኔ እንድታየው ብሰጣት ላንተ ላከችልህ። ያበዱትን እና በጸሃይ ላይ የሚንቀለቀሉ እህቶች ቢያሳዝኑኝ፣ በቅርቡ በድብቅ በመጠለያው ያነሳሁት ነው። እንግዶች ሃገር ቤት ይመጣሉ ስለተባለ እና ለሃላፊዎች ሁኔታውን ለማሳየት ያነሳሁትን ቪዲዮ ነው!” ብሎ በጠራራው ጸሃይ አቁሞ ካወራኝ በኋላ ከእኔ ጋር እዚህ አካባቢ መቆሙን ከአሸባሪ ጋር እንደ መተባበር ይቆጠራል የሚል በነገር ቀልድ ሸንቁጦኝ መልሴን ሳይጠብቅ እየሳቀ ተሰናብቶኝ እየተጣደፈ ወደ ቆንስሉ ግቢ አመራ  …
ፊቴን ወደ ወደቁት ሁለት እህቶች መለስ ቀለስ እያደረግኩ ብቻየን ቀረሁ! የማደርገው ጠፋኝ … አሁንም መልሸ መላልሸ ወደ ቆንስል ሃላፊዎች ደወልኩ … ወዳጀ እውነቱን ነው፣ አያነሱም!… ሁሌ ሲከፋኝ እና መፍትሔ ሳጣ የምጠይቀውን ጥያቄ ራሴን ጠየቅኩት … ግን ለምን?  አልኩ … መልስ ባላገኝም …!
ብዙም ሳልቆይ ወደ ቆንስሉ ግቢ አመራሁ፣ ወደ ግቢው ዘልቄ ገባሁ፣  ግቢው በሰው ተሞልቷል። ኢትዮጵያዊው ወገን የሳውዲ ምህረት አዋጅ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከመጠናቀቁ በፊት የተለያዩ ሰነዶችና አገልግሎት ፈልጎ የመጣ መሆኑን አውቃለሁ፣ እኒህኞቹ ችግር ቢገባኝም፣  ዛሬ አንገብጋቢ ሆኖ አልታየኝም። ተጋፍቸ ወደ ቆንስል ሃላፊው የሚወስደው በር ብደርስም ወደ ፎቅ የሚወስደው በር በካሜራና በአውቶማቲክ በር ተጠርቅሟል። የበሩን መክፈቻ በመጫን አያንጫረርኩት ለማስከፈት ሞከርኩ፣ አልተቻለም … ተሰላችቸ ልመለስ ስል መልስ ተሰጠኝ “ሁሉም ዲፕሎማቶች ስብሰባ ላይ ናቸው”  የሚል መልስ! ከቶ ለማን ይሆን የሚሰበሰቡት?  አልኩ … ለእኛ መሆኑ አልዋጥልህ አለኝ እና እያጉረመረምኩ ግቢውን ለቅቄ ወደ መጠለያው አመራሁ …
ወደ መጠለያው ከመግባቴ በፊት ወድቀው ያየኋቸውን እህቶች ለማንሳት ከመጠለያው በር ያገኘኋትን እህት ትተባበረኝ ዘንድ ለምንኳት፣ “እሽ!” አለችኝ! ተያይዘን ወደ ወደቁት እህቶች  አመራን … አገኘናቸው አግባብተን ማስገባት ቀርቶ ማነጋገር አልቻልነም …  ይህች እህቴ ያየችውን ማመን አቅቷት በእንባ ተሞላች፣ ሳታስበው ሃዘን ውስጠ ከተትኳት፣ አዘንኩ! እሷኑ አይዞሽ ብየ ሸኝቸ፣ ለራሴው ሰላም አጥቸ ወደ መጠለያው አመራሁ …
ከዚህ ቀደም በደረሰኝ መረጃ የተመለከትኳቸው ያበዱ የታመሙትን ጨምሮ ጤነኞች ተፈናቃይ እህቶች ከግቢው ፈሰው ተመለከትኩ … ልብስ ታጥቦና ሳይታጠብ እንደ ሃገር ቤት በየአጥሩ፣  በደረጃው፣ በመሰላሉና በበሮቹ ላይ ተሰቅሏል … ሻንጣው በአንድ ጥግ ተከምሯል … ይህን ጨምሮ አሳዛኙን የተፈናቃዮች ውሎ በፎቶ ሆነ ቪዲዮ ማንሳት ክልክል ነው ስለተባለ ማንሳት አልፈልግኩም! ግቢው ጉስቁልናቸው ከፊታቸው በሚነበብ እህቶች፣  ባዘኑ በተጨነቁ፣ በውስጥ ደዌ የተደቆሱ፣ በአዕምሮ ጭንቀት በተለከፉ፣ በተዳከሙ፣ ተስፋ በቆረጡ እህቶች ጢም ብሎ ሞልቷል፣ ወደ 150 ደርሰዋል፣ የሚያድሩት በጠባቧ ክፍልና ሜዳ ላይ እንደሆነ ሰምቻለሁ … ያየሁት አንገቴን አስደፍቶ አሳፈረኝ!  ወደ ካፍቴሪያው ዘለቅኩ …
በካፍቴሪያው እንደገባሁ መቀመጫ ስፈልግ ቅድም በር አግኝቸው የነበረው ወንድምና ካፍቴርያውን ሳይሳለሙ ውለው ከማያድሩት ሌሎች ባልንጀሮቸ ተቀምጦ አየሁት … የደመቀ ወሬ ይዘዋል።እንዴት እንዳየኝ ባይገባኝም እጁን እያወናጨፈ ጠርቶ እንድቀመጥ ጋበዘኝ! ራመድ ራመድ ብየ ሄጀ ሰላምታ ከተለዋዎጥኩ በኋላ ተቀመጥኩ፣ ከቀናት በፊት በካፍቴርያው ያለውን የሟች ጠቅላይ ሚኒስትርን ፎቶ በቦርሳዋ ስትደበድብ ያየኋት እህት በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከጓኛዋ ጋር ተረጋግታ ተቀምጣለች። ዛሬ ተሽሏታል ብየ ሳላበቃ “ወግዱልኝ!” ብላ አምባርቃ ጮኸች …  ከወዳጆቸ ጋር ወንበር ስቤ ከተቀመጥኩባት ቅጽበት እስክነሳ በጠረጴዛው ይወራ የነበረውን ወሬ ለመጻፍ ግን ይከብደኛል … ብቻ በግቢው ችግረኛ ግፉዕ ወገን እየተንገላታ እንደሆነ ተረስቷል … ሰብዕና ሳይሆን ተራ የፖለቲካ ቡትቶ ጉዳይ ሆኖ እና የባጥ የቆጡን  ወሬ እያመጡ የማውራቱ እና የመፈላሰፉ ወሬ ግን ያስጠላል …. በሽታ ሆነኝ …
ከቶ ይህ መከራ እየታየ እንዴት ይታረፋል! ብጣቂ መረጃ እንኳ እንካችሁ! ከእረፍት ስመለስ ከደረሰኝ እና ከማውቀው መረጃ አልፎ አልፎ ጨልፊም ቢሆን በቅርቡ ሳላስቃኛችሁ አልቀርም …
ለሁሉም አንድየ ቸር ያሰማን! የምስራች የምናዎራ ያድርገን!
ነቢዩ ሲራክ

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በዚምባቡዌ


በዚምባቡዌ አቋርጠዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመሻገር የሞኮሩ 38 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች የዚምባቡዌን ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዉ በመታሰራቸዉ ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉ ተነገረ።

epa03809922 Zimbabweans check election results posted outside a polling station in Mbare, Harare, Zimbabwe, 01 August 2013. Prime Minister Morgan Tsvangirai on 01 August declared Zimbabwe's general election to be 'null and void' due to allegations of vote rigging and warned the country was on the brink of a crisis. The country's most important independent network of election observers announced it too doubted the legitimacy of the ballot. The 89-year-old Zimbabwean president, Robert Mugabe, who has been at the helm of the country since 1980, has vowed to step down if he is declared the loser in the election. EPA/AARON UFUMELI
ስደተኞች የተያዙት ከሞዛምቢክ ወደዚምባቡዌ ተሻግረዉ፥ ከዚምባቡዌ በአዉቶቡስ ወደደቡብ አፍሪቃ ሲጓዙ ነበር። የዚምባቡዌ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች ከተያዙበት ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ባይትስብሪጅ በተባለዉ መቆጣጠሪያ ኬላ ላይ እንደታሠሩ ነዉ። በሐራሬ- ዚምባቡዌ የዶቸ ቬለ ወኪል ኮሎምቦ ስማቭሁንጋ እንደሚለዉ ስደተኞቹ ምግብ የሚያቀብላቸዉ ካላገኙ በረሐብ ይጎዳሉ።
በዚምባብዌ ፖሊስ መግለጫ መሰረት እነዚ እድሜያቸው በ20 እና30 መካከልየሚገኙ 38 ኢትዮጵያውያን በሞዛምቢክ በኩል ኣድርገው ነው የዛሬ ሳምንት ወደዚምባብዌ የዘለቁት። በህገወጥ መተላለፊያዎች በኩል። የተያዙትም ቢሆን ከምስራቃዊትዋ የዚምባብዌ ከተማ ከሙታሬ ኣውቶቡስ ተሳፍረው በባይትብሪጅ የማቐረጫ ኬላ በኩል ወደደቡብ ኣፍሪካለ መሻገር ሲሞክሩ ነው ተብለዋል። የባይትብሪጅ ኬላ ጠባቂ ፖሊሶች ኣዛዥ እንደሚሉት እነዚህ ስደተኞች በእሳቸው ኣጠራር ህገወጥ ፈላሾች በህገወጥ መንገድ ወደኣገሪቱ በመግባታቸው ምርመራ እየተካሄደቸው ይገኛል። በዚሁ ወንጀልም ክስ ይጠብቃቸዋል። ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደኣገሪቱ የገቡ በርካታ ስደተኞች ኣሉ። የሁሉም ጉዳይ በኣገሪቱ ህግ መሰረት ይዳኛል ይላሉ የባይትብሪጅ ፖሊስ ኣዛዥ ላውሬን ሴቪንሄንጎ የዚህን ኣይነት ወንጀል ለማጣራት የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም የሚሉት ላውሬንሴ እነዚህን ስደተኞች ኣሳፍሮ ድንበር ለማሻገር ሲጘዝ የተገኘው ኣውቶቡስ ደግሞ ንብረትነቱ የፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ዛኑ PF ፓርቲ
Zimbabwe's President Robert Mugabe addresses the crowd gathered to commemorate Heroes Day in Harare August 12, 2013. Mugabe told critics of his disputed re-election to go hang on Monday, dismissing his rivals as Western-sponsored stooges at a liberation war commemoration that was boycotted by his principal challenger. The Movement for Democratic Change (MDC) of Mugabe's rival Morgan Tsvangirai filed a court challenge on Friday against the announced landslide win of Mugabe and his ZANU-PF party in the July 31 vote, alleging widespread rigging and intimidation. REUTERS/Philimon Bulawayo (ZIMBABWE - Tags: POLITICS ELECTIONS HEADSHOT)
ሁነኛ አባል መሆኑም ሌላው ቅሌት ነው ሲሉም ኣክለዋል።
ንብረትነቱ የም/ቤት እንደራሴ በሆነ ኣውቶቡስ 38 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሳፈራቸውን በመረጃ ስናረጋግጥ ለመያዝ ኣላመነታንም ያሉት እኚሁ የፖሊስ ኣዛዥ የኢሚግሬሺን ባልደረቦችም ለዚሁ መተባበራቸውን ኣመስግነዋል። ባለስልጣናት ኣውቶቡሶችን ለህገወጥ ስደት እስከማመቻቸት ሲደርሱ ለመታገስ ኣይቻለንም ሲሉም ኣዛዡ ተናግረዋል።
በዚምባብዌ ኃራሬ የሚገኘው የዶቸ ቬሌ ባልደረባ ኮሎምበስ ማብሁንጋ እንደሚለው ደግሞ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በእርግጥ ለውሳኔ ማስቸገሩ ኣይቀርም። ምክኒያቱም በዚምባብዌ ህግ መሰረት ያለፈቃድ የገባማንኛውም ስደተኛ ተይዞ ወደኣገሩ እንዲመለስ ነው የሚደረገው። ኣሁን ግን ዚምባብዌ ይህንን ለማድረግ ኣቅሙም የላትም።
ኮሎምበስ እንደሚለው በርካታ ስደተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሩዋንዳ፣ ኤርትራ እና ኮንጎ እየመጡ ወደደቡብ ኣፍሪካ ይሻገራሉ። ድንበር ላይ ሲያዙ ግን የማጎሪያ ካምፑ ይዞታ ኣሁን ኢትዮጵያውያኑ የሚገኙበት ማለት ነው በጣም ኣስቸጋሪ ነው። ስንቅ የሚያቀብል ዘመድ ከሌላቸው በተለይ ለምግብም ሊቸገሩ ይችላሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ኮሎምበስ እንደሚለው ኃራሬ የሚገኙት የኣፍሪካ ኣገሮች ኢምባሲዎች ደግሞ ለዜጎቻቸው ደንታ ያላቸው ኣይመሉም።
ዚምባብዌ ከደቡብ ኣፍሪካ ጋር ባላት ቀጥተኛ ድንበር የተነሳ በኣፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ወደሆነችው ደቡብ ኣፍሪካ የበርካታ ኣገሮች ስደተኞች መሸጋገሪያ ሆና መቆየትዋ ይታወቃል። ሶስት ሚሊየን ያህል የራስዋ የዚምባብዌ ዜጎችም በደቡብ ኣፍሪካ እንደሚገኙ ሲታወቅ አብዛኞቹ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የገቡ ናቸው። በየዓመቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደዚምባብዌ እንዲመለሱ ቢደረጉም ወዲያውኑ ግን በሌላ አቅጣጫ ተመልሰው እዚያው ደቡብ ኣፍሪካ ይገባሉ ተብለዋል።
ጃፈርአሊ
ነጋሽመሐመድ

Tuesday, October 29, 2013

ጆሮ ያለው ይስማ!!!

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…


2የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…
ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ
ተስፋሁን ጫመዳ የተባለ አንድ ወጣት ኢትዮጳያዊ ነበር፡፡ የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልመችህ ቢለው በተለያየ አጋጣሚ ተው  ማለት ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን ተው ባይ አይወድምና በክፉ አይኑ ተመለከተው ይሄኔ ተስፋሁን የሚመጣበትን ጦስ ሸሽቶ መጪው ጊዜ መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ እስኪያልፍ ያለፋል ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኢህአዴግ ግን ዝም አላለውም ከተሰደደበት ሀገር አፍኖ ወደ ሀገርቤት መለሰው፡፡ መመለስ ብቻም አይደለም እስር ቤት ዶለው፡፡ መዶል ብቻም አይደለም በቅርቡ ተስፋሁን በእስር ቤት በቂ ህክምና አጥቶ ህወቱን ተነጠቀ፡፡
ዳዊት ከበደ የተባለ ሌላ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነበር፡፡ እርሱም የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልጣመውም እና መምከር ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን በሚመክሩት ላይ መከራ የሚያበዛ ነውና በክፉ አይኑ ተመለከተው፡፡ ይሄኔ ዳዊት ከጎልያድ ጋር ይጋፈጥበት ወንጭፍ በእጁ አልነበረምና ቀን እስኪልፍ ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኋላ ላይ ግን እንደ ተስፋሁን አፍነው ሳይወስዱትም ራሱ “እንደውም አልፈራችሁም” ብሎ ወደ ሀገርቤት ተመለሰ፡፡ “ይገሉኝም እንደሁ ይሰቅሉኝም እንደሁ ይሄው መጣሁልዎ ያለምጣም ኢህአዴግ ብዬ ሰደብኩዎ” ብሎ ሁሉ ልክ ልካቸውን ነገሯቸዋል ነው የሚባለው…  ነገር ግን እንደ ተስፋሁን እስር አልጠበቀውም፡፡  እንኳንስ ህወቱን ሻንጣውም አደጋ ላይ አልወደቀም፡፡
ሶስተኛ አንቀጽ እኔ
“አውቶብሱ መጣ ጎማው ሸተተኝ እኔም ከሰሞኑ ተሳፋሪ ነኝ” ብዬ ዥው ብዬ ወደ ሀገሬ ብሄድ የሚጠብቀኝ ምን ይሆን… እንደ ተስፋሁን ታስሮ ህይወት ማጣት፣ እንደ ውብሸት ታስሮ ይቅርታ ማጣት፣ እንደ ርዮት ታስሮ ጠያቂ ማጣት፣ እንደ እስክንድር ታስሮ ቤተሰብ ማጣት ወይስ እንደ ዳዊት ታስሮ አሳሪ ማጣት!? (በቅንፍም የሆነውስ ሆኖ ግን ስንት አመት ሰው ሀገር እቆያለሁ የሆነ ቀንማ ሄጄ መቀወጤ አይቀርም፡፡ (በሌላ ቅንፍም ደግሞ ሳላግጥ፤ ቢያንስ ግን ለጨዋታም ለቃለ ምልልስም እንዲመች የባቡር ግንባታው እንኳ ይለቅና እንተያያለን…!))

