Tuesday, September 24, 2013

ኦሮማይ፣ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

September 21, 2013
ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)
ሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍም ያነሳሳኝ ይህ የወያኔ በቀቀኖች ልቅ ያጣ የፀረ ሻብያ ውትወታ ወያኔ የምትባለው የጠባብ ዘረኞች ቡድን ለዚህ ዛሬ ለደረሰችበት የዘረፋና የልዕልና ደረጃ የበቃችው ከቶ በማን ትከሻ ሆነና ነው ። ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ወደ ኤርትራ ስለሄዱ ይህ ሁሉ ውንጀላ ደጋፊ ተብዬቹ የሚነዙት ወያኔ በሻብያ ሁለገብ ድጋፍ የማቴሪያል የትጥቅ የዕቅድና የሃሳብ መመሪያ ውጪ እንኳን ሚኒሊክ ቤተመንግስት ልትደርስ ቀርቶ ተከዜንም ባልተሻገረች ነበር።በአንድ ወቅት የኤርትራው መከላከያ ሚንስትር ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ስለ ወያኔዎቹ ያለውን እጅግ የወረደ ንቀት የገለጸበትን አባባል እንዳስታውስ አሰገደደኝ ‘’እኛ ከነጀነራል ደምሴ ቡልቱና ከነጀነራል ረጋሳ ጅማ ጋር በመዋጋታችን ኩራት‘’ የሚሰማን በመሆኑ ከነዚህ የፍየል እረኛ ወያኔዎች ጋር ፈጽሞ ለንጽጽር የማይቀርቡ እጃቸውን ይዘን ለዚህ ያደረስናቸው እኛነን ሲል ነበር ከአመታት በፊት የተናገረው። ወያኔዎች በሻብያ የበላይ ሹማምንት ብቻ ሳይሆን በተራው ተጋደልቲ ጭምር የሚናቁና እንደ ሻብያ አገልጋይ የሚታዩ ስለመሆናቸው ከሁለት አስዕርተ አመታት በኋላ እንኳ አለመለወጡን በረባው ባረባውም በባነኑ ቁጥር የሻብያ ስም እንደሚያስበረግጋቸው ዘወትር ከአፋቸው አለመጥፋቱን የምናስተውለው ሲሆን የሰሞኑ ደግሞ ተባብሶ የሚታየው ጫጫታ አንዱ የወያኔዎች የፍርሃት ማሳያ ይመስለኛል።
የወያኔ መሪዎች የትግራይን ገበሬ ልጆች በግዴታ ለሻብያ አሰልፈው እያዘመቱ ፈንጅ ማምከኛና በማስደረግ የፈጸሙት የሎሌነት አሳፋሪ ገሃድ እየወጣ ባለበት በአሁኑ ወቅት አበው በቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ነው እንዲሉ እሱ ብቻ ሕልመኛ እሱ ብቻ ባለራዕይ የነበረውና በሞት ተለይቶ እንኳ ወሬው የገነነለት መለስ ዜናዊ እንዲህ ለራሱ የሚያሸረግድ አድርባይ የሎሌ መንጋ ትቶ እንደሄደ ትላንት እርሱም ለሻብያ ካድሬዎች ይንበረከክ እንደነበረ ታሪኩን የሚያውቁት ሲመሰክሩ ቆይተዋል በተለይም ወያኔዎች ከሻብያ ጫማ ስር ለመዋላቸው የሚቀርብባቸው ማስረጃ የኢትዮጽያን ተፈጥሯዊ የባህር በር አሣልፈው ከመስጠት አልፈው የኤርትራ ነጋዴዎች የጅማን ቡና የለገደንቢን ወርቅ ከማህል ሃገር በብር እየገዙ ለውጭ ገበያ በዶላር ያቀርቡ የነበረበትን ሁኔታ አንድ እግር ቡና የማታብቅለው ኤርትራ ከቡና ላኪ ሃገሮች ተርታ መሰለፍ እስክትደርስ ድረስ የተካሄደውን የወያኔ ተንበርካኪነት ስናስታውስ ሻብያ በአዲስ አበባው ኤንባሲ ውስጥ የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሬውን ሲያደራ እዚያው ኤንባሲ ውስጥ እስር ቤት አቋቁሞ የፈለገውን ሲያደርግ የነበረበት የጌታና የሎሌ ታሪክ የተዘነጋ ይመስል ወያኔና ጭፍሮቿ ሻብያን ቀንድና ጭራ ልትቀጥልልለት የምታደርገው መፍጨርጨር ተመልካች የማይታደምበት ተራ ኮሜዲ ከመሆኑም በላይ እውነተኞቹ የትግራይ ልጆች እንደ አስራት አብረሃምና እንደ ገብረመድህን አርዐያ ያሉት ይህንን የሚታወቅ ታሪክ በተባ ብዕራቸው ትውልድ እንዲያውቀው ከትበው ያስቀመጡት በመሆኑ ዝርዝር ሃተታ አያስፈልገውም ።
ዘረኝውና ዘራፊው የወያኔ ጥርቃሞ በእንዲህ ያለ የሻብያ የጭን ገረድነት የገለማ ታሪክ እያለው ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ከሻብያ ጋር ቢተባበሩ ከኢሳያስ ጋር ቢነጋገሩ ከቶ ሊቃወም የሚችልበት የሞራል መሠረት የሌለው መሆኑን ወናፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ ሊረዱ በተገባ ነበር። የኢትዮጽያ ልጆች በመረጡት አጀንዳ በመሰላቸው የትግል ስትራቴጂ ከማንኛውም ምድራዊ ሃይል ጋር የመነጋገር የመተባበር ሙሉ መብትና የተሟላ የሞራል የበላይነት ስላላቸው ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ደም በመምጠጥ ላይ ያለውን ዘራፊ ሌባና ሰውበላው ወያኔን ለማስወገድ ከሻብያ ጋር አይደለም ከሴጣንም ጋር ቢዋወሉ የሚያስመሰግን እንጂ ከቶም የሚያስወቅስ አለመሆኑን ማንም ሊያሰምርበት የሚገባው አብይ ነጥብ ሃገራችንና ሕዝባችን ከወያኔ የከፋ ምድራዊ ጠላት የለውምና ነው። ኢትዮጽያዊ ሃይሎች ከማንኛውም ወገን የሚደረግላቸውን የገንዘብ የማቴሪያልና የስልጠና እገዛ ሃገርና ወገንን ለመታደግ እስካዋሉት ድረስ ከማንም ጋር ቢተባበሩ ከቶም በታሪክ ሊያስወቅሳቸው የሚያስችል ባለመሆኑ በያዙት ጎዳና በልበሙሉነትና በወኔ ሊጓዙ በመቃተት ላይ ያለው የወገናቸው የሰቆቃ ድምጽ ግድ ይላቸዋል። ነገር ግን የሃገርን ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ ማናቸውም ውልና ስምምነት ውስጥ ቢገቡ ወያኔ ለሻብያ ቂጣ ጋጋሪና መንገድ መሪ በመሆን እንደፈጸመው የውርደት ታሪክ እነሱም እንዳይደግሙት ሊጠነቀቁና አካሄዳቸውን ከጊዜያዊ ፍላጎት አንጻር ሳይሆን ከዘላቂ ጥቅም አንጻር እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ባሻገር ወያኔን ለመደምሰስና ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በተቀናጀና ሁሉን ወገን ባሳተፈ መልኩ እንዲሆን ሠፊ የፖለቲካ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ስራ በስፋትና በጥራት እንዲካሄድ ከህዝቡና ከአጋር ወገኖች የሚገኝ ትግሉን በጥንካሬ ለመወጣት እንዲቻል የሚያግዝ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም በማፈላለጉ ላይ ያለይሉኝታ ሊንቀሳቀሱ ይገባል። እዚህ ላይ ባለፈው ሰሞን እንደትልቅ የሃገር ክህደት ወያኔዎችና አንዳንድ ህዝባችን የተጫነበት ድቅድቅ የዘረኝነትና የግፍ ጭለማ ያልታያቸውና የሃገራችን እጣፋንታ ያልገባቸው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ቅንጡ ፖለቲከኞች ሲያራግቡት የሰነበቱት የማጥላላት ዘመቻ ግንቦት 7 ከሻብያ ግማሽ ሚለዮን ብር የመቀበሉ ቱማታ በእኔ እምነት የሚያስወቅስ ሳይሆን የትግሉ እድገት አንድ ደረጃ እንደደረሰ ማሰያ በመሆኑ ከወያኔ ጋር ለሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የገንዘብም ሆን የቁሳቁስ ድጋፍ ከሻብያ አይደለም ከሠይጣንም ቢገኝ አመስግኖ መቀበል የሞራል ድጋፍ ያለው አካሄድ በመሆኑ አስፈላጊ አይደለም እንጂ የተገኘው ድጋፍ በአደባባይ ቢገለጽ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። በተለይ በተቃውሞው ጎራ ያለው ወገን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባው መሠረት በሌለው እንቶፈንቶ ለመነታረክ ግዜ ከማጥፋት ይልቅ በየራሳችን ይዝን የተነሳንውን አላማ ከግብ ለማድረስ መትጋት ላይ ትኩረት ማድረግ ቢቻል ወያኔ ይህን ያህል ችግር አትሆንብንም ነበር ። ስለሆነም ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነንን የሌሎችን እንቅስቃሴ ሂደቱን ባንደግፍ እንኳ ተቋዋሚ ልንሆንበት የሚያስችላን አንዳች የፖለቲካ አመክንዮ ስለሌለን በመተባበር በጋራ መቆም ባንቸል በመከባበር በየራሳችን መንገድ መጓዙ የመከራውን መንገድ የሚያሳጥር በመሆኑ ላይ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።
በኤርትራ በኩል የአመጽ ትግሉን እናካሂዳለን ብለው በድፍረት የቀረቡትን ወገኖች ስለቁርጠኝነታቸው አድናቆት መቸር ሲገባ አንዳንደ የዘረኛው ቡድን ተላላኪዎችና የመንደር ራድዮ ጣቢያዎች ጉዳዩን አጣመው ስላቀረቡት ብቻ ያን ይዞ የትችትና የስድብ ዘመቻ ማካሄድ ተገቢም ካለመሆኑም በላይ በእርስ በርስ ሽኩቻ የሕዝባችን መከራ እንዲራዘም ማድረግ ስለሚሆን ሁሉም ወገን ተገቢነት ባለውና ስልጡን በሆነና መቻቻልን ባሰላሰለ መንገድ ሁሉም የትግል ሃይሎች ቢቻል ጎን ለጎን ካልሆነም በመከባበር ግባቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ከጎንዮሽ መጠላለፍ እንዲታቀቡ የደጋፊው ህብረተሰብ አሰላለፍ ከስሜታዊነትና ከጠባብ የቡድን አመለካከት ባሻገር ሠፊውን አላማ ላይ ያነጣጠረ ብልህ አካሄድን ማቀናጀት ሁሉም አትራፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ሂሳብ በመሆኑ ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል። ከዚህ ባሻገር ካሮጌ ፖለቲካችን የወረስነው የስማበለው የባልቴቶች የአሉባልታ ተረት ተረት ይዞ መጓዝ የደረስንበት ዘመን የማይዋጀውና የንቃተ ህሊና ደረጃ ወደማይፈቅድበት የማሰብ አድማስ የሰፋበት ሁኔታ መከሰቱን በመረዳት በሎጅክና በትንተና ሃሳባችንን እስካላስረገጥን ድረስ አዲሱ ትውልድ የማይቀበለው ባለመሆኑ በተለይ እድሜ ጠገብ ፖለቲከኞቻችን ከዚህ አንጻር የትውልድና የአመለካከት መጠነሰፊ ሽግሽግ በግዜ ሂደት መከሰቱን አውቃችሁ በየአቅጣጫው እየተካሄደ ያለውን ትግል በጥራትና በግልጽ ለውይይት እንዲቀርብ በማድረግ በአመጽ ጎዳና እንዘምታለን የሚሉትን ሃይሎች በነጠረ ሂስና ግለሂስ ጥንካሬና ድክመታቸውን እንዲለዩ ህዝባችንም አቅጣጫውን እንዲያስተካክል የሚረዳ ተሳትፏችሁ በጥበብ የተሞላ መሆን ይኖርበታል። አለያ የኔብጤው ወኔና እውቀት አጠር ዲያስፖራ ሠልፍ እንኳ ለመውጣት በደረቅ በጋ ስካርቭ የሚደርብና አርቴፊሻል ጢም የሚቀጥል ፍርሃት ያራደው አውታታ ፤ የወያኔን አገዛዝ ለመደምሰስ ዱር እንገባለን የሚሉትን ሃይሎች መደዴ በሆነ ቋንቋ ሲዘልፍና የግለሰቦችን ስብዕና ሲዘልፍ ላስተዋል ምን ያህል ከሞራል አልባነት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ ምስኪን ወገን በመኖሩ እንዲህ አይነቱ የስድብ ሱሰኛ በምክር አይደለም በጸበልም የሚተወው ባለመሆኑ ለእንዲህ አይነቱ የአስተሳሰብ ድውይ ከማዘን በስተቀር ሌላ ሃይል ማበከን ተገቢ አይመስለኝም ።
አዲሱ ትውልድ ይጠይቃል በበቂ መልስለት ይከተልሃል፤ ይህ ነው መሬት ላይ ያለው ሃቅ ቅንጅት ሚሊዮኖችን ያነቃነቀው ሕዝባዊ አጀንዳና የሚታይ ራዕይ ስላስቀመጠ ነበር። በቅርቡ የተመሠረተው ሠማያዊ ፓርቲ በመሪዎቹ ቁርጠኝነትና ባቀረቡት ወቅታዊ አጀንዳ አንጻር ከስምንት አመታት በኋላ ታላቅ ህዝባዊ ሠልፍ በማድረግ የፈጠሩት መነቃቃት ፓርቲው ከተመሰረተ አጭር ግዜው ቢሆንም ያለው ተደማጭነቱ ከአንጋፋዎቹ ልቆ እንዲገኝና ተስፋ እነዲጣልበት ያደረገው የድርጅቱ መርሆ በሎጅክ የተቃኘና አላማውን ግልጽ በማድረጉ ይመስለኛል። ሕዝብ የሚከተለው ትውልዱ ለትግል የሚነሳው ወቅቱ ከፈጠረው አዲስ ሁኔታ አንጻር እንጂ በታሪክ ቡልኮ ተጀቡኖ በተረትና ሃሜት በሚነዳ የፖሮፓጋንዳ ዘመቻ አይደለም፤ ያ በስማ በለው በደመነፍስ ትውልድ ከሚነዳበት የስብስቴ አመለካከት ላያዳግምና ተመልሶ ላይመጣ በማስተዋልና በስልጣኔ እየተሻረ በመሄድ ላይ በመሆኑ ብዙዎች ያወሩለትን ጥቂቶች ጀምረው ያቆሙትን የአመጽ ትግል በአዲስ መልክ እናስቀጥላለን ብለው የተነሱትን ሃይሎች የማይደግፍበት ምክንያት ቢኖረው እንኳ ከመርህ አንጻር ሊቃወም የሚችልብት ምንም በቂና ውሃ የሚቋጥር አሳማኝ ምክንያት ባለመኖሩ ሂደቱን በጥንቃቄ ይከታተላል።
