የዘረኛው ወያኔ ወታደሮች የግራዚያኒን ሀውልት ግንባታ የተቃወሙ ኢትዮጵያዊያንን አሰሩ

የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ታዋቂውን የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያምንና ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ለአንድ ቀን ካሰሩዋቸው በሁዋላ በመታወቂያ ዋስ መልቀቃቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ አመለከተ። ተያይዞ የደረሰን ዘገባ እንዳመለከተው ከእስረኞች መካከል አንዳንዶቹ ብሄር ተብለው ሲጠየቁ ኢትዮጵያውዊ በማለት በመመለሳቸው ዘራቸው ሳይቀር እንደተሰደበ ታውቋል። ከዚሁ በተጨማሪም በርካታ ወጣቶች የኢሜል እና የፌስ ቡክ የሚስጢር ቁልፋቸውን ( ፓስወርድ) እንዲሰጡ መገደዳቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ዶ/ር ያእቆብና ሌሎች ሰዎችም የታሰሩት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ፈቃድ አልተጠየቀም በሚል ሰንካላ ምክንያት መሆኑን ታውቋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሊቪዥን ኢሳት ከዶር ያቆብ ጋር ቃለምልልስ ያደረገ ሲሆን ዶር ያቆብ በቃለ ምልልሱ የወያኔ ወታደሮች የወሰዱባቸው እርምጃ የሚያመለክተው አገዛዙ ለግራዚያኒ ጠበቃ መቆሙን ነው ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ኢሳት ከባለራእይ ወጣቶች ማህበር መሪ ወጣት ሀብታሙ አያሌው ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ላይ ወጣት ሃብታሙ እንደተናገረው ለዚሁ ተቃውሞ ፈቃድ የጠየቁት ከ 14 ቀናት በፊት እንደነበር ገልጾ በታሰሩት ላይ የተደረገው ምርመራ ከጉዳዩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳልነበረው አያይዞ ተናግሯል ፣ በመጨረሻም ወጣት ሀብታሙ ዛሬም አንድ አባላቸው ታስሮ እንደነበር ገልጾ ወዴት እየሄድን እንደሆን አናውቅም ብሎአል።
No comments:
Post a Comment