Wednesday, July 31, 2013

ጴጥሮሳዊነት (ፕ/ር መሰፍን ወልደማርያም)

July 30, 2013
ቀደም ሲል « እግዚአብሔርና እኛ» በሚለው ርዕስ ስር የተነገረውን አንዳንድ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት ጸረ ሃይማኖት ሊያስመስሉት ይሞክሩ ይሆናል። አይደለም ። እንዲያውም ሃይማኖትንና ሃይማኖተኛነትን የሚያጸና ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ሃይማኖት ቢኖረው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና በእግዚአብሔርም ላይ ያለው እምነት ብርቱ ነው። ይህንን ከመገንዘብ የተነሳና በዚያው ፍቅርና እምነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በምንም መንገድ ጸረ ሃይማኖት መስሎ ሊታይ አይገባም።Prof. Mesfin Woldemariam
ችግሩ ሌላ ነው። ችግሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመንፈሳዊ ተግባርና ኃላፊነት የሚያበቃ ሁኔታ አለመኖርና ወደፍጹምነት የሚጠጋ የመንፈሳዊነት ድርቀት ነው። እ.አ.አ. በ1977 ዓ.ም. ጉለሌ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለካቶሊክ ሚስዮናውያን ንግግር እንዳደርግ ተጠይቄ የኅብረተሰባችን የመንፈስ ውድቀት (ክስረት) በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ተናግሬ ነበር። በዚያ ንግግር ውስጥ የሚከተለው በከፊል ይገኝበት ነበር።
በየቀኑ የጭካኔ ወሬ እንሰማለን። ወጣቱ ለወደፊት መዘጋጀቱን ትቶ፤ ክፉኛ ለሁለት ተከፍሎ እርስበርሱ ለመጫረስ ተነሥቶአል። ለበለጠ ግድያና መጨራረስ ጩኸት እንሰማለን፤ የእናቶችና የሚስቶችን ጩኸት እንሰማለን፤ የሐዘን ልብሳቸውንም እናያለን። የሞትን አደጋ በየአቅጣጫው እናያለን። የፍቅርን አለመኖር እንሰማለን፤ እናያለን፤ የተስፋን አለመኖር እንሰማለን፤ እናያለን። ንዴትን እናያለን፤ እንሰማለን፤ ተስፋቢስነትን እንሰማለን፤ እናያለን፤ ሐዘንን እንሰማለን፤ እናያለን። ከዚህም በላይ ንዴቱም ተስፋቢስነቱም ሐዘኑም ይሰማናል። ሕይወት አጠራጣሪና በቀላሉ የሚጠፋ ሆኖአል። እንሰማለን፤ እናያለን፤ እናያለን፤ እንሰማለን። ምንም አናደርግም። ይህ ምንም ያለማድረግ ውሳኔና ይህ በኅብረተሰቡ ኑሮ ውስጥ ያገባኛል የሚል ስሜት መጥፋት ግልጽ የሆኑ የወላጆችን፤ የአስተማሪዎችንና የሃይማኖት መሪዎችን የመንፈስ ውድቀት የሚያመለክቱ ናቸው። ለግፍ፤ ለበደልና ለጥቃት እንድንገብር፤ ግፍን በደልንና ጥቃትን አየሰማንና እያየን ምንም እንዳናደርግ የሚያደርገን ምንድን ነው?
እኔ እንደሚመስለኝና እንደማምነውም የጉዳዩ ባለቤት ራሳችን መሆናችንን ተገንዝበን ኃላፊነቱንና የሚያስከትለውንም ውጤት ላለመቀበል የፈጠርነው የመከላከያ ዘዴ ጉዳያችንን ሁሉ ወደእግዚአብሔር መወርወሩን ነው። የሚደንቀው ነገር የሃይማኖት መሪዎችን መለየቱ ለምን አስፈላጊ ሆነ? የሃይማኖት መሪዎች «ሥጋቸውን የበደሉ፤ለነፍሳቸው ያደሩ» ናቸው ይባላል። የሃይማኖት መሪዎች ለጽድቅ ማለት ለእውነት እንዲሁም ለፍትሕና ለእኩልነት የቆሙ ናቸው ተብሎ ይታመናል። ለሃብትና ለሥልጣን ግድ ስለሌላቸው ከዚህ ዓለም ጣጣ ውጭ ናቸው ይባላል። እንግዲህ እንደዚህ ዓይነቶቹ ለእግዚአብሔር አድረናል የሚሉ ሰዎች ለግፍ ለበደልና ለጥቃት እንዲገብሩ የሚያደርጋቸው ከየት የመጣ ኃይል ነው? ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም። ለዚህ ዓለም ሕይወት ካላቸው ጉጉት ብቻ የሚመነጭ ነው። የሚጎድላቸው ጴጥሮሳዊነት ነው።
የአቡነ ጴጥሮስ መንፈስ እንደሐውልታቸው የተረሳ ይመስለኛል። አቡነ ጴጥሮስ እንደሌሎቹ ሁሉ ኢጣልያ ኢትዮጵያን የወረረችው «የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ነው»፤ በማለት የኢጣልያ ወታደር የኢትዮጵያን ሕዝብ አበሳውን ያሳየው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው በማለት ሊገብሩና የተደላደለ ኑሮ ለመኖር ይችሉ ነበር። አቡነ ጴጥሮስ የራሳቸውንና የአገራቸውን ጉዳይ ወደ እግዚአብሔር ሳይወረውሩ ኃላፊነታቸውን ሳይሸሹ «እምቢኝ አሻፈረኝ!» አሉ። በእምቢተኛነታቸውም የኢጣልያን ክርስቲያንነትና ሥልጡንነት ፈተና ውስጥ ከተቱት። በእምቢተኛነታቸው ለእግዚአብሔር ለአምላከ ጽድቅ ያላቸውን ፍቅርና ክብር፤ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ጽናት፤ ለጨበጡት መስቀል ለመስዋዕትነት ምልክቱ ያላቸውን ስሜት ለአገራቸውና ለወገናቸውም ያላቸውን ታማኝነት አረጋገጡ። በመትረየስ ተደበደቡ።ዛሬ በዚህ ድርጊት ኢትዮጵያ ትኮራለች፤ ኢጣልያ ታፍራለች።
ጴጥሮሳዊነት የምለው የአቡነ ጴጥሮስን ዓይነት የእምቢተኛነት መንፈስ ነው። ጴጥሮሳዊነት በእግዚአብሔር አምላክ ጽድቅነት (ጽድቅ እውነት ማለት ነው) አምኖ የራስንም ኃላፊነት ከነውጤቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ መቀበል ነው። ጴጥሮሳዊነት በመሠረቱ መንፈሳዊነት በመሆኑ የሚመካበት ኃይል መንፈሳዊ እንጂ አካላዊ ወይም ጠመንጃ አይደለም። የጴጥሮሳዊነትም ዓላማ አስፈላጊ ከሆነ ለእምነቱ ለመሞት እንጂ ለመግደል አይደለም። ሰው ሲገደል የሚቀረው በድን ሬሣ ነው። ገዳዩም ከዚያ ከበድን ሬሣ የተለየ፤ ወይም ከተጠቀመበት የመግደያ መሣሪያ የማይለይ ነው። በአካል ደረጃ ገዳይና የተገዳዩ ሬሣ ቢመሳሰሉም፣ በመንፈስ ደረጃ የማይገናኙ ናቸው። እውነትን እገድላለሁ ብሎ የሰውን ሕይወት የሚያጠፋ በድን፣ እውነትና የሰው ደም እንዳስደነበረውና እንዳቃዠው ከበድንነት ወደበድንነት ይተላለፋል። ለእውነት የተገደለው ግን እውነትን በሕይወቱ መስዋዕትነት አዳብሮና አፋፍቶ ያልፋል። መግደል የአእምሮ በሽተኞችና የልጆች ጨዋታ ነው። ለመሞት መዘጋጀትና ለእውነትና ለእምነት መሞት ግን ወኔን ይጠይቃል፤ መንፈሳዊ ወኔን።
የኢትዮጵያ ባህል ለጠመንጃ የሚሰጠው ክብር ከራሱ ከሰውነት ክብሩ ጋር የተያያዘ ነው። ጠመንጃ ኃይል ይሆናል፤ አያስጠቃም። ገዳይ ጀግና ተብሎ ይከበራል። ሠርቶ ከመክበር ያንድ መኳንንት ሎሌ ሆኖ ጠመንጃ መሸከም ያስከብር ነበር፤ አሁንም አልቀረም። ይህንን ክፉና የማይጠቅም ባህል በጴጥሮሳዊነት መለወጥ ያስፈልገናል። በጠመንጃ ኃይል ከመተማመን በመንፈሳችን ኃይል መተማመኑ ወደተሻለ የእድገት ጎዳና ያመራናል። ለጠመንጃ የማይበገር መንፈስ በመሀከላችን ሲዳብር ከጠመንጃ ይልቅ በጽሑፍ፤ ከጥይት ይልቅ በቃላት ቅራኔዎቻችንን ማለሳለሱ ወደሥልጣኔ ፈር ውስጥ ያስገባናል። እምነታችን የቱንም ያህል ቢለያይ፣ ሃሳባችን ቢራራቅና መግባባት የሚያስቸግር ቢሆንም ሃሳቦቻችን ይጋጩ፣ይፋጩ እንጂ እኛ ጎራዴ መዝዘን ወይም ጠመንጃ አጉርሰን፣ ከአእምሮና ከመንፈስ ደረጃ ወደእንሰሳነት ደረጃ ወርደን ስንጋደል እምነቶቻችንና አሳቦቻችን ያደፍጣሉ እንጂ እንደማይሞቱ ይግባን።
ጴጥሮሳዊነት በአቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት ላይ የተመሠረተ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው፣ የተሰውበትም ዋና ምክንያት የኢትዮጵያ ነፃነት በመሆኑ ጴጥሮሳዊነትን ኢትዮጵያዊነት እንበለው እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሰው ልጆች ታሪክ በየአገሩ የሚያሳየው የሰው መንፈስ ነው። ስለዚህም ጴጥሮሳዊነት ዓለም አቀፋዊነት ባሕርይም አለው።
እውነትን ክዶ በውሸት ከመኖር ለእውነት ሞቶ እውነትን ሕያው ማድረግ የመንፈስ ዕርገት ነው። እንዲህ ዓይነቱ የመንፈስ ዕርገት የሚቀጥለውን ትውልድ ከእንሰሳት ደረጃ ወደላቀ የሰውነት ደረጃ ያነሣዋል። ከዚህ የተሻለ ውርስ አይኖርም። ጠመንጃ የያዘ ሁልጊዜም እንዲያሸንፈን መንፈሳችን ከተዳከመ ለጠመንጃ መድኃኒቱ ጠመንጃን ማንሣት እየሆነ እስከዛሬ እንደነበረው ወደፊትም ይቀጥላል። ይህንን የቁልቁለት መንገድ በጴጥሮሳዊነት ልናቆመውና ወደዕርገት እንዲያመራን ማድረግ እንችላለን። የእያንዳንዳችንን ውሳኔ የሚጠይቅ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከየት ወዴት? ገጽ 42-43
ተጻፈ 1986 ዓ.ም.

Ethiopian migrants tell of torture and rape in Yemen

Ethiopian High Court’s Institutional capacity, bleak: Clients


ESAT News
July 30, 2013
 Clients of the Ethiopian High Court have said that the institutional capacity of the court is at a critical state. They said the Court has moved down both in quality and capacity terms. They also said that the current High Court has been worse than the former regime’s Kebele Courts.
The Ethiopian High Court deals with financial and material cases and at times also courts criminal cases. The Court has no proper sanitation and electric generators that serve when power blackouts occur affecting the legal processes.
Some of the other problems that the clients stated are: giving verdict before evidences were sufficiently gathered, cancelling impounding orders and helping suspects to sell their properties and flee, selecting and removing files from charge files, some staffers of the Court, who also act as brokers, influencing judges on their decisions, failure of judges to pay attention and seriously  read charge files, and attempting to establish contact with clients involved in cases that involve huge sums of money.  Judges have also complained that they are given too many cases and files to handle and stated that they sought the Administration to appoint additional human resource.
In related news, it has been leant that a serious problem is being observed in the purchase of land in Addis Abeba. Many people that have purchased and retained a map have found themselves in conflict with other people that presented similar rights of possession.