Monday, October 28, 2013

አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል?


እነሆ ይቺ ሀገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስ
የሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ
በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤
ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር፡፡ የሩቁን (የጨለማውን ዘመን) ትተን፣
የቅርቡን እንኳን ብንመለከት በወጡበት መንገድ፣ ቁልቁል ተምዘግዝገው መውደቃቸውን መረዳቱ
አይቸግርም፡፡ አዛውንቱ አፄ ኃይለስላሴ፣ ‹‹ቆራጡ›› ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም እና ‹‹ታጋዩ›› አቶ መለስ
ዜናዊ እጅ የሰጡት ለህዝብ ፍላጎት ሳይሆን ለጠመንጃና ለተፈጥሮአዊ ኃይል ነው፡፡ የሶስቱም የአመፃ ‹‹የዳቦ
ስም›› ደግሞ ተመሳሳይ ነበር፡- ‹‹ለሀገርና ህዝብ ጥቅም››፡፡
ንጉሰ ነገስቱ ልጅ እያሱን ያስወገዱበት ምክንያት ‹‹ሀገርን ከሚያጠፉ ጋር በማበሩና ህዝብን ከማስተዳደር ይልቅ፣ ለግላዊ ምቾት ጊዜውን
በዋል ፈሰስ በማዋሉ ነው›› የሚል ሰበብ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በግልባጩ እርሳቸውም ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ አደባባይ ባናወጠ
ንቅናቄ ተገፍተው፣ ገደል አፋፍ በቆሙባት በዛች ዕለት፣ የሠራዊቱን መለዮ ባጠለቀ አንጋች የተነበበላቸው የክስ ደብዳቤ፡- ‹‹ሀገርን
ለቆሞ-ቀር፣ ሀብትን ለቤተሰብና ለግለሰቦች ጥቅም መመዝበር፣ ህዝብን ለከፋ ጭቆናና ሰቆቃን ላዘነበ ረሀብ መዳረግ…›› የሚል እንደነበረ
ስናስታውስ ‹ታሪክ ራሱን ደገመ› ያሰኛል፡፡ በዚህ መልኩ ‹‹በደልና ግፍ ከምሽግ አስወጣን›› ባሉ ወታደራዊ መኮንኖች የተመሰረተው
የደርግ መንግስትም አስራ ሰባት ዓመት ሙሉ እንዳሻው ሲገድል፣ ሲፈልጥ፣ ሲሸልል… ቆይቶ ‹‹ብሶት ከትምህርት ገበታ አፈናቀልን›› ባሉ
በረኸኞች ፍፃሜው ይሆን ዘንድ ግድ ሆነበት፡፡ ታሪክም የሚነግረህ ይህንኑ ነው፤ ሌላ የለም፡፡ ያገዛዝ ጭቆናና መከራ ያስመረረው
አደባባዩን በኃይል ሲነጥቅ-ሲነጥቅ ዛሬ ላይ መድረሱን፡፡ በርግጥ ይህ እርግማን አይደለም፤ ለጨቋኞች በልክ የተሰፋ ፍትሀዊ ፍርድ
የሚተላለፍበት አማራጭ መንገድ እንጂ፡፡
የሆነው ሆኖ ዛሬም ቢሆን ትውልድ እንጂ ታሪክ አልተቀየረምና፣ የለውጥ መንገዶች በሙሉ ሄደው ሄደው ወደ አደባባይ የሚገፉ
ሆነዋል፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ‹የነፃነት በር በብላሽ አይከፈትም› ያለው ማን ነበር? ...ርግጥ ነው መለስ ዜናዊም በርሃ ሳለ ‹‹ምኹሕዃሕ
ዘይፍለዮ ማዕፆ›› (ማንኳኳት ያልተለየው በር) በተሰኘ ታንክ ተደግፎ በፃፈው መፅሀፉ ላይ የደርጉን ፋሺስትነት ከመተንተኑ
በተጨማሪም ከጓደኞቹ ጋር ተስፋ ሳይቆርጥ ባደረገው ትግል ነፃነቱን ተቀዳጅቷል፡፡ ይሁንና በለስ ቀንቶት በትረ-ስልጣን ከጨበጠ
በኋላ ግን፣ የአስተዳደር ዘይቤውን የወረሰው ታግሎ ከጣለው ስርዓት ዶሴ እንደነበር ለመረዳት ብዙ አላስጠበቀም፤ ቀድሞ
የተተገበረውን አሻሽሎ፣ በከፋ መልኩ ደጋግሞ ተግብሮታል፡፡ የመፅሀፉ ዋና ገፅ-ባህሪ ‹‹እነይ ስላስ›› በእንባ እንደታጠቡት፣ በድህነት
እንደጎበጡት ሁሉ ዛሬም የኢትዮጵያ እናቶች በደህነት አጥንታቸው ገጥጧል፤ ለእስርና ለስደት በተዳረጉት ልጆቻቸው ጉልበታቸውን
ታቅፈው በሀዘን እንዲወዛወዙ ተፈርዶባቸዋል፤ ሥራ-አጥ ጎረምሳ ልጆቻቸውን ለመቀለብ ላይ-ታች ከመማሰን አልተገላገሉም፤
‹‹ለግርድና›› ወደ አረብ ሀገር የተሰደዱትን ሴት ልጆቻቸውን እያሰቡ በስጋት እየተናጡ ነው… እናም በኢህአዴግና እነርሱ ‹‹ፋሺስት››
በሚሉት በደርጉ ስርዓት መካከል የታየው የአስተዳደር አይነት የጊዜና የሰዎች ልዩነት ብቻ እስኪመስል ድረስ የአንድ ሳንቲም ግልባጭ
መምሰሉ ‹‹ነፃ አውጪ››ነቱን ምፀት አድርጎታል፡፡ በበረሃ የተደረሰው መዝገበ ቃላትም ‹‹ህዝብ በሁለት ይከፈላል›› ይላል-በ‹‹ደጋፊ›› እና
‹‹ተቃዋሚ›› ጎራ፡፡ ተቃዋሚ የተባለውንም የምድር እርግማን ሁሉ ይፈፀምበት ዘንድ ያዝዛል፤ ጭቆና፣ ግፍ፣ ጭካኔን… በህዝብ
ደህንነትና ሰላም ስም ማንበር፤ በህገ-መንግስት ትከሻ ማንጠልጠል፤ ህልምን፣ ምርጫን፣ ህዝበ-ውሳኔን… በክንደ-መሳሪያ መተርጎም…
በዚህ የተነሳ የለውጥ ሃዋርያት ወደ አደባባዩ ይጎርፉ ዘንድ ወቅቱ ግድ ብሏል፤ በርግጥም ስርዓቱ በደልን ዘርተው፣ በደልን በሚያፀድቁ፤
ጭቆናን ከዳር ዳር በሚያዳርሱ፤ በፍትሕ በሚዘባበቱ፤ ከመልካም አስተዳደር በእጅጉ በራቁ፤ በሀገር ሀብት ራሳቸውንና ዘመዶቻቸውን
ባበለፀጉ፤ ስቃይንና መከራን የአገዛዝ ስልት ባደረጉ፤ በአማላይ ዕቅድና ፖሊሲ በሚሸነግሉ፤ የምርጫን ውጤት እንደፍቃዳቸው
ማገለባበጥ በተካኑ… የተዋቀረ በመሆኑ እነሆ ሕዝቡ ለድፍን ሃያ ሁለት ዓመታት አሳር መከራውን እንዲቆጥር ተፈርዶበታል፡፡
መቼስ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በሥልጣን ስለቆየው የኢህአዴግ አስተዳደር ክስረትና ሽንፈት በእንዲህ አይነቱ የመፅሄት ፅሁፍ
ተንትኖ ለመጨረስ ቀርቶ፣ ጠቅሶ እንኳን ማለፍ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ ገመና በዜጎች መሀል አለመተማመን
ከመፍጠር አንስቶ በሀገር ጥቅም መደራደር፣ ህግን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ፣ ሰላዮችን አለቅጥ በሕዝብ መሀል መሰግሰግ፣
የሠብዓዊም ሆነ የፖለቲካ መብቶችን መጨፍለቅ፣ የሀገር ሀብትን መዝረፍና ማዘረፍ፣ በሥልጣን መባለግ፣ የልማት አጀንዳን
ለፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት ብቻ መጠቀም፣ በዚህም የሥራ-እጥ ቁጥርን ማናር፣ የኑሮ ውድነትን ማሻቀብ፣ ዜጎችን ማፈናቀል፣ በሠላማዊ
ህዝብ ላይ የታጠቀ ኃይል ማዝመት፣ ፍርሃትን ማንገስ… እያለ ይቀጥላልና ስንቱን ዘርዝሮ መጨረስ ይቻላል? ይህ ተቆጥሮ የማያልቅ ሃያ
ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረ አሳረ-መከራም ነው ብዙሃኑን ‹አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል?› የሚል ጥያቄ እንዲያንሰላሰል ገፊ ምክንያት
የሆነው፡፡ ተቀራራቢው መልስም ከሚከተሉት አንዱ ሊሆን ይችላል፡- የሞትን ያህል፣ በእስር ቤት የመበስበስን ያህል፣ በስደት
የመንከራተትን ያህል ወይም ለተጨማሪ ሃያ፣ ሰላሳ፣ አርባ… የጭቆናን ዓመታት ያህል?
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካገዛዙ ባህሪይ አንፃር ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ ለጥያቄው መልስ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንድ እንኳ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም፡፡
ምክንያቱም የስርዓቱ ስር የሰደደ ሴራ ‹ግደል› ሲባል የሚገድል፣ ‹ተኩስ› ሲባል የሚተኩስ፣ ‹አፍን› ሲባል ‹ለምን?› ብሎ የማይጠይቅ
የታጠቀ ኃይልን ማሰልጠኑ እና በሀሰት ለመክሰስ የማያመነታ ህሊና ቢስ ዓቃቢ ህግን፣ በሀሰት ለመፍረድ የማያቅማማ ዳኛን፣
በአጠቃላይ ሰጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛ ሎሌ ትውልድ… ለመፍጠር አቅዶ መስራቱ ነውና፡፡
በአናቱም የምሁራኖቻችን አድርባይነትም ሆነ ዝምታ ለከፋፋይ አገዛዙ ጉልበት ሆኖታል፡፡ አብዛኛዎቹም ነገን አጥብቀው የሚፈሩ፣
ከሀገርና ህዝብ ጥቅም በላይ የግል ምቾታቸው የሚያስጨንቃቸው መሆንን መርጠዋል፡፡ የተቀሩት (ገቱ ያላቸው) ጥቂት ታላላቆችም
ቢሆኑ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፤ ወይም ሞክረው አልተሳካላቸውምና ለዛሬቷ ኢትዮጵያ ‹‹የቁልቁለት መንገድ›› የድርሻቸውን
ማንሳታቸው አከራካሪ አይሆንም፡፡
ሌላው ትልቁ እንቅፋት ደግሞ የአገዛዙ ቂመኝነት ከዕለት ዕለት፣ ከዓመት ዓመት እየከፋ መምጣቱ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በአስከፊዎቹ
የሀገሬ እስር ቤቶች የከረቸመባቸውን እነዛን (ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን) የህሊና እስረኞች ‹ማኪያቬላዊ በቀል› በተሰኘው
መፅሀፉ ምሪት ፍዳቸውን ከማስቆጠር አልተመለሰም፡፡ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ…
የድርጊቱ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ ርግጥ ነው መንግስት ሰዎቹን ያሰረው ለሕዝብ ጥቅም ሲል እንደሆነ ዛሬም ድረስ ለማሳመን እየለፈለፈ
ነው፤ ይሁንና እስካሁን ያልነገረን ማሰቃየቱ፣ ፍትህ መንፈጉና ጠያቂ መከልከሉ… ለማን ጥቅም ሲባል እንደሆነ ነው፤ ለሕዝብ ይሆን?
ከሁሉም በላይ ግራ የሚያጋባው ነገር ደግሞ የእስረኞቹ ጠባቂዎች ልበ-ደንዳናነት ነው፤ የእነርሱን ያህል የተጎሳቆሉ፣ የእነርሱን ያህል
የተገፉ፣ የእነርሱን ያህል የተበደሉ ታሳሪዎችን ለማንገላታትና ለማሰቃየት ያላቸው ሞራል የበዛ ነውና፡፡
መቼም በዚህ ዘመን የእኛዎቹን እስር ቤቶች ያህል አስከፊ የሰቆቃ ቦታዎች በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ አይመስለኝም (ለካስ! እንዲህ
ዘመን የተጣላት፣ ታሪክ የተቃረናት ሀገር ዜጋ መሆን የከፋ ስቃይ ኖሯል!!) …ይህ ሁኔታም ይመስለኛል ከስርዓቱ አጋፋሪና አጫፋሪዎች
ይልቅ ጨካኙን በሽር አልአሳድን በሶሪያ ጎዳናዎች የሚፋለሙት ነፃነት ናፋቂዎች በሥጋ የተዛመዱህ ያህል እንድትቆረቆርላቸው
ያደረገው፤ ከጨቋኝ የሀገርህ ገዥዎችም ይልቅ፣ በየትኛውም ክፍለ ዓለም ያሉ ጭቁን ህዝቦችን ‹ወገኔ› እንድትል ያደረገው፤ ከእነርሱ
የመንፈስ አንድነትን፣ የነፍስ ትስስርን በፅኑ ስለምትጋራ ነው፡፡ አንተም ጭቁን ነህና የተጨቋኞች አበሳ ይቆጠቁጥሀል፤ አንተም
መብትህና ክብርህ ተገፏልና፣ ተመሳሳዩ ከተፈፀመባቸው ሕዝቦች ጎን መቆምህ ግድ ነው፡፡ …ከዚህ በተረፈ ‹እንመራሀለን› የሚሉህ
ወንድሞችህ፣ ልብህን በጩኸት ከማሸበር፣ ዘመንህን ካለፉትም በላይ የከፋ ከማድረግ፣ ለዓመታት ቀጥቀጠው ከመግዛት ያለፈ የፈየዱት
ቁም-ነገር የለምና ለእነርሱ ቀረቤታና ሀዘኔታ ከቶም ሊሰማህ አይችልም (በነገራችን ላይ አንዳንድ ለውጥ ናፋቂዎች ስርዓቱን ከመላው
የትግራይ ተወላጆች ጋር ደርበው መውቀሳቸውና መክሰሳቸው ስህተትና ለሀገር አንድነት ጠንቅ መሆኑን አምነው ካልተቀበሉ የትግሉን
ዕድሜ ከማራዘሙም በላይ ለከፋ ችግር መዳረጉ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ መልኩም ተሰልቶ የሚመጣ ውጤትም የኢህአዴግን ስህተት
በእጥፍ መመንዘር ነው የሚሆነው፡፡ እናም ምርጫው ሁለት ይመስለኛል፤ ይህ አይነቱን ሸውራራ /ጨለምተኛ/ አተያይ አስተካክሎ
ታላቂቷን ኢትዮጵያ በጋራ መገንባት፣ አሊያም የህወሓትን መንገድ በመከተል ለውጡን በዜሮ አባዝቶ ሀገርን እንደአንባሻ ዘጠኝ ቦታ
ለሚከፋፍል አደጋ ማጋለጥ)
የመነቃቃት መንፈስ…
ጥያቄው ይህ ነው፡- ህማማቱ ስንት ቀን ይፈጃል? የማራኪና ተማራኪ አስተዳደር ዕድሜው ምን ያህል ይረዝማል? ስለምንድር ነው
ባለስልጣናት አስፈራሪ፣ ቀለብ ሰፋሪ ህዝብ ደግሞ ተስፈራሪ የሆኑት? ማን ነውስ መብታቸውን የሚጠይቁ የሃይማኖት መሪዎችን-
አክራሪና አሸባሪ፣ ተቃዋሚዎችን-በሀገር ላይ የሚያሴሩ፣ ጋዜጠኞችን-የጠላት ሀገር ተላላኪ ያደረገው? በየትኛው ህግስ ነው ስርዓትን
መደገፍ-ሀገር ወዳድ፣ መቃወም-ይሁዲነት የሆነው? …ግና እመነኝ ውንጀላው በጉልበታም ገዥዎች ዘንድ የተለመደ የፖለቲካ ጨዋታ
ነው፡፡ በተቀረ ነፃነትን ያጣጣሙ ነባር ሀገራትን ትተህ፣ የቅርቦቹን እነቱኒዚያን ብትወስድ እንኳ፣ አደባባዩ ሽንፈት ያወጀባቸው
ገዥዎቻቸው ተመሳሳዩን ይፈፅሙ እንደነበር ድርሳናቶቻቸው ይነግሩሀል፡፡ ምንም እንኳ ዛሬ ታሪክ ቢሆኑም፡፡
ያንተም ጨቋኝ ገዥዎች ታሪክ የሚሆኑት፣ ይህ ሁሉ አሳረ-ፍዳ ከእነጦስ ጥንቡሳሱ ሊወገድ የሚችለው ዋጋን በሰማይ በሚከፍለው
‹‹ንሰሃ›› አይደለም፣ ጎዳናዎችን በሚያጥለቀልቅ ህዝባዊ ቁጣ እንጂ፡፡ እናም የአደባባዩን ርቀት ከጭቆናው ጋር እያለካኩ፣ የፍርሃት
ሰንሰለትን አየበጠሱ፣ በሁከተኛው ስርዓት ላይ የሚጮኹ የነፃነት ድምፆችን ማስነሳቱ አማራጭ አልባ መፍትሄ ነው፤ እነዛ ጎበዛዝቶች፣
በሚከፍሉት ዋጋ ታጋይ እንጂ ትግል እንደማይሞት እያስመሰከሩ፣ መንገዶቹን የሚያንቀጠቅጡ ፋኖዎች ከቁም እንቅልፍ የሚባንኑበትን
ዕለት ማሳጠር የግድ ይላል፡፡
በዚህም አለ በዚያ ይህ ኩነት ይለወጥ ዘንድ ስደት መፍትሄ አይሆንም፤ ማሳደዱን፣ ማስፈራራቱን፣ ማደህየቱን፣ ማሰር፣ መግደሉን…
ከቶም ቢሆን ሀገር ጥሎ በመሄድ ማሸነፍ አይቻልም፤ ምክንያቱም የስርዓቱም ፍላጎት ይኸው ነውና፤ የተቃወመውን፣ በስልጣን
አደገኛነት የጠረጠረውን ከሀገር በማባረር፣ ከአደባባዩ ይበልጥ ማራቅ፣ ከአይን መሰወር፣ በዚህም ለውጥ ያረገዘውን የቁጣ ቀን ማዘግየት፡፡ ለዚህም ነው ‹እኔ ምን አገባኝ›ም ሆነ ስደት መፍትሄ አይሆንም የምለው፡፡ አዎን! ሀገሪቱን የጥቂቶች ብቻ ለማድረግ
የተያዘውን ግብግብ ማጨናገፍ የምትችለው መሬት በሚያርድ ሠላማዊ ቁጣ ብቻ ነው፤ የሰብዓዊ መብት አፈናም ሆነ ሥራ እጥነትና
ድህነት የሚያሰድዳቸው ወንድም እህቶቻችን የባሕር ሲሳይ የሚሆኑበትን አሳዛኝ ዕጣ መለወጥ የምትችለው በአደባባይ ቁጣ ነው፤
የህሊና እስረኞችን ነፃነት ማወጅ የምትችለው እጅ ለእጅ ተያይዘህ የጎዳና ቁጣን በማሰማት ነው፤ ረሀብና ድህነትንም ማጥፋት
የምትችለው በቅድሚያ በሰንካላ ፖሊሲና ደካማ አስተዳደር በሚመራው ስርዓት ላይ መቆጣትና ማምረር ስትችል ነው፡፡ ይህ ሲሆን
ብቻ ነው ኢትዮጵያ የአንተም ሀገር የምትሆነው፡፡
 የጥሪው ድምፅ
‹‹ሰላም ይሉናል፣
ጥርሳቸውን እያፋጩ በጥል
ቤት እያፈረሱ በበቀል
ኑሮን እያደረጉ ገደል
ሰላም ይሉናል፣
እኛ እንግዛ፣ እናንተ ተገዙ
እኛ እንዘዝ፣ እናንተ ታዘዙ
እኛ እናስብ፣ እናንተ ደንዝዙ
ንገሯቸው እባካችሁ
ሰላም ነፃነት ነው ብላችሁ
ዝም አትበሉ
እሪ በሉ
ጠመንጃቸውን እስቲጥሉ፡፡›› (ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ‹‹ዛሬም እንጉርጉሮ›› የግጥም መድብል)
እነሆም የሀገሬ ጀግኖች ከአንቀላፉበት አዚም ይነቁ ዘንድ ጩኸቱ በርክቷል፤ የደውል ድምፁም አስተጋብቷል፤ አምነት የሚጣልበት
የአርነቱን ‹ሙሴ›ም፡-
‹‹ጥሩት አያ’ገሌን ያሳየን መንገዱን
መሪ ነው ያጣነው፣ ስናቋርጥ ዱሩን›› (አንዱአለም አባተ ‹‹የረዘመ ትንፋሽ›› የግጥም መድብል) የሚሉ ድምፆች እያፈላለጉት ነው፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁም፡- ይህ ሲሆን ነው በነብያቶች አንደበት የተነገረው በኢትዮጵያ ‹‹ታህሪር›› ታሪክ የሚሰራበት፣ ጭቆና-ድባቅ
የሚመታበት፣ ያጎነበሰ አንገት-የሚቃናበት፣ የተሰበረ ልብ-የሚጠገንበት፣ የደከመ መንፈስ-የሚበረታበት፣ ነፃነት የሚዋጅበት፣
በምኩራቦቹ ፍትህ-የሚሰበክበት፣ ህግ-የሚከበርበት፣ አድሎአዊነት-የሚወገዝበት… ይሆናል፤ ደጀ ሰላሞቹም የሰብዓዊ መብት
የሚከበርባቸው፣ የመኖር ዋስትና የሚረጋገጥባቸው…፤ አውደ ምህረቶቹም ያለቀሱ የሚስቁበት፣ የአዘኑ የሚፅናኑበት… ይሆናል፡፡ ይህ
ነው ነብያቶቹ የተናገሩት የተስፋው ቀን፤ የተስፋው ምድር፡፡ … እነሆም በገዥዎች ላይ ሰቆቃንና ዋይታን ከሚያዘንበው የመጨረሻዎቹ
ቀናት በፊት እንዲህ ማለትን ወደድኩ…
 አንድ ምክር-ለጓዶች
ደጋግማችሁ የአደባባይ ተቃውሞን፣ ሕዝባዊ ንቅናቄን ለማውገዝ እንደ ምክንያት የምትጠቀሙበት ‹‹ሀገሪቱን በልማት ጎዳና አከነፍናት፣
እድገታችን ለተከታታይ ዓመታት ከሁለት ዲጂት በላይ ከሆነ ሰነበተ›› የሚለው ሀቲት፣ተራ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም እስቲ
‹‹ይሁን›› ብለን ብንቀበለው እንኳ እንደምኞታችሁ የተቃውሞው ድምፆች ይዘጉ ዘንድ የግድ እንዲህ የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መመለስ
ይኖርባችኋል፡- የፖለቲካ ነፃነት አለመኖሩስ? በስርዓቱና በአምሳሉ የተቀረፁ ተቋማት ተአማኒነት ማጣታቸውስ? ጎሳን እየነጠሉ ለፖለቲካ
ጥቅም ማዋሉስ? አዋጅና ፖሊሲ ከመፅደቃቸው በፊት ሀቀኛ ተቀናቃኞች፣ ገለልተኛ ምሁራን እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በድፍረት
እንዲተቹበት አለመደረጉስ? (‹ሰው በእንጀራ ብቻ ይኖራል!› የሚል እምነት አራማጅ የሆኑትን የኢቲቪ ሸንጋይ ‹‹ምሁራኖች››ን
እርሷቸውና ማለቴ ነው)፣ ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ የሚያበረታ መደላድል አለመኖሩስ? ማንም ሰው ባመነበት ሃሳብ መደራጀት
አለመቻሉስ? የህግ የበላይነት ከወረቀት አለመዝለሉስ? መከላከያ ሠራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስና የደህንነት ተቋሙ ተጠሪነታቸው ከህገ-
መንግስቱ ይልቅ ለፓርቲ መሆኑስ? …እናም ‹ህዝብን ከፍ ከፍ አድርጎ ያከበረ መንግስት መንበሩ የፀና ይሆናል!›› እንዲል ጠቢቡ፣
የረዣዥም ተራሮቻችንን አናት ሳይቀር ለማንቀጥቀጥ በማስገምገም ላይ ያለው ይህ ብርቱ የቁጣ ድምፅ የሚረግበው፤ የፈረሱ ቅፅሮችን
በጋራ ለማነፅ በመሀከላችን መተማመን የሚሰፍነው፤ ‹ባቢሎናውያን›ነት ሰክኖ፣ እርስ በእርስ መደማመጥ የሚቻለው እነዚህ ከላይ
የተጠቀሱት የለውጥ ፈላጊው ወሳኝ ጥያቄዎች በአስቸኳይ ሁሉንም ወገን በሚያሳምን መልኩ መፍትሄ የተሰጣቸው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ ሌላ መፍትሄ የለም -ታሪክን በከፋ መልኩ ከመድገም በስተቀር፡፡
መልካም ዕድል!
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com – October 27

