Friday, January 11, 2013


ጉዕሽ አበራ ማነዉ?

ጉዕሽ ኣበራ ቆላ ተንቤን በሚባለዉ በተንቤን ኣዉራጃ ተወልዶ ያደገ እና ለሆዳቸዉ ከሚያድሩ አደርባዮች እና ህዝባቸዉ ከሚያስጨፍጭፉ አንዱ ሲሆን በት/ቱ ሰነፍ እና ኣቃጣሪ የሆነ ግለGuesh Abera TPLF spy ሰብ ነዉ፡፡
ጉዕሽ በቅርቡ በተንቤን በኣሉላ ኣባ ነጋ ስም ሲጠራ የነበረዉ ት/ቤት በመለሰ በመቀየሩ ከተደሰቱት ሰዎች አንዱ ሲሆን ተንቤን ምን ታመጣላቹ? ተንቤኖች ስታለቅሱ ትኖራላቹ እያለ በተንቤን ተወላዶች ሽብር ሲፈጥር የነበረ እና ኣሁንም በተንቤን ተወላጆች ክፍፍል ለመፍጠር የቤት ስራ ተሰጥቶት እየሰራ ያለ ሰዉ ነዉ፡፡ጉዕሽ አበራ የኣሉላ ት/ቤት ተቀይሮ መለስ ተብሎ እንዲጠራ ካደረጉት ካድሬዎች አንዱ ሲሆን የከተማዉ ስም ተንቤን ቀርቶ መለስ ዜናዊ ተብሎ ከተማዉ ራሱ እንዲጠራ እናደርጋለን እያለም ሲናገር የሚደመጥ ሰብእናዉ ሽጦ ለሆዱ ያደረ የሰዎች መጠቀሚያ የሆነ አሳፋሪ ሰዉ ነዉ፡፡
ጉዕሽ በብዛት ዓጋመ፣ ተምቤን፡ እንደርታ እና ራያ የሚያንቆሸሹ ፅሕፎች በፌስ ቡክ እና በሌሎች የህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚለጥፍ ሰዉ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በተንቤን ተወላጆች እንደ ወንጀለኛ እና ከዳተኛ የሚቆጠር ሰዉ ነዉ፡፡ ጉዕሽ ንፁሃን የትግራይ ልጆች ለማስወንጀል እና ለማሸበር ስም የሚቀያይርና ለትግራይ ተወላጆችም አገራቹ አትገቡም፡ ፎታቹ ኤርፖርት ገብቶዋል እያለ በህዝብና መንግስት ክፍተት እየፈጠረ የሚገኝ በተፈጥሮ የዋህ ግን ለሰዎች መጠቀሚያ በጣም ምቹ የሆነ ሰዉ ነዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ጉዕሽ የትግራይ በተለይም የተንቤን ተወላጆች እንዲገደሉ እና እንድታሰሩ ስም ዝርዝር ኣሳልፎ የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም በ የተንቤን እና በሌሎች የትግራይ ተወላጆች ጥርስ የገባ ሰዉ ነዉ፡፡ ጉዕሽ ኣበራ ወደ ኣሜሪካ ከመጣ 3ት ዓመት ያደረገ ሲሆን በኣሜሪካ ቤት ተሰጥቶት የሚኖር እና በተንቤንም በነፃ መሬት ተሰጥቶት በህዝብ ገንዘብ ቤት የገነባ ሰዉ ነዉ፡፡ ጉዕሽ በተደጋጋሚ ኣሉላ ኣባነጋ ፡ ሃፄ ዮሃንስ ፡ ሓየሎም ኣረአያን እና ሌሎች ጀግኖች የሚያጥላሉ ፅሕፎች የሚለጥፍ እና በቅርቡም እኔ እኮ የተንቤን ልጅ ኣይደለሁም ስለሆነም የተንቤን ጉዳይ ዠብ ይብላዉ ብሎ ይናገር እንደነበር አሱ በቅርበት የሚያዉቁ ይናገራሉ፡፡ ጉዕሽ በአሁኑ ሰኣት ዉጪ በሚኖሩ የተንቤን ተወላጆች ሙሉ በሙሉ የተገለለ እና በየማንነት የቀዉስ ዉስጥ የሚገኝ ሰዉ ነዉ፡፡
እ/ሔር አገራችን ይጠብቅልን

በደቡብ ኢትዮጵያ የሱሪ ህዝብ ላይ የመንግስት ወታደሮች ጭፍጨፋ አካሄዱ

Postby Admas » Yesterday, 11:48
ኢሳት ዜና:- በደቡብ ኢትዮጵያ በሱሪ አካባቢ ተገኝቶ ያየውን ሁኔታ በብዕሩ ያሰፈረ በአንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የውጭ አገር ዜጋ የሚከተለውን ሪፖርት ልኳል።