በዚህ የስልጣኔና የጥበብ ዘመን ላይ ቆመን ከቶስ ስል አመጽ ትግል ማንሳት ለምን አስፈለገ ጦርነት የሰውን ልጅ የሚበላ እሳት ነው። አመጽ ሃገር የሚያወድም መሠረተ ልማትን የሚንድ ኋላቀር መፍትሔ ነው፤ የሰላሙን ትግል ማበረታታት ሲገባ ለምን የአመጽ መንገድ እንደ መፍትሔ ይቀመጣል የሚሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው። እርግጥ ነው ዲያቢሎስ ካልሆነ በቀር ጦርነትን መልካም ነው የሚል አንዳችም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ፍጡር አለ ለማለት አይደፈርም። እንደምኞታችን ነገሮች በተቃውሞ ሠልፍና በሕዝባዊ እንቢተኝነት ቀለውልን ከላያችን የተጫነው ግፈኛ አገዛዝ አሽቀንጥረን ብንጥል መልካም ነበር። ይህ ግን ቀላል ሆኖ አልተገኘም የተከፈለውና በመከፈል ላይ ያለው መስዋዕትነት አንሶ አልነበረም አመጽ ታሳቢ የሆነው። ሃገራችንን የወረረው የወያኔ ቡድን ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለምን መሠረት ያደረገ ሣይሆን ፤ የዘር አመለካከትን ዶግማና ቀኖናው በማድረግ ኋላቀር አካሄዱንና፤ ኢ ዲሞክራሲያዊነቱን የተቃወመውን ወገን በሙሉ የሚመለከትበት ሸውራራ አተያይ ፀረ ትግራይ በሚል በመሆኑ ከእንዲህ አይነቱ ጠባብና ድኩማን አመለካከት ባለው ሃይል ከሚመራ ቡድን ጋር የሚደረግ ስልጡን የፖለቲካ ትግል ውጤቱ ፍሬ አልባ በመሆኑ ሊገዳደረው የሚችል የሃይል እንቅስቃሴ አማራጭነቱ ሁሉን ወገን ከተረዳው የከረመ ቢሆንም አለመታደል ሆኖ የትግሉን እንቅስቃሴ ማቀናበሪያ ወሳኝ ኮሪደር በማግኘት ዙሪያ ስንቸገርና ባለውም ጠባብ አማራጭ ለመጠቀም ሳንችል የቆየንባቸው ትርምስ የተሞላ ሰፊና ወርቃማ ግዜያቶች ባክነዋል።
አመጽ የጭቁኖች ድምጽ ነው ሲል የተናገረው ጠቢብ ማን ነበር ፤ አዎን አመጽ የሰውነት ክብርን ማረጋገጫ የነፃነት እስትንፋስ ማግኛ የባርነት ሰንሠለትን የሚበጥስ ጽኑ መዶሻ ነው። በሃገራችን የዛሬን አያድርገውና እንኳን ሃብትና ንብረቱ እየተቀማ ከነ ቤተሰቡ ጎዳና ሊጣል ቀርቶ ክፉ ቃል ተናግሮ ስብዕናውን የተዳፈረውን አደብ ሳያስገዛ የማይኖር ከምንም ነገር በላይ ለክብሩ ዘብ የሚቆም ማንነቱ ተዋርዶ በሞቀ ጎጆው ከመኖር ይልቅ ክብሩን ለማስመለስ ዱርቤቴ ማለትን የሚመርጥ ጀግና ሕዝብ እንደ እባብ ተሽሎክሉኮ በገባው የማንም መደዴና ቀን የሰጠው ወፍዘራሽ ዘረኛ የወያኔ መቀለጃ ሆኖ ለስደት ለሞት ለእስርና ለምድራዊ ስቃይ የተዳረገው መብቱን ለማስከበር አመጽን አማራጭ ባለማድረጉ መሆኑን እያየንው ነው።
ወያኔዎች በለስ ቀንቶዐቸው ድፍን ኢትዮጽያን ሲወሩ በየሄዱበት ያገኙትን አሮጌ አካፋና ቀደዳ በርሜል ሳይቀር እየጫኑ ወደትውልድ ስፍራቸው ሲያግዙ ከነበረበት ቅራቅንቦ ሰብሳቢነት እድሜ ለታላቋ ሃገራችን ዛሬ ይህው እኒያ ከገላቸው እድፍና ከጎፈሬያቸው ተባይ ውጪ የረባ ጃኬት እንኳ ያልነበራቸው ሽፍቶች ይህው ዛሬ ድፍን ሃገር በጠኔ እየተመታ በረሃብ አለንጋ በሚለበለብበት ልጆቹን በፈረቃ የሚቀልብበት የኑሮ ምስቅልቅል ውስጥ ወድቆ ልጆቹ በየትምህርት ቤቱ ደጃፍ ረሃብ አዙሮ እየጣላቸው ባለበት ሁኔታ ላይ የወያኔው አባላት ጉቶ እየሞቁ ድብዳብ ላይ ተወልደው እዛው አጎዛ ላይ እንዳላደጉ ይህው የህዝብን ሃብት በመዝረፍ በህንጻ ላይ ህንጻ በሃብት ላይ ሃብት እያከማቹ ከራሳቸው አልፈው በድብቅ ላስቀመጧቸው እቁባቶቻቸው ወርቅና አልማዝ መኪናና ቪላ ስጦታ የሚያቀርቡበት ታጋይ ከበርቴዎችና ልማታዊ ዘራፊዎች ሕገ ወጥ ብልጽግና አካብተው ቅንጦት የሚያደርጋቸውን ባሰጣበት በዚህ ወቅት ትውልዱ ኑሮ ዳገት ሆኖበት የከፋውን ስደት ተያይዞት የሲናይ በርሃ አሸዋ ሲሳይ የቀይባህር አሳ ቀለብ እየሆነ እንደወጣ የቀረው የእምዬ ኢትዮጽያ ልጅ የሚደርስበት ሰቆቃ ዓለምን እስኪሰለች ድረስ የተለመደ የሰርክ ተግባር በመሰለበት በዚህ ዘመን ፤ በሃገር ውስጥ ያለው በገፍ በሚቀርብለት ጫት ደንዝዞ በምዕራቡ ዋልጌ ባህል ነፍዞ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች በሆነ የሞራልና የተስፋ መቁረጥ ጭለማ ተውጦ የትግሬው ነጻ አውጪ አባላት ልጆች ከህዝብ በሚዘረፍ ገንዘብ በአውሮፓና በኣሜሪካ ውድ ኮሌጆች እንዲማሩ እየተደረገ ባለበት የፋሽስት አገዛዝ ውስጥ የአንድ አናሳ ብሄር ሰዎች ተጨፍልቆ እየቃተተ በስቃይ በሚኖርበት ሁኔታ ውስጥ ህዝባችን ቢያምጽ ይነሰው በእውነቱ ይህ ትውልድ እነዚህን የቀን ጅብ ወያኔዎች ለመታገል ከሰይጣንስ ጋር ቢተባበር ከቶ ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?
ተወልደው ካደጉበት ጎጆ ቀልሰው ትዳር ይዘው ጫካ መንጥረውና ከአውሬ ታግለው ከባዱን የኑሮ ዳገት በላብ በወዛቸው አቅልለው በሰላም ሃገሬ መንደሬ ብለው የእርሻን ጥበብ የአኗኗር ዘይቤን ሃይማኖትንና ግብረገብነትን በየሄዱበት አስተምረው በቋንቋና በባህል የተለያቸውብ ወገን የራሳቸው አድርገው ተዛምደውና ተጋብተው በሰላም ለዘመናት ከኖሩበት ቅዬ ሃገራችሁ አይደለም በሚል ያፈሩትን ሃብት ነጥቆ ተማሪዎች ከትምህርታቸው በግድ እንዲፈናቀሉ በማድረግ በክፋትና ቂም በቀል አንድን ህዝብ ለማጥፋት የሚያደባውን እርጉሙን የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ይህ ሕዝብ መፋለም ይነሰው በጉራፈርዳ በቤኒሻንጉል በአፋርና በጋንቤላ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች የተፈጸመው የዘር ማጥፋትና ሁን ብሎ በድህነት የመቅጣት ወያኔያዊ ሴራ በእውነቱ ከወንጀልም ወንጀል ከሃጢያትም ሃጢያት የሚሆነው ይህንን ሳጥናዔላዊ ቡድን አለመታገል ብቻ ነው።
ነብሳቸውን ይማረውና አያቴ ‘’ ጣሊያን ምን አጠፋ በከንቱ ኩነኔ ሃገሩን አጠፉት መለስና ላይኔ’’ ብለው ነበር ያኔ ገና ወያኔ ሃገር ስትወር ፋሽስት ጣሊያን ያልፈጸመውን ግፍ ኦርቶዶክስና አማራ የሚባል ተቋምና ህዝብን ለማጥፋት እቅድ ነድፎ መርዝ አዘጋጅቶ የመጣን አርዮሳዊ ሃይል ለሺህ ዘመናት የውጪና የውስጥ ሃይሎችን በጽናት በመመከት ህልውናዋን አስጠብቃ የኖረችውን የታሪክ ማህደሯን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንድትከፋፈል የዘረኞች ምሽግ በመሆን ሃዋርያዊ ሃላፊነቷን ዘንግታ የጥፋት አላማው ማራመጃ ለማድረግ በመለመላቸው ጥቅመኛና ዘረኛ ጻጻሳትና ፓትርያርክ ተብዬ በማዘጋጀት በቤተክርስቲያኒቱና በምዕመኑ ላይ ሲደርሰ የቆየው በደልና ግፍ በቀላሉ ተዘርዝሮ አያልቅም። ወያኔ በቤተክርሰቲያኒቱ ላይ ያለውን ጥላቻ በማስፋፋት ይደረጋል ተብሎ አይደለም ሊታሰብ እነኳ የማይሞከረውን ታላቁን የዋልድባ ገዳም ለስኳር ልማት በሚል በገዳሙና በመናኝ ባህታውያኑ ላይ የተፈጸመው ግፍ ስንቃኝ የውጭ ወራሪ ሃይል ይህን ያህል ይዳፈራልን? ታዲያስ ይህ ጉግማንጉግ ፀረ ኦርቶዶክስ የሆነ የወያኔ መንጋ ከቶስ ከሰይጣን የሚለየው በምንድን ነው? ይህንን ወንጀለኛና መንጋ ዘረኛ ይወገድ ዘንድ የዚህች ታላቅ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን አድዋ ላይ ጌቶቹ ጣሊያኖችን በጸሎትና በሰይፍ እንዳሸነፈ በዚህም ሃገር በቀል የፋሽስት ሎሌን ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል በውግዘትም በሞራልም ማገዝ ለቤተክርስቲያኗ ሰላም መረጋገጥን ለምዕመኖቿ መረጋጋትን የሚያስገኝ ትርጉም ያለው መልካም ሁኔታ ሊገኝ የሚችለው ይህ የዘረኛ መንጋ ተጠራርጎ ሲወገድ ብቻ በመሆኑ ይህንን ትግል ማገዝ የቤተክርስቲያኒቱና የምዕመናኑ መንፍሳዊ ግዴታ ጭምር ነው።
የሃይማኖት ተቋማትን ማጥፋት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር እኩይና ሠይጣናዊ አላማ ሌላው ያነጣጠረበት የኢትዮጽያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከአመታት በፊት ይህው ከፋፋይ ዘረኛ የወያኔ ቡድን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የስልጣኑ ማደላደያ በማድረግ ከጎኑ ለማሰለፍ የሞከረበት እኩይ አላማው ከቅርብ አመታት ወዲህ ከታወቀ በኋላ መላው ሙስሊም በአንድ ድምጽ ያቀረበውን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ በሃይለ ለመጨፍለቅ ከምዕመኑ ጋር ያደረገው ትንቅንቅ የሙስሊም ወንድሞቻችን ዓለምን ያስደመመ እጅግ ዘመናዊና ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ጨዋነትን ምንም ያህል መርሐቸው ቢያደርጉም የወያኔ ቡድን ሠላማዊ ቋንቋ የሚገባው ባለመሆኑ ለሠላት የወጣውን የሙስሊም ማህበረሰብ ህጻን ከአዋቂ ሣይመርጥ በተለያዩ ቦታዎች የፈጸመውን ጅምላ ፍጅት የምታስታውስ ሙስሊም ወገን ይህንን የደደቢት ጭራቅ ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በመንፈሳዊ ቡራኬም ሆነ በቀጥተኛ ተሳትፎ
ክንድህን ሠብስበህ እንዳትታገለው ከቶስ የሚያግድህ ምንድነው? እየተጨቆኑ መኖር ለሃገርህና ለእምነትህ ታግለህ በክብር ማለፍ ነው።
ለማጠቃለል ኢትዮጽያ እንደሃገር ትቀጥል ዘንድ ትውልዷም ተሰዶ ከማለቁ በፊት ይህን ሃገር አፍራሽና መንጋ ቅጥረኛ ከቅድስት ሃገራችን ለማስወገድ እየተካሄደ ያለውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ዘር ሃይማኖት ሳንለይ በጋራ ቆመን በጽናትና በብርታት የመደገፍ የማበረታታት የማገዝ ታሪካዊም ሞራላዊም ሆነ መንፈሳዊ ግዴታ አለብን። በትግል አለም መውደቅ መነሳት ያለና የነበረ በመሆኑ ትላንት በሄድንባቸው መንገዶች ውጤት ባናገኝም ስልታችንን በማስተካከል ጥበብ በተሞላበትና ቁርጠኝነት ባለው መልኩ እንጓዝ ዘንድ መሪ ሃይል ሆናችሁ የወጣችሁ ሃይሎች በየትኛውም የትግል ስልትና ያላችሁ ያለ የሌለ ሃይላችሁን በማስተባበር የወያኔን ተፍጻሜተ መንግስት ለማቅረብ የሚረዳ አመራር በመቀየስ ታግላችሁ እንድታታግሉን ግዜው ግድ ይላችኋል።
ታላቁ ደራሲ ኦሮማይ በሚለው መጽሃፉ የሳላቸው የገሃዱ ታሪካችን አካል የነበረው ቀይ እንቡጥ የተባለው በለጋ ወጣቶች የተመራው የሃገር ፍቅር ሰራዊት ውጤቱ የማታ ማታ ቢበላሽም በለጋ እድሜያቸው በቆራጥነትና በጀግንነት አንድ ስትራቴጂክ ተራራ ለማስለቀቅ የከፈሉት ወደር የሌለው መስዋዕትነት ይህ ትውልድ ዞር ብሎ በማሰብ ነፃነቱን ረግጠው በሃገሩ ባይተዋር ባደረጉትና ሃገራዊ ድርሻውን ነጥቀው ባቋቋሙት የንግድ ኢንፓየር እነሱ በቁንጣን ሲወጠሩ የሃገሬ ወጣት ከረሃብ ጋር ሲታገል በየድልድይ ስር የሚያድርበት የአፓርታይድ አገዛዝ እንዲያከትም መፍትሄው ያለው በአዲሱ ትውልድ መዳፍ ውስጥ በመሆኑ ያአህዛብ አሽከርና የችጋር ጓደኛ ሆኖ ተሰቃይቶ ከመሞት ታሪክ ሰርቶ ለታሪክም ለህሊናም የሚጠቅም በጎ ተግባር ፈጽሞ ለመገኘት በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ የሚደረገው ትግል በማገዝ ህዝባችንን ልንታደግ ሃገራችንን ልንጠብቅና ሃይማኖታችንን አስከብረን በነጻነት እንድንኖር ወያኔን ለማስወገድ የሚካሄደውን ሁለገብ ትግል በትጥቅ ይሁን በሰላም ከኤርትራ ይሁን ከሱዳን ከሱማሌ ይሁን ከጅቡቲ በሚነሳ የአመጽ ሃይል ይሁን በሕዝባዊ ንቅናቄ ሁሉን ባለን አቅምና ጉልበት ልናግዝ ታሪክ ትውልድ ሞራልና መንፈሳዊ ሕይወታችን ግድ ይለናል። በጽናትና በጋራ ቆመን ጠላቶቻችንን ለመደምሰስ እግዚያብሄር ሃይልና ብርታት ይሁነን።
ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር!!!