አሣ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል 2)


July 31, 2013
ናደዉ፣ ከዋሽንግቶን ዲሲ
ባለፈዉ ሳምንት “እስቲ ቂማችን ጥቂት እናቆየዉ” በሚለዉ በዚህ አምድ የመጀመርያዉ ፅሁፌ በዳያስፖራዉ ዉስጥ ሰርገዉ ስለገቡ የወያኔ ጨካኝ አገዛዝ አባሎችና ሆድአደር ጀሌዎቻቸዉ ጥቂት በጣም ጥቂት ለማለት ሞክሬአለሁ።፦ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ ሆነና፣ ተላላኪዎቻቸዉ ተደፈርን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸዉን አንድ ወዳጄ ነገረኝ። ላለፉት አስራ አምስት አመታት ያህል እጅግ የተካኑበትን የተቃዋሚዉ ወገን አመራሮችን በስም እየጠቀሱ ጥላሸት መቀባት ዳያስፖራዉን ለመከፋፈል በወያኔ በጀት ተመድቦላቸዉ በሚያሰራጩት አጉራ ዘለል ራዲዮኖቻቸዉ ሲያላዝኑ ዉለዉ አደሩ ማለትንም ሰማሁ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ በተጠቀሱት የወያኔ ተላላኪዎችና ሆድ አደሮች ዉስጣቸዉ ሆኖ ለረጅም ጊዜያት መረጃዎችን ሲሰበስብ በመቆየቱ እነሆ አሁን እንደ መንደርደሪያ አይነት ባለፈዉ ፅሁፍ ዉስጥ ነካ ነካ ለማድረግና ተጠንቀቁ ማንነታችሁን እናዉቃለን አይናችሁን ሸፍኑና እናሞኛችሁ ማለት ከእንግዲህ ወዲያ አይሰራም ተመቸን ብሎ ከወያኔ በሚከፈላችሁ የመንደር ራዲዮ ሠዉን መዘርጠጥ ይቁም ለማለት ብጫ ካርድ ለማሣየት ሞክሬአለሁ፥ ይህ ግን እንደሞኝነት መቆጠሩን በዚህ ሰሞን ይህ ሆድ አደር መቶ አለቃ ያለፈዉን ፅሁፍ በመጥቀስ እንዳበደ ውሻ ግምታዊ ዘለፋውን ለማቅረብ መንገታገቱ ተመልክቻሁ፧Inside Washington Little Ethiopia
በዚህ ምክንያት የሆነዉን ሁሉ በማስጃ በተደገፈ ፅሁፍ ቁልጭ አድርጌ ለማቅረብ ወንኩ፧እኔ አሁንም አጠገባቸዉ ነኝ። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች እንገናኛለን። በሚገባም እንተዋወቃለን። ከአጋላጭ ፅሁፎቼ በኋላ በሕዝብ ፊት እዉነቱን በገሀድ ፍርጥ አድርጌ በራሳቸዉ ራዲዮ ላይ ከጋበዙኝ ለመቅረብ ዝግጁ ነኝ። ይህን ካልኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ዛሬዉ የአጋላጭ ትኩረት አቅጣጫዪ ልዉሰዳችሁ።
ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ ማነዉ? ምክትል የመቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ አሥመራ ከተማ ቃኘዉ ስቴሽን ይገኝ በነበረዉ የፖለቲካ መምሪያ ዉስጥ በካድሬነት ያገለግል የነበረ በዚያን ወቅት የሥራ ባልደረቦቹን መቆምያ መቀመጫ የሚያሳጣና ከፋፋይና ተንኮለኛ ስለነበር ከአጠቃላይ ባህርይው የተነሳ ትንኩሽ በሚል ቅፅል ስም የሚያዉቁት የሠራዊቱ አባሎች ዛሬ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ይገኛሉ።ከዚያ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘዉ በወቅቱ ከፍተኛ ፩ በሚባለዉ መስተዳድር የአራዳ የአኢወማ ሊቀመንበርና ካድሬ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በከፍተኛዉ መዝናኛ ክበብ እሱ በሚመጣበት ሰአት ብዙዎቻችን ወጣቶች ሹልክ ሹልክ እያልን ከቦታዉ የምንሰወርበትን የብሄራዊ ዉትድርና ጭፍን የምልመላን ሽሽት ወቅት አንደነበር ዛሬ ብዙዎቻችን በቁጭት እናስታዉሰዋለን፤ አሁን ደግሞ ይኸዉ ግለሰብ ማልያዉን ገልብጦ የሌላዉ ጨካኝ አምባገነን አገዛዝ ሰርጐ ገብ ተላላኪ መሆኑ ፧ቀደም ሲል ይህንን ግለሰብ የምናዉቀውን ብዙዎቻችንን አስገርሞናል።
ይህ ጓድ አይኑን በጨዉ አጥቦ ጅብ በማያዉቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንደሚባለዉ እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ መጣ።እኛም የሰፈሩ ወጣቶች የዛሬዎቹ ጎልማሶች አገኘነዉ አሁን ድረስ አንድ ጓደኛችን ባገኘዉ ቦታ ሁሉ ለዱላ ይጋበዝበታል እኛም ያለፈዉን እርሳዉ ብለን ገላጋይ መሆናችን አልቀረም። ያለፈዉ በደል ሳያንሰዉ አሁን ደግሞ ሌላ ቁማር ጀመረ፣ራዲዮ ጣቢያና ቤተክርስቲያን ከፈተ ።በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያዊነት ራዲዮ የሚልና ኡራኤል ቤተክርስቲያን፤ ራዲዮ ጣቢያዉን ራሱ ብቻዉን የሚያስተዳድረዉ ሲፈልግ የሚከፍተዉ ሲያሻዉ የሚዘጋዉ፤ ቤተክርስቲያኑንም እንዲሁ ቀዳሽ ቄስ ካገኘ አገኘ ካላገኘ ቅዳሴዉን በካሴት ያስነካዋል፧እሱ ማንን ፈርቶ አገሩ አሜሪካ አይደል!
እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ይሏችኋል ይህ ነዉ!ጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ ዛሬም አለ ! በተመሳሳይ ተግባር ላይ፧ ይህ የወያኔ ተላላኪ የዋሽንግተን ዲሲንና የአካባቢዉን ኢትዮጵያዊ ይቅርታ ካልጠየቀ በተጨበጠ ማስረጃ አርጩሜዬን ማንሳቴ እዉነት ሊሆን ነዉ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ላለፉት ሀያሁለት አመታት እንደመዥገር ተጣብቆበት ደሙን በመምጠጥ ላይ ያለውን ፋሽስታዊ አምባገነን አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ዜጎች በተለያየ አቅጣጫ በአንድነት ርብርብ በማድረግ ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ከእንደዚህ አይነት ሆድአደር እበላባይ ተርታ አጉራዘለል ግለሰብ ጋር እሰጥ አገባ መግጠሙ ደግ ባይሆንም የሱና የመሰሪ ጓደኞቹ አካሄድ በሕዝባዊዉ ትግል ላይ የሚያሳድረዉ ተፅእኖ ቀላል ባለመሆኑ ቀይ ካርድ ማሳየቱ ወቅቱ የሚጠይቀዉ ቁም ነገር ነዉ። ያለፈዉን የመንደርደርያ ፅሁፍ የተመለከቱ ወገኖች በተለይ ደግሞ በዚህ ግለሰብ ጥቃት የደረሰባቸው ኢትዮጵያዉያኖች ሀብት ንብረታቸውን ተቀምተዉ ያዘኑትን ጨምሮ ራዲዮ ጣቢያው ሲመሠረት አብረዉ አጋር የነበሩና በራዲዮኑ ስም የሚሰራዉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን የማፍረስ ደባና የሚዘረፈዉ የየዋህ አገር ወዳዶች ገንዘብና ንብረት የተነሳ ጥለዉት የሄዱት አባሎቹ የሰጡት አጋላጭ የድምፅና የፅሁፍ ማስረጃ በጄ ገብቷል።ለዚህ ነው የዛሬዉን ርእሴን የመረጥኩበት ሁለተኛዉ ምክኒያቴ፧የንጉሴ ወልደማርያም ሀገር ፍቅር ራዲዮ፣የመቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ ኢትዮጵያዊነት ራዲዮ፧የፀሀዬ ደባልቄ ሰላም ራዲዬ፤ልዩ ራዲዮና የዮሴፍ ግዛቸዉ አንዲት ኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያዎች በዋሽንግተንና አካባቢዉ የሚገኘዉን ኢትዮጵያዊ ከወያኔ አምባገነን ስርዓት ምስረታ ማግሥት ጀምሮ ገንዘቡን በመዝረፍና የትግል ተነሳሽነት ወኔዉን በማኰላሸት የጨካኙን የወያኔ አምባገነን ሥርዓትእድሜ እያራዘሙለት ይገኛሉ።
በዚህ ጽሁፍ መደምደሚያ ላይ አንባቢዎቼን ላስገነዝብ የምፈልገዉ አንድ ቁምነገር ፧አለ ፧ይኸዉም መቶ አለቃዉ የወያኔን አምባገነን አገዛዝሥርአት ከማዉገዙ ጎን ለጎን የሚያስተላልፋቸዉ ከፋፋይ የተቃዋሚ መሪዎችንና ታዋቂ አገር ወዳድ ግለሰቦችን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጐደለዉ በአጉራዘለል ቋንቋ መዝለፍ ጥቅሙ ለማን ነዉ? የማንን ጡንቻ ነዉ የሚያፈረጥመዉ የየትኛዉስ የትግል ጎራ ነዉ የሚኮስሰዉ?! ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያኖች የህሊና ፍርድ እተወዋለሁ!የዚህ ግብዝ ማንነት የቆመለትንም አላማና ተልእኮ ማወቅ ያስችላል። ገንዘብ ሲያጣም ሆነ ሲያገኝም የሚያሳብደዉን የጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉን አይን ያወጣ መሠሪ ከፋፋይ እንቅስቃሴዎች ከነማስረጃዎቼ በሚቀጥለዉ ፅሁፊ እመለስበታለሁ ፅሁፎቹም የሚያተኩሩት በሚከተሉት ነጥቦች ዙርያ ይሆናል፦
፩ኛ፦ቤተክርስቲያን በመክፈት ስለሚያገኘዉ ጥቅምና በዚህ ዙርያ የፈፀማቸዉን አስነዋሪ ተግባራት፣
፪ኛ፦ከስራ ጓደኞቹ ጋር በመሆን የተሰበሰበ የዕቁብ ገንዘብ ይዞ ስለመሰወሩ
፫ኛ፦በደርግ ዘመን በወገኖቻችን ላይ ያደርስ ስለነበረዉ በደል
፬ኛ፦በሚያሰራጨዉ ራዲዮ ላይ በአንድ ወቅት ሼክ መሐመድ አላሙህዲንን በመዝለፉ ምክንያት ስለተመሰረተበት ክስና አማላጅ ልኮና እግር ላይ ወድቆ ይቅርታ ስለመጠየቁ
፭ኛ፦ደራሽ ግብረሀይል ብለዉ በድርቅ በተጐዱ ወገኖቻችን ስም የተሰበሰበዉን ከሁለት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ከንጉሤ ወልደማርያምጋርበመሆንዘርፈዉስለተሰወሩት ገንዘብ
፮ኛ፦በቅንጅት መሪዎች መፈታት ማግስት ኢንጅነር ኃይሉ ሻወልን በማጥመድ ይህንን ተትሎ ከመሠል ጓደኞቹ ጋር በመሆን ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት የተጫወተዉ ከፍተኛ ሚና
፯ኛ፦ቀደም ሲል ከዋሽንግተን ዲሲ በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፈዉን የቪኦኤ ራዲዮ ጣቢያ ለማዘጋት የተቃዉሞ ሰልፍ በማደራጀት ስላስተባበዉ እንቅስቃሴ
፰ኛ፦እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ከቅርብ አመታት ወዲህ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ሕዝቡን ለትግል በማነሳሳት ላይ የሚገኙት የኢሕአፖ ወጣቶች ክንፍ ዉስጥ ሰርጎ በመግባት ከእናት ድርጅታቸዉ ለመነጠል የሚያደርገዉን እንቅስቃሴና መሰል ወያኔያዊ ተልዕዎቹን በዝርዝር እንመለከታለን
ዉድ ለአንባቢዎች፦ እነዚህን የመሳሰሉ የዳያስፖራውን አንድነትና ትግል በወያኔ የምፅዋት ገንዘብ ሽባ የሚያደርጉትን አረመኔ ሆድ አደር ተላላኪዎች በቃችሁ እንበላቸዉ!!!
ክፍል ፫ ይቀጥላል፦ ናደዉ።

Tuesday, July 30, 2013

Ginbot7 Popular Force Song (Ethiopia)

የሀዘን መግለጫ፣ አንድነት ፓርቲ በቁርጥ ሰዓት ጀግናውን ኢትዮጵያ ልጅን በማጣቱ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል

July 30, 2013
ፍኖተ ነፃነት
አቶ ግርማ ወ/ሰንበት በ1984 ዓ.ም. መዐህድን በመመስረት፣ ህይወታቸው እስካለፈበት ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) የብሄራዊ ም/ቤት አመራር አባል በመሆን ታግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፓርቲያችን አንድነት ከፍተኛ አመራር ሰጭ በመሆን ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን ለማሳካት ግንባር ቀደም አርበኛ በመሆን ሲታገሉ የቆዩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ናቸው፡፡Ato-Girma-w-senbet
አንድነት ፓርቲ በቁርጥ ሰዓት ጀግናውን ኢትዮጵያ ልጅን በማጣቱ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል፡፡
የአቶ ግርማ ወ/ሰንበት የቀብር ስነስርዓት ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ 6 ሰዓት በሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን ስለሚፈፀም የአንድነት ፓርቲ አባላትም በስፍራው በመገኘት በክብር እንድንሸኛቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣሪ መፅናናቱን እንዲሰጣቸው እንመኛለን፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት

Comments

1 comments

Monday, July 29, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የወያኔን ቁንጮዎች ስጋት ላይ ጥሏል

የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የወያኔን ቁንጮዎች ስጋት ላይ ጥሏል

July 25, 2013
ህዝብን ለማስፈራራት በታቀደ መለኩ እንደተለመደው የወያኔ ባለስልጣናት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ እጅግ ስላሰጋቸው የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የሚከተለውን አስፍረዋል፣
የሰማያዊው ፓርቲ ጥቁር ተግባራት
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ያቀረባቸው ጥያቄዎች የተሰላፊዎች ጥንቅርና መሰረታዊ ዓላማ በእጅጉ አነጋጋሪ ለሆኑ ጉዳዮች መነሻና መንደርደሪያ ሆነውኛል።
ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ባለመስማማትና በልዩነት ራሳቸውን ያገለሉ፣ መርህ ይከበር በሚል ተሰባስበው የነበሩ ግለሰቦች የመሰረቱት ፓርቲ ነው፡፡ ወደ ኋላ ስንመለስም በ1997 ዓ.ም ቅንጅትን ከመሰረቱትና የከሸፈውን አመጽ በማስተባበርና በመምራት ከፊትና ከኋላ የነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀድሞውን ማንነታቸውን ሳይለቁ በአዲስ መልክና በአዲስ ኮፍያ ለመንቀሳቀስ እየሞከሩ ያሉ ናቸው፡፡
አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሕገ መንግስቱ በሰጠው መብት በሰላምና በሕጋዊ መንገድ ሕጉንና ስርዓቱን አሟልቶ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል፡፡ ሰማያዊም ፓርቲ ሆነ ሌሎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውጭ ከሚገኘው ጽንፈኛና አክራሪ ኃይል ጋር በመቀናጀት በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እናመጣለን በሚል ለረዥም ጊዜያት ውስጥ ውስጡን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም እውነቱን የተረዳው ሕዝብ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ይህንን ሊቀበላቸው አልፈቀደም፡፡
ከውጭ የአሸባሪው ግንቦት ሰባት ቴሌቪዥን ጣቢያ «ኢሳት» ባለፉት አመታትም ሆነ አሁን ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሕዝባዊ ሰልፍ አይነት እንዲካሄድ በዚህም ጠንካራ ጸረ-መንግስት እንቅስቃሴና አመጽ በአዲስ አበባና በክልሎች እንዲቀጣጠል፤ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆኑ፤ ሀገሪቷ ሰላሟ ደፍርሶ ወደ ሁከት፣ ብጥብጥና ስርዓተ አልበኛ ሁኔታ እንድታመራ፤ ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልጫሩትና ለማቀጣጠል ያለኮሱት እሳት የለም፡፡ አሁንም ሕዝቡ የተረጋጋ ሰላማዊ ሕይወቱን፣ የሀገሩን ሰላምና ደህንነት አጥብቆ የሚፈልግ በመሆኑ ይኸው እኩይ ሙከራቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ካለፈው አመት ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በርቀት ካለው ጽንፈኛው አክራሪ ሀይል ጋር በውስጣዊ ትስስር በመቀናጀት፤ አጀንዳ በመጋራት ሌላው የሴራ መንገድ አላዋጣቸው ሲል፤የሙስሊም ወንድሞቻችንን ትግል እንደግፋለን፤ ከጎናቸው እንሰለፋለን፤ መንግስት በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ ገብቷል፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ ወዘተ የሚሉ መፈክሮችን በአገር ውስጥ ደጋፊዎቻቸው በጋዜጦች በዌብ ሳይቶች (በተለይም በአረቡ ዓለም መገናኛ ብዙሀንና ድረ ገጾች) በመጠቀም የፖለቲካ ድጋፋቸውን ለማስፋት በእጅጉ ደክመዋል፡፡አሁንም ገፍተውበታል፡፡
በአሜሪካና በሌሎች አገሮች የሚገኙ የጽንፈኛው ግንቦት ሰባት አክራሪ ቡድን አባላትና ደጋፊዎች በጅምላው የሙስሊሙን ጥያቄ እንደግፋለን በሚል ስብሰባ አካሂደዋል፣ ሰልፍ ጠርተዋል፡፡ ከሂጅራ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የገንዘብ እርዳታ አሰባስበዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ሸብ ረብ ሲያካሂዱ በኢትዮጵያ የአክራሪ እስልምና አደጋ መሰረት እየጣለና የሸረሪት ድሩን እያደራ መሆኑን እያወቁም ቢሆን ይክዳሉ፡፡
እነሱ የሚፈልጉት ምንም ሆነ ምን ከጎናቸው ተሰልፎ ኢሕአዴግን የሚጥል ሀይል ማበራከት በሚለው የጨለማ አስተሳሰብ የተቃኘ ነው፡፡ ስለዚህም ጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች በየሳምንቱ የዓርብ ጁምአ ጸሎት፤ለስግደት በወጣው ሕዝበ ሙስሊም መካከል መፈክር በማሰማትና በማስተጋባት ሲያካሂዱት የነበረውን እንቅስቃሴ ተቃዋሚው ሀይል አይኑን ጨፍኖ ሕጋዊ ጥያቄ ነው በማለት ድጋፉን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህንኑ አንድነት፣ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በአይዞአችሁ ባይነት እያጋፈሩና ስፖንሰር እያደረጉት ይገኛሉ፡፡ ጉዳዩ ኢሕአዴግን የመደገፍ ወይንም ያለመደገፍ ጉዳይ ሳይሆን የአክራሪ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መከሰት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ሕልውናና የደህንነት ጉዳይ መሆኑን ከጥላቻ ወጥቶ ማስተዋል ያልቻለ ተቃዋሚ ይሏል ይህ ነው።
መንግስትና የኢትዮጵያ ሕዝብ የችግሩን መሰረታዊነትና አሳሳቢነት በውል የተረዳው በመሆኑ ይህንን አደጋ ለመቅረፍ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፣ ውጤታማም ሆነዋል፡፡ ምንም እንኳ ሰማያዊ ፓርቲ ያካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ ለሌሎች ጸረ ሰላም ኃይሎች አጀንዳ ማራመጃነትና መጠቀሚያነት ያገለገለ ቢሆንም። ሁከትና ብጥብጥ ሳይነሳ፤ በትዕግስት ማስጨረሱ የመንግስትን ብስለት በገሀድ ያረጋግጣል፡፡
ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ የወሰደው ጽንፈኛ ተቃዋሚ በድርጊቱ በመግፋት በክልሎችም ሰልፉን እያስተባበረ ይገኛል፡፡ መድረክ በመቀሌ ሰልፍ ለማድረግ ተከለከልኩ ሲል አንድነት ደግሞ ሁለት ወር የሚዘልቅ ሰልፍ በየክልሉ ለማድረግ ፕሮግራም አውጥቷል፡፡ የግብፆች እቅድ፤በአገር ውስጥ ተቃዋሚ በመጠቀምና በገንዘብ በመርዳት መንግስትን ማዳከም፤መወጠር የሚለው ስትራቴጂያቸው በገሀድ ነፍስ ሲዘራ እያየን ነው ማለት ነው፡፡ በመሰረቱ ሀገር በስራ እንጂ በሰልፍና በጩኸት አትለወጥም፣ አታድግምም፡፡ የውጭ ሀይሎች ተላላኪና መሳሪያ መሆን፤ የሀገርን ልማትና እድገት ለማጨናገፍ በፖለቲካ ሽፋን መንቀሳቀስ በሀገር ላይ የሚፈጸም ከባድ ወንጀል ነው፡፡ በሰማያዊው ፓርቲ ሰልፍ ላይ የታየው የሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት ብቻ ሳይሆኑ በአብዛኛው ለአክራሪዎች ወግኖ የቆመው ኃይል ነው፡፡ይህም ሰማያዊው ፓርቲ አስቀድሞ ውስጥ ውስጡን የማስተባበር ስራ መስራቱን በገሀድ ያረጋግጣል፡፡ መካከለኛ እድሜ ላይ ያሉና አዛውንቶች ጭርሱንም በሰልፍ ላይ የሉም ማለት ይቻላል፡፡
የሰልፈኛው ቁጥር አናሳ ከመሆኑ አንጻር ያን ያህልም ግምት የሚሰጠው እንዳልሆነ በግልጽ የሚታወቅ ቢሆንም፣ «ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ» ዓይነት ተረት ሆነና 100 ሺ ሰው ሰልፍ ወጥቷል ሲሉ የሰማያዊ ፓርቲ ኃላፊ ከእውነታው የተጣላ መግለጫ ለተለያዩ ሚዲያዎች ሰጡ፡፡ ኢትዮ ምሕዳር ጋዜጣም ይህንኑ በማስተጋባት ይሁን በራሱ ስሜት ተነሳስቶ እንደሆነ አይታወቅም በመጀመሪያ ገጹ ላይ «100 ሺ ሰዎች ሰልፍ ወጡ» ሲል ግነቱን በመድገም ዘገባ አቅርቧል፡፡ መልእክቱ አያሻማም፣ ለቀጣዩ ሰልፍ ሰዎች እንዲሰናዱ በኋላም ብዙ መቶ ሺዎች ወጡ ለማለት እንዲመች የተዘጋጀ የቅድመ ፕሮፖጋንዳ ስራ ወይም የቅስቀሳ ማስታወቂያ መሆኑ ነው፡፡
ሌሎቹም የውስጥና የውጭ ሚዲያዎች ከ1997 በኋላ የነበረው ፍርሃት ተሰበረ በሚል በመቶ ሺዎች ሰልፍ ወጡ፤ መንግስት በሶስት ወራት ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ ካልሰጠ ተቃውሞውና ሰልፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ተቃዋሚውም የበለጡ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማድረግ እቅድ እያወጣ ነው፣ ተባብሮ እየሰራ ነው የሚሉ ዘገባዎችንም አንብበናል፡፡
ለዚሁም ተግባራዊነት አሜሪካና አውሮፓ ከሚገኙ አክራሪ ተቃዋሚ ሀይሎች ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እየተካሄደና ከወዲሁም ለመንቀሳቀስና ለማስተባበሪያ የሚሆን ገንዘብ በተለያዩ ሽፋኖች ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን አንዳንድ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በቀጣይም መሰል የተቃውሞ ሰልፎችንና የአደባባይ ስብሰባዎችን ለማደራጀት እንደሚንቀሳቀሱ እየገለጹ ይገኛሉ።
የአረቡ ዓለም ዓይነት አብዮት በመፍጠር በሁከትና በትርምስ መንግስትን በኃይል ለመጣል ይቻላል ብለውም ዕምነት ይዘዋል። ይህ ግን ኢ-ሕገመንግሥ ታዊና ሕገወጥ ከመሆኑም በላይ የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሊያስተናግደው የማይችል ከንቱ ምኞት ከመሆን የዘለለ አይሆንም።፡፡ እነሱ እንዳሰቡት ሕብረተሰቡ የስውር ሴራቸውና የአመጻቸው ተባባሪ ይሆናል ተብሎም ጭራሽ አይታሰብም። በዚህ ዓይነቱ ድርጊት ጀርባ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የእነማን እጅ አለ? የነማንን ጥቅም ለማስከበርና ዓላማ ለማሳካት ነው ይህ ሁሉ እየታሰበ ያለው? ለዚህ ዓላማ መሳካት ሲባልስ በተለያየ መንገድ ከውጭ የሚገባ ስውር ድጋፍ የለም ወይ? የተለያዩ ክፍተቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የሚራወጡ የተለያዩ የውጭና የውስጥ ኃይሎች የሉም ወይ? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች አንስቶ በሚገባ መፈተሽ ተገቢ ይሆናል። የመንግሥትን ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በመፍራት ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ በመንግስትም ሆነ በግል የገንዘብ ተቋማት በኩል ግዙፍ ገንዘብ በቀጥታ አይልኩም፡፡ ሽብርተኞች በውጭው ዓለም እንደሚያደርጉት ሁሉ እነዚህም ጨዋታውን የሚያካሂዱትና ገንዘብ የሚያስገቡት ሕጋዊ ባልሆኑ የተለያዩ ስውር መንገዶች ነው፡፡
ይህ ሁሉ ደፋ ቀና በእርግጥ በዚህች አገር የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ሳይሆን የሀገሪቷን ሰላም በማደፍረስ ወደ ሁካታና ትርምስ ማዕከልነት ለመለወጥ በዚህም ጥፋትና ውድመት መካከል በሚፈጠር የመርፌ ቀዳዳ በሚያህል ክፍተት ተሽሎክሉኮ በሕገወጥነትና በኃይል ሥልጣን መጨበጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የቀን ቅዥታቸው ግን በምንም መንገድ ዳር የሚደርስ አይሆንም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከጀርባ ሆነው በፋይናንስ በመርዳት ለሚያደርጉት ርብርብ ውስብስቡን ገጽታቸውን ስለሚረዳው ፈጽሞ አይንበረከክም፡፡
የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ግንባታና ሌሎችን የተጀመሩ ፈጣን የልማት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚራወጡት በተቃዋሚነት ስም ያሉ ሰማያዊ ፓርቲን የመሳሰሉና ሌሎች የሃይማኖትና የፖለቲካ ጽንፈኞች እንቅስቃሴ በአንዳንድ የውጭ ሀይሎች ስለላና መረጃ እንዲሁም ቀጥተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ሊታገዙ እንደሚችሉ መገመት ከእውነታው የራቀ አይሆንም። ይህን ለማለት የሚያስደፍረውም በአቋም ደረጃ እያራመዱት ያለውና በተግባርም እንተረጉመዋለን የሚሉት ሁሉ ያለው ተመሳሳይነት ነው። የሰማያዊ ፓርቲ፣የአንድነትም ሆነ የመድረክ ሽር ጉድ ለሰላም፣ለዕድገት፣ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መስፈን ሳይሆን በአቋራጭ ራሳቸውን ለሥልጣን ለማብቃት የሚያደርጉት የህልም እሩጫ ነው።
ለዚህም ሕዝቡን ለማነሳሳት፣በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ስም መነገድ፤የሕዝብ ስሜትን ይቀሰቅስልናል ብለው የሚያስቡትን የተዘጋና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውን አጀንዳ ሁሉ ከተቀበረበት አውጥቶ የሌለ ሕይወት ለመስጠት አቧራ ማስነሳት፣ በአሸባሪነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በነጻ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉ ሰዎችንና ቀደም ብሎም የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸውን በተመለከተ ከፍርድ ቤት ይልቅ ራሳቸውን ፈራጅ አድርገው በመሰየም ይፈቱ ማለትና በዚህም አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን መደገፍ ነው ስራየ ብለው የያዙት፡፡
ታላቅ የሆነ ሀገራዊ ጉዳይ እያለ ያንን ለማሰናከልና ለውጭ ሀይሎች መሳሪያ በመሆን ሕዝቡን ለመከፋፈል መሮጣቸው ማንነታቸውን ይበልጥ አጋልጦታል፡፡ ማንም በዚህ የሚዘናጋና የሚታለል አይኖርም፡፡ ጥሪያቸውም ሆነ ቅስቀሳቸው ተቀባይነት የለውም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነትና የመድረክ ጥቁር ተግባራት ሀገሪቷን ወደ ጥፋት አቅጣጫ ለመውሰድ ያነጣጠረ እንጂ ለሕዝብ ጥቅምና ክብር ከማሰብ የመነጨ አይደለም፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ግን የታሪክና የትውልድ ተጠያቂነትም እንደሚኖርባቸው ጠንቅቀው ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

Wednesday, July 24, 2013

“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ” ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?