የአድዋዉ ልጅ አድዋ ገባ” የአርማጭሆ ልጅ የት ይግባ?!! (ናደዉ ከዋሽንግተን ዲሲ)


October 27, 2013
የአድዋዉ ልጅ አድዋ ገባ”
የአርማጭሆ ልጅ የት ይግባ?!!
እንደምን ከረማችሁ ዉድ የኢካዴፍ እድምተኞች “እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየዉ” በሚል ርእስ የጀመርኩትን መጣጥፍ “በአሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” ቀጥዪ ከክፍል 1-7 ድረስ ይህ ድህረ ገፅ ለንባብ አብቅቶልኛል ክፍል 8-9 ግን ከአንድም ሁለቴ በአደራ ደብዳቤ ሳይቀር ልኬ ሚዛን ባለመድፋቱ ለንባብ አልበቃም(የቅርጫት ራት ሆኗል) ሚዛን የሚደፋ ፅሁፍ ለማቅረብ አስቤ ፅሁፎቼን ቆየት ማድረግ በወሰንኩ ማግስት ዛሬ October 24, ምሽት አንድ ወዳጄ ስልክ ደዉሎ ሰበር ዜና ጀባ አለኝ የአዉራምባዉ አምደኛ ተጋዳላይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወደ ዘረኛ ግብረአበሮቹ ጉያ መሸጎጡን አጫወተኝ ከላይ በጠቀስኩት ርእስ እንደጠቀስኩት ይህ ሰላይ የትግራይ ጉጅሌ መልእክተኛ አዚህ ሰሜን አሜሪካ ኢሳትንና ሌሎች ጠንካራ ናቸዉ የሚባሉትን ተቃዋሚ ድርጅቶች የመሰለል ተልእኮዉን አጠናቅቆና የዳያስፖራዉን ተቃዋሚ ጓዳ ጎድጓዳ ሰልሎ የቃረማቸዉን የኦዲዮ ቪዲዮና ዳጎስ ያለ ጥራዝ ተሸክሞ አሜሪካ በገባበት አኳኋን ተመልሶ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ገባላችሁ ቡራኬዉንም ተቀብሎ በአዲስ አበባዉ ሸራተን ሆቴል የወሬ ቅራቅምቦዉን ለህወሀት የዜና አዉታሮችና የስለላዉ መረብ ክፍል አለቆቹ እያጋታቸዉ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ አሉን።Dawit-Kebede-Awramba-Times-146x200
እዚህ ያለዉ አጃቢዉ ሆድ አደሩ የስዉር ስለላ መረብ ጓዱ የአርማጭሆዉ ጓዱ ወስላታ የደርግ ካድሬ ምርጫዉ ስንሻዉ ቀሪ የመበታተን አጀንዳቸዉን ለማስፈፀም የመመርያ የኪስ ማስታወሻዉን ዳጎስ ካለ የደም ገንዘብ ጋር ተረክቦ ቀጣይ ጥሪዉን ይጠባበቃል በቅርቡም የህወሃት አባልነት ደብተሩ ከምስጋና ጋር እጁ ይገባል።
ነገ አሱም አይኑን በጨዉ አጥቦ ሚስቱንና ልጆቹን እንደለመደዉ ጥሎ ይከተለዋል እስከዚያዉ በአዲስ መልክ በአዲስ መሠሪ ተልእኰ ራዲዮ ጣቢያ የጥላቻና የጋጠወጥ “ዘለፋ ስንቁ” የመንደር አደግ ራዲዮኑን ያገማናል። እኛም ሃይ አንለዉ እጆቻችንን ጉንጮቻችን ላይ አድርገን የገለማ ቀረርቶዉንና ቱማታዉን እናዳምጥለታለን።
ወገኖቼ ኢትዮጵያዉያን ጨካኝና አምባገነን ገዢዎቻችን አገራችንን ጥለንላቸዉ በስደት የመኖር መብታችንን እየከለከሉን ነዉ። ዛሬም እንደትናንቱ በተመሳሳይ ድራማ ያፌዙብናል። አለቆቼ በድለዉኛል አስጥሉኝ አይነት ቀልድ፥እኛም ቄጠማ ጎዝጉዘን ርችት ተኩሰን እንኳን ወደህሊናችሁ ተመለሳችሁ እንላቸዋለን ጓዳ ጎድጓዳችንን መዝብረዉ አላግጠዉብን ተመልሰዉ ይሄዳሉ። ዛሬም እደግመዋለሁ፦”እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየዉ”

Thursday, October 24, 2013

100,000 children live in the streets of Addis Ababa - Shocking Documentary

ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት?


ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።
ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?
በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።
በዚህ ረገድ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች አሉ፤ ለምሳሌ:
  1. ወያኔ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “እንቢ አንጣላልህም” ያሉት መሆኑ የሚያኮራ ነው። ወያኔ ከጠበቀው በተቃራኒ የሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ መታየቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው። አብሮነታችንን ማጎልበትና ይህንን በአደባባይ፣ በአዳራሾች፣ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ውጭ የተጀመረው አገር ቤት መዳረሱ የማይቀር ነው። ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።
  2. ወያኔ በአባይ ግድብ ስም በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን “ከአባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ” “ከአባይ በፊት ሙስና ይገደብ” እያሉ ወዋጮዎቹን እንቢ ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የታየው ጽናት በጣም አበረታች ነው። የወያኔ ሹማምንት በአባይ ጉዳይ እንኳንስ ገንዘብ ስብሰባም ሊሰበሰቡ አልቻሉም። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
  3. ኢትዮጵያዊያን በስፖርትና በኪነጥበባት መስኮች የሚያደርጓቸው መሰባሰቦች ለትግሉ ትልቅ እገዛ ይሰጣሉ። የኢትዮጵያ ስፓርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) ከወያኔና ከወያኔ ሸሪክ ቱጃር ጋር ያደረገው ትንንቅ የሚያኮራ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን አገር፣ ነፃነት፣ ክብር ይበልጥብኛል ብለው የቀረቡላቸውን አጓጊ ማባበያዎችን “እንቢ” ብለዋል። ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
  4. ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ አበበ ገላው በመለስ ዜናዊ ላይ፤ ዘንድሮ ደግሞ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድና አቶ መስፍን የዘረኛው ወያኔ ግንባር ቀደም አስተባባሪ በሆነው ስብሀት ነጋ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ በጣም የሚደገፍና በውጭ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ባህል ሊሆን ይገባዋል።
  5. በስዊድን የሚገኙ የሕግ ባለሙያዎች የጀመሩት እና በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለው የወያኔ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ የማቅረብ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
እነዚህ መልካም ሥራዎች ምሳሌቶች ሲሆኑ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። አንዳንዱን ለአብነት ያህል ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
  1. በአገራችን ውስጥ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ከፈለግን ወያኔን ማስደንገጥ፣ ማሸበር፣ ካስፈለገም ማስወገድ የሚችል የአመጽ ኃይል መኖሩ ወሳኝ ነው። እንዲህ ዓይነት የወገን ኃይል ከጀርባው መኖሩ ሲሰማው ነው ሕዝብ ለእንቢተኝነት የሚነሳሳው። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ኃይል ቢቻል መቀላቀል፤ ካልተቻለም በአባላት ምልመላ፣ በፋይናንስ፣ በሎጂስቲክስና ዲፕሎማሲ መደገፍ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ከሁሉ የላቀ የእምቢተኝነት መገለጫ ነው።
  2. ትግሉ እየመረረ መሆኑ በመረዳት በርቀት ሆነን ከመብሰክሰክ በትግል ላይ ያሉትን ድርጅቶች መቀላቀል ሌላው አሁኑኑ ልናደርገው የሚገባ ነገር ነው። ድርጅቶች “አይረቡም” ብለን ስላጣጣልናቸው አይጠናከሩም። ድርጅቶችን ማጠናከርና ማዘመን ያለብን እኛው ነው። መሪዎችን ማውጣት ያለብን እኛው ነው። እስካሁን ድርጅቶችን ያልተቀላቀልን ካለን መቀላቀልና ትግሉን ማጧጧፍ ይኖርብናል።
  3. በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወያኔን “እንቢ” እንበል። “እንቢ” የማለትን አጋጣሚ ማሳለፍ የለብን። “እንቢ” ማለት የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ብዙዎች ናቸው። ለምሳሌ: -
ሀ) ወያኔ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አዲስ የገንዘብ ማለቢያ ለማድረግ አቅዶ ተነስቷል። ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችን በ2 ዓመት ጨርሼ አስረክባለሁ በሚል ማባበያ በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ለመሰብሰብ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይኸንን ነገር አጠንክረን “እንቢ” ማለት ይኖርብናል። “ለኛ ቤት ከመሰጠቱ በፊት፤ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መወደቂያ ያግኙ” ማለት ካልቻልን በራሳችን ማፈር አለብን። የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታትን አምባገነኖችን በገንዘብ አትደግፉ እያልን እኛ ራሳችን ወያኔን በገንዘብ የምንደግፈው ከሆነማ ከነሱ ብሰን መገኘታችንን እንወቀው።
ለ) ወያኔ በስደተኛ ስም በመካከላችን የሰገሰጋቸውን ካድሬዎችን የማጋለጥ ዘመቻ ማፋፋም አለብን። የወያኔ ደጋፊዎችን በኤርትራ ስደተኞች ስም እንደሚገቡ መረጃዎች አሉ። በደል ደርሶብናል ብለው መንግሥታትን አሳምነው የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አጠቃን ካሉት አገዛዝ ጋር የሚሠሩ መሆናቸው የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን አጠናቅረን ለየሀገሩ መንግሥታ ማቅረብ እንደ አቢይ ሥራ መያዝ ይኖርብናል።
ሐ) የወያኔ ባለሥልጣናት የሚገዟቸውን ቤቶች፤ የሚያስተዷድሯቸውን ቢዝነሶች እያደንን ማጋለጥ ይኖርብናል።
መ) የወያኔዎች ሹማምንት በአሜሪካና አውሮፓ በነፃነት ሊዘዋወሩ አይገባም። በሄዱት ሁሉ ተቃውሞና ውርደት ሊከተላቸው ይገባል።
ሠ) የወያኔ ቢዝነሶች ላይ ማዕቀብ ማድረግን (ቦይ ኮት) መልመድ አለብን። ጥረቶቻችንን በፈጠራ ከደገፍን ወደ አገር ቤት የምንልከው ገንዘብ የወያኔ የውጭ ምንዛሬ ረሀብ ማስታገሻ የማይሆንበት መንገድ መሻት አለብን።
ረ) ለወያኔ ባለሥልጣኖች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማዋረድ መጀመር አለብን። ስምንተኛ ክፍል እንኳን በወጉ ላልጨረሱ ሰዎች የማስትሬት ዲግሪ እንደሰጡ ማሳወቅ የኛ ኃላፊነት መሆን አለበት።
በግንቦት 7 እምነት ትግሉ በሁሉም ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያዊያን በያለሉበት ቦታ በተደራጀና በተቀናጀ መልክ ወያኔን ፊት ለፊት ከተጋፈጥን የድላችን ቀን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

የታሪክ ተጠያቂወች አንሁን፤ ለወቅቱ አገራዊ ጥሪ መነሳት አሁን ነው።



 አክሎግ ቢራራ (ዶር)
በቁጥር ሰባት የደመደምኩት፤ አገርን ከአስከፊ አደጋ ለመከላከል ከተፈለገ፤ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ
ለሰው ርህራሄ ከሌለው፤ ዘርፎ ለዘራፊ ዳራጊ ከሆነ የዘረኛ ስርአት አላቆ ለፍትሃዊ አማራጭ የሚቨጁ
አገር አቀፍ ተቋሞችን መገንባት ያስፈልጋል። አለበለዚያ፤ አገራችን ሁልጊዜ ያልተረጋጋ ች ሆና
ትቆያለች፤ ህዝቧም በድህነት አለንጋ ሲገረፍ፤ ወጣቱ ሲስደድ ይኖራል። መፍትሄው በእጃችን ነው።
ይህን አስፈላጊ ለውጥ ለማድረግ የባህል፤ በመጀመሪያ፤ ያስተሳሰብ፤ የአሰራር፤ የአደረጃጀትና የአመራር
ለውጥ መጀመር አለበት (Paradigm shift in thinking, organization and leadership)።
ለፍትሃዊ ለውጥ የሚደረግ ጉዞ የማንኛውም አገራዊ የሆነ ተቃዋሚ ግለሰብ፤ የማንኛውም ማህበራዊና
የፖለቲካ ድርጂት፤ የማንኛውም ብሄር፤ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ፤ ወዘተ አላማ መሆን
ይኖርበታል። የውጭ ጠላቶች፤ የውስጥ ደጋፊወች ባጠመዱልን “የከፋፍለህ ግዛው ክልል” ወጥመድ
ከቆየን አሰቃቂውን የህወሓት/ኢሃዴግ አገዛዝ ለመለወጥ አንችልም። እነ “አቦይ ስብሃት” የሚናገሩት
ፕሮፓጋንዳ ይቀጥላል።
የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ከሞት አፋፍ ያደረሰ ህመም (Critical illness and condition)
በቅርብ የሚያውቁ ታዛቢወች እንደሚሉት ከሆነ፤ በህይወት መቆየታቸው ያጠራጥራል። ቢቆዩም፤
ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያን ሊገዙ/ሊመሩ አይችሉም። ስለሆነም፤ ተተኪ መሪ ወይንም መሪዎች
መሰየማቸው አይቀርም። የገነቡት አገዛዝ ይቀጥላል። ለዚህ ሽግግር ከጀርባ ሆኖ ድጋፍ የሚሰጠው
የአሜሪካ መንግስት ነው። ህወሓት/ኢሃዴግ፤ የአሜሪካ መንግስት፤ ኢንቬስተሮችና ሌሎች ደጋፊወች
የመለስ አገዛዝ እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። መረጋጋት (Stability)ተደጋጋፊ ጥቅም ስላለው።
በሌላው አንጻር ሲታይ ግን፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብና በአፍሪካ ቀንድ ያንዣበበውን የአልካይዳ ሆነ ሌላ
አደጋ በዘላቂነት ለመከላከል፤ ብዙ ቢሊየን ዶላር ለሚያፈሰው የአሜሪካ መንግስት፤ ዘላቂና
አስተማማኝ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችለው አገዛዝ የህወሓት/ኢሃዴግ መንግስት አይደለም። የኢትዮጵያ
ሕዝብ ይህን ያውቃል፤ የአሜሪክ መንግስት የኢትዮጵያ ሕዝብን ፍላጎት ቸል ብሎታል። ዘላቂነትና
ፍትሃዊ የሆነ አገዛዝና እድገት እውን የሚሆነው፤ በህዝብ የተደገፈ፤ በህግ የበላይነት የተመሰረተ፤
ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ፤ ተቋሞቹ አገራዊ የሆኑ፤ መንግስቱ፤ አስተዳደሩ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ
አገልጋይ የሆነ፤ ባጭሩ፤ ለህዝብ ተወካይ የሆነ አገዛዝ (Governance) ሲገነባ ብቻ ነው። ይህን
ለማድረግ፤ ህወሓት/ኢሃዴግ መፍርስ አለበት። ይህን አማራጭ የማቀርብና የመደራደር ተግባርና
ሃላፊነት የተቃዋሚው ክፍል እንጂ፤ የህወሓት ወይንም የአሜሪካ መንግስት አይደለም። ስለሆነም፤
ለአንድ አገራዊና ህዝባዊ ስር ነቀል እንቅስቃሴ ካሰብን፤ በመቻቻል ተነስተን በስራ የምናሳይበት ወቅት
አሁን ነው። መግለጫ ማውጣት በቂ አይደለም። በመጀመሪያ እድሎች በፍጥነት እያመለጡን መሆኑን
መቀበል አለብን።
በ July 17, 2012, Thomas Mountain የተባለ አስመራ የሚኖር ጋዜጠኛ ስለ መለስ ዜናዊ መንግስት
“መፈራረስ” (Crumble) ና ሰለ ኢትዮጵያ መጥፋት የደረሰበት ድምዳሜ ሊሆን/ላይሆን ይችላል። እኔ 2

ኢትዮጵያ ትጠፋለች ብየ አልቀበልም። እሱ መሆኑ አይቀርም ባይ ነው። አስመራ ተቀምጦ ይህን ቢል
አያስገርምም። የኢትዮጵያ በዘር ተከፋፍሎ የመጥፋት ሴራ የተጠነሰሰው በውጭ ጠላቶቿና በኤርትርያ
ተገንጣይ ቡድኖች ነው። አሁንም መጥፋቷን ስራ ላይ ለማዋል የተዘጋጁ እንዳሉ አንጠራጠር።
እ.አ.አ.በ 1993 መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ “ከመቶ አመታት አይበልጥም፤ ከዚህ የተለየ ነው ብለው
የሚቃዡ ግለሰቦች የሚያወሩት ልብ ወለድ ነው” ያሉት ከሚያደንቁት ኢሳያስ አፈወርቂና ከሌሎች ጸረ
ኢትዮጵያ ከሆኑ ግለሰቦችና ግንባሮች የተማሩትን ነው። ህወሓት የተጸነሰው በዚህ መሰረታዊ ፍልስፍና
ነው። ስለሆነም፤ አደጋው አሁንም እያንዣበበ ነው። አገርን ለመታደግ የምንፈልግ ግለሰቦችና
ድርጂቶች ይህን የሚያንዣብብ አደጋ በጥልቅ ካላየን፤ ለዚህ አማራጭ ለመስጠት ብቁ ሁነን
ካልደረስን፤ ታሪክ የሚወቅሰው ኢሳይያስን ወይንም መለስን ሳይሆን እኛን ነው። እነሱ አላማቸውን
ያውቃሉ፤ እኛ አላማ ቢስ ሁነን እንታያለን። ይህ ሁኔታ በፍጥነት መለወጥ አለበት።
ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ እንቁም/እንናግር፤
አሜሪካኖች በአሁኑ ወቅት የመለስን መታመም በማጤን፤ አድራጊ ፈጣሪ (Power brokers) ሁነው
አማራጮችን ለእኛ በምስጢር ሲደራደሩልን፤ አገር አቀፍ የሆነው የተቃዋሚ ድምጽ የት ሄደ ብሎ
መጠየቅ አስፈላጊ ነው። እኛስ አገራችን ለማስቀደም ምን እየሰራን ነው? ተባብረን ድምጽ እያሰማን
ነው? ለምድን ነው አነድ አገር አቀፍ የሆነ፤ ሁሉንም የሚያካትት/የሚያነጋግር፤ በኢትዮጵያ አንድነት፤
በመላው ሕዝቧ እኩልነትና ሉአላዊነት፤ በሰብአዊ መብቶችና ክብር፤ በነጻነት፤ በፍትህ-ርትህ፤ በህግ
የበላይነት፤ በነጻ ምርጫ፤ ወዘተ መስፈርቶች የሚመራ አለም አቀፍ ስብሰባ (a Grand National
Coalition) አሁን ለማድረግ የማንነሳው ብለን መጠየቅ አለብን። አገራችን ከአደጋ ለማዳን ከፈለግን፤
የምንቃወመውን የጭቆና አገዛዝ ለመለወጥ ፍላጎት ካለን፤ ይህ ታላቅ ጥምረት (Grand Coalition)፤
ሽግግር ምን እንደሚመስል አገር ቤት ካሉ አገር አቀፍ ከሆኑ ተቃዋሚ ድርጂቶች ጋር በመወያየት
አግቫቭ ያላቸውን አማራጮች መቅረጽ ይኖርባቸዋል። ሽግግሩ ወደ ዘላቂ መፍትሄ ሊመራ የሚችለው፤
ኢትዮጵያን ከአደጋ ለማዳን፤ አብሮ በመቻቻል ለመኖር፤ ፍትሃዊ ስርአት ለመገንባት የሚፈልጉ ሁሉ
ሲካተቱና ሲሳተፉ ነው። ህወሓት/ኢሃዴግ ተካፋይ እንዲሆን ያልተቆጠበ ጥረት መደረግ የሚኖርብት
ይህን አላማ በማጤን ነው።
በእኔ ግምት፤ ህወሓትና እሃዴግ ውስጥ እርቅን፤ መቻቻልን የሚፈልጉ አሉ፤ እነዚህን መሳብ፤
ማነጋገር፤ መቅረብ ጥበብ ነው። የበላይ አዛዡ ህወሓት(ትግሬ) ቢሆንም፤ የአገራችን የጦር ሃይል
ከሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጣ ነው። ተራው ሰራዊት ለሃገር እንዲያስብ ማድረግ የሁላችንም
ሃላፊነት ነው። የውጭ መንግስታት፤ በተለይ፤ የአሜሪካ መንግስት ይህን የእርቅ፤ የመመካከር፤
አማራጭ ለመቀበል የሚገደድበት ምክንያት እንዳለ በተደጋጋሚ አሳይቻለሁ።
ይህን አላማ እውን ለማድረግ መጠየቅ ያለብን ጉዳይ “ኢትዮጵያዊያን፤ ነገሮች ከመበላሸታቸው፤
ሁኔታወች ከቁጥጥር ውጭ ከመድረሳቸው በፊት አማራጮችን በጋራ ተወያይተው፤ በጋራ ለማቅርብ
የሚችሉት” ቀን መቸ ነው፤ የሚጎተቱስ በምን ምክንያት ነው የሚለውን ጥያቄ በማቅረብ ነው።
የተማረው፤ አገር ወዳዱ፤ በመድብለ ፓርቲ፤ ወዘተ የሚያምን ሁሉ መሰብሰብ፤ መነጋገር፤ መመካከር፤
አማራጮችን ማቅርብ ያለበት ያለመሰብሰብ/ያለመተባበር አደጋን በማየት ነው፡፡ የምእራብ አገሮች፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ወዘተ ሊያከብሩን የሚችሉት ብቃት ያለን መሆኑን፤ ሃላፊነት የሚሰማን መሆኑን
በተግባር ስናስመሰክር ብቻ ነው። ወሬ ስለተወራ ብቃት አይደለም፤ ስራ ስለተሰራ ብቻ ነው።
የሃገራችን ሕዝብ ዋና ጥሪ መመለስ ብቃት ያሳያል። ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ አለሁ የማለት ጥያቄ
ፋታ እነደማይሰጥ መገንዝብ የብቃት መለኪያ ነው። 3