Tuesday, September 17, 2013

የመስከረም 12 ሰልፍ በታቀደለት ጊዜ ይካሔዳል (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማገለጫ)

September 16, 2013
.
የመስከረም 12 ሰልፍ በታቀደለት ጊዜ ይካሔዳል!!!!!
ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች ህገ ወጥ እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ነሐሴ 3ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው መስከረም 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል እንዲያውቀዉ አድርጓል፡፡ ይህንን ተከትሎ የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል ጳጉሜ 1 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የሰለፉን ዓላማ፣ የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመርና የሰልፉ መዳረሻ ከግንባታ ስራና ከፀጥታ ጥበቃ ጋር ያለውን ችግር አስመልክቶ ማብራሪያ እንደሚያስፈልግ በጠየቀዉ መሠረት፡-Blue Party Ethiopia
1ኛ. የሰልፉ ዓላማ፤
በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር፣ዜጐች በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር፣ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11፡3 በግልፅ የተደነገገው መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ኃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው ድንጋጌ እንዲከበር፣ መንግሥት የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚሉትን ጥያቄዎች በሰላማዊ ሠልፍ መንግሥትን ለመጠየቅ መሆኑን፤
2ኛ. የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመር
መነሻው ከፓርቲው ጽ/ቤት ግንፍሌ አካባቢ ተነስቶ በአራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል በኩል በአሮጌው ቄራ በአምባሳደር ቴአትር አልፎ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ በዚህ መንገድ ላይ ምንም ዓይነት የግንባታ ሥራ የሌለበትና ሠልፉ የሚደረገውም እሁድ ከጥዋቱ 3፡ዐዐ-7፡00 ሰዓት ባለው የእረፍት ቀን በመሆኑ በዕለቱ ምንም ዓይነት የመንግሥት ሥራና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበትና መድረሻ ቦታችንም መስቀል አደባባይ ከቅርብ ቀናት በፊት በኃይማኖት ተቋማት አስተባባሪነት ሠልፍ የተደረገበት መሆኑና ወደፊትም መስከረም 12 ቀን ከሚደረገው ሠልፍ አንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሁሉም ማዕዘናት በሚመጡ ምዕመናን የመስቀል በዓል የሚከበርበት ቦታ መሆኑን ጳጉሜ 04 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፍነው ደብዳቤ አብራርተናል፡፡
የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1987 አንቀፅ 6 ቁጥር 2 “የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጁ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱትን በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ስፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያት ካለው ምክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ምንጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሔድ አይችልም ማለት አይችልም” በሚለው መሰረት የእዉቅና ጥያቄ የቀረበለት አካል በፅሁፍ በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ ቢኖርበትም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡
ፓርቲያችን በሕግ የሚጠበቅበትን ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ በሰልፉ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፉን በመቆጣጠርና የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያውክን ሁኔታ በማስወገድ የሰላማዊ ሰልፈኞች መብቶችን ለመጠበቅ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች በአዋጁ ቁጥር 3/1987 የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውኑ እናሳስባለን፡፡
መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
Blue Party