haile gebreselasse
የዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር ጦርነት በማካሄድ ለውጥ ማስመዝገበ መቻላቸውን አስምሮበታል።
“የባለ ራዕዩ መሪ” አቶ መለስ ገድል ለመዘከር በተዘጋጀ ቅንብር ላይ  በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ የታየው ሃይሌ “አሁን የት ነው ያለነው?” በማለት ጠይቆ “አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ለማግኘት ነው የምንጋፋው? አውሮፓ ሄደን እዛው ለመቅረት ነው…” በማለት ስደትን መርጠው ከአገራቸው የሚወጡትን ሸርድዶ አልፏል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለስደት የሚዳርግ ጉዳይ የለም ወደ ማለት አዝምሞ ተናግሯል። ሃይሌ ይህን ይበል እንጂ በተቃራኒው እስረኞች እንዲፈቱና የፖለቲካ እርቅ እንዲሰፍን እሰራለሁ ከሚሉት ፕሮፌሰር ይስሃቅ ጋር በሽምግልና እያገለገለ መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ የሚታው እስርና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች የሃይሌን አስተያየት “ለንብረት ዋስትና የሚከፈል የንግግር ቫት” በማለት አጣጥለውታል።
ከኤርትራ ጋር ከተደረገው በቀር በኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል ጦርነት እንዳልተካሔደ ኢህአዴግን የሰላም አባት አስመስሎ ሃይሌ አመልክቷል። በዚሁም ምክንያት ቀደም ሲል ለጦርነት ይውል የነበረው የአገሪቱ በጀት ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ዞሯል ብሏል። የኢህአዴግ ተወካይ መስሎ አስተያየት የሰጠው ሃይሌ “ይህ አሁን የታየው ለውጥ በአስርና አስራ አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ነው። አሁን ባለው አካሄድ ከአስር ዓመት በኋላ እንደርሳለን?” ሲል የራሱን ትንቢት አስቀምጧል።
ተቆራርጦ በሚቀርበው አስተያየት እነ ፕሮፌሰር እንድሪያስን በማጀብ ሃይሌ  በመዝገበ ቃላት ላይ ኢትዮጵያን “ረሃብ” በማለት የሚተረጉማት ቃል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግሯል። “ከሃያ ዓመት በኋላ” አለ ሃይሌ “በመዝገበ ቃላት ላይ የኢትዮጵያ ውርስ ትርጉም ሃብታም በሚል ይቀየራል” ብሏል።
“ድሮ ትረዱን ነበር፤ እናመሰግናለን። አሁን ደግሞ እንረዳችሀዋለን እንላቸዋለን” ሲል አውሮፓና አሜሪካን የመሳሰሉ ታላላቅ አገሮች የኢትዮጵያን እጅ እንደሚናፍቁ ሃይሌ ከምኞት ባለፈ ስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሯል። አገሪቱን ለሃያ አንድ ዓመታት ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ ባልገለጹበት ሁኔታ ሃይሌ ከአስር እስከ ሃያ ዓመት ኢትዮጵያ ሃብታም አገር እንደምትሆን መናገሩ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሊገባቸው እንዳልቻለ ብዙዎች እየገለጹ ነው።
“ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል” ሲል ኢህአዴግን የመከረው ሃይሌ የበታች ባለስልጣናት መንግስትን እንዳያሰድቡ መክሯል። “መንግስት ይህንን አድርጉ ላይል ይችላል” የሚለው ሃይሌ የበታች ባለስልጣኖች የሚፈጽሙት ሙስና “መንግስትን ያስወቅሰዋል” በሚል ተቆርቋሪነቱን በይፋ አስታውቋል። ዋናዎቹን የሙስና ተዋናዮች ነጻ በማውጣት የታች ባለስልጣኖችን “እያንገዋለለ” አሳጥቷቸዋል።
“… ለህሊናቸው ሲሉ እንደ መንግስት በማሰብ መስራት አለባቸው” ሲል ትዕዛዝ አዘል ምክርና ማሳሰቢያ ለበታች ባለስልጣናት ያስተላለፈው ሃይሌ የአስተያየቱ መነሻ ከኢህአዴግ ጋር የፈጠረው ዝምድና ውጤት እንደሆነ እየተነገረ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “ሃይሌ ሃብቱ እየበዛ ሲሄድና የተበደረው ገንዘብ ሲጨምር ኢህአዴግን ወክሎ መናገር ጀመረ” ብለዋል።
አትሌቶችን ሰብስቦ የአቶ መለሰን ሃዘን ሳግ በያዘው ድምጽ እያለቀሰ የገለጸው ሃይሌ ነፍሳቸውን ይማረውና በአቶ መለስ አይወደድም ነበር። በህይወት እያሉም በተደጋጋሚ ያናንቁት ነበር። ሃይሌን እንደሚያደንቁት ተጠይቀው አርቲስት ቻቺን በማሞገስ ጭራሹኑ እንደማያወቁት ዘለውት አልፈውት ነበር። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ለሃይሌ ቁብ እንደሌላቸው የሚያውቀው ሃይሌ ከአንድ ማስታወቂያ ሰራተኛ ልቆ በፕሮፓጋንዳ ተግባር ላይ መሰማራቱ በቅርብ ጓደኞቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ አድርጎታል።
በአዳማው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በመገኘት ውድ ሽልማቱን ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በማበርከት የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ የታየው ሃይሌ፤ በዚያው ጉባኤ ላይ አቶ መለስንና ኢህአዴግን ማሞገሱ በወቅቱ በርካታ አስተያየት እንዲሰነዘርበት ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ያነጋገራቸው እንዳሉት ሃይሌ ወደ ፖለቲካው መንደር በፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑን በማስረዳት የሚያውቁትንም ተናግረዋል።
ጣና ሃይቅ ዳርቻ ከልማት ባንክ በአርባ ሚሊዮን ብር የገዛውን ሆቴል ከሁለት ወር በኋላ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በትዕዛዝ እንደነጠቁት በታላቅ ቅሬታ ለህዝብ አስታውቆ የነበረው ሃይሌ የባህር ዳርን ቤተ መንግስት የመጠቅለል ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ነው የቅርብ ወዳጁ ለመረጃ አቀባያችንየተናገሩት።
በኦሜድላ ስፖርት ክለብ ውስጥ ሰራተኛ የነበሩትና ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሃይሌ ቅርብ ሰው “ሃይሌ ቤተመንግስትን ይወዳል። ኢትዮጵያንም የመምራት ህልም አለው” በማለት ጭራሽ ተሰምቶ በማያውቀው ጉዳይ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
የአማራ ክልል መንግስት ለሲድኒ ኦሊምፒክ ጀግኖች ግብዣ ባደረገበት ወቅት የባህር ዳር ቤተ መንግስት ጎብኝተው እንደነበር አስተያየት ሰጪው ያስታውሳሉ። ሃይሌ የጃንሆይን መኝታ ክፍል ከተመለከተ በኋላ አሰበ። ከአፍታ በኋላ አልጋቸው ላይ ተቀመጠ። አልጋውን ወደ ላይ ወደታች ካወዛወዘው በኋላ “… ይህንን ቤተ መንግስት…” በማለት እንደሚኖርበት መዛቱን አስታውሰው ተናግረዋል።
ሃይሌ ዝም ብሎ እንደማይናገር ያወሱት እኚሁ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሃይሌ ይህንኑ ህልሙን ተግባራዊ ለማድረግ ዘመቻ የጀመረ እንደሚመስላቸው አስታውቀዋል። በቀጣዩ 2005 ምርጫ ሃይሌ እንደሚሳተፍ በርግጠኛነት ተናግረዋል። ሃይሌ ሁለት ጊዜ በግል ፓርላማ ለመግባት እንደሚወዳደር ካስታወቀ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ከምርጫ ዘመቻ ማግለሉን መግለጹ ይታዋሳል።
ሃይሌ ፖለቲከኛ የመሆን የኖረ ህልም እንዳለው ያወሱት ባልደረባው ከተናገሩት በተቃራኒ ሃይሌ የፈለገውን መሆንና ማድረግ የግል ውሳኔው እንደሆነ የሚከራከሩለት አልጠፉም። ሃይሌ ሃብት አለው፣ ከፍተኛ ዝና ገንብቷል። ኢትዮጵያዊያን የማይረዱት እውቅናና ክብር በውጪው ዓለም እንዳለው የሚገልጹት ተከራካሪዎች “አንድ ሰው በተናገረ ቁጥር ለንግግሩ ቀንድና ጭራ መቀጠል ነውር ነው። ሰዎች የመሰላቸውን እንዳይናገሩም የሚገድብ ክፉ ልምድ ነው” ባይ ናቸው። “አያይዘውም ሃይሌ የኢህአዴግ አባል ቢሆን እንኳ አስገራሚ አይሆንም” በማለት ጠርዝ ደርሰው ይሟገታሉ።
በርካታ አትሌቶች የኦህዴድ አባላት እንደሆኑ የሚጠቁሙት እነዚህ የሃይሌ ተከራካሪዎች “ሃይሌ ኢህአዴግን ቢቀላቀል መነጋገሪያ የሚሆነው ጉዳይ ብአዴን ወይስ ኦህዴድ ይሆናል የሚለው ነው” ብለዋል። አርሲ የተወለደው ሃይሌ በሩጫ ከተሳካለት በኋላ በተለያዩ ጉዳዮችና መጠነኛ ግንባታ ወደ ባህር ዳር መጠጋጋቱ በትውልድ አካባቢው ተወላጆች ቅሬታ እንዳስነሳበት በተለያዩ ጊዚያቶች መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየው


July 24, 2013
ይህንን ርዕስ የመረጥኩት ያለምክንያት አይደለም፤ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ንፁሃን ዜጎችን በጠራራ ፀሐይ ሲያስጨፈጭፍ አገር ሲሸነሽኑና የአገር ሀብት ዘርፈው ሕዝብ ለሕዝብ ሆድና ጀርባ አድርገው ሲያበቁ ሌላ ማሊያና ሜዳሊያ አጥልቀው ሲመጡ ርችት ተኩሰን ስለምንቀበላቸው የጭቃ ውስጥ እሾሆች ጥቂት ለማለት ነው።
ጨካኙን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ከድተውና አውግዘው የሚመጡትን ግለሰቦች ከመቀበልም አልፎ የተቃዋሚው ጎራ ፓርቲ አመራር ያደርጋቸዋል። አንድ ሰሞን ከበሮአቸውን እንደልቅላቸዋለን ጥቂት ቆይተው ያፌዙብናል፣ ያላግጡብናል፣ ያላዝኑብናል ተመልሰው ጓዳ ጎድጓዳችን ፈትሸው፣ ሰልለው አሰልለው ወደ ጨካኝ ጓደኞቻቸው ቤት ከብዙ መረጃዎቻችን ጋር ይመለሳሉ።
ወያኔዎች በተመሳሳይ መልኩ የሕዝብን ትግል ለከርሣቸው ለውጠው ተቀበሉን ያሉዋቸውን የአንድ ሰሞን መበሸሸቂያ አድርገው እንደሸንኮራ መጥጠው ይተፏቸዋል፣ እንደሲጋራ ቁራጭ ሜዳ ላይ ይጥሏቸዋል፣ የውሃ ላይ ኩበት ያደርጓቸዋል። አቶ ልደቱ አያሌውና ሟቹ መለስ ዜናዊን ወገባቸው እስኪንቀጠቀጥ አጎንብሰው ይቅርታ የጠየቁትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አዛውንት እንደምሳሌ ብጠቅሳቸው ብዙዎች በሀሳቤ ይስማማሉ። እነዚህ ማፈሪያዎች ዛሬም አሉ በቴሌቪዥኑ መስታወት አይናቸውን በጨው አጥበው በተቃዋሚ ፓርቲ ስም ያላግጣሉ፣ እኛም ቂማችን ጥቂት አላቆየነውም፣ ጥቂቶቻችን ለይቅርታ ምክንያቶችን እንደረድርላቸዋለን። አዎ ዛሬም አይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ እያሉን ነው።
ዛሬም የሕዝብ ወገን ነን የምንለው የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅቶችና አገር ወዳድ ግለሰቦች ከስህተታችን አልተማርንም ዛሬም እነሱ ቅጥፈታቸውን አልተዉም፣ ቀጥለዋል። እኛ ግን ካሸለብንበት ኛ አልነቃንም። እና ለዚህ ነው እየደጋገምኩ ቂማችንን ትንሽ እንኳን እናቆየው ያልኩት። የይሉኝታ ትግል ትግል ሳይሆን ልፊያ ነው። መላፋት ደግሞ የመከረኛውን ወኛችን የሥቃይ ዘመን ያራዝመዋል። ልቀጥል – -
አፍቃሪ ኢህአዴግ የሆነው ንብረትነቱ የታጋይ አማረ አረጋዊ ሪፖርተር ጋዜጣ አዲስ አበባ ከተማ ሆኖ ከኢህአዴግ ሕወሓት ጀምሮ የደጋፊ ተቃዋሚ ተግባሩን እያከናወነ ይኸው 21 ዓመት ዘልቋል። ከተፈቀደለት ቀይ መስመር አለፍ ሲል የአለቆቹን ቁንጥጫ እያጣጣመ ዛሬም አለ። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ፤ እዚህ ጉያችን ውስጥ ተሸጉጦ ስለሚገኘው እንደብዙዎቹ ስደተኛ አቻዎቹ በባሌ ሳይሆን በቦሌ ካለቆቹ በጥንቃቄ መመሪያ ተሰጥቶት ስለተላከው ያውራምባ ድረ-ገጽ ባለቤት ታጋይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ነው። ይህ ያድዋ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እንደስደተኛ ጓደኞቹ የወያኔ ወከባና እንግልት በዛብኝ፣ ሕይወቴ ላይ አደጋ በማንዣበቡ የምወዳትን ሃገሬን ጥዬ መጣሁ ብሎ በሙያ ባልደረቦቹና በወያኔ ተጠቂ ወገኖች ትብብርና ድጋፍ በመጠየቁ ብዙዎቻችን ለቤት ኪራይና ለዕለት ጉርሱ ለተወሰኑ ወራት መደጎማችን አልቀረም። በተለያዩ ውጭ አገር በሚገኙ ሜዲያዎች እየቀረበ ከእንግዲህ ወዲያ እዚህ ሆኜ የወያኔን ፋሽስታዊ አምባገነን አገዛዝ እታገላለሁ አለን፣ የዳያስፖራው ማስ ሜዲያዎችም በተከታታይ ሰፊ የአየር ሽፋን ሰጥተውት ሰበከን፣ አደመጥነው፣ አዘንንለት።
የወያኔ ሰላይ ይሆናል የሚለው የብዙዎች አስተሳሰብ ላይ ብዥታን ፈጠረ። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ የሆነውን ኢሳት – የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጠጋ አለ። ይህን ተቋም ፈተሸው፣ እሱና አለቆቹ እንዳሰቡት ዘው ብሎ ለመግባት ግን አልቻለም። አቅም አጣ፤ አንዳንድ እንቅስቃሴዎቹ ጥርጣሬን መጫራቸው አልቀረም። በዚህም በማኩረፍ የራሱን ድረ-ገጽ አቋቁሞ ኢሳትንና መሰል የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎችን ለማፍረስ በግልጽ መንቀሳቀስ ጀመረ። በዚህ እኩይ ተልዕኮው ራሱን ማሳወቅ ናፈቀ፤ አዎ እርግጥ ነው ሊዋጋ የመጣው አምባገነኑን የሕወሓትን አገዛዝ ሳይሆን ተቃዋሚን ነበር። “ሰይጣን ሲያታልል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይጠቅሳል” እንዲሉ እሱም እንዲህ ሆነ። ከአዲስ አበባው ሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት ጋር በመሆን በራሱ ድረ-ገጽ ላይ “ሪፖርተር ቲቪ” የሚባል የቴሌቪዥን ስርጭት ማስተላለፍ ጀመረ። ይህ አካሄዱ ኢሳትን የማጥፋት አንዱ ተልዕኮው ነበር።
ሌሎችም ተመሳሳይ ተልዕኮ ያላቸውን የወያኔ ሜዲያዎችን ተቀላቀለ። በቨርጂኒያ የሚገኘውን ሠላም ሬዲዮን፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን ልዩ ሬዲዮንና ኢትዮጵያዊነት ሬዲዮዎች ጥቂቶቹ ናቸው። ወገኖቼ እንግዲህ እንዲህ ሆነላችሁ የዘንድሮ ጨዋታ። አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽና ከላይ የጠቀስኳቸው የወያኔ ሬዲዮዎች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው የዳያስፖራውን ችግር ለማኮላሸት የትግል አንድነቱን ለመስለብ መነሳታቸው እውነት ነው። ይህ አፍቃሪ ወያኔ ግለሰብ ዛሬ በገሃድ ያንድነት ኃይሎችን ለማጥፋት ከተነሱት ተቋማትና የዋህ ግለሰቦች ጋር ለመሥራት እንቅልፍ አጥቶ እያደረ ነው – ዛሬ።
ብዙዎች አካሄድህ አያምርም አስተካክል አሉት፤ ተልዕኮው ነውና አሻፈረኝ እምቢኝ አለ። ዳር ቆመው ተው አይሆንም “ከእባብ ዕንቁላል እርግብ እንዴት ትጠብቃላችሁ?” ያሉትን ብልህ ወገኖች ጆሮ የሚሰጣቸው ጠፋ። ዛሬ ግን ያሉት እውን ሆነ።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ይህን ማስታወሻ ስከትብ ያንድ የትግል ጓዱ አመጣጥና አካሄድ ትዝ አለኝ። አዎ ተመሳሳይነት ያለው የሕወሓት መልዕክተኛ ታጋይ ጋዜጠኛ ፀሐዬ ደባልቄ። ይህ ግለሰብ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረ (በደርግ አገዛዝ ዘመን ማለቴ ነው) በዚያን ዘመን ታታሪ ሠራተኛ በሚል ከማስታወቂያ ሚኒስቴሩ የጉርሻ ሽልማት እንደተበረከተለት ዛሬ በትዝብት የሚያስታውሱት የሙያ ባልደረቦቹ አጫወቱን። ዳሩ ምን ይሆናል ጥቂት እንኳን ሳይቆይ ባዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድ አባላቸው ሲዘዋወር ጥሎት የሄደው የወያኔ ሕወሓት ሰርጎ ገቦች የስም ዝርዝር የያዘ ዶኩመንት በደርግ የደህንነት ሠራተኞች እጅ ወደቀ። እዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉት በአጠቃላይ የትግራይ ተወላጆች ነበሩ።
በዝርዝሩ ውስጥ የጋዜጠኛ ፀሐዬ ደባልቀው ስም በመገኘቱ ደርግ ከነጓደኞቹ ለቃቅሞ ከርቸሌ ወረወረው፤ ኢህአዴግ በገባ ማግስት ከከርቸሌ ወጣ፣ ላደረገው አስተዋጽዖ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት ሥልጣን ድረስ የወያኔ አገዛዝ ሰጠው (ሾመው)። “የወያኔ ሥልጣን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው” እንደሚባለው በወያኔ ክፍፍል ወቅት የዛሬ 12 ዓመት ገደማ ይህ ሰው ራሱን በዋሽንግተን ዲሲ አገኘው – የፖለቲካ ጥገኛም ሆነ። የመኖሪያ ወረቀቱ ተፈቀደለት የስደተኞች ማመልከቻ በማዘጋጀት ሥራ (Case worker) ላይ ተሠማራ። ጥቂት ቆየና በቀጥታ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የወያኔ ኤምባሲ ውስጥ ትልቅ ባለሟል ሆነ። ከዚያም አልፎ በቨርጂኒያ በሚገኘው የሠላም ሬዲዮ ጣቢያ አዘጋጅና አቅራቢ ሆኖ እስከዛሬ ድረስ ወያኔያዊ አፍራሽ ተልዕኮውን ያካሂዳል። ዛሬ የዚህ ግለሰብ ወዳጅ በተመሳሳይ ወያኔን አውግዞና ጥገኝነት ጠይቆ የመኖሪያ ፈቃዱን አቀፈ፣ ታጋይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ። መተካካት ይሏችኋል ይሄ ነው።
አውራምባ ታይምስ የሚባለው ድረ-ገጽ ምን እየሠራ ነው? የባለቤቱስ ተልዕኮ ምንድነው? ከፊትና ከኋላው ያለውስ ማን ይሆን? እንደጋሪ ፈረስ የሚጎትታቸውስ የዋሆች እነማን ናቸው? የዚህን መሰሪ ተልዕኮ ፍርፋሪ የሚቀላውጡትስ እነማን ናቸው? እስቲ ትንሽ እንፈትሽ።
አውራምባ ታይምስ (ቁጥር 2 ሪፖርተር ጋዜጣ) በሚለው የሚያስማሙን ነጥቦችን ለግንዛቤ እንዲረዳ ልሞክር። ይህ የታጋይ ዳዊት ከበደ ከመግቢያዬ ላይ የጠቀስኳቸው በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የትግል አጋሮቹ ማለትም የሀገር ፍቅር ሬዲዮ፣ ልዩ ሬዲዮ፣ የኢትዮጵያዊነት ሬዲዮና ቨርጂኒያ የሚገኘው በታጋይ ፀሐዬ ደባልቄ የሚመራው ሰላም ሬዲዮ ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው የዳያስፖራውን ትግል ለማኮላሸት መንቀሳቀሳቸውን እያየን ነው። በጣም የሚገርመው ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው በአቶ ምርጫው ስንሻው ባለቤትነት የሚተዳደረው የኢትዮጵያዊነት ሬዲዮ ሲሆን፤ ይህ ራስ ወዳድ ግለሰብ በደርግ አገዛዝ ዘመን የቀበሌ ካድሬ የነበረ በወቅቱ በፈፀማቸው ድርጊቶች ብዙዎች ያዝኑበታል። ዛሬም በግል ሬዲዮ ጣቢያው የእነዚህን አፍራሽ የወያኔ ተላላኪዎች የሚተርፋቸውን ፍርፋሪ ለመለቃቀም እነዚህን የጥፋት መልዕክተኞች በሬዲዮው ላይ ለማቅረብ የከፋፋይነት ተግባሩን በብቃት እየተወጣ ነው። ይህ ግለሰብ ሃገራችን ኢትዮጵያ በከፍተኛ ድርቅ በተጠቃችበት ወቅት ማለትም በ2002 አካባቢ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የቀድሞው ኮንቬንሽን ሴንተር አዳራሽ ውስጥ እሱና የሀገር ፍቅር ሬዲዮ ባለቤት በቅንጅት ባቋቋሙት የገንዘብ ማሰባሰቢያ “ደራሽ ግብረ ኃይል” በሚል መጠሪያ በመጠቀም ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የተሰበሰበውን ከ200 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ሰብስበው ከዚያ ውስጥ በተወካያቸው አማካኝነት 200 መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር በወቅቱ ለወያኔ ይርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ስምዖን መቻሌ አስረክበው ቀሪውን ከመቶ ሺህ ዶላር በላይ የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ ይዘው በመጥፋታቸው የዋሽንግተን ነዋሪ ገንዘባችን ተበላ ብሎ ቢጮህ ሰሚ ማጣቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ይህም አልበቃው ብሎ በቅንጅት ፓርቲ እንቅስቃሴ ወቅት መሪዎቹ ከእስር በተፈቱ ማግስት የኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ጋሻ ጃግሬ በመሆን ለልዩነታቸው ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረገ ግለሰብ መሆኑ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገባ ይታወቃል። ግለሰቡ የጥቅም ሱሰኝነቱን ለመወጣት ሲል ብቻ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ እየገባ የሚፈጽማቸውን የክህደት እንቅስቃሴዎች በዚህ ድረ-ገጽ ማስፈሩን ለጊዜው ማቆየት ይገባልና ትቼዋለሁ።
ዋናው ቁም ነገር በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች እንደነዚህ ያሉ ሆድ አደር ግለሰቦችን በቃችሁ የምንላቸው መቼ ነው? ላለፉት 21 ዓመታት አታለውናል፣ ገንዘባችንን ዘርፈውናል፣ ጊዜያችንን አቃጥለዋል፣ አንድነታችንንና የትግል ስሜታችንን አኮላሽተውብናል፤ ዛሬ ደግሞ ወያኔ ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው በቡድን ተደራጅተው እንደመዥገር በብብታችን ውስጥ ተሸጉጠው ደማችንን እየመጠጡት ነው። እና ምን እናድርግ፣ እንዴት ለዚህ ችግር መፍትሔ እንፈልግ?!
ሰሞኑን ዘ-ሐበሻ በተባለው ድረ-ገጽ ላይ ከኢየሩሳሌም አርአያ የቀረበው ጥቆማ ሁኔታውን ገሃድ አድርጎታል። በዚህ ድረ-ገጽ ላይ የሰፈረውን አጋላጭ ማስረጃ ቃል በቃል ላስቀምጥና ፅሑፌን ላብቃ።

በረከት ስምዖን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርነት ከሚመራው ግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምዖን የሚመሩት የመንግሥት አካል በምሥጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ ባንድ ድረ-ገፅ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው ባገር ውስጥ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አለው፣ ከግንቦት 7 የኝዘብ ድጋፍ ይደረግለታል በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮች የፓርቲውን አመራሮች “ከሽብርተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት” ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ “ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚመራ ነው” በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ሕልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረጽዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከረበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ አገር ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ የፓርቲው ባለሥልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደላኩለት ምንጮች አጋለጡ። በመጀመሪያ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ)፣ በማስከተል 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምሥጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሠረት ጋዜጠኛው ለሕወሓት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።
“እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየው” ለምን?!!
  • አሰፋ ማሩና ወጣት ሽብሬ በጠራራ ፀሐይ በጥይት ተደብድበዋል፣
  • ከ200 በላይ ዜጎች በአደባባይ ባልሞ ተኳሽ አውሬዎች ተጨፍጭፈዋል፣
  • የአማራው ዜጋ እየተፈናቀለ ከነሕይወቱ ወደ ገደል ተጥሏል፣
  • የኦሮሞው ወገናችን ያገሪቱን እሥር ቤቶች አጣቧል፣
  • በዋልድባ ገዳም አባቶች እየተቀጠቀጡ እየተሰደዱ ነው፣
  • የሙስሊሙ ሕብረተሰብ እየተቀጠቀጠ በእሥር እየማቀቀ ነው፣
  • ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች በኢትዮ ኤርትራ ትርጉም የለሽ ጦርነት ተማግደዋል፣
  • ዛሬም ዜጎች በየእስር ቤቱ አይናቸው፣ ብልታቸው እና ጡታቸው በጉጠት እየተቀረጠፈ ነው፣ ሌላም ሌላም ብዙ እጅግ ግፍ ላለፉት 22 ዓመታት . . .
አዎ እስቲ ቂማችንን ትንሽ እንኳ እናቆየው፤ በራችንንም ገርበብ እናድርግ። ምጥንቃቅ አሉ ገዢዎቻችን – ጠንቀቅ ነው ደጉ!
- – - ይቀጥላል – - -
ከናደው

Sunday, July 21, 2013

በህገ ወጥ የዘመቻ እስር የሚሊዮኖች ድምፅ አይታጠፍም!!!


 ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በመጀመር በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን
ማንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና
ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት
እያስኬደው ይገኛል፡፡
አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ሀይል በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ
ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄዎቹ አስተጋቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው
ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ
እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ነው፡፡
በጎንደርና ደሴ ከተማ በ7/11/2005 ያደረግናቸው ሰላማዊ ሰልፎች ስርዓቱ ዘብ ቆሜለታለሁ እያለ በየዕለቱ ከሚያነበንበው ህገ-
መንግስት በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኝ አይነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሊደረግ የታቀደውን ሰላማዊ ሰልፍ
እንዲያውቅ የተቋቋመ የመንግስት ባለስልጣን እወቅልኝ ላለው አካል ለሰልፉ ሰላማዊነት አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ በደብዳቤ
ማሳወቅ አልያም ሰልፉን ለአንድ ሳምንት እንዲራዘም በቂና አሳማኝ ምክንያት በማቅረብ በደብዳቤ መጠየቅ ከአንድ ሃላፊነትና ህዝብን
የማስተዳደር ስልጣን ከወሰደ አካል የሚጠበቅ ቢሆንም በሁለቱ ከተሞች የሚገኙ ሃላፊዎች ግን ፈርመው ለተቀበሏቸው ደብዳቤዎች
ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡
ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን
አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ አዋክበዋል፡፡ ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የተለጠፉ የሰላማዊ
ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ
ከማድረጋቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን
ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡
በጥቂቱ ለመግለጽ የሞከርናቸውን መሰናክሎች በማለፍ በሁለቱ ከተሞችም ሕዝቡ በገፍ አደባባይ በመውጣት ፍጹም ሰላማዊነቱን
በጠበቀ መልኩ ጥያቄውን አስተጋብቶና ተቃውሞውን አሰምቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሷል፡፡ አንድነት ፓርቲም ለደሴና ለጎንደር ህዝብ
ያለውን ታላቅ አክብሮት በመግለጽ በሌሎች የአገሪቱ ከተሞች በቀጣይ ፕሮግራሙ በሚያደርጋቸው የተቃውሞ ሰልፎች ለሚገኙ ዜጎች
አርአያነታቸው የጎላ እንደሚሆን እምነቱን ይገልጻል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አንድነት በያዘው እቅድ መሰረት የጸረ ሽብር አዋጁ በህገ መንግስቱ እውቅና የተቸራቸውን መብቶችን
የሚጨፈልቅና ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መሰረዝ ይገባዋል የሚሉ ዜጎች ወደ ዋናው የፓርቲው በጽ/ቤት
በመምጣት የተቃውሞ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚጠይቅ ‹‹ከሚሊዮኖች ለምን አንዱ አይሆኑም›› የሚል በራሪ ወረቀት በሁሉም የአዲስ
አበባ ወረዳዎች ለማሰራጨት የተጀመረውን እንቅስቃሴ መታወቂያቸውን ለማሳየት በማይፈቅዱ ደህንነቶች ነን ባዮችና በፖሊስ ጥምረት
በሕገወጥነት እየተደናቀፈ መገኘቱ አሳዝኖናል፡፡
ፖሊስ የአንድ ፓርቲ ወገንተኛ ሳይሆን ህዝብን ማገልገልና ሁሉንም በህግ መነጽር መመልከት የሚገባው አካል ቢሆንም ሚዛናዊነትን
ባልጠበቀ ሁኔታ ህገ መንገስታዊ መብታችንን በመጠየቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የምናቀርበውን አቤቱታ ለማደናቀፍ መሞከሩና
አባላቶቻችንን እግር በእግር እየተከታተለ ለእስር መዳረጉን በቸልታ ለመመልከት አንፈቅድም፡፡
በራሪ ወረቀቱን መበተን ከጀመርንበት ደቂቃ ጀምሮ አባላቶቻችን እየታሰሩና ፍርድ ቤት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ፖሊስ ፍርድ ቤት
ባቀረባቸው ወጣቶች ላይም አንድነት የሚባል ፓርቲ መኖሩን አጣርቼ እስክመጣ የ10 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱና ፍርድ ቤቱም
የተጠየቀውን መፍቀዱ የምንገኝበት ሰዓት ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ እንድንገነዘብ የሚያደርግ ነው፡፡
በየክፍለ ከተማው የሚገኙ የፖሊስ ኮማንደሮች ከህግ አግባብ ውጪ በመንቀሳቀስ አባላቶቻችንን ማሰራቸውና በአንዳንዶቹም ላይ
አካላዊ ድብደባ ማድረሳቸው ነጻ የፍትህ ስርዓትና ተጠያቂነት ቢኖር በወንጀል የሚያስጠይቃቸው በሆነ ነበር፡፡ አንድነት በአባላቶቹናበእንቅስቃሴው ላይ የተከፈተውን ህገ ወጥ የፖሊስ ዘመቻ ለማስቆምና በደል ፈጻሚዎቹም በታሪክ፣ በህዝብና በህሊና ዳኝነት ይጠየቁ
ዘንድ ለማድረግና በድጋሚ የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ለመፈተሸ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመምራት ተዘጋጅቷል፡፡
ፓርቲው የሚደረጉበትን ህገ ወጥ የአፈና ድርጊቶች በመቋቋም የጸረ ሽብር አዋጁ እንዲሰረዝ እያሰባሰበ በሚገኘው የህዝብ ድምጽ
እንደሚገፋበት በድጋሚ በማረጋገጥ ይህንኑ አላማ ከግብ ለማድረስ መስዋዕትነት ለመክፈል የቆረጡ አባላቱንና ደጋፊዎቹን ስለ
ቁርጠኝነታቸውና ታማኝነታቸው ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅም እስከነፃነት ድረስ ይቀጥላል፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት)
ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
July 18, 2013

ብርቱ ሰው! (The Iron Man) (ከተመስገን ደሳለኝ)



ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ
…አራት ኪሎ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ ከጓደኞቼ ጋር የደራ ወግ በመያዜ፣ የእጅ ስልኬ የ‹‹መልስ ስጠኝ›› ጩኸቱን ደጋግሞ ሲያሰማ ልብ
አላልኩትም፤ እናም ጮኾ ጮኾ ሲጨርስ፣ እንደገና ይጀምራል፡፡ ይኼኔ ጥሪውን እንዳላስተዋልኩ የተረዳው ጓደኛዬ ወደ ስልኩ
ሲያመላክተኝ፣ ቁጥሩን አየሁት፤ አውቀዋለው፡፡ የእስክንድር ነጋ ባለቤት የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነው፤ አነሳሁት፡፡
‹‹በጣም ይቅርታ! ከሰዎች ጋር ጨዋታ ላይ ሆኜ ነው ያልሰማሁት…››
‹‹ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር፤ የት ነህ?››
‹‹ምነው? ምን ተፈጠረ?››
‹‹በስልክ አልነግርህም፤ መገናኘት አለብን››
‹‹እኔ አራት ኪሎ አካባቢ ነኝ››
‹‹ጥሩ! እኔም ፒያሳ ስለሆንኩ ‹ቲሩም ካፌ› እንገናኝ››
‹‹አሁኑኑ መጣሁ፡፡››
የሆነ ሆኖ የስልክ ንግግራችን ቢቋረጥም ድምጿ ከወትሮ የተለየ ስለሆነብኝ በእጅጉ ግራ ተጋባሁ፤ ምን አጋጠማት? እስክንድር ምን ሆነ?
መቼም ኢህአዴግ ‹‹አስተዳድረዋለሁ›› የሚለውን ህዝብ ከፋሽስቱ ጣሊያንም በከፋ ጭካኔ እያሰቃዩ መደሰትን መገለጫው አድርጎታል፤
ታዲያ ዛሬ ደግሞ ምን ፍጠሪ እያላት ይሆን? ጥቂት ጥያቄዎች በውስጤ ቢመላለሱም፣ ጓደኞቼን በአጭሩ ተሰናብቼ በፍጥነት ‹‹ቲሩም
ካፌ›› ደረስኩ፤ ቀድማኝ ስላገኘኋትም ወንበር ከመያዜ በፊት፡-
‹‹እስክንድር ከነበረበት ዞን ተቀይሯል!›› ስትለኝ በደንብ አልሰማኋት ኖሮ ‹‹ወደ ዝዋይ ተቀየረ›› ያለች መስሎኝ ደነገጥኩ፤ በሁኔታዬም
የተናገረችውን አለመረዳቴ ገባትና፡-
‹‹ወደ ሌላ ዞን ተቀይሯል›› ብላ ደገመችው፡፡ ኡፍ-ፍ… በእፎይታ ተንፍሼ ሳበቃም፣ ወንብር ከሳብኩ በኋላ ወዴት እንደተቀየረ ጠየኳት
‹‹ወደ ዞን ሁለት››
‹‹ማን ነገረሽ?››
‹‹ዛሬ አግኝቼው ነበር፤ ‹በጣም ስለምፈልገው፣ ነገ ምንም ጉዳይ ቢኖረው ይሰርዝና ይዘሽው ነይ› ብሎኛል፤ ከባድ ጉዳይ ከሌለህ ሄደን
እናግኘው›› አለችና መልሴን መጠበቅ ጀመረች፡፡ …ለጥቂት ደቀቃዎች ያህል በፀጥታ ከራሴ ጋር ተነጋገርኩ፡፡ ‹‹ከባድ ጉዳይ ከሌለህ…››
ያለችውን አስፈላጊ ስላልሆነ ችላ አልኩት፤ ምክንያቱም እስክንድር ነጋ ለምን እንደታሰረ እና ይህ ሁሉ መዓት ለምን እንደወረደበት ጠንቅቄ
አውቃለው፤ ታዲያ! ነገ እርሱን ከማግኘት የከበደ ምን አይነት ጉዳይ ሊኖረኝ ይችላል? ያልገባኝ ነገር ግን የቃሊቲ ኃላፊዎች ከቤተሰቡ
ውጪ ማንም እንዳይጠይቀው ከልክለውት እያለ እንዴት ብዬ ላገኘው እንድምችል ነው? ለደቂቃ ያህል በውስጤ ባስበውም መግቢያ
ቀዳዳ አልታይህ ስላለኝ ይህ እንዴት ሊሳካ እንደሚችል እርሷኑ መልሼ ስጠይቃት፣ በፈገግታ ተሞልታ፡-
‹‹ከነገ ጀምሮ ማንም ሰው እንዲጠይቀው ተፈቅዷል፤ ሆኖም ፍቃዱ ብዙ ላይቆይ ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለው ሌላ ሰው ከመስማቱ
በፊት መጀመሪያ አንተን ማግኘት ፈልጓል›› አለችና ምርጊት የሆነብኝን ስጋት ገፈፈችው፡፡ መሀል ፒያሳ ድንገት የወረደ-ታላቅ የምስራች! …አቤት! ጀግናዬ! እንዴት ናፍቆኝ ነበር? ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በህዳር ወር 2004 ዓ.ም ሲሆን፣ ያን ጊዜ ከታሰረ 45ኛ ቀኑ ነበር፡፡
ዛሬስ? በልቤ መቁጠር ጀመርኩ፤ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት… ድፍን አስራ ዘጠኝ ወር (አንድ ዓመት ከሰባት ወር) አልፎታል፡፡ …በመጨረሻም
ከስርዓቱ ተለዋዋጭ ባህሪ አኳያ በ‹‹አማኝነት›› እና በ‹‹መናፍቅነት›› መሀል ብዋልልም፣ ጠዋት ሁለት ሰዓት ቃሊቲ እንድንገናኝ
ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡
በቀጥታ ወደ ‹‹አሲምባ›› (መኖሪያ ቤቴ) አመራሁ፡፡
ከአንድ ቀን በፊት ደብረዘይት ሄደው የነበሩት ባልደረቦቼ ሙሉነህና ዳዊት በፍጥነት ወደ ‹‹አሲምባ›› እንዲመጡ በስልክ ነገሬያቸው
ሳበቃ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ነገን መናፈቅ ጀመርኩ፡፡ ኦ! እንዴት አይነት ግሩም ቀን ነው! ብቻዬን አወራለሁ፤ እስቃለሁ፡፡ እስክንድር
ሆይ! በአይነ ስጋ ልንተያይ የሰዓታት ዕድሜ ብቻ ቀርቶናል!!
…በኢትዮጵያ ምድር፣ በኢህአዴግ መንግስት ‹‹ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት›› እንዲከበር እና ስርዓቱ ከጠመንጃ ማምለክ ህግን ወደ
ማክበር ይመጣ ዘንድ የከፈለው መስዕዋትነት በአንድ መጣጥፍ ተዘርዝሮ እንደማያልቅ ለውጥ ፈላጊው ወገን ብቻ ሳይሆን፣ እንደ‹‹ክፉ
እንጀራ አባት›› ከስር-ስሩ እየተከተሉ በሾኬ የሚጥሉት እነበረከት ስምዖንም ያውቃሉ፡፡ በፍርድ ቤት የአስራ ስምንት ዓመት እስር
የተወሰነበትም ለ‹‹ጥፋተኝነቱ›› ማስረጃ ተግኝቶበት እንዳልሆነም ጨምረው ያውቃሉ፡፡ ሀገሬውም ያውቃል፡፡ እኔም አውቃለሁ፤ ወዳጄ
እስክንድር ንፁህ ነው፤ በተለይም ‹‹በህቡዕ ህገ-ወጥ ድርጅት መስርቶ ፀረ ህገ-መንግስት እንቅስቃሴ ሊያደርግ ሲል ደረስንበት›› ያሉት
ውንጀላ ፍፁም ሀሰት ለመሆኑ በነፍሴም በስጋዬም እምላለሁ፤ ዘመኔን ሙሉ እንዲህ አይነት ነጭ ውሸት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምክንያቴን
በአዲስ መስመር ልንገራችሁ፡፡
(ታሪኩ የሚጀምረው ግንቦት 22/2003 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት አካባቢ ስልክ ደውሎ የት እንዳለው ጠይቆኝ፣ በአስር ደቂቃ ውስጥ
ተገናኘተን ለምን እንደፈለገኝ ካስረዳኝ በኋላ ነው፤ እናም በዕለቱ የተነጋገርነውን እንደወረደ ላስቀምጠው)
‹‹ምን ታስባለህ?››
‹‹ስለምኑ?››
‹‹ስለአጠቃላይ ሁኔታው››
‹‹እስኬ! አልገባኝም?››
‹‹ከዚህ በኋላም ዝም ብለን እየፃፍን ነው መቀጠል ያለብን ብለህ ታስባለህ?››
‹‹ታዲያ! ሌላ ምን አማራጭ አለን?›› በአግራሞት ጠየኩት፡፡ ያሰበውን ዘርዝሮ ነገረኝ፡፡ …ለየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የማይወግን
የ‹ሲቪክ ማህበር› መስርተን ህዝቡ መብቱን እንዲጠይቅ ከመቀሰቀስ ጀምሮ ፓርላማው ህጋዊ ስላልሆነ ፈርሶ በአስቸኳይ (ሁሉንም
የፖለቲካ ድርጅቶች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚያሳትፍ) አዲስ ምርጫ እንዲደረግ የአደባባይ ስብሰባና ሰልፍ ማዘጋጀትና የመሳሰሉትን
እንቅስቃሴ መፍጠር እንደሚቻል ጆሮ-ገብ በሆነ ድምፁ አብራራልኝ፡፡ በተመስጦ አዳመጥኩት፡፡ እፁብ ድንቅ አሳብ!
በመጨረሻም በተግባራዊው እንቅስቃሴ ላይ ከተነጋገርን በኋላ፣ ኢህአዴግ ለውንጀላው ክፍተት እንዳያገኝ እያንዳንዷን ድርጊት በህጋዊ
መንገድ ብቻ እንዲሆን ጥንቃቄ ማድረግን ጨምሮ ስራችንን ለመጀመር የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከሀገር ውስጥም ሆነ ውጪ ካሉ
ኢትዮጵያውያን ሳንጠይቅ በጋራ ለመሸፈን ተስማምተን፣ መስራች አባል የሚሆኑትን ስድስት ሰዎች የማሰባሰቡ ስራ የእኔ ሆኖ (ይህንን
ሰበብ አድረገው ፍትህ ጋዜጣን ሊነጥቁን ስለሚችሉ እኔ በቀጥታ የቡድኑ አባል እንዳልሆን ያቀረበውን ስጋት ተቀብዬ) ከአራት ቀን በኋላ
ምስረታው እውን መሆን እንዳለበት ወስነን ተለያየን፡፡
በቀጠሮው ቀን እስክንድርና ስድስቱ ወጣቶች ተገናኝተው ስለጉዳዩ በስፋት አብራርቶላቸው፤ በሃሳቡ ከተስማሙ በኋላ እስክንድርን
ሰብሳቢ፣ የጋዜጣችንን ምክትል አዘጋጅ ሙሉነህ አያሌውን ም/ሰብሳቢ፣ ሪፖርተራችንን ዳዊት ታደሰን ፀሀፊ አድርገው መርጠው፣ በቃለ-
ጉባኤው ላይ ፈርመው ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ (በተሰበሰቡ ቁጥር በሁለት ኮፒ ቃለ-ጉባኤ ይያዛል፣ አንዱ እስክንድር ጋ፣ አንዱ እኔ ጋይቀመጣል) ደግመው ተገናኙ፤ ሰለሱ…፡፡ ከዚህ በኋላ እቅዱን የተመለከተ ዝርዝር መግለጫ በጋዜጣችን ላይ የሚወጣበት ቀን ተወሰነ፡፡
ሆኖም መግለጫው አርብ ከመውጣቱ በፊት ረቡዕ እስክንድር ‹‹የግንቦት ሰባት አባል እና የህዕቡ ድርጅት መስርተሃል›› በሚሉ ክሶች
ከደረዘን በሚልቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተከቦ ተያዘና ማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያ ታሰረ፡፡ መርማሪ ፖሊሶቹም የእምነት-ክህደት ቃሉን
ሲጠይቁት ህጋዊ የ‹‹ሲቪክ ማህበር›› ከስድስት ወጣቶች ጋር በመመስረት ላይ መሆኑን አስረድቶ ሲያበቃ የግንቦት ሰባት አባልም
ተባባሪም አለመሆኑን አፅንኦቶ ሰጥቶ ተናገረ፡፡ ምርመራውም ተጠናቆ ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ሲጀምር ሙሉነህና ዳዊት በመከላከያ
ምስክርነት ቀርበው ማህበሩን አብረው እንደመሰረቱ፣ ሃሳቡ የእስክንድር ብቻ ሳይሆን የእነርሱም መሆኑን ህዝብ በታደመበት ችሎት
መሰከሩ፤ ግና! ለ‹‹ካንጋሮ ፍርድ ቤት›› ከዕውነታው ይልቅ የእነበረከት ስምዖን ድራማ ይበልጣልና ሀቁን ሊቀበል አልወደደም፡፡ …በቃ!
እውነታውም የንፅህና ማረጋገጫውም ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም (አሁን ወደ ርዕሰ-ጉዳያችን እንመለስ)
መንግዶች ሁሉ ወደ ቃሊቲ…
እሁድ ጠዋት
ከጋዜጠኛ ሰርካለም ቀድመን በመድረሳችን እንደ ሊማሊሞ ዳገት ጠመዝማዛና ረጅም የሆነውን የእስረኛ ጠያቂዎች ሰለፍ ተቀላቅልን
ተራችንን መጠበቅ ጀመርን፤ ከድፍን ሀምሳ አምስት ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ተራችን በመድረሱ አሰልቺውን ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ገባን፤
ስለፍትህ የሚጮኸው ሰው ወደ ተጣለበት-‹‹ዞን ሁለት››
‹‹እስክንድርን አየዋለሁ›› ብዬ እርግጠኛ ስላልሆንኩ፣ ሙሌ ወደ ዲጄው (ጠያቂዎች የሚፈልጉትን እስረኛ ስም ሲነግሩት
በማይክራፎን የሚጠራ ታሳሪ ነው) ተጠግቶ ‹‹እስክንድር ነጋን›› ሲለው በስጋት ነበር የማስተውለው፤ ይኹንና ዲጄው የተነገረውን
ተቀብሎ ‹‹እስክንድር ነጋ፣ እስክንድር ነጋ….›› እያለ ሲጮኽ ድንገተኛ ደስታ አጥለቀለቀኝ፤ ኦ አምላኬ! ምኞቴ እውን ይሆን ዘንድ
እርዳኝ! …በስሜት ተሞልተን እስረኞች በሚወጡበት በር ላይ ለበርካታ ደቂቃዎች አፈጠጠን፤ ሆኖም ጥቂት ታሳሪዎች ተከታትለው
ከመምጣታቸው በቀር እስክንድር የለም፤ ዝምታ በተጫነው ገፅታ እርስ በእርስ ተያየን፤ ኩም-ኩምሽሽ ልንል ይሆን? …የዲጄው ድምፅ
‹‹ታምራት ገለታ፣ ታምራት ገለታ…›› ብሎ ያሰመጠንን የስጋት ፀጥታ አደፈረሰው፤ ይህን ስም አውቀዋለሁ፤ አንድ ሰሞን ከዜናነትም
አልፎ፣ የመፅሄቶች እና የጋዜጦች ዋነኛ ማሻሻጫ ሆኖ እንደ ነበር አስታውሳለሁ፤ የጥሪው ድምፅ አየር ላይ ናኝቶ አፍታም ሳይቆይ
‹‹እያንገዋለለ/ አባባ ታምራት›› ውሃ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ልብስ በጥቁር ከረባት ለብሶ፣ አይኑ ላይ ጥቁር መነፅር ሰክቶ በፈገግታ
ወደ ሚመለከቱት ሶስት ወጣት ሴቶች ወደ ቆሙበት አቅጣጫ ሲሄድ አየሁት፤ ሶስቱም ብስል ቀይ ናቸው፡፡ የሰውየው አለባበስ የእስረኛ
አይመስልም፤ ምናልባት ተከታዮቹ ሊጠይቁት ሲመጡ ‹‹ዛሬም አምላክ ነኝ-አርጋለሁ፣ እበራለሁ›› ብሎ እያጭበረበረ ሊሆን ይችላል፡፡
…እስክንድር ግን አሁንም አልመጣም፡፡ ለዲጄው ነገርኩት፤ በተሰላቸ ድምፅ፡-
‹‹ጠብቀው ይመጣል›› አለኝ፤
‹‹ከእርሱ በኋላ የተጠሩ እስረኞች እየመጡ ነው›› መለስኩለት፤ በፀበኛ አስተያየት ገረመመኝና ‹‹እስክንድር ነጋ፣ እስክንድር ነጋ…›› ሲል
አምባረቀ፤ ሰከንዶች አለፉ፡፡ አንድ ደቂቃ፣ ሁለት ደቂቃ… ሰዓታት ያለፉ ቢመስለኝም፣ አይኖቼን ከእስረኛ መውጫው ላይ አልነቀልኩም፤
ሸምገል ያሉ አንድ እስረኛ መጡ፤ ከኋላቸው ደግሞ ሌላ ሰው ተከትሏል፤ አየሁት፤ እርሱ ራሱ ነው፤ ልቤ በደስታ ወከክ ሲል ይታወቀኛል፡፡
አይን-ለአይን ተያየን፤ ደግሜ አየሁት፤ አላመንኩም፡፡ አዎን! ራሱ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ ባርኔጣውን አጥልቋል፤ ፊቱ በማራኪ ፈገግታ
ተሞልቷል፤ እርሱም በጣም የተደሰተ ይመስላል (ለነገሩ እንዴት አይደሰት! ከአስራ ሰባት ወራት በኋላ ከቤተሰቡ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ
ከጠያቂዎች ጋር ሲገናኝ!) አጠገባችን እስኪደርስ አፍጥጬ ተመለከትኩት፤ በጭራሽ እስር ቤት የቆየ አይመስልም፤ አብሬው በዋልኩባቸው
ጊዜያት ሁሉ ከራሱ አልፎ በእኔም ላይ ይጋባ የነበረው ያ ጠንካራ መንፈሱ ዛሬም አብሮት አለ-ክቡድ መንፈስ፡፡ ‹‹ብሶት የወለደው››
ገዥው ፓርቲ ለሃያ ዓመታት የመከራ ናዳ ቢያወርድበትም-አልተበገረም፡፡ ይህ ሰው መቼም የሚሸነፍ፤ መቼም እጅ የሚሰጥ፤ መቼም
የሚከሽፍ አይመስለኝም፡፡ የእስር ቤት ኑሮም የትግል ፍላጎቱን ይበልጥ ኃያል አድርጎታል፡፡ ብርቱው-ሰው (The Iron Man) እስክንድር
ነጋ፡፡
የሆነ ሆኖ መሀላችን ያለው የሽቦ አጥር የፈቀደልንን ያህል እጅ-ለእጅ ተነካክተን ሰላምታ ተለዋወጥን (ናፈቆትን የማያረካ-ሰቀቀን) እና
ያሰብኩትን ያህል ባይሆንም ለተወሰኑ ደቂቃዎች አውርተን ስናበቃ ለምን እንደፈለገኝ ነገረኝ፡፡
‹‹ትግሉ መቆም የለበትም፤ እጅ አንሰጥም፤ አሁን የምነግርህን በሙሉ በአእምሮህ እንድትይዘው እፈልጋለሁ››‹‹ግዴለም፤ ንገረኝ ለሶስት ተረዳድተን እናስታውሰዋለን››
‹‹በጣም ጥሩ! መልዕክቱን ራስ ከፃፍከው በኋላ ለአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እንዲደርስ እና በመረጥከው ሚዲያ ላይ እንዲታተም
አድርገው›› አለና ከሸሚዝ ኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት አወጥቶ ከዚህ በታች የምታነቡትን መልዕክት ያለ ማስታወሻ ደብተር እንድይዘው
አብራራልኝ፤ (በድጋሚ ወደ ቃሊቲ አምርቼ፣ መልዕክቱን በትክክል መረዳቴን አረጋግጫለሁ)
ግልፅ ደብዳቤ ለኦባማ አስተዳደር!
ሁላችንም እንደምናውቀው በሀያኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ ዓስርታት በተለያዩ ክፍለ አህጉራት ውስጥ ባሉ ታዳጊ ሀገር ህዝቦች
የተነሱ የፖለቲካ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በቀዳሚነት በጠመንጃ ኃይል የተደገፉ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ የታሪክ ክስተት
ማለፏን የሚመሰክረው ዛሬም ወታደራዊ ስርዓቱን ብቻ ሳይሆን፣ ይህንን መንገድ የመረጡትን ጥቂት የተቃዋሚ ድርጅቶችንም በጦር
ኃይል ድል አድርጎ ስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና የቀዝቃዛው ዓለም ጦርነት ማብቃትና የአሜሪካ ብቸኛ ልዕለ ሀያል
ሀገር ሆኖ መውጣት በኃይል የሚደረጉ ‹‹ፀረ-አምባገነን›› ንቅናቄዎች ሰላማዊውን መንገድ ብቻ እንዲከተሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡
የለውጡም ዋነኛ መግፍኤ አሜሪካ ለሰላማዊ ትግል የምትሰጠው ከፍ ያለ ቦታ ብቻ ሳይሆን የምታደርገው እገዛም መሆኑ አከራካሪ
አይደለም፡፡ በእርግጥ የአሜሪካ አስተዳደር በሰላማዊ ትግል ላይ ያለው አቋምና ለትግሉ የሚያደርገው ቀጥተኛ አበረታችነት የሀገሪቱ
መስራች አባቶች ካነፁት የሞራል እና የፖለቲካ እሴት እንደሚነሳም አውቃለሁ፡፡
በኢትዮጵያ የ1983 ዓ.ምን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ የተስተዋለው ‹‹ሰላማዊ የትግል አማራጭ›› እምነት አውድም ከዚሁ
የአሜሪካ መንግስት አቋም ጋር የተዛመደ ሲሆን፣ ባለፉት ሀያ ሁለት ዓመታትም በሀገራችን ዓላማቸውን በሰላማዊ ትግል ያራመዱ ወገኖች
በሙሉ በዚህ ከመሰረታዊ የነፃነተ እሴቶች የሚነሳውን የአሜሪካንን ድጋፍ እውነተኝነት በፍፁም ልብ በመቀበል መሆኑ አይሳትም፡፡ ነገር
ግን በዚህ እምነት ተቀኝተው የትግሉን አማራጭ ለመከወን ሲታትሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ‹‹ስቴት
ዲፓርትመንት›› በየዓመቱ የሚያወጣውን ሪፖርት መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡ እናም ሞት፣ እስር፣ ስደት እና ሌሎች መከራዎች በትግሉ
አራማጆች ላይ የደረሰ (እየደረሰ) መሆኑ ለአሜሪካን የተደበቀ ጉዳይ አይደለም፡፡
ይኽም ሆኖ በግሌ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር ‹‹ካለ ዲሞክራሲ ዕርዳታ የለም!›› የሚለውን መሰረታዊ የውጪ ጉዳይ
መርሁን ለማስከበር አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደበትም የሚል እምነት ስላለኝ፣ ኢህአዴግ ለህግ የበላይነት ተገዢ እንዲሆን ከሀገሪቱ
ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታም ሆነ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ካለው አጠቃላይ ግንኙነት አንፃር፣ አሜሪካ የሚከተሉትን ተፅእኖ
መፍጠሪያ አማራጮች ብትከተል በሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የነፃነት እንቅስቃሴ በእጅጉ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ፡፡
1.የኢኮኖሚ ማዕቀብ
አሜሪካ በየዓመቱ የምታደርገውን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ደረጃ በደረጃ የሚቀንስ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ ብትተገብር ኢህአዴግ ህግ አክባሪ
እንዲሆን የሚገደድበትን ሁኔቴ ማመቻቸት ትችላለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ማዕቀቡ ዋነኛ ግቡ ማድረግ የሚኖርበት ስርዓቱ ለአፈና
የሚጠቀምባቸውን (ምንም አይነት የኢኮኖሚ ፋይዳ የሌላቸውን) ተቋማትና መንገዶች መሆን ይኖርበታል፡፡
2.የበረራ ማዕቀብ /Flight Embargo/
በሁለተኛነት መተግበር ያለበት ማዕቀብ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሀገር ሀገር የመዘዋወር መብትን የሚያግድ ቢሆን
አስፈላጊውን ውጤት ያመጣል፡፡ ይህ የበረራ እግድ የተወሰኑ የስርዓቱ ቀዳሚ ባለስልጣናትን ብቻ የሚመለከት መሆን ይኖርበታል፡፡
3.የሰብዓዊ ዕርዳታ /Humanitarian Aid/
ሁለቱ ማዕቀቦች ሲጠነክሩ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን /Humanitarian Aid/ ማቋረጥ አይኖርባትም፡፡
ምክንያቱም የዚህ አይነቱ የዕርዳታ መስተጓጎል ዜጎችን ለከፋ ስቃይ ሊዳርግ የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነውና፡፡
ዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ማዕቀቦች በኢህአዴግ አስተዳደር ላይ ከጣለች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ሁሉን
አቀፍ የዲሞክራሲ መብቶችን የማስከበር ትግል በከፍተኛ ሁኔታ ታግዛለች፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ሀገሪቷ ከቆመችበት ስለሰው ልጆች
ነፃነት የመቆርቆር የሞራል ኃላፊነት ጋር በጥብቅ ይተሳሰራል፡፡የማዕቀቦቹ መተግበር ለኢትዮጵያ አምስት ዋና ዋና ጥቅሞችን ያስገኛል፡፡
1.የሰላማዊ ትግል ተዓማኒነትን ያጠናክራል
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተሞከረ ያለው ሰላማዊ ትግል የተሻለ አማራጭ እንደሆነ የትግሉ አራማጆችና ደጋፊዎች እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡
2. ለለዘብተኞቹ
ይህ አይነቱ ጫና ከሚፈጥራቸው አዎንታዊ ለውጦች አንዱ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ ለዘብተኛ የአመራር አባላት እና ካድሬዎች ለበለጠ
የፖለቲካ መብቶች መከበርና የተሻለ ስርዓታዊ ክፍትነትን ለማበረታታት ያላቸውን ተነሳሽነት እንዲያጠናክሩ ማድረግ ማስቻሉ ነው፡፡
3. ለአክራሪዎቹ
በድህረ-መለስ ኢህአዴግ ውስጥ ለዘብተኛ እና እጅጉን ፅንፈኛ ኃይሎች እንዳሉ ተስተውሏል፡፡የዚህ ማዕቀብ ተፅዕኖም ፅንፈኞቹ
የስርዓቱ ባለስልጣናት ከሚያቀነቅኑት ኢ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድና የጥላቻ ፖለቲካ እንዲታቀቡ አድርጎ ፖለቲካዊ መቻቻልን እንዲቀበሉ
ያስገድዳቸዋል፡፡
4.ለሲቪክ ማህበራት እና ጋዜጠኞች
በሰላማዊው መንገድ በነፃነት እንቅስቃሴው ውስጥ በጉልህ ሲሳተፉ የነበሩትን እና እየተሳተፉ ያሉትን ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት
ተሟጋች ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት እየከፈሉ ያለው መስዕዋትነት ከፍ ያለ ዋጋ እንዳለው ከማረጋገጡም በላይ የተሻለች ኢትዮጵያን
ለመፍጠር ብቸኛው መንገድ ሰላማዊና ህገ-መንግስታዊ የትግል አማራጭ እንደሆነ እንዲያምኑና ትግላቸው ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል
እርግጠኛ ሆነው በመንገዳቸው እንዲፀኑ ያደርጋቸዋል፡፡
5. ለአሜሪካ መንግስት
የአሜሪካ መንግስት እነዚህን ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን እርምጃዎች መውሰዱ፣ ለኢትዮጵያውያን አሜሪካ ያለባትን የሞራል ኃላፊነት
እየተወጣች መሆኑን ከማሳመን በዘለለ የገባችውን ቃል በመተግበር በሰላማዊ መንገድ አላማቸውን ሲያራመዱ ለስርዓቱ ጥቃት የተጋለጡ
ፖለቲከኞች እና የመብት ተሟጋቾችን መታደግ አስችሎ፣ ከታሪክ ተጠያቂነት ዕዳ ነፃ ያወጣታል፡፡
በጥቅሉ እነዚህ ተመጋጋቢ ሂደቶች ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገውን ትግል በማፋጠን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቶች
የተከበሩባት ሀገር ለመፍጠር ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው የማይናወፅ እምነት አለኝ፡፡
እስክንድር ነጋ /ከቃሊቲ እስር ቤት/
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Friday, July 19, 2013

