ከቤሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ አማሮች በጨካኙ የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት ወከባ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተሰማ

ዘጋቢያችን አክሎ እንደገለጸው የወያኔ ሆድ አደር ባለስልጣናት ተፈናቃዮቹን ከተማውን ለቀው ወደ ወረዳቸው እንዲሄዱ ያስጠነቀቁዋቸው ሲሆን፣ የተቀሙትን ሀብትና ንብረት በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡ ደግሞ “ቀድሞ ማን ሂዱ አላችሁ አናውቅም” በማለት የመለሱላቸው መሆኑን ገልጿል።
ከቤሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለውና ከሞት ተርፈው ቀያቸው የደረሱትና በገዛ ቀያቸው ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ተጥለው የሚገኙት 2 ሺህ አባወራዎች፣ ከንጽህና ጉድለት ጋር በተያያዘ በሽታ ተነስቶ ህጻናትና ሴቶች ሊያልቁ ይችላሉ በማለት ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸው ተያይዞ የደረሰን ዘግባ ያመለክታል።
በሌላ በኩል ደግሞ አሁንም የቤንሻንጉል ጉሙዝን ክልል ለቀው ባልወጡ አርሶአደሮች ላይ የሚፈጸመው ግድያና እንግልት መጨመሩ የታወቀ ሲሆን የተፈናቃዮችን ሀብት ለመዝረፍ በተደረገ ሙከራ ትናንት አንድ ግለሰብ በጥይት ተመትቶ መሞቱና ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
No comments:
Post a Comment