Wednesday, September 11, 2013

በበዓል ቀን የርሃብ አድማ – ርዕዮት ምን ልትነግረን ነው? September 11, 2013

በብሄራዊ በዓላት ቀን በአብዛኛው ከወደ እስር ቤት የሚሰማው ዜና አስደሳች ነበር፡፡ይህንን አጼዎቹ ፣ሰው በላው የደርግ ስርዓትና ብሶት ወለደኝ ያለን ኢህአዴግ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ በዘንድሮው አዲስ አመትም የመንግስትን ይቅርታ በማግኘት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል፡፡በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተቸራቸው እስረኞች መካከል ታዋቂ ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች አለመኖራቸው ተፈቺዎቹ በደረቅ ወንጀል ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ለመናገር ብዙ መድከም አይጠይቅም፡፡
መንገስት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ሂሩት ክፍሌና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር አቅርበውት ለነበረ የይቅርታ አቤቱታ የእምቢታ ምላሽ መስጠቱም ይቅርታ የሚገባውና የማይገባው በመንግስት ማውጫ ውስጥ ስለ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡የይቅርታው ጉዳይ ለጊዜው ይዘግይልንና በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ በበዓል ቀን ስለ ተፈጸመ ግፍ ላካፍላችሁ፡፡ ጋዜጠኛዋን በበዓሉ ዋዜማ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡በመጠየቂያ ሰዓት መድረስ የቻልን ቢሆንም ጥበቃዎቹ
‹‹ርዕዮት የምትጠየቀው በዋናው በር ሆኗል፡፡ስለዚህ ወደ ዋናው በር ሂዱ››
አሉን፡፡ዋናው በር ፈጣን ተራማጅ በ10 ደቂቃ የሚደርስበት በመሆኑ ሰዓቱ እንዳይረፍድና እንዳንከለከል በማለት መሮጥ ጀመርን፡፡
ዋናው በር ግብረ ገብነት አልያም ፖሊሳዊ ስነ ምግባር በዞረበት ለሰላምታ እንኳ አግኝቷቸው የማያውቁ የሚመስሉ ጠባቂዎች
‹‹በዚህ በኩል እስረኛ አይጠየቅም ሂዱ ››
አሉን፡፡ ግትር ብለን በዚህ በኩል ግቡ ተብለናል አልን፡፡ሰዓቱ እየሄደ ፖሊሶቹም በአቋማችን የበለጠ በመበሳጨት እየዛቱ ነው ፡፡በመካከሉ የርዕዮት ታናሽ እህት እስከዳር አለሙና እጮኛዋ ስለሺ ሀጎስ ከግቢው ውስጥ እየተጣደፉ ወጡ፡፡ ስለሺ አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወናጨፈ ብቻውን ያወራል፣እስከዳርን በሙሉ አይን ማየት ያስፈራል፡፡ ፊቷ በርበሬ መስሎ በእንባ ጎርፍ እየታጠበች ነው፡፡አብሮኝ የነበረው ሰውና እኔ ለመግባት እናደርግ የነበረውን ትንቅንቅ በመተው ሁለቱን ለማጽናናት እና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ መወትወቱን ተያያዝነው፡፡
ርዕዮት ቤተሰቦቿን እንዳገኘች
‹‹ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፣ችግር ውስጥ ነኝ››
ትላቸዋለች፡፡በዚህ ወቅት በዙሪያዋ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ጋዜጠኛዋ ላይ በመጮህ
‹‹ስለ ራስሽ ብቻ አውሪ››
ይሏታል፡፡
‹‹የነገረችን እኮ ስለ ራሷ ነው››
የእስከዳር ምላሽ ነበር፡፡ በዚህ መሃል በጊዜያዊነት የሴቶች ዞን ሃላፊ የሆነች ፖሊስ
‹‹እናንተ አቅማችሁ ጋዜጣ ላይ ነው ከፈለጋችሁ ሂዱና እንዳንጠይቃት ተከለከልን በሉ፡፡››
በማለት በዚህ ቦታ ለመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚያቅበንን የስድብ መዓት በስለሺ ፣በርዕዮትና በእህቷ ላይ ታወርዳለች፡፡
ርዕዮት ሁኔታውን መቋቋም ተስኗት ሃላፊዋን ለምን እንዲህ አይነት በደል እንደምትፈጽምባት ለመጠየቅ ስትሞክር እየገፈታተሩ ወደ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ እነ ስለሺን ግቢውን እንዲለቁ ያደርጋሉ፡፡
በንጋታው መስከረም 1/2006 ነው፡፡የመንግስት ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የቴሌቭዥኑን መስኮት በአዲስ አመት ቀና መልዕክት አጨናንቀውታል፡፡አዲስ ቀን አዲስ ገጠመኝ እንደሚፈጥር ተስፋ ያደረጉት የርዕዮት ቤተሰቦች ከቃሊቲ አልቀሩም፡፡ነገር ግን የሰሙት ነገር በቀኑ እንጂ በአስተዳደሩ መካከል ለውጥ ወይም ዕድሳት አለመኖሩን ነው፡፡ለካ የአዲስ አመት በጎ መልእክት የሚያስተላልፉልን መሪዎቻችን ያሉት
‹‹በድሮው ቀን ነው፡፡››
ርዕዮትን እንዲጠይቁ የተፈቀደላቸው
‹እናቷ፣አባቷና የነፍስ አባቷ ብቻ ናቸው››
እነ ስለሺ ከቃሊቲ ሃላፊዎች ዛሬ ያደመጡት መንፈስ ሰባሪ ቃል ነው፡፡ የህግ ባለሞያው አቶ አለሙ ጌቤቦ ድርጊቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ ቃሊቲ ደርሰው ልጃቸውን ሳይጠይቁ ተመልሰዋል፡፡ወላጅ እናቷ ያመጡትን ምግብ ለማስገባት ቢሞክሩም ርዕዮት በቃሊቲ የሴቶች ዞን ጊዜያዊ ሃላፊ እየደረሰባት የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወም የርሃብ አድማ በመጀመሯ እናት ያመጡትን ምግብ የሚቀበላቸው አላገኙም፡፡
ወዳጄ ስንቶቻችን ነን አዲሱ ዓመት በጾም ቀን ዋለ ብለን የተከፋን?ይህው እንግዲህ በዓሉን ርዕዮት በርሃብ አሳልፋዋለች፡፡
የርዕዮት የርሃብ አድማ መልእክቱ ግልጽ ነው፡፡አቅም ያላት በራሷ ላይ በመሆኑ ራሷን በመቅጣት ህገ ወጦችን እምቢ አለቻቸው በዚህ ሰላማዊውን ታጋይ ማህተመ ጋንዲን መሰለችው፡፡ሰዎቹ እየበሉ በርሷ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየተራበች በምታስተላልፈው መልእክት የህሊና ርሃብተኞች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡
ከቃሊቲ ውጪ ያለንም ምግብ ወደ አፋችን ባስጠጋን ቁጥር ርዕዮት የቃሊቲ አጥር ሳይበግራት ትመጣብናለች፡፡በምግብ ብቻ በማይኖርባት አለም በምግብ ብቻ ለመኖር ለምናደርገው ከንቱ ሩጫም ርሃቧ ትልቅ ደወል ይሆንብናል፡፡ 1185860_10200561003368447_1105290103_n

Friday, September 6, 2013

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል! SHAREBAR አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል! በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ ህዝቡ የትግሉ መሪ ተዋናይና ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ላለፉት ሶስት ወራት ፓርቲያችን ባስቀመጠው ስትራቴጂ እቅድ መሠረት ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ ቆይቱዋል፡፡ በሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማለትም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረገጥ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል ሰኔ 13ቀን 2005 በይፋ ለጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ሕዝባዊ ንቅናቄው በእቅድ መመራት ከመጀመሩ በፊት ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የህዝባችን ተጨባጭ ኑሮ ላይ ጥናት በማድረግ የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረቡ የፓርቲያችን አብይ ጥያቄ ሆኖ መገኘቱም የንቅናቄውን ወቅታዊነት ያገናዘበ አድርጎታል፡፡ በእቅዳችን መሰረት በመላው ሃገሪቱ ለመጀመሪያው ዙር በተመረጡ ቦታዎች ያደረግናቸው ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአባሎቻችን፤ በደጋፊዎቻችንና በህዝባችን ጠንካራ ትግልና መስዋእትነት ንቅናቄው የተሳካ ሲሆን ፓርቲያችን ለተከፈለው ዋጋ ሁሉ አድናቆቱን ይገልፃል፡፡ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመታገዝ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ ከህግና ሥርዓት ውጪ ማስፈራራት፤ ማሸማቀቅ፤እስራትና ድብደባ በአባሎቻችን ላይ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የቅስቀሳ ቁሳቁስም በአካባቢ የፀጥታ ሰራተኞች ተዘርፈውብናል፡፡ እንዲሁም ህዝብ በነፃ አስተሳሰብ አማራጩን እንዳይከተል በአካባቢ ካድሬዎችና አመራሮች ማስፈራራትና ዛቻ ደርሶበታል፡፡ መርሃ ግብሩም ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን ህዝባዊ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ዜጎቻችን በመኖሪያ ቀያቸው ሰርቶ የማደርና በነፃነት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡ በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዘብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ ከህግ ውጭ የገጠሙን መንግስታዊ ተፅእኖዎች ሁሉ ነፃነቱን በተነፈገውና በለውጥ ፈላጊው ህዘባችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተልኮአችን ሊሳካ ችልዋል፡፡ የሚሊዮኖችን ድምፅ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎቻችን በንቃትና በቁጭት የተሳተፍበት በመሆኑ አመርቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ካደረግናቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ልዩ የሚያደርገው የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት መሆኑ ነው፡፡ በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ እስካሁን ካወጣቸው አፋኝ ህጎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠናክሮ የመጣውን ህዝባዊ የፖለቲካ ተቃውሞ የበለጠ ለመደፍጠጥ አሳሪ ደንቦች ለማውጣት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳቀሰ ለመሆኑ ከገጠመን መልካም አስተዳደር እጦት መገንዘብ ችለናል፡፡ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የነፃነት ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች ነሐሴ 30 ቀን 2005 አዲስ አበባ

                                                አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ ህዝቡ የትግሉ መሪ ተዋናይና ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ላለፉት ሶስት ወራት ፓርቲያችን ባስቀመጠው ስትራቴጂ እቅድ መሠረት ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ ቆይቱዋል፡፡
በሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማለትም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረገጥ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል ሰኔ 13ቀን 2005 በይፋ ለጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ሕዝባዊ ንቅናቄው በእቅድ መመራት ከመጀመሩ በፊት ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የህዝባችን ተጨባጭ ኑሮ ላይ ጥናት በማድረግ የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረቡ የፓርቲያችን አብይ ጥያቄ ሆኖ መገኘቱም የንቅናቄውን ወቅታዊነት ያገናዘበ አድርጎታል፡፡
በእቅዳችን መሰረት በመላው ሃገሪቱ ለመጀመሪያው ዙር በተመረጡ ቦታዎች ያደረግናቸው ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአባሎቻችን፤ በደጋፊዎቻችንና በህዝባችን ጠንካራ ትግልና መስዋእትነት ንቅናቄው የተሳካ ሲሆን ፓርቲያችን ለተከፈለው ዋጋ ሁሉ አድናቆቱን ይገልፃል፡፡
በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመታገዝ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ ከህግና ሥርዓት ውጪ ማስፈራራት፤ ማሸማቀቅ፤እስራትና ድብደባ በአባሎቻችን ላይ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የቅስቀሳ ቁሳቁስም በአካባቢ የፀጥታ ሰራተኞች ተዘርፈውብናል፡፡ እንዲሁም ህዝብ በነፃ አስተሳሰብ አማራጩን እንዳይከተል በአካባቢ ካድሬዎችና አመራሮች ማስፈራራትና ዛቻ ደርሶበታል፡፡ መርሃ ግብሩም ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን ህዝባዊ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ዜጎቻችን በመኖሪያ ቀያቸው ሰርቶ የማደርና በነፃነት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡
በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዘብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ ከህግ ውጭ የገጠሙን መንግስታዊ ተፅእኖዎች ሁሉ ነፃነቱን በተነፈገውና በለውጥ ፈላጊው ህዘባችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተልኮአችን ሊሳካ ችልዋል፡፡
የሚሊዮኖችን ድምፅ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎቻችን በንቃትና በቁጭት የተሳተፍበት በመሆኑ አመርቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ካደረግናቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ልዩ የሚያደርገው የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት መሆኑ ነው፡፡
በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ እስካሁን ካወጣቸው አፋኝ ህጎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠናክሮ የመጣውን ህዝባዊ የፖለቲካ ተቃውሞ የበለጠ ለመደፍጠጥ አሳሪ ደንቦች ለማውጣት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳቀሰ ለመሆኑ ከገጠመን መልካም አስተዳደር እጦት መገንዘብ ችለናል፡፡
የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የነፃነት ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
            “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”
የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች
ነሐሴ 30 ቀን 2005
አዲስ አበባ

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!

September 6, 2013

የወጣት አመራሮቹን ሰላማዊ የትግል መስመር ይደግፋል!

ያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡Ethiopian news
በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ከደበደቡና ካሰቃዩ በኋላ ለሰዓታት አስረዋቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ከተፈቱ በኋላ ለእሁዱ ስብሰባ ተመልሰው ዝግጅት እንዳያደርጉ የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪዎች የፓርቲዉን ጽ/ቤት እስከ እሁድ ድረስ በመቆጣጠር ኮምፒውተሮችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ ሠንደቅዓላማዎችን፣ መፈክሮችን፣ … በማውደም፤ የሚፈልጉት በመውሰድ ሰልፉ እንዳይካሄድ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመሰክር ከበቂ በላይ የፎቶግራፍ፣ የሰው፣ … ማስረጃ ቢኖርም ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉንም በመካድ ለዓለምአቀፍ ሚዲያ አንዳች ነገር እንዳልተደረገ በመናገር የተለመደውን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ደግሟል፡፡
ጥያቄው ግን ሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ያሉ ቁርጠኛ ወጣቶች ያነሱት ይህ የመብት ጥያቄ ለምን ህወሃት/ኢህአዴግን ለምን አሸበረው? ለምንስ እንዲህ ያለውን ራሱን የሚያጋልጥ ተግባር እንዲፈጽም አደረገው? መልሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ልምድ በሌለውና በማያውቅበት የሰላማዊ ትግል ጠንክረው ስለመጡበት ብቻ ነው! ለዚህ ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል በጽናት መብታቸውን ለማስከበር የሚታገሉት ሙስሊም ወገኖቻችንና ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡
ህወሃት/ኢህዴግ ባስቀመጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ ለእሁዱ ሰልፍ ከሁለት ወር በፊት ደብዳቤ አስገብቶ ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሰሞን ህወሃት/ኢህአዴግ ባቀናበረው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “አሸባሪነትንና አክራሪነትን” ለማውገዝ ሕዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ በጥሪ ብቻ ያላበቃው ዘመቻ የከተማው ነዋሪ በግድ፣ በማስፈራራት፣ በጉቦ፣ … ሰልፍ እንዲወጣ የተቀናበረም ነበር፡፡ ይህ ሰልፍ በሚካሄድበት ቀን ታቅዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ትዕይንተሕዝብ ካልተጨናገፈ በስተቀር ህወሃት/ኢህአዴግ በጠራው በራሱ ሰልፍ ላይ የሚደርስበት ክስረት መራራ እንደሚሆን ግልጽ ነበር፡፡
ከሰልፉ ጥሪ በፊት በተካሄደው ጉባዔ ወቅት “በኢትዮጵያ ህዳሴ የሃይማኖቶች ተስማምቶ መኖር” አስፈላጊነት የተሰበከ ሲሆን ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በወቅቱ “የሃይማኖት አክራሪነትን” እንዲያጋልጡ ተሰብሳቢዎቹን በመጠየቅ መንግሥት በዚህ ዙሪያ የሚወስደውን እርምጃ አንደሚቀጥልበት አስጠንቅቀው ነበር፡፡ ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈጸመው ተግባር አሸባሪና አክራሪ ራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑን ያጋለጠበት ነው፡፡
የሃይማኖት ተቋማት ጉዳይ ያገባኛል በማለት ጉባዔ የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግባ፤ የራሳችንን መሪዎች እንምረጥ፣ መብታችን ይከበር” በማለት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል እየጮሁ ያሉትን ሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ መመለስ ያልፈለገ ወይም ያልቻለ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የራሱን ካድሬዎች በሃይማኖት መሪነት ሽፋን በመሾምና ሙስሊሙን ኅብረተሰብ በመከፋፈል የአፈናና የመብት ረገጣ ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡ ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር በሌሎች ሃይማኖቶችም የቀጠለ ለመሆኑ በሃይማኖት ተቋማት ስም የተጠራው ጉባዔና ሰልፍ በቂ ምስክር ነው፡፡
ህወሃት ገና ከጥንስሱ የሃይማኖት ጉዳይ የማይስበው፤ በበረሃው ቆይታ በተደጋጋሚ በአሸባሪነት ተግባር ላይ ለመሠማራቱ የተመሰከረለት መሆኑ፤ ራሱን በፈጣሪ የለሽ የሌኒኒስታዊ ፍልስፍና ያጠመቀ መሆኑ ራሱ የመሰከረውና በግልጽ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ አሁን “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉዳይ ያገባኛል፤ የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ” ማለቱ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ የአህያ ቁርበት አንጥፉልኝ ያለው ዓይነት ነው፡፡
በአመሠራረቱ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ካሉት “የድምጻችን ይሰማ” ሙስሊም ወገኖች፣ የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ፣ የሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ወገኖች ጋር ያለውን ኅብረት ይገልጻል፡፡ የጋራ ንቅናቄው ባለው ዓለምአቀፋዊ ዕውቅናና ግንኙነት በመጠቀምም የህወሃት/ኢህአዴግን ቋት ለሚሞሉት ለለጋሽ አገራት፣ ለሕግ ተቋማት፣ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሚዲያ ተቋማት፣ ወዘተ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የመብት ረገጣ ያሳውቃል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ እስካሁን የፈጸመውን የሽብር ተግባርና ወደፊት ለሚያደርሰው ማንኛውም በደል በቀጥታ ተጠያቂ እንዲሆን መረጃው በሕግ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
በአገራችን በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሟቹ ጠ/ሚ/ር ቀጥተኛ ትዕዛዝ ህወሃት/ኢህአዴግ የፈጸመው የ193 ዜጎች ግድያ፣ የፖለቲካ መሪዎች እስር፣ አፈና፣ የመብት ረገጣ፣ … ያስከተለውን ፍርሃት ለመጀመሪያ ጊዜ በመግፈፍ የፖለቲካ ትዕይንተሕዝብ ያደረገው የሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ “ድምጻችን ይሰማ” የሚያደርጉት በትክክለኛ የሰላማዊ ትግል መርህ ላይ የተመሠረተው እልህ አስጨራሽና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ትግል እንዳለ ሆኖ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር አብሮ ተጠቃሽ ነው፡፡
አርቆአሳቢና ራሳቸውን በሰላማዊ ትግል ዲሲፒሊን ያነጹ ወጣቶች ተሰባስበው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰላማዊ ትግል በትክክለኛው መንገድ ከተከናወነ በኢትዮጵያ እንደሚሠራ በተግባር ያስመሰከረ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን “ሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር አይሠራም” የሚለውን ስሜታዊ አስተሳሰብ ከሥሩ የመታ ትግል በመሆኑ የጋራ ንቅናቄው ለሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችንና አመራሮች ከፍ ያለውን አድናቆት ይሰጣል፡፡ በተለይም በሰላማዊ ትግል መስመር ስማቸው በዓለም የሚጠራው መሃትማ ጋንዲ፣ ዶ/ር ኪንግ፣ ማንዴላ፣ … በወጣትነታቸው ይህንን ዓይነቱን የትግል መስመር ከመምረጣቸው አኳያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የተጠና እንቅስቃሴና የዓላማ ጽናት ሌሎችም የእናንተን መስመር እንዲከተሉ የሚያደፋፍር እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ የያዛችሁትን እርግጠኛ አቋም እንድትመረምሩ ሊያደርጋችሁ እንደማይገባ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአጽዕኖት ያስታውቃል፡፡ ለመስከረም 12፤ 2006 ዓ.ም. የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ከዚህ በፊት በሊቢያ በቅርቡ በግብጽ አሁን ደግሞ በሶሪያ ሕዝብን እያስተላለቀና እጅግ ደም እያፋሰሰ ያለውን ዕልቂት ተመልክታችሁ አገራችሁን በምንም ዓይነት መልኩ ወደ ደም መፋሰስና ዕልቂት እንዳትገባ የሚደርግ ሰላማዊ የትግል መስመር መምረጣችሁ የጋራ ንቅናቄው ምስክርነት የሚሰጠው ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየትኛውም የአመጽና የሽብር ተግባር ጋር በግድ በማያያዝ ሊኮንናችሁ፣ ሊወነጅላችሁ፣ ወዘተ ቢሞክርና ወደፊትም ይህንኑ ለማድረግ ቢያስብ እስካሁን የፈጸማችሁት ሰላማዊ ሥራችሁና የትግል ስትራቴጂያችሁ በገሃድ የሚመሰክረው ከመሆኑ ባሻገር የጋራ ንቅናቄው ዓለም ሁሉ ይህንን ምስክርነት እንዲያውቅ በማስረጃነት የሚያስመዘግበው ነው፡፡
ትክክለኛውን የትግል መርሆ የተከተለ ሰላማዊ ትግል ከዚህ በፊት የሠራና አሁንም ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ መተግበር እንደሚችል ጠንቅቆ ያወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚነሱትን ሁሉ ገና በእንጭጩ ሲቀጭ ቆይቷል፡፡ ተስፋ በማስቆረጥ፣ በመከፋፈል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት፣ በመግደል፣ ወዘተ የፓርቲ አመራሮችን ያስወግዳል፤ ትግሉ ወደ ተራው አባል ከመዝለቁና አባሉ በራሱ አመራርና የትግሉ ባለቤት መሆን ከመቻሉ በፊት ይበታትናል፡፡ ይህንን የሚያደርገው ከባህርይውና ከለመደው የደም ማፍሰስ አገዛዝና ትግል ውጪ ያለ አካሄድ ሥልጣኑን ስለሚያናጋውና መጨረሻውን ስለሚያቃርበው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የትግል መስመር ተጠናክሮ ወደ ሙሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴና እምቢተኝነት ከተቀየረ ህወሃት/ኢህአዴግ መመከት የማይችልበት ደረጃ ስለሚደርስ ህልውናው ያከትማል፡፡ “ሥልጣን ወይም ሞት” በማለት የፖሊስና የመከላከያ ኃይሉን እስካፍንጫው በማስታጠቅ ዕድሜውን እየገፋ ያለው ህወሃት/ኢህአዴግን ወደ ሙሉ ህዝባዊነት የተቀየረ ሰላማዊ ትግልን መቆጣጠርም ሆነ ማጨናገፍ አይችልም፡፡ ለዚህ ነው ሰላማዊ ትግል በህዝቡ ዘንድ በሙላት ሳይሰርጽና መርሆዎቹ ተግባራዊ ሳይሆኑና ገና በጅምሩ ማጥፋት፣ ማውደም፣ ማሰቃየት፣ ወዘተ የሚፈልገው፡፡ በወጣቶች የተገነባው የሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየረደሰ ያለው ሁኔታ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ፍትሕ መስፈን የሚታገል እንደመሆኑ በሰላማዊ የትግል መስመር ላይ ያሉ ድርጅቶችንም ሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ይደግፋል፤ ያበተረታታል፡፡ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚመጣ ለውጥ በአገራችን ያለማቋረጥ ሲፈስ የቆየውን የደም ጎርፍ እንዲቀጥል፤ ቂምና በቀል እንዲስፋፋ፤ መጪውን ትውልድ በፍርሃትና በማያቋርጥ የደም መፋሰስ አዙሪት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ ሳይሆን፤ በፍትሕ ላይ የተመሠረተ ዕርቅ እንዲሰፍን፤ የአንዱን ነጻነት ብቻ የሚያስከብር ሳይሆን “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚል የጠነከረ ምሶሶ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ በአገራችን ለዓመታት የተረጨውንና እስከ ቤተአምልኮዎች የዘለቀውን የዘር ፖለቲካና የዘረኝነት አመለካከት ማምከን የምንችለው በሌላ መንገድ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” እንስጥ የሚለውን ታላቅ መርህ ከፍ ስናደርግ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄው ያምናል፡፡ ይህንን አመለካከት ከሚጋሩ ሁሉ ጋር በጋር ይሠራል፤ ይንቀሳቀሳል፡፡
በአገራችን ላይ እስካሁን በበሽታ፣ በረሃብ፣ በድህነት፣ በእርስበርስ ጦርነት፣ … ብዙ ደም ፈስሷል፡፡ ከዚህ በኋላ የምንሄድበት መንገድ ይህንኑ እንዲቀጥል የሚያደርግ በጭራሽ ሊሆን አይገባውም፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም ይህንኑ ሊያስተውልና “በለመድኩት የአፈና አካሄድ እቀጥላለሁ” ከሚለው ዕብሪተኛ አስተሳሰቡ ሊመለስ ይገባዋል፡፡ በውስጡ ያሉት የትግራይ ተወላጆችም ይሁኑ ሌሎች የአገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚወጡበትና የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራርን በግልጽ በመተቸት ሁላችንም ወደ ዕርቅ የምንመጣበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ሥርዓቱ “ከእንጥሉ መበስበሱን” ሟቹ ጠ/ሚ/ር የመሰከሩለት በመሆኑ ምንም የሚደበቅ ነገር ስለሌለ ጉዳዩን ይፋ ለማውጣት የሚያስፈራ ነገር የለም፡፡ የጋራ ንቅናቄው ይህንን የጥሪ ደወል እስካሁን ሲያሰማ ቆይቷል፤ አሁንም ይህንኑ ይደግማል፡፡ ሆኖም ይህ በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ላሉትና ለመሰል ድቃይ ድርጅቶች የምንሰጠው “ከሥርዓቱ ተለዩ” የሚለው ጥሪ የሚያቆምበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ምላሽ የመስጫው ጊዜ ነገ ወይም አንድ ቀን ሳይሆን ዛሬ፤ አሁን ነው፡፡ የአፈናና የጭቆና ሥርዓት ጸንቶ አይቆይም፡፡ እንኳን እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ያለው ዘረኝነትን መመሪያው፤ የአገር ውርደት ክብሩ የሆነ አገዛዝ ይቅርና በህዝባዊነታቸውና ብሔረተኝነታቸው የተመሰከረላቸው አገዛዞችም ጨቋኝ በመሆናቸው ብቻ እንደማይነሱ ሆነው ወድመዋል፤ ፈርሰዋል፡፡
ፈጣሪ ሁላችንንም የማስተዋልና ትክክለኛውን መንገድ የመምረጥ ጥበብ ይስጠን፡፡ የልቦና ዓይናችንን ከፍቶ የዘረኝነትን፣ የጥፋትን፣ የብቀላን፣ የውድመትን አስከፊነት እንድናስተውልና የሰላምንና የዕርቅን መንገድ እንድንመርጥ ይርዳን፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የመረጣችሁትን ሰላማዊ መንገድ በምንም አትቀይሩት፤ ከእርሱ የሚበልጥም ሆነ የሚሻል መንገድ የለምና!! ሌሎች የእናንተን ዓይነት መንገድ አስቀድመው ከጀመሩ ጋር በኅብረትና በመቻቻል ሥሩ፡፡
ለውጥ በአገራችን ይመጣል! ይህ የማይቀር ሃቅ ነው! ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች፤ ነጻ የምትወጣው ግን በሌላ ነጻ አውጪ ሳይሆን “ነጻ አውጪ ነኝ” የሚለውን ጭምር ነጻ በሚያወጣው እውነትና ፍትህ ነው፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
ለዚህ ደብዳቤ ምላሽም ሆነ ለተጨማሪ መረጃ ለአኢጋን ሚዲያና ሕዝብግንኙነትን ግብረኃይል(media@solidaritymovement.org) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org)በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ፡፡