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ
HOME » መግለጫ / PRESS RELEASE » “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ
DEC 20, 12 • BY  • 

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

ቀን ታህሳስ 11  2005
የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችን በዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል፣ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት ነው።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወያኔን በኃይል የማስወገድ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሥልጣን ሽግግር በሃገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛዉም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ፣ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግሥታዊ የመከላከያ፣ የፓሊስና የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዖ የማድረግ ተልዕኮ ይዞ የተነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ ነው።
የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል ራዕይና ተልዕኮ የተቀዳው በቀጥታ ሕዝብ በህይወቱ በደሙ በስቃይና በመከራ ውድ መስዋዕትነት ከከፈለለት የ1997 ብሄራዊ ምርጫ ነው።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን እውን ያደረገው ወያኔ የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በስልጣን ለመቆየት በምርጫው ማግስትና እስካለንበት ወቅት በወሰደውና እየወሰደ ካለው የእብሪት እርምጃ ነው።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወያኔ ድርድርና እርቅ የማይገባው፣ ትዕግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ  አሳቢነት እንደ ሞኝነት የሚቆጥር በዚህም ስሌት ሕዝብን ለዘላላም እየረገጠና እየዘረፈ ለመግዛት ቆርጦ የተነሳ እኩይ ኃይል መሆኑ ጠንቅቆ  የተረዳ ነው። የወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተወለት ምርጫ በዝምታ በባርነት መገዛት ወይም ለነጻነት መዋጋትን ብቻ መሆኑን የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል ።
በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ የተሰባሰብን ዜጎች በደማችን የሚፈስ የቀደምቶቻችንን የነጻነት ቅርስ ተሸካሚዎች ነንና ባርነትን አማራጭ አድርገን ለመቀበል ከቶውኑ አይቻለንም። ብቸኛው ምርጫ የወያኔን የባርነት ግብዣ በአመጽ መክተን በወያኔ  መቃብር ላይ የነጻነትን ሰንደቅ ማውለብለብ ነው።
ዛሬ በሃገራችን በወያኔ አምባገነናዊ እብሪት ያልታፈነ፣ ያልተዋረደና ያልተዘረፈ የሃገሪቱ ዜጋ አይገኝም። የወያኔ ሹማምንት በሃብት ላይ ሃብት፤ በድሎት ላይ ድሎት ሲጨምሩ፣ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ ግን መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መንገላታት፣ መታሰር፣ መደብደብና መገደል ሆኗል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት፣ የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም። የዚህ  ሁሉ ሰቆቃ አብይ ምክንያት የወያኔ ዘረኛ አምባገነን አገዛዝ ነው። ወያኔ ከሥልጣን ሳይባረር አንዳችም በጎ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሰብ አይቻልም።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የወያኔን እኩይ ባህሪያትና ተፈጥሮ በመመርመር፣ የወያኔ  የአመጽ እብሪት በሕዝባዊ አመጽ የሚተነፍስበት ሁኔታ  እስካልመጣ ድረስ፣ ወያኔ መብታቸውን ከመጠየቅ ውጭ ምንም እንከን የሌለባቸውን ንጹሃን ዜጎች ከማሰር፣ ሰቆቃ ከመፈጸም፣ ከመግደል ከማሳደድና  ከማፈናቀል እንደማይቦዝን ከልብ ያምናል።
ሁላችንም ሃገራችንን ነጻነታችንን የምንወድ  ዜጎች ያለን ምርጫ ቀበቷችንንና  መቀነታችንን ጠበቅ፣ ሃሞታችንን ኮስተር አድርገን ወያኔ ያሳጣንን ሰላምና ነጻነት፡ የቀማንን ሃገርና አንድነት በመራራው ትግላችን ማስመለስ ብቻ  ነው።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በዛሬው እለት ራሱን ይፋ ያደረገው ይህ ወያኔን የማስወገድ ትግል የተጀመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀውና ትግሉን እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪውን ለማሰማት ነው ።
  1. ህገ- መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ ተቃውሞዎች ለማድረግ ጥረት ያደረጉ ዜጎች በሽብርተኛነት እየተከሰሱ በእድሜ ልክ እስራት ሲቀጡና ሰቆቃ ሲፈፀምባቸው የታዘባችሁ ወጣቶች፤
  2. ለሃይማኖት እኩልነት በመታገላቸው በእስር ላይ እየማቀቁ፣ እየተገረፉና እየተሰቃዩ  ያሉ የሙስሊም ምዕመናን ተወካዮች ጉዳይ የሚያሳስባችሁ ወገኖች፤
  3. በቤተክህነትና በክርስትና ተቋማት ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ የሚያንገበግባችሁ ወገኖች ሁሉ፤
  4. ለወያኔዎችና ሸሪኮቻቸው እድገትና ምቾት ሲባል ከይዞታችሁ የተፈናቀላችሁ ወገኖቻችን ሁሉ፤
  5. በወያኔ ቱጃሮች ሥራችሁ መቀማቱ ሳያንስ፣ ገቢን ሳይሆን ወገንተኛነትን መስፈረት ባደረገ መመዘኛ ከአቅም በላይ የሆነ የወያኔ ግብር፣ ታክስና መዋጮ የተማረራችሁ ነጋዴዎች፤
  6. ማኅበራችሁ በወያኔ ፈርሶ ወይም ተጠልፎ የጋራ ድምፃችሁን የምታሰሙበት፣ ከቀጣሪያችሁ ከወያኔ  ጋር ፍትሃዊ የጉልበታችሁን ዋጋ ክፍያ መደራደሪያ  ያጣችሁ ላብአደሮች፣ መምህራን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች፤
  7. ምንም አይነት የአካዳሚ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ጥራቱን ያልጠበቀ ትምህርት እንድትከታተሉ የተፈረደባችሁ፣ ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ ከየኮሌጁና ከየዩንቨርስቲው ስትመረቁ እጣችሁ ድንጋይ ማንጠፍ የሆነው ወጣት ተማሪዎች ፣
  8. በነጻነት ወጥቶ  መግባት፣ ሰርቶ ለመኖር የተሳናችሁ፣ በገዛ ሃገራችሁ ገና በጎልማሳ እድሜችሁ የወላጆቻችሁ ጡረተኞች እንድትሆኑ የተፈረደባችሁ፣ እንደ ወላጆቻችሁ ትዳር መስርታችሁ ልጆች ወልዳችሁ የመሳም እድላችሁ በወያኔ ዘረኛና ዘራፊ ፖሊሲዎች ጨንግፎ የቀረባችሁ፣ አደገኛ በረሃዎችንና ባህሮችን በማቋረጥ ለመሰደድ ልባችሁ እየከጀለ ያለ የሃገራችን ውድ ወጣቶች፤
  9. በአረብ ሃገራት ለባርነት ስራ በወያኔ እየተሸጣችሁ፣ እጣችሁ ተገዶ  መደፈር፣ በፈላው ወሃ መቀቀል፣ መደብደብ፣ መዋረድና ከፎቅ ላይ እየተወረሩ ክቡር ህይወትን ማጣት ለሆነው ውድ እህቶች፣
10. ለኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ግድ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በሙሉ፤
11. የሕዝብ ድምጽ ይከበር በማለታችሁ፣ ለሃገር አንድነትና ክብር መሰለፍ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባችሁ እንደ ባዕድ ጦር የተበተናችሁና የተገፋችሁ፣ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በሚታየው ዘረኛነት እየተቃጠላችሁ፣ በሕዝብ ላይ ዝመቱ በተባላችሁ ቁጥር ከህሊናችሁ ጋር መዳማት የመረራችሁ  የኢትዮጵያ ወታደሮች እና፤
12. በድህነት አስገዳጅነት፣ እንዲሁም በሌሎችም ማስፈራሪያዎችና ጫናዎች የወያኔ/ኢህአዴግ ድርጅቶች አባል የሆናችሁ ወገኖቻችን በሙሉ፣
ዛሬ ነገ ሳትሉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይላችንን ተቀላቀሉ።
ተባብረን ወያኔን እናስወግድ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
አድራሻ:  ስልክ ቁጥር – +442081230056
ኢሜል አድራሻ pr@ginbot7pf.org