ዲሰምበር 20፣ 2012 የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በባሌሳ ሱሪ መንደር፣ ቢያሆላ ወይም በአገሬው ቋንቋ ነጭ ድንጋይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መጡና ነዋሪዎችን ከበቡዋቸው። ወታደሮቹ ወንዶችን መንግስት ይህ እልቂት ፣ ሴቶችንና ህጻናትን እርስ በርስ ካሰሩ በሁዋላ ወደ ዲዲቢ ጫካ ወሰዱዋቸው። 7 ወጣቶች ብቻ ሲያመልጡ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ረሸኑዋቸው። በመንደሩዋ 154 ሱሪዎች ይኖሩ ነበር።እንዳይነገርበት የሚችለውን ሁሉ እየጣረ ነው። እግዚአብሄር ይመስገን ዜናው ይፋ ወጣ። ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄ ያለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት ለምን ይሆን የኢትዮጵያን መንግስት የሚደግፉት? አሸባሪነትን መደገፍ ሳይሆን መዋጋት አልነበረባቸውም?የሟቾቹ አስከሬን በዲቢዲብ ጫካ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ እንዲቀበር ተደርጓል። አንዳንድ አስከሬኖች በጥንብ አንሳ አሞሮች እና በአውሬዎች ተበልተዋል። አብዛኞቹ ህጻናት በአቆቦ ወንዝ ላይ ተጥለዋል። ከጭፍጨፋው በሁዋላ ወታደሮች ይህን ድርጊት ሪፖርት ባደረገው ላይ ሁሉ ከዚህ የበለጠ አስከፊ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

በሱሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንደቀጠለ ነው። በየወሩም እየከፋ በመሄድ ላይ ነው። ማንም ግን ስለችግሩ የተናገረ አካል የለም። በምእራብ አገሮች በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ የምእራብ ሚዲያዎች ሰፊ የዜና ሽፋን እንደማይሰጡት ሁሉ ፣ በደቡብ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ መጠን ሲገደሉ ግን የዜና ሽፋን ሊያገኙ አልቻሉም።

ባለፉት ሳምንታት ብቻ 147፣ ከሶስት ወራት በፊት 30፣ ከአራት ወራት በፊት ደግሞ 70 ሰዎች ተገድለዋል።

የሱሪ ህዝብ በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን ይገኛል። ሱሪዎች ቻይ፣ ቲርማጋ እና ባሌሳ እየተባሉ በሶስት ይከፈላሉ። ሱሪዎች ከኦሞ ወንዝ በስተምስራቅ በኩለ ከሚኖሩት ሙርሲዎች ይመሳሰላሉ። አንድ አይነት ባህልና አንድ ቋንቋ ይናገራሉ። ዛሬ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች መሬቶቻቸውን ለመውሰድ እያፈናቀሉዋቸው ነው። ዲፊድ፣ ዩኤስ አይዲ፣ ቻኢና፣ ህንድ፣ የአውሮፓ ህብረትና ሳውዲ አረቢያ እነዚህን ባለሀብቶች እየደገፉ ጥፋቶች እንዲሰሩ እያደረጉ ነው።

አሁን የተፈጸመው ጭፍጨፋ ምክንያቱ ሰፈራ ነው። ሱሪዎች መሬታቸውን ለቀው መንግስት ባዘጋጀላቸው የሰፈራ ጣቢያ እንዲሄዱ ተነግሮአቸዋል ምክንያቱ ደግሞ መሬታቸው ለአንድ የወርቅ ማእድን ፈላጊ ኩባንያ በመሰጠቱ ነው። ሱሪዎች መሬታችንን ለቀን አንሄድም ይላሉ። የኩባንያው ሰራተኞች ደግሞ ስራችንን ማከናወን አልቻልንም በማለት ክስ ያሰማሉ።

አንድ የባለራእይ ወጣቶች የአመራር አባል ተይዛ ታሰረች መርፌ እንደተወጋች ተገልጿል

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራር ጸሀፊ የሆነችው ወ/ት ወይንሸት ተይዛ የታሰረችው ትናንት ሲሆን፣ ዛሬ የስራ ባልደረቦቿ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ቃሉዋን እንድትሰጥ ለማድረግ ቢሞክሩም ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሊሳካላቸው አልቻለም። ወጣቷ መርፌ እንደተወጋች እና ቃሊቲ አካባቢ ከአንድ ክፍል ውስጥ መገኘቷን የማህበሩ ምክትል ሊቀመንበር ወጣት ሚካኤል ለኢሳት ተናግሯል
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ወ/ት ወይንሸት ለፖሊስ ቃሉዋን ሰጥታ ስትወጣ አነጋግረናታል። በቃለምልልሱ በኤሌክትሪክ ቶርች መደረጓንና ስቃይ ሲፈጸምባት ማደሩዋን በተዳከመ ደምጽ ተናግራለች።
ማህበሩ የፊታችን ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ስብሰባ መጥራቱ የታወሳል።


    በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ ታቅዶ የነበረውን የግድያ ሴራ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አወገዙ

    ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ኢሳት ዜና:- በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ላይ ሊቃጣ የነበረውን የግድያ ወንጀል ተከትሎ  በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ጥገኝነት ጠይቀው  የሚኖሩ የመንግስት ሰላዮችን ለማጋለጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ  ቆርጠው መነሳታቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቃል።
    “በአበበ ገላው ላይ ሊሰነዘር የነበረው የግድያ ወንጀል በኤፍቢአይ መርማሪዎች መክሸፉ ቢያስደስተንም፣ በስደት፣ ዲሞክራሲና ነፃነት በሰፈነበት አገር ወያኔዎች እንዲህ አይነት አስከፊ ወንጀል ለመፈፀም ማሰባቸው እጅግ አስቆጥቶናል፤በጣምም አበሳጭቶናል” በማለት ኢትዮጵያኑ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
    በኖርዌይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የመንግስት ሰዎች  ለነፃነት፣ለዲሞክራሲና ለፍትህ በሚታገሉና በኖርዌይ በሚገኙ ወገኖች ላይ በአካል፣ በስልክ፣በኢ-ሜይልና በሌሎች መንገዶች ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረጋቸውን ያስታወሱት ኢትዮጵያኑ፣  ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ሁኔታ እንዳይከሰት  ፀረ ዲሞክራሲና ኢሰብአዊ ድርጊት ፈፃሚዎችን አጋልጠው በማውጣት ህጋዊ ምርመራ እንዲደረግባቸው እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
    ከዚህ በፊት በተለያዩ የዜና አውታሮች እንደተዘገበው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የማይችሉና የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎባቸው  በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ መኖራቸው ይታወቃል፡፡

    በአላማጣ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ታሰሩ

    ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ኢሳት ዜና:- ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከተማዋን የወረሩዋት የፌደራል ፖሊሶች ተቃውሞውን አስነስተዋል በማለት የጠረጠሩዋቸውን ሰዎች ይዘው በማሰር ላይ ናቸው። ወጣቶችን ጨምሮ በከተማዋ እና በዙሪያ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ታስረዋል።
    ወረዳው ባለስልጣናትን ህዝቡን ለማነጋገር ስብሰባ መጥራታቸውም ታውቋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በነገው እለት መንግስት የሚያቀርበውን አማራጭ በመስማት ምናልባትም ተመሳሳይ ተቃውሞ ሊካሄድ ይችላል።
    ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት አለመጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

      Tuesday, January 8, 2013

      ግንቦት7 በሀረር ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

      ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ህወሀት መራሹ መንግስት በሀረር በታዳጊው  ላይ የወሰደውን ኢሰብአዊ ድርጊት በጽኑ አውግዟል።

      ዜጎች መብታቸውን በጠየቁ በጥይቅ የቆላሉ ያለው መግለጫው፣ ከእንዲህ አይነት አስከፊ ስርአት ለመላቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ኢትዮጵያውያን የትግል ጽናት በመማር ለእውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል።

      ህወሀት መራሹ መንግስት ቅንጣት ያህል ለዜጎች መብት መከበር ደንታ የሌለው ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትን በመቅጠፍ፣  በስልጣኑ የሚመጣበትን ለመመከት ማናቸውንም ወንጀሎች ከመፈጸም እንደማይመለስ ለማሳየት የአርፋችሁ ተቀመጡ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ህጻናትን በመግደል የአውሬነት ባህሪውን ቀጥሎበታል የሚለው ግንቦት7 ፣ ብቸኛው መፍትሄ በጽናት መታገል መሆኑም አስምሮበታል።

      በተመሳሳይ ዜና በአለፈው አርብ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ በደቡብ ወሎ በርካታ ሙስሊሞች መታሰራቸው ታውቋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጸጥታ ሀይሎች በጥቆማ ቤት ለቤት እየዞሩ በርካታ ወጣቶችን በደሴና አካባቢዋ በሚገኙ ቀበሌዎች ይዘው አስረዋል።