Wednesday, September 4, 2013

ወያኔ የሚገነፍል ድስት ነዉ

September 4, 2013
ኤፍሬም ማዴቦ
ስፖርት በጣም እወዳለሁ፤ ወቅታዊ ዜናና ጥናታዊ ፊልምም አዘወትራለሁ። ከሁለቱ ዉጭ ግን ኢትዮጵያ እያለሁም ሆነ ዛሬ በስደት ኑሮዬ ከቴሌቪዥን ጋር ብዙም አልዋደድም . . .  ግን አንዳንዴ እበድ ሲለኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቴሌቪዥን ሆኖ ከመተኛቴ በፊት ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ።  አዎ . . . አብዳለሁ። ሆዴ ያመቀዉ ቁጣና ልቤ የተሸከመዉ የ22 አመት በደል ቀለል የሚለኝ ሳብድ ነዉና ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ። ምን ላድርግ ተሰድጄ ልበድ እንጂ በወያኔዋ ኢትዮጵያማ እነ በረከት ካልፈቀዱ ማበድም አይቻልምኮ!   አደራ እንግዲህ እንደኔ ጠንካራ ቆዳ የሌላችሁና በትንሹም በትልቁም እየተበሳጫችሁ ዕቃ የምትወረዉሩ ሰዎች ኢቲቪን ከመክፈታችሁ በፊት ባንካችሁ ዉስጥ ቴሌቪዥን መግዢያ ትርፍ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጡ፤ አለዚያ እዉነትም ማበዳችሁ ነዉ።
ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የወያኔን ፀባይ በተከታታይ እንዳየሁት የወያኔ ፀባይ ከበቅሎ፤ ከድስት ወይም ከሁለቱም ጋር ተመሳስሎብኛል። በቅሎ የታሰረችበትን ገመድ በጠሰች ቢሉት “በራሷ አሳጠረች” ብሎ መለስ አሉ የበቅሎዋ ጌታ። በቅሎ መታሰሪያዋን በበጠሰች ቁጥር የምትጎዳዉ እራሷን ነዉ፤ ግን በቅሎ በጭራሽ ከስህተቷ አትማርምና ሁሌም ገመዷን እንደበጠሰች ነዉ። አምባገነኑ ወያኔም እንደዚሁ ነዉ።  ድስት ሁሉም ባይሆንም አንዳንዱ በጣዱት ቁጥር ይገነፍላል፤ የሚገነፍል ድስት ደግሞ የሚያበላሸዉ እራሱን ነዉ። ወያኔ ድስትም በቅሎም የሚሆነዉ ዕድሜዉን ለማራዘም ነዉ፤ ሆኖም ሲገነፍልም ሆነ ገመዱን ሲበጥስ እድሜዉ ያጥራል እንጂ አይረዝምም።
ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሐይማኖቶች ጉባኤ ይካሄዳል ሲባል ሰምቼ ባለፉት ሁለት አመታት ካልጠፋ ነገር አገራችን የምትታመሰዉ በሐይማኖት ጉዳዮች ነዉና እስኪ ዜናዉን ከምንጩ ልስማ ብዬ ኢቲቪ ላይ አፈጠጥኩ። መቼም ኢቲቪ በብዙ ነገሮች ሊያበሳጫችሁ ይችላል ግን  ዛቻ፤ ዉሸትና፤ ዘራፊ ባለስልጣኖች ሲሞገሱ መስማት ከፈለጋችሁ ግን ሌላ ዬትም ቦታ መሄድ አያስፈልጋችሁም በዚህ ኢቲቪ የልባችሁን ያደርስላችኋል።
ወያኔ ስልጣን ይዞ በቆየባቸዉ አመታት ሁሉ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ ጨንቋት ያላማጠችበትና ግራ ግብቷት ድረሱልኝ ያላለችበት አንድም ግዜ የለም። ወያኔ ባለፉት ሃያ አመታት ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያን እንዳልነበረች ለማድረግ ያልቆፈረዉ ጉድጓድና ያልሸረበዉ ደባ ባይኖርም ባለፉት ሁለት አመታት ይዞብን የመጣዉ ሸርና ተንኮል ግን የክርስቲያኑንና የሙስሊሙን ማህብረሰብ የአንድ ሺ አራት መቶ አመታት በሰላም አብሮ የመኖር ባህል የሚያደፈርስና አገራችንን አስከፊ የሐይማኖቶች ግጭት ዉስጥ የሚከት አደገኛ ሴራ ነዉ። ለወትሮዉ ፖለቲካዉን በዘር፤በቋንቋና በክልል ቋጥሮ ማዶ ለማዶ የለያየን ወያኔ ዘንድሮማ ጭራሽ የፓርቲ አባልነታችንን ብቻ ሳይሆን የምናመልክበትን የእምነት ቦታና አለም በቃኝ ብለን የምንመንንበትን ገዳም ጭምር አኔ ነኝ መርጬ የማድላችሁ ማለት ጀምሯል። በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጳጳስ አዉርዶ ጳጳስ ሾሞባቸዋል፤ የወንጌላዉያን ቤ/ክርሲቲያኖችን ፓስተር አንዴ አስታራቂ አንዴ አማላጅ እያደረገ ቤ/መንግሰትና ቃሊቲ መሃል ተላላኪ አድርጎታል፤አሁን በቅርቡ ደግሞ ፊቱን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በማዞር የራሱን መጅሊስ ሾሞባቸዋል።
ወያኔ ጥንታዊቷን የኦርቶዶክስ ቤ/ክርሰቲያናችንን የአገር ዉስጥና የአገር ዉጭ ሲኖዶስ በሚል በመከፋፈል ወንጌላዉያኑን አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ እኔ ነኝ የማምለክ ነጻነት የሰጠኋችሁ እያለ በማስፈራራት የክርስቲያኑን ህብረተሰብ ለግዜዉም ቢሆን ጭጭ አሰኝቶ እንዳሰኘዉ መቆጣጠር ችሏል። በድርጅታዊ ጥንካሬዉ፤ በምዕመኑ መካከል በገነባቸዉ የግንኙነት መስመሮችና  በእምነት ቀናኢነቱ ከክርስቲያኑ እጅግ በጣም በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኘዉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን  የወያኔን ፈላጭ ቆራጭነት አልቀበልም ብሎ ወያኔንና ዘረኝነቱን ፊለፊት በመጋፈጥ ላይ ይገኛል። ሰለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ  ሐይማኖቴን አትንካብኝ በሚለዉ በሙስሊሙ ህብረተሰብና አጎንብሰህ ተገዛ በሚለዉ ወያኔ መካከል በተፈጠረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በመታመስ ላይ ትገኛለች። እኔም ሞኝ ይመስል ኢቲቪ ላይ ያፈጠጥኩት ይካሄዳል የተባለዉ የሐይማኖት ጉባኤ ይህንን አገራችን ላይ የተደቀነዉን አደጋ ተመልክቶ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ብዬ ነበር። ግን የወያኔ ነገር ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነዉና የሐይማኖት ጉባኤ ተብሎ የቀረበዉ ጉድ እንደ አኬልዳማና ጂሃዳዊ ሐረካት ሆን ተብሎ  ህዝብን ለማደናገር የተሰራ ድራማ ነዉ እንጂ በችግሮች ላይ ተወያይቶ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርብ ጉባኤ አይደለም። በአኬልዳማ ድራማና ሰሞኑን በተካሄደዉ የሐይማኖቶች ጉባኤ መካከል ልዩነት ቢኖር አንዱ የቴሌቪዥን ድራማ ሌላዉ ደግሞ የመድረክ ላይ ድራማ መሆናቸዉ ብቻ ነዉ።
በዚህ የሐይማኖቶች ጉባኤ ተብዬዉ የአዳራሽ ውስጥ ድራማ ላይ የተገኙት አብዛኛዎቹ ተዋንያን የዚያ “የድንጋይ ማምረቻ” ተቋም ዉጤቶች የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች፤ የወያኔ ባለስልጣኖችና ኤሳዉ ታላቅነቱን ለምግብ እንደሸጠ የሐይማኖት አባትነታቸዉን ለጥቅም የሸጡ ካህናት ለመሆናቸዉ ምስክር የሚያሻ አይመስለኝም፤ ቴሌቪዥኑ መስኮት ዉስጥ አንደተከበበ አዉሬ የሚቁለጨለጨዉ አይናቸዉ ምስክር ነዉ።  ድራማዉን በኢቲቪ ስመለከት ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማያዉቁ የወያኔ ባለስልጣኖች እንዳሰኛቸዉ እንደሚናገሩ ስለማዉቅ እነሱ ተናገሩም አልተናሩ ከነሱ ብዙም የምጠብቀዉ ነገር አልነበርም። ይልቁን ጉባኤዉን ስከታተል እጅግ በጣም የገረመኝና የራሴኑ ጆሮ ማመን ያቃተኝ አንድ በሰማይም በምድርም ተጠያቂነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባትና በዋሸ ቁጥር ኩራት የሚሰማዉ በረከት ስምኦን ያደረጉት እንደ ብርሀንና ጨለማ የተቃረነ ንግግር ነዉ። መቼም እርግጠኛ ነኝ የበረከትንና የአባዉን   ፊት ሳያይ ንግግራቸዉን ብቻ ያዳመጠ ሰዉ የቱ ነዉ በረከት የትኛዉ ናቸዉ የሀይማኖት አበት ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ለሁሉም እኚያ የሐይማኖት አባትና በረከት እንዲህ ነበር ያሉት
የሐይማኖት አባት                        መንግስት ትዕግስቱን አብዝቶታል  . . . . እርምጃ ይዉስድ
በረከት ስምኦን                መንግስት ኃይሉ አለዉ ግን መታገሱ ጠቃሚ ነዉ
መቼም አንደህ አይነቱን ጉድ ከጉድም ጉድ የሚያዳምጡ ሰዎች ጆሯቸዉን ሲያማቸዉ፤ ሲበሳጩና አንጀታቸዉ ሲቃጠል ይታየኛል . . ደግሞስ ለምን አይበሳጩ ለምንስ አንጀታቸዉ አይረር?  ትዕግስት ምን አንደሆነች የማያዉቃት ወያኔ ለዛዉም በበረከት ስምኦን አፍ መታገሱ ጠቃሚ ነዉ ነዉ ብሎ ሲናገር የትዕግስት አባት የሆነዉን እግዚአብሄርን አገለግላለሁ ባዩ ቄስ “ትዕግስት በዛ እርምጃ ይወሰድ” ብለዉ መንግስትን የሚማጸኑበት ግዜ መጣ . . . ያዉም ስራዉ ዜጎችን መግደል የሆነዉን መንግስት!  እግዚኦ!  ለመሆኑ አንደ አገርና እንደ ህዝብ ስነምግባራችንና ሀይማኖታዊ እሴታችን እንደዚህ የዘቀጠበት ግዜ ኖሮን ያዉቃል? የወደፊቱን አገር ተረካቢ ትዉልድ በስነምግብርና በግብረገብ አንጾ የማሳደግ ኃላፊነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባት መንግስትን አሁንስ አበዛኸዉ ሂድና ግደል እንጂ የሚሉ ከሆነ ይህ እዉነት ሳይሰማ ያደገ ትዉልድ ስራዉ መግደል ብቻ ሊሆን ነዉኮ . . .   አረ እግዚኦ ማረን!  እባክህ ማረን!