አሁንም ክፍፍል እየጎዳን ነው፤
መጠንቀቅ ያለብን ግን እኛ ተበታትነን፤ ኢትዮጵያን ካለባት አደጋ ልናድን አንችልም። አማራጭ
ለመስጥት አንችልም። ኢትዮጵያ ከፈራረሰች ዋጋ ከፋዩ አንድ ብሄር፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ መደብ
ወዘተ አይሆንም። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከባድ ዋጋ ይከፍላል። የመገንጠል፤ የእርስ በእርስ
ጦርነትን ጉዳት ባለፉት አስርት አመታት አይተናል። የባህር በር ማጣት ያመጣውን ጉዳት ብቻ ማየት
ይበቃል። ችግሩን ሳጤነው የምፈራው አበይት ነገር፤ የማናየው/ የምናየው ተደጋጋሚ ድክመት አለ።
አሁንም ወርቃማ የሆኑ፤ አገርን ከክፋ አደጋ ለማዳን፤ የነጻነትና የመልካም አስተዳደር ድልድይ
ለመዘርጋት የሚያስችሉ፤ ተጨባጭ ሁኔታወች የፈጠሩት እድሎች እያመለጡን ነው። እስካሁን
ልንጠቀምባቸው አልቻልነም። የተማረው የሰው ሃይላችን አያል ቢሆንም፤ የሃገራችንና የወገኖቻችን
እድል የሚወስኑት ምእራባዊያንና የእነርሱ ደጋፊ የሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ለምን?
በመከፋፈላችን። ስለሆነም፤ የእኛ መኖር፤ የእኛ መማር፤ የእኛ ድርጂት ማቋቋም ለኢትይጵያና ስብጥር
(Diverse) ሕዝቧ ትርጉሙ ምንድን ነው ብለን መጠየቅና መልስ መስጠት ተገቢ ነው።
አገራዊ የሆነ፤ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊነት በሩ ክፍት የሆነ አገር አቀፍና ከብሄር በላይ
የተደራጀ የፖለቲካ ተቋም በህወሓት መዳከሙ፤ በብልሃት፤ በጥበብ፤ በአርቆ አሳቢነት፤ በመቻቻል፤
መለኪያውች የሚዳኝ አመራር አለመኖሩ አደጋውን አባብሶታል። የነጻነት ጉዞውን ገትቶታል። ለዚህ
ነው፤ አሜሪካኖች ለእኛ እየወሰኑ ያሉት። መኖራችን ያልተቀበሉት ስለተከፋፈልን ብቻ ነው።
ማውንቴን የተባልው ጋዜጠኛ ይህን ድክመት ስላየ፤ ኢትዮጵያ ትበታተናለች ብሎ በእኛ አገር እጣ
ላይ ደመደመ። ቴሬንስ ላየንስም በቅርቡ ያወጣው ዘገባ ይህን ያለመረጋጋት አደጋ ያመለክታል።
አንዳንዶቻችን፤ ጋዜጠኛው አስመራ ሆኖ ህወሓትን ስለሚቃወም ጉዳቱን አልተረዳነም። የተቃዋሚው
ክፍል መበታተኑ፤ በብሄር የተደራጁና የታጠቁ ክፍሎች “አላማችን መገንጠል ነው” ማለታቸው
ለህወሓት አመራርና ለአሜሪካ መንግስት ሚና ፋታ ሰጥቷል። የአሜሪካ መንግስት (የውጭ ጉዳይና
የስለላ ድርጂቶች ልኡካን በመጠቀም) ከመቸውም ጊዜ የበለጠ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ
ገብቶ ውሳኔወችን የሚሰጥበት ምክንያት የመፈራረስ አደጋውን ስላየ፤ የአካባቢውን አደጋ ስለመዘነ፤
ተቃዋሚው ክፍል መከፋፈሉንና በአንድ አገራዊ አጀንዳ አለመቆሙን ስለተገነዘበ ነው።
አሜሪካ የወሰደው እርምጃ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነት፤ ለሃገራችን አንድነትና ጥንካሬ አስቦ ሳይሆን፤
በአፍሪካ ቀንድ ያለውን አደጋ ለመከላከል፤ የአሜሪካን ጥቅም ለማስከበር፤ ለዚህ ታማኛ የሆኑ
መሪወችን ለመመልመል ነው። እኛ በአንድ ላይ ሁነን ድምጽ ብናሰማ፤ ቢያንስ ሽግግሩን ለማሻሻል
እንችላለን የሚል ግምት አለኝ።
ይህን አደገኛ ሁኔታ እያየን፤ አሁንም የምንዳኘው፤ ጊዜ ባለፈበት የግለሰብ፤ የራስ ቡድን አደረጃጀትና
አመራር ነው። ትኩረታችን ተቃዋሚው ክፍል ምን አማራጭ አዘጋጅቷል በሚለው ተፈላጊ ቁም ነገር
ላይ ሳይሆን፤ በህወሓት መሪ ላይ የደረሰውን ህመም በሚመለከት ሁኗል። ብንወድም፤ ባንወድም፤
ብንቀበልም ባንቀበልም፤ ማውንቴን አስመራ ሆኖ ቢበይን/ባይበይንም፤ የህወሓት አመራር ራሱን
ስለመተካካት (Succession) እቅድ ካወጣ ቆይቷል። በተቃዋሚው ክፍል ያለውን ሁኔታ ስናይ ግን
እንኳን ከዚህ ደረጃ ለመድረስ (ተተኪ ለማዘጋጀት ቀርቶ)፤ አሁንም እርስ በእርሱ ለመተማመን፤
ለመፈላለግ፤ በዙር ጠረጴዛ ተቀምጦ ስለ ሃገር፤ ሰለወገን ለመነጋገር አልቻለም። ህወሓት ያዘጋጀው
የመተካካት አማራጭ የሚገዛው ለአንድ አላማ ብቻ ነው። ተተኪወች የሚመረጡት በታማኝነት፤
በስርአቱ ጠባቂነት፤ በአሜሪካ ጥቅም አገልጋይነት፤ በጥቅም፤ ተብሎ እንጂ የነጻነት ለውጥ ሃዋርያት
በመሆናቸው አይደለም። ሊሆንም አይችልም። አንዳንድ ተመልካቾች የሚሉት፤ ተተኪወቹ የባሰ
“ተኩላ፤ የባሰ በዝባዥ፤ የባሰ ጨቋኝ” ወዘተ ይሆናሉ የሚል ነው። ሌሎች ደግሞ፤ የተሻለ ሁኔታ 4

ይፈጠራል ይላሉ። ሊሆኑ፤ ላይሆኑ ይችላሉ። ዋናው መነጋገሪያ መሆን ያለበት የመለስ ተተኪ
የህወሓት አባላት ምን ያደርጉ ይሆን የሚለው፤ በምንም ልንቆጣጠረው የማንችለው ጉዳይ
አይደለም። እኛ ማድረግ ያለብን ከመለስ ባሻገር አይተን የተቃዋሚው እምቅ ሃይል (Potential
Force) አሁን ምን መስራት ይገባዋል የሚለውን አንገብጋቢ አገራዊ/ወገናዊ ጥሪ ነው።
የተዳፈነ እሳት ሲቀጣጠል፤
በአሁኑ ወቅት፤ ለግለሰብና ለህብረተሰብ ደህንነት፤ ለሰባዊ መብቶች፤ ለሃይማኖት መብት፤ ለነጻነት፤
ለፍትህ-ርትእ፤ ለህግ የበላይነት በተከታታይ የሚታገለው ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በዚህ
ዲሞክራሳዊ የሆነ የህዝብ ትግል ድምጻቸውና አቋማቸው የማይሰማው በውጭና በአገር ውስጥ
የሚገኙ የማህበራዊና የፖለቲካ ተቃዋሚ አካሎች ናቸው ለማለት ይቻላል። ህወሓት አያሰራን አለ
የሚለው እውነት ቢሆንም፤ ዘላቂ መልስ አይደለም። የሶሪያ ህዝብ በብዙ ሽህ እየሞተ መንግስቱን
ከመገልብጥ አፋፍ ላይ የደረሰው በፍርሃት አይደለም። ለነጻነት ባለው ድፍረትና ህብረት ነው።
የሚያበረታታው፤ የሃገራችን ህብረተሰብ ከፖለቲካ መሪወች መቅደሙ ብቻ አይደለም። የእስልምና
ሃይማኖት መሪወችና አባላት ለመብታቸው ሲታገሉ፤ የክርስቲያን አባቶች በየገዳሙ ሲነሱ አብሮ
የሚታገለው ወጣቱ፤ ሴቱ፤ አባቱ፤ እናቱ፤ ከተሜውና ገጠሬው፤ ወዘተ መሆኑ ጭምር ነው።
የሃይማኖት ክፍሎች አገራዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸው፤ ለነጻነት አብረው መታገላቸው፤ በያቅጣጫው
መተባበራቸው ፤ ለሃገርና ለነጻነት ያለው ፍላጎትና ትግል የማይገታ መሆኑን አስምሮበታል። እምቁ
ሃይል መንቀሳቀስ ጀምሯል፤ ምልክቶቹ ሁሉ የካቲትን፤ ምርጫ ዘጠና ሰባትን ይመስላሉ። ሕዝቡ
አስተዋይ በመሆኑ፤ የሚያስበው ከመለስ ባሻገር ነው ለማለት የሚያስደፍሩ ምልክቶች አሉ። ይህ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካሬ ጎን ነው። የኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ይህን አይቀበሉም።
ከመለስ ባሻገር እንይ፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ አንድ መሪ ብቻውን አገር ለመግዛት፤ ወይንም ድርጂት ለማስተዳደር አይችልም
የሚለውን ተመክሮ ካለፈው ታሪኩ ተምሯል። አምባ ገነን ቢሆንም፤ መሪው ውጤት ለመቀዳጀት
የሚችለው ደጋፊወችን መርጦ የስራና የጥቅም ተካፋይ በማድረግ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ማን፤
ምን እንደሆነ በሚገባ ያውቃል። ስለሆነም፤ ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ
ስርአቱ የፈጠረው ጠንካራ በጥቅም ላይ የተመሰረተ ድርጂትና ደጋፊወች የሉትም ብሎ አንደማሰብ
ይሆናል የሚል ግምት እንደሌለው አልጠራጠርም። ህዝቡ፤ መለስ ዜናዊ ቢኖሩ ባይኖሩ፤ ስርአቱ
ይቀጥላል ብሎ ያምናል። ለእኛም፤ ስርአቱ የፈጠራቸውን መተኪያወችና ተቋሞች መገንዝብ ለትንተናና
አማራጭ ለመቅረጽ ይረዳናል። መተካካትን ስናይ፤ ግለሰብ ቢታመም፤ እነደማንኛውም ህያው ከዚህ
አለም ቢያርፍ፤ ገዥው ፓርቲና የፈጠረው መንግስት እንዲቆዩ በቂ ዝግጂት አድርጓል። አሜሪካኖችም
የህወሓት ሽግግር የረጋ እንዲሆን በማሰብ እየረዱት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ስለዚህ፤
ህወሓት “የዳበሳ ጉዞ” ሳይሆን፤ በእቅድ የሚመራ ስልት እየተከተለ ነው። የህወሓት/ኢሃዴግ
ተጠቃሚወች፤ ያገኙትን ስልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ከመጠበቅ ወደኋላ አይመለሱም።
ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በውስጥ የሚነጋገርበት፤ “በዳበሳ ጉዞ” የሚመራው የተቃዋሚው ክፍል ብቻ
ነው የሚለውን ነው። ህዝቡ የቅንጂት መሪወች ያደረጉትን ስህተት የረሳው አይመስልም። ቶማስ
ማውንቴንና ሌሎች በጀምላው እነደሚሉት፤ ስርአቱ እንደ እምቧይ ካቭ ይናዳል ማለት ዘበት ነው።
ሆኖም፤ አምባ ገነን አመራርና አንድ መሪ የበላይ የሆነበት አገዛዝ መሪው ሲታመም ወይንም ሲሞት
ይሸበራል፤ ይብረከረካል። እንዳየነውና እንደምንሰማው፤ አንዳንዱም አውጭኝ ይላል። ብዙወቹ፤
አስቀድመው ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ልከዋል፤ ሃቭት አሽሽተዋል፤ ቤት ገዝተዋል። እንደሚሰማው 5

ከሆነ፤ ፈሪወች አገር ይለቃሉ፤ ገንዝብ ያሸሻሉ። ሁሉም ይሸሻል ማለት ዘበት ነው። ዋና
ተጠቃሚወችና ተቋሞች ይቆያሉ። በተለይም፤ የስለላና የመከላከያ ተቋሞች መሪ የስርአቱ
ደጋፊወች/ጠባቂወች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ውጭ በስደት ከምንኖረው የበለጠ ያውቀዋል።
የኤርትርያ ተወላጆች እንዴት ተመረጡ?
የመተካካትን አስፈላጊነት፤ የጠቅላ ሚኒስትሩ ህመም አስጊ መሆኑ ሲታወቅ፤ የህወሓት የስለላና
የመከላከያ የበላይ ባለስልጣኖች ያደረጉት ይገልጸዋል። አሁን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት፤ የጠቅላይ
ሚንስትሩ ታማኝ የህብረምጣኔ አማካሪ፤ አቶ ነዋይ ገብረአብና የውጭ ጉዳይ ዋና የበላይ አቶ ብርሃኔ
ገብረክርስቶስ--ሁለቱም የኤርትርያ ተወላጆች--የተደገፉት በመከላከያና ስለላ ድርጅቶች የበላዮች ነው
ተብሎ አዲስ አበባ በሰፊው ይወራል። አሜሪካኖች እንዳሉበትም ይነገራል። ይህ የመተካካት ስልት
ለህወሓት አደገኛ ሁኔታ እንደፈጠረና አነደሚፈጥር መገመት ይቻላል።በህወሓት ውስጥና በኢሃዴግ
ውስጥ ፉክክር መፍጠሩ የማይቀር ነው። አገር ወዳድ በሆኑ የትግራይ ተወላጆችና በኤርትርያ ምርጦች
መካከል የሚኖረው ፉክቻ መታየቱ አይቀርም። ሆኖም፤ ለጊዜው፤ የህወሓት የመተካካት መልክ
በሽግግሩ የተከታታይነትን፤ የዘላቂነትን ምኞትና አስፈላጊነት ያንጸባርቃል። የአሁኑ አወቃቅር
የሚያሳየው ችሎታ ሳይሆን፤ ለህወሓትታማኝ መሆን ቁልፍ መሆኑን ነው።
ታዲይ “ምን ይደረግ” የሚለው ዝንኛው የሌኒን መሰረተ ሃሳብ የሚያገለግለው እዚህ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በተከታታይ ሲጠይቀው የቆየ ጥያቄ አሁንም መልስ አላገኝም-- ህዝቡ ለመብቱ
ሲነሳ ተቃዋሚው ክፍልስ ምን ይሰራል? ምን ይጠብቃል?
ታላቁን ክፍተት እንሙላው፤
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መታመማቸው አከራካሪ አይደለም። የእግዚአብሄር ፍጥረት መሆናቸውን
አንርሳ። ፈላጭ፤ ቆራጭ፤ በሰላሚዊ ግለሰቦች ላይ ፈራጂ፤ ሰውን አዋራጂ፤ አማራውን “አህያ ነህ”
ባይ፤ ሰንደቅ አላማችን “ጨርቅ ነው” ባይ፤ “ሌብነት ጀግንነት ነው” ባይ፤ ከተፈጥሮ አደጋ ሊያድናቸው
አይችልም። መልአክ ስላልሆኑ፤ ዘላለማዊ ሊሆኑ አይችሉም። ብዙ ተመልካቾች የሚመኙት በህይወት
እንዳሉ የገነቡት አሰቃቂ ስርአት ተገርስሦ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን ተጎናጽፎ እርሳቸውንና የቅርብ
ግብረ አበሮቻቸውን ለህግ እንዲያቀርባቸው፤ እንዲፋረዳቸው ነው።
ይህ እንዳለ ሆኖ፤ በተደጋጋሚ ለማቅረብ የምፈልገው ዋና ነጥብ አለ። ይህም፤ ዛሬ እንደትላንቱ፤
አገራዊና ሁሉን አቀፍ የሆነ የተቃዋሚ ድርጂት አለመኖሩ፤ ለሽግግር የሚያበቃ፤ ትሁት፤ አገር ወዳድ፤
የማያዳላ፤ ትጉህ፤ አቻቻይ፤ ሚዛናዊ፤ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ያገባዋል ባይ፤ የኢትዮጵያና የአለም
ህዝብ ብቁነቱን የሚቀበለው፤ ለመደራድር ድፍረትና ትጋት፤ ጥልቀትና አስተዋይነት ያለው አመራር
አለመኖሩ ትልቅ ክፍተት ነው (Immense vacuum in national political organization and wise
and seasoned leadership)። የኢትዮጵያን ሕዝብ እንቅልፍ የነሳው ነው ለማለት ያስደፍራል።
ለዚህ ክፍተት በአስቸኳይ መልስ ለመስጠት ካልቻልን ታሪክ የሚወቅሰው ህወሓትን ብቻ ሳይሆን
(በእርሱ ላይ ታሪክ ሲፈርድ ቆየቷል፤ ወደፊትም ይፈርዳል)፤ የተቃዋሚውን ዘርፍ ጭመር ነው። ራስን
ከመውደድ፤ ጉረኛ ከመሆን፤ ከመከፋፈል፤ ከመጠላለፍ፤ ከሃገር በላይ ለስምና ለግል ዝና ከማጎብደድ፤
ለስልጣን ተገዥ ከመሆን የሚመጣውን ጉድ ወደጎን ትቶ ከሌላው ላይ ጉድ አለብህ ሲሉ ከመኖር
የሚታየው ሁኔታ ሃላፊነት መጉደሉን ነው። የህዝብ ጥያቄ ሃላፊነት ከጎደለው፤ አይጠቅምም፤
አያስተማምንም፤ ለውጣ አያመጣም። የዚህ አይነቱ ባህርይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት አያሟላም።
ባለፈው እንዳየነው፤ የህዝብን፤ በተለይም የወጣቱን ተስፋ ይበርዘዋል። እነ አንዷለም አራጌ፤ እነ 6

