የህወሀት መሪዎች በድርጅቱ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ለመምከር መቀሌ ገቡ

የተከፋፈሉት የህወሀት መሪዎች በተከታታይ ስብሰባ ተቀምጠዉ ለ11ኛ ጉባኤያቸዉ የሚሆን አጀንዳ መቅረጽ ተስኗቸዉ ብዙ ከሰነበቱ በኋላ ከሰሞኑ ያለ አጀንዳ ከመሰብሰብ ያዳናቸዉን የግብር ይዉጣ አጀንዳ እንዳዘጋጁ ለማወቅ ተችሏል። መቀሌና ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ የህወሀት መከፋፈል በግልጽ እተነገረ ሲሆን ግንባሩ በዚህ እሁድ በሚጀመረዉ 11ኛ ጉባኤዉ ላይ ተአምር ሰርቶ አንድነቱን ካላረጋገጠ ደደቢት ዉስጥ የተጠነሰሰዉ ህወሀት መጨረሻዉ መቀሌ ዉስጥ ሊጀመር ይችላል ብለዉ የሚያምኑ ለህወሀት ቅርበት ያላቸዉ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደገመቱ ዘጋቢያንች ከመቀሌ የላከልን ዜና ያስረዳል።
በአሁኑ ወቅት አንጋፋዋ የመቀሌ ከተማ በአንድ በኩል በህወሀት አርማና በወያኔ ሰንደቃላማዎች ያሸበረቀች ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በየመንገዱ ላይ ጠመንጃ አንግበዉ የሚርመሰመሱት ወታደሮችና መንገዱን ያጣበቡት ወታደራዊ ፒክ አፕ መኪናዎች ከተማዋን አጨናንቀዋታል። ጭራሽ ይህም አልበቃ ብሏቸዉ የወያኔ ካድሬዎች ከቤት ወደ ቤት እየተዘዋወሩ ህዝቡ የጉባኤዉን ማብቃት አስመልክቶ ድጋፉን ለህወሀት እንዲገልጽ በመወትወት ላይ መሆናቸዉን ዘጋበያችን አክሎ የላከልን ዜና ያስረዳል።
No comments:
Post a Comment