ልጅ እያለሁ አንድ በኃይሉ እሼቴ የሚባል “መሆኑ ይገርማል የተገላበጦሽ አህያ ወደሊጥ ዉሻ ወደ ግጦሽ” ብሎ የዘፈነ አለግዜዉ የተፈጠረ ዘፋኝ ነበር  . . ያኔ የማይመስል አባባል ይመስለኝ ነበር፤  ይሄዉና ዘመን ቆጥሮ ደረሰ። በረከት ስምኦንን በተመለከተ ያንን ንግግር ከልቡ ይናገረዉ ወይ ለማሽሟጠጥ አላዉቅም ሆኖም በረከት ያዉ በረከት ነዉና ስለሱ ምንም የምለዉ የለኝም። እኚያ የሐይማኖት አባት ግን ይህንን አሳፋሪ ንግግር የተናገሩት ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ያንን ለትዉልድ ሁሉ ኩራት የሆነዉን ታሪካዊ ንግግር በተናገሩበት ከተማ ዉስጥ ነዉና አሳቸዉ ያለ እፍረት አፋቸዉን እንደከፈቱ እኔም በድፍረት አፌን አከፍትባቸዋለሁ . . . ምን ላድርግ 1ኛ ሳሙኤል 2፡1 ላይ  “አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ” ይላልኮ አባ እራሳቸዉ ያስተማሩኝ ቅዱስ መጽሐፍ።  ለሁሉም “እናቷን ምጥ አስተማረች” እንዳይሆንብኝ እንጂ  እኚያ ወያኔን “ምነዉ መንግስት ትዕግስት አበዛ” ብለዉ ያወገዙት አባት ተሸክመዉ የሚዞሩትን መ/ቅዱስ አንብበዉት ከሆነ እዚያ ቅዱስ መጽሐፍ ዉስጥ ትዕግስት የሚለዉ ቃል 33 ግዜ ተጠቅሷል። “አትግደል” የሚለዉ ትዕዛዝ ደግሞ ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ሲሆን ቅዱስ ታቦቱ ላይም የሰፈረ ቃል ነዉ። መጽሐፍ ቅዱስ ትዕግስትን አስመልክቶ  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 25፤15 ላይ “በትዕግስት ማግባባት ታላቅ ተቃወሞን ያበርዳል፤መሪዎችን ሳይቀር በሃሳብ እንዲስማሙ ያደርጋል” ይላልኮ! ለመሆኑ ትዕግስቱን ተትህ ግደል እንጂ ብለዉ ወያኔን የተማፀኑት የሐይማኖት አባት የኦርቶዶክስ አባ ናቸዉ፤ የካቶሊክ ካርዲናል፤ የፕሮቴስታንት ፓስተር ወይስ በሐይማኖት ስም የመጡ የወያኔ ካድሬ? ማናቸዉ እኚህ ታገሱ ፤ ትዕግስትን ገንዘባችሁ አድርጉ፤“መግደል” ኃጢያት ነዉና ሰዉ አትግደሉ ብለዉ ማስተማር ሲገባቸዉ የተገላቢጦሽ “ግደል” እያሉ የሚማጸኑ የሐይማኖት ሰዉ?
ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ያነሱትን የመብትና የነጻነት ጥያቄ በተመለከተ ፖለቲካና ሐይማኖት፤ካድሬነትና ቅስና ተቀላቅሎባቸዉ ግራ ተጋብተዉ ህዝብን ግራ ከሚያጋቡ ሰዎች አንዱ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ነዉ። ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንደ መለስ ዜናዊ ምላስ እንቆርጣለን ብሎ እንዳይዝት እንኳን ምላስ ለመቁረጥ ቤ/መንግስት ከመግባቱ በፊት በነጻነት ያመልከዉ የነበረዉን አምላኩን ለማምለክም የወያኔ ፈቃድ ያስፈልገዋል። ደሞ ምንም ቢሆን ሰዉዬዉ የአገር መሪ ነዉና ችግሮችን እፈታለሁ በሚል ሚዛናዊ እርምጃ ልዉስድ ቢል እሱ እራሱ በስልክ እየታዘዘ የሚሰራ ሰዉ ነዉ። መቼም በወያኔዋ ኢትዮጵያ እንዲህ አይነቱ ነገር አይታሰብም እንጂ ኃ/ማሪያም ዳሳለኝ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳዉን ጥያቄ ከሐይማኖት፤ከባህልና ከስነምግባር አንጻር አይቶ ትክክለኛ ጥያቄ ነዉ ብሎ ጥያቄዉን ለመመለስ ቢሞክር እንኳን ብዙም ሳይቆይ “እንደወጣች ቀረች” ተብሎ ይተረትበታል አንጂ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ህዝባዊ ጥያቄዎችን መመለስ ቀርቶ እሱ እራሱ ያሻዉን ጥያቄ መጠየቅም አይችልም ። እንግዲህ ይህ እራሱን መሆን የተሳነዉና ሦስት ቅርቃሮች ዉስጥ ገብቶ የተቀረቀረዉ ኃ/ማሪያም ነዉ አንዴ ተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንወስዳለን፤ አንዴ የሙስሊሙ ጥያቄ የሸሪአ ጥያቄ ነዉ፤ ይባስ ሲለዉ ደግሞ ከሙስሊሙ ትግል ጋር የተባበረ ሁሉ ሽብርተኛ ነዉ እያለ ያልተጻፈ መጽሐፍ የሚያነብበዉ። ለመሆኑ ይህ ጧትና ማታ የጓድ መለስን ራዕይ ተግባራዊ እናደርገለን እያለ የሚዘምረዉ ኃ/ማሪያም  “ተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንወስዳለን” ሲል የጌታዉን ራዕይ ተግባራዊ ማድረጉ ይሆን?
ባለፉት ሦስት ሳምንታት በተለይ ባለፈዉ ቅዳሜ በወያኔ ጌቶቹ እየተመራ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የወሰዳቸዉ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር እርምጃዎች ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ያለዉን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለሚከታተሉ አገሮች ያረጋገጠዉ ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኛ ስርዐት ለማስወገድ የሚከተለዉን እስትራቴጂ በጥልቀትና በስፋት መመርመር እንዳለበት ነዉ። እስካዛሬ እንዳየነዉ ወያኔ በልመናም፤ በሰላማዊ ትግልም፤ በአመጽም ሆነ በሌላ በምንም አይነት መንገድ እንድንታገለዉ የማይፈልግና እኔ ብቻ ዝንተ አለም እንደገዛኋችሁ ልኑር የሚል ልቡ ያበጠ አምባገነን ነዉ። ህዝባዊ ተሳትፎን በተመለከተ የወያኔ ፍላጎት አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም በዚያ እሱ እንደ ቤቱ ጓዳ በሚቆጣጠረዉና በየአምስት አመቱ በሚደረገዉ ምርጫ እንድናጅበዉ ብቻ ነዉ። ከዚህ ዉጭ ዲሞክራሲና መብት የሚባል ቃል ስሙን ያነሳ ሰዉ ወይ ይታሰራል፤ ይደበደባል፤ከአገር ይሰደዳል አለዚያም ይገደላል። የወያኔና የእኛ ሠላማዊ ትግል በይዘትም በቅርጽም እጅግ በጣም የሚለያይ ይመስለኛል። የወያኔ ሠላማዊ ትግል እኔን ብቻ ስሙኝ ወይም በየአምስት አመቱ በምርጫ አጅቡኝ ነዉ። እኛ ሠላማዊ ትግል የምንለዉ ደግሞ መብታችን ይከበር ብለን ባሰኘን ግዜና ቦታ የተቃዉሞ ሠልፍ ማድረግ፤ የስራ ማቆም አድማ ማድረግና ወያኔ ህገመንግስቱን የሚጻረር መመሪያና ህግ ሲያወጣ በፍጹም አንቀበልም ብለን በህዝባዊ እምቢተኝነት ማመጽ ነዉ። ይህንን አድርገን ቢሆን ኖሮ ዛሬ እስክንድርን፤ አንዱአለምን፤ ርዕዮትንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሠላማዊ ዜጎችን ቃሊቲ የወረወረዉ ህግ አይኖርም ነበር። ሠላማዊ ትግል የሚባለዉ እንደዚህ አይነቱ ትግል ነዉና ወያኔን ማፋጠጥ ያለብን በዚህ አይነቱ ትግል ነዉ፤ ካለዚያ የትግላችንን እስትራቴጅ ፈትሸን ለግዜዉ የወያኔን ጥቃት ባይመጥንም ወያኔ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ሁለቴ እንዲያስብ የሚያደርግ የትግል እስትራቴጅ መንደፍ አለብን። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔን በመሳሪያ ለመፋለም የቆረጡ ኃይሎችን ቢቻል መደገፍ አለዚያም ጣታችንን እነሱ ላይ መጠንቆሉን ማቆም አለብን።
ከሰዐት በኋላ ረፋዱ ላይ ከስራ ወጥቼ ቴሌቪዥኑ ፊት ስደቀን የአገሬ የኢትዮጵያ ነገር አይኔ ላይ ይመጣና አንዳንዴ ግርም ይለኛል፤ አንዳንዴ ይጨንቀኛል፤ አንዳንዴም ይነድደኛል። የከሰሞኑ ግን አታምጣ ነዉ።  አግራሞቱም፤ ጭንቀቱም፤ ንዴቱም እንደ ክፉ መንፈስ በአንዴ ተከመሩብኝ። መቼም የኢትዮጵያ ነገር የማይገርመዉ ኢትዮጵያዊም ሆነ የዉጭ አገር ሰዉ ያለ አይመስለኝም፤ ደግሞስ የኢትዮጵያ ነገር ለምን አይገርምም?  መንግስት ተብዬዉና አገር እመራለሁ ባዩ ወያኔ የምትወደዉ እንድዬ ልጇ እንደሞተባት አሮጊት አመት ጠብቆ ተዝካር ሲያወጣ . . . .  ጎበዝ ለመሆኑ ተዝካር የሚያወጣ መንግስት አይታችሁ ወይም ሰምታችሁ ታዉቃላችሁ? አኔ እንኳን መስማት አስቤዉም አላዉቅም። የሚገርመዉ ወያኔ ያንን የፈረደበትንና የዛሬ አመት እያስፈራራ በጉልበት ያስለቀሰዉን ህዝብ ብቻ ሰብስቦ የጌታዬን ተዝካር አዉጡልኝ ቢል ኖሮ ነገሩ እኛዉ በእኛ ነዉና ስቀን ዝም እንል ነበር፤ ግን ጉደኛዉ ወያኔ ተዝካር ድረሱልኝ ብሎ የጠራዉኮ የጎረቤት አገር መሪዎችን ጭምር ነዉ። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነኝና ተዝካር ለሟቹም ለቋሚዉም አይጠቅምም ብዬ አምናለሁ፤ ሆኖም ተዝካር ትክክለኛ ነገር ነዉና መዘከር አለበት የሚሉ ወገኖች ተዝካር የማዉጣት መብታቸዉ እንዲከበር ሽንጤን ገትሬ የምታገል ሰዉ ነኝ። ግን የኢትዮጵያ መንግስት ሲባል የኦርቶዶክሱ፤ የሙስሊሙ፤ የጴንጤዉ፤ የካቶሊኩና የሌሎቹም የዬትኛዉም አይነት እምነት ተከታዮችና ስለሐይማኖት ግድ የሌላቸዉም ሰዎች መንግስት ስለሆነ ተዝካር ማዉጣጥ ቀርቶ ስለተዝካር መልካምነትም ሆነ መጥፎነት መናገርም የለበትም የሚል የፀና እምነት አለኝ። በረከት ስምኦንና ሽመልስ ከማል አይገባቸዉም አንጂ የሚገባቸዉ ቢሆን ኖሮ ሐይማኖትና መንግስት ተቀላቀሉ የሚባለዉ እንደዚህ መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ ተዝካር ሲያወጣ ነዉ አንጂ ሐይማኖትና ፖለቲካ ሲነካኩ አይደለም፤ እነሱማ መነካካት አለባቸዉ፤ የአገሪቱ ህገመንግስትም ይህንን አይከለክልም።