እስክንድር ነጋ፤ ሌሎች፤ ባልፈጸሙት ወንጀል የውሸት ምስክር እየቀርበ፤ ለሃገራቸው መኖር አለመኖር፤
ለመላው ህዝብ ሰብአዊ መብት መከበር፤ ለነጻነት፤ ለሰው ክብር፤ ለፍትህ-ርትእ በመቆማቸው ብቻ
ሲወነጀሉ እያየን፤ ይህን አስጨናቂ የአገራዊ ድርጂት አስፈላጊነት፤ የአመራር ክፍተት ለመዝጋት አሁን
አለመነሳታችን በህዝብ እያስጠየቅን ነው። ለሃገርና ለመላው ህዝብ “የቆምኩ ነኝ” የሚል ብቸኛ
(Opposition groups that operate in silos) ተቃዋሚ ሁሉ እውነተኛ ገጹን ማሳየት ያለበት
ልዩነቶችን ወደጎን ትቶ ለአንድ ሃገራዊ አላማ፤ ለነጻነት፤ ለእኩለንት፤ ለህዝብ የበላይነት፤ ለመድብለ
ፓርቲ ስርአት፤ ተባብሮ መስራት ነገ ሳይሆን፤ አሁን በተግባር ማሳየት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ
ይህ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ደጋግሞ የሚለው፤ እስካሁን የተጓዝነው “የጨለማ” ፖለቲካ ጉዞ የትም
አላደረሰንም። በመለያዩታችን የሃገራችን የባህር በር ተዘግቷል። ጥገኛ ሆነናል። ህወሓት በምስጢር
ተዋውሎ ከአንድ ሽህ ስድስት መቶ ስኩየር ኪሎሜትር በላይ የሚሆን ለም መሬት፤ ወንዞች፤
ተራራውች፤ የማእድን ሃብት ምንጮችን ለሰሜን ሱዳን አስረክቧል። የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተራበ፤
በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ለም መሬት ለውጭ መንግስታት፤ ድርጂቶችና ምርጥ የትግራይ ተወላጆች
አዛውሯል። የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በገፍ እንዲሰደድ አድርጓል። በገፍ ወደ መካከለኛው ምስራቅ
እነደሸቀጥ የሚላኩት እህቶቻችን ለመብታቸው የቆመላቸው መንግስት የለም። የህወሓት አባላት የሰው
ንግዱ ተጠቃሚወች መሆናቸውን ህዝቡ ያውቃል። ህወሓት/ኢሃዴግ፤ በአማራ፤ በኦሮሞ፤ በአዋሽ
ሸለቆ፤ በሶማሌ፤ በአፋር ወዘተ ህዝብ ላይ ኢሰብአዊ በደል ፈጽሟል። በአማራው ህብረተሰብ ላይ
ሲጸነስ የጀመረውን የብሄር ማጽዳትና መቀነስ አላማ አሁንም እያካሄደው ነው። በጎንደር በሁለት
የአማራ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ወንድ ወጣቶች ላይ ህወሓት የፈጸመው የሚዘገንን ድርጊት ማንም
ሊረሳው አይችልም። የሟቾችን አጽም ለመቀጣጫ ብሎ በመንገድ መጎተት ከኢሰባዊነት በላይ የሆነ
አረመኔያዊ ወንጀል ነው። በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደዚህ ያለ ዘግናኝ ድርጊት
የሚካሄድባት ኢትዮጵያ በ July 17, 2012, Economist, “Zenawi’s Police State” ብሎ የሰየመው
መንግስት የሚያካሂደው የመለስ ዜናዊ የጭቆና መንግስት ውጤት ነው። የአምባገነን አመራር መልክ
ይህን ይመስላል።
“ነገ በእኔም ይደርሳል”፤
እኛ ብዙ ጉድና ግፍ እያየን ችግሩ ነገ በያንዳንዳችን ላይ እንደሚደርስ አልተረዳነውም። የሁለቱ
ጎንደሬወች ሬሳ በአደቫቫይ በመሬት ሲጎተት፤ የተጎተተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭምር መሆኑን
የተገነዘብነው ጥቂቶች ነን ለማለት ይቻላል። ክብሩ የተገፈፈው፤ የተዋረደው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ
ነው። የሚያሳየው ሰቆቃ፤ በምንም ለሰው ክብር ደንታ የሌለው፤ አዋራጂ የመንግስት ስርአት እንዳለ
ነው። ይህ ስርአት፤ ማንኛውም ፍትህ ፈላጊ ግለሰብ ዋጋ እንደሚከፍል ደጋግሞ አሳይቷል። ታዲያ፤
እንደዚህ የመሰለውን የሰው ክብር ገፋፊ መንግስት ሊያቆየው የቻለው የራሱ ጥንካሬ ብቻ አይደለም።
የተቃዋሚው ክፍል መበታተን፤ የእኛ ቸልተኝነት፤ የእኛ በረባ ባልረባው መከፋፈል፤ የእኛ መናናቅ፤
የእኛ በዘር መደራጀት፤ በብሄር የተደራጁ እንቅስቃሴወች አሁንም እንገነጠላለን፤ አብረን ለመኖር፤
አብረን አዲስ ለሁሉም የሚቨጅ ስርአት አንገነባም ማለታቸው ወዘተ እየጎዳንና የህወሓትን አገዛዝ
እድሜ እያራዘመው ነው። የተከፋፈለ ቤት የጠላት መግቢያ በር እንደሚከፍት ሁሉ፤ የእኛም
መከፋፈል፤ በመነጣጠል እያስመታን ነው። አደጋው ህወሓት እየለየ ሲመታን በተመልካችነት፤ “ከእኔ
አልደረሰም” በሚል የሞኝ አስተሳሰብ ደጋግመን መቀበል ልማዳችን ስለሆነብን ነው። አገራዊ ድርጂትና
አመራር ለዚህ ሰቆቃ መልስ ሊሰጥ በቻለ ነበር። 7

የኢትዮጵያና የመላው ሕዝቧ ጥልቀት ያለው ችግር (Intractable problems)፤ በውስጥ ብቻ ሳይሆን
በውጭ ጠላቶችም የተደገፈ ነው። ጠላቶቻችን እርስ በእርሳችን አናክሰው ሊያጠፉን ባዘጋጁልን
ወጥመድ ውስጥ የመውደቅ እድላችን የሚያሳየው የራሳችን ከመከፋፈል የመጣ ድክመትን ነው።
በውስጥ፤ ሌላው ቀርቶ ህወሓት ቁመንለታል ለሚለው ለትግራይ ህብረተሰብ አልሆነም፤ ሊሆንም
አይችልም። ይህ ህብረተሰብ፤ በኢትዮጵያዊነቱ የኮራ፤ ከሌሎች እህቶቹና ወንድሞቹ ጋር አብሮ ተሰለፎ
የውጭ ጠላትን የመከተ፤ የባህር በሩን ያስከበረ፤ በሃይማኖቱ የጸና፤ አብሮ መኖርን ከዘረኝነት በላይ
የመረጠ ነው። የኦሮሞ ህብረተስብም እንደዚሁ ነው። ለመላው የትግራይ ህዝብ ደንታ የሌለው
የማፍያ ቡድን በዘረፋ፤ በመስረቅ፤ በመበዝበዝ፤ በማፈን፤ በመግደል፤ በማሳደድ፤ በመዋሸት፤
ለማዋረድ ሲል የሰውን አጽም በመንገድ በመጎተት ሃይሉን የሚያሳይ፤ ገንዝብና ሌላ ሃብት በማሸሽ
የሚያምን ቡድን ነው። ስርአቱ ካልተለወጠ ሰቆቃው ይቀጥላል።
ይድነቃችሁ ብሎ፤ ለሃገራቸው የሚያስቡ፤ ችሎታና ብቃት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እንደሌሉ አድርጎ፤
ምርጥ የኤርትራ ዘር ያለባቸውን ታዛዦች መርጦ ለወቅቱ ተተኪ ሲያደርግ ሌላውን እንደማያምን፤
እንደማያከብር የሚያሳይ አገዝዝ መሆኑን አስመስክሯል። ይህ ተራ የዘረፋ ቡድን ማንኛውንም
ለመብቱ፤ ለሰላም፤ ለነጻነት፤ ለፍትህ የቆመ ሁሉ እንደጠላት ይቆጥረዋል።
እንሰብሰብ፤ እንተባበር፤
ለዚህም ጭምር ነው፤ አሁን መሰብሰብ፤ አብሮ መስራት፤ ከብሄር በላይ ማሰብ፤ በአንድ ድምጽ፤
ለአለም ህዝብ አቅዋም ማሳየት፤ አገር ቤት ካሉ አገራዊ ከሆኑ ተቃዋሚ ስብስቦች ጋር ኩታ ገጠም
መሆን የሚያስፈልገው። ይህን ካላደረግን፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢታመሙም፤ ባይታመሙም፤ ሌላም
አደጋ ቢደርስባቸው፤ ባይደርስባቸው ያለው አሰቃቂ ስርአት በተጠቃሚወች ይተካል። ያለው የበላይ
ተጠቃሚ ባለስልጣን ቡድን “ጂብ” ይመስላል ብንል፤ መጭው/ተተኪው ደግሞ አንበሳና ነብር ሆኖ
ያገኘውን ሃይልና ጥቅም በበለጠ ያስጠብቃል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ አለ። የተከፋፈለ ተቃዋሚ
እስካለ ድረስ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና በሌላ መልኩ ይቀጥላል።
የምእራብ አገሮች፤ በተለይ አሜሪካ፤ እንደ ሕንድና ሳውዲ አረቢያ ያሉ የመሬት ነጣቂወች፤ ስርአቱ
እንዲቀጥል የተቻላቸውን ድጋፍ ይሰጣሉ። እነሱ የማያዩት፤ እኛ መግፋት ያለብን፤ የምእራብ
መንግስታትን ማሳመን ያለብን፤ የህዝቡ እንቅስቃሴ በምንም የማይገታ መሆኑን ነው። ይህን ማለት በቂ
ሊሆን አይችልም። እድሉን የመጠቀም ምርጫው የተቃዋሚው ክፍል መሆኑን ያለ ይሉኝታ መግፋት
አገራዊ ጥሪ መሆኑን ተቀብሎ “ተባበሩ፤ አትከፋፍሉን” ማለት የሞራል ግዴታ ነው። ለዚህ፤ ታላቅ
አገራዊ፤ ሁሉን አቀፍ ስብስባ በፍጥነት አካሂዶ ያሉትን ገንቢ አማራጮች ተወያይቶ በጋራ ማቅረብ
የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው።

