April 25, 2013 12:45 pm
ወደ ቤንሻንጉል የተመለሱት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በፍኖተሰላምና በተለያዩ አካባቢዎች ተበትነው ከቆዩ በኋላ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እስካሁን እርሻ አለመጀመራቸውንአስታውቀዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እንዳስታወቁት ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንደሚመለሱ ተነግሯቸው ቢመጡም፣ ስፍራው ሲደርሱ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለህብረተሰቡ አስቀድመው የተከራየነውን መሬት እንዳያስረክቡን በመቀስቀሳቸው ሊቀበሏቸው እንዳልፈለጉ አስረድተዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት አካላት “ተመልሰው የመጡት መሬታችሁን ሊቀሟችሁ ነው እንዳታቀርቧቸው” ተብለዋል የሚሉት ተፈናቃዮቹ “እርሻችንን እንዳትነኩ ወደ መሬታችንም እንዳትደርሱ” መባላቸውን ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡
በዚሁ ምክንያት እጅግ ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ መንግስት በአካባቢው በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፃመውን ግፍ እንዲያስቆም ተማፅነዋል፡፡ አክለውም “እኛ ያለ ባለመሬቱና ያለ መንግስት ፈቃድ የሰው መሬት አንነካም፤ ይህንን የአካባቢው የመንግስት አካላት ለህብረተሰቡ ሊያስረዱልን ይገባል፡፡ ሰርተን ለመኖር ተቸግረናል” ብለዋል፡፡
No comments:
Post a Comment