ሌላዉ ከሰሞኑ ያየሁት የወያኔ ጉድ  . . . ማንን እንደሚቃወም ባላዉቅም ወያኔ ሠላማዊ ሠልፍ የሚወጣ ብቸኛዉ የአለማችን መንግስት  ነዉ። ወገኖቼ ይህ ጉድ ካልገረመን፤ ካልጨነቀንና ካልነደደን ሌላ ምን. . . ምን . . . .  ምን! ደግሞኮ የ39 አመቱ ጎልማሳ ወያኔ ሠላማዊ ሠልፍ የጠራዉ ገና በእግሩ መሄድ ካልጀመረዉ ከሠማያዊ ፓርቲ ገር ሽሚያ ገብቶ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል ካላገደ በቀር ሠላማዊ ሠልፍ ማድረግ ህገመንግስታዊ መብት ነዉ፤ወይም  ዜጎች ሠላማዊ ሠልፍ ለመዉጣት ማሳወቅ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አያሻቸዉም። ወያኔ ሠማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ሠልፍ ለጸጥታ ወይም ለሌላም ጉዳይ ብሎ እንዳይካሄድ ቢፈልግ ኖሮ ብቸኛዉ አማራጭ ወይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር መደራደር አለዚያም ፍርድ ቤቶች የራሱ ንበረቶች ቢሆኑም ለይስሙላም ቢሆን እዚያ መሄድና ፍርድ ቤቱን ማሳመን ነበረበት እንጂ ልቡ እንዳበጠ የመንደር ዉስጥ ወጠጤ በተራ ዝርፊያና ድብደባ ላይ አይሰማራም። መንግስት ማለት ያሰኘዉን ነገር ሁሉ የሚያደርግ ተቋም አለመሆኑን ወያኔም ሆነ ወያኔ በተተቸ ቁጥር ምጣድ ላይ እንደቆየ ተልባ የሚንጣጡት ደጋፊዎቹ ሊረዱት ይገባል።
ባለፈዉ ቅዳሜ ወያኔ ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር ሠልፍ ልዉጣ አትወጣም በሚል በገባዉ እሰጥ አገባ በህግም በሃሳብም በሠማያዊ ፓርቲ በመሸነፉ የተሸናፊዎች ብቸኛ መሳሪያ የሆነዉን ጉልበትና በህግ ያልተገደበ ኃይል በመጠቀም የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችን በቆመጥና በሰደፍ ሲደበድብ ዉሏል፤ የፓርቲዉን ጽ/ቤት ሰብሮ በመግባት ንብረት ሰርቋል እንዱሁም ፓርቲዉ በህጋዊ መንገድ የተከራየዉን ጽ/ቤት ከብቦ አካባቢዉን የጦርነት ወረዳ አስመስሎታል። መስበር፤ መዝረፍ፤ ሠላማዊ ዜጎችን መደብደብና የአካባቢን ጸጥታ መንሳት . . . . ለመሆኑ ማነዉ ሽብርተኛዉ?  አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ አለማችን ብዙ አምባገነን መሪዎችን አስተናግዳለች፤ እንደ ወያኔ አይነቱ ተራ ዱሪዬና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ንፍጣቸዉን የተናፈጡበትን መሀረብ ጭምር የሚሰርቅ ተራ ሌባ የሆነ ስርዐት ግን ዬትም አገር ዉስጥ ታይቶ አይታወቅም። ይህ ስርዐተ አልበኛ የሆነ የወንበዴ አገዛዝ ከአሁን በኋላ የሚወስደዉ እርምጃ ለሁላችንም ግልጽ የሆነ ይመስለኛል፤ ትናንት በአንዱ አለም አራጌ፤ በእስክንድር ነጋ፤ በበቀለ ገርባና ኦብላና ሌሊሳ ላይ የተመሰረተዉ የግፍ ከስ ዛሬ በሠላማዊ ፓርቲ መሪዎች ላይ መመስረቱ አይቀርም፤ የሚያሳዝነዉ በሠማያዊ ፓርቲ መሪዎች ላይ መረጃ ሆነዉ የሚቀርቡት እነዚሁ ባለፈዉ ቅዳሜ ከፓርቲዉ ጽ/ቤት የተዘረፉት የፓርቲዉ ህጋዊ ሰነዶች ናቸዉ። እንገዲህ ያታያችሁ . . .  ከሳሾቹ ሌቦች፤ ዳኞቹ ሌቦች ምስክሮቹ ሌቦች፤ ማስረጃዉም በሌብነት የተሰበሰበ ማስረጃ ነዉ . . .  “እዛዉ ሞላ እዛዉ ፈላ”  . . .  እንደዚህ ነዉ የወያኔ ነገር … ሁሉም ነገር በሌብነት!
ባለፈዉ ቅዳሜ ወያኔ ከብዕርና ከመጽሐፍ ዉጭ እጃቸዉ ሌላ ምንም ነገር ጨብጦ የማያዉቀዉን ነፃነትና ፍትህ ናፋቂ ወጣቶች ወራሪ ጠላትን ለማጥቃት በሰለጠኑ የልዩ ኮማንዶ ኃይሎች ሲደብድብ ዉሏል። ሴቶች እህቶቻችንን ባዕዳን አረቦች ከሚያድርሱባቸዉ የአካልና የሂሊና ጉዳት እጅግ በጣም በከፋ መልኩ ተድብድበዋል፤ ክብራቸዉንና ሰብእናቸዉን በሚያንቋሽሽ ስድብ ተሰድበዋል። ከሁሉም የሚያሳዝነዉ ወጣት ሴቶቻችን ልብሳቸዉን እንዲያወልቁ ተደርገዉ በዉስጥ ሱሪያቸዉ ብቻ ጭቃ ዉስጥ እንዲንከባሉ ተደርገዋል። በቀጥታ ከዲስ አበባ በደረሰኝ መረጃ መሠረት የወያኔ ደነዝ አግአዚ ቅልቦች በ1997ቱ ምርጫ ማግስት በግልጽ የነገሩንን ቃል አሁንም በማያሻማ መልኩ አስረዉ እየደበደቡ በሚያሰቃዩዋቸዉ የሠማያዊ ፓርቲ አባላት ፊት አንደዚህ ሲሉ ደግመዉታል -
እንገዛችኋለን . . .  መግዛት ብቻ ሳይሆን እንረግጣችኋለን!! ደማችንን አፍስሰንና አጥንታችንን ከስክሰን የያዝነዉን ስልጣን አሁንም እንሞትለታለን እንጂ በፍጹም አንለቅም። በሠላማዊ ትግል ስልጣን መያዝ ቀርቶ ከዛሬ በኋላ እኛ ሳንፈቅድላችሁ ከቤታችሁም አትወጡም። ስለህግ አታዉሩ ህግ ማለት እኛ ነን።
ዉድ ኢትዮጵያዉያን ለወያኔ ጅላጅሎችና ጋጠወጦች የማንገዛና የማንረገጥ መሆናችንን ብቻ ሳይሆን ታቦት ተሸክመዉ እባካችሁ ማሩን ብለዉ እስኪለምኑን ድረስ መርገጥ ማለት ምን ማለት መሆኑን ማሳየት የምንችል መሆናችንን በተግባር ማሳየት አለብን። ለአገራቸን ግድ ከሌላቸዉ፤ ታሪካችንን ከናቁና ለሰብዕናችንና በተለይም ለሴት እህቶቻችን ክብር ከሌላቸዉ እኛስ እነዚህን አዉሬዎች ለምን መታገስ አለብን፤ ለምን መሸከም አለብን ለምንስ እነሱ አድርጉ የሚሉንን ማድረግ አለብን? የታለ ያ ባርነትን የሚጸየፈዉ ኢትዮጵያዊታችን? የታለ ያ ጥቃትን በፍጹም የማይቀበለዉ ኢትዮጵያዊ ወኔያችን? የታለ ያ “እታለም” ስትደፈር ዱር ቤቴ ብሎ የሚሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን? የታለ ያ በ1970ዎቹ የትግል ጓዱ በደርግ ባንዳዎች እጅ እንዳይወድቅ ሲል ብቻ ፖታሲየም ሳይናይድ እየቃመ የሞትን ፅዋ የጨለጠዉ ኢትዮጵያዊ ጅግንነታችን. . .  የታለ?  . . .የታለ? . . .የታለ?  የወያኔ ዘረኞች ረግጠዉ ሊገዙን ሞተዋል፤ ዛሬም ይህ ረጋጭ ስርአታቸዉ እንዲቀጥል ለመሞት ቆርጠዋል? እኛስ ምነዉ ላለመረገጥ፤ ላለመገዛትና እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በዘረኞች እንዳይገደሉ ስንል የማንሞተዉ ለምንድነዉ? ጎበዝ እኔ አልሞትም ብንልም በቁማችን ሞተናልኮ፤ አንዱኑ በክብር እንሙትና ለወገኖቻችንና ለአገራችን ቤዛ እንሁን አንጂ!
የኢትዮጵያ ህዝብ ህግ አክባሪ ህዝብ ነዉ፤ ሆኖም ወያኔ የራሱን ህገመንግስት ጥሶ በህግ ያልተገደበ ኃይል ሲጠቀም ወይም ህጉን የጻፈዉ አካል እራሱ ያላከበረዉን ህግ ማክበር ሞኝነትና እራስን ለጥቃት ማጋላጥ እንጂ ህግ አክባሪነት አይደለም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ከበስተጀርባዉ የማስፈጸሚያ ኃይል የሌለዉ ህግ እንደማይጠቅመን ሁሉ ህግ የማይገዛዉ ልቅ የሆነ ኃይልም ይጎዳናል እንጂ በፍጹም አይጠቅመንም። ስለዚህ እንደ አገርና እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን በህግ ያልተገደበ ኃይል የጨበጡ የወያኔ ዘረኞችን ወይ ህግ እንዲገዛቸዉ ማስገደድ አለዚያም ማስወገድ አለብን። በህግ አክባሪነትና በስርአተልበኝነት መካከል ምንም አይነት ማመቻመች ወይም ድርድር ሊኖር አይገባም።
ከዉጭ ራቅ ብሎ ለተመለከተዉ የወያኔ አገዛዝ ሽብርተኝንትን ለማጥፋት ወይም ለመቆጣጠር ከአቅሙ በላይ ሽር ጉድ ሲል ይታያል፤ ነገሩ “ላም ባልዋለችበት ኩበት ለቀማ” ሆነ እንጂ ወያኔ ሽብርተኝነት ከኢትዮጵያ መጥፋቱን ለማረጋገጥ ከፈለገ ማድረግ ያለበት ነገር አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም ሳይዉል ሳይድር ዛሬዉኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ማሸበሩን ማቆም ነዉ። ሽብር እየፈጠሩ የአገርን ሠላምና ጸጥታ አስከብራሁ ማለት የለየለት ምግባረብልሹነት የመሆኑን ያክል ህዝብን በመግደል የተካነ መንግስትን ምነዉ ዝም አልክ ግደል እንጂ ብሎ መማጸንም ምግባረብልሹነት ብቻ ሳይሆን አማኑኤል የሚያስኬድ የዕምሮ በሽታ ነዉ። በዚህ አጋጣሚ የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችን፤ አባላትንና ደጋፊዎችን ትክክለኛዉን ሠላማዊ ትግል አሳይታችሁኛልና ባርኔጣዬን አንስቼ ለእናንተ ያለኘን አድናቆት መግለጽ እወዳለሁ። የቆማችሁለትን የፍትህ፤ የነጻነት፤ የዲሞክራሲና የእኩልነት እሴቶች እንደ ጦር የሚፈሩ ጉግማንጉጎች በሚወስዱት የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ተደናግጣችሁ ከቆማችሁለት ትክክለኛ አላማ ወደ ኋላ እንደማትሉ እርግጠኛ ነኝ። እዉነትና የእትዮጳያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ነዉና ማሸነፋችን የተረጋጋጠ ነዉ . . .  ኑ ተነሱ የወያኔን ሽብርተኝነት አብረን እንዋጋ!