ክፍል ዘጠኝ የመተባበርን ጥቅም በበለጠ ያቀርቫል

ፍራንክፈርት፣ ሳዋ ፣ሳሃራ ፣ ሜዲትራንያን፣ ላምባዱሳ



በልጅግ ዓሊ
ይህ የሆነው ጀርመን ፍራንክፈርት ውስጥ ነው። ወቅቱ በጋው ላይ ነው። እንደ አብዛኛው የአውሮፓ
ከተማዎች የፍራንክፈርት ውበት በበጋው ደመቅ ያለ ነው። በእንደዚህ ደስ በሚል ቀን ከትልቁ ባቡር ጣቢያ
ተነስቼ ሃብትቫኸ(Hauptwache) ወደሚባለው የከተማው ማዕከል ከዚያም አልፌ በእግር መጓዝን
እወዳለሁ። በጉዞዬ ወቅት በስተጎን እያለፍኩት የምሄደው ካይዘር መንገድ(Kaiserstraße) በመባል
የሚታወቀው የሴተኛ አዳሪዎች መንደር አለ። እዚህ መንገድ አካባቢ ተኮልኩለው የሚውሉትን ዕጽ
ተጠቃሚዎች በጎን እየገላመጥኩና የስልጣኔን በሽታ እያወገዝኩ አልፋለሁ።
እነሱን አልፌ ሴተኛ አዳሪዎቹ ከሚገኙበትን ፎቅ ስደርስ የተለመደውን ግር ግር ማየት ደስ ይለኛል።
ሴቶቹን ፍለጋ ፎቁን ለመውጣት የሚራወጠው ጎረምሳና አንዳንዴም የሽማግሌ ችኮላ የማያቋርጥ የሁል ጊዜ
ክስተት ነው። ገና ጀርመን እንደመጣን ለማየትም ይሁን ለሌለ ነገር በዚህች ፎቅ ዙሪያ ያልተመላለስን
አልነበረም። የተለያዩ ሃገር ሴቶች በሚማርክ ሁኔታ ደንበኛ ሲጠብቁ ማየት የሚገርም ነው። ገንዘብ ቀንሺ፣
የለም አንተ ጨምር፤ ክርክሩ አይጣል ነው። በምንም ቋንቋ የማይግባቡ የሁለት አህጉር ሰዎች በምልክት
ተግባብተው አንሶላ ተጋፈው በትንሽ ደቂቃ ይለያያሉ። ተግባራዊ ንቅናቄ እንጂ ንግግር የለም። በገንዘብ
የተስማማው ጭልጥ ብሎ ክፍሉ ውስጥ ሲገባና ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ደግሞ ላብ ጠምቆት የግንባሩን ላቦት
እየጠረገ ፈትለክ ብሎ ለማምለጥ የሚደርገው ሙከራ ሲገባ አንበሳ ሲወጣ ድመት ያስመስለዋል። ጥድፊያው
ከበዛበት የአውሮፓ ኑሮ ጋር እንኳን ሲወዳደር ካይዘር መንገድ ላይ ከሁሉም የበለጠ ጊዜ ወርቅ ነው።
ሰውየው ከወጣ በኋላ እመቤቲቱ ተሽሞንሙና እንደገና ከሌላው ጋር መደራደር ትጀምራለች። ይህ ሁሉ
በሃብታሙ የጀርመን ሃገር በሕግ ተፈቅዶ የሚደረግ አይመስልም።
ከፎቆቹ በታች ደግሞ እየተከፈለ የሚታይ ራቁታቸውን የሚደንሱ ቆነጃጅቶች አሉ። እነዚህን ማየት
የሚያዘወትሩት በብዛት ግዜ ያለፈባቸው ሽማግሌዎች ናቸው። ልብ ብሎ ለተመለከታቸው ሽማግሌዎቹ እኛ
ካረጀን ምን ዓይነት ሰውነት ተፈጥሮ ይሆን? ብለው ይህኑን አዲስ ሰውነት በማየት ልጅነታቸው ይመለስ
ይመስል ጠዋት ማታ ይመላለሳሉ።
ይህን ሁሉ ቲያትር ሳይመለከት ሻንጣ እየጎተተ ወደ ከባቡር ጣቢያ የሚነጉድ መንገደኛ ደግሞ ባቡር
እንዳያመልጠው ይኳትናል። እኔም ይህንን ሁሉ እየታዘብኩ የተለመደ ጉዞዬን እቀጥላለሁ። ፍራንክፈርት
በየዓመቱ ትለወጣለች። ሕንጻዎቹም እኛ ስንመጣ እንደነበሩት አይደሉም። ቁመታቸው እያደገ፣ ጥራታቸው
እየጨመረ መሄዱ የሚገርም ነው። የስራ መስኮችም በዚያው ልክ ይከፈታሉ። የውጭ ዜጋው ቁጥርም
ከሥራው መስክ ጋር አብሮ ይጨምራል።
ከሌሎች ከተሞች የሚገኙ ዜጎቻችን ሥራ ፍለጋ ወደ ፍራንክፈርት በመምጣታቸው የዜጎቻችንን
ቁጥር በዚያው ቀጥር እያበዛው መጥቷል። ከቁጥራችን መብዛት የተነሳ እንኳን የሩቁን፣ ከቅርብ ጎረቤቶቻችን
ጋር መነጋገር ተስኖናል። ከመብዛታችን የተነሳ መንገድ ላይ ስንተያይ ሰላም መባባል ከቆመ ስንበትበት ብሏል።
እንዲውም የቆየና አዲስ መጤ የሚ’ለይበት በሰላምታ ሆናል። የቆየው የስደተኛ ጉዳዩ ስለተፈጸመለት
የማያውቀውን ሰው ሰላም ማለቱን ትቶታል። አዲሱ ግን የሃገሩን ልጅ ወገኑን ሲያይ ብቸኝነቱ የሚቀልለት፣
ችግሩም የሚፈታለት፣ እየመሰለው ሰላም ማለት ያበዛል።
እኔ ግን ገና እንደ አዲስ መጤ ነው የሚያደርገኝ። ሰላም ሳልል ማለፍ አሁንም አይሆንልኝም።
እንኳን የሃገራችንን፣ የአህጉራችንንም ዜጎችን አላልፍም። እንዲውም በሰላምታዬ ግራ ተጋብተው የት ነው
የምናውቀው ብለው ለሚጨነቁት የተደጋገመ ሰላምታ እሰጣለሁ። በመርሳታቸው ራሳቸውን እንደ ጥፋተኛ
ቆጥረው ዓይናቸውን እስከሚያጥፉ ድረስ ትክ ብለው የሚያዩኝ ጥቂት አይደሉም።
ከዕለታት በአንዱ የተለመደ ጉዞዬ ላይ ወጣት የሆነ ዜጋችንን ሰላም አልኩት። ፈገግ ብሎ ጠጋ አለኝ።
ሁኔታው ከዚህ ቀደም የሚያውቀኝ መሆኑን ያሳብቃል። ዘንግቸው ይሆን? አሁን ጉድ ፈላ። አሁን የት ይሆን
የሚያውቀኝ? እኔው ራሴ ግራ ተጋባሁ። ሰላምታ ተለዋውጠን መንገዳችንን አንድ አድርገን ጉዟችንን ቀጠልን።
“እዚሁ ፍራንክፈርት ነው የምትኖረው?’’§የኔ ጥያቄ ነበር።
“አይደለም አብረን ነው የምንኖረው ያወቅከኝ መስሎኝ ነው’ኮ።’’§ረጋ ብሎ መለስ። ፍራንክፈርት፣ ሳዋ ፣ሳሃራ ፣ ሜዲትራንያን፣ ላምባዱሳ በልጅግ ዓሊ
 2
 “ኦ ይቅርታ ዘንግቼ ይሆናል።’’ እንደ ሃፍረት ተሰማኝ። ማፈሬን አውቆብኝ በፈገግታ አበረታታኝ።
 “ሰፈር ሁልጊዜ መንገድ ላይ ሰላም ስለምትለን የለየኸን መስሎኝ ነበር።’’
 አሁን ገባኝ። የምኖርበት አካባቢ ከሚገኘው ቡና ቤት ደጃፍ ላይ በበጋው ተሰብስበው ከማያቸው
ወጣቶች መሃል ነው። “ይቅርታ ብዙ ስለሆናችሁ አልለየኋችሁም። ሁል ጊዜ ቡና ቤቷ ጋ ተሰብስባችሁ
ሳያችሁ ከእናንተ ጋር ተቀምጬ መጫወትን እፈልጋለሁ ግን እንዳልደብራችሁ በሚል ስጋት. . .’’ብየ የት
እንደምንተዋወቅ ሲገባኝ በድፍረት ቀጠልኩ።
“ሁል ጊዜ ሰላም ስትለን ደስ ይለናል። ለጓደኞቼ በሞላ ትመቻቸዋለህ። ከቆዩት ሰዎች በደንብ ሰላም
የምትለን አንተ ነህ። ምን ችግር አለው ብትመጣና ብትቀመጥ። መጫወት እንችላለን። ግን አንዳንዱ የእኛ
ጨዋታ ላይመችህ ይችላል።’’§
እንዲህ የተጀመረ ጓደኝነት ነበር “ቀለበቴን ስጧት’’§በሚለው መጽሐፌ ውስጥ የተካተተውን “የሁለት
ትውልድን ወግ’’§ የወለደው። በሁለት ትውልድ ወግ ውስጥ የሰሃራን ጉዳይ ስተርክ በወቅቱ ከወጣቶቹ
የሰማሁት አንድ ሌላ የሚያሳዝን ታሪክ ወደፊት የተሟላ መረጃ ሳገኝ እጽፈዋለሁ ብዬ የቆጠብኩት ጉዳይ
ነበር። ሳዋ - የኤርትር ወታደር ማሰልጠኛ ቦታን ይመለከታል። ጥረቴ ሁሉ ሳይሳካ ዓመታት ተቆጠሩ።
በእርግጥ ስለ ሰዋ ከሚሰማው በላይ የተጨበጠ ማስረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ግን ምክንያት አለው።
የኢሳያስ አፍወርቂ የስለላ ሰንሰለለት ረጅም ነው።
ችግሩ እንደዚህ ነው። ሳዋ ውስጥ የሚካሄደው ግፍ በጣም አስከፊ ነው። ከመገረፍ እስከ መገደል
በየቀኑ የሚደረግ ክስተት ነው። ሳዋን መቃወም በግል ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ላይም መዓትን መጥራት ነው።
የኢሳያስ ሰላዮች እንኳን ኤርትራ ውስጥ ውቅያኖስ ተሻግረው አውሮፓ ውስጥ የሚጠረጥሩት ግለሰብ ከኖረ
ይህን ሰው አያድርገኝ ማለት ነው። ሽማግሌ አባቱ ወይም አሮጊት እናቱ፣ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ
የሚደርሰባቸው መከራ አይጣል ነው። ኤርትራ በዓለም ከሚገኙት አሰቃቂ እስር ቤቶች አንዷ ለመሆን
የበቃችው በዚህ የስለላ ድርጅት ምክንያት ነው። ኤርትራ ውስጥ ስንት የፖለቲካ እስረኞች አሉ? ከሚለው
ቁጥር ስንት ነጻ ሰዎች አሉ የሚለው መቁጠር ያንሳል ይላሉ። ታዛቢዎች።
ከወጣቶቹ ጋር ስንወያይ የሰማኋቸው አስገራሚ ታሪኮች ለዚህ ምስክር ይሆናሉ። አንድ ጊዜ
ለመጥፋት ጉዞ የጀመረ፣ ሕይወቱን ለማጣት የሚያጣጥር ሰው ሕይወቱን ለማዳን በቅርብ በሚገኘው ከተማ
የማይሄድበት፣ ዕርዳታ የማይጠይቅበት፣ ሃገር ኤርትራ ነች። ልጅ አባቱን፣ ወንድም እህቱን ፣ ጎረቤት ጎረቤቱን
የሚሰልልበት ሃገር ኤርትራ ነች። አንዴ ከዛች ሃገር ፣ ከሰዋ ስልጠና ለመጥፋት ጉዞ ከጀመሩ መቀጠል እንጂ
አቋርጦ መመለስ የሚባል ነገር የለም። እንኳን ራስ መሞከር የሚጠፉ ሰዎች መኖራቸውን እያወቁ አለመናገር
የሚስከትለው አደጋ ከባድ ነው።
ይህ ከሳዋ ጋር የተያያዘ የከረመ ታሪክ ለብዙ ጊዜያት አብሮኝ ኖሯል። በተለይ በቅርብ ጊዜ ተሳክቶልኝ ሰሃራ
በርሃን ለማየት ችያለሁ። በዚያ ሙቀቱ በበዛበት፣ ዱቄት የሆነው አሸዋ አይን ውስጥ
እየገባ በሚቆረቁርበት፣ እግር አሸዋው ላይ መራመድ አቅቶት ባለህበት ሂድ
እንደተባለ ወታደር አንድ ቦታ በሚረግጥበት፣ ሙቀቱ ሰውነትን ላብ በላብ
በሚደርግበት፣ ቦታ ላይ ብቻ ሆኖ ሞትን መጠበቅ ምን ይመስላል? የዛ ወጣት
ታሪክ ሰሃራ በርሃ ውስጥ ትዝ አለኝ። እንዲህ ባለው በርሃ ውስጥ ጥርት ያለውን
ሰማያዊ ሰማይ እየተመለከተ ወጣቱ፤ ጉልበቱ ደክሞ፣ ልቡ በውሃ ጥማት ፈንድታ
ነው ለዛለለም ያሸለበው።
ይህ በርሃ ውስጥ ሕይወቱ ያለፈው ወጣት ከአዲስ አበባ በወያኔ ከተባረሩትና ኤርትራዊ ሃማሴኖች
“አምቼ’’§ ብለው ከሚጠሯቸው መሃል አንዱ ነበር። “አምቼ’’§ ተብለው የተጠሩበት አዲስ አበባ ውስጥ
በሚገጣጠመው መኪና አምሳያ ነው። የተገጣጠሙ ኤርትራውያን ለማለት ነው። ወጣቱ በወያኔ ተባሮ፤ ተገዶ
ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኤርትራ ተላከ። በኤርትራ ስልጣን ላይ ከሚገኙት ሃማሴኖች ጋር ምንም አንድ ዓይነት
የሚያደርገው ጉዳይ አልነበረም። “ናፅነት’’§የሚሉትንም ሆነ የሻዕብያን ዓላማ አይጋራቸውም። በትዕግስት ግን
ችሏቸው ኖረ። በተለይ ያሰቃዩት የነበሩት “አመቼ’’§ተብለው እንደሱ ከአዲስ አበባ ከመጡት ውስጥ የሻዕብያ
አባል የሆነ ዘመድ ያላቸው ለኢሳያስ ታማኝ ለመባል ጭራቸውን የሚቆሉት ነበሩ።
 በዚህ በዛም ብለው ለሳዋ ወታደርነት መለመሉት። ከሳዋ ጠፍቶ ጉዞ ወደ ሱዳን ከሌሎቹ ጓደኞቹ
ጋር ጀመረ። የኤርትራ በረሃ ውስጥ እንዳለ ያለመደውን በረሃ ስላልቻለው ደከመ። ውሃ ጥማቱ በዛበት። ጉዞ ፍራንክፈርት፣ ሳዋ ፣ሳሃራ ፣ ሜዲትራንያን፣ ላምባዱሳ በልጅግ ዓሊ
 3
መቀጠል አቃተው። ሌሎቹን ጓደኞቹን ትተውት እንዲሄዱ ጠየቃቸው። እነሱም ትንሽ ራቅ ካሉ በኋላ ቅርብ
ወደሚገኘው የገበሬ ቤት እንደሚሄድ አሳመናቸው። እሺ ብለው ትንሽ አለፍ ብለው ይመለከቱት ጀመር።
ወጣቱ ግን ከተቀመጠበትም አልተነሳም። ይበልጥ መሬቱ ላይ ተኝቶ ሞቱን ይጠብቅ ጀመር። ጓደኞቹ ሊነጋ
ሰለሆነና ቢያዙ የሚመጣውን አደጋ በመገመት ጥለውት ሄዱ። ልጁ እዛው ቦታ ላይ በውሃ ጥም ልቡ ፈንድታ
ሞቶ ጠዋት ገበሬዎች አገኙት። ቤተሰቦቹ እንደ አጋጣሚ የሚያውቁት የሻዕብያ ባለስልጣን ነበርና በገንዘብ
ብዛት ካለ ብዙ ስቃይ ክፉውን ቀን ተወጡት።
“ሳዋ በምድር ላይ ከሚገኙት ገሃነብ ስፍራዎች ሁሉ የከፋ ነው። ስልጠናውን ተወው ማንም ወታደር
ይሰለጥናል። ሳዋ ግን መሰልጠን ብቻ ሳይሆን በተለይ አዲስ አበባ የነበርነው ኤርትራውያን ለነጻነት ትግሉ
ብዙ አስተዋጽዖ አላደረጉም በሚል ቂም የያዙ የሻብዕያ ወታደሮች ቂማቸውን የሚወጡበት ቦታ ነው።
በውስጣቸው ያለውን የበታችነት ስሜት እኛን በማሰቃየት የበላይነታቸውን ለማሳየት እንቅልፍ ያጡ
ይመስላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አምቼ ያልሆኑት ወጣቶች እኛ ባመጣነው ነጻነት ትንደላቀቃለህ በማለት
ከመከራው ትንሽ እንዲቀምሱ መከራቸውን ያሳይዋቸዋል። በተለይ ጴንጤዎችና ጆሆቫዎች የሚታሰሩት ሳዋ
ውስጥ ነው። ለሻዕብያዎች ኤርትራ የእነሱ ብቻ ነች። ሌሎቻችን ግን ለእነርሱ ሸክም ነን። ሊጠፉ አስበዋል
በሚል ብቻ የምንገረፈውን ልነግርህ አልችልም። ተመልሶ ወደ ሳዋ መሄድ ማለት በቁም በእሳት መቃጠል
ነው። ስለዚህ በመንገድ እንሞታለን እንጂ ተመልሰን የኤርትራን ምድር አንረግጥም።’’
ይህ ነበር የብዙዎቹ ቃል ስለ ሳዋ። ወጣቶቹ ይህንን ጉዳይ ሲያስረዱኝ ፊታቸው ላይ እመለከት
የነበረውን ጥላቻ አስታውሰዋለሁ። ያ ኤርትራውያን በተለይ በውጭ የነበሩት ከነፃነት በኋላ የነበራቸው የተስፋ
እንጀራ እንዲህ መለወጡ ምን ጊዜም ይገርመኛል። ብዙውን የማስታውሰው ነው።
ፍራንክፈርት ገና እግራችን ሲረግጥ፣ የኤርትራ “ናፅነት’’§ ገና ፈር ሳይዝ፣ ባቡር ጣቢያው (ሃብት
ባንሆፍ ውስጥ) አንድ ኢንተር ሲቲ የሚባል ቡና ቤት ነበር። አሁን ፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ ስለ ተቀያረ ያ
ቦታ በሌላ ተለውጧል። እዛ ቡና ቤት ፀጉራቸውን ያጎፈሩ፣ ሰውነታቸው ኪሲታ የሆኑ ብዙ ኤርትራውያን
የሻዕብያ ደጋፊዎች ተሰብሰበው ፖለቲካ ይቀዱ ነበር። የጀበሃ ደጋፊዎች ደግሞ ከባቡር ጣቢያው ፊትለፊት
የነበረ የግል ቡና ቤት ነበራቸው። ሁለቱ እንደ ዘይትና ውሃ አይደበላለቁም ነበር።
እዚህ ቡና ቤት የሻዕብያ ደጋፊዎች ተሰብስበው በየቀኑ የሚወያዩትን ለመስማት እጓጓ ነበር። አንድ
ቀን ተሳካልኝ። እነሱ የማያውቁት ካስል ከሚባለው ቦታ የመጣ የጀበሃ አባል እያስተረጎመልኝ ሰማሁት።
በውይይታቸው ኤርትራ በቅርብ እንደ ታይዋን ፣ እንደ ሆንግ ኮንግ፣ እንደ ጃፓን ትሆናለች የሚል የተስፋ
አምባሻ ይግምጡ ነበር። እንደ አማራጭ መፈክር “ኤርትራ የግላችን፣ ኢትዮጵያ የጋራችን’’§የሚል የስግብግቦች
መፈክርም ነበራቸው። በትግራይ ተወላጆች ላይ የነበራቸውም ንቀት አልፎ አልፎ “አጋሜ’’§የሚለውን እንደ
ሃገር መጠሪያ ቃል ሳይሆን እንደ ስድብ ይጠቀሙበት ነበር። “ሃድጊ’’§ደግሞ ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ ስም
ነው። ብዙዎቹን ገደብ የሌለው የኢሳያስ ፍቅር ናላቸውን አዙሮት ነበር። ይህ አላግባብ የሆነ የመሪ ፍቅር
የሚያመጣውን በሽታ ከልምድ ሰለማውቀው ከልቤ ነበር ያዘንኩላቸው።
ይህ ለኢሳያስ የነበራቸው ቅጥ ያጣ ፍቅር አንድ ነገር አስታወሰኝ። እድገት በሕብረት ታውጆ ጃንሜዳ
ተሰልፈን በነበረበት ወቅት እነ መንግሥቱ በጂፕ ሆነው በዘማቹ ውስጥ ሲሄዱ ላንቃችን እስከሚሰነጠቅ
“መንጌ’’§ ብለን የጮኽንለት ፋሽሽቱ መንግሥቱ ከጥቂት ዓመታት በኋላ እኛኑ እየገደለ በየመንገዱ መጣሉ
ነበር ትዝ ያለኝ። የኢሳያስም ከዛ የበሳ ሆነና አረፈው። ሚኒስተር በጥፊ የሚመታ፣ የፈለገውን የሚያስገድል፣
የሚያስር፣ የውጭ ጋዜጠኛን የሚሳደብ ቅጥ ያጣ ባለጌ መሪ ሆነ።
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ያ የብዙ ሰዎች ሕይወት የፈሰሰበት “ናፅነት’’§ ያመጣል ተብሎ የነበረው
ብልጽግና ቀርቶ፣ ኩሩ የነበረው የኤርትራ ሕዝብ ተዋርዶ፣ በስደት በበረሃና በባሕር የሚያልቀውን ወጣት
ስቆቃ የሚሰቀጥጥ ሆኗል። ኤርትራም እንኳን ታይዋንን ልትመስል መንግስት ከሌላት ከሶማሊያ ብሳ
በኢኮኖሚ ወድቃ ትገኛለች። እነዛም አፍሮ ኤርትራውያን እንደ በፊቱ የተስፋውን ምግብ መመገብ አቁመው
በተስፋ መቁረጥ በካይዘር መንገድ በሚገኙት ቁማር ቤቶች ወይም ርካሽ የቢራ ቤቶች ብዙዎቹ ደንበኛ
ሆነዋል። የበረቱት ወደ አሥመራ ሳይሆን ወደ አዲስ አበባ ንግድ ጀምረዋል። ወጣት ኤርትራውያን በተለይም
“ከናፅነቱ’’§በኋላ የተወለዱት የሃገራቸው ሁኔታ ያኔ ፍራንክፈርት ስንመጣ እንደነበሩት አፍሮ የሻዕቢያ አባላት
አይመለከቱትም።
 ፍራንክፈርት፣ ሳዋ ፣ሳሃራ ፣ ሜዲትራንያን፣ ላምባዱሳ በልጅግ ዓሊ
 4
ወጣቶቹ እንደ ሻዕብያው ተዋጊዎች በባዶ ተስፋ ተወጥረው “ሓደ ሕዝቢ፣ ሓደ ልቢ’’§
የሚለውን ባዶ መፈክር ማሰማት ትተዋል። ሻብያዎቹ በርሃ እንደነበሩበት ወቅት
ተርበው መኖር አይሹም። አዲሱ ትውልድ መቸገርን አይፈልግም። በየቀኑም
በኤርትራ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው “የናጽነት’’§ የጦርነት ታሪክ አይመስጣቸውም።
ነጻነቱ ለውጥ ከሌለውና የባሰ ከሆነ ባፍንጫችን ይውጣ ባዮች ናቸው። በዚህም
ምክንያት መከራውን ችለው ወደ ተሻለ ዓለም ጉዟቸውን ቀጥለዋል።
አብዛኛዎቹ የኤርትራ ወጣቶች ሃገራቸውን ለቀው በሱዳን አድርገው በሰሃራ በርሃ አቆርጠው ሊቢያ
ከደረሱ በኋላ በመርከብ ወደ ኢጣሊያን ላምባዱሳ ይጓዛሉ። ይህ አስከፊና አደገኛ የሆነ ጉዞ ለብዙ ወጣቶች
ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሜዲትራንያን ባሕር ውስጥ በሚደርሰው አደጋ
ከሚሞቱት ስደተኞች ውስጥ የኤርትራውያን ቁጥር ከፍተኛ ነው። በዚህ አሰቃቂ ጉዞ የሚሳተፉት
ኤርትራውያን ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊዎች ፣ ሶርያውያን፣ ግብጾችና ሌሎችም የአፍሪካ
ሃገሮች ዜጎች ይጓዛሉ።
እንደ አጋጣሚ ሰሃራ በተጓዝኩበት ወቅት ሜዲትራንያን ባሕር ጠረፍ ላይ
በድብቅ ቦታ ከኢሳያስ ጨካኝ አገዛዝ ያመለጠውን ወጣት በስልክ አነጋግሬው
ነበር። ዘመዶቹ ስዊድንና ጀርመን እንደሚገኙ አስረድቶኝ፣ ዋናው ዓላማው
ከእነርሱ መገናኘት ነበር። በሜዲትራንያን ባሕር ጠረፍ ላይ ወደ ላምባዱሳ
የሚወስዱትን መርከቦች ዓይነት ተመልክቻቸዋለሁ። ብዙዎቹ ተጥለው የሰነበቱ
ሲሆኑ በኢጣሊያን ፖሊሶች ቢያዙ እንኳን እንደ ንብረት ብዙ ጉዳት
የማያስከትሉ ናቸው። (ፎቶው ስደተኞቹን ወደ ላምባዱሳ(ኢጣልያ)
የሚያጓዙበት መርከብ ዓይነት ነው።
ይህንን ወጣት ስለጉዞው በትክክል ጠይቄው ነበር። አንድ ሺህ ኢሮ ከፍለው በመርከብ ከሚሻገረው
ግለሰብ ጋር ይገናኛሉ። ቀሪውን አምስት መቶ ኢሮ መርከብ ላይ ሲሳፈሩ ለመክፈል ይስማማሉ።
የሜዲትራንያን ባሕር ማዕበሉ ቀዝቀዝ በሚልበት ወቅት ይነገራቸውና ይዘጋጃሉ። ዝግጅቱ ቀላል ነው። ሁለት
ወይም ሦስት ሱሪ መልበስ፣ ከላይም ልብስ መደራረብ፣ የሚብለጨልጭ ወይም የሚያበራ ነገር አለመያዝ ብቻ
ነው። በትንንሽ ጀልባ ተሳፍረው ተለቅ ወደ አለው መርከብ ይወሰዳሉ። በዛ ተጭነው ጉዞ ወደ ላምባዱሳ
ያደርጋሉ። ጉዞው ምንም ቅርብ ቢሆን በመርከቦቹ እርጅና፣ ሳያስቡት በሚነሳ ማዕበል ፣ ባልተጠበቀ ንፋስ
ምክንያቀት የሚፈጠረው አደጋ ብዙ ነው።
ሊቢያ ውስጥ እነዚህ ስደተኞች የባሕሩን መርጋትና፣ አመቺው ጊዜ እስከሚዘጋጅላቸው ድረስ
በድብቅ ቤት ውስጥ ይቀመጣሉ። ማንም ሰው እንዳያያቸው ከተደበቁበት አይወጡም። የሚያጓጉዟቸው
መርከበኞች እስኪጠሯቸው መደበቅ ነው። ከዛ በኋላ ቀኑ ሲደርስ አንድ በአንድ ይሳፈሩና ጉዞ ይጀምራሉ።
የሊቢያ ሁኔታ ለጥቁሮች ከጋዳፊ በኋላ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ለጥቁር ያለቸው ጥላቻ ድሮ ከነበረው በብዙ
እጅ ጨምራል።
ቱኒዚያ ውስጥ ከሊቢያ ርካሽ ነዳጅ እያመጡ የሚሸጡ ግለሰቦችን ወደ ሰሃራ እየተጥጋን ስንሄድ
አግኝቼ ነበር። ከመኪና ወርጄ ወደ ሊቢያ መሄድ እንደምፈልግና ሊወስዱኝ ይችሉ እንደሆን ለሙከራ ያህል
ጠይቄያቸው ነበር። ቱኒዚያኖቹ በግልጽ ይህ ሊሆን እንደማይችልና በተለይ አፍሪካውያን ሊቢያ ውስጥ
በአሁኑ ወቅት እየተሰቃዩ እንደሆነ ነው ያስረዱኝ። ስለ ሊቢያ ሁኔታ ሲያስረዱኝ በአሁኑ ወቅት ሕግ
እንደሌለና ጠብመንጃ ብቻ ሃገሪቷን እንደሚገዛ ነበር የነገሩኝ። በጣም የሚገርመው እኔ ከቱኒዙያ ሳልወጣ
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስተር በታጠቁ ሰዎች ታግቶ ነበር። በኋላም ተፈታ።
ለአንድ ሳምንት ያህል ከሳሃራ ጀምሮ የሜዲትራንያንን ባሕር ዳርቻ እየዞርኩ ለማየት ሞክሬለሁ።
የሚጠቀሙባቸውን መርከቦች ተመልክቻለሁ። የማይመለከታቸው ሰዎች ደህንነት ለመጠበቅ ስል ለጊዜው
ሙሉውን ሪፖርት አዘግቸዋለሁ። የምጠብቃቸው ሁኔታዎች ሲሳኩ ደግሞ ሙሉውን ለአንባብያን ለማድረስ
እሞክራለሁ።
ክፍል አንድ ሲመች ይቀጥላል። ቱኒዚያ Oct. 17/2013
Beljig.ali@gmail.com
ስለ ስደተኞቹ የሚያስብ ሁሉ በሰላም ይክረም!

Monday, October 21, 2013

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::


 20 בOctober 2013 0 Comments
ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል::
ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ethiopian_troops_pickupገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::
በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::
ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::
ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::
መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ

Saturday, October 12, 2013

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!


ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።
ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።
እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።
ሌላው ኃይለማሪያም የሚናገረዉ ቃል ጠፍቶት በተደጋጋሚ ሲንተባተብ የታየዉ በሽብርተኝነት አካባቢ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ ነዉ። በእኛ እይታ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋነኛው አገር በቀል አሸባሪ ህወሃት እና ህውሃት ብቻ ነው። ህወሃት ስልጣን ላይ ያቆየኛል ብሎ ከገመተ የማይመሰርተው የክስ ዓይነት፤ የማያፈሰው የንጹህ ሰው ደም ፤የማያፈነዳው የቦንብ እና የፈንጂ ዓይነት እንደሌለ ከሃውዜን እስከ አዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ቋሚ ምስክሮች ናቸው። ይህንን እኩይ ተግባሩን ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው በዊክ-ሊክ ላይ የወጣው መረጃም አሳይቷል።
የህውሃት ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሠላማዊ ትግሉን ለማፈን ከፈለገ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰቡትን ዜጎች ከሌላ ከማንም ጋር ማነካካት አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሁሉ አንደ ኃይለማሪያም ሞቶ የተቀበረን ሰዉ ራዕይ የተሸከሙ የአመለካከት ደሃዎች ሳይሆኑ የራሳቸው አስተሳሰብና ህያዉ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አነዚህን ሠላማዊ ታጋዮች ከማይገናኝ ሌላ ኃይል ጋር አቆራኝቶ ለመምታት መሞከር ለኃይለማሪያምም ሆነ ለጌቶቹ አይበጃቸዉም። ዛሬ በወያኔ ነብሰ ገዳይ ወታደሮች ተከብቦ እዩኝ እዩኝ የሚለዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ የነደደ ቀን ደብቁኝ ማለት ይመጣልና ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት የበደለዉን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ የነጻነት ኃይሎችን እንዲቀላቀል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።
በመጨረሻም ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ስለ ግንቦት ሰባት ተጠይቆ ሲመልስ ግንቦት ሰባት “በህልም ውስጥ ያለ ድርጅት” ነው ብሏል። ታድያ ምነዉ ተኝቶ ህልም የሚያልም ድርጅት ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል? ለምንስ ይሆን ወያኔና ታማኝ ሎሌዉ ኃ/ማሪያም ያገኙትን ሁሉ ግንቦት ሰባት እያሉ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት? ያገኛችሁትን ሁሉ የግንቦት ሰባት አባል እያላችሁ ትከሳላችሁ? ለምንስ በግንቦት ሰባት ስም ታስራላችሁ? ትገርፋላችሁ? ትገድላላችሁ? ተኝቶ ለሚያንቀላፋ ድርጅት ለምን ትሸበራላችሁ፤ ለምንስ እንቅልፍ አጥታችሁ ትባዝናላችሁ? ግንቦት ሰባት እናንተ አልገባችሁም አንጂ መነሻውንና መድረሻውን አጥርቶ የሚያውቅ፤ ከደመናው ባሻገር ፍንትው ያለ የነፃነት ዉጋገን የሚታየው ባለ ታላቅ ራዕይ ድርጅት ነው። አስኪ ምናልባት ቢገባችሁ ተረት ቢጤ እንንገራችሁ፤
“አንዲት ሚዳቋ ነበርች አሉ። ሚዳቆ ከመሬት ገንዘብ ተበድራ ሲትኖር ከእለታት አንድ ቀን መሬት አፍ አውጥታ ብድሬን መልሽ አንጂ ብላ ትጠይቃታለች። ሚዳቆዋም ደንግጣ ከነበረችበት ቦታ ፈትለክ ብላ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥታ እፎይ ያንን ድምጽ ከአሁን በኋላ አልሰማም አለች። መሬትም በይ ብሬን ክፈይኝ ስትል ዳግም ጠየቀቻት። እንዴ ይህች መሬት የሌለችበት ዬት አገር ሊሂድ ብላ ሚዳቆ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተፈተለከች። ከዚያም እያለከለከች በቃ አሁንስ አታገኚኝም ስትል አሁንም መሬት ብቅ ብላ እየጠበኩሽ ነውኮ ብድሬን ክፈይ እንጂ ስትል ጠንከር አድርጋ ጠየቀቻት። ሚዳቆዋም መሬት የሌለችበት ልትደረስ ስትበር ስትበር ሳንባዋ ፈንድቶ ሞተች”ይባላል።
የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንደ መሬት ናቸው። የትም ሂዱ፤ የትም ግቡ ይከተሏችኋል። መስጊድ ዉስጥ አሉ፤ ቤተክርስትያናት ውስጥ አሉ። ቤተመንግሰት ዉስጥም አሉ። የሌሉበት ቦታ የለም። መፍትሄው እንደ ሚዳቆዋ መሸሽ አይደለም። መፍትሄው ዜጎች የሚያነሷቸውን የፍትህ፤ የእኩልነ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አድምጦ ትክክለኛ መልስ መስጠትና ከዕዳ ነጻ መሆን ብቻ ነዉ ። ከዚህ ዉጭ ጥያቄን ላለመስማት ወይም ሰምቶ ለመደፍጠጥ የሚደረገው ከንቱ ሩጫ መጨረሻው እንደ ሚዳቆዋ መፈንዳት እንጂ ህይወት አይሆንላችሁም።
እኛ ግንቦት ሰባቶች ዘረኛዉንና አሸባሪውንና የወያኔ ስርዐት ለመደምሰስና ህዝብ በነፃነት ያለፍርሃት የሚኖርበትን አገር ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ከእንግዲህ የሚያቆመን ምንም ነገር የለም። የምንታገለዉ ለህዝብ ጥያቄያችንም ህዝባዊ ጥያቄ ነዉና እኛም አንደጥያቄዉ በየመስጊዱ፤ በየቤተክርሲቲያኑና በየሰፈሩ ዉስጥ አለን።እኛ የሌለንበት ስፍራ የለም። በዚህ አጋጣሚ የዘመናት ትግላችን ፍሬዉ የሚታይበት ቀን እጅግ በጣም ቅርብ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አገር ተረካቢ የሆነዉ ወጣቱ ትዉልድ እራሱን፤ ወገኖቹንና እናት አገሩን ለማዳን የሚደረገዉን የነጻነት ትግል እየመጣ እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን አቅርበናል። ኑ እና ተቀላቀሉን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወሰዱ


October 11, 2013
Update:
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡
***
ጉዳዩ እንደዚህ ነው መንግስት ነኝ ባዩ በስራው ግን ከማፍያ ቡድን እምብዛም የማይለየው ህወሀት/ኢህአዴግ በተለየም የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ አጠናክረው የቀጠሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ስጋት ውስጥ ጥሎታል።
“ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ይህን ህዝብ ውስጥ በፍጥነት እየሰረጸ የመጣውን እንቅስቃሴ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ለማዳከምና ብሎም ለማምከን ህወሀት/ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ስልት ቡድኑ ምን ያህል “የሞራል የበታችነት” እንደተላበሰ የሚያሳይ ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ የተከራየውን ጽህፈት ቤት ለመረከብ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም በቦታው ይገኛል። ይሁንና ቀድመው በቦታው የተገኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ሰዎች ቤቱን እኛ ቀደም ብለን የተከራየነው ስለሆነ የሚገባው ለኛ ነው በማለት ወዝግብ ያነሳሉ… እንግዲህ አንባብያን እራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራው ሀይል የሰፈር “ጢቦ” ሆኖ መጣ ማለት ነው…
ይህ በዚህ እንዳለ ነው አሁን በቅርቡ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን ኢንጅነር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችችን ወደ ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዷቸው።
የሰማያዊ ፓርቲ ሁኔታውን እንዲህ በማለት በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ ጠቅሶታል፣
የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር) 
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ) 
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